ከወር በፊት በዲሴምበር 24 የሆነ የማላቀው አካል ፌስቡኬን ሀክ ማድረጉን በኢሜል ደረሰኝ። በወቅቱ በኛ ሀገር ሌሊት ስለነበር ጉዳዩን ያወቅኩት በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ወደፌስቡክ ልገባ ስል ነበር። አካውንቱ ላይ መጠባበቂያ ቁጥሬን ሳይቀር ሪሙቭ አድርገው በሌላ የኢትዮጵያ ቁጥር ተክተውት ስለነበር ያለኝ ብቸኛ አማራጭ በኢሜሌ አማካኝነት December 25 ላይ አካውንቱን ሪከቨር አድርጌ ቁጥሩን ማስወገድ ነበር። በወቅቱ አካውንቱን ከመለስኩት በኃላ ጉዳዩ ትልቅ ነገር ስላልመሠለኝ ለጀመዓ ሹራ ግሩፖች ብቻ ነግሬ ቀለል አድርጌ ትቸው ነበር።
...
በዛች ቅጽበት በርካታ ነገር መደረጉ የገባኝ ግን ዛሬ አቡ ዩስራ ሲደውልልኝ ነው። በነዛ ጊዜያት ግሩፕ ላይ አብረውኝ የነበሩ ወንድሞችን ኡስታዝ Sadiq Mohammed Ahmed ጨምሮ ሁሉንም በኔ አካውንት በገቡበት ወቅት ሪሙቭ አድርገዋቸዋል። የግሩፑን ክሬተር (ሱመያ የሚል አካውንት) ሪሙቭ ማድረግ ስለማይቻልና ጠዋት አጋጣሚ እኔም አካውንቱን ማስመለስ ባልችል ኑኖ ግሩፑን ሙሉ ለሙሉ ወስደውት ነበር። ይህ ሁሉ መሆኑን ግን እስከዛሬዋ ቀን ድረስ አሏህ ﷻ ምስክሬ ነው ምንም የማቀው ነገር የለም። አቡ ዩስራ ከግሩፑ ሪሙቭ መደረጉንና ምክንያቱን ሲጠይቀኝ ግሩፑ ከነ አካቴው ጠፍቶ ካልሆነ በስተቀር ማንም በጤናው አቡ ዩስራን ሪሙቭ ሊያደርገው እንደማይችል ስለማውቅ "ሁላችንም የለንም በለኛ" እያልኩት ወደ ግሩፑ ገባህ። ስገባ ግን ደነገጥኩ እሱ ብቻ ሳይሆን ሁሉም አድሚኖች የሉም። ያለሁት እኔ ብቻ ነኝ..!
...
በዚህም ምክንያት ጉዳዩን ለአቡ ዩስራ በግርምት ስነግረው በአጋጣሚ ስክሪን ሹት አድርግሎኝ ብሎኝ ከታች ያለውን ላኩለት። አልሐምዱሊላህ አቡ ዩስራ በጣም አስታዋሽ ነውና ቴሌግራም የኡስታዞች ግሩፕ ላይ አካውንቴ ሀክ ተደርጎ እንደነበር የተናገርኩበትን ቀን ሪፕላይ አድርጎ በዚያ ቀን መሆኑን ነገረኝ። ሀቂቃ ይህንን ጉዳይ ሌላ ሰው ቢሆን በጣም ያስከፋና ያበሳጭ ነበር። ወንድሞቼ ግን ሙሉ ለሙሉ የሚያውቁኝና እንደዚህ አይነት ስህተት እንደማልፈጽሞ የሚተማመኑብኝ ቢሆንም ትንሽም ቢሆን የተከፋ ወንድምና እህት ካለ አሏህ ﷻ በሚያውቀው ፈጽሞ ይህ ተግባር የኔ እንዳልሆነና ከታች እንደምታዩት አካውንቱም በእጄ እንዳልነበረ በቀናነት እንድትረዱት በማሰብ ለማብራራት ተገድጃለሁ። በዚህ አጋጣሚ ካወቅነው ከዚህ ተግባር ሌላም ክስተት አብሬያችሁ በምሰራበት ፔጅም ሆነ ግሩፕ በሌሎቻችሁም ተፈጽሞ ከሆነ እንደምታዩት ፈጽሞ የማላቀው ነገር እንደሆነ እንድትረዱልኝ ነው። ጀዛኩሙሏሁ ኸይራ።
___
© የሕያ ኢብኑ ኑህ
Show more ...