cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

Більше
Рекламні дописи
35 616
Підписники
+3624 години
+1917 днів
+50830 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

03:18
Відео недоступнеДивитись в Telegram
አሥ ሠላም ዐለይኩም ያ ጀመዓህ! ወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር ይህንን የሃይማኖት ንጽጽር መተግበሪያ"application" ለሕዝበ ሙሥሊሙ አዘጋጅቷል። በገጠር አውታረ መረብ"network" የሌላቸው እና በከተማ የአውታረ መረብ ችግር ያለባቸው ያለ አውታረ መረብ ይህንን መተግበሪያ በማውረድ መጠቀም ይችላሉ። አውርደው በውስጡ ያለውን ርእሰ ጉዳይ እንዴት መጠቀም እንዳለብዎ እዚህ ላይ የተቀመጠውን ቪድዮ ይመልከቱ! ሁላችንም በፓስት፣ በኮሜት፣ በራሳችሁ የጊዜ መስመር"timeline" ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ መሆን ይችላሉ። ወጀዛኩሙላህ ኸይራ! Check out "Wahid Islamic Apologetics" https://play.google.com/store/apps/details?id=com.hexlabs.wahid.islamicapologetics
Показати все...
8.95 MB
በሽታ ከሰው ወደ ሰው እንደሚጋባ ሁሉ ጤንነትም ከሰው ወደ ሰው ይጋባል። ጤናማ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር መዋል ጤናማ አስተሳሰብ እንድንይዝ ያረገናል። ሰው የአስተሳሰብ እና የድርጊት ውጤት ነው። የአስተሳሰብ ውጤት ሰው ለራሱ እራሱ የሚሰጠው እና የሚነገረው ነገር ያ ማንነቱ ነው። ወሒድ ማለት ወሒድ ለወሒድ የነገረው ነገር ነው። ለራሴ እችላለው፣ እሞክራለው፣ እጎብዛለው ብዬ ካልኩት እችላለው፣ እሞክራለው፣ እጎብዛለው፥ በተቃራኒው ለራሴ አትችልም፣ አረባም፣ ደካማ ነኝ ካልኩት እራሴ የማይችል፣ የማይረባ እና ደካማ እሆናለው። የድርጊት ውጤት ሰው አስተዳደጉ እና አዋዋሉ በሕየወቱ ላይ አውንታዊ ሆነ አሉታዊ ተጽእኖ ማድረግ ይችላል። ልጆቻችንን በጥሩ አስተዳደግ ማሳደግ እና አዋዋላቸውን ማሳመር አለብን! ይህ ትውልድን የመቅረጽ መርሓ ግብር ለትውልድ የሚሆን መደላድል ነው። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የቆስጠንጢኒያ ጉባኤ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 5፥75 የመርየም ልጅ አል መሢሕ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ ቆስጠንጢኖስ ከአባቱ ከንጉሥ ቊንስጣ እና ከእናቱ ከንግሥት እሌኒ 272 ድኅረ ልደት ተወልዶ በ306 ድኅረ ልደት የምዕራቡ የሮም ግዛት ንጉሠ ነገሥት ሆነ፥ በ313 ድኅረ ልደት ለክርስትና ሃይማኖት ዕውቅና የሰጠ ሲሆን በ 325 ደግሞ የኒቂያ ጉባኤ ሊቀ መንበር በመሆን መራ። ቆስጠንጢኖስ የፀሐይ አምልኮ አምላኪ ስለነበር እሑድን የፀሐይ ቀን"sun day" በማድረግ ሰንበትን ከሰባተኛው ቀን ወደ መጀመርያው ቀን አሸጋገረ፥ ይህ ንጉሠ ነገሥት መስቀልን የጦር ሠራዊቱ ዓርማ አድርጎ ይጠቀምበት ጀመር። ቆስጠንጢኖስ ክርስትናን የተቀበለው ቀደም ሲል ቢሆንም የተጠመቀው ግን ሊሞት ገደማ ነው፥ እርሱ ቱርክ የምትገኘውን ከተማ በ 330 ድኅረ ልደት "ቆስጠንጢኒያ" በማለት ከቆረቆረ በኃላ በ 337 ድኅረ ልደት ሞቷል። ከቆስጠንጢኖስ ሞት በኃላ በ381 ድኅረ ልደት በንጉሥ ቀዳማይ ቴዎዶስዮስ ሊቀ መንበርነት የቆስጠንጢኒያ ጉባኤ ላይ 150 ኤጲጵ ቆጶሳት ከመላው ዓለም ተሰብስበው የሎዶቂያው ኤጲስ ቆጶስ አቡሊናርዮስ እና የቆስጠንጢኒያ ኤጲስ ቆጶስ መቅደንዮስ ያነሱትን ሙግት ለመታደም መጡ። ፨አቡሊናርዮስ፦ "ኢየሱስ ሥጋ እንጂ ነፍስ የለውም፥ በነፍስ ፋንታ መለኮት ተተክቷል። አብ እና ወልድ በውጫዊ ግብር"outward function" ወይም በምጣኔ ግብር"economic function" ይለያያሉ፥ አብ ላኪ ወልድ ተላኪ በመሆን የተለያየ የሥራ ድርሻ አላቸው" በማለት ሙግቱን አቀረበ። ፨መቅደንዮስ፦ "መንፈስ ቅዱስ የአምላክ እስትንፋስ እና ኃይል እንጂ እራሱን የቻለ አካል እና አምላክ አይደለም" በማለት ሙግቱን አቀረበ። ጉባኤው "ኢየሱስ እራሱ የቻለ የሰው ነፍስ አለው" በማለት እና "አብ እና ወልድ በውጫዊ ግብር አንድ ግብር እና ፈቃድ አላቸው" በማለት አቡሊናርዮስን አወገዙት። እንዲሁ፦ "መንፈስ ቅዱስ እራሱ የቻለ አካል እና አምላክ ነው" በማለት መቅደንዮስን አወገዙት። "መንፈስ ቅዱስ "ሆ ቴዎስ ሆ ኑማ ቶ ሐጊዎን" Ο Θεός ο Πνεῦμα τὸ Ἅγιον ማለትም "እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ"God the Holy Spirit" በማለት አጸደቁ፥ በተጨማሪም ኢየሱስን፦ "ቶን ኤክ ቶዩ ፓትሮስ ጌኒቴንታ ፕሮ ፓንቶን ቶን ኣይኦኖን τὸν ἐκ τοῦ Πατρὸς γεννηθέντα πρὸ πάντων τῶν αἰώνων ማለትም "ከአብ ከዘመናት በፊት የተወለደ" ወይም በአገራችን "ዓለም ሳይፈጠር እና ዘመን ሳይቆጠ ከአብ ያለ እናት ተወለደ" በማለት የአቋም መግለጫ ተሰጠ። ከዚህ ጉባኤ ተነስተን ጥያቄ እናጭራለን፦ ፨በቆስጠንጢኒያ ጉባኤ አንድ መለኮት የአብ ገንዘብ ሲሆን ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ከእርሱ ይጋራሉ ማለት ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ከአብ ውጪ ከሆኑ ሌላ መለኮት አይሰኙምን? ፨አንዱ አምላክስ አምላክነትን ከእርሱ ሌላ ያጋራልን? ፨በውጫዊ ግብር አብ እና ወልድ የየራሳቸው የሥራ ድርሻ ከሌላቸው እና በውጫዊ ግብር አንድ ግብር ካላቸው ወልድ ሲላክ አብም ተልኳልን? ወልድ ሲወለድ አብ ተወልዷልን? ፨እንደ እናንተ ትምህርት በብሉይ ወልድ መልአክ እየሆነ ሲላክ ወይም መንፈስ ቅዱስ ሲላክ አብም ተልኳልን? ፨ዓለም ሳይፈጠር የተወለደው የአብ ልጅ ለማርያም የባሕርይ ልጇን ነውን? ከእርሷ ተገኝቷልን? የማርያም ልጅ ፍጡሩ ለአብ የባሕርይ ልጁ ነውን? ያ ፍጡር ከአብ ተገኝቷልን? የ 325 የኒቂያ ጉባኤ "ኢየሱስ ከአምላክ የተገኘ አምላክ ነው" የሚለው ትምህርት አቡሊናርዮስ፦ "ኢየሱስ ሥጋ እንጂ ነፍስ የለውም፥ በነፍስ ፋንታ መለኮት ተተክቷል" የሚለውን ውሳኔ ገፋፍቶታል። "ኢየሱስ ሙሉ ሰው ነው" የሚለው ደግሞ ንስጥሮስ ላይ ተጽዕኖ አርጎበታል፥ በኤፌሶን ጉባኤ ኢንሻላህ እናያዋለን። የመርየም ልጅ አልመሢሕ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፦ 5፥75 የመርየም ልጅ አል መሢሕ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ ክርስቲያኖች ሆይ! ከዚህ ውስብስብ ትምህርት ወጥታችሁ በአንድነት ላይ ሁለትነት፣ መከፋፈል፣ መባዛት የሌለበትን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩት ጥሪያችን ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Показати все...
ጉባኤው የማታ ማታ ኢየሱስ "ቴዎን ኤክ ቴዉ" Θεὸν ἐκ Θεοῦ ማለትም "ከአምላክ የተገኘ አምላክ ነው" በማለት አጸደቀ፥ "አምላክ አምላክን አህሎ እና መስሎ፣ ከባሕርይ ባሕርይ ወስዶ፣ ከአካል አካል ወስዶ ተወለደ" በማለት "ሆ ቴዎስ ሆ ሁዎስ" Ο Θεός ο γιος ማለትም "እግዚአብሔር ወልድ"God the Son" የሚል የአቋም መግለጫ ተሰጠ። ከዚህ ጉባኤ ተነስተን ጥያቄ እናጭራለን፦ ፨በኒቂያ ጉባኤ ድንጋጌ ላይ አምላክ አምላክን ከወለደ ሁለት አምላክ አይሆንም? ፨አምላክ አምላክን አስገኘ የሚለው ትምህርት ሕሊናስ ይቀበለዋልን? ፨ማስገኘት መንስኤ መገኘት ውጤት ከሆነ መቀዳደም ስላለ ጅማሮ እና መነሾ ያለው አምላክ ምን ዓይነት አምላክ ነው? ይህ የነገረ ክርስቶስ"Christology" ውዝግብ ጠመዝማዛ መንገዱ የጀመረው ከዚህ ጉባኤ ጀምሮ ነው። አንብሮስ ዘሚለን "አብ የወልድ ኑባሬ ምንጭ እና ሥር ነው"ይለናል፦ "አብ የወልድ ኑባሬ ምንጭ እና ሥር ነው" Exposition of the Christian Faith (Ambrose) > Book IV(4) Chapter 10 Number 133 አብ አስገኚ ወልድ ግኝት ከሆነ በመስኤ እና በውጤት በመካከላቸው መቀዳደም አለ፥ ዛሬ ላይ ዐበይት ክርስቲያኖች፦ "ወልድ ከአብ ባሕርይ ባሕርይን ወስዶ፣ ከአካሉ አካልን ወስዶ እና አብን አህሎና መስሎ ከእርሱ ወጣ፣ ተወለደ፣ ተገኘ" በማለት አሏህን ወላዲ መሢሑን ተወላዲ በማድረግ ለአሏህ ቁራጭን አደረጉለት፦ 43፥15 ከባሮቹም ለእርሱ ቁራጭን ልጅ አደረጉለት፡፡ ሰው በእርግጥ ግልጽ ከሓዲ ነው፡፡ وَجَعَلُوا لَهُ مِنْ عِبَادِهِ جُزْءًا ۚ إِنَّ الْإِنسَانَ لَكَفُورٌ مُّبِينٌ ከአንዱ አምላህ ባሕርይ ባሕርይን ወስዶ፣ ከአካሉ አካልን ወስዶ፣ እርሱን አህሎና መስሎ ከእርሱ ወጣ፣ ተወለደ፣ ተገኘ ማለት የአምላክን አንድነት ክፉኛ የሚያናጋ ትምህርት ነው። በዚህ ውዝግብ ጊዜ አምላካችን አሏህ እነዚያን «አሏህ ልጅን ወልዷል» ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት ቁርኣንን አወረደው፦ 18፥4 እነዚያንም «አሏህ ልጅን ወልዷል» ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا አምላካችን አሏህ አንድ ነው፥ እርሱ የሁሉ መጠጊያ ነው። አምላክ ከወለደ ይባዛል፥ ከተወለደ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ይወሰናል፣ ያድጋል፣ ይሞታል። አሏህ ግን አንድ ነውና አልወለደም አልተወለደምም፦ 112፥1 በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ 112፥2 «አሏህ የሁሉ መጠጊያ ነው»፡፡ اللَّهُ الصَّمَدُ 112፥3 «አልወለደም አልተወለደምም»፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ አሏህ መውለድ መወለድ የሚባል ባሕርይ ስለሌለው ብጤ፣ አምሳያ፣ ተፎካካሪ፣ እኩያ፣ ወደር፣ እኩያ አንድም የለውም፦ 114፥4 «ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም»። وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ "ኩፉው" كُفُو ማለት "ወደር" "እኩያ" "አቻ" "ብጤ" "አምሳያ" "ተፎካካሪ" "ባላንጣ" ማለት ሲሆን እርሱ የሚተካከለው አቻ እና እኩያ እንዲሁ የሚመሳሰለው አምሳያ እና ቢጤ ከሌለው «አሏህ ወለደ» ያሉት እነርሱ በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፦ 37፥152 «አሏህ ወለደ» አሉ፥ እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡ وَلَدَ اللَّهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ ክርስቲያኖች ሆይ! ከዚህ ውስብስብ ትምህርት ወጥታችሁ በአንድነት ላይ ሁለትነት፣ መከፋፈል፣ መባዛት የሌለበትን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩት ጥሪያችን ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Показати все...
የኒቂያ ጉባኤ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 112፥3 «አልወለደም አልተወለደምም»፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ ጥንት ላይ የነበሩ ነቢያት እንዲሁ ኢየሱስ እና ሐዋርያት አሓዳዊያን"Unitarian" የነበሩ ሲሆን ከሐዋርያት ኅልፈት በኃላ የተነሱ የቤተክርስቲያን አበው ደግሞ በሂደት "ክልዔታውያን"Binitarian" ነበሩ። ከክልዔታውያን አበው መካከል ጠርጡሊያኖስ"Tertullian" ስለ ወልድ ሲናገር እንዲህ ይለናል፦ "አብ አጠቃላይ ባሕርይ ነው፥ ነገር ግን ወልድ የአጠቃላዩ መገኘት እና ክፍል ነው" (Against Praxeas (Tertullian), Chapter 9). አንድ ሰው ሰውነቱ ከራሱ ጋር ኖሮ ኖሮ ልክ ሲወልድ አባት እንደሚባለው አንድ አምላክ አምላክነቱ ከራሱ ጋር ኖሮ ኖሮ ልክ ሲወልድ አብ ተባለ የሚል ትምህርት ያስተማረው ጠርጡሊያኖስ ዘካርቴጅ ነው፦ "ምክንያቱም አምላክ እንዲሁ አብ ነው፥ እንዲሁ ደግሞ እርሱ ፈራጅ ነው። ሁልጊዜም አምላክ በሆነው መሠረት ላይ ብቻ እርሱ ግን ሁልጊዜ አብ እና ፈራጅ አልነበረም፥ ከወልድ በፊት አብ ሊሆን አይችልም፤ እንዲሁ ከኃጢአት በፊት ፈራጅ ሊሆን አይችልም። ነገር ግን በእርሱ ዘንድ ኃጢአት ባልነበረበት እና እንዲሁ ወልድ ባልነበረበት ወቅት ጊዜ ነበር፥ የመጀመሪያው ጌታ ፈራጅ ሆኖ እና የኃለኛ አብ ሆኖ መመሥረት ነበር። በዚህ መንገድ እርሱ ጌታ ሊሆን ከነበረባቸው ነገሮች በፊት ጌታ አልነበረም፥ ነገር ግን እርሱ ግን ወደፊት በሆነ ጊዜ ብቻ ጌታ ሊሆን ነበር። ልክ እንደዚሁ እርሱ በወልድ አብ እንደ ሆነ በኃጢአትም ፈራጅ ሆነ። Against Hermogenes (Tertullian) chapter 3 ተመልከቱ! አብ ያለ አባትነት ከፍጥረት በፊት ወልድን እስከሚወልድበት ጊዜ ብቻውን በአምላክነት ነበር የሚለው እሳቤ የጠርጡሊያኖስ እሳቤ ነው፦ "ከፍጥረት በፊት እስከ ወልድ ውልደት ነበረ፥ ከሁሉ ነገር በፊት አምላክ ብቻውን ነበረ"። Against Praxeas (Tertullian) Chapter 5. በዚህ ወቅት የትርጓሜ ትምህርት ቤት"School of Thought" በእስክንድሪያ እና በአንጾኪያ ነበር፥ የእስክንድሪያን ትምህርት ቤት በአፍላጦን"Plato" ፍልስፍና ሰርጎገብ መሠረት ያረገ ሲሆን የአንጾኪያው ትምህርት ቤት ደግሞ በአሪስጣጣሊስ"Aristotle" ፍልስፍና መሠረት ያረገ ነው። በእስክንድሪያ ትምህርት ቤት ይማር የነበረው አትናቴዎስ ዘእስክንድሪያ "ከአምላክ አምላክ ተወለደ" የሚል አቋም ሲኖረው በአንጾኪያ ትምህርት ቤት ይማር የነበረው አርዮስ ዘሊቢያ "ከአምላክ አምላክ ተፈጠረ" የሚል አቋም ነበረው፥ አርዮስ ዘሊቢያ ስለ አቋሙ እንዲህ ይለናል፦ "አብ ወልድን ከወለደው የተወለደው መጀመሪያ ነበረው፥ ከዚህም ክስተት የተነሳ ልጁ ያልነበረበት ጊዜ እንደ ነበረ ግልጥ ነው። ስለዚህም እርሱ [ወልድ] ምንነቱ ካለመኖር እንደ ነበረው ነው"። (Socrates of Constantinople, Church History, Book I, Ch. 5.) በሁለቱ ውዝግብ የመጀመሪያው ዓለም ዓቀፍ ሲኖዶስ በኒቂያ ተካሄደ፥ "ሲኖዶስ" σύνοδος ማለት "ጉባኤ" "ስብሰባ"council" ማለት ነው። ኒቂያ፣ ቆስጠንጢኒያ፣ ኤፌሶን እና ኬልቄዶን በጥንት ጊዜ ቱርክ ውስጥ የሚገኙ ከተሞች ናቸው። በ325 ድኅረ ልደት በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት የኒቂያ ጉባኤ ላይ 318 ኤጲጵ ቆጶሳት ከመላው ዓለም ተሰብስበው "ሆሙኡሲዮስ" እና "ሆሞኡሲዮስ" የሚባሉ ክርክሮችን ለመታደም መጡ፥ "ሆሙኡሲዮስ" ὅμοιοιούσιος የአርዮስ አቋም ሲሆን "ሆሞኡሲዮስ" ὁμόιοιούσιος ደግሞ የአትናቴዎስ አቋም ነው። "ኡሲያ" οὐσία የሚለው ቃል "ኤይሚ" εἰμί ማለትም "ነኝ" ከሚል አያያዥ ግሥ የተገኘ ሲሆን "ህላዌ" "ሃልዎት" "ኑባሬ" የሚል ትርጉም አለው፥ "ሆሙስ" ὅμοιος ማለት "የተለያየ" ማለት ሲሆን "ሆሞስ" ὁμός ማለት ደግሞ "ተመሳሳይ" ማለት ነው። ፨አርዮስ፦ "ወልድ ፍጡር ነው፥ አንዱ አምላክ አብ እና ኢየሱስ "ሆሙኡሲዮስ" ὅμοιοιούσιος ማለትም "የተለያየ ህላዌ" እንጂ ተመሳሳይ አይደለም" በማለት ኢየሱስ "ሆሙኡሲዮን ቶ ፓትሪ" ὅμοούσιον τῷ Πατρί ማለት "ከአብ ጋር የተለያየ ህላዌ ነው" የሚል አቋም ነበረው። ፨አትናቴዎስ፦ "ወልድ ፍጡር አይደለም፥ አንዱ አምላክ አብ እና ኢየሱስ "ሆሞኡሲዮስ" ὁμόιοιούσιος ማለትም "ተመሳሳይ ህላዌ" እንጂ የተለያየ አይደለም" በማለት ኢየሱስ "ሆሞኡሲዮን ቶ ፓትሪ" ὁμόούσιον τῷ Πατρί ማለት "ከአብ ጋር ተመሳሳይ ህላዌ ነው" የሚል አቋም ነበረው።
Показати все...
የሃይማኖት ንጽጽር ኮርስ በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society" 13ኛ ዙር የሙቃረናህ ደርሥ! "ሙቃረናህ" مُقَارَنَة የሚለው ቃል "ቃረነ" قَارَنَ ማለትም "አነጻጸረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንጽጽር" ማለት ነው፥ ሙቃረናህ የሃይማኖት ንጽጽር"Comparative Religion" ሲሆን በዱኑል ኢሥላም እና እና በክርስትና መካከል ያለው የሥነ መለኮት አንድነት እና ልዩነት እየተነጻጸረ የሚቀርብበት ጥናት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 7 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሁለት ተርም አለው። ፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ አሳብ በፈጣሪ እሳቦት ላይ የሚያውጠነጥነው፦ 1.በነገረ ሥላሴ ጥናት"Triadogy" 2.በነገረ ክርስቶስ ጥናት"Christology" 3.በነገረ ማርያም ጥናት"Mariology" 4. በነገረ መላእክት ጥናት"angelology" 5. በነገረ ምስል ጥናት"Iconlogy" ላይ ነው። ፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በቅዱሳን መጽሐፍት ላይ የሚያውጠነጥነው፦ 1.በአህሉል ኪታብ"People of the Book" 2.በመጽሐፍት"scriptures" 3. በመጽሐፍ አጠባበቅ"preservation" 4.በመጽሐፍት ልኬት"Standardization" 5. በባይብል ግጭት"Contradiction" 6. በኦሪት"Torah" 7. በወንጌል"Gospel" ላይ ነው። አባሪ ኮርሶች፦ 1. ዐቂዳህ"creed" 2. ሥነ ምግባር"ethics" 3. ሥነ አመክንዮ"logic" 4. ሥነ ልቦና"psychology" 5. ሥነ ቋንቋ"linguistics" ናቸው። ለመመዝገብ ከታች የተዘረዘሩት አድሚናት በውስጥ ያናግሩ! ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://t.me/arhmanu እኅት ሰላም፦ http://t.me/SeuweSe አኅት ዘሃራ፦ https://t.me/Zhara_mustefa እኅት አበባ፦ http://t.me/selemtewa ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ! ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!
Показати все...
ተአምረ ማርያም የዘወትር መቅድም ቁጥር 35-36 ገጽ 7 ግዕዙ፦ "ወቅድመ ስዕላ ስግዱ! ዘኢሰገደ ላቲ ይደምስስ እምቅዋሙ ወኢይትዐወቅ ዝግረ ስሙ። ወይበሉ መላእክተ ሰማይ ኲሎሙ አሜን"። ትርጉም፦ "በስዕሏ ፊት ስገዱ! ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ! ስም አጠራሩ አይታወቅ። በሰማይ ያሉ መላእክትም ይደረግ ይሁን ይበሉ"። "በስዕሏ ፊት ስገዱ! ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ" የሚል እያለ "እኛ ለስዕል አንሰግድም" ብሎ ማቄሉን እዛው የማያነቡትን ያቂል! በኦርቶዶክስ መምህራን "እኛ ለስዕል አንሰግድም" የሚል እንዲህ ዓይነት ለውጥ እንዴት ሊመጣ ቻለ? ሲባል መልሱ የሙሴ አምላክ ለሙሴ፦ "የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ፣ የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፣ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም” ብሎ አዞልታ፤ እንደውም መዝሙረኛው፦ "ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ይፈሩ" ስለሚል ነው፦ ዘሌዋውያን 26፥1 እኔ ያህዌህ አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ ”ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ”፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ። ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር ”የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም”*፤ መዝሙር 97፥7 ”ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ፤ መላእክቱ ሁሉ ስገዱለት። ሰው ለሠራው የእጅ ሥራ እንዴት ይሰገዳል? በኦርቶዶክስ፣ በካቶሊክ እና በአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለስዕል የጸጋ ስግደት ይሰገዳል፤ ልብ አድርግ የጸጋ ስግደት ስገዱ የሚል ትእዛዝ የለም። በተቃራኒው ለተቀረጸ ምስል "አትስገድላቸው" የሚል ትእዛዝ ቢኖር እንጂ። ይህንን አስፈሪ ወንጀል እያየ ወደ ክርስትና የሚገባ ሰው ቂል ካልሆነ ወይም በጥቅማ ጥቅም አሊያም በተቃራኒ ፆታ ፍቅር መነደፍ ካልሆነ በስተቀር አይሞክረውም። ይህንን ፍርድ እያወቀ ወደ ኢሥላም የማይመጣ በእሳት የሚጫወት ነው፦ 41፥37 ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ “አትስገዱ”፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአሏህ “ስገዱ” ፡፡ እርሱን ብቻ “የምታመልኩ” እንደ ኾናችሁ ”ለሌላ አትስገዱ”፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُون " እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! በኢሥላም ፈጣሪ ከሆነው ከአንዱ አምላክ ከአሏህ ውጪ የሚሰገድለት ማንነት ሆነ ምንነት የለም። ስዕል የሰው እጅ ሥራ ነው፤ ለዚህ ግዑዝ ነገር የምትሰግዱ ካላችሁ ጊዜው ሳይረፍድ ወደ አሏህ በንስሓ ተመለሱ! ከአሏህ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱምና፦ 7፥197 እነዚያም ከእርሱ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱም። وَٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَسْتَطِيعُونَ نَصْرَكُمْ وَلَآ أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Показати все...
ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

00:16
Відео недоступнеДивитись в Telegram
ለስዕል አትሰግዱምን? በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 41፥37 ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ “አትስገዱ”፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአሏህ “ስገዱ” ፡፡ እርሱን ብቻ “የምታመልኩ” እንደ ኾናችሁ ”ለሌላ አትስገዱ”፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُون በግሪክ "ኢኮን" εἰκών በዕብራይስጥ “ኤሊል” אֱלִיל ማለት "ስዕል"image" ማለት ሲሆን በሰሌዳ ላይ በቀለም፣ በጠመኔ፣ በእርሳስ አለዚያም በሌላ ነገር ተስርቶ በዓይን በማየት የሚገነዘቡት የአንድ ማንነት ወይም ምንነት ምስል ነው። አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ላይ ሥዕልን እንዲህ ይገልጹታል፦ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግሥ ወመዝገበ ቃላት 673 "ስዕል ማለት በቁም መልክ፣ የመልክ ጥላ፣ ንድፍ፣ አምሳል፣ ንድፍ በውኃ፣ በመጽሔት፣ በጥልፍ፣ በስፌት ወይም በቀለም በወረቀት ገዝፎ ተጽፎ ከደብር፣ ከእብን፣ ከእጽ፣ ከማዕድን ታንጦ፣ ተቀርጦ፣ ተሸልሞ፣ አጊጦ የሚታይ የሚዳሰስ ነገር ነው፡፡" ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ በአንድ ትምህርቱ ላይ ዓይኑን በጨው አጥቦ "እኛ ለስዕል አንሰግድም" ብሎ ሽምጥጥ አርጎ ክዷል፥ በተግባር ለስዕል እየሰገዱ እና በትምህርታቸው ውስጥ ለስዕል መሰገድ እንዳለበት እያስተማሩ "አሞኛችሁ ዘንድ ዓይናችሁን ጨፍኑ"በማለት ተከታዩን ያሞኛል፦
Показати все...
8.03 MB
በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር ድረ ገጽ ላይ አዲስ የተለቀቁ 👇 1) የባሕርይ እናት https://www.wahidislamicapologetics.org/የባሕርይ-እናት/ 2)ታላቁ ገደል/ https://www.wahidislamicapologetics.org/ታላቁ-ገደል/ 3) ተዋዱዕ https://www.wahidislamicapologetics.org/ተዋዱዕ/ 🌐 ወደ ድረ ገጹ ለመግባት http://www.wahidislamicapologetics.org
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.