cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

Show more
Advertising posts
68 213Subscribers
+3724 hours
+3537 days
+1 68830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ያገዘፍከውና ያሳነስከው የዛሬዋ ሕይወት በትናንትናውና በነገው መካከል እንደ ሳንዱዊች የተጣበቀች ሂደት ነች፡፡ እነዚህ ሁለቱ የሕይወት ገጽታዎች በዛሬው የሕይወትህ ሂደት ላይ ትልቅ ድርሻ አላቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከእነዚህ ሁለት ገጽታዎች መካከል ያገዘፈው ህይወትህን የማንቀሳቀስ አቅም አለው፡፡ የትናንትናውን ስታገዝፈው፣ የነገው ይደበዝዛል፤ የነገውን ስታገዝፈው ደግሞ የትናንትናው ይደበዝዛል፡፡ በእነዚህ ሁለት ምርጫዎች መካከል የመወሰን መብቱም አቅሙም አለህ፡፡ ብዙ የተሳካላቸው ሰዎች የትናንትናውን ልምምዳቸው “መልካምም” ሆነ “መጥፎ” ያንን ሳይክዱና ፈጽመው ሳይጥሉት ነገር ግን ከትናንትናው ይልቅ የነጋቸውን በማግዘፍ እንደሚያምኑ ይናገራሉ፡፡ የትናንትናውን በማግዘፍና የነገውን በማግዘፍ መካከል መምረጥ ማለት በመቃብር ውስጥ ባለውና በመሕጸን ውስጥ ባለው መካከል እንደመምረጥ ነው፡፡ የትናንትናህ መቃብር ውስጥ ነው - ሞቷል! በተቃራኒው፣ የነገህ ደግሞ በማህጸን ውስጥ ነው - ሊወለድ ተዘጋጅቷል! የትኛውን ትመርጣለህ? ለየጥኛው ትኖራለህ? የትናውን ስታሰላስል ታሳልፋለህ? ወደየትኛው አቅጣጫ መሄድ ትፈልጋለህ? ያለፈው ታሪክ አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ካለፈው ታሪክ ይልቅ የነገው ራእይህ ሲገዝፍ ሕይወት ወደፊት ትሄዳለች፡፡ ከመጣህበት ይልቅ የምትሄድበት ሲገዝፍ! ካለፈው ስቃይ ይልቅ ከዚያ በመማር የያዝከው የመለወጥ ሂደት ሲልቅ! ካለፈው ስኬት ይልቅ የነገው የላቀ ደረጃ ሲተልቅ! አስገራሚ ሕይወት!!! አስገራሚ የወደፊት!!! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623
Show all...
👍 100 51🔥 8🤩 3
የስልጠና እድል! With Dr. Eyob Mamo ከሃገር ቤት ውጪ ለምትገኙ ሁሉ የተዘጋጀ በ Zoom የሚሰጥ የስልጠና እድል፡፡ ራእይ . . . • የተፈጠርንነትን የሕይወት ትርጉም የምናገኝበት . . . • ከተሰላቸንበት የሕይወት ዑደት የምንወጣበትና ወደ ዓላማችን አቅጣጫን የምንይዝበት . . . • ለራሳችን ብቻ ከመኖር ባሻገር በሌሎች ላይ ተጽእኖ የማምጣት መትረፍረፍ ውስጥ የምንገባበት . . . . . . ብቸኛው መንገድ! በማስወቂያ ፖስተሩ ላይ ባለው መረጃው መሰረት መመዝገብ ትችላላችሁ! አያምልጣችሁ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Show all...
👍 89 19😁 4
ልቆ የመገኘት ምርጫ (“ምርጫና ውሳኔ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ) አንደኛው ምርጫህ ለማድረግ የተጠየከውንና የሚጠበቅብህን ብቻ በማድረግ መወሰን ነው፡፡ ሌላኛው ምርጫህ ግን ከሚጠበቅብህና ከሚገባህ በላይ በማከናወን ልቆ መገኘት ነው፡፡ አንድ ሁለት ልጆች የነበሩት ገበሬ ነበረ፡፡ ሁለቱ ልጆቹ በእርሻ ስራው አይለዩትም ነበር፡፡ አባት ለታናሹ ልጁ የበለጠ ሃላፊነት ስለሚሰጠውና ስለሚያምነው ሁል ጊዜ ታላቅየው ጥያቄ ይፈጥርበት ነበር፡፡ አንድ ቀን አባት አምስት መቶ ብር በእጁ ላይ እንዳለውና፣ አምስት በጎችን እጁ ላይ ባለው የገንዘብ መጠን ቢያገኝ የመግዛት እቅድ እንዳለው ለታላቅ ልጁ እየነገረው ሳለ፣ ታላቅ ልጅ ይንን አጋጣሚ በመጠቀም ለምን ከእርሱ ይልቅ ለታናሹ የበለጠ ሃላፊነትን እንደሚሰጠው ጠየቀው፡፡ ይህንን ሲወያዩ ታናሽ ልጅ በዚያ አልነበረም፡፡ አባትም ቀጥተኛ መልስ ቢሰጠው ይገነዘበዋል ብሎ ስላላሰበ በብልሃት ሊያስተምረው ፈለገ፡፡ አባት ለታላቅ ልጁ፣ “እሰቲ እነዚያ ከብት የሚያረቡት ሰዎች ቤት ሂድና በግ ይሸጡ እንደሆነ አጣርተህ ተመለስ፣ ከዚያም ጥያቄህን እመልስልሃለሁ” አለው፡፡ ታላቅ ልጅ ሄዶ ተመለሰና፣ “አዎን የሚሸጡ በጎች አሏቸው” አለ፡፡ አባትም፣ “ሂድና ዋጋቸው ስንት እንደሆነ ጠይቅ” አለው፡፡ ልጅም ሄዶ መጣና፣ “ባለ 100 ብር በጎች አላቸው” አለው፡፡ አባት እንደገና፣ “ሂድና ነገውኑ በጎቹን ብንገዛቸው እኛ ድረስ ሊያመጡልን እንደሚችሉ ጠይቅ” አለው፡፡ ልጅም ሄዶ መጣና፣ “አዎን ይችላሉ” አለው፡፡ አባትም ታናሽ ወንድምህን ጥራው እስቲ አለው፡፡ ታናሽ ልጅ ሲመጣ አባት፣ “እስቲ እነዚያ ከብት የሚያረቡት ሰዎች ቤት ሂድና በግ ይሸጡ እንደሆነ አጣርተህ ተመለስ” አለው፡፡ ታናሽየው ሄዶ ተመለሰና፣ “ባለ 100 ብር፣ ጎችና እና ባለ 150 ብር በጎች አሏቸው፡፡ ነገውኑ ብንፈልግ ሊያመጡልን እንደሚችሉ ጠይቄ ተስማምተዋል” ብሎ ለአባቱ ነገረው፡፡ በመጨመርም፣ “ስለዚህ፣ የተለየ ሃሳብ ኖሮን ካልነገርኳቸው በስተቀር አምስት በጎችን በ100 ብር ሂሳብ ነገውኑ እንዲያመጡልን ተስማምቼአለሁ” አለው፡፡ አባት ወደታላቅ ልጁ ዘወር ብሎ ሲመለከት፣ ታላቅ ልጁ የራሱንና የታናሽ ወንድሙን መልስ በማሰነጻጸር ላይ እንዳለ ያስታውቅ ነበር፡፡ “አየህ ልጄ፣ አንተንና ታናሽ ወንድምህን የጠየኳችሁ አንድ አይነት ጥያቄ ነው፡፡ ያመጣችሁልኝ መረጃ ግን በጣም ይለያያል፡፡ አንተ ያችኑው የተጠየከውን ጥያቄ ነው ይዘህ የመጣኸው፡፡ ሌላ መረጃ ስፈልግ እንደገና ደጋግሜ መላክ ነበረብኝ፡፡ እርሱ ግን እኔ የፈለኩትን ፍላጎቴን በሚገባ በመረዳት የቻለውን ያህል መረጃ ይዞልኝ ነው የመጣው፣ ከተጠየቀውም በላይ ስራ ሰርቶ ነው የመጣው፡፡ ሁል ጊዜ ከአንተ ይልቅ ለእርሱ ሃላፊነትን የምሰጠው ለዚህ ነው፡፡” በማለት ቀድሞ ለጠየቀው ጥያቄ መልስን ሰጠው፡፡ ለነገሩ፣ ታላቅ ልጅ ገና መልሱ ሳይብራራ ገብቶት ነበር፡፡ የተባሉትንና የሚጠበቅባቸውን ብቻ አድርገው እጆቻቸውን የሚሰበስቡ ሰዎች ተግባርን በማከናወንና የተጠበቀባቸውን ነገር በማድረግ አንጻር ትክክለኛ ነገር አድርገዋል፡፡ በእድገት ልቆ ከመገኘት አንጻር ሲታይ ግን ባሉበት የሚረግጡ አይነት ሰዎች ናቸው፡፡ ይህ አይነቱ ምርጫ ሰዎች ሊያከናውኑ ከሚችሉት አቅማቸው በታች እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች በእድገትና በተቀባይነት አልፈዋቸው ሲሆዱ እያዩ “ለምን?” እያሉ ከመጠየቅ ያለፈ እድገት አይኖራቸውም፡፡ “ለምን ለሌሎች ያደላሉ? … ለምን ሰውን ይመርጣሉ? …” https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Show all...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

77👍 56😱 1
ልቆ የመገኘት ምርጫ
Show all...
👍 17 4
አዲስ መጽሐፍ! በቅርብ ቀን ይጠብቁ! “የልጆች አስተዳደግ” በዶ/ር ኢዮብ ማሞ ልጆችን የማሳደጊያ ስኬታማ መመሪያዎች! ከመጽሐፉ መግቢያ የተወሰደ ትናንትና የነበረ እድል ዛሬ ያለመኖሩን ያህል ትናንትና የነበሩ ችግሮችም መልካቸውን ለውጠው ብቅ ይላሉ፡፡ ይህ እውነታ በልጆችም ሕይወት መንጸባረቁ የማይካድ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ልጆች የሚያጋጥማቸው እድሎች፣ ምርጫዎችና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ከመቸውም በበለጠ ሁኔታ ለወላጆች የቤት ስራ ሆኗል፡፡ ይህ የልጆች አስቸጋሪ ሁኔታ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ የወላጆች ሸክም መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ወላጆች የልጆቸውን የወደፊት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ በእነሱ እጅ እንደሆነ አምነው መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡ ልጆችን አስመልክቶ በአንድ ሃገር ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ተቋም ሊራው የማይችለውን ስራ የመስራት አቅሙም፣ እድሉም ሆነ ሃላፊነቱ ያለው በወላጆች ላይ ነው፡፡ በዚህች አነስተኛ መጽሐፍ ውስጥ ወላጆች በልጆቻቸውን ሁለንተናዊ እድገት ላይ ሊኖራቸው ስለሚገባ የመልካም ተጽእኖ ተሳትፎ በስፋት እንመለከታለን፡፡ የዚህ መጽሐፍ ዋና ዓላማ በልጆች አስተዳደግ ሂደት ላይ ወላጆች ሊያስቡባቸውና ራሳቸውን ሊሰለጥኑባቸው የሚገባቸውን ዋና ዋና ሃሳቦች መጠቆምና መሰረታዊ ግንዛቤን ማስጨበጥ ነው፡፡ የመጽሐፉ አወቃቀር ክፍል አንድ - ልጅ የመውለድ ጉዳይ ክፍል ሁለት - ልጆችን መቆጣጠር እና ማሳደግ ክፍል ሶስት - ልጆችን ማወቅ እና መቀበል ክፍል አራት - ልጆች የሚማሩባቸው መስኮች ክፍል አምስት - ልጆችን ማስተማር የሌለብን ነገሮች ክፍል ስድስት - የልጆችን ብልህነት መለየትና መደገፍ ክፍል ሰባት - ልጆችን ከመገፋት መጠበቅ ማጠቃለያ - የልጆችን ለውጥ መከታተል!
Show all...
👍 140 62🤩 2😱 1
ጠንካራው መልእክት! “በሚጮህ ድምጽና በጠንካራ ድምጽ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ” (ካታወቀ ምንጭ) የሚጮህ ሁሉ ጠንካራ አይደለም፤ ጠንካራ ሁሉ አይጮህም! ተገቢ ያልሆነን ነገር ለሚያደርግባችሁ ሰው የክልከላ መልእክትን ለማስተላለፍ የግድ መጮህ የለባችሁም፡፡ መልእክታችሁ ግን ጠንካራ መሆን አለበት፡፡ በሌላ አገላለጽ ጩኸት የጥንካሬ ምልክት አይደለም፡፡ እንዲያውም ሁል ጊዜ እየጮህን ስሜታችን ሲረግብ አሁንም ለሁኔታው ተጋላጭ ሆነን ራሳችንን የምናቀርብ ከሆነ ጩኸታችን የመልእክታችንን ደካማነት ነው የሚያሳየው፡፡ ይህንን ለማረም ከፈለግን ሳንጮህ ጠንካራ መልእክትን ማስተላለፍ እንችላለን፡፡ እንዴት? . . . 1. በትንሹም በትልቁም ስሜታዊ ባለመሆን አንዳንድ ነገሮችን ታግሶ ማለፍ፡፡ 2. ሰዎች የአካል፣ የስሜትና የስነ-ልቦና ጤንነታችንን አደጋ ላይ የሚጥልን ሁኔታ ሲያደርጉ ስሜታችንን በግልጽ ማሳወቅ፡፡ 3. በተግባር የማንደግፋቸውንና የማናሳያቸውን ስሜታዊነቶች በቃልና በአንደበት ከመናገር መቆጠብ፡፡ 4. በጨዋ ንግግራችን እና በተረጋጋ ስሜት የገለጽናቸውን አቋሞቻችንን በጠንካራ ተግባር ማሳየት፡፡ 5. ከሰዎቹ ዘላቂ የሆነንና በተግባር የሚታይ ለውጥን እስከምናገኝ ድረስ ከግንኙቱ ራሳችንን መጠበቅ፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Show all...
👍 171 67🔥 3🤩 2
ኃዘንተኛ ለመሆን ከፈለጋችሁ . . . ሃዘንተኛ ሰው ሆናችሁ መኖር ከፈለጋችሁ ቀላሉ መንገድ ሁልጊዜ፣ በሁሉም ቦታና በሁሉም ሁኔታ፣ ሁሉንም ሰው ለማስደሰት ሲጦዙ መኖር ነው፡፡ ማንም ሰው እንዳያዝንባችሁ፣ ቅር እንዳይሰኝባችሁን ሁል ጊዜ ሁሉም ሰው በእናንተ ሃሳብም ሆነ ተግባር ደስተኛ እንዲሆን የምትፈልጉ ከሆነ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ አደገኛ የስሜት ቀውስ ውስጥ መግባታችሁ አይቀርም፡፡ ጉዳዩ ግን ከዚያም ትንሽ ሰፋ ያለ ነው፡፡ ቀላላል እውነቶች . . . • ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚጦዝ ሰው ሰዎችን ለማስደሰት ሌላ ሌላውን ሲኖር ራሱን ሆኖ መኖር አይችልም፤ ራሱን ሆነ የማይኖር ሰው ደግሞ በፍጹም ደስተኛ መሆን አይችልም፡፡ • ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚጦዝ ሰው ለማስደሰት በሚፈልገው ሰው ቁጥጥር ስር ይውላል፤ ሰው ተቆጣጥሮ እንደፈለገ የሚያደርገው ሰው ደግሞ በፍጹም ደስተኛ መሆን አይችልም፡፡ • ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚሯሯጥ ሰው በየሰዓቱና በየቀኑ የሚለዋወጥ የስሜት ውጣውረድ (ሙድ) ውስጥ ራሱን ያገኘዋል፤ ስሜቱ (ሙዱ) በየጊዜው የሚለዋወጥ ሰው ደግሞ በፍጹም ደስተኛ መሆን አይችልም፡፡ • ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚጦዝ ሰው “ሰዎችን ያስደስትልኛል” ከሚለው ሃሳብ አንጻር እንጂ ከዓላማ አንጻር መኖር አይችልም፤ ከዓላማ ውጪ የሚኖር ሰው ደግሞ ደስተኛ መሆን አይችልም፡፡ በሕይወታችሁ ሰዎችን ማስደሰት እጅግ ደስታን የሚሰጥ ልምምድ መሆኑን ማስመራችንን ሳንዘነጋ፣ የሕይወታችሁ ዋና ዓላማ ግን ማንም ሰው ቅር እንዳይሰኝባችሁ፣ በክፉ እንዳያስባችሁ፣ እንዳያወራባችሁ፣ እንዳይገፋችሁ . . . ከሆነ የዚህች ምድር አጭር እድሜያችሁን በኃዘን የምታሳልፉ ሰዎች ናቸው፡፡ በመጨረሻም፣ ሁሉንም ሰው ማስደሰት እንደማይቻል ትደርሱበትና ያን ጊዜ ደግሞ ያንን የማይቻል ነገር ለመቻል ስትጦዙ ዓመታቶቻችሁን ስላባከናችሁ በመቆጨት ታዝናላችሁ፡፡ በሉ እንግዲህ፣ ማድረግ ወደምትችሉትና ወደሚገባችሁ እውነታ ተመለሱ! ማድረግ የምትችሉት፣ በገባችሁና በአቅማችሁ መጠን ለራሳችሁ ጨዋ ኑሮን መኖር፣ ለሰዎች ደግሞ መልካም ሰው መሆንና ሁልጊዜ ከስህተት ለመታረም የተዘጋጀ ልቦና ማዳበር መሆኑን አትዘንጉ፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Show all...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

203👍 122🔥 11😱 7
ኃዘንተኛ ለመሆን ከፈለጋችሁ . . .
Show all...
👍 21 2
መስማማት ሲቻል! (ትምህርት በፈገግታ) ባልና ሚስቱ እጅግ በከረረ ጸብ ተጣልተውና ተኮራርፈው ነው ያመሹት፡፡ ሚስትየው ሻወር ውስጥ እያለች፣ ባልየው፣ “ጠዋት የውጪ ሃገር በረራ ስላለብኝ በ12፡00 ሰዓት ቀስቅሺኝ” የሚል መልእክት ወረቀት ላይ ጽፎላት ራስጌዋ ጋር አድርጎላት እንዳኮረፈ ተኛ፡፡ ጠዋት እንቅልፍ ጥሎት የበረራው ሰዓት አልፎ ነቃና የጻፈላትን መልእክት ችላ ስላለች በብስጭት ቀድማ ወደነቃችው ወደሚሰቱ ሊሄድ ሲነሳ ራስጌው ጋር፣ “12፡00 ሰዓት ሆኗልና ተነሳ” የሚል መልእክት ወረቀት ላይ ተጽፎ አገኘ፡፡ ከዚህ ሁሉ መስማማቱ አይሻልም???!!! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Show all...
😁 169👍 69 46🤩 15
Coming Soon ! በዶ/ር ኢዮብ ማሞ የሚሰጥ ወሳኝ የስልጠኛ እድል - ርዕስ፡- “በራእይ የሚመራ ሕይወት” "የራሳችን ዓላማ ከሌለን የሌላን ሰው ዓላማ እንዳስፈጸምን ኖረን እናልፋለን!" የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ • የራእይን ትክክለኛ ትርጉም ለይቶ ለማወቅ! • የግልን ራእይ ግልጽና ተግባራዊ በሆነ መልኩ ለመቅረጽ! • የግልን ራእይ ለማሳካት መከተል የሚገባንን ሂደቶች በሚገባ ለመገንዘብ! • ከሌሎች ሰልጣኞች ጋር በመገናኘት የእነሱን ልምድ ለመከፋፈል! • ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ በግል በመገናኘት ኮቺንግ ለመቀበልና ለጥያቄዎቻችን መልስን ለማግኘት! ለስድስት ቅዳሜ ጠዋቶች ብቻ! ለጥራት ሲባል የሰልጣኞች ቁጥር ከ50 በታች የተገደበ! ሙሉ መረጃውን በቅርብ ቀን ይጠብቁ!
Show all...
👍 193 50🔥 8😁 1