cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

DW Amharic

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Больше
Рекламные сообщения
42 095Подписчики
+6124 часа
+2797 дней
+1 45730 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Показать все...
የሚያዚያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና

የኦፌኮ አመራሮች እስራት፤ የፓርቲው መግለጫ ሩዋንዳ፤ ለዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውንጀላ ምላሽ ሰጠች ቤኒን፤ ፖሊስ ሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኮሰ ሃማስ አዲሱን የእስራኤል የእርቅ ሃሳብ እንደሚያጤን አስታወቀ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ጥሪ አትሌት መዲና ኢሳ በ 5ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረች

አትሌት መዲና ኢሳ በ5ሺህ ሜትር ከ20 ዓመት በታች የሩጫ ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረች። የ19 ዓመቷ መዲና ዛሬ በሄርዞግንአውራህ ጀርመን የተካሄደውን ውድድር የጨረሰችው 14 ደቂቃ ከ 38 ሰከንድ በመሮጥ እንደሆነ አዲዳስ በ X የማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል። የአዲዳስ ኩባንያ አዲዜሮ ሮድ ቱ ሪኮርድስ ባዘጋጀው በዚሁ የሴቶች ውድድር አትሌት መልክናት ውዱ 2ኛ ፣ ፎቲየን ተስፋይ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡ 4ኛ ከወጣችው ኬንያዊት በቀር እስከ 8ኛ የወጡት ኢትዮጵያዊያን ነበሩ። በወንዶች ኢትዮጵያዊያኑ ዮሚፍ ቀጀልቻ 13 ደቂቃ ከ 00 ሰከንድ በመግባት አሸንፏል። የሀገሩ ልጅ ይሁኔ አዲሱ 2ኛ ወጥቷል። ለባህሬን የሚሮጠው ብርኃኑ በለው ሶስተኛ ሆኖ አጠናቋል።
Показать все...
Показать все...
የኦፌኮ አመራሮች እስራት፤ የፓርቲው መግለጫ

መንግስት አመራሮቼ እና አባላቶቼ ላይ የሚያደርሰው እስራት እና ደብዛ ማጥፋት ማጥፋት አማሮኛል ሲል የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) አመለከተ። ፓርቲው ትናንት ዓርብ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ እየደረሰብኝ ነው ያለው የአመራሮች እና አባላት እስራት እና ደብዛ ማጥፋት የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል አቋዋሜን አያናውጥምም ብሏል ።

ሩሲያ ሌሊቱን የዩክሬን ኃይል ማመንጫ ላይ የሰነዘረችውን የአየር ጥቃት ተከትሎ የአየር መከላከያ እና ፈጣን የጦር መሣሪያዎች እንዲቀርብላቸው የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ አዲስ ጥሪ አስተላለፉ። ዘሌንስኪ እንዳሉት ዩክሬን በቂ መጠን ያለው የሚሳኤል ማክሸፊያ እና ሌሎች የጦር መሣሪያዎች ከተሞቿን ለመጠበቅ እና ለማሸነፍ ያስፈልጓታል። "ሽብር ሁል ጊዜ መሸነፍ አለበት። እኛን የሚረዳን ሁሉ ሀቀኛ የሩሲያ ሽብርን ተቃዋሚ ነው" ብለዋል ዘሌንስኪ። እንደ ዩክሬን ገለፃ ሩሲያ ዛሬ በሦስት ክልሎች በሚገኙ የኃይል ማመንጫዎች ላይ ብርቱ ጥቃት ሰንዝራ ሁለት የኃይል ሰራተኞች ሲገደሉ አራት የኃይል ማመንጫዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ዩክሬን እንዲሁ ከአንድ ወር ገደማ በፊት በሩሲያ ሚሳኤል እና ሰው አልባ አይሮፕላኖች በነዳጅ እና ኃይል ማመንጫ ዘርፏ ላይ ብርቱ ጉዳት መድረሱን አስታውቃ ነበር። ሩስያ እስከ ባለፈው ህዳር ወር ድረስ ከ 60 ጊዜ በላይ በኃይል መሠረተ ልማቷ ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ዩክሬን አስታውቃ ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ ዩክሬን ዛሬ በደቡብ ሩሲያ በሚገኙ ሁለት የነዳጅ ዘይት ማጣሪያ ፋብሪካዎች ላይ የተሳካ ጥቃት መፈጸሟን አስታውቃለች። ከዚህም ሌላ ዩክሬን ሌሊቱን በከባድ ሰው አልባ አውሮፕላን አንድ ወታደራዊ አየር ማረፊያ ላይ ጥቃት መፈፀሟን አስታውቃለች። የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን በአንዱ የነዳጅ ዘይት ማጣሪያ ፋብሪካ ላይ ቃጠሎ መነሳቱን እና ስራ በከፊል መቋረጡን ዘግበዋል። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በዩክሬን ሰው አልባ አይሮፕላኖች ጥቃት አምስት ሰዎች መቁሰላቸውን አስታውቋል።
Показать все...
Показать все...
ክፍል 6«ወድቆ መነሳት»

እምነት ባለፈው ጊዜ ከገጠማት ሱስ ለመላቀቅ ከሀኪም ባለሙያ ጋር ተገናኝታለች። ጀምበሬ በበኩሏ ኦንላይን ባቀረበችው ቪዲዮ ፍጹምነት ባለመርካቷ ከውስጣዊ ግፊቶቿ ጋር እየታገለች ነበር። ራሂምም በፍቅር ወጥመድ የገባ ይመስላል። ከሳምንት በኋላ የሶስቱ የወንድማማች ልጆች ታሪክ እንዴት ይቀጥላል?

የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ እና በርካታ አለም አቀፍ ባለስልጣናት በሳምንቱ መጀመሪያ ሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ተገኝተው በጋዛ ሰላም የሚሰፍንበት ስምምት ላይ እንደሚወያዩ ተገለፀ። የዓለም የኤኮኖሚ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ዛሬ እንደገለፁት ስብሰባው የሚካሄደው ሰኞ በሚጀምረው የዓለም የኤኮኖሚ ጉባኤ ጎን ለጎን ነው። ፕሬዚዳንት ቦርጌ ብሬንደ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት "ቁልፍ ሚና ተጫዋቾች በዚያው በሪያድ ስለሚገኙ የሚካሄዱት ውይይቶች ወደ እርቅ ሂደት ሊያመሩ ይችላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል። በጉባኤው ላይ የዩናይትድ ስቴትስ እና የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የባህሬን ባለስልጣናት እንደሚገኙ ሮይተርስ ዘግቧል። የግብፁ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሳሚህ ሹክሪ የግብፅ ተደራዳሪዎች አርብ ዕለት እስራኤል ውስጥ የጋዛን ጦርነት አቁሞ የቀሩትን የእስራኤል ታጋቾች ለማስፈታት ስላደረጉት ጥረት ከምን እንደደረሰ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። የሀማስ ቡድን በበኩሉ ዝርዝር ውስጥ ሳይገባ ከእስራኤል የቀረበውን አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት አጤኖ ምላሽ እንደሚሰጥ ዛሬ አስታውቋል።
Показать все...
Показать все...
ትኩረት በአፍሪቃ፣ የደቡብ አፍሪቃ 30 ዓመት ዴሞክራሲ፣ ጎርፍ በአፍሪቃ

የሕዝቡ ምጣኔ ሐብታዊና ማሕበራዊ ፍላጎቶች በመጓደላቸዉ በገዢዉ የANC ፓርቲና በባለስልጣናቱ ላይ ያለዉ ቅሬታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያየለ ነዉ።የምጣኔ ሐብት ተንታኝ ዳንኤል ሲልከ እንደሚሉት ANC ዕዉቁ መሪዉ ኔልሰን ማንዴላ ገቢር ያደረጉትን የሥነ-ምግባር ሥርዓት አለማክበሩ የሐገሪቱን ሕዝብ ክፉኛ አበሳጭቷል።

የቤኒን ፖሊስ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ሰዎችን በአስለቃሽ ጭስ መበተኑን በስፍራው የነበረ የዣንስ ፍራንስ ፕረስ ወኪል ገለፀ። መጠነኛ ቁጥር ነበራቸው የተባሉት ሰልፈኞች ያለውን ከፍተኛ የኑሮ ውድነት በመቃወም የኢኮኖሚ ማዕከል በሆነችው ኮቶኑ ከተማ ነበር ዛሬ አደባባይ የወጡት። በፖሊሶች ተከቦ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተገኙት ሰልፈኞች የሀገሪቱን ብሔራዊ መዝሙር ይዘምሩ እንደነበርም ተዘግቧል። በሀገሪቱ ካሉ የሰራተኛ ማህበራት ትልቁ የሚባለው እና የዛሬው ሰልፍ አስተባባሪ CSA ቤኒን በ X የማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው ከማህበሩ መሪ በተጨማሪ ሌሎች 12 በሰልፉ ላይ የተገኙ ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። ፖሊስ ስለ ድርጊቱ መግለጫ አልሰጠም።
Показать все...
Показать все...
የሚያዚያ 19 ቀን 2016 የአድማጮች ማህደር ዝግጅት

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት በአፕል ኩባንያ ላይ የሰነዘረው ክስ "መሠረተ ቢስ ውንጀላ" ነው ሲል የሩዋንዳ መንግሥት አጣጣለ። የሩዋንዳ መንግሥት ይህን ያለው ግዙፉ አፕል ኩባንያ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል ወደ ጎረቤት ሀገር ሩዋንዳ በህገ-ወጥ መንገድ የሚገቡ ማዕድናትን በመግዛት ወደ ሌሎች አለምአቀፍ አከፋፋዮች ያሰራጫል በማለት ከወነጀለች ከአንድ ቀን በኋላ ነው። ፓሪስ የሚገኙ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጠበቆች ሀሙስ ዕለት አፕል በዚህ ድርጊቱ ከቀጠለ ህጋዊ እርምጃ ሊጠብቀው እንደሚችል የላኩት ማስጠንቀቂያ ግልባጭ እንደደረሰው አዣንስ ፍራንስ አክሎ ገልጿል። የሩዋንዳ መንግሥት ቃል አቀባይ ዮላንዴ ማኮሎ “መሰረተ ቢስ ክሶችን እና ግምቶችን በማሰራጨት በአለም ላይ ካሉት ትልልቅ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው አፕልን ስም በማጥፋት የመገናኛ ብዙኃን ፍላጎትን ለመሳብ የተደረገ ሙከራ ነው »ሲሉ ውንጀላውን አጣጥለዋል። ከዚህም ሌላ ቃል አቀባይዋ ይህ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሩዋንዳ ላይ በተደጋጋሚ ከሰነዘረችው ኃሰተኛ ውንጀላዎች የቅርብ ጊዜው ነው ብለዋል። ለዘመናዊ ስልኮች እና ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ግብዓት በሚሆኑ ማዕድኖች የታደለችው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሰዉን M23 አማፂ ቡድን ሩዋንዳ ትደግፋለች በሚል በተደጋጋሚ ሀገሪቱን መወንጀሏ ይታወሳል። የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ውንጀላውን አስተባብለው በበኩላቸው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኪጋሊ ያለ የሁቱ ሚሊሽያን ትደግፋለች ሲሉ ይወቅሳሉ።
Показать все...