cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

DW Amharic

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Show more
Advertising posts
41 796Subscribers
+6224 hours
+4047 days
+1 43230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Show all...
የዓለም ዜና፤ ሚያዝያ 11 ቀን 2016 ዓ.ም

በቤጂንግ የግማሽ ማራቶን ውድድር ቻይናዊ ሯጭን ሆን ብለው አሸናፊ አድርገውታል የተባሉት ኢትዮጵያዊ እና ኬንያዊ አትሌቶች እንዲሁም ቻይናዊዉ አትሌት የወሰዱትን ሜዳሊያና ሽልማት ተነጠቁ። ኬንያ የመከላከያ ኢታማዦር ሹሙን ጨምሮ ሌሎች ዘጠኝ ከፍተኛ መኮንኖች በሄሊኮፕተር አደጋ ከሞቱ። ዛሬ በሃገሪቱ የሦስት ቀናት ሃዘን ታወጇል። በ1 ሚሊየን የምርጫ ጣቢያዎች ድምጻቸውን የሚሰጡ ህንዳውያን ለስድስት ሳምንታት የሚዘልቀዉን ምርጫ ዛሬ ጀመሩ። አሜሪካ በተመድ የፀጥታ ም/ቤት ውስጥ ሙሉ አባል ለመሆን ፍልስጤም ያቀረበችዉን ማመልከቻ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቷን ተጠቅማ ዉድቅ አደረገች።

Show all...
ዐይነ ሥውሩ የስፖርት ዘጋቢ በሀዋሳ ኤፍ ኤም 97.7

oይነሥውር መሆኑ የስፖርት ዘገባ ከመሥራት እንዳላገደው ይናገራል።ጋዜጠኛ መረጃዎችን አሰባስቦ እና ተንትኖ ለአድማጮቹ የሚያደርስ መሆኑን የጠቀሰው ሙሉቀን “ እኔ ይህንኑ የዘገባ ሥራ ለዛውም በስፖርት ዘርፍ እየሠራሁ እገኛለሁ, እይታን ከሚፈልጉ ከኮሜንታተርነት እና ከዳኝነት ሥራዎች በስተቀር አንድ አይነ ሥውር ስፖርትን መዘገብ ይችላል» ብሏል ፡፡

Show all...
የወባ በሽታ ስርጭት በጊምቢ ወረዳ

በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ የወባ በሽታ መስፋፋቱና ከ200 በላይ ሰዎች በወባ መታመማቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። በዚህ ቶሌ በተባለው አካባቢ የሚገኙ ዜጎች የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ ተፈናቅለው ወሎ እና ደብረብርሃን ቆይቶ በየካቲት ወር 2016 መጀመሪያ ላይ ወደቤታቸው የተመለሱ ናቸው።

Show all...
ሰሞነኛው «የትራንስፖርት እቀባ» እና ተጽእኖው

ባለፈው ሳምንት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር በተገደሉበት ምሥራቅ ሸዋ ዞን መቂ ከተማ ከሰሞኑ በኅቡዕ ታወጀ ከተባለው የመጓጓዣ አገልግሎት እቀባ ጋር በተያያዘ ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱ እየተነገረ ነው።

Show all...
የፖለቲከኛ በቴ ህልፈትና የቤተሰቡ እጣ ፈንታ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የነበሩት ፖለቲከኛ በቴ ዑርጌሳ በአሰቃቂ ሁኔታ በትውልድ አካባቢያቸው መቂ ከተማ ተገድለው ከተገኙ 11 ቀናት አልፈዋል። በዚህ ጊዜ ውስጥም በርካቶችን ያስቆጣው የፖለቲከኛው ግድያ በርካታ ሁነቶችን አስተናግዷል።

Show all...
የቦታ ይገባኛል ዉዝግብ፤ ከጠ/ሚዉ እንወያይ ጥያቄ፤ የሰብዓዊ ርዳታ ማሰባሰብያ ለኢትዮጵያ

የአማራና የትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት መከሰቱ ለምን? ጠ/ሚ አቢይ አሕመድ ከመገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ጋዜጠኞች ጋር እንዲወያዩ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት መጠየቁ፤ በኢትዮጵያ ለሚታየዉው የከፋ የሰብዓዊ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት በመንግሥትና ዓለምአቀፍ አጋሮች በተጠራው የገንዘብ ማሰባሰብ 610 ሚሊዮን ዶላር መሰብሰቡ።

Show all...
በትግራይና አማራ አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭቶችን ስለመፍታት የምሁራን አስተያየት

በትግራይና አማራ አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፈታት እንዳለባቸው ምሁራን አመለከቱ።

የተወደዳችሁ የዶቼ ቬለ ቤተሰቦች ጤና ይስጥልን ! ዘወትር ቅዳሜ የሚተላለፈው የአድማጮች ማኅደር ዝግጅታችን እንደተለመደው የእናንተን መልዕክቶች ይጠብቃል። ሀገራዊ ፤ማህበራዊ ፣ኤኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ከየአካባቢያችሁ ካያችሁት፣ ከገጠማችሁ አልያም ትኩረት ይሻል የምትሏቸውን ሃሳቦች ፤ የሙዚቃ እና የስነ ጽሁፍ ክህሎታችሁን ፤ ዓለማቀፋዊ ወቅታዊ ጉዳዮችን ጨምሮ በጽሁፍ አልያም በድምጽ ልትልኩልን የምትችሉ መሆኑን ልንገልጽ እንወዳለን፤ ቀድመው የደረሱንን አዋዝተን ከአየር እናውላለን ። ዶቼ ቬለ ሃሳባችሁ የሚስተናግድበት ፣ ድምጻችሁ የሚሰማበት የእናንተው ቤት !
Show all...
የሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ዋና ዋና ዜናዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የልጃገረዶች ጠለፋ መባባሱ ተገለጠ። በክልሉ ኮሬ ዞን ውስጥ «እየተባባሰ መጥቷል» ባሉት ጠለፋ የተነሳ ሴት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ መቸገራቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ቡርኪና ፋሶ ሦስት የፈረንሳይ ዲፕሎማቶችን ከሀገር አባረረች። ፈረንሳይ ውሳኔውን አሳዛኝ ብላዋለች። የደቡብ ሱዳን ፖለቲከኞች በሀገሪቱ ምርጫ ለማካሄድ አስቸኳይ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው የተመድ አሳሰበ። ደቡብ ሱዳን ራሷን የቻለች ሀገር ከሆነችበት ከጎርጎሪዮሳዊው 2011 ዓ,ም አንስቶ ምርጫ አላካሄደችም። ኢራን እስራኤል የኒኩሊየር ተቋሟ ላይ ጥቃት የምትሰነዝር ከሆነ በአጸፋው የእስራኤልን የኒኩሊየር መሰረተ ልማት ኢላማ እንደምታደርግ አስጠነቀቀች። ዝርዝሩን ያንብቡ ያድምጡ https://p.dw.com/p/4ewXO?maca=amh-RED-Telegram-dwcom 👉🏾 @dwamharicbot
Show all...
የሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የልጃገረዶች ጠለፋ መባባሱ ተገለጠ። በክልሉ ኮሬ ዞን ውስጥ «እየተባባሰ መጥቷል» ባሉት ጠለፋ የተነሳ ሴት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ መቸገራቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ቡርኪና ፋሶ ሦስት የፈረንሳይ ዲፕሎማቶችን ከሀገር አባረረች። ፈረንሳይ ውሳኔውን አሳዛኝ ብላዋለች። የደቡብ ሱዳን ፖለቲከኞች በሀገሪቱ ምርጫ ለማካሄድ አስቸኳይ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው የተመድ አሳሰበ። ኢራን እስራኤል የኒኩሊየር ተቋሟ ላይ ጥቃት የምትሰነዝር ከሆነ በአጸፋው የእስራኤልን የኒኩሊየር መሰረተ ልማት ኢላማ እንደምታደርግ አስጠነቀቀች።

Show all...
ለወልቃይትና ራያ አወዛጋቢ አካባቢዎች ፖለቲካዊ መፍትሔ ተጠየቀ

የወልቃይት፣ ጠገዴ ጠለምትና ራያ ጉዳይ በፖለቲካዊ ውሳኔ እንዲፈታ በአሜሪካ የሚገኙ 8 ኢትዮጵያ ሲቪክ ድርጅቶች ጥሪ አቀረቡ።