cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

DW Amharic

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Show more
Advertising posts
41 788Subscribers
+6224 hours
+4047 days
+1 43230 days
Posts Archive
Show all...
የተወደዳችሁ የዶቼ ቬለ ቤተሰቦች ጤና ይስጥልን ! ዘወትር ቅዳሜ የሚተላለፈው የአድማጮች ማኅደር ዝግጅታችን እንደተለመደው የእናንተን መልዕክቶች ይጠብቃል። ሀገራዊ ፤ማህበራዊ ፣ኤኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ከየአካባቢያችሁ ካያችሁት፣ ከገጠማችሁ አልያም ትኩረት ይሻል የምትሏቸውን ሃሳቦች ፤ የሙዚቃ እና የስነ ጽሁፍ ክህሎታችሁን ፤ ዓለማቀፋዊ ወቅታዊ ጉዳዮችን ጨምሮ በጽሁፍ አልያም በድምጽ ልትልኩልን የምትችሉ መሆኑን ልንገልጽ እንወዳለን፤ ቀድመው የደረሱንን አዋዝተን ከአየር እናውላለን ። ዶቼ ቬለ ሃሳባችሁ የሚስተናግድበት ፣ ድምጻችሁ የሚሰማበት የእናንተው ቤት !
Show all...
የሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ዋና ዋና ዜናዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የልጃገረዶች ጠለፋ መባባሱ ተገለጠ። በክልሉ ኮሬ ዞን ውስጥ «እየተባባሰ መጥቷል» ባሉት ጠለፋ የተነሳ ሴት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ መቸገራቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ቡርኪና ፋሶ ሦስት የፈረንሳይ ዲፕሎማቶችን ከሀገር አባረረች። ፈረንሳይ ውሳኔውን አሳዛኝ ብላዋለች። የደቡብ ሱዳን ፖለቲከኞች በሀገሪቱ ምርጫ ለማካሄድ አስቸኳይ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው የተመድ አሳሰበ። ደቡብ ሱዳን ራሷን የቻለች ሀገር ከሆነችበት ከጎርጎሪዮሳዊው 2011 ዓ,ም አንስቶ ምርጫ አላካሄደችም። ኢራን እስራኤል የኒኩሊየር ተቋሟ ላይ ጥቃት የምትሰነዝር ከሆነ በአጸፋው የእስራኤልን የኒኩሊየር መሰረተ ልማት ኢላማ እንደምታደርግ አስጠነቀቀች። ዝርዝሩን ያንብቡ ያድምጡ https://p.dw.com/p/4ewXO?maca=amh-RED-Telegram-dwcom 👉🏾 @dwamharicbot
Show all...
የጀርመን ፖሊስ ለሩሲያ ይሰልሉ ነበር ያላቸውን ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አዋለየጀርመን አቃቤ ህግ ትናንት ሃሙስ፤ በባቫሪያን ግዛት የቤይሮይት ከተማ ፖሊስ ለሩሲያ በመሰለል የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። የጀርመን እና የሩሲያ ዜግነት ያላቸው እነዚህ ተጠርጣሪዎች ለጥፋት ዓላማ የሚውሉ ፈንጂዎችን አዘጋጅተዋል ሲል በካርልስሩሄ ከተማ የጀርመን ፌደራል አቃቤ ህግ ቢሮ ገልጿል።በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር የሚገኙት እነዚህ ተከሳሾች ዲዬተር ኤስን እና አሌክሳንደር ጄን የሚባሉ ሲሆን፤ የፌደራል ፖሊስ ከባቫሪያን ግዛት ፖሊስ ጋር በመሆን የተከሳሾችን ቤት እና የስራ ቦታዎች ፈትሿል። ለሩሲያ ይሰልሉ ነበር የተባሉት ሁለቱ ተከሳሾች በጀርመን የሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ሰፈሮችን ጨምሮ ጥቃት ሊሰነዝሩ የሚችሉባቸውን ዒላማዎችን ሲቃኙ ነበር ተብሏል።አቃቤ ህግ እንደገለፀው ዲዬተር ኤስን የተባለው ተከሳሽ ከሩሲያ ሚስጥራዊ አገልግሎት ሰጪ ወኪል ጋር ግንኙነት ነበረው።ተከሳሹ ከጥቅምት 2023 ዓ/ም ጀምሮ እርምጃ ከተወካዮቹ ጋር ሀሳብ ሲለዋወጥ እንደነበር ተገልጿል።
Show all...
ወደ ኦሮሚያ ክልል ጊምቢ ወረዳ የተመለሱ ተፈናቃዮች በወባ በሽታ እየተጠቃን ነው አሉ።በደብረብርሃን እና ጃማ መጠለያ ጣቢያ ተጠልለው የነበሩ እና ወደ ቀያቸው የተመለሱ ተፈናቃዮች ለወባ ወረርሽኝ መጋለጣቸውን ገለፁ። በየካቲት ወር 2016 መጀመሪያ ወደ ምዕራብ ወለጋ ግምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ የተመለሱት እነዚህ ተፈናቃዮች የወባ በሽታ ስርጭት በአካባቢው በመስፋፋቱ ከ200 በላይ ሰዎች በወባ መታመማቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።በቦታው የመድኃኒት ባለመኖሩ በርካታ ሰዎች በወባ በሽታ እየተጎዱ እንደሚገኙ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች አብራርተዋል፡፡ የዞኑ ጤና መምሪያ በበኩሉ በአካባቢው የወባ ስርጭት መኖሩን ገልጸው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቤታቸው ከተመለሱ ጊዜ አንስቶ ህኪምና በነጻ እየተሰጠ ይገኛል ብሏል፡፡ ባለሙያዎች በቦታው በጊዜያዊነት ተመድቦ እየተሰራ ነው ብሏል፡፡ዘገባውን ያደረሰን የአሶሳው ዘጋቢያችን ነጋሳ ደሳለኝ ነው። ሙሉ ዘገባውን በማታው የዜና መፅሄት ጠብቁን።
Show all...
በጠለፋ ምክንያት ሴት ልጆች ወደ ትምህርት ቤት የማሄዱባት የኮሬ ዞን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጠለፋ እየተባባሰ በመምጣቱ ሴት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ መቸገራቸውን ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል። በዞኑ በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ አስተማሪ የሆነ ቅጣት ስለማይሰጥም ሴት ልጆች ወጥተው ለመግባት ሥጋት ውስጥ መውደቃቸውን ነው ነዋሪዎቹ ለዶቼ ቬለ የተናገሩት ፡፡ በዞኑ በያዝነው ግማሽ ዓመት ብቻ የጠለፋ ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል የተባሉ የ24 ልጃገረዶች ሥም ዝርዝር ይፋ መደረጉን ተከትሎ ወላጆችና የህዝብ ተመራጮች በዞኑ የህግ አካላት ላይ ጫና እያደረጉ ነውም ተብሏል። ዘገባውን ያደረሰን የሀዋሳው ዘጋቢያችን ሽዋንግዛው ወጋየሁ ነው።ሙሉ ዘገባውን በማታው የዜና መፅሄት ጠብቁን።
Show all...
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በፍልስጤም አባልነት ላይ ነገ ድምፅ ይሰጣል የፀጥታው ምክር ቤት የፍልስጤምን የተባበሩት መንግስታት ሙሉ አባልነት ላይ ድምጽ ለመስጠት ለመጭው አርብ ቀጠሮ ይዟል። በአሁኑ ጊዜ ከ10 ተዘዋዋሪ አባላት አንዷ የሆነችው አልጄሪያ «የፍልስጤም ግዛት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል እንድትሆን» የሚል ጥያቄ አቅርባለች። የአልጄሪያን ጥያቄ ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በፍልስጤም አባልነት ላይ በነገው ዕለት ድምፅ እንደሚሰጥ ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዘግቧል። 15 አባላት ያሉት የፀጥታው ምክር ቤት ነገ ዓርብ ከጠዋቱ 3 ሰአት ላይ፤«የፍልስጤም ግዛት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሆና እንድትገባ”በቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ድምፅ ይሰጣል ሲል ሮይተርስ ዲፕሎማቶችን ጠቅሶ ዘግቧል። እንደ ሮይተርስ ዘገባ የምክር ቤቱ ውሳኔ ቢያንስ ዘጠኝ የድጋፍ ድምጽ የሚያስፈልገው ሲሆን ፤እርምጃው እስከ 13 የምክር ቤት አባላት ድጋፍ ሊኖረው ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። ይህም ሀሳቡን በመቃወም ዩኤስ አሜሪካ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት እንድትጠቀም ያስገድዳል ሲል ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል።
Show all...
የኢንቨስትመንት ፎረም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን የኢቨስትመንት ስራ ለማስጀመር ባለሀብቶችንና የፋይናንስ ተቋማት ያሳተፈ የእንቨስትመንት ፎረም ዛሬ በአሶሳ ተጀምሯል፡፡ የክልሉ የመሬትና ህብት ስራ ማደራጃ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም መንገሻ ለአልሚ ባለሀብቶች እስካሁን ከግማሽ ሚሊዩን በላይ ሄክታር መሬት የተላለፈ ሲሆን ባደረጉት ማጣራት ወደ ስራ የገቡና ውጤት ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ውስን መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ በጸጥታ ችግር ወቅት የስራ መሳሪያቸው የወደመባቸው ባለሀብቶችም የባንክ ወለድ እንዲዘረዝላቸውና ንረብታቸው እንዲተካላቸው ጠይቋል፡፡
Show all...
ምዕናባዊ ኦቲዝም፤ የዲጅታል ዘመን ልጆች ስጋት ባለሙያዎች እንደሚሉት በተንቀሳቃሽ ስልኮች፣በታብሌት፣በቴሌቪዝን እና በሌሎች ዲጅታል መሳሪያዎች ላይ ረዘም ያለ ጊዜ የሚያሳልፉ ልጆች ለጭንቀት እና ለመረበሽ፣ ለትኩረት ማጣት፣ ለንግግር እና ለቋንቋ መዘግየት እንዲሁም ለግንዛቤ እድገት ውሱንነት ይዳረጋሉ። የሰዎችን ስሜት የመረዳት እና የመግባባት ችሎታቸውንም ይቀንሳል።https://p.dw.com/p/4erN2?maca=amh-Facebook-dw DW
Show all...
የኢትዮጵያ ገበያ ለውጭ ባለወረቶች ሲፈቀድ ባለሙያዎች ተስፋ እና ሥጋት ተሰምቷቸዋል የኢትዮጵያ መንግሥት የችርቻሮ ንግድ ለውጭ ባለወረቶች ሲፈቅድ ከ2 ሺሕ-10 ሺሕ ስኩዌር ሜትር የሚሰፉ ሱፐርማርኬቶች እንዲገነቡ ይፈልጋል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ መመሪያ በወጪ፣ ገቢ እና ጅምላ ንግድ ዘርፎች የውጭ ባለወረቶች እንዲሳተፉ የሚፈቅድ ነው። የመንግሥት ጉልህ ፖሊሲ ለውጥ ለአንዳንድ ባለሙያዎች ተስፋ ለሌሎች ሥጋት ያጫረ ሆኗል። https://p.dw.com/p/4etWA?maca=amh-Facebook-dw
Show all...
የአማራ ክልል መንግሥት «ህወሓት ጦርነት ከፍቶብኛል» አለ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት «ህወሓትና ግብረ አበሮቹ» ያላቸው አካላት ሁለቱ ወገኖች የይገባኛል ጥያቄ ከሚያነሱባቸውና ሰሞኑን በኃይል ከያዟቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ እንዲወጡ አሳሰበ። የአማራ ክልላዊ መንግሥት በመግለጫው የፕሪቶሪያው ስምምነት እንዲተገበርም ጠይቋል።https://p.dw.com/p/4et3Y?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
Show all...
«አስከሬን አግኝተን መቅበር አልቻልንም» የሟቾች ቤተሰብ ባለፈው ሳምንት ዓርብ አዲስ አበባ ውስጥ የተገደሉት የፋኖ አባላት አስከሬን እስካሁን ለቤተሰብ አለመሰጠቱን የሟቾች ቤተሰቦች ተናገሩ። አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬለ የሰጡ የቤተሰብ አባላት ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ከፌዴራል ፖሊስ እስከ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቢመላለሱም የሟቾቹን አስከሬን ተረክበው ለመቅበር አለመቻላቸውን አስረድተዋል። https://p.dw.com/p/4etMd?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
Show all...
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ከጋዜጠኞች ጋር እንዲወያዩ ጥያቄ ቀረበ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ያደረጉትን ተከታታይ ውይይት ከመገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ጋዜጠኞች ጋርም እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጠየቀ። ምክር ቤት የውይይት ጥያቄውን ከሦስት ሳምንት በፊት ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ማስገባቱን እና ምላሽም እየተጠባበቀ መሆኑን አስታውቋል።https://p.dw.com/p/4et7D?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 dw.com
Show all...
https://p.dw.com/p/4etQH?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
Show all...
የግብርና ኢንቨስትመንት መድረክ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ1300 በላይ ባለሀብቶች መሬት የተረከቡ ቢሆንም የሚፈለገውን ያህል ውጤት ሳይገኝ መቆየቱ ተገለጸ። ባለሀብቶች የተሳተፉበት ክልል አቀፍ የግብርና ኢንቨስትመንት መድረክ ትናንት በአሶሳ ከተማ ተካሂዷል። https://p.dw.com/p/4ess?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
Show all...
ለኢትዮጵያ የሰባዊ እርዳታ ማሰባሰቢያ መርሃግብር በጀኔቭ በኢትዮጵያ በድርቅ፤ ጎርፍና ጦርነት ምክኒያት ለከፍተኛ ችግር የተዳረጉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለመርዳት የሚያስችል ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ለማሰባሰብ ትናንት ሲዊዘርላንድ ጀኔቭ በተዘጋጀ መርሃ ግብር፤ ከለጋሾች 630 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱ ተገለጸል። https://p.dw.com/p/4etQH?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
Show all...
https://p.dw.com/p/4etXf?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
Show all...
የሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
Show all...
በምሽቱ የዶይቸ ቬለ የሬድዮ ቀጥታ ሥርጭታችን ከምናቀርብላችሁ በጥቂቱ! ውድ የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች፦ ነጋሽ መሐመድ በሚመራው የዕለቱ የዶይቸ ቬለ የሬድዮ ቀጥታ ሥርጭታችን ከሚቀርቡ ዝግጅቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል ። * የአማራ ክልላዊ መንግሥት ከአወዛጋቢ አካባቢዎች እንዲወጣ ለሕወሃት ያስተላለፈው ማስጠንቀቂያ፤ *ባለፈው ዓርብ አዲስ አበባ ላይ መገደላቸው የተነገረው የፋኖ አባላት አስከሬን እስካሁን ለቤተሰቦቻቸው አለመሰጠቱ፤ * ከጋዜጠኞች ጋር እንዲወያዩ ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ጥያቄ መቅረቡየሚሉት ይገኙበታል ። የዛሬው የሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዝግጅት ደግሞ፦ እንደ ሞባይል፣ ታብሌት እና ቴሌቪዝንን የመሳሰሉ ዲጅታል ቴክኖሎጅዎችን አብዝቶ ከመጠቀም ጋር ተያይዞ በልጆች ላይ ስለሚከሰተው ምናባዊ ኦቲዝም ላይ ያተኩራል።« ምዕናባዊ ኦቲዝም፤ የዲጅታል ዘመን አዲስ ስጋት» በሚል ርእስ ተቀናብሯል ። የቀጥታ ሥርጭታችን ምሽት አንድ ሰአት ላይ በሬዲዮ እንዲሁም በፌስቡክ እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን ። በየዕለቱ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ ስርጭታችን ይጀምራል። ዝግጅቶቻችን በአጭር ሞገር በራዲዮ፤ 15,275 ኪሎ ኸርዝ 19 ሜትር ባንድ እና 11 ሺሕ 830 ኪሎ ኸርዝ 16 ሜትር ባንድ በዚህ ወቅት ይደመጣል። ከዚህ በተጨማሪም በፌስቡክ DW Amharic ብላችሁ በቀጥታ ስርጭታችንን መከታተል ትችላላችሁ። ስርጭቱ ካለፋችሁ ደግሞ በፌስቡክም ሆነ ከድረገጻችን DW Amharic ብላችሁ ልትፈልጉን፤ እንዲሁም በዚህ ማገናኛ https://t.me/dw_amharic ይፋዊ የቴሌግራም ገጻችን አባል መሆን ትችላላችሁ ። በምሽቱ ሥርጭት ከእኛ እና ከወዳጆቻችሁ ጋ እንድትሆኑ ከወዲሁ እንጋብዛለን ።
Show all...
የአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግና የአውሮጳ ሊግ ፍልሚያዎች በአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግ ግጥሚያ ዛሬም ማታም ሁለት ወሳኝ ግጥሚያዎች ይኖራሉ ። በምሽቱ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ በሚደረጉ ግጥሚያዎች፦ የጀርመኑ ባዬርን ሙይንሽን ከእንግሊዙ አርሰናል ጋ ይፋጠጣል ። ሌላኛው የእንግሊዝ ቡድን ማንቸስተር ሲቲ ከስፔኑ ሪያል ማድሪድ ጋ ይፋለማል ። ሁለቱም ጨዋታዎች በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር በተመሳሳይ ከምሽቱ 4 ሰአት ላይ ይጀምራሉ ። በትናንትናው እለት በነበሩ ግጥሚያዎች፦ አንድ ለዜሮ ሲመራ የነበረው እና አንድ ተጨዋቹን ጨዋታው በተጀመረ 29ኛ ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ያጣው ባርሴሎና በፓሪ ሳን ጃርሞ የ4 ለ1 ብርቱ ሽንፈት አስተናግዷል ። በደርሶ መልስ የ6 ለ4 ድልም ፓሪ ሳን ጃርሞ ወደ ግማሽ ፍጻሜው አልፏል ። በተመሳሳይ ሰአት በነበረ ሌላ ግጥሚያ፦ ቦሩስያ ዶርትሙንድ አትሌቲኮ ማድሪድን 4 ለ2 በደርሶ መልስ 5 ለ4 አሸንፎ ለግማሽ ፍጻሜው ደርሷል ። በአውሮጳ ሊግ ደግሞ፦ ነገ አታላንታና ሊቨርፑል፤ ዌስትሀምና ባዬር ሌቨርኩሰን፤ ሮማ ከሚላን እንዲሁም ማርሴይ ከቤኔፊካ ጋ የመልስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ ። በተለይ በመጀመሪያ ግጥሚያው በሜዳው አንፊልድ የ3 ለ0 ሽንፈት ያስተናገደው ሊቨርፑል ብርቱ ፈተና ይጠብቀዋል ።
Show all...
የዶይቸ ቬለ የዩቲዩብ ገጻችን ይከተሉ! ውድ አድማጮቻችን ፦ የተለያዩ መገናኛ አውታሮችን በመጠቀም አድማሳችንን በማስፋት ዝግጅቶቻችንን በዩቲዩብም ማቅረብ ጀምረናል ። የአዲሱና የትክክለኛው የዶይቸ ቬለ ዩቲዩብ ገጽ አባል በመሆን ዝግጅታችንን ተከታተሉ ። በትክክለኛው በዚህ የዩቲዩብ አድራሻችን፦ https://www.youtube.com/channel/UC3-RNH75BEZslJLEoIAxa2A አባል ይሁኑ። ለወዳጆቻችሁም ያጋሩ ።
Show all...
ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች፦ ዶይቸ ቬለ ከዕለት ተዕለት መደበኛ የዜና ዘገባዎቹ ባሻገር የተለያዩ ጉዳዮች ላይም ትኩረት በመስጠት ዝግጅቶችን ያቀርባል ። ከእነዚህ ጉዳዮች መካከል አንዱ በአዳጊ ሴቶች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ የሚያተኩረው «ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች፦» የተባለው መሰናዶዋችን ይገኝበታል ። ይህን የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች የቪዲዮ ዘገባዎችን https://www.facebook.com/dw.amharic/videos/632916898986164 እና ሌሎችም እየተመለከታችሁ አስተያየት ጥቆማችሁን አድርሱን ። ለወዳጆቻችሁም ዘገባዎቹን ብታጋሩ ደስ ይለናል ። እናመሰግናለን። #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute
Show all...
የዶይቸ ቬለ የዩቲዩብ ገጻችን ይከተሉ! ውድ አድማጮቻችን ፦ የተለያዩ መገናኛ አውታሮችን በመጠቀም አድማሳችንን በማስፋት ዝግጅቶቻችንን በዩቲዩብም ማቅረብ ጀምረናል ። የአዲሱና የትክክለኛው የዶይቸ ቬለ ዩቲዩብ ገጽ አባል በመሆን ዝግጅታችንን ተከታተሉ ። በትክክለኛው በዚህ የዩቲዩብ አድራሻችን፦ https://www.youtube.com/channel/UC3-RNH75BEZslJLEoIAxa2A አባል ይሁኑ። ለወዳጆቻችሁም ያጋሩ ። ዶይቸ ቬለ በዓበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪቃ፣ የአውሮጳ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ የዜና ዘገባዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ትንታኔዎችን ያቀርባል ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መጽሄት እና የዓለም ዜና ከሰኞ እስከ ዓርብ በዶይቸ ቬለ ዩቲዩብ ገጻችንም https://www.youtube.com/channel/UC3-RNH75BEZslJLEoIAxa2A ላይ ይቀርባሉ ። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ እና በሳተላይትም በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። አሁኑኑ የዶይቸቬለ የዩቲዩብ ገፅ ደምበኛ ይሁኑ! https://www.youtube.com/channel/UC3-RNH75BEZslJLEoIAxa2A ዶይቸ ቬለን በዩቲዩብም ይከተሉ!
Show all...
በአላማጣ «ከፌደራል የፀጥታ ተቋማት ጋር ያጋጠመ አንድም ነገር የለም» ሕወሓት የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ጠላት የሆኑ ኃይሎች ግጭት ለመፍጠር እየጣሩ ነው ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከሰሱ። https://p.dw.com/p/4er9F?maca=amh-RED-Telegram-dwcom 👉🏾 @dwamharicbot
Show all...
የኔቶ የ75 ዓመት ጉዞና ፈተናዎቹ ፑቲን ቢቃወሙም ኔቶ መስፋፋቱን በመቀጠል ለቀድሞዎቹ የሶቭየት ኅብረት ግዛቶች ጆርጅያና ዩክሬን የኔቶ አባል እንዲሆኑ ቃል ገባላቸው። ያኔ ግን ፑቲን ስልታቸውን ቀየሩ። በጆርጅያ ላይ ጥቃት በመሰንዘር የተወሰነውን የጆርጅያ መሬት ያዙ። በ2014 የዩክሬንዋን የክሪምያ ልሳነ ምድር ገነጠሉ።በ2022 ሩስያ በዩክሬን ላይ ጦርነት ከፈተች። https://p.dw.com/p/4erHL?maca=amh-RED-Telegram-dwcom 👉🏾 @dwamharicbot
Show all...
የኔቶ የ75 ዓመት ጉዞና ፈተናዎቹ ፑቲን ቢቃወሙም ኔቶ መስፋፋቱን በመቀጠል ለቀድሞዎቹ የሶቭየት ኅብረት ግዛቶች ጆርጅያና ዩክሬን የኔቶ አባል እንዲሆኑ ቃል ገባላቸው። ያኔ ግን ፑቲን ስልታቸውን ቀየሩ። በጆርጅያ ላይ ጥቃት በመሰንዘር የተወሰነውን የጆርጅያ መሬት ያዙ። በ2014 የዩክሬንዋን የክሪምያ ልሳነ ምድር ገነጠሉ።በ2022 ሩስያ በዩክሬን ላይ ጦርነት ከፈተች። https://p.dw.com/p/4erH?maca=amh-RED-Telegram-dwcom 👉🏾 @dwamharicbot
Show all...
ሁሉን ሰው ሊያጋጥም የሚችለው የአጥንት መሳሳት የአጥንት መሳሳት ችግር በሁሉም ሰው ላይ ሊከሰት የሚችል እንደሆነ የዘርፉ የህክምና ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ችግሩ በሚያጋጥሙ አደጋዎች አጥንት በቀላሉ እንዲሰበር ያደርጋል። አጥንት ጥንካሬ የሚረዳ ነገር ይኖር ይሆን? https://p.dw.com/p/4erDn?maca=amh-RED-Telegram-dwcom 👉🏾 @dwamharicbot
Show all...