cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

Show more
Advertising posts
68 631
Subscribers
+524 hours
+2137 days
+1 38330 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች! እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
4 5252Loading...
02
https://vm.tiktok.com/ZMMGd1bgB/
8 4395Loading...
03
ብቁ ናችሁ! ከሕይወት ትልልቅ የፍርሃት ምንጮች አንዱ “ብቁ ያለመሆን” ፍርሃት ነው፡፡ በሰዎች ለመወደድ፣ ለመፈቀር፣ ተቀባይነት ለማግኘት፣ ለማወቅ፣ ለመሰልጠን፣ እድገት ለማግኘት . . .ብቁ እንዳልሆንን የማሰብ ፍርሃት! እውነት እውነቱን እንነጋገር፡፡ አንድ ሰው እናንተን ለመቀበልና ለመውደድ የማይችል ወይም የማይፈልግ ከሆነ፣ ይህ ማለት እናንተ የዚያ ሰው አይደላችሁም ማለት ነው - አለቀ! ይህ ማለት ግን የዓለም መጨረሻ ነው ማለት አይደለም፡፡ ይህ ሰው እናንተን የመቀበልና የመውደድ ብቃቱ ወይም ፍላጎቱ የለውም ማለት ነው እንጂ እናንተ ተቀባይነት የማግኘትና የመወደድ ብቃቱና ማንነቱ የላችሁም ማለት አይደለም፡፡ እናንተን የመውደድም ሆነ የመቀበል ብቃቱና ፍላጎቱ ያለው ብዙ ሰው በዙሪያችሁ እንዳለ አስታውሱ፡፡ እነሱን ለማየትና ለመገናኘት ግን “ካልተቀበለኝና ከልወደደኝ” ብላችሁ ችክ ካላችሁት ሰው ላይ አይናችሁን ማንሳት፣ ስሜታችሁንም ማላቀቅ የግድ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ለጊዜው ከባድ ነው፣ ነገር ግን በሚልየን የሚቆጠሩ ሰዎች ችለውታልና እናንተም ትችላላችሁ! አንድ ነገር አልሆን ሲላችሁ ሁል ጊዜ እናንተ ለዚያ ነገር ብቁ ስላልሆናችሁ እንደሆነ የማሰብን የእሳቤ ንድፍ መቀየር አለባችሁ፡፡ በዚያ ምትክ ያ ሰውም ሆነ ሁኔታ ለእናንተ የማይመጥን ስለሆነ እንደቀረላችሁ ማሰብም አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜም እንዳለ አትዘንጉ፡፡ በአጭሩ፣ ለመወደድ ብቁ ናችሁ! ለማደግ ብቁ ናችሁ! ለማወቅ ብቁ ናችሁ! በዚህ ዓለም ፈጣሪ ለሰው ልጆች ደስታና ስኬት ለፈጠረው መልካም ነገር ሁሉ ብቁ ናችሁ! ሕይወት ትክክለኛውን ሰውና ስፍራ ገልጣ እስከምታቀርብላችሁ ድረስ ግን ራሳችሁን በመቀበል የድርሻችሁን መወጣት የግድ ነው፡፡ https://t.me/Dreyob
9 81963Loading...
04
በጥራት ማደግ! ሁለት አይነት እድገቶችና ትልቅነቶች አሉ፡፡ አንደኛው ውጫዊ እድገትና ትልቅነት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” ነው፡፡ 1. ውጫዊ እድገትና ትልቅነት ሰዎች በገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣ በዝና፣ በስልጣን እና በመሳሰሉት ነገሮች ሲያድጉ፣ “ውጫዊ እድገትና ትልቅነት” አገኙ እንለዋለን፡፡ ይህ እድገትና ትልቅነት ምንም እንኳን በራሱ ምንም ችግር ባይኖረውና እንዲያውም ለጥቅም የሚውል ቢሆንም ብቻውን ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ 2. “ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” ሰዎች በመልካም ስብእና፣ በጤናማ አመለካከት፣ በስሜት ብልህነት፣ በራእይ እና በጥበብ ሲያድጉ፣ “ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” አገኙ እንለዋለን፡፡ ይህ እድገትና ትልቅነት ከማንኛውም ነገር በፊት ሊቀድም የሚገባው የእድገትና የትልቅነት ዘርፍ ነው፡፡ አንድ ሰው ከላይ የተጠቀሱትን አይነት ውጫዊ እድገትንና ትልቅንን እያስመሰዘገ ውስጣዊ እድገት ሲጎድለው ከራሱ ሕይወት ጀምሮ እስከ ቤተሰቡ፣ የስራ ስምሪቱና በሃገር ደረጃ የሚያስከትለው ቀውስ ይህ ነው አይባለም፡፡ የገንዘብ አቅሙን ለማይረባ ነገርና ለሕገ-ወጥ ተግባር የሚጠቀም ማነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን? በዝናውና በታዋቂነቱ የሚኩራራውና ሰውን የሚንቀው ማን ነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን? በስልጣኑ ተጠቅሞ ሰውን የሚደቁስና እንደፈለገ የሚሆን ማን ነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን? በመጀመሪያ በውስጣችን እንደግ! ከሁሉም በፊት በጥራትና በብቃት ትልቅ እንሁን! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
11 50067Loading...
05
https://vm.tiktok.com/ZMMsLwDqy/
10 8415Loading...
06
https://vm.tiktok.com/ZMMsLURPL/
10 3164Loading...
07
ያስቸገረኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር! ተወልዶ ካደገበት ሃገሩ በተፈጠሩ ማሕበራዊ ቀውሶች ምክንያት ወደሌላ ሃገር በስደት ለመሄድ የቆረጠ አንድ ሰው ረጅም፣ አድካሚና አስፈሪ የሆነን በረሃ ለቀናት በእግሩ በመሄድ ካቋረጠ በኋላ እጅግ ደክሞና ዝሎ ነበር፡፡ በመጨረሻም በደረሰበት አንዲት ከተማ ውስጥ በተሰጠው እርዳታ ትንሽ አገገመ፡፡ የዚህን ሰው ጉዞ የሰማና ለሕብረተሰቡ ለማቅረብ የፈለገ አንድ ጋዜጠኛ አገኘውና አንድን ጥያቄ ጠየቀው፡፡ “ተጉዘህ የመጣኸው በረሃ ብዙ ሰው የማይደፍረው በረሃ ነው፡፡ ለመሆኑ በመንገድህ ላይ በጣም የጎዳህና ያስቸገረህ ውኃ ጥም ነበር? ምግብ ማጣት ነበር? አውሬ ነበር? ሽፍቶች ነበሩ? ወይስ . . . ? የዚህ ስደተኛ መልስ ለጋዜጤኛው ያልተጠበቀ ነበር፡፡ በዚህ አደገኛ በረሃ አቋርጬ ስመጣ በጣም ያስቸገሩኝ የጠቀስካቸው ትልልቅ ነገሮች አልነበሩም፡፡ ጉዞየን በጣም አድካሚና አስቸጋሪ ያደረገብኝ በእርምጃዬ ወቅት ጫማዬ ውስጥ እየገባ የሚቆረቁረኝና አላራምድ ያለኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር፡፡ የሕይወት ጉዞም እንዲሁ ነው! አብዛኛውን ጊዜ የሚያስቸግረን፣ የሚቆረቁረን፣ አላራምድ የሚለንና ከዓላማችን የሚጎትተን ችግር ትልልቁ አይደለም፡፡ በየቀኑ የሚያጋጥሙን ጥቃቅን “አሸዋዎች” ናቸው፡፡ ትንንሽ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ባህሪይ፣ ትንንሽና አናሳ ወሬን የሚያወሩ ሰዎች ሁኔታ፣ ትንንሽና ስሜትን የሚነካኩ የየቀን ገጠመኞች . . . ጉዟችንን አዳጋችና አድካሚ ያደርጉታል፡፡ “በትንንሽ” ሰዎችና ሁኔታዎች ሳትበገሩ ትልቁ የሕይወት ስእልና ዓላማችሁ ላይ በማተኮር ወደፊት መገስገስን ያወቃችሁበት ጊዜ ዋናውን የሕይወት ድል የተጎናጸፋችሁበት ጊዜ ነው፡፡ በርቱ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623
11 802117Loading...
08
ከኢትዮጵያ ውጪ ለምትኖሩ በዚህ ሊንክ ግቡና ተመዝገቡ ክፍያውንም እዛው ላይ እንዴት እንደምትከፍሉ ይነግራል:: ኢትዬጽያ ለምትኖሩ ይህ ስልጠና የሚሰጥበት ሰአት ለናንተ ሌሊት ስለሚሆን ላይመች ይችላል:: https://forms.gle/NkcpF5jQwrUVVf47A
11 4061Loading...
09
የስልጠና እድል! With Dr. Eyob Mamo ከሃገር ቤት ውጪ ለምትገኙ ሁሉ የተዘጋጀ በ Zoom የሚሰጥ የስልጠና እድል፡፡ ራእይ . . . • የተፈጠርንነትን የሕይወት ትርጉም የምናገኝበት . . . • ከተሰላቸንበት የሕይወት ዑደት የምንወጣበትና ወደ ዓላማችን አቅጣጫን የምንይዝበት . . . • ለራሳችን ብቻ ከመኖር ባሻገር በሌሎች ላይ ተጽእኖ የማምጣት መትረፍረፍ ውስጥ የምንገባበት . . . . . . ብቸኛው መንገድ! በማስወቂያ ፖስተሩ ላይ ባለው መረጃው መሰረት መመዝገብ ትችላላችሁ! አያምልጣችሁ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
11 35513Loading...
10
መፍራትን አትፍራው! እንደ ፍርሃት፣ ድንጋጤና ስጋት አይነት ስሜቶች ሰው ከአደጋ እንዲጠነቀቅ ከፈጣሪው የተሰጡ ስጦታዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ስሜቶች በአግባቡ ልንጠቀምባቸውና ከአደጋ ልንጠበቅባቸው ሲገባን ለአንዳንድ ሰዎች የኑሮ ዘይቤ ሆነዋል፡፡ የመውደቅ ፍርሃት፣ የመክሰር ፍርሃት፣ ያለመወደድ ፍርሃት፣ ብቻ የመቅረት ፍርሃት፣ … ጣጣችን ብዙ ነው፡፡ በፍርሃት ስንወረስ፣ ሕይወታችንን በራእይ መምራት እናቆምና ለፍርሃት ምላሽ በመስጠት መምራት እንጀምራለን፡፡ ከአንዱ ራእይ ወደሌላኛው በማለፍ ሕይወትን “ልናጠቃት” ሲገባን የመጣው ሁሉ የኑሮ ገጠመኝ የሚያጠቃን ቋሚ ኢላማዎች እንሆናለን፡፡ ቆመን ለመጣው ወይም የመጣ ለመሰለን ጥቃት ምላሽ በመስጠት ጊዜአችንን እናባክናለን፡፡ ይህ ሲሆን የቆመ ኢላማ ሆንን ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው ከአንዱ ግብ ወደሌላኛው በአላማ የምንንቀሳቀስ ሰዎች ስንሆን አይኖቻችን ከችግሩ ላይ ይነሱና መፍትሄው ላይ ማረፍ ይጀምራሉ፡፡ የፍርሃትህ ጥልቀት አእምሮህ የፈቀደለት ያህል ነው” - Unknown Source ፍርሃት በሕይወትህ ብቅ ጥልቅ ማለቱ አያስፈራህ፡፡ በዚያ ፍርሃት ምክንያት ግን መንቀሳቀስ እስኪያቅትህ ድረስ እንዳትታሰር ፍራ፡፡ ማንኛውም ሁኔታ አንተን የማስፈራራት ሙከራ የማድረግ ሙሉ መብት አለው፡፡ አንተ ካልፈቀድክለት ግን ሊያስፈራራህ አይችልም፡፡ ትፈራለህ፣ ፈሪ ግን አይደለህም፡፡ “በፍጹም አልፈራም” ብለህ ካሰብክና ከተናገርክ ከፍርሃት የተደበቅህ ሰው እንደሆንክ አመልካች ነው፡፡ በሌላ አባባል፣ የፍርሃት ስሜት እንዳይመጣ መከልከል አትችልም፣ ይህንን ስሜት ለማስተናገድ የተፈጠረ ማንነት ስላለህ፡፡ ሆኖም፣ የፍርሃትን ጥልቀትና በአንተ ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ጉዳት የመወሰን ሙሉ መብትም ሆነ ብቃት አለህ፡፡ https://t.me/Dreyob
13 01459Loading...
11
ሃሳብን ወደ ተግባር መለወጥ አንድን ያመንንበት ሃሳብ ወደ ተግባር ለመለወጥና ስኬታማ ለመሆን ከፈለግን የሚከተሉት ሶስት መሰረታዊ ልምምዶች ያስፈልጉናል፡፡ 1. እውቀት ለመተግባር በፈለግነው ማንኛውም ጽንሰ-ሃሳብ አንጻር በቂ እውቀት ማዳበር በምንም ነገር ሊተካ የማይችል ልምምድ ነው፡፡ ካለእውቀት የሚጀመር ነገር ረጅም ርቀት ለመሄድ ካለመቻሉም ባሻገር አንድ እርምጃ ለመራመድ እንኳን እውቀቱን በጨበጡ ሰዎች ላይ የምንደገፍ ያደርገናል፡፡ 2. እምነት በአንድ ማከናወን በፈለግነው ነገር ላይ በቂ ወይም ለመነሻ የሚሆን እውቀት ካዳበርን በኋላ ወደፊት ለመገስገስ ከፈለግን የምንጀምረው ነገር እንደሚሰራ በሙሉ ልባችን ልናምን ይገባናል፡፡ እንደሚሳካም ሆነ ወደፊት እንደምንገሰግስ ልባችን ያላመነበትን ነገር መጀመር አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ፣ ቢጀመርም እንኳን ዘላቂነቱ አጠራጣሪ ነው፡፡ 3. እርምጃ ማድረግ የፈለግነውን ነገር አወቅነውም አላወቅነውም፣ እንደሚሰራ አመንንበትም አላመንበት፣ የመጨረሻው የውጤታማነት ምስጢር ያለው በዚያ ነገር ላይ እርምጃ በመውሰዳችን ላይ ነው፡፡ እርምጃና ተግባራዊነት የሌለው እውቀትም ሆነ እምነት የትም አይደርስም፡፡ በቂ እውቀት! ጽኑ እምነት! የማያዳግም እርምጃ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
13 34591Loading...
12
ጥገኝነት ጥገኝት ማለት በራሳችን ለመቆም ካለመቻላችን ወይም ካለመፈለጋችን የተነሳ በሰዎች ላይ ተደግፈን ስንኖር ማለት ነው፡፡ ለጊዜውና አንድን አስቸጋሪ ሁኔታ እሰከምናልፍ ድረስ በሰው ላይ ጥገኛ መሆን ችግር የሌለውናሁሉም ሰው የሚልፍበት የሕይወት እውነታ ነው፡፡ ነገር ግን ጥገኛ የምንሆንባቸውን ሁኔታዎች መለየት፣ ለምን በሰዎች ላይ ጥገኛ ለመሆን እንደተገደድን መገንዘብና እስከመቼ በዚህ ሁኔታ እንደምንኖር አስበንበት ከሁኔታው የመላቀቅ እቅድ ማውጣት አስፈላጊ ነው፡፡ የሰው ጥገኛ ሆኖ በራሱ ላይ ያለውን ግምት ትክክለኛና ሚዛናዊ አድርጎ ለማቆየት የሚችል ሰው ማግኘት ያስቸግራል፡፡ ጥገኝነት በራሳችን ላይ ያለንን ግምት ስለሚያወርደው ማለት ነው፡፡ ጥገኝነት መራራ ያደርገናል፣ እኛን ለሚጎዱ ሰዎች አጋልጦ ይሰጠናል፣ የራሳች የሆነ ነገር እንድንገነባ አይፈቅድልንም፡፡ ከላይ እንደጠቀስነው አንዳንድ ጊዜ ምንም እንኳን ካለንበት አስቸጋሪ ሁኔታ የተነሳ ለተወሰነ ጊዜ የሰው ጥገኛ ብንሆንም ከዚያ የመውጣት ፍላጎቱ፣ እቅዱና ጥረቱ ሲኖረው ውስጣችንን ጠንካራ ያደርገዋል፡፡ ሁል ጊዜ ልንሰራባቸው የሚገቡን የጥገኝነት አይነቶች፡- 1. የገንዘብ ጥገኝነት፡- ራስን ችሎ ለመኖር ካለመፈለግ ወይም ካለመቻል ራስን ወደመቻል ለመሻጋገር እንስራ፡፡ 2. የስሜት ጥገኝነት፡- በሰዎች ላይ የስሜት ጥገኛ ከመሆናችን የተነሳ እንደ እነሱ ወቅታዊ ሁኔታ የሚዘባረቀውን ስሜታችን በማስተካከል የራሳችን ስሜት የምንቆጣጠረው ራሳችን ወደመሆን እንደግ፡፡ 3. የእውቀት ጥገኝነት፡- ሁልጊዜ ሰዎችን በመጠየቅና ከእነሱ በምናገኘው መልስ ላይ ብቻ በመደገፍ ከመኖር በራሳችን እውቀትን ወደመቅሰምና በእውቀት ወደመሻሻል ደረጃ ለመድረስ እንስራ፡፡ https://m.youtube.com/user/naeleyob623
14 60483Loading...
13
https://youtu.be/nT7B3DCX3c8?si=FhISUDk2KFXcdv1V
14 49513Loading...
14
እስቲ ሰዎችን ተዋቸው! በከተማ፣ በመንደር፣ በሰፈር፣ በጉርብትናም ሆነ በስራ . . . አካባቢያችሁ ያሉ ሰዎች በማንነታቸው፣ በመልክ በቁመናቸው፣ በዘራቸው፣ በኃይማኖታቸው፣ በኢኮኖሚ ደረጃቸውና በመሳሰሉት ምክንያት በእናንተ በምንም መልኩና በማንኛውም መጠን አድሎ፣ መገለልና መገፋት ከደረሰባቸው፣ ከተገፉ፣ ከተጎዱ፣ ከፈሩ፣ ከሰጉ . . . ቀናችሁ ያልተሳካ፣ የወደፊታችሁም የጨለመ እንደሆነ ለማስታወስ እወዳለሁ፡፡ እስቲ ሰዎችን ተዋቸው! ይኑሩበት!
14 56533Loading...
15
ከኃዘን ድባብ ውጡ! አሁን ላላችሁበት ሁኔታ የእናንተ የትናንትና ምርጫና ውሳኔያች መዋጮ ኖረውም አልኖረውም፣ ሙሉ ሃላፊነቱን ካልወሰዳችሁ፣ በኃዘን ድባብ ውስጥ ስለምትኖሩ ወደ ኋላ ትንሸራተታላችሁ፡፡ “ዛሬን እንደዚህ የሆንኩት ከእገሌ የተነሳ ነው” ብለን ማሰባችን፣ መናገራችንና ሰውን መውቀሳችን ከሃላፊነት አያድነንም፡፡ ዛሬ ላለንበት ሁኔታ ሙሉ ሃላፊነት መውሰድ ስንጀምር ነገ ወደየት አቅጣጫ መሄድ እንዳለብን ጥርት አድርገን ማየት እንጀምራለን፡፡ የትናንትናችንን በመራራነትና በወቃሽነት ስሜት ማሰብ የሚያስከትለው የኃዘን ድባብ የነገውን የማየት አቅማችንን ይጋርደዋል፡፡ ለትናንትናው ስህተት መድሃኒቱ የነገ ራእይ ነው፡፡ የነገን ራእይ ለማየት ደግሞ ዛሬ ላለንበት ሁኔታ ሙሉ ሃላፊነትን በመውሰድ ካለብን ኃዘን መላቀቅ የግድ ነው፡፡ አዲስ ምልከታ፣ አዲስ እቅድ፣ አዲስ ጅማሬ፣ አዲስ ግንኙነት፣ አዲስ ሃሳብ . . . ያዙ! ካለፈው ተማሩ! ያለፈውን ተው! የወደፊት ሕይወታችሁ ያለው ነገ ላይ ስለሆነ ነገን ናፍቁ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
14 01870Loading...
16
ወይ ፍቱት ወይ አስፈቱት! የአብዛኛዎቻችን ችግር የማይፈታው ከችግራችን ግዝፈት የተነሳ ሳይሆን ችግር እንዳለብን አምነን እና ከራሳችን ጋር እውነተኛ ሆነን እርዳታን ለማግኘት ፈቃደኛ ባለመሆናችን ነው፡፡ “ችግሬ አንድ ቀን በራሱ ይሄዳል” ብላችሁ ራሳችሁን አታታሉ፡፡ ችግራችሁን ፍቱት! እናንተ መፍታት ካቃታችሁ ደግሞ እርዳታ ጠይቁና አስፈቱት! ዛሬ እርዳታን ለማግኘት ከምትከፍሉት ጊዜ፣ ገንዘብና የመሳሰሉት ማንኛውም አይነት ክፍያዎች በበለጠ ሁኔታ ያልተፈታው ችግራችሁ የኋላ ኋላ ብቅ ብሎ ያስከፍላችኋል፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
17 90975Loading...
17
https://vm.tiktok.com/ZMMg2sK5u/
15 4045Loading...
18
ተቀባይነትን ለማጣት ቀላሉ መንገድ! በማንኛውም መስክ በሚኖራችሁ የሰው-ለሰው ግንኙነት ውስጥ ቀስ በቀስ ተቀባይነትን፣ ተከባሪነትን፣ ተፈላጊነትንና የሰዎችን አብሮነት ማጣት ከፈለጋችሁ የሚከተሉትን አጓጉል ባህሪያት ግለጹ፡፡ 1. ብዙ ማውራት፡- ብዙ ማውራት የእውቀትና የተግባር ማጣት ምልክት ነው፡፡ ለሌላው ሰው ሃሳብ ጊዜ ባለመስጠት ሁል ጊዜ እሱ ብቻ ከሚያወራ ሰው አካባቢ መሆን የሚፈልግ ሰው የለም፡፡ 2. በሆነ ባልሆነው መነጫነጭ፡- መነጫነጭ የአቅመ-ቢስነት ምልክት ነው፡፡ የሚነጫነጭ ሰው አቅም የሌለው ሰው ከመሆኑም በላይ የሰሚውንም አቅም ስለሚጨርስ ሰዎችን ያርቃል፡፡ 3. አሉታዊነት፡- አሉታዊነት ያልበሰለ ማንነትና አመለካከት ምልክት ነው፡፡ በሁሉም ነገር ላይ አዎንታዊውን ከማግኘትና ከማውራት ይልቅ አሉታዊውን የሚያራግብ ሰው ቢጤዎቹን ብቻ ነው የሚሰበስበው፡፡ 4. ተቃዋሚነት፡- ተቃዋሚነት የቅንአትና የመበለጥ ስሜት ምልክት ነው፡፡ ሁል ጊዜ ሰዎችን የመቃወምን ሃሳብ ከሚሰነዝር ሰው አካባቢ መክረም የሚፈልግ ሰው የለም፡፡ 5. ጽንፈኝነት፡- ጽንፈኝነት የዓላማ ቢስነት ምልክት ነው፡፡ ዓለማ የሌላቸው ሰዎች የቀረበላቸውን የአክራሪነት አጀንዳ መከተልን ያዘውትራሉ፡፡ ውጤቱም ጨዋና ሚዛናዊ ሕይወት መኖር የሚፈልጉ ሰዎችን ማራቅ ነው፡፡ 6. ስስነት፡- ስስነት ያልዳነ ቁስል የመመኖሩ ምልክት ነው፡፡ በሆነ ባልሆነ ነገር ከሚጎዳ ሰው ጋር በመሳቀቅ መኖር የሚፈልግ ሰው ማግኘት ከባድ ነው፡፡ 7. ግትርነት፡- ግትርነት የጠባብነት ምልክት ነው፡፡ ግትር ሰዎች አመለካከታቸው ጠባብ ስለሆነና ከእነሱ ሃሳብና አቋም ውጪ መቀበልን ስለማይፈለጉ ሰዎችን ያርቃሉ፡፡ ምናባት፣ “ሰዎች ትንሽ ቀርበውኝ ይሸሹኛል . . . ከሰዎች ጋር ያለኝ ግንኙት አይቆይም . . . ሁሉም ሰው ትንሽ ካወቀኝ በኋላ ይርቀኛል . . .” እና የመሳሰሉት ስሜቶች ካሏችሁ የተጠቀሱትንና መሰል አጉል ባህሪያቶቻችሁን ለማጤንና ለማስተካከል ሞክሩ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የራሳችንን አጉል ባህሪይ እኛው ማወቅ ያስቸግረናልና ችግራችንን ለመለየት የቅርብ ወዳጆቻችንንና ጓደኞቻችንን መጠየቅ እንችላለን፡፡ የፍቅርና የትዳር አጋሮቻችንም እኛ ከምናስበው በላይ እኛን የማወቅ ብቃት ስላላቸው ከእነሱም ለመስማት ክፍት እንሁን፡፡ ከማሕበራዊ ተቀባይነት ውጪ ምንም ነገር ማከናወንም ሆነ ወደየትም ከፍታ ማደግ ስማትችሉ አስቡበት! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
20 169169Loading...
19
ተቀባይነትን ለማጣት ቀላሉ መንገድ!
16 6675Loading...
20
በፍጹም ተስፋ እንዳትቆርጡ! “አንድ እድሜ ልኩን ማየት የተሳነው ሰው አይኑ ሲበራለት መጀመሪያ የሚጥለው እድሜ ልኩን ምርኩዝና ምሪት ሆኖ ያገለገለውን ዱላ ነው” ይባላል፡፡ “አንድ ሕጻን ጥርስ ሲያወጣ መጀመሪያ የሚነክሰው ያለፉትን ወራት ሲመግበው የነበረውን የእናቱን ጡት ነው” ይባላል፡፡ በጎ ነገር በማድረጋችሁና ጨዋ ማንነት በመያዛችሁ ምክንያት በሰዎች የደረሰባችሁ ነገር ምንም ያህል ቢጎዳችሁና ስሜቱ ደስ ባያሰኝም፣ እናንተ ላይ ብቻ የደረሰና አዲስ ነገር ግን አይደለም፡፡ ከደረሰባችሁ ሁኔታ የተነሳ ጨዋ ማንነታችሁን አትጣሉ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
21 247140Loading...
21
መፍትሄው እኛው ጋር ነው! • ቀኑን ሙሉ የሚያቆይ አቅም ካጣችሁ - ለምን በጊዜ በመተኛትና በቂ እንቅልፍ ማግኘት አታስተካክሉትም? • የሰውነታችሁ አቋም ሁኔታ ካሳሰባችሁ - ለምን አመጋባችሁንና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ልማዳችሁን በማስተካከል አታርሙትም? • ማከናወን ለምትፈልጓቸው ወሳኝ ነገሮች ጊዜ እንዳጣችሁ ከተሰማችሁ - ለምን የማሕበራዊ ሚዲያውንና የቻቱን ጊዜ በመወሰን መፍትሄ አትሰጡትም? • የገንዘብ እጥረት ካለባችሁ - ለምን ስራ አትሰሩም? ለምን ተጨማሪ ስራ አትፈልጉም? ለምን ሌላው ሰው መስራት የመይፈልገውን ስራ በመስራት ራሳችሁን አታሻሽሉም? • እውቀት እንደሌላችሁ ከተሰማችሁ - ለምን አታነቡም? ለምን ስልጠናን አትወስዱም? ለምን በመማር እውቀታችሁን አታሰፉም? • ሰዎች ችላ ያሏችሁ ሲመስላችሁ የመገፋት ስሜት የሚያጠቃችሁ ከሆነ - ለምን የራሳችሁን ዓላማ በመከታተል ራሳችሁን “ቢዚ” አታደርጉም? ከላይ በተጠቀሱትና በሌሎች የተለያዩ የሕይወታችሁ መስኮች ላይ ራሳችሁን ማሻሻል ከፈለጋችሁ የሚከተሉትን የግብ አወጣጥና ትግበራ ሂደቶችን መከተል ይጠቅማችኋል፡፡ 1. የት ነው ያለሁት? 2. የት መድረስ ወይም ምን ማከናወን እፈልጋለሁ? 3. መቼ ነው ተከናውኖ ማየት የምፈልገው? 4. እዚህ ግብ ለመድረስ እንደምችል ውስጤ አምኖበታል? 5. እዚህ ግብ ላይ ለመድረስ ሊገጥሙኝ የሚችሉ እንቀፋቶች ምንድን ናቸው? 6. እነዚህን እንቅፋቶች በምን መልኩ ነው የማልፋቸው? 7. ወደዚህ የተሻለ ስፍራ ለመግባት ራሴን በምን መልክ ማሻሻል አለብኝ? 8. ወደዚህ ግብ ለመድረስ ሊያግዘኝ የሚችል ሰው ማን ነው? 9. ከዚህ ግብ የማገኘው ጥቅም ምንድን ነው? 10. በየቀኑ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩና በየዓመቱ ማከናወን ያለብኝ ነገሮች ምንድን ናቸው? ግልጽ የሆነን ግብ በማውጣት ወደፊት የማይንቀሳቀስ ሰው ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ራሱን ኋላ ቀር ሆኖ እንደሚያገኘው ምንም ጥርጥር አይግባው፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
18 767223Loading...
22
መፍትሄው እኛው ጋር ነው!
17 7867Loading...
23
ያገዘፍከውና ያሳነስከው የዛሬዋ ሕይወት በትናንትናውና በነገው መካከል እንደ ሳንዱዊች የተጣበቀች ሂደት ነች፡፡ እነዚህ ሁለቱ የሕይወት ገጽታዎች በዛሬው የሕይወትህ ሂደት ላይ ትልቅ ድርሻ አላቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከእነዚህ ሁለት ገጽታዎች መካከል ያገዘፈው ህይወትህን የማንቀሳቀስ አቅም አለው፡፡ የትናንትናውን ስታገዝፈው፣ የነገው ይደበዝዛል፤ የነገውን ስታገዝፈው ደግሞ የትናንትናው ይደበዝዛል፡፡ በእነዚህ ሁለት ምርጫዎች መካከል የመወሰን መብቱም አቅሙም አለህ፡፡ ብዙ የተሳካላቸው ሰዎች የትናንትናውን ልምምዳቸው “መልካምም” ሆነ “መጥፎ” ያንን ሳይክዱና ፈጽመው ሳይጥሉት ነገር ግን ከትናንትናው ይልቅ የነጋቸውን በማግዘፍ እንደሚያምኑ ይናገራሉ፡፡ የትናንትናውን በማግዘፍና የነገውን በማግዘፍ መካከል መምረጥ ማለት በመቃብር ውስጥ ባለውና በመሕጸን ውስጥ ባለው መካከል እንደመምረጥ ነው፡፡ የትናንትናህ መቃብር ውስጥ ነው - ሞቷል! በተቃራኒው፣ የነገህ ደግሞ በማህጸን ውስጥ ነው - ሊወለድ ተዘጋጅቷል! የትኛውን ትመርጣለህ? ለየጥኛው ትኖራለህ? የትናውን ስታሰላስል ታሳልፋለህ? ወደየትኛው አቅጣጫ መሄድ ትፈልጋለህ? ያለፈው ታሪክ አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ካለፈው ታሪክ ይልቅ የነገው ራእይህ ሲገዝፍ ሕይወት ወደፊት ትሄዳለች፡፡ ከመጣህበት ይልቅ የምትሄድበት ሲገዝፍ! ካለፈው ስቃይ ይልቅ ከዚያ በመማር የያዝከው የመለወጥ ሂደት ሲልቅ! ካለፈው ስኬት ይልቅ የነገው የላቀ ደረጃ ሲተልቅ! አስገራሚ ሕይወት!!! አስገራሚ የወደፊት!!! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623
20 97499Loading...
24
የስልጠና እድል! With Dr. Eyob Mamo ከሃገር ቤት ውጪ ለምትገኙ ሁሉ የተዘጋጀ በ Zoom የሚሰጥ የስልጠና እድል፡፡ ራእይ . . . • የተፈጠርንነትን የሕይወት ትርጉም የምናገኝበት . . . • ከተሰላቸንበት የሕይወት ዑደት የምንወጣበትና ወደ ዓላማችን አቅጣጫን የምንይዝበት . . . • ለራሳችን ብቻ ከመኖር ባሻገር በሌሎች ላይ ተጽእኖ የማምጣት መትረፍረፍ ውስጥ የምንገባበት . . . . . . ብቸኛው መንገድ! በማስወቂያ ፖስተሩ ላይ ባለው መረጃው መሰረት መመዝገብ ትችላላችሁ! አያምልጣችሁ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
31 82443Loading...
25
ልቆ የመገኘት ምርጫ (“ምርጫና ውሳኔ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ) አንደኛው ምርጫህ ለማድረግ የተጠየከውንና የሚጠበቅብህን ብቻ በማድረግ መወሰን ነው፡፡ ሌላኛው ምርጫህ ግን ከሚጠበቅብህና ከሚገባህ በላይ በማከናወን ልቆ መገኘት ነው፡፡ አንድ ሁለት ልጆች የነበሩት ገበሬ ነበረ፡፡ ሁለቱ ልጆቹ በእርሻ ስራው አይለዩትም ነበር፡፡ አባት ለታናሹ ልጁ የበለጠ ሃላፊነት ስለሚሰጠውና ስለሚያምነው ሁል ጊዜ ታላቅየው ጥያቄ ይፈጥርበት ነበር፡፡ አንድ ቀን አባት አምስት መቶ ብር በእጁ ላይ እንዳለውና፣ አምስት በጎችን እጁ ላይ ባለው የገንዘብ መጠን ቢያገኝ የመግዛት እቅድ እንዳለው ለታላቅ ልጁ እየነገረው ሳለ፣ ታላቅ ልጅ ይንን አጋጣሚ በመጠቀም ለምን ከእርሱ ይልቅ ለታናሹ የበለጠ ሃላፊነትን እንደሚሰጠው ጠየቀው፡፡ ይህንን ሲወያዩ ታናሽ ልጅ በዚያ አልነበረም፡፡ አባትም ቀጥተኛ መልስ ቢሰጠው ይገነዘበዋል ብሎ ስላላሰበ በብልሃት ሊያስተምረው ፈለገ፡፡ አባት ለታላቅ ልጁ፣ “እሰቲ እነዚያ ከብት የሚያረቡት ሰዎች ቤት ሂድና በግ ይሸጡ እንደሆነ አጣርተህ ተመለስ፣ ከዚያም ጥያቄህን እመልስልሃለሁ” አለው፡፡ ታላቅ ልጅ ሄዶ ተመለሰና፣ “አዎን የሚሸጡ በጎች አሏቸው” አለ፡፡ አባትም፣ “ሂድና ዋጋቸው ስንት እንደሆነ ጠይቅ” አለው፡፡ ልጅም ሄዶ መጣና፣ “ባለ 100 ብር በጎች አላቸው” አለው፡፡ አባት እንደገና፣ “ሂድና ነገውኑ በጎቹን ብንገዛቸው እኛ ድረስ ሊያመጡልን እንደሚችሉ ጠይቅ” አለው፡፡ ልጅም ሄዶ መጣና፣ “አዎን ይችላሉ” አለው፡፡ አባትም ታናሽ ወንድምህን ጥራው እስቲ አለው፡፡ ታናሽ ልጅ ሲመጣ አባት፣ “እስቲ እነዚያ ከብት የሚያረቡት ሰዎች ቤት ሂድና በግ ይሸጡ እንደሆነ አጣርተህ ተመለስ” አለው፡፡ ታናሽየው ሄዶ ተመለሰና፣ “ባለ 100 ብር፣ ጎችና እና ባለ 150 ብር በጎች አሏቸው፡፡ ነገውኑ ብንፈልግ ሊያመጡልን እንደሚችሉ ጠይቄ ተስማምተዋል” ብሎ ለአባቱ ነገረው፡፡ በመጨመርም፣ “ስለዚህ፣ የተለየ ሃሳብ ኖሮን ካልነገርኳቸው በስተቀር አምስት በጎችን በ100 ብር ሂሳብ ነገውኑ እንዲያመጡልን ተስማምቼአለሁ” አለው፡፡ አባት ወደታላቅ ልጁ ዘወር ብሎ ሲመለከት፣ ታላቅ ልጁ የራሱንና የታናሽ ወንድሙን መልስ በማሰነጻጸር ላይ እንዳለ ያስታውቅ ነበር፡፡ “አየህ ልጄ፣ አንተንና ታናሽ ወንድምህን የጠየኳችሁ አንድ አይነት ጥያቄ ነው፡፡ ያመጣችሁልኝ መረጃ ግን በጣም ይለያያል፡፡ አንተ ያችኑው የተጠየከውን ጥያቄ ነው ይዘህ የመጣኸው፡፡ ሌላ መረጃ ስፈልግ እንደገና ደጋግሜ መላክ ነበረብኝ፡፡ እርሱ ግን እኔ የፈለኩትን ፍላጎቴን በሚገባ በመረዳት የቻለውን ያህል መረጃ ይዞልኝ ነው የመጣው፣ ከተጠየቀውም በላይ ስራ ሰርቶ ነው የመጣው፡፡ ሁል ጊዜ ከአንተ ይልቅ ለእርሱ ሃላፊነትን የምሰጠው ለዚህ ነው፡፡” በማለት ቀድሞ ለጠየቀው ጥያቄ መልስን ሰጠው፡፡ ለነገሩ፣ ታላቅ ልጅ ገና መልሱ ሳይብራራ ገብቶት ነበር፡፡ የተባሉትንና የሚጠበቅባቸውን ብቻ አድርገው እጆቻቸውን የሚሰበስቡ ሰዎች ተግባርን በማከናወንና የተጠበቀባቸውን ነገር በማድረግ አንጻር ትክክለኛ ነገር አድርገዋል፡፡ በእድገት ልቆ ከመገኘት አንጻር ሲታይ ግን ባሉበት የሚረግጡ አይነት ሰዎች ናቸው፡፡ ይህ አይነቱ ምርጫ ሰዎች ሊያከናውኑ ከሚችሉት አቅማቸው በታች እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች በእድገትና በተቀባይነት አልፈዋቸው ሲሆዱ እያዩ “ለምን?” እያሉ ከመጠየቅ ያለፈ እድገት አይኖራቸውም፡፡ “ለምን ለሌሎች ያደላሉ? … ለምን ሰውን ይመርጣሉ? …” https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
18 101117Loading...
26
ልቆ የመገኘት ምርጫ
15 5079Loading...
27
አዲስ መጽሐፍ! በቅርብ ቀን ይጠብቁ! “የልጆች አስተዳደግ” በዶ/ር ኢዮብ ማሞ ልጆችን የማሳደጊያ ስኬታማ መመሪያዎች! ከመጽሐፉ መግቢያ የተወሰደ ትናንትና የነበረ እድል ዛሬ ያለመኖሩን ያህል ትናንትና የነበሩ ችግሮችም መልካቸውን ለውጠው ብቅ ይላሉ፡፡ ይህ እውነታ በልጆችም ሕይወት መንጸባረቁ የማይካድ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ልጆች የሚያጋጥማቸው እድሎች፣ ምርጫዎችና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ከመቸውም በበለጠ ሁኔታ ለወላጆች የቤት ስራ ሆኗል፡፡ ይህ የልጆች አስቸጋሪ ሁኔታ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ የወላጆች ሸክም መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ወላጆች የልጆቸውን የወደፊት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ በእነሱ እጅ እንደሆነ አምነው መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡ ልጆችን አስመልክቶ በአንድ ሃገር ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ተቋም ሊራው የማይችለውን ስራ የመስራት አቅሙም፣ እድሉም ሆነ ሃላፊነቱ ያለው በወላጆች ላይ ነው፡፡ በዚህች አነስተኛ መጽሐፍ ውስጥ ወላጆች በልጆቻቸውን ሁለንተናዊ እድገት ላይ ሊኖራቸው ስለሚገባ የመልካም ተጽእኖ ተሳትፎ በስፋት እንመለከታለን፡፡ የዚህ መጽሐፍ ዋና ዓላማ በልጆች አስተዳደግ ሂደት ላይ ወላጆች ሊያስቡባቸውና ራሳቸውን ሊሰለጥኑባቸው የሚገባቸውን ዋና ዋና ሃሳቦች መጠቆምና መሰረታዊ ግንዛቤን ማስጨበጥ ነው፡፡ የመጽሐፉ አወቃቀር ክፍል አንድ - ልጅ የመውለድ ጉዳይ ክፍል ሁለት - ልጆችን መቆጣጠር እና ማሳደግ ክፍል ሶስት - ልጆችን ማወቅ እና መቀበል ክፍል አራት - ልጆች የሚማሩባቸው መስኮች ክፍል አምስት - ልጆችን ማስተማር የሌለብን ነገሮች ክፍል ስድስት - የልጆችን ብልህነት መለየትና መደገፍ ክፍል ሰባት - ልጆችን ከመገፋት መጠበቅ ማጠቃለያ - የልጆችን ለውጥ መከታተል!
16 81065Loading...
28
ጠንካራው መልእክት! “በሚጮህ ድምጽና በጠንካራ ድምጽ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ” (ካታወቀ ምንጭ) የሚጮህ ሁሉ ጠንካራ አይደለም፤ ጠንካራ ሁሉ አይጮህም! ተገቢ ያልሆነን ነገር ለሚያደርግባችሁ ሰው የክልከላ መልእክትን ለማስተላለፍ የግድ መጮህ የለባችሁም፡፡ መልእክታችሁ ግን ጠንካራ መሆን አለበት፡፡ በሌላ አገላለጽ ጩኸት የጥንካሬ ምልክት አይደለም፡፡ እንዲያውም ሁል ጊዜ እየጮህን ስሜታችን ሲረግብ አሁንም ለሁኔታው ተጋላጭ ሆነን ራሳችንን የምናቀርብ ከሆነ ጩኸታችን የመልእክታችንን ደካማነት ነው የሚያሳየው፡፡ ይህንን ለማረም ከፈለግን ሳንጮህ ጠንካራ መልእክትን ማስተላለፍ እንችላለን፡፡ እንዴት? . . . 1. በትንሹም በትልቁም ስሜታዊ ባለመሆን አንዳንድ ነገሮችን ታግሶ ማለፍ፡፡ 2. ሰዎች የአካል፣ የስሜትና የስነ-ልቦና ጤንነታችንን አደጋ ላይ የሚጥልን ሁኔታ ሲያደርጉ ስሜታችንን በግልጽ ማሳወቅ፡፡ 3. በተግባር የማንደግፋቸውንና የማናሳያቸውን ስሜታዊነቶች በቃልና በአንደበት ከመናገር መቆጠብ፡፡ 4. በጨዋ ንግግራችን እና በተረጋጋ ስሜት የገለጽናቸውን አቋሞቻችንን በጠንካራ ተግባር ማሳየት፡፡ 5. ከሰዎቹ ዘላቂ የሆነንና በተግባር የሚታይ ለውጥን እስከምናገኝ ድረስ ከግንኙቱ ራሳችንን መጠበቅ፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
19 227106Loading...
29
ኃዘንተኛ ለመሆን ከፈለጋችሁ . . . ሃዘንተኛ ሰው ሆናችሁ መኖር ከፈለጋችሁ ቀላሉ መንገድ ሁልጊዜ፣ በሁሉም ቦታና በሁሉም ሁኔታ፣ ሁሉንም ሰው ለማስደሰት ሲጦዙ መኖር ነው፡፡ ማንም ሰው እንዳያዝንባችሁ፣ ቅር እንዳይሰኝባችሁን ሁል ጊዜ ሁሉም ሰው በእናንተ ሃሳብም ሆነ ተግባር ደስተኛ እንዲሆን የምትፈልጉ ከሆነ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ አደገኛ የስሜት ቀውስ ውስጥ መግባታችሁ አይቀርም፡፡ ጉዳዩ ግን ከዚያም ትንሽ ሰፋ ያለ ነው፡፡ ቀላላል እውነቶች . . . • ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚጦዝ ሰው ሰዎችን ለማስደሰት ሌላ ሌላውን ሲኖር ራሱን ሆኖ መኖር አይችልም፤ ራሱን ሆነ የማይኖር ሰው ደግሞ በፍጹም ደስተኛ መሆን አይችልም፡፡ • ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚጦዝ ሰው ለማስደሰት በሚፈልገው ሰው ቁጥጥር ስር ይውላል፤ ሰው ተቆጣጥሮ እንደፈለገ የሚያደርገው ሰው ደግሞ በፍጹም ደስተኛ መሆን አይችልም፡፡ • ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚሯሯጥ ሰው በየሰዓቱና በየቀኑ የሚለዋወጥ የስሜት ውጣውረድ (ሙድ) ውስጥ ራሱን ያገኘዋል፤ ስሜቱ (ሙዱ) በየጊዜው የሚለዋወጥ ሰው ደግሞ በፍጹም ደስተኛ መሆን አይችልም፡፡ • ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚጦዝ ሰው “ሰዎችን ያስደስትልኛል” ከሚለው ሃሳብ አንጻር እንጂ ከዓላማ አንጻር መኖር አይችልም፤ ከዓላማ ውጪ የሚኖር ሰው ደግሞ ደስተኛ መሆን አይችልም፡፡ በሕይወታችሁ ሰዎችን ማስደሰት እጅግ ደስታን የሚሰጥ ልምምድ መሆኑን ማስመራችንን ሳንዘነጋ፣ የሕይወታችሁ ዋና ዓላማ ግን ማንም ሰው ቅር እንዳይሰኝባችሁ፣ በክፉ እንዳያስባችሁ፣ እንዳያወራባችሁ፣ እንዳይገፋችሁ . . . ከሆነ የዚህች ምድር አጭር እድሜያችሁን በኃዘን የምታሳልፉ ሰዎች ናቸው፡፡ በመጨረሻም፣ ሁሉንም ሰው ማስደሰት እንደማይቻል ትደርሱበትና ያን ጊዜ ደግሞ ያንን የማይቻል ነገር ለመቻል ስትጦዙ ዓመታቶቻችሁን ስላባከናችሁ በመቆጨት ታዝናላችሁ፡፡ በሉ እንግዲህ፣ ማድረግ ወደምትችሉትና ወደሚገባችሁ እውነታ ተመለሱ! ማድረግ የምትችሉት፣ በገባችሁና በአቅማችሁ መጠን ለራሳችሁ ጨዋ ኑሮን መኖር፣ ለሰዎች ደግሞ መልካም ሰው መሆንና ሁልጊዜ ከስህተት ለመታረም የተዘጋጀ ልቦና ማዳበር መሆኑን አትዘንጉ፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
22 751138Loading...
30
ኃዘንተኛ ለመሆን ከፈለጋችሁ . . .
18 5955Loading...
31
መስማማት ሲቻል! (ትምህርት በፈገግታ) ባልና ሚስቱ እጅግ በከረረ ጸብ ተጣልተውና ተኮራርፈው ነው ያመሹት፡፡ ሚስትየው ሻወር ውስጥ እያለች፣ ባልየው፣ “ጠዋት የውጪ ሃገር በረራ ስላለብኝ በ12፡00 ሰዓት ቀስቅሺኝ” የሚል መልእክት ወረቀት ላይ ጽፎላት ራስጌዋ ጋር አድርጎላት እንዳኮረፈ ተኛ፡፡ ጠዋት እንቅልፍ ጥሎት የበረራው ሰዓት አልፎ ነቃና የጻፈላትን መልእክት ችላ ስላለች በብስጭት ቀድማ ወደነቃችው ወደሚሰቱ ሊሄድ ሲነሳ ራስጌው ጋር፣ “12፡00 ሰዓት ሆኗልና ተነሳ” የሚል መልእክት ወረቀት ላይ ተጽፎ አገኘ፡፡ ከዚህ ሁሉ መስማማቱ አይሻልም???!!! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
19 342108Loading...
32
Coming Soon ! በዶ/ር ኢዮብ ማሞ የሚሰጥ ወሳኝ የስልጠኛ እድል - ርዕስ፡- “በራእይ የሚመራ ሕይወት” "የራሳችን ዓላማ ከሌለን የሌላን ሰው ዓላማ እንዳስፈጸምን ኖረን እናልፋለን!" የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ • የራእይን ትክክለኛ ትርጉም ለይቶ ለማወቅ! • የግልን ራእይ ግልጽና ተግባራዊ በሆነ መልኩ ለመቅረጽ! • የግልን ራእይ ለማሳካት መከተል የሚገባንን ሂደቶች በሚገባ ለመገንዘብ! • ከሌሎች ሰልጣኞች ጋር በመገናኘት የእነሱን ልምድ ለመከፋፈል! • ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ በግል በመገናኘት ኮቺንግ ለመቀበልና ለጥያቄዎቻችን መልስን ለማግኘት! ለስድስት ቅዳሜ ጠዋቶች ብቻ! ለጥራት ሲባል የሰልጣኞች ቁጥር ከ50 በታች የተገደበ! ሙሉ መረጃውን በቅርብ ቀን ይጠብቁ!
18 67338Loading...
33
ተሳስታችኋል! • አንድ ሰው ትቷችሁ ስለሄደ ብቻ ከዚያ ሰው ውጪ መኖር እንደማትችሉ የምታስቡ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!! • አንድ ሰው ስለጎዳችሁ ብቻ ሰው ሁሉ ሊጎዳችሁ እንደሚችል ወደማመን ፍርሃት የመጣችሁ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!! • አንድና ሁለት ነገሮች ስላልተሳኩላችሁ ብቻ ስኬተ-ቢስ እንደሆናችሁ አምናችሁ ተቀብላችሁ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!! • ፈተናን ስለወደቃችሁ ብቻ ውዳቂ እንደሆናቸው ወደማሰብ መጥታችሁ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!! • አንድ ሰው ወይም ሁኔታ ስላስቆሟችሁ ብቻ ወደፊት መቀጠል እንደማትችሉ ወደማመን ዝቅታ ወርዳችሁ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!! ፈጣሪ የሰጣችሁ ሕይወት ከየእለት የልምምድ ውጣ-ውረዳችሁ በላይ ነች . . . ሰዎች ከሚያደርጉባችሁ፣ ከሚያስቡባችሁና ከሚያወሩባችሁ በላይ ነች . . . ከሆነላችሁና ካልሆነላችሁ ነገር በላይ ነች . . . ከተሳካውና ካልተሳካው ነገር በላይ ነች! ሕይወታችሁ የሚሽከረከረው ከሰዎችና ከሁኔታዎች መለዋወጥ አንጻር ወደሆነ ሕይወት የወረዳችሁ ጊዜ የስህተትን ሁሉ ትልቅ ስህተት እንደሰራችሁ አትዘንጉ፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
20 232163Loading...
34
ጥያቄ፡- ሰላም ዶክተር፡፡ ማግባት እፈልጋለው ለትዳር እሚሆን ወንድ አጣሁ። የሚቀርቡኝ ወንዶች በሙሉ ምክንያቱን ሳይነግሩኝ ይለዩኛል፡፡ መጥፎ ሰው ግን አደለሁም። አሁን አሁንማ ማንም አይጠይቀኝም ምን ይሻለኛል? መልስ፡- አሁን ባለንበት ወቅት ትክክለኛና እስከ ትዳር የሚዘልቅ ፍቅረኛ ማግኘት ትንሽ ከበድ እያለ መምጣቱን ሁላችንም እንስማማበታለን ብዬ አስባለሁ፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ዘርፈ-ብዙ በመሆኑ እዚህ ለመዘርዘር ያስቸግራል፡፡ አንደኛውን ምክንያት ለመጠቆም ያህል፣ ጋብቻንና መሰል ማሕበራዊ ሂደቶችን አስመልክቶ የተለያዩ ፍልስፍናዎችና ንጽረተ-ዓለሞች እየተስፋፉ በመሄዳቸውና አንድ ወጥ ምልከታ እየቀረ በመሆኑ ነው፡፡ የትዳር አጋር ማግኘት ከባድ የሆነባቸው ምክንያቶች በርካታ የመሆናቸው እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ እንደማንኛውም ማሕበራዊ ግንኙነት የሚያገኙን ሰዎች ሁሉ በእኛ ላይ ያላቸው አመለካከትና የሚያሳዩን ሁኔታ ተመሳሳይ ሲሆን ከሁሉም በፊት ራሳችንን ነው መጠየቅ ያለብን፡፡ ከመልክና ከቁመና ስንጀምር፣ ሁሉም ሰው የማይቀበለው መልክና ቁመና አለ ብዬ አላስብም፡፡ ለአንዱ የሚስበው ለሌላው አይስበውም፤ ለአንዱ ግድ የማይሰጠውን ሁኔታ ደግሞ ሌላው የሚመኘው አይነት ይሆናል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ሰው የአንቺን አካላዊ ሁኔታ አይቀበለውም ለማለት አስቸጋሪ ነው፡፡ ምንም እንከን ሳይኖርሽ የትዳር አጋር ያላገኘሽበት ተፈጥሯዊ ሂደት ሊኖር መቻሉ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ምናልባት አብዛኛው ወንድ ስጋት እንዲያድርበት የሚያደርግ ሁኔታ አቀራረብ እንዳይኖረሽ ለማየት ሞክሪ፡፡ 1. መስፈርት ማብዛት - አንዳንድ ሴቶች ከወንድ የሚጠብቁት መስፈርት ቢሰበሰብ በአንድ ሰው ላይ ሊገኝ እስከማይችል ድረስ ብዙና ከባድ ነው፡፡ የገንዘቡ፣ የእውቀቱ፣ የቁመናው፣ የአመለካከቱ፣ የራእዩ፣ የሴት አያያዙ . . . መስፈርት ሲበዛ ወንዶችን ሊያርቅ ይችላል፡፡ 2. ነገር አክራሪ መሆን - አንዳንድ ሴቶች መካበድ የሌለበትን ነገር በማካበድና በማክረር ወንዶች እንዲርቋቸው ያደርጋሉ፡፡ 3. ገና እንደተገናኙ የአቋም መግለጫ ማብዛት - አንዳንድ ሴቶች እንዲረግላቸው የሚፈልጉትና የማይፈልጉት ነገር ብዛቱ ብቻ ሳይሆን ገና በትውውቅ ጊዜ በአንድ ላይ ተዘርግፎ መነገሩ ወንድን ያርቀዋል፡፡ 4. አጉል ጠንካራነት - አንዳንድ ሴቶች ከልክ ያለፈ ኮስታሮች፣ ጠንካሮች፣ በወንድና በሴት መካከል ምንም አይነት ልዩነት እንደሌለ (እኩልነትን ወይም የበላይነትን) ለማሳየት የሚሞክሩ አይነት ባህሪይን ሲኖቸውና ያንን ሲያንጻበርቁ ወንድን ሊያሸሹ ይችላሉ፡፡ 5. ለራስ አለመጠንቀቅ - አንዳንድ ሴቶች “እኔን የሚፈልግ ሰው ቢያምርብኝም ባያምርብኝም እንዳለሁኝ ሊቀበለኝ ይገባል” የሚል መነሻው ትክክለኛ የሆነን፣ ነገር ግን እንደወረደ ተግባራዊ ከሆነ ወንዶችን ሊያርቅ የሚችል አመለካከት አላቸው፡፡ ራስን መሆንና ራስን አለመንከባከብ ግን የተለያዩ እንደሆኑ ሊያስቡ ይገባል፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
22 655150Loading...
35
ማግባት እፈልጋለው ለትዳር እሚሆን ወንድ አጣሁ።
19 6425Loading...
36
“ቆልፎ ያስቀረኝ ጽሑፍ!” ሳይጀመር የተደመደመ ሕይወት ከሶስት አመት በፊት አንድ የአርባ አመት እድሜ ላይ የነበረ ሰው ሳማክረው፣ የሚሰራውን የስራ አይነት ከገለጠልኝ በኋላ እንዲህ ሲል አጫወተኝ፡- “የምሰራውን ስራ አልወደውም፣ ምክንያቱም በእጄ ላይ ብዙ ሞያዎች እያሉኝ ስራዬ ግን ምንም ሞያ የማይጠይቅና ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ የማያልፍ ክፍያ የሚከፍል ነው፡፡ በዚህ ስራ ከተሰማራሁ አስራ ሁለት አመቴ ነው፡፡ አሁን ግን እጅግ መረረኝ”፡፡ ይህንን ንግግሩን ካደመጥኩ በኋላ በመጀመሪያ የጠየኩት ጥያቄ፣ “ለምን በዚህ ስራ ይህንን ያህል አመት ለመቆየት ፈለክ?” የሚል ነበር፡፡ “በፍላጎት ነው ብለህ ነው?!” አለኝ፣ አንገቱን በማቀርቀር፡፡ “ታዲያ በምንድን ነው?” አልኩት፣ ከተል አድርጌ፡፡ እርሱም በግልጽነት ለምን በዚያ ስራ እንደከረመ በግልጽ ነገረኝ፡፡ “ገና በሃያዎቹ መጨረሻ እድሜዬ ላይ አንድ ቀን በመንገድ ቆሜ ያንኑ ስራዬን እንዴት መቀየር እንዳለብኝ በማሰላሰል ላይ ሳለሁ ነፋስ ያባረረው አንድ የመጽሔት ቁራጭ ፊቴ ደረሰ፡፡ ማንበብ ስለምወድ አነሳሁትና ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ሳይቀደድ የተረፈው ክፍል ርእስ እንዲህ የሚል ነበር፣ `የሚሆነው ይሆናል፣ የማይሆነው ደግሞ አይሆንም`፡፡ ቀልቤን ሳበኝና ማንበብ ቀጠልኩ፡፡ በወቅቱ የሚበላኝን የሕይወቴን ሁኔታ እንዳከከልኝ ተሰማኝ”፡፡ ትንሽ በዝምታ ከተዋጠ በኋላ መናገሩን ቀጠለ፡፡ “ጽሁፉን ሙሉውን ሳነበው የሚናገረው የአንድ ሰው ፍጻሜ ገና ሳይወለድ የተወሰነና የተደመደመ እንደሆነ፣ ሁሉም ሰው ሕይወት የሚያቀብለውን የቅድመ-ውሳኔ ገጠመኝ ከመቀበልና ከመኖርና ውጪ ምንም ማድረግ እንደማይችል ነው፡፡ በጣም ደነገጥኩኝ፡፡ ጽሑፉ ባለሁበት ኖሬ፣ በዚሁ ሁኔታ ከማለፍ ውጪ ምንም ብታገል የተመደበልኝን መለወጥ እንደማልችል በደንብ አድርጎ አሳመነኝ፡፡ አለቀ! ከእለት ጉርስ ለማያሻግር ስራ ሰክኜ ለአመታት የመቆየቴ ሁኔታ የተቀበልኩት የመጣው ያንን ጽሑፍ ካነበብኩኝ በኋላ ነው፡፡” “ለምን የጽሑፉን ሃሳብ ዝም ብለህ አምነህ ተቀበልከው” አልኩት፡፡ ሲመልስልኝም፣ “እኔ ቤተሰቦቼ ማን እንደሆኑ የማላውቅ፣ እድሜዬን ሁሉ ብቻዬን ታግዬ የኖርኩ ሰው ነኝ፡፡ ራሴንና ኑሮዬን ለመለወጥ የሞከርኩ፣ ነገር ግን ሁሉም ነገር አልለወጥ ብሎ ያስቸገረኝ ሰው እንደሆንኩ ቀድሞውኑ አስብ ስለነበረ ጽሑፉ ያንኑ ዝንባሌዬን አጠናከረውና አመንኩት፡፡” ከዚህ ንግግራችን በኋላ ከእሱ ጋር ብዙ የምክክር ጊዜ አሳልፈናል፡፡ አሁን አመለካከቱን፣ ራሱንና ስራውን ለውጦ እንዲያውም ሌሎችን መካሪና ደጋፊ ሆኗል፡፡ በቅርቡ ሳገኘው ያየሁበት ለውጥ አስገራሚ ነው፡፡ ይህንን ታሪኩንም በጽሑፌ እንዳካፍልም ፈቀደልኝ፡፡ የሚኖሩት ኑሮ አንዴ የተወሰነና ሊለወጥ የማይችል እንደሆነ የሚያስቡ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ ፈረንጆቹ ይህንን አመለካከት fatalistic attitude ይሉታል፡፡ ያለቀለትና ቅድመ-ድምዳሜ ተወስኖለት የተጀመረ ሕይወት እንዳለን ማመንን የሚጠቁም ሃሳብ ነው፡፡ ይህ አይነቱ አመለካከት ያላቸው ሰዎች በሕይወታቸው ያለውን ምንም ነገር ለመቀየር አቅሙ እንደሌላቸው ነው የሚያስቡት፡፡ የወቅቱ ኑሯቸው ሁኔታ ለእነሱ የተመደበና ምንም ቢታገሉ ሊለወጥ እንደማይችል ያስባሉ፡፡ ስለዚህም የነበረውንና ያለውን በመቀበል ያዘግማሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች በዙሪያቸው ብዙ ሰዎች በማለም፣ በመስራትና በማመን ሕወታቸውን ሲለውጡ እያዩ እንኳን ንቅንቅ አይሉም፡፡ ምክንያቱም እነዚያኞቹ በሕይወታቸው የሚያዩት ለውጥም ሳይቀር ቀድሞውኑ ለእነሱ የተወሰነላቸው እንደሆነ ስለሚስቡ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ራስን ለማሻሻል ምንም አይነት መነሳሳት ስማይኖራቸው የመጣላቸውን እየተቀበሉና ያንኑ እየኖሩ ዘመናቸውን ይጨርሳሉ፡፡ ሕይወት ግን እንደዚያ አይደለችም፡፡ ሕይወት የምርጫ መስክ ነች፡፡ ሕይወት የዘራነውን የምናበቅልባት መሬት ነች፡፡ ሕይወት ፈቃዳችንን፣ ጉልበታችንንና ሌሎችንም እሴቶቻችንን አስተባብረን ከአንድ ደረጃ ወደሌላኛው ደረጃ እንደመሰላል የምንወጣት የምታጓጓ መስክ ናት እንጂ ታሪካቸው ተጽፎና አልቆ ያከተመለትና ፍጻሜ የተበየነባቸው ሰዎች መተራመሻ አይደለችም . . . https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
20 691119Loading...
37
“ቆልፎ ያስቀረኝ ጽሑፍ!” ሳይጀመር የተደመደመ ሕይወት
17 28011Loading...
38
የሕይወት ዋጋው ስንት ነው? አንድ ልጅ አብሮ የሚውላቸው አቻዎቹ ሁል ጊዜ እያቃለሉና እንደተራ ሰው እየቆጠሩት ይቸገር ነበር፡፡ አንድ ቀን ወደ አባቱ ሄደና “አባዬ የሕይወት ዋጋው ስንት ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡ አባቱ በማይረሳ ምሳሌ ሊያስተምረው ስለፈለገ፣ አንድ ከረጅም አመታት በፊት በብዙ ብር ገዝቶ ያስቀመጠውን ብዙም ተፈልጎ የማይገኝ የከበረ ድንጋይ (precious stone) በእጁ ሰጠውና ይህንን የከበረ ድንጋይ ይዘህ ወደ ሶስት ቦታዎች በየተራ ሂድ፡፡ በመጀመሪያ፣ መንደር ውስጥ ያለ ገበያ ሂድና እዚያ ስትደርስ በአንድ እጅህ የከበረውን ድንጋይ ይዘህ በማሳየት ሌላኛው እጅህን ከፍ አድርገህ ሁለት ጣቶችህን አሳያቸው፡፡ ያንን ስታደርግ የሚነገሩህን ዋጋ ስማና ምንም መልስ ሳትሰጥ ሂድ፡፡ በመቀጠልም፣ ይህንንው ተግባር በአካባቢያችን ወዳለው የከበሩ ድንጋዮች ወደሚታዩበት ሚውዚየም ድገመው፡፡ በመጨረሻም ይህንኑ ተግባር ከሚውዚዬሙ አልፍ ብሎ ወደሚገኘው ውድ የተባሉ የከበሩ ድንጋዮች ወደሚሸጥበት ሱቅ ሂድና ድገመው አለው ልጁ እደተነገረው ገበያ ሄደና ድንጋዩን በአንድ እጁ አቅርቦ በሌላ እጁ ሁለት ጣቶቹን ከፍ አድርጎ ሲያሳይ አንድ ሴት እየሮጠች መጣችና፣ “2 ብር ከሆነ አሁኑኑ ከፍዬ እወስደዋለሁ” አለችው፡፡ ልጁም እንደተነገረው መልስ ሳይሰጥ ትቶ ሄደ፡፡ በመቀጠልም ወደ ሚውዚየሙ ሄደና ድንጋዩን በአንድ እጁ አቅርቦ በሌላ እጁ ሁለት ጣቶቹን ከፍ አድርጎ ሲያሳይ አንድ ጎልማሳ ፈጥ መጣና፣ “200 ብር ከሆነ አሁኑኑ እወስደዋለሁ” አለው፡፡ ልጁም እንደተነገረው መልስ ሳይሰጥ ትቶ ሄደ፡፡ በመጨረሻም የከበረ ድጋይ መሸጫ ሱቅ ሄደና ድንጋዩን በአንድ እጁ አቅርቦ በሌላ እጁ ሁለት ጣቶቹን ከፍ አድርጎ ሲያሳይ በእድሜ ጠና ያሉት የሱቁ ባለቤት፣ “ይሄንን ብዙም ተፈልጎ የማይገኝ የከበረ ድንጋይ ከየት አገኘኸው፡፡ 2 ሚሊየን ከሆነ አሁኑኑ እወስደዋለሁ” አሉት፡፡ ልጁም ወደ አባቱ ተመለሰ፡፡ አባቱ ጋር መጥቶ ያጋጠመውን ሲነግረው፣ አባትዬው የሕይወት ዋጋው ልክ እንደዚህ ነው፡፡ የዚህን የከበረ ድንጋይ ዋጋ በዚህ መልኩ ከፍና ዝቅ ያደረገው ያቀረብክበት ቦታ እንደሆነ ሁሉ፣ አንተም ራስህን ያቀረብክለት ቦታና ሰው ዋጋህን ወይ ከፍ ወይም ዝቅ ያደረገዋል፡፡ ምርጫው ያንተ ነው፡፡ ውድ አንባቢዎቼ፣ እንደተግባባን ተስፋ አደርለሁ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
24 963226Loading...
39
የሕይወት ዋጋው ስንት ነው?
21 24322Loading...
40
ያለፈው ታሪክ ጉዳይ! “ያለፈውን ታሪክ ያላወቁ ሰዎች ያንንው ታሪክ ከመድገም ውጪ ሌላ ምንም ምርጫ የላቸውም” – Unknown Source የቤተሰቦቻችሁን ያለፈ ታሪክ በሚገባ አጥኑና ከእሱ ተማሩ! መልካሙንና የተሳካውን አሻሽሉት፡፡ ጤና-ቢሱንና ያልተሳካውን አትድገሙት! የመሪዎቻችሁን (የሃገር፣ የሕብረተሰብ፣ የኃይማኖት . . . ) ያለፈ ታሪክ በሚገባ አጥኑና ከእሱ ተማሩ! መልካሙንና የተሳካውን አሻሽሉት፡፡ ጤና-ቢሱንና ያልተሳካውን አትድገሙት! እናንተ ዛሬ የምትከተሉትን ዓላማ (ስራ፣ ንግድ፣ ራእይ . . . ) ከዚህ በፊት ያራመዱ ሰዎችን ያለፈ ታሪክ በሚገባ አጥኑና ከእሱ ተማሩ! መልካሙንና የተሳካውን አሻሽሉት፡፡ ጤና-ቢሱንና ያልተሳካውን አትድገሙት! ከዚህ በፊት ሞክራችሁት አልሄድ ያለውንና አሁንም እንደገና ለማሳካት የምትታገሉትን ሁኔታ ያለፈ ታሪክ በሚገባ አጥኑና ከእራሳችሁ ጉዞ ተማሩ! መልካሙንና የተሳካውን አሻሽሉት፡፡ ጤና-ቢሱንና ያልተሳካውን አትድገሙ! ከትናንት ውጪ ዛሬ የለም! ከዛሬ ውጪ ነገ አይኖርም! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
25 89093Loading...
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች! እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Show all...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

99👍 28🎉 4🤩 2
Show all...

29👍 11
Photo unavailableShow in Telegram
ብቁ ናችሁ! ከሕይወት ትልልቅ የፍርሃት ምንጮች አንዱ “ብቁ ያለመሆን” ፍርሃት ነው፡፡ በሰዎች ለመወደድ፣ ለመፈቀር፣ ተቀባይነት ለማግኘት፣ ለማወቅ፣ ለመሰልጠን፣ እድገት ለማግኘት . . .ብቁ እንዳልሆንን የማሰብ ፍርሃት! እውነት እውነቱን እንነጋገር፡፡ አንድ ሰው እናንተን ለመቀበልና ለመውደድ የማይችል ወይም የማይፈልግ ከሆነ፣ ይህ ማለት እናንተ የዚያ ሰው አይደላችሁም ማለት ነው - አለቀ! ይህ ማለት ግን የዓለም መጨረሻ ነው ማለት አይደለም፡፡ ይህ ሰው እናንተን የመቀበልና የመውደድ ብቃቱ ወይም ፍላጎቱ የለውም ማለት ነው እንጂ እናንተ ተቀባይነት የማግኘትና የመወደድ ብቃቱና ማንነቱ የላችሁም ማለት አይደለም፡፡ እናንተን የመውደድም ሆነ የመቀበል ብቃቱና ፍላጎቱ ያለው ብዙ ሰው በዙሪያችሁ እንዳለ አስታውሱ፡፡ እነሱን ለማየትና ለመገናኘት ግን “ካልተቀበለኝና ከልወደደኝ” ብላችሁ ችክ ካላችሁት ሰው ላይ አይናችሁን ማንሳት፣ ስሜታችሁንም ማላቀቅ የግድ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ለጊዜው ከባድ ነው፣ ነገር ግን በሚልየን የሚቆጠሩ ሰዎች ችለውታልና እናንተም ትችላላችሁ! አንድ ነገር አልሆን ሲላችሁ ሁል ጊዜ እናንተ ለዚያ ነገር ብቁ ስላልሆናችሁ እንደሆነ የማሰብን የእሳቤ ንድፍ መቀየር አለባችሁ፡፡ በዚያ ምትክ ያ ሰውም ሆነ ሁኔታ ለእናንተ የማይመጥን ስለሆነ እንደቀረላችሁ ማሰብም አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜም እንዳለ አትዘንጉ፡፡ በአጭሩ፣ ለመወደድ ብቁ ናችሁ! ለማደግ ብቁ ናችሁ! ለማወቅ ብቁ ናችሁ! በዚህ ዓለም ፈጣሪ ለሰው ልጆች ደስታና ስኬት ለፈጠረው መልካም ነገር ሁሉ ብቁ ናችሁ! ሕይወት ትክክለኛውን ሰውና ስፍራ ገልጣ እስከምታቀርብላችሁ ድረስ ግን ራሳችሁን በመቀበል የድርሻችሁን መወጣት የግድ ነው፡፡ https://t.me/Dreyob
Show all...
160👍 100🔥 7😁 2🎉 2🤩 2
Photo unavailableShow in Telegram
በጥራት ማደግ! ሁለት አይነት እድገቶችና ትልቅነቶች አሉ፡፡ አንደኛው ውጫዊ እድገትና ትልቅነት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” ነው፡፡ 1. ውጫዊ እድገትና ትልቅነት ሰዎች በገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣ በዝና፣ በስልጣን እና በመሳሰሉት ነገሮች ሲያድጉ፣ “ውጫዊ እድገትና ትልቅነት” አገኙ እንለዋለን፡፡ ይህ እድገትና ትልቅነት ምንም እንኳን በራሱ ምንም ችግር ባይኖረውና እንዲያውም ለጥቅም የሚውል ቢሆንም ብቻውን ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ 2. “ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” ሰዎች በመልካም ስብእና፣ በጤናማ አመለካከት፣ በስሜት ብልህነት፣ በራእይ እና በጥበብ ሲያድጉ፣ “ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” አገኙ እንለዋለን፡፡ ይህ እድገትና ትልቅነት ከማንኛውም ነገር በፊት ሊቀድም የሚገባው የእድገትና የትልቅነት ዘርፍ ነው፡፡ አንድ ሰው ከላይ የተጠቀሱትን አይነት ውጫዊ እድገትንና ትልቅንን እያስመሰዘገ ውስጣዊ እድገት ሲጎድለው ከራሱ ሕይወት ጀምሮ እስከ ቤተሰቡ፣ የስራ ስምሪቱና በሃገር ደረጃ የሚያስከትለው ቀውስ ይህ ነው አይባለም፡፡ የገንዘብ አቅሙን ለማይረባ ነገርና ለሕገ-ወጥ ተግባር የሚጠቀም ማነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን? በዝናውና በታዋቂነቱ የሚኩራራውና ሰውን የሚንቀው ማን ነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን? በስልጣኑ ተጠቅሞ ሰውን የሚደቁስና እንደፈለገ የሚሆን ማን ነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን? በመጀመሪያ በውስጣችን እንደግ! ከሁሉም በፊት በጥራትና በብቃት ትልቅ እንሁን! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Show all...
142👍 89🔥 7😱 1
Show all...

22👍 15
Show all...

15👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
ያስቸገረኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር! ተወልዶ ካደገበት ሃገሩ በተፈጠሩ ማሕበራዊ ቀውሶች ምክንያት ወደሌላ ሃገር በስደት ለመሄድ የቆረጠ አንድ ሰው ረጅም፣ አድካሚና አስፈሪ የሆነን በረሃ ለቀናት በእግሩ በመሄድ ካቋረጠ በኋላ እጅግ ደክሞና ዝሎ ነበር፡፡ በመጨረሻም በደረሰበት አንዲት ከተማ ውስጥ በተሰጠው እርዳታ ትንሽ አገገመ፡፡ የዚህን ሰው ጉዞ የሰማና ለሕብረተሰቡ ለማቅረብ የፈለገ አንድ ጋዜጠኛ አገኘውና አንድን ጥያቄ ጠየቀው፡፡ “ተጉዘህ የመጣኸው በረሃ ብዙ ሰው የማይደፍረው በረሃ ነው፡፡ ለመሆኑ በመንገድህ ላይ በጣም የጎዳህና ያስቸገረህ ውኃ ጥም ነበር? ምግብ ማጣት ነበር? አውሬ ነበር? ሽፍቶች ነበሩ? ወይስ . . . ? የዚህ ስደተኛ መልስ ለጋዜጤኛው ያልተጠበቀ ነበር፡፡ በዚህ አደገኛ በረሃ አቋርጬ ስመጣ በጣም ያስቸገሩኝ የጠቀስካቸው ትልልቅ ነገሮች አልነበሩም፡፡ ጉዞየን በጣም አድካሚና አስቸጋሪ ያደረገብኝ በእርምጃዬ ወቅት ጫማዬ ውስጥ እየገባ የሚቆረቁረኝና አላራምድ ያለኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር፡፡ የሕይወት ጉዞም እንዲሁ ነው! አብዛኛውን ጊዜ የሚያስቸግረን፣ የሚቆረቁረን፣ አላራምድ የሚለንና ከዓላማችን የሚጎትተን ችግር ትልልቁ አይደለም፡፡ በየቀኑ የሚያጋጥሙን ጥቃቅን “አሸዋዎች” ናቸው፡፡ ትንንሽ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ባህሪይ፣ ትንንሽና አናሳ ወሬን የሚያወሩ ሰዎች ሁኔታ፣ ትንንሽና ስሜትን የሚነካኩ የየቀን ገጠመኞች . . . ጉዟችንን አዳጋችና አድካሚ ያደርጉታል፡፡ “በትንንሽ” ሰዎችና ሁኔታዎች ሳትበገሩ ትልቁ የሕይወት ስእልና ዓላማችሁ ላይ በማተኮር ወደፊት መገስገስን ያወቃችሁበት ጊዜ ዋናውን የሕይወት ድል የተጎናጸፋችሁበት ጊዜ ነው፡፡ በርቱ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623
Show all...
👍 224 86🔥 14😁 1😱 1
ከኢትዮጵያ ውጪ ለምትኖሩ በዚህ ሊንክ ግቡና ተመዝገቡ ክፍያውንም እዛው ላይ እንዴት እንደምትከፍሉ ይነግራል:: ኢትዬጽያ ለምትኖሩ ይህ ስልጠና የሚሰጥበት ሰአት ለናንተ ሌሊት ስለሚሆን ላይመች ይችላል:: https://forms.gle/NkcpF5jQwrUVVf47A
Show all...
Dr Eyob's Vision class registration form

Fill out the form completely and submit

👍 36😱 3
Repost from Dr. Eyob Mamo
Photo unavailableShow in Telegram
የስልጠና እድል! With Dr. Eyob Mamo ከሃገር ቤት ውጪ ለምትገኙ ሁሉ የተዘጋጀ በ Zoom የሚሰጥ የስልጠና እድል፡፡ ራእይ . . . • የተፈጠርንነትን የሕይወት ትርጉም የምናገኝበት . . . • ከተሰላቸንበት የሕይወት ዑደት የምንወጣበትና ወደ ዓላማችን አቅጣጫን የምንይዝበት . . . • ለራሳችን ብቻ ከመኖር ባሻገር በሌሎች ላይ ተጽእኖ የማምጣት መትረፍረፍ ውስጥ የምንገባበት . . . . . . ብቸኛው መንገድ! በማስወቂያ ፖስተሩ ላይ ባለው መረጃው መሰረት መመዝገብ ትችላላችሁ! አያምልጣችሁ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Show all...
👍 54 9😱 2😁 1
Repost from Dr. Eyob Mamo
Photo unavailableShow in Telegram
መፍራትን አትፍራው! እንደ ፍርሃት፣ ድንጋጤና ስጋት አይነት ስሜቶች ሰው ከአደጋ እንዲጠነቀቅ ከፈጣሪው የተሰጡ ስጦታዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ስሜቶች በአግባቡ ልንጠቀምባቸውና ከአደጋ ልንጠበቅባቸው ሲገባን ለአንዳንድ ሰዎች የኑሮ ዘይቤ ሆነዋል፡፡ የመውደቅ ፍርሃት፣ የመክሰር ፍርሃት፣ ያለመወደድ ፍርሃት፣ ብቻ የመቅረት ፍርሃት፣ … ጣጣችን ብዙ ነው፡፡ በፍርሃት ስንወረስ፣ ሕይወታችንን በራእይ መምራት እናቆምና ለፍርሃት ምላሽ በመስጠት መምራት እንጀምራለን፡፡ ከአንዱ ራእይ ወደሌላኛው በማለፍ ሕይወትን “ልናጠቃት” ሲገባን የመጣው ሁሉ የኑሮ ገጠመኝ የሚያጠቃን ቋሚ ኢላማዎች እንሆናለን፡፡ ቆመን ለመጣው ወይም የመጣ ለመሰለን ጥቃት ምላሽ በመስጠት ጊዜአችንን እናባክናለን፡፡ ይህ ሲሆን የቆመ ኢላማ ሆንን ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው ከአንዱ ግብ ወደሌላኛው በአላማ የምንንቀሳቀስ ሰዎች ስንሆን አይኖቻችን ከችግሩ ላይ ይነሱና መፍትሄው ላይ ማረፍ ይጀምራሉ፡፡ የፍርሃትህ ጥልቀት አእምሮህ የፈቀደለት ያህል ነው” - Unknown Source ፍርሃት በሕይወትህ ብቅ ጥልቅ ማለቱ አያስፈራህ፡፡ በዚያ ፍርሃት ምክንያት ግን መንቀሳቀስ እስኪያቅትህ ድረስ እንዳትታሰር ፍራ፡፡ ማንኛውም ሁኔታ አንተን የማስፈራራት ሙከራ የማድረግ ሙሉ መብት አለው፡፡ አንተ ካልፈቀድክለት ግን ሊያስፈራራህ አይችልም፡፡ ትፈራለህ፣ ፈሪ ግን አይደለህም፡፡ “በፍጹም አልፈራም” ብለህ ካሰብክና ከተናገርክ ከፍርሃት የተደበቅህ ሰው እንደሆንክ አመልካች ነው፡፡ በሌላ አባባል፣ የፍርሃት ስሜት እንዳይመጣ መከልከል አትችልም፣ ይህንን ስሜት ለማስተናገድ የተፈጠረ ማንነት ስላለህ፡፡ ሆኖም፣ የፍርሃትን ጥልቀትና በአንተ ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ጉዳት የመወሰን ሙሉ መብትም ሆነ ብቃት አለህ፡፡ https://t.me/Dreyob
Show all...
👍 104 45🤩 9🔥 5🎉 3