cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

Show more
Advertising posts
33 984Subscribers
+1024 hours
+1007 days
+43930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

owdHDfiZEE0QIDiRJgmgFBjfQgR4AFsuYBwFCs.mp4
Show all...
ኤጲስ ቆጶሱ ማር ማሪ ኢማኑኤል በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 2፥120 አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ከአንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል"Bishop Mar Mari Emmanuel" በሲድኒ አውስትራሊያ በሚገኘው የሶሪያውያን ቤተ ክርስቲያን"Assyrian Church" ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ በአሁን ሰዓት "ክርስቶስ መልካም እረኛ ቤተ ክርስቲያን"Christ The Good Shepherd Church" ውስጥ ያገለግሉ ነበር። የሶሪያውያን ቤተክርስቲያን የንስጥሮስ ትምህርት ተከታይ ሲሆኑ የንስጥሮስ ትምህርት "ኢየሱስ በአንድ ስም ሁለት ማንነት"person" አለው፥ በፍጹም አምላካዊ ማንነት የአብ ልጅ በፍጹም ሰዋዊ ማንነት የማርያም ልጅ" የሚል ትምህርት ነው፥ ይህ ትምህርት በ 431 የኤፌሶን ጉባኤ የተወገዘ ሲሆን ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል የእዛ እሳቤ አራማጅ ናቸው። በዓለም ላይ ያሉ ብዙ ኦርቶዶክሶች እኚህን አባት እንደ ኦርቶዶክስ አባት አርገው የሚመለከቱት ትምህርታቸው ከራሳቸው ትምህርት ጋር አነጻጽረው በቅጡ መረዳት የማይችሉት ናቸው፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን የንስጥሮስ ትምህርት በካቶሊክ፣ በምሥራቅ ኦርቶዶክስ፣ በጽብሐዊ ኦርቶዶክስ እና በፕሮቴስታንት የተወገዘ ምንፍቅ ና ነው። ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል በተለያየ ርእሰ ጉዳይ በእንግሊዝኛ መርሐ ግብር የተለያ እሳቦትን በመተናኮል እና በመጎንተል በዓለም ላይ ይታወቃሉ። እስራኤልን፣ ምዕራባውያንን፣ አሜሪካንን፣ ግብረ ሰዶማ ውያንን ሳይቀር ይተቻሉ፥ አልፎ አልፎ ካቶሊክን፣ ፕሮቴስታንትን ሲላቸውም ዲኑል ኢሥላምን ሲወርፉ ይሰማል። ትላንት አንድ ሰው በሚያስተምሩበት ቤተክርስቲያን አደጋ አድርሶባቸው ህክምና ላይ እዳሉ እየተሰማ ነው። አደጋ ያደረሰባቸው ማንነት እስካሁን እንዳልተጣራ እየታወቀ ክርፋታቸው በተገኘው አጋጣሚ የሚያዝረከርኩ ክርስቲያኖች ለሙሥሊም ያላቸው ጥላቻ ምን ያክል የከፋ እና የከረፋ መሆኑን የምታውቁት ሰውዬውን "ሙሥሊም ነው" በማለት ዲናችንን መዝለፍ እና ማብጠልጠል ተያይዘውታል። ሰውዬው ሙሥሊም ቢሆንስ? ሰውዬውን "ትክክል አይደለም" ብሎ እራሱን ማውገዝ እንጂ ዲናችንን ለምን አሳቻ ሰዓት ላይ ጠብቃችሁ ትጎነትላላችሁ? ስንት እና ስንት ሙሥሊሞች በክርስቲያኖች ተገለው እንደ ኖርማል እየታየ አንድ ክርስቲያን ስለተገደለ ክርስትናን የእውነት ሚዛን አርጎ መውሰድ ቂልነት ነው። በእርግጥም ኤጲስ ቆጶሱ ማር ማሪ ኢማኑኤል ለዲኑል ኢሥላም ያላቸው ጥላቻ አይጣል ነው፥ በአገኙት አጋጣሚ ዲናችንን በማበሻቀጥ እና በማብጠልጠል የዘመኑን ዋንጫ ወስደዋል። ከዚህ ሁሉ የገረመኝ ተከታዮቻቸው "ዓይን ስለ ዓይን ጥርስ ስለ ጥርስ" የሚለውን ሕግ ይዘው "የእጁን እንስጠው" ብለው ግብግብ ሲይዙ ነበር። "ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት" የሚለው የሚሠራው ስብከት ላይ ብቻ ነው፦ ማቴዎስ 5፥38 ‘ዓይን ስለ ዓይን ጥርስም ስለ ጥርስ፡’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት። አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ሃይማኖታቸውን እስከምንከተል ድረስ እንዳይወዱን አሏህ በቁርኣኑ ነግሮናል፦ 2፥120 አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ከአንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ አሏህ ለእነርሱ ልብ ይስጣቸው! ለእኛም ትእግስቱን ይስጠን! አሚን። አንብበው ሼር በማድረግ አስነብቡ! ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
የሃይማኖት ንጽጽር ኮርስ በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society" 12ኛ ዙር የሙቃረናህ ደርሥ! "ሙቃረናህ" مُقَارَنَة የሚለው ቃል "ቃረነ" قَارَنَ ማለትም "አነጻጸረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንጽጽር" ማለት ነው፥ ሙቃረናህ የሃይማኖት ንጽጽር"Comparative Religion" ሲሆን በዱኑል ኢሥላም እና እና በክርስትና መካከል ያለው የሥነ መለኮት አንድነት እና ልዩነት እየተነጻጸረ የሚቀርብበት ጥናት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 7 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሁለት ተርም አለው። ፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ አሳብ በፈጣሪ እሳቦት ላይ የሚያውጠነጥነው፦ 1.በነገረ ሥላሴ ጥናት"Triadogy" 2.በነገረ ክርስቶስ ጥናት"Christology" 3.በነገረ ማርያም ጥናት"Mariology" 4. በነገረ መላእክት ጥናት"angelology" 5. በነገረ ምስል ጥናት"Iconlogy" ላይ ነው። ፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በቅዱሳን መጽሐፍት ላይ የሚያውጠነጥነው፦ 1.በአህሉል ኪታብ"People of the Book" 2.በመጽሐፍት"scriptures" 3. በመጽሐፍ አጠባበቅ"preservation" 4.በመጽሐፍት ልኬት"Standardization" 5. በባይብል ግጭት"Contradiction" 6. በኦሪት"Torah" 7. በወንጌል"Gospel" ላይ ነው። አባሪ ኮርሶች፦ 1. ዐቂዳህ"creed" 2. ሥነ ምግባር"ethics" 3. ሥነ አመክንዮ"logic" 4. ሥነ ልቦና"psychology" 5. ሥነ ቋንቋ"linguistics" ናቸው። ለመመዝገብ ከታች የተዘረዘሩት አድሚናት በውስጥ ያናግሩ! ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://t.me/arhmanu እኅት ሰላም፦ http://t.me/SeuweSe አኅት ዘሃራ፦ https://t.me/Zhara_mustefa እኅት አበባ፦ http://t.me/selemtewa ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ! ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!
Show all...
አምላካችን አሏህ ሰው እርስ በእርስ ሥጋውን እንዲበላላ ሐላል አላደረግም፥ ከዚያ በተቃራኒ የሰው ሥጋ መብላት ሐራም ነው፦ 49፥12 ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ! አንደኛችሁ የወንድሙን ሥጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? መብላቱን ጠላችሁት ሐሜቱንም ጥሉት፡፡ አሏህን ፍሩ! አሏህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا ۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 106 አነሥ ኢብኑ-ማሊክ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ወደ ሰማይ በተወሰድኩኝ ጊዜ ከነሐስ የሆነ ጥፍር ኖሯቸው ፊቶቻቸውን እና ደረቶቻቸውን የሚቧጥጡ በሆኑ ሰዎች በኩል አለፍኩ። እኔም፡- "ጂብሪል ሆይ! እነማናቸው እነዚህ? ስለው፥ እርሱም፦ "እነዚህ የሰዎችን ሥጋ የሚበሉ እና ክብራቸውን የሚነኩ ናቸው" አለኝ"። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لَمَّا عُرِجَ بِي مَرَرْتُ بِقَوْمٍ لَهُمْ أَظْفَارٌ مِنْ نُحَاسٍ يَخْمِشُونَ وُجُوهَهُمْ وَصُدُورَهُمْ فَقُلْتُ مَنْ هَؤُلاَءِ يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَؤُلاَءِ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ لُحُومَ النَّاسِ وَيَقَعُونَ فِي أَعْرَاضِهِمْ ‏"‏ እዚህ ቁርኣን እና እዚህ ሐዲስ ላይ ሐሜት ልክ የሰውን ሥጋ እንደ መብላት ሐራም ከሆነ የሰውን ሥጋ ለምግብነት መጠቀም ሐራም ነው። ሰው ከሞተ በኃላ ሥጋው ሬሳ ነውና መቅበር እንጂ የሞተ ሰው ሥጋ መብላት በቁሙ ያለው ሰው ሥጋ እንደ መብላት ይቆጠራል፦ ሡነን እብኑ ማጃህ መጽሐፍ 6, ሐዲስ 184 ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የሞተ ሰው አጥንት መስበር በሕይወት እያለ እንደ መሰባበር ነው"። عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ كَسْرُ عَظْمِ الْمَيِّتِ كَكَسْرِهِ حَيًّا ‏"‏ ‏ ኢማም ሙሐመድ ኢብኑ ኢድሪሥ አሽ ሻፊዒይ "የሞተ ሰው ሥጋ ሕይወትን ለማትረፍ በረሃብ ጊዜ ይፈቀዳል" ብለዋል፥ ለዚህ አባባል ምንም ዓይነት የቁርኣን ሆነ የሐዲስ ደሊል እንከሌለ ድረስ ንግግራቸው ውድቅ ይሆናል። እርሳቸው በ 204 ዓመተ ሒጅራህ በትህትና "የእኔን ንግግር የሚቃወም ሶሒሕ ሐዲስ ሲኖር በሐዲሱን ተግብሩ! ቃሌን ተዉት" ብለዋል፦ "የእኔን ንግግር የሚቃወም ሶሒሕ ሐዲስ ሲኖር በሐዲሱን ተግብሩ! ቃሌን ተዉት"። إذا صح الحديث خلاف قولي فاعملوا بالحديث واتركوا قولي ጃሚዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 37 ሐዲስ 106 አቢ ሠዒድ አል ኹድሪይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ማንም ይሁን መልካሙን የበላ፣ በሡናህ የተገበረ እና ሰዎች ከሚያስከትለው መዘዝ የታደገ ወደ ጀናህ ይገባል"። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ مَنْ أَكَلَ طَيِّبًا وَعَمِلَ فِي سُنَّةٍ وَأَمِنَ النَّاسُ بَوَائِقَهُ دَخَلَ الْجَنَّةَ ‏"‏ ‏.‏ "ሐላል" حَلاَل ማለት "የተፈቀደ" ማለት ሲሆን በተቃራኒው "ሐራም" حَرَام "የተከለከለ" ማለት ነው። አንድ ጉዳይ ሐላል ወይም ሐራም ማለት የሚቻለው የዓለማቱ ጌታ አሏህ በቁርኣን የነገረን እና ተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” በሐዲሳቸው የነገሩን ብቻ እና ብቻ ነው፥ ሐላል የሆነ ጉዳይ ሆነ ሐራም የሆነ ጉዳይ በሸሪዓችን በግልጽ የተቀመጡት ብቻ ናቸው፦ 7፥157 "መልካም ነገሮችንም ለነርሱ ይፈቅድላቸዋል፥ መጥፎ ነገሮችንም በእነርሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል"፡፡ وَيُحِلُّ لَهُمُ الطَّيِّبَاتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيْهِمُ الْخَبَائِثَ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 23, ሐዲስ 4 አን-ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ሐላል ግልጽ ነው፥ ሐራምም ግልጽ ነው። በሁለቱ መካከል ያለው ግን አጠራጣሪ ነገር ነው”። قَالَ سَمِعْتُ النُّعْمَانَ بْنَ بَشِيرٍ، – وَلاَ أَسْمَعُ أَحَدًا بَعْدَهُ يَقُولُ – سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏”‏ إِنَّ الْحَلاَلَ بَيِّنٌ وَإِنَّ الْحَرَامَ بَيِّنٌ وَبَيْنَهُمَا أُمُورٌ مُشْتَبِهَاتٌ ‏”‏ አንድ ጉዳይ በግልጽ መፈቀዱ እና መከልከሉ ካልተገለጸ "ተፈቅዷል" "ተከልክሏል" ማለት የለብንም፥ ያልተፈቀደ እና ያልተከለከለ ነገር ጉዳይ አጠራጣሪ ነው፥ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ፦ "የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት ያረጋጋል፥ ውሸት ግን ያጠራጥራል" ብለውናል፦ ጃምዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 2708 አቢል ሐውራእ አሥ-ሠዕዲይ እንደተረከው፦ "እኔ ለሐሠን ኢብኑ ዐሊይ፦ "ከአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ምን ሐፈዝክ? ብዬ አልኩኝ፥ እርሱም፦ "ከአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሐፈዝኩኝ፦ "የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት ያረጋጋል፥ ውሸት ግን ያጠራጥራል"። عَنْ أَبِي الْحَوْرَاءِ السَّعْدِيِّ، قَالَ قُلْتُ لِلْحَسَنِ بْنِ عَلِيٍّ مَا حَفِظْتَ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ حَفِظْتُ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ دَعْ مَا يَرِيبُكَ إِلَى مَا لاَ يَرِيبُكَ فَإِنَّ الصِّدْقَ طُمَأْنِينَةٌ وَإِنَّ الْكَذِبَ رِيبَةٌ ‏"‏ "መሽቡህ" مَشْبُوه የሆኑ ነገሮችን መተው ተመራጩ ሒክማህ ነው። አምላካችን አሏህ በግልጠተ መለኮት "ሐላል" ያለው "ሐላል" ማለት "ሐራም" ያለው "ሐራም" ማለት ትልቅ ታዛዥነት ነው፦ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 29, ሐዲስ 117 ሠልማን አል ፋርሢይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” ስለ ቅቤ፣ ስለ ዓይብ እና ስለ አህዮች ተጠየቁ፥ እርሳቸው እንዲህ አሉ፦ "ሐላል አሏህ በመጽሐፉ የፈቀደው ነው፥ ሐራም አሏህ በመጽሐፉ የከለከለው ነው። عَنْ سَلْمَانَ الْفَارِسِيِّ، قَالَ سُئِلَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ عَنِ السَّمْنِ وَالْجُبْنِ وَالْفِرَاءِ قَالَ ‏ "‏ الْحَلاَلُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ فِي كِتَابِهِ وَالْحَرَامُ مَا حَرَّمَ اللَّهُ فِي كِتَابِهِ "‏ ‏.‏ አምላካችን አሏህ ሡናን ከሚተገብሩ ሙእሚን ያድርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
ን የሚቧጥጡ በሆኑ ሰዎች በኩል አለፍኩ። እኔም፡- "ጂብሪል ሆይ! እነማናቸው እነዚህ? ስለው፥ እርሱም፦ "እነዚህ የሰዎችን ሥጋ የሚበሉ እና ክብራቸውን የሚነኩ ናቸው" አለኝ"። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لَمَّا عُرِجَ بِي مَرَرْتُ بِقَوْمٍ لَهُمْ أَظْفَارٌ مِنْ نُحَاسٍ يَخْمِشُونَ وُجُوهَهُمْ وَصُدُورَهُمْ فَقُلْتُ مَنْ هَؤُلاَءِ يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَؤُلاَءِ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ لُحُومَ النَّاسِ وَيَقَعُونَ فِي أَعْرَاضِهِمْ ‏"‏
Show all...
የሰው ሥጋ ይበላልን? በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡ 7፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ አምላካችን አሏህ በመልእክተኞች በኩል "ከመልካሞቹ ምግቦች ብሉ" ብሎ ነግሮናል፥ እነዚህ መልካም ምግቦት የሰጠን ሲሳይ ናቸው፦ 23፥51 እናንተ መልእክተኞች ሆይ! ከመልካሞቹ ምግቦች ብሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፡፡ እኔ የምተሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነኝ፡፡ يَا أَيُّهَا الرُّسُلُ كُلُوا مِنَ الطَّيِّبَاتِ وَاعْمَلُوا صَالِحًا ۖ إِنِّي بِمَا تَعْمَلُونَ عَلِيمٌ 2፥172 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእነዚያ ከሰጠናችሁ ሲሳይ መልካሞቹን ብሉ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደኾናችሁ አሏህን አመስግኑ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُلُوا مِن طَيِّبَاتِ مَا رَزَقْنَاكُمْ وَاشْكُرُوا لِلَّهِ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ ጃሚዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47 ሐዲስ 41 አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህም መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "እናንተ ሰዎች ሆይ! አሏህ መልካም ነው፥ እርሱ መልካም እንጂ አይቀበልም። አሏህ ምእመናንን መልእክተኞችን ባዘዘው መሠረት አዘዛቸው። እርሱም፦ "እናንተ መልእክተኞች ሆይ! ከመልካሞቹ ምግቦች ብሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፡፡ እኔ የምተሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነኝ" አለ፥ እርሱም፦ "እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእነዚያ ከሰጠናችሁ ሲሳይ መልካሞቹን ብሉ" አለ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّ اللَّهَ طَيِّبٌ وَلاَ يَقْبَلُ إِلاَّ طَيِّبًا وَإِنَّ اللَّهَ أَمَرَ الْمُؤْمِنِينَ بِمَا أَمَرَ بِهِ الْمُرْسَلِينَ فَقَالَ ‏:‏ ‏(‏يَا أَيُّهَا الرُّسُلُ كُلُوا مِنَ الطَّيِّبَاتِ وَاعْمَلُوا صَالِحًا إِنِّي بِمَا تَعْمَلُونَ عَلِيمٌ ‏)‏ وَقَالَ أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُلُوا مِنْ طَيِّبَاتِ مَا رَزَقْنَاكُمْ ‏)‏ ‏"‏ ‏.‏ በተቃራኒው በክትን፣ ደምን፣ የእሪያ ሥጋን እና ከአሏህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር መብላት ሐራም ነው፦ 2፥173 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የእሪያ ሥጋን እና በእርሱም ማረድ ከአሏህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ بِهِ لِغَيْرِ اللَّهِ በክትን፣ ደምን፣ የእሪያ ሥጋን እና ከአሏህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር መብላት ቢሆንም በረሃብ ምክንያት በሞት አፋፍ ላይ ላለ ሰው ሕይወት ለማትረፍ ተፈቅዷል፦ 2፥173 ሽፍታ እና ወሰን አላፊ ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም። አሏህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَلَا إِثْمَ عَلَيْهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ ነገር ግን በማንኛውም ወቅት እና ሁኔታ ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ እና ሁለት ዓይነት ደም መብላት ሐላል ነው፥ ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ ዓሣ እና አንበጣ ሲሆኑ ዓሣ እና አንበጣ የማይታረዱ ሥጋ ናቸው። ሁለት ዓይነት ደም ደግሞ ጉበት እና ጣፊያ ናቸው፦ 16፥14 እርሱም ያ ባሕርን ከእርሱ እርጥብ ሥጋን ልትበሉ እና ከእርሱም የምትለብሱትን ጌጣጌጥ ታወጡ ዘንድ ያገራ ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي سَخَّرَ الْبَحْرَ لِتَأْكُلُوا مِنْهُ لَحْمًا طَرِيًّا وَتَسْتَخْرِجُوا مِنْهُ حِلْيَةً تَلْبَسُونَهَا 5፥96 የባሕር ታዳኝ እና ምግቡ ለእናንተ እና ለመንገደኞችም መጠቀሚያ ይኾን ዘንድ ለእናንተ ተፈቀደ፡፡ የየብስ አውሬ በእናንተ ላይ እርም ተደረገ፡፡ أُحِلَّ لَكُمْ صَيْدُ الْبَحْرِ وَطَعَامُهُ مَتَاعًا لَّكُمْ وَلِلسَّيَّارَةِ ۖ وَحُرِّمَ عَلَيْكُمْ صَيْدُ الْبَرِّ مَا دُمْتُمْ حُرُمًا ۗ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 29, ሐዲስ 64 ዐብደሏህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ እና ሁለት ዓይነት ደም ለእኛ ተፈቅዶልናል፥ ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ ዓሣ እና አንበጣ ሲሆን ሁለት ዓይነት ደም ደግሞ ጉበት እና ጣፊያ ነው"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ "‏ أُحِلَّتْ لَنَا مَيْتَتَانِ وَدَمَانِ فَأَمَّا الْمَيْتَتَانِ فَالْحُوتُ وَالْجَرَادُ وَأَمَّا الدَّمَانِ فَالْكَبِدُ وَالطِّحَالُ ‏"‏ ‏.‏ ቡሉጉል መራም መጽሐፍ 1 ሐዲስ 1 አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአሏህም መልእክተኛ"ﷺ" ስለ ባሕር እንዲህ አሉ፦ "እርሱ ውኃው ንጹሕ ነው፥ ሙታኑ እንስሳት ለመብላት ሐላል ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ‏- رضى الله عنه ‏- قَالَ: قَالَ رَسُولُ اَللَّهِ ‏- صلى الله عليه وسلم ‏-فِي اَلْبَحْرِ: { هُوَ اَلطُّهُورُ مَاؤُهُ, اَلْحِلُّ مَيْتَتُهُ } ይህንን ከተረዳን ዘንዳ አምላካችን አሏህ የሰውን ልጅ ያከበረው ፍጡር ነው፥ ሐላል ምግብ ከየብስ እና ከባሕር እንዲመገቡት የአደምን ልጆች አሏህ በየብስ እና በባሕር አሳፈራቸው። ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች ከማዕድናት፣ ከዕጽዋት፣ ከእንስሳት በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጣቸው፦ 7፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ 7፥70 በየብስ እና በባሕር አሳፈርናቸው፥ ከመልካሞች ሲሳዮች ሰጠናቸው፡፡ وَحَمَلْنَاهُمْ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ وَرَزَقْنَاهُم مِّنَ الطَّيِّبَاتِ 7፥70 ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው፡፡ وَفَضَّلْنَاهُمْ عَلَىٰ كَثِيرٍ مِّمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلًا አምላካችን አሏህ ሰው እርስ በእርስ ሥጋውን እንዲበላላ ሐላል አላደረግም፥ ከዚያ በተቃራኒ የሰው ሥጋ መብላት ሐራም ነው፦ 49፥12 ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ! አንደኛችሁ የወንድሙን ሥጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? መብላቱን ጠላችሁት ሐሜቱንም ጥሉት፡፡ አሏህን ፍሩ! አሏህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا ۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 106 አነሥ ኢብኑ-ማሊክ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ወደ ሰማይ በተወሰድኩኝ ጊዜ ከነሐስ የሆነ ጥፍር ኖሯቸው ፊቶቻቸውን እና ደረቶቻቸው
Show all...
አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ! እንኳን የዒዱል ፊጥር በሰላም አደረሳችሁ! ተናፍቆ የሚመጣ እና ሳይጠገብ የሚሄድ ብቸኛው ወር የረመዷን ወር ነው። አሏህ ከእኛም ከእናንተ መልካም ሥራዎችን ይቀበለን! አሚን። ዒድ ሙባረክ!
Show all...
"ኢየሱስ በቀጣይ እሑድ ይመጣል" ልደታ ቤተክርስቲያን መምህርት አስካለ በልጅነታችን ኢየሱስ፦ ፨በዕለተ እሑድ ፨በቀኑ 29 ቀን ፨በወሩ መጋቢት ወር ፨በዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ከገጠመ ይመጣል ብላ አስተምራናለች። ባሕረ አሳብን ቀምረው የአገራችን ሊቃውንት "በዘመነ ዮሐንስ እሑድ በመጋቢት 29 ቀን ይመጣል" ባሉት መሠረት እየጠበቅን ነው። ይህን ካልሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሐሰተኛ ነቢያት ተለይታ አትለይም። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
Show all...