cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
35 721
مشترکین
-1224 ساعت
-37 روز
+37930 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የኤፌሶን ጉባኤ ክፍል አንድ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 5፥17 እነዚያ "አሏህ እርሱ የመርየም ልጅ አል መሢሕ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ሐዋርያት ኢየሱስን "ነቢይ፣ መልእክተኛ እና መሢሕ" ሲሉት ከሐዋርያት ህልፈት በኃላ የተነሱት የሁለተኛው ክፍለ ዘመን ክልዔታውያን ሰዎች ኢየሱስ ከአንዱ አምላክ ሌላ ሁለተኛ አምላክ አድርገው ተቀብለውት ነበር። ከዚህ በፊት የጻፍኩትን ይህንን ጽሑፍ ይመልከቱ! https://t.me/Wahidcom/3687 በመቀጠል የኒቂያ ጉባኤ ላይ ኢየሱስን "ከአምላክ የተገኘ አምላክ" በማለት እና የቆስጠንጢንያ ጉባኤ ደግሞ "ከፍጥረት በፊት ከአብ ተወለደ" የሚለው የነገረ ክርስቶስ ውዝግብ የሄደበት ጠመዝማዛ እና ዘወርዋራ መንገድ ሲቦተረፍ አንዱ ቀዳዳ ለመድፈን በሌላው መቦተርፉ ውዝግቡን አባባሰው እንጂ አላበረደውም፥ ከላይ "ከአምላክ የተገኘ አምላክ" "ከፍጥረት በፊት ከአብ ተወለደ" የተባለውን መለኮታዊ አካል ታች ድንግል ማርያም ማሕፀን ከተፈጠረው ሰብአዊ አካል ጋር ማገጣጠሙ ላይ ትልቅ ውዝግብ ስለፈጠረ የኤፌሶን ጉባኤ ተመሠረተ። የዚህን ጉባኤ ነገረ ክርስቶሳዊ ውዝግብ ለመረዳት አንዳንድ ሥነ መለኮታዊ ስያሜ እንመልከት! "ፕሮሶፓን" πρόσωπον የሚለው ቃል "ፕሮስ" እና "ኦፓስ" ከሚለው ከሚሉት ሁለት ቃላት የተዋቀረ ነው፥ "ፕሮስ" πρός ማለት "ዘንድ" ማለት ሲሆን "ኦፕስ" ὤψ ማለት "ዓይን" ማለት ነው። በጥቅሉ "ፕሮሶፓን" πρόσωπον ማለት "ፊት" ማለት ሲሆን "ፊት" ለድራማ ወይም ለቲያት ፊት ላይ የሚያጠልቁት "ጭንብል"mask" እራሱ "ፕሮሶፓን" πρόσωπον ይባላል፥ ለምሳሌ፦ ማቴዎስ 6፥17 "ፊትህን" ታጠብ። τὸ πρόσωπόν σου νίψαι, እዚህ አንቀጽ ላይ "ፊት" ለሚለው የገባው ቃል "ፕሮሶፓን" πρόσωπον እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሙያዊ ፍቺው "እኔ" የሚል ቅዋሜ ማንነት"person" ለማመልከት ይመጣል። "ሂፓስታቲስ" ὑπόστασις ማለት ደግሞ "ባሕርይ"substance" ማለት ነው፦ ዕብራውያን 1፥3 እርሱ የክብሩ መንጸባረቅ እና የባሕርዩ ምሳሌ ነው። ὃς ὢν ἀπαύγασμα τῆς δόξης καὶ χαρακτὴρ τῆς ὑποστάσεως αὐτοῦ, እዚህ አንቀጽ ላይ "ባሕርይ" ለሚለው የገባው ቃል "ሂፓስታቲስ" ὑπόστασις እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን በሥነ መለኮት ጥናት "ሂፓስታቲስ" ሙያዊ ፍቺው "ፕሮሶፓን" πρόσωπον ለሚለው ተለዋዋጭ ቃል ለማመልከት ይመጣል፥ ለምሳሌ፦ በአንድ ግጻዌ መለኮት ሦስት አካላት ለማመልከት ዲዮናስዮስ ዘእስክንድሪያ ይጠቀምበታል፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 91 ቁጥር 18 "እርሱ ዛሬም ከሦስቱ አካላት አንዱ ነው፥ ሰው ከመሆኑ አስቀድሞ ሰው ከመሆኑም በኃላ በሦስት አካላት አራተኛ አካል ሳይጨምር አብን መንፈስ ቅዱስን በአንድ ባሕርይ ይመስላቸዋል"። ሥላሴ "የሦስት አካላት ኅብረት"Trihypostatic union" የመባሉ ምክንያት ይህ ነው። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ በሥነ ኑባሬ ጥናት "እኔ" የሚል ማንነት "መለኮታዊ አካል"Divine Person" ያለ ሲሆን በተመሳሳይ እኔ የሚል ማንነት ሰብአዊ አካል"Human Person" አለ፥ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ "ወልድ ከሁለት አካል አንድ አካል" ሲል ይህንኑ ታሳቢ አርጎ ነው፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 73 ቁጥር 3 "እርሱ ወልድ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ሆነ"። እዚህ ዐውድ ላይ "አካል" ሲባል "ገላ"body" ሳይሆን ማንነት"person" ነው፥ መለኮት ማንነት እንጂ ገላ ስላልሆነ "ከሁለት አካል" ሲባል "ከሁለት ገላ" ሳይሆን "ከሁለት ማንነት" ማለት ነው። አካል"Hypostasis" ከባሕርይ ተለይቶ የተቀመጠ ስለሆነ ቴዎዶስዮስ ዘእስክንድርያ "ከሁለት አካላት አንድ አካል እንደሆነ ከሁለት ባሕርያት አንድ ባሕርይ" በማለት አካል እና ባሕርይን ለይቶ አስቀምጦታል፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 92 ቁጥር 12 "በሥጋ ከእርሷ የተወለደው እርሱ ፍጹም አምላክ ነው፥ ፍጹም ሰው ነው። ከሁለት አካላት አንድ አካል እንደሆነ ከሁለት ባሕርያት አንድ ባሕርይ እንደሆነ እናውቃለን"። "ባሕርይ" የሚለው ቃል "ባሕር" ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን "መሠረት" ማለት ነው፥ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገጽ 262 ተመልከት! "ባሕርይ" በቀላል ዐማርኛ "ምንነት" ማለት ነው፥ ምንነት የማንነት መሠረት ሲሆን ማንነት ደግሞ የምንነት መገለጫ ነው። አንድ ሰው "ሙሉ ሰው"fully man" ነው" ስንል "እኔ" የሚል ማንታዊ መገለጫ እና "ሰው" የሚል የማንነቱ ምንነታዊ መሠረት አለው። "አንተ ማን ነህ? ስባል "እከሌ" "እከሊት" በመባል እኔነቴን በማመልከት "ወሒድ ነኝ" እላለው፥ "አንተ ምንድን ነህ? ስባል "ሰው ነኝ" በማለት ምንነቴን እናገራለው። አንድ አምላክ "ሙሉ አምላክ"fully God" ነው" ስንል "እኔ" የሚል ማንታዊ መገለጫ እና "አምላክ" የሚል የማንነቱ ምንነታዊ መሠረት አለው። የኤፌሶን ጉባኤ በንስጥሮስ እሳቤ እና በቄርሎስ እሳቤ መካከል ፍጹም አምላክ እና ፍጹም ሰው የማገጣጠሙ እና የማጣመሩ ውዝግብ ነው፥ በእርግጥ ያንን ፍጹም አምላክ አሏህን "ፍጹም ሰው መሢሑ ነው" ማለት ክህደት ነው፦ 5፥17 እነዚያ "አሏህ እርሱ የመርየም ልጅ አል መሢሕ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ ከድንግል ማርያም ሰው የሆነውን አካል "እውነተኛ የባሕርይ አምላክ ነው" በማለት ክህደቱን ዘርቷል፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 29 ቁጥር 20 "ከእመቤታችን ከቅድስት ከድንግል ማርያም የነሳው ይህ ሥጋም እውነተኛ የባሕርይ አምላክ ነው"። ያልሞላ ጋን ይመስል የተንቦጫቦጩበት ይህ ትምህርት ውጤቱ ዐበይት ክርስትና "ፈጣሪ ፍጡር ሆነ" የሚል ትምህርት ሆነ፦ ሃይማኖተ-አበው ምዕራፍ 112 ቁጥር 31 "ወፈጣሪ ኮነ ፍጡረ እንተ ይእቲ እምህላዌነ ድንግል ዘበአማን ማርያም" ትርጉም፦ "ፈጣሪ ከእኛ ባሕረይ ከተገኘች በእውነት ድንግል ከምትሆን ከማርያም ፍጡር ሆነ" ሲሆን "ፈጣሪ ፍጡር ሆነ" የሚለውስ ትምህርት ሕሊና ይቀበለዋልን? ከፍጹም አምላክ የተገኘውን ልጅ እና ከፍጹም ሰው የተገኘውን ልጅ የማገጣጠሙ ውስብስብ የንስጥሮስ እሳቤ እና የቄርሎስ እሳቤ ኢንሻላህ በቀጣዩ ክፍል እንዳስሳለን! ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
የተደበቀው እውነት መጽሐፍ በገበያ ላይ የጠፋ ቢሆንም ቤተል መሥጂድ አጠገብ አት ተቅዋ ኢሥላማዊ መጻሕፍት መሸጫ ውስጥ ይገኛል። እረ ሌሎችም መጻሕፍት እዚህ የመጻሕፍት መደብር ውስጥ ይገኛል። ጎራ ይበሉ! ለበለጠ መረጃ በ 0911663699 kubera ብለው ይደውሉ።
نمایش همه...
ይመሰክራሉ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 36፥65 ዛሬ በአፎቻቸው ላይ እናትምና እጆቻቸው ያነጋግሩናል፡፡ እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ሁሉ ይመሰክራሉ፡፡ الْيَوْمَ نَخْتِمُ عَلَىٰ أَفْوَاهِهِمْ وَتُكَلِّمُنَا أَيْدِيهِمْ وَتَشْهَدُ أَرْجُلُهُم بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ አምላካችን አሏህ በትንሳኤ ቀን እንዲመሰክሩ የሚያደርጋቸው ፍጡራን በዱንያህ ውስጥ መናገር የማይችሉ ፍጥረታትን ነው፥ ለምሳሌ የሰው ምላስ፣ ጆሮ፣ ዓይን፣ እጅ፣ እግር እና ቆዳ አሁን ላይ የማይናገር ሲሆን የትንሳኤ ቀን ግን አሏህ እንዲናገሩ በማድረግ ይመሰክራሉ፦ 24፥24 በእነርሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ነገር በሚመሰክሩባቸው ቀን ከባድ ቅጣት አላቸው፡፡ يَوْمَ تَشْهَدُ عَلَيْهِمْ أَلْسِنَتُهُمْ وَأَيْدِيهِمْ وَأَرْجُلُهُم بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ 41፥20 በመጧትም ጊዜ ጆሮዎቻቸው፣ ዓይኖቻቸው እና ቆዳዎቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ነገር በእነርሱ ላይ ይመሰክሩባቸዋል፡፡ حَتَّىٰ إِذَا مَا جَاءُوهَا شَهِدَ عَلَيْهِمْ سَمْعُهُمْ وَأَبْصَارُهُمْ وَجُلُودُهُم بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ 36፥65 ዛሬ በአፎቻቸው ላይ እናትምና እጆቻቸው ያነጋግሩናል፡፡ እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ሁሉ ይመሰክራሉ፡፡ الْيَوْمَ نَخْتِمُ عَلَىٰ أَفْوَاهِهِمْ وَتُكَلِّمُنَا أَيْدِيهِمْ وَتَشْهَدُ أَرْجُلُهُم بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ በእርግጥም ሰው በራሱ ላይ አስረጅ ነው፥ ከሓዲ መሆኑን በራሱ ላይ በራሱ ምላስ፣ ጆሮ፣ ዓይን፣ እጅ፣ እግር እና ቆዳ ይመሰክራል፦ 75፥14 በእርግጥም ሰው በራሱ ላይ አስረጅ ነው። بَلِ الْإِنسَانُ عَلَىٰ نَفْسِهِ بَصِيرَةٌ 6፥130 "በራሳቸውም ላይ እነርሱ ከሓዲዎች የነበሩ መኾናቸውን መሰከሩ"፡፡ وَشَهِدُوا۟ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ أَنَّهُمْ كَانُوا۟ كَٰفِرِينَ 7፥37 "እነርሱም ከሓዲያን እንደነበሩ በራሳቸው ላይ ይመሰክራሉ"፡፡ وَشَهِدُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ أَنَّهُمْ كَانُوا كَافِرِينَ በትንሳኤ ቀን የአንገት ቅርፅ ከእሳት ይወጣል፥ ለእርሱ የሚያይበት ዓይኖች፣ የሚሰማበት ጆሮዎች እና የሚናገርበት አንደበት ይኖረዋል፦  ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 39, ሐዲስ 2775 አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "በትንሳኤ ቀን የአንገት ቅርፅ ከእሳት ይወጣል፥ ለእርሱ የሚያይበት ዓይኖች፣ የሚሰማበት ጆሮዎች እና በሦስት ሰዎች ላይ ተወክያለው፥ እነርሱም፦ በእያንዳንዱ አረመኔ አንባገነን ላይ፣ ከአሏህ ሌላ አምላክን የሚጣራ ሁሉ እና ቀራፆች ናቸው" ብሎ የሚናገርበት አንደበት ይኖረዋል"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ يَخْرُجُ عُنُقٌ مِنَ النَّارِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ لَهُ عَيْنَانِ تُبْصِرَانِ وَأُذُنَانِ تَسْمَعَانِ وَلِسَانٌ يَنْطِقُ يَقُولُ إِنِّي وُكِّلْتُ بِثَلاَثَةٍ بِكُلِّ جَبَّارٍ عَنِيدٍ وَبِكُلِّ مَنْ دَعَا مَعَ اللَّهِ إِلَهًا آخَرَ وَبِالْمُصَوِّرِينَ ‏"‏ ‏ “ሐጅ” حَجّ የሚለው ቃል “ሐጀ” حَجَّ ማለትም “ጎበኘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “ጉብኝት” ማለት ነው። የአላህ ቤት የሚጎበኝ ተባዕት “ሓጅ” حَاجّ ሲባል የአላህ ቤት የሚምትጎበኝ እንስት ደግሞ “ሓጃህ” حَاجَّة‎ ትባላለች፥ የሓጅ ወይም የሓጃህ ብዙ ቁጥር ደግሞ “ሑጇጅ” حُجَّاج‎ ይባላሉ። እሳት ለቅጣት የሚያይበት ዓይኖች፣ የሚሰማበት ጆሮዎች እና የሚናገርበት አንደበት እንደሚኖረው ሁሉ በሐጅ ሥርዓት ላይ ሐጀሩል አሥወድ በነኩት ሑጇጅ ላይ መልካም ምስክር ይመሰክራል፦ ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 155 ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ስለ ሐጀሩል አሥወድ እንዲህ አሉ፦ "ወሏሂ! አሏህ በትንሳኤ ቀን ሐጀሩል አሥወድ ከሚያይበት ዓይኖች እና በሐቅ በሚነካው ላይ ለመመስከር ከሚናገርበት አንደበት ጋር ያስነሳዋል"።   عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فِي الْحَجَرِ ‏"‏ وَاللَّهِ لَيَبْعَثَنَّهُ اللَّهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ لَهُ عَيْنَانِ يُبْصِرُ بِهِمَا وَلِسَانٌ يَنْطِقُ بِهِ يَشْهَدُ عَلَى مَنِ اسْتَلَمَهُ بِحَقٍّ ‏"‏ ‏ አንድ የማይናገርን ግዑዝ ነገር አሏህ እንዲናገር ማድረግ ምንም አይሳነውም፥ ምክንያቱም አሏህ ከግዑዝ አፈር ሰውን ፈጥሮ እንዲናገር ማረጉ በራሱ የእርሱ ችሎታ ነው። እሩቅ ስንሄድ በባይብል ኢያሱ ታላቁን ድንጋይ ወስዶ በእግዚአብሔር መቅደስ አጠገብ ከነበረችው ከአድባሩ ዛፍ በታች አቆመው፥ ከዚያም ለሕዝቡ፦ "እነሆ፥ የተናገረንን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ "ሰምቶአልና" ይህ ድንጋይ ይመሰክርብናል፤ እንግዲህ አምላካችሁን እንዳትክዱ ይህ ምስክር ይሆንባችኋል" አላቸው፦ ኢያሱ 24፥26-27 ኢያሱም ይህን ቃል ሁሉ በእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ጻፈ፤ ታላቁንም ድንጋይ ወስዶ በእግዚአብሔር መቅደስ አጠገብ ከነበረችው ከአድባሩ ዛፍ በታች አቆመው። ኢያሱም ለሕዝቡ፦ እነሆ የተናገረንን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ "ሰምቶአልና" ይህ ድንጋይ ይመሰክርብናል፤ እንግዲህ አምላካችሁን እንዳትክዱ ይህ ምስክር ይሆንባችኋል" አላቸው። "ሰምቶአልና" የሚለው ቃል ይሰመርበት! ታላቁ ድንጋይ የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ የሚሰማበት ጆሮ አለውን? ሰምቶስ የሚመሰክርበት አንበት አለውን? ምን ያስደንቃል? ድንጋይም ከግንብ ውስጥ ይጮኻል እኮ፥ የሚያጅበው ድንጋይም ከግንብ ውስጥ ሲጮኽ እንጨትም ከውቅር ውስጥ ሰምቶ ይመልስለታል፦ ዕንባቆም 2፥11 ድንጋይም ከግንብ ውስጥ ይጮኻል፥ እንጨትም ከውቅር ውስጥ ይመልስለታል። የድንጋይ እና የእንጨት መናገር እና መስማት ለመቀበል ፍልስፍና ካላስፈለገ አሏህ በትንሳኤ ቀን ሐጀሩል አሥወድ ከሚያይበት ዓይኖች እና በሐቅ በሚነካው ላይ ለመመስከር ከሚናገርበት አንደበት መኖሩን ለመቀበል ፍልስፍና መስፈርት አይደለም። ምነው ድንዮች በሰው አንደበት፦ "ሆሣዕና በሰማይ ላለው አምላካችን፥ ሆሣዕና በእግዚአብሔር ስም ለመጣ መድኃኒታችን ምስጋና ይሁን" ብለውና እኮ፦ ተአምረ ማርያም ምዕራፍ 80 ቁጥር 24 "ድንዮች በሰው አንደበት፦ "ሆሣዕና በሰማይ ላለው አምላካችን፥ ሆሣዕና በእግዚአብሔር ስም ለመጣ መድኃኒታችን ምስጋና ይሁን" እያሉ ከደብረ ዘይት ተራራ ወደ ዮሳፍጥ በረሀ እየዘለሉ እና እየዘመሩ ተመለሱ"። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።  ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
نمایش همه...
ፍትሕ ለቢላል! እኔም ቢላል ነኝ።
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
03:18
Video unavailableShow in Telegram
አሥ ሠላም ዐለይኩም ያ ጀመዓህ! ወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር ይህንን የሃይማኖት ንጽጽር መተግበሪያ"application" ለሕዝበ ሙሥሊሙ አዘጋጅቷል። በገጠር አውታረ መረብ"network" የሌላቸው እና በከተማ የአውታረ መረብ ችግር ያለባቸው ያለ አውታረ መረብ ይህንን መተግበሪያ በማውረድ መጠቀም ይችላሉ። አውርደው በውስጡ ያለውን ርእሰ ጉዳይ እንዴት መጠቀም እንዳለብዎ እዚህ ላይ የተቀመጠውን ቪድዮ ይመልከቱ! ሁላችንም በፓስት፣ በኮሜት፣ በራሳችሁ የጊዜ መስመር"timeline" ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ መሆን ይችላሉ። ወጀዛኩሙላህ ኸይራ! Check out "Wahid Islamic Apologetics" https://play.google.com/store/apps/details?id=com.hexlabs.wahid.islamicapologetics
نمایش همه...
8.95 MB
በሽታ ከሰው ወደ ሰው እንደሚጋባ ሁሉ ጤንነትም ከሰው ወደ ሰው ይጋባል። ጤናማ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር መዋል ጤናማ አስተሳሰብ እንድንይዝ ያረገናል። ሰው የአስተሳሰብ እና የድርጊት ውጤት ነው። የአስተሳሰብ ውጤት ሰው ለራሱ እራሱ የሚሰጠው እና የሚነገረው ነገር ያ ማንነቱ ነው። ወሒድ ማለት ወሒድ ለወሒድ የነገረው ነገር ነው። ለራሴ እችላለው፣ እሞክራለው፣ እጎብዛለው ብዬ ካልኩት እችላለው፣ እሞክራለው፣ እጎብዛለው፥ በተቃራኒው ለራሴ አትችልም፣ አረባም፣ ደካማ ነኝ ካልኩት እራሴ የማይችል፣ የማይረባ እና ደካማ እሆናለው። የድርጊት ውጤት ሰው አስተዳደጉ እና አዋዋሉ በሕየወቱ ላይ አውንታዊ ሆነ አሉታዊ ተጽእኖ ማድረግ ይችላል። ልጆቻችንን በጥሩ አስተዳደግ ማሳደግ እና አዋዋላቸውን ማሳመር አለብን! ይህ ትውልድን የመቅረጽ መርሓ ግብር ለትውልድ የሚሆን መደላድል ነው። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
نمایش همه...
የቆስጠንጢኒያ ጉባኤ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 5፥75 የመርየም ልጅ አል መሢሕ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ ቆስጠንጢኖስ ከአባቱ ከንጉሥ ቊንስጣ እና ከእናቱ ከንግሥት እሌኒ 272 ድኅረ ልደት ተወልዶ በ306 ድኅረ ልደት የምዕራቡ የሮም ግዛት ንጉሠ ነገሥት ሆነ፥ በ313 ድኅረ ልደት ለክርስትና ሃይማኖት ዕውቅና የሰጠ ሲሆን በ 325 ደግሞ የኒቂያ ጉባኤ ሊቀ መንበር በመሆን መራ። ቆስጠንጢኖስ የፀሐይ አምልኮ አምላኪ ስለነበር እሑድን የፀሐይ ቀን"sun day" በማድረግ ሰንበትን ከሰባተኛው ቀን ወደ መጀመርያው ቀን አሸጋገረ፥ ይህ ንጉሠ ነገሥት መስቀልን የጦር ሠራዊቱ ዓርማ አድርጎ ይጠቀምበት ጀመር። ቆስጠንጢኖስ ክርስትናን የተቀበለው ቀደም ሲል ቢሆንም የተጠመቀው ግን ሊሞት ገደማ ነው፥ እርሱ ቱርክ የምትገኘውን ከተማ በ 330 ድኅረ ልደት "ቆስጠንጢኒያ" በማለት ከቆረቆረ በኃላ በ 337 ድኅረ ልደት ሞቷል። ከቆስጠንጢኖስ ሞት በኃላ በ381 ድኅረ ልደት በንጉሥ ቀዳማይ ቴዎዶስዮስ ሊቀ መንበርነት የቆስጠንጢኒያ ጉባኤ ላይ 150 ኤጲጵ ቆጶሳት ከመላው ዓለም ተሰብስበው የሎዶቂያው ኤጲስ ቆጶስ አቡሊናርዮስ እና የቆስጠንጢኒያ ኤጲስ ቆጶስ መቅደንዮስ ያነሱትን ሙግት ለመታደም መጡ። ፨አቡሊናርዮስ፦ "ኢየሱስ ሥጋ እንጂ ነፍስ የለውም፥ በነፍስ ፋንታ መለኮት ተተክቷል። አብ እና ወልድ በውጫዊ ግብር"outward function" ወይም በምጣኔ ግብር"economic function" ይለያያሉ፥ አብ ላኪ ወልድ ተላኪ በመሆን የተለያየ የሥራ ድርሻ አላቸው" በማለት ሙግቱን አቀረበ። ፨መቅደንዮስ፦ "መንፈስ ቅዱስ የአምላክ እስትንፋስ እና ኃይል እንጂ እራሱን የቻለ አካል እና አምላክ አይደለም" በማለት ሙግቱን አቀረበ። ጉባኤው "ኢየሱስ እራሱ የቻለ የሰው ነፍስ አለው" በማለት እና "አብ እና ወልድ በውጫዊ ግብር አንድ ግብር እና ፈቃድ አላቸው" በማለት አቡሊናርዮስን አወገዙት። እንዲሁ፦ "መንፈስ ቅዱስ እራሱ የቻለ አካል እና አምላክ ነው" በማለት መቅደንዮስን አወገዙት። "መንፈስ ቅዱስ "ሆ ቴዎስ ሆ ኑማ ቶ ሐጊዎን" Ο Θεός ο Πνεῦμα τὸ Ἅγιον ማለትም "እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ"God the Holy Spirit" በማለት አጸደቁ፥ በተጨማሪም ኢየሱስን፦ "ቶን ኤክ ቶዩ ፓትሮስ ጌኒቴንታ ፕሮ ፓንቶን ቶን ኣይኦኖን τὸν ἐκ τοῦ Πατρὸς γεννηθέντα πρὸ πάντων τῶν αἰώνων ማለትም "ከአብ ከዘመናት በፊት የተወለደ" ወይም በአገራችን "ዓለም ሳይፈጠር እና ዘመን ሳይቆጠ ከአብ ያለ እናት ተወለደ" በማለት የአቋም መግለጫ ተሰጠ። ከዚህ ጉባኤ ተነስተን ጥያቄ እናጭራለን፦ ፨በቆስጠንጢኒያ ጉባኤ አንድ መለኮት የአብ ገንዘብ ሲሆን ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ከእርሱ ይጋራሉ ማለት ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ከአብ ውጪ ከሆኑ ሌላ መለኮት አይሰኙምን? ፨አንዱ አምላክስ አምላክነትን ከእርሱ ሌላ ያጋራልን? ፨በውጫዊ ግብር አብ እና ወልድ የየራሳቸው የሥራ ድርሻ ከሌላቸው እና በውጫዊ ግብር አንድ ግብር ካላቸው ወልድ ሲላክ አብም ተልኳልን? ወልድ ሲወለድ አብ ተወልዷልን? ፨እንደ እናንተ ትምህርት በብሉይ ወልድ መልአክ እየሆነ ሲላክ ወይም መንፈስ ቅዱስ ሲላክ አብም ተልኳልን? ፨ዓለም ሳይፈጠር የተወለደው የአብ ልጅ ለማርያም የባሕርይ ልጇን ነውን? ከእርሷ ተገኝቷልን? የማርያም ልጅ ፍጡሩ ለአብ የባሕርይ ልጁ ነውን? ያ ፍጡር ከአብ ተገኝቷልን? የ 325 የኒቂያ ጉባኤ "ኢየሱስ ከአምላክ የተገኘ አምላክ ነው" የሚለው ትምህርት አቡሊናርዮስ፦ "ኢየሱስ ሥጋ እንጂ ነፍስ የለውም፥ በነፍስ ፋንታ መለኮት ተተክቷል" የሚለውን ውሳኔ ገፋፍቶታል። "ኢየሱስ ሙሉ ሰው ነው" የሚለው ደግሞ ንስጥሮስ ላይ ተጽዕኖ አርጎበታል፥ በኤፌሶን ጉባኤ ኢንሻላህ እናያዋለን። የመርየም ልጅ አልመሢሕ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፦ 5፥75 የመርየም ልጅ አል መሢሕ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ ክርስቲያኖች ሆይ! ከዚህ ውስብስብ ትምህርት ወጥታችሁ በአንድነት ላይ ሁለትነት፣ መከፋፈል፣ መባዛት የሌለበትን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩት ጥሪያችን ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
نمایش همه...
ጉባኤው የማታ ማታ ኢየሱስ "ቴዎን ኤክ ቴዉ" Θεὸν ἐκ Θεοῦ ማለትም "ከአምላክ የተገኘ አምላክ ነው" በማለት አጸደቀ፥ "አምላክ አምላክን አህሎ እና መስሎ፣ ከባሕርይ ባሕርይ ወስዶ፣ ከአካል አካል ወስዶ ተወለደ" በማለት "ሆ ቴዎስ ሆ ሁዎስ" Ο Θεός ο γιος ማለትም "እግዚአብሔር ወልድ"God the Son" የሚል የአቋም መግለጫ ተሰጠ። ከዚህ ጉባኤ ተነስተን ጥያቄ እናጭራለን፦ ፨በኒቂያ ጉባኤ ድንጋጌ ላይ አምላክ አምላክን ከወለደ ሁለት አምላክ አይሆንም? ፨አምላክ አምላክን አስገኘ የሚለው ትምህርት ሕሊናስ ይቀበለዋልን? ፨ማስገኘት መንስኤ መገኘት ውጤት ከሆነ መቀዳደም ስላለ ጅማሮ እና መነሾ ያለው አምላክ ምን ዓይነት አምላክ ነው? ይህ የነገረ ክርስቶስ"Christology" ውዝግብ ጠመዝማዛ መንገዱ የጀመረው ከዚህ ጉባኤ ጀምሮ ነው። አንብሮስ ዘሚለን "አብ የወልድ ኑባሬ ምንጭ እና ሥር ነው"ይለናል፦ "አብ የወልድ ኑባሬ ምንጭ እና ሥር ነው" Exposition of the Christian Faith (Ambrose) > Book IV(4) Chapter 10 Number 133 አብ አስገኚ ወልድ ግኝት ከሆነ በመስኤ እና በውጤት በመካከላቸው መቀዳደም አለ፥ ዛሬ ላይ ዐበይት ክርስቲያኖች፦ "ወልድ ከአብ ባሕርይ ባሕርይን ወስዶ፣ ከአካሉ አካልን ወስዶ እና አብን አህሎና መስሎ ከእርሱ ወጣ፣ ተወለደ፣ ተገኘ" በማለት አሏህን ወላዲ መሢሑን ተወላዲ በማድረግ ለአሏህ ቁራጭን አደረጉለት፦ 43፥15 ከባሮቹም ለእርሱ ቁራጭን ልጅ አደረጉለት፡፡ ሰው በእርግጥ ግልጽ ከሓዲ ነው፡፡ وَجَعَلُوا لَهُ مِنْ عِبَادِهِ جُزْءًا ۚ إِنَّ الْإِنسَانَ لَكَفُورٌ مُّبِينٌ ከአንዱ አምላህ ባሕርይ ባሕርይን ወስዶ፣ ከአካሉ አካልን ወስዶ፣ እርሱን አህሎና መስሎ ከእርሱ ወጣ፣ ተወለደ፣ ተገኘ ማለት የአምላክን አንድነት ክፉኛ የሚያናጋ ትምህርት ነው። በዚህ ውዝግብ ጊዜ አምላካችን አሏህ እነዚያን «አሏህ ልጅን ወልዷል» ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት ቁርኣንን አወረደው፦ 18፥4 እነዚያንም «አሏህ ልጅን ወልዷል» ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا አምላካችን አሏህ አንድ ነው፥ እርሱ የሁሉ መጠጊያ ነው። አምላክ ከወለደ ይባዛል፥ ከተወለደ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ይወሰናል፣ ያድጋል፣ ይሞታል። አሏህ ግን አንድ ነውና አልወለደም አልተወለደምም፦ 112፥1 በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ 112፥2 «አሏህ የሁሉ መጠጊያ ነው»፡፡ اللَّهُ الصَّمَدُ 112፥3 «አልወለደም አልተወለደምም»፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ አሏህ መውለድ መወለድ የሚባል ባሕርይ ስለሌለው ብጤ፣ አምሳያ፣ ተፎካካሪ፣ እኩያ፣ ወደር፣ እኩያ አንድም የለውም፦ 114፥4 «ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም»። وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ "ኩፉው" كُفُو ማለት "ወደር" "እኩያ" "አቻ" "ብጤ" "አምሳያ" "ተፎካካሪ" "ባላንጣ" ማለት ሲሆን እርሱ የሚተካከለው አቻ እና እኩያ እንዲሁ የሚመሳሰለው አምሳያ እና ቢጤ ከሌለው «አሏህ ወለደ» ያሉት እነርሱ በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፦ 37፥152 «አሏህ ወለደ» አሉ፥ እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡ وَلَدَ اللَّهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ ክርስቲያኖች ሆይ! ከዚህ ውስብስብ ትምህርት ወጥታችሁ በአንድነት ላይ ሁለትነት፣ መከፋፈል፣ መባዛት የሌለበትን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩት ጥሪያችን ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.