cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

DW Amharic

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ko'proq ko'rsatish
Advertising posts
41 742Obunachilar
+1224 soatlar
+3987 kunlar
+1 37030 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Обуначиларнинг ўсиш даражаси

Ma'lumot yuklanmoqda...

የሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ዋና ዋና ዜናዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የልጃገረዶች ጠለፋ መባባሱ ተገለጠ። በክልሉ ኮሬ ዞን ውስጥ «እየተባባሰ መጥቷል» ባሉት ጠለፋ የተነሳ ሴት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ መቸገራቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ቡርኪና ፋሶ ሦስት የፈረንሳይ ዲፕሎማቶችን ከሀገር አባረረች። ፈረንሳይ ውሳኔውን አሳዛኝ ብላዋለች። የደቡብ ሱዳን ፖለቲከኞች በሀገሪቱ ምርጫ ለማካሄድ አስቸኳይ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው የተመድ አሳሰበ። ደቡብ ሱዳን ራሷን የቻለች ሀገር ከሆነችበት ከጎርጎሪዮሳዊው 2011 ዓ,ም አንስቶ ምርጫ አላካሄደችም። ኢራን እስራኤል የኒኩሊየር ተቋሟ ላይ ጥቃት የምትሰነዝር ከሆነ በአጸፋው የእስራኤልን የኒኩሊየር መሰረተ ልማት ኢላማ እንደምታደርግ አስጠነቀቀች። ዝርዝሩን ያንብቡ ያድምጡ https://p.dw.com/p/4ewXO?maca=amh-RED-Telegram-dwcom 👉🏾 @dwamharicbot
Hammasini ko'rsatish...
የሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የልጃገረዶች ጠለፋ መባባሱ ተገለጠ። በክልሉ ኮሬ ዞን ውስጥ «እየተባባሰ መጥቷል» ባሉት ጠለፋ የተነሳ ሴት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ መቸገራቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ቡርኪና ፋሶ ሦስት የፈረንሳይ ዲፕሎማቶችን ከሀገር አባረረች። ፈረንሳይ ውሳኔውን አሳዛኝ ብላዋለች። የደቡብ ሱዳን ፖለቲከኞች በሀገሪቱ ምርጫ ለማካሄድ አስቸኳይ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው የተመድ አሳሰበ። ኢራን እስራኤል የኒኩሊየር ተቋሟ ላይ ጥቃት የምትሰነዝር ከሆነ በአጸፋው የእስራኤልን የኒኩሊየር መሰረተ ልማት ኢላማ እንደምታደርግ አስጠነቀቀች።

Hammasini ko'rsatish...
ለወልቃይትና ራያ አወዛጋቢ አካባቢዎች ፖለቲካዊ መፍትሔ ተጠየቀ

የወልቃይት፣ ጠገዴ ጠለምትና ራያ ጉዳይ በፖለቲካዊ ውሳኔ እንዲፈታ በአሜሪካ የሚገኙ 8 ኢትዮጵያ ሲቪክ ድርጅቶች ጥሪ አቀረቡ።

Hammasini ko'rsatish...
ስለድንበር ውዝግቡ የመቐለ ነዋሪዎች ምን አሉ?

በተለይም ከቅርብ ቀናት ወዲህ በትግራይ እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭቶች እያገረሹ ይገኛሉ። በዚህም ሞትና መፈናቀል ተከስቷል። የሁለቱ ክልል አስተዳደሮችም እርስ በራሳቸው እየተወነጃጀሉ ይገኛሉ።

Hammasini ko'rsatish...
የሽዋልኢድ ዓመታዊ በዓል በጥንታዊቷ ሐረር ከተማ

ለጥንታዊቷ ሀረር ከተማ ከወራት በፊት በዓለም አቀፉ የሳይንስ ፣ የትምህርት እና የባህል ድርጅት በእንግሊዝኛ ምኅፃሩ/ UNESCO ሁለተኛ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበው የሽዋልኢድ ዓመታዊ በዓል የከተማይቱን የቱሪስት መዳረሻነት እድል ይበልጥ ያሰፋል የሚል እምነት አሳድሯል።

Hammasini ko'rsatish...
አሳሳቢው የልጃገረዶች ጠለፋ በኮሬ ዞን

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን «እየተባባሰ መጥቷል» ባሉት ጠለፋ የተነሳ ሴት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ መቸገራቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ ። በዞኑ በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ አስተማሪ የሆነ ቅጣት ስለማይሰጥ አሁን ላይ ሴት ልጆች ወጥተው ለመግባት ሥጋት ውስጥ መውደቃቸውን ነው ነዋሪዎቹ ለዶቼ ቬለ የተናገሩት ።

Hammasini ko'rsatish...
የውጭ ጉዳይ መግለጫ ስለጄኔቫ ድጋፍ ማሰባሰብና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች

በኢትዮጵያ ለተከሰተው የከፋ የሰብአዊ ቀውስ ድጋፍ ለማሰባሰብ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ውስጥ በተደረገው ዓለም አቀፍ ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራ ከታቀደው እጅግ ዝቅ ያለ ገንዘብ ቃል መገባቱ ተገለጠ ። 3.24 ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ ታቅዶ ቃል የተገባው ግን 630 ሚሊዮን ዶላር መሆኑም ተጠቅሷል ።

Hammasini ko'rsatish...
የአውሮጳ ኅብረት ልዩ የመሪዎች ጉባኤ አጀንዳዎችና ውሳኔዎች

ረቡዕ ሚያዝያ 9 ቀን የጀመረው የ27ቱ የአውሮጳ ኅብረት አገሮች የመሪዎች ስብሰባ ዛሬ ከስአት በኋላ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቅቋል ። የጉባኤው አጀንዳ ምን ነበር? ትናንት እና ዛሬ የተከናወነው የኅብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ምንስ ውሳኔ አሳልፎ ተጠናቀቀ?

Hammasini ko'rsatish...
ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ የእደ ጥበባት ዓውደ ርዕይ

የዓዉደ ርእዩ መጠርያ ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ ይሰኛል። ኢትዮጵያ ብዙ ንጹሕ ምንጮች አልዋት። ከነዚህ ንጹሕ ምንጮች መካከል፤ የራስዋን ድርሳናት፤ ሥነ- ነገር የከተበችባቸዉ ፊደላት የሚጠቀሱ ናቸዉ። እግዚቢሽኑን የሚመሰገን ፤ የወጣቶቹ ሥራ ለሃገሪዉ ሃገሩን፤ ነባር ባህሉን እና እዉቀቱን እንዲያዉቅ የሚያደርግ ብዙ ምንጮችንም የሚያሳይ ነዉ።

የጀርመን ፖሊስ ለሩሲያ ይሰልሉ ነበር ያላቸውን ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አዋለየጀርመን አቃቤ ህግ ትናንት ሃሙስ፤ በባቫሪያን ግዛት የቤይሮይት ከተማ ፖሊስ ለሩሲያ በመሰለል የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። የጀርመን እና የሩሲያ ዜግነት ያላቸው እነዚህ ተጠርጣሪዎች ለጥፋት ዓላማ የሚውሉ ፈንጂዎችን አዘጋጅተዋል ሲል በካርልስሩሄ ከተማ የጀርመን ፌደራል አቃቤ ህግ ቢሮ ገልጿል።በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር የሚገኙት እነዚህ ተከሳሾች ዲዬተር ኤስን እና አሌክሳንደር ጄን የሚባሉ ሲሆን፤ የፌደራል ፖሊስ ከባቫሪያን ግዛት ፖሊስ ጋር በመሆን የተከሳሾችን ቤት እና የስራ ቦታዎች ፈትሿል። ለሩሲያ ይሰልሉ ነበር የተባሉት ሁለቱ ተከሳሾች በጀርመን የሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ሰፈሮችን ጨምሮ ጥቃት ሊሰነዝሩ የሚችሉባቸውን ዒላማዎችን ሲቃኙ ነበር ተብሏል።አቃቤ ህግ እንደገለፀው ዲዬተር ኤስን የተባለው ተከሳሽ ከሩሲያ ሚስጥራዊ አገልግሎት ሰጪ ወኪል ጋር ግንኙነት ነበረው።ተከሳሹ ከጥቅምት 2023 ዓ/ም ጀምሮ እርምጃ ከተወካዮቹ ጋር ሀሳብ ሲለዋወጥ እንደነበር ተገልጿል።
Hammasini ko'rsatish...
ወደ ኦሮሚያ ክልል ጊምቢ ወረዳ የተመለሱ ተፈናቃዮች በወባ በሽታ እየተጠቃን ነው አሉ።በደብረብርሃን እና ጃማ መጠለያ ጣቢያ ተጠልለው የነበሩ እና ወደ ቀያቸው የተመለሱ ተፈናቃዮች ለወባ ወረርሽኝ መጋለጣቸውን ገለፁ። በየካቲት ወር 2016 መጀመሪያ ወደ ምዕራብ ወለጋ ግምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ የተመለሱት እነዚህ ተፈናቃዮች የወባ በሽታ ስርጭት በአካባቢው በመስፋፋቱ ከ200 በላይ ሰዎች በወባ መታመማቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።በቦታው የመድኃኒት ባለመኖሩ በርካታ ሰዎች በወባ በሽታ እየተጎዱ እንደሚገኙ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች አብራርተዋል፡፡ የዞኑ ጤና መምሪያ በበኩሉ በአካባቢው የወባ ስርጭት መኖሩን ገልጸው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቤታቸው ከተመለሱ ጊዜ አንስቶ ህኪምና በነጻ እየተሰጠ ይገኛል ብሏል፡፡ ባለሙያዎች በቦታው በጊዜያዊነት ተመድቦ እየተሰራ ነው ብሏል፡፡ዘገባውን ያደረሰን የአሶሳው ዘጋቢያችን ነጋሳ ደሳለኝ ነው። ሙሉ ዘገባውን በማታው የዜና መፅሄት ጠብቁን።
Hammasini ko'rsatish...