cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

ኢዜማ ኢትዮጵያ የሁሉም ዜጎች መብት የተከበረባት፣ ማኅበራዊ ፍትህ የሰፈነባት ሰላማዊ እና የበለፀገች ሀገር እንድትሆን የሚሠራ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ነው።

Show more
Advertising posts
3 583Subscribers
-224 hours
-177 days
-7330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በ #ኢዜማ ወጣቶች እየተሰናዳ በሚቀርበው #የኔ_ፖለቲካ የተሠኘው መርኃግብር የሀገራዊ ምክክር ሚና በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ውይይት ተከናወነ። በውይይቱ የመነሻ ፅሁፍ ከማቅረብ በተጨማሪ ከተሳታፊዎች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች መልሶችን የሠጡት የነፃነት እና እኩልት ፓርቲ ሊ/መንበር የሆኑት ዶ/ር አብዱልቃድር ዓደም በሀገራዊ ምክክሩ በሀገራችን ያሉ ችግሮች ሁሉ መልስ ያገኛሉ ከሚል የተለጠጠ ግምትና ተስፋ መላቀቅ እንደያሚስፈልግ እና በሚገባው ልክ ማሰብ ጠቃሚ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የመርኃግብሩን የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሐላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ ሀገራዊ ምክከሩ የተሳካ እንዲሆን ኢዜማ የአቅሙን ሁሉ እንደሚያደርግ በተያያዘም በሒደቱ ላይ የሚታዩ ችግሮችንም እየነቀሰ እንደሚያመላክት አሳውቀዋል፡፡ እንደምሳሌነትም በዋናነት ይህን ሥራ ለመስራት በኢዜማ የተቋቋመው የሀገራዊ ምክክር ኮሚቴ ከዚህ ቀደም አትኩሮት ቢሰጣቸው ብሎ የሚያስባቸውን ሥራዎች ጠቅሶ ለምክክር ኮሚሽኑ ደብዳቤ ማስገባቱን አስታውሰዋል፡፡ አክለውም በምክክሩ ላይ ጠብመንጃዎች ሁሉ ተቀምጠው በምትካቸው እስኪርብቶዎች ቢነሱ የተሻለ አማራጭ መሆኑን ሲያስረዱ እስክሪብቶም ጠብመንጃም ይዞ ምክክርን ማሰብ ሀገራዊ ምክክሩ የተነሳላትን ዓላማ እንዳያሳካ ያደርገዋል የሚል ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ #የዜግነት_ፖለቲካ #ማኅበራዊ_ፍትሕ #ዴሞክራሲያዊ_ፌደራሊዝም #ኢዜማ
Show all...
በ #ኢዜማ ወጣቶች እየተሰናዳ በሚቀርበው #የኔ_ፖለቲካ የተሠኘው መርኃግብር የሀገራዊ ምክክር ሚና በሚል ርዕስ እየተካሔደ ይገኛል። በውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፓርቲው ም/መሪ ዮሐንስ መኮንን ፓርቲዎች መተባበር ባለባቸው ሀገራዊ ጉዳይ ላይ አብሮ መሥራትን ሊያዳብሩ ይገባል በሚፎካከሩባቸው ጉዳዮችም ቢሆን ሕግ እና ሥርዓትን ባከበረ መልኩ፤ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓትን እና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ሐሣቦችን ማመንጨት ያለመ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል። ከዚያም በመቀጠል የነፃነት እና እኩልት ፓርቲ (#ነእፓ) ሊ/መንበር የሆኑት ዶ/ር አብዱልቃድር ዓደም የመነሻ ጽሑፍ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
Show all...
የመርኃግብር ማስታወሻ! #የኔ_ፖለቲካ ርዕስ: የሀገራዊ ምክክር ሚና መነሻ ጽሑፍ አቅራቢ: ዶ/ር አብዱልቃድር አደም (የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ሊ/መንበር) ቀን: ነገ ቅዳሜ ሚያዚያ 19/2016 ዓ.ም. ሰዓት: ከቀኑ 8:00 ቦታ: ስታዲየም አከባቢ በሚገኘው የ #ኢዜማ ዋና ጽ/ቤት ፕ/ር መሥፍን ወ/ማርያም አዳራሽ 👉 ለማንኛውም ዜጋ ክፍት የሆነ መድረክ አዘጋጅ: የ #ኢዜማ ወጣቶች መምሪያ
Show all...
የመርኃግብር ማሥታዘሻ! #የኔ_ፖለቲካ ርዕስ: የሀገራዊ ምክክር ሚና መነሻ ጽሑፍ አቅራቢ: ዶ/ር አብዱልቃድር አደም  (የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ሊ/መንበር) ቀን: ቅዳሜ ሚያዚያ 19/2016 ዓ.ም. ሰዓት: ከቀኑ 8:00 ቦታ: ስታዲየም አከባቢ በሚገኘው የ #ኢዜማ ዋና ጽ/ቤት ፕ/ር መሥፍን ወ/ማርያም አዳራሽ 👉 ለማንኛውም ዜጋ ክፍት የሆነ መድረክ አዘጋጅ: የ #ኢዜማ ወጣቶች መምሪያ
Show all...
#የኔ_ፖለቲካ ርዕስ:
የሀገራዊ ምክክር ሚና
መነሻ ጽሑፍ አቅራቢ: ዶ/ር አብዱልቃድር አደም  (የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ሊ/መንበር) ቀን: ቅዳሜ ሚያዚያ 19/2016 ዓ.ም. ሰዓት: ከቀኑ 8:00 ቦታ: ስታዲየም አከባቢ በሚገኘው የ #ኢዜማ ዋና ጽ/ቤት ፕ/ር መሥፍን ወ/ማርያም አዳራሽ 👉 ለማንኛውም ዜጋ ክፍት የሆነ መድረክ አዘጋጅ: የ #ኢዜማ ወጣቶች መምሪያ
Show all...
በ #ኢዜማ ሴቶች መምሪያ የሚዘጋጀው የውይይት መርኃግብር የሴቶች ፖለቲካ ተሣትፎ ከሕግ አንፃር በሚል ርዕስ ተካሔደ። በውይይቱ የፓርቲው ሊ/መንበር እንዲህ አይነት ውይይቶች ኢዜማ መሠረታዊ የፖለቲካ አስተሳሰቦቼ ከሚላቸው ጋር በመመልከት የፓርቲውን አማራጭ ፖሊሲ ለማሻሻል እና በሚወጡ ሕጎች ላይ ተፅዕኖ ለማድረግ የሚረዳ በመሆኑ የሚበረታታ መሆኑን እና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል። የውይይቱን መነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት የፓርቲው ሕገ ደንብ ተርጓሚ እና አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ሠላማዊት ገ/እግዚአብሔር የሴቶች የፖለቲካ ተሣትፎ በዓለም አቀፍ እንዲሁም ሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ወቅቶች በወጡ የሕግ ድንጋጌዎች እንዴት በአዎንታዊ እና አሉታዊ መንገድ እንደቃኙት እንዲሁም አሁን ላይ በሕግ ደረጃ የተቀመጡ ድንጋጌዎችን ጠቅሰው አብራርተዋል። #የዜግነት_ፖለቲካ #ማኅበራዊ_ፍትሕ #ዴሞክራሲያዊ_ፌደራሊዝም #ኢዜማ
Show all...
Go to the archive of posts