cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

ፍልስፍና  እውነትን በመፈለግ- ሀሳዊ እምነቶችን በማጋለጥ እና ጭፍን አመለካከቶችን በጥበብ በመመርመር ወደ ላቀ አሰተሳሰብ ያሻግራል። በዚህ ቻናል አለም ላይ ያሉ ፍልስፍናዎች ፤ ርዕዮት አለሞች ፤  ሀይሞኖቶች እና አስተሳሰቦች በነፃነት ይዳሰሳሉ።

Show more
Advertising posts
19 984
Subscribers
+16424 hours
+4437 days
+59430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ነፃ ነፃነት... ...የቀጠለ 🔥[ከቂም ነፃ አይደለንም]… ስለት የቆረጠው ጣትህ ደም እስከመች ነው ይፈስ ዘንድ የምትተወው?… ነገር የጓጎጠው ልብህስ ገላ እስከመች ነው ይቆስል ዘንድ ችላ የምትለው?… የጣትህ ደም ፍሰት አንተ ችላ ብትለውም በደምህ ውስጥ ያሉት ፕላትሌትስ ከየቦታው ተጠራርተው በሚሰሩት ግድብ /Blood clotting/ ይቋረጣል… የልብህ ቁስል ግን ፈቅደህ በምትሰጠው ይቅርታ እንጂ በሌላ መንገድ አይጠግም… ይቅርታ ከሚደረግለት በላይ ለአድራጊው የሚሰጠው ሰላም ትልቅ ነው… ቂመኛ ስትሆን በዳዬ ያልከውን ባየህ አልያም ባሰብክ ቁጥር በደሉ ከደረሰብህ የአንድ ጊዜ ሁነት በላይ ደጋግመህ ትታመማለህ… ይቅር ስትል ግና ከመጀመሪያው ቁስልም ትፈወሳለህ… ያልኖርክበትን ዘመን ጠቅሰህ የለውጥን እርሾ ነው የክፋትን ቁርሾ የምታሻትተው?… የትናንትን በደል ቆጥረህ በግመል ሽንት ነው በቀስት አቅጣጫ ጉዞህን የምትቃኘው?… ቅድመ አያትህ ለአያትህ ያሻገረውን ክፋት ትተህ ጥበቡን ቀምር፣ አያትህ ለአባትህ የተወውን ጠብመንጃ ጥለህ ሞፈሩን አንሳ፣ ከአባትህ የፍቅር ታሪክ ለልጅህ ጦማር አዘጋጅ… ‘ስታልፍ’ የሚነበበው ታሪክህ እርሱ ብቻ ነውና… ~~~ 🔥ከጥበቃ ነፃ አይደለንም  በአገኘዋለሁ ተስፋ ውስጥ እንደታሰርን አለን… በይመጣል ጥበቃ ውስጥ እንደታበትን አለን… ለኑረት አንዳች አበርክቶ የሌለው ሁሉ ቁጭ ብሎ ይጠብቃል… ከሰማይ ይጠብቃል… ከምድር ይጠብቃል… ከወዳጁ ይጠብቃል… ከመንግስት ይጠብቃል… ከጥበቃ ነፃ ስላይደለ ግምቱ ፍርሽ ሲሆንበት ይበሳጫል… ከሌሎች የሚጠበቀውን ልክ አበጅቶ “ከአንተ አይጠበቅም” ይላል… ደግሞ ወዲህ የሚጠብቀውን የማያውቅም አለ… ሳሙኤል ቤኬት አንድ ጊዜ “Waiting for Godot” የሚል አብሰርድ ድራማ ጽፎ ነበር… በድራማው ውስጥ የሚታዩት ሁለት ገጸባሕሪያት ካሉበት ጭንቅ ያወጣቸው ዘንድ In the middle of nowhere ቆመው የማያውቁትን አንድ ነገር ሲጠብቁ ይታያል… ተጠባቂው ሲመጣ ባይታይም እነርሱ ግን ጥበቃቸውን አያቋርጡም… አንደኛው ገጸባሕሪ በመሰላቸት “Nothing happens, nobody comes, nobody goes, it’s awful!” ይላል… ያም ሆኖ ቀረ ብለው አይንቀሳቀሱም… ምክንያቱም ጎዶትን እየጠበቁ ነው… ESTRAGON – Let’s go. VLADIMIR – We can’t. ESTRAGON – Why not? VLADIMIR – We’re waiting for Godot. … የድራማው ፀሐፊ አንድ ጊዜ በጋዜጠኛ ተጠየቀ፡ “ጎዶት ማን ነው?”… ቤኬት መለሰ፡ “እኔም አላውቀውም” ማድረግ የምትችለውን ሁሉ ማድረግ ነፃነት አይደለም… ከአድራጊነትህ ጋር ኃላፊነት አለ… ተግባርህ የሌሎችን ጉዳት ካስከተለ ከፀፀት አትነፃም… እንዳሻህ መናገር ወይም መፃፍ ነፃነት አይደለም… ቃልህ የአብሮ መኖር ሚዛን ካዛባ አልያም ጎራ ለይቶ ደም ካቃባ ከተጠያቂነት አትድንም… ነፃነት ብቻነትም አይደለም… ኑረት ለሌሎች ባለን አበርክቶት እንጂ በራስ ደሴት ጡዘት ከቴም አትሞላም… ነፃነት እንደልቡ መኖር አይደለም… እንደ ደንቡ መመላለስ እንጂ… እህስ… ኦርጅናሌው ነፃነት የልጅነት ንጽሕና ይመስለኛል!! እንደልጅ ልጅነት – እንደ ሕፃን ‘ጅልነት’ የመኖር ድፍረት… የልጅነት ዓለም ከራሱ ከ’ነፃነትም’ ነፃ ያወጣል… ነፃ ነኝ ከሚለው ባዶ እምነትም ጭምር… ልጅነት ነፃነትን ይኖራታል እንጂ አያነፃጽራትም… ነፃ ነኝ አይደለሁም ውዝግብ የሌለበት ኑረት ነው ‘ነፃ ነፃነት’… የሚኖሩት ግን የማያስቡት… ከራስ ውስጥ የሚወልዱት… ፈቅዶ የሚቸርህ አልያም ከፍቶ የሚነሳህ የሌለበት እውነት ነው ነፃነት… ይህ ነፃነት ከሰንሰለት ስርም ሆነ ከግዞት መሃል ሆነህ ልታጣጥመው ትችላለህ… ከደቋሽ ክንድና አደፍራሽ ሁከት ሳትርቅም ልትኖረው ትችላለህ… ምክንያቱም ‘ነፃ’ ነፃነት ነውና… ብዙ ፍቅር!! ሰላም!! @Zephilosophy @Zephilosophy
Show all...
ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ @zephilosophy ⚜በዙሪያችን ያለው ደመና በውስጣችን ያለውን ጸሐይ ከልሎታል… የየዕለታችን አመድ የመነሻችንን ፍም አዳፍኖታል… የአስተዳደጋችን ቅኝት የዕይታ አድማሳችንን ከልሎታል፣ የአስተምሯችን ስሪት፣ የየቤተእምነታችን መሰረት፣ የአካባቢ፣ የሃገር፣ የሚዲያና የአብሮ ውሎ ሸንጓችን ጨለማ የማንነታችንን ግዝፈት ውጦታል… ትልቁን ምስል ለማየት ስለተሳነን ባየነው ልክ ራሳችንን ሰርተናል… በምልዓት ማየት ስላልጀመርን ለሽንቁር ማንነት ራሳችንን አሳልፈን ሰጥተናል… ነባሩን ዘዬ ስላልፈተሽን አዲስ መንገድ ማየት አቅቶናል… የነገሩንን ስላመንን የሆነውን መጠየቅ ትተናል… አይቻልም ስላሉን አለመደፈሩን ተቀብለናል… እናም ዛሬ ታላቁ ማንነታችን በጥልቅ ጨለማ ውስጥ ተኝቷል … @zephilosophy @zephilosophy
Show all...
ነፃነት!! ደምስ ሰይፉ “ነፃ ሆነን ብንፈጠርም በየሄድንበት እንደታሰርን ነው” ይላል ሩሶ… “Man is born free, and everywhere he is in chains. One man thinks himself the master of others, but remains more of a slave than they are.” ~ Jean Jacques Rousseau … ይህን ጥቅስ ለረጅም ጊዜ አብሰልስዬዋለሁ… በርከት ላሉ ጊዜያትም በነፃነት የትርጉም ፈለጌ ላይ ተጋድሞ ማለፊያ ነስቶኝ ያውቃል… ‘ነፃ ነኝ’ ብዬ ባሰብኩ ቁጥር ድንገት ከች ይልና የተተበተብኩበትን ድር ያሳየኛል… ምንም ጥያቄ የለውም – አባባሉ እውነት ነው… እንዲያውም በነፃነት ትርጓሜያችን፣ በአማናዊው ነፃነትና በኑሮአችን መሃል ያለውን ተምታቶሽ ሰከን ብለን እንድናይ የሚረዳን ታዛም ይመስለኛል… ~ ስለ ነፃ ንግግር፣ ስለ ነፃ ጽሑፍ፣ ስለ ነፃ አስተሳሰብ… ወዘተ ከሚሰብከው ዘመነኛ ብያኔ በፊትም ሆነ አሁን ነፃነት አለ… ልዩነቱ የትርጓሜና ግንዛቤ ብቻ ይመሰለኛል… ትርጉምና አረዳዳችን ከግለሰባዊ ተሞክሮአችን ደጃፍ ሳይሆን ከውጪያዊው ቅኝት አፍ ስለሚቀዳ እውነቱና ትርክቱ ሳይገናኝ ይኖራል… እርግጥ ነፃነትም እንደበርካታዎቹ እሳቤዎች የግለሰቦች መረዳት ጥላ ስለሚያጠላበት ወጥ ትርጓሜ እንዲኖረው አይጠበቅም… የትርጉም ማጠንጠኛው ውጪያዊ ጫና ላይ ሲንጠለጠል ግን ነፃነት ‘ነፃ’ መሆኑ ይቀራል… ~ የምንም ነገር ትርጉም ‘ይህ ብቻ ነው’ በሚል ዶግማ ውስጥ ሲታጠር ነፃነት ያሳጣል… ዶግማዊነት አጥር አበጅቶ ከመስክ እውነት መፋታትን ያነግሳል… ልክ ‘ጉድጓድ ውስጥ ተቀምጦ የጉድጓዱ አፍ ከሚፈቅደው ስፋት በላይ ሰማዩን እንዳለማዋቅ’… ራስህን ወደ አንድ አጥር ከወረወርክ በኋላ ከአጥሩ ማዶ ላለው ኑረት እውቅና ያለመስጠት ንፍገት እንጂ ‘እዚያስ ቤት ምን አለ’ የሚል በጎነት አይስተዋልብህም… እዚህም ነፃነት አለ… ~ የነፃ መሆን አለመሆን ነገር አወዛጋቢ ነው… ለአንተ ነፃነት የሆነ ነገር ለሌላው ‘መታሰር’ ሊሆን ይችላል… ያንቺ የባርነት ጥግ ለሌላዋ የነፃነት ጠገግ ሊሆን ይችላል… አንዳንዴ ነፃ ወጣን ባልንበት ነገር ተመስጠን የነገርየው ሎሌ የመሆን ዕጣ ሊወድቅብን ይችላል… የሆነው ሁሉ ሆኖ ግን፡- 🔥[ከማሰብ ነፃ አይደለንም]… ማሰብን ትልቅ ቁምነገር የሚያደርገው ማሕበረሰባዊ ግንዛቤያችን ሰውን ከማሽን ለይቶ አያይም… በቀን ውስጥ ከሰባ ሺህ በላይ የሃሳብ ሰበዝ አዕምሮአችንን ሲያባትል እንደሚውል ስናስብና ስንቱን ሃሳብ ፈቅደን እንደምናስብ ስንጠይቅ የነፃነት ነገር ይገባናል… የሃሳብ ፈለጋችን ሲሶው እንኳ በገዛ ፈቃዳችን አይተለምም… እግረ አዕምሮአችን በደረሰበት የምንደርስ እንጂ የፈቀድነውን የምናስስ አይደለንም… ሰው በትክክል የሃሳብ ማሽኑ ባሪያ ነው… በአዕምሮችን ላይ እንሰለጥን ዘንድ ገና ነፃ አልወጣንም!!… ነፃ ከሆንክ አዕምሮህን ፀጥ አድርገው… ~ 🔥[ከስሜት ነፃ አልወጣንም]… በሚግለበለብ የስሜት እሳትና ከስሎ ሲያበቃ በሚያምድ ፀፀት መሃል ስንታኘክ የምንውለው ለዚህ ነው… ለበርካታዎቹ የስሜት ጥያቄዎቻችንን የእምቢታ ድፍረት የለንም… ስሜት ግዘፍ ነስቶ ከክፉ ግብረ መልሱ ጋር ሲያጋትረን ነው ልክ ያለመሆን እምነት ሆድ ሆዳችንን የሚበላው… ስሜቱን በሚያስተናግደውና በስሜቱ ምላሽ በሚቆጨው እኔነት መሃል ልዩነት ኖሮ አይደለም ሰበብና ድርጊት የተለያየ አቀባበል የቆያቸው – እኛ በስሜት ላይ ስላልሰለጠንን እንጂ… ከስሜቱ አንድ ስንዝር የቀደመ ሰው ከስሜቱ ምስ ከሚለጥቁ እልፍ ኪሎሜትሮች ድካም ይድናል… 🔥[ከነኝታ ነፃ አይደለንም]… ‘ እንዲህ ነኝ’ – ‘እንዲያ ነኝ’ ስትል የምትውለው ከነኝታህ ተጽዕኖ መላቀቅ ባለመቻልህ ነው… ነኝታህ ከመሆንታህ ይበልጥብሃል… የሆንከው ግን ነኝ ከምትለው የማይናጸር ጥልቅ ነው… ነኝታህ የመሆንታህን ብርሃን ያደበዝዛል… ነኝታህ ከጎሳህ፣ ከስራህ፣ ከችሎታህ፣ ከሃብትህ፣ ሐይማኖትህ… ወዘተ ይመነጫል… መሆንታህ ግና የአማናዊው ተፈጥሮህ መሰረት ነው… The essence of who you are in the deepest level. አግዮስ፣ ንዑድ፣ ክቡር፣ ጽሩይ… ነኝ የምትለውን ሁሉ አውልቀህ ብትጥል ምን የሚቀር ይመስልሃል?… ምንም!… መሆንታው ላይ የቆመ ግና ያልሆነው ስለሌለ ነኝ የሚለው አይኖረውም… የሚያጣው ስለሌለው ባዶነት አይሰማውም… ~ @zephilosophy
Show all...
የድርሻህን ተወጣ "Be the change that you wish to see in the world.” Mahatme Gandhi "የማቀርብልህ ትልቅ ጥያቄ አለኝ፡- የተሻለች አዲስ ዓለም ለመፍጠር ይቻል ዘንድ  የበኩልህን ምን ዓይነት አስተዋጽኦ እያበረከትህ ነው?» ሁሉን  ነገር በፖለቲከኞቹ ላይ ብቻ እያሳበብክ ነው አሊያም በዙሪያህ ባሉት ሰዎች ላይ ወይስ በወላጆጅህ እና በአስተዳደግህ እያማረርክህ ነው፡፡ ይህን ማድረግ ራስህን እንደ ሰለባ መቁጠር ይሆናል፤ ምጡቅ አእምሮአዊ ችሎታቸውን በማጋራት ታላቅ ለውጥ መፍጠር ሲችሉ ራሳቸውን ሰላባ አድርገው በመቁጠር ጊዜያቸውን በሚያባክኑ ሰዎች ዓለም የተሞላች ነች፡፡ እማሆይ ቴሬዛ ግሩም አድርገው ገልጸውታል ‹‹እያንዳንዳችን የየራሳችን ደጃፍ ብናጸዳ ድፍን ዓለም ንጹሕ ይሆን ነበር፡፡» በሌሎች ማሳሰብ ራሰን ማዳከም ነው፡፡ አንተ ተጽእኖ ልትፈጥር እንደማትችል ለራስህ መንገር ኃይልህን ማምከን ነው። በከፊል እርቃኑን ሆኖ የሚዞር ‹‹ማሕተመ ጋንዲ› የተባላ ደቃቃ ሰው ድፍን ሕንድን ነፃ አውጥቷል፡፡ ሮዛ ፓርክስ ተብላ የምትጠራ ሴት በአውቶብስ ላይ የተቀመጠችበትን ወንበር ለነጭ ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆኗ የጥቁሮችን መብት ለማስከበር የተደረገ ታላቅ የተቃውሞ እንቅስቃሴን ለኩሳለች፡፡ ‹‹ተራ› ሰዎች እጅግ ልዩ ነገሮችን ለመፈጸም ይችላሉ፡፡ የ«The Body Shop›› መሥራች አኒታ ሮዲክ የተናገረችው ያስደምመኛል፡- «ተጽእኖ ለመፍጠር የማትችል ትንሽ ፍጡር እንደሆንክ  የምታስብ ከሆነ ቢንቢ ባለበት ክፍል ውስጥ ለመተኛት ሞክር፡፡» ከሕይወትህ፣ ከተቀጠርክበት ድርጅት ወይም ከምትኖርበት ሀገር የማትወድደው ነገር ምንድር ነው? ዝርዝር አዘጋጅ፡፡ በጽሑፍ አሥፍረው፡፡ ድምፅህን ከፍ አድርገህ ተናገረው፡፡ ከዚያም ነገሮችን ለማሻሻል አንዳች ነገር አድርግ፡፡ ከትንሽ አሊያም ትልቅ እርምጃ ከመውሰድ መጀመር ትችላለህ፡፡ ምርጫህን የመወስን ኃይልህን በተግባር ስትገልፅ ኃይልህ ይበዛል። ተጽእኖ ለመፍጠር በምትችልበት አድማስ ውስጥ ሆነህ ነገሮችን የተሻሉ ለማድረግ ስትጥር ተጽእኖ የምታሳድርበት አድማስ ይሰፋል፡፡ ስለሆነም፣ ከአሁን ጀምሮ የድርሻህን ተወጣ፡፡ አንተ የድርሻህን ስትወጣ ምድሪቱ የተሻለች ሥፍራ ትሆናለች፡፡ጋንዲ እንዳለው "በዓለም አንተ ልታየው የምትፈልገውን ለውጥ ራስህ ኹነው።አለም ላይ ሰላም ፣ ፍቅር እንዲኖር ከፈለክ አፍቃሪ እና ሰላማዊ በመሆን ከራስህ ጀምር" ✍️ሮቢን ሻርማ ሌላውን ለማስተማር በቅንነት #ሼር አድርጉ @zephilosophy
Show all...
ግሩም_ትረካ_የካህሊል_ጂብራን_ህይወት_እና_ሥራዎች[email protected]30.18 MB
ሞትን የምንፈራው ስምንድነው? ምንጭ ፦ ውስጣዊን ማንነት ማወቅ (ክሪሽናሙርቲ) ትርጉም ፦ ተስፋሁን ምትኩ ወደ መሬት የምትወድቅ ቅጠል ሞትን የምትፈራ ይመስላችኋል? አንዲት ወፍ ሞትን እየፈራች የምትኖር ይመስላችኋል? ሞት ሲመጣ በፀጋ ትቀበለዋለች እንጂ ስለእሱ አትጨነቅም፡፡ ህይወቷን የምታሳልፈው በመኖር፣ ነፍሳትን በማደን፣ ጎጆ በመስራት፣ በማዜም፣ መብረር ስለሚያስደስት ብቻ በመብረር ነው። አዕዋፋት ክንፎቻቸውን ሳያማቱ በነፋሱ እየተገፉ ብቻ ሲበርሩ አይታችሁ አታውቁም? እንዴት ያለ ሃሴት እያደርጉ ነው! ስለሞት አይጨነቁም፡፡ ሞት ከመጣ መልካም ነው፤ በቃ፡፡ ሳይጨነቁ ነው የሚኖሩት፣ አይደለም እንዴ? እኛ ሰዎች ነን ስንኖር ሁልጊዜ ስለሞት የምንጨነቀው፡፡ ታድያ እየኖርን አይደለንም፤ እየሞትን እንጂ፡፡ አዛውንቶች ወደ መቃብራቸው ተጠግተዋል፡፡ ወጣቶችም ሩቅ አይደሉም፡፡ የምናውቀውን፣ የሰበሰብናቸውን ነገሮች እንዳናጣ ስለምንፈራ የሞት ነገር ያሰጋናል። ባላችንን ወይም ሚስታችንን፣ ልጃችንን ወይም ጓደኞቻችንን እንዳናጣ እንፈራለን፤ የተማርነውን፣ ያጠራቀምነውን እንዳናጣ እንፈራለን፡፡ የሰበሰብነውን ነገር በሙሉ - ጓደኞቻችንን፣ ንብረቶቻችንን፣ ጠባዮቻችንን -ይዘን መሄድ ብንችል ኖሮ ሞትን አንፈራም ነበር፡፡ ለዛም ነው ስለ ሞትና ከዚያ በኋላ ስለሚመጣው ነገር ንድፈ - ሃሳቦችን የፈጠርነው፡፡ እውነታው ግን ሞት እርግጠኛ መሆኑ ነው። አብዛኞቻችን  ከሚታወቀው ... መነጠል አንፈልግም፡፡ ከሚታወቀው ጋር ሙጭጭ ማለታችን ደግሞ ፍርሀት ፈጥሮብናል። የማይታወቀው በሚታወቀው አይታይም። በሚታወቀው የተገነባው አእምሮ ግን  "ሊያበቃልኝ ነው" ይላል - ስለዚህም ይፈራል። ስለነገ ሳትጨነቁ፣ ስለነገ ሳታስቡ የአሁኗን ቅፅበት መኖር ብትችሉ -ይህ ማለት ግን በዛሬ ብቻ ተጠመዱ ማለት አይደለም- የሚታወቀውን ጠቅላላ ሂደት ብታውቁ የሚታወቀውን ትተዉና አስደናቂ ነገር ሲከሰት ታስተውላላችሁ፡፡ ለአንድ ቀን ሞክሩት - የምታውቁትን ነገር በሙሉ እርሱት፣ ወደጉን አስቀምጡትና ምን እንደሚከሰት ተመልከቱ፡፡ ስጋታችሁን ከቀን ወደ ቀን፣ ከሰዓት ወደሰዓት ፣ ከቅፅበት ወደቅፅበት ተሸክማችሁት አትዙሩ፣ አራግፉት፡፡ ይህን ጊዜ ከዚያ ነፃነት እጅግ የተለየ፣ ኑሮና ሞትን ያቀፈ ህይወት ሲወለድ ታያላችሁ፡፡ ሞት የአንድ ነገር መጨረሻ ነው፡፡ ከመጨረሻው በኋላ ደግሞ መታደስ አለ:: @Zephilosophy @Zephilosophy
Show all...
<<ቅናት ከንጽጽራዊ ባህሪ የሚመነጭ ተረፈ ምርት ነው» ምንጭ ፦ ሁለንተና (ኦሾ) ትርጉም ፦ አባድር ቅናት የሚመነጨው ከንጽጽርና ከውድድር ነው፡፡ ከልጅነታችን ጀምሮ እያነጻጸርንና እየተነጻጸርን መኖር ለምደናል። ስንማረው ኖረናል፡፡ የሆነ ሰው የተሻለ ቤት አለው። ሌላው ውብ የሆነ ሰውነት ይኖረዋል። አንዳንዱ ከሌላው የበለጠ ገንዘብ አለው፡፡ ሌላኛው ደግሞ መስህብ ያለው ሰብእና ባለቤት ነው... እነዚህን ነገሮች እየተመለከትንና ከእነዚህ ሰዎች ጋር እራሳችንን እያነጻጸርን ነው የኖርነው፡፡ አሁንም ይህንን ተነጻጻሪነት እየገፋችሁበት እራሳችሁን በሌላው አካል መመዘኑን ከቀጠላችሁበት ውጤቱ ቅናት ይሆናል። ቅናት ከንጽጽራዊ ባህሪ የሚመነጭ ተረፈ ምርት ነው። እራሳችሁን ማነጻጸር ካቆማችሁ ግን የቅናት ስሜታችሁ ሙሉ ለሙሉ ይጠፋል። እራሳችሁን እንጂ ሌላኛውን አካል እንዳልሆናችሁ ስትረዱ ንጽጽር የሚባለው ነገር ይቆማል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ተረፈ ምርቶችም ያበቃላቸዋል። እራሳችሁን ከዛፎች ጋር ማወዳደር የለባችሁም። ካወዳደራችሁ ግን እኔስ ለምን አረንጓዴ አልሆንኩም የሚል ከፍተኛ የቅናት ስሜት ይሰማችኋል። አምላክ ለዛፎቹ የቸራቸውን አበባ ስለምን ለእኔ ነፈገኝ የሚል አይነት ስሜት ያድርባችኋል። እራሳችሁን ከወፎች ከወንዞችና ከተራራዎች ጋር ካነጻጸራችሁ ደግሞ ቅናታችሁ ከሚፈጥርባችሁ የስቃይ ጭነት የተነሳ ከነአካቴው መኖር ይከብዳችኋል። እያንዳንዱ ሰው ልዩና ተነጻጻሪ ያልሆነ በመሆኑ ተነጻጻሪነት የማያስኬድ ባህሪ ነው። ሁሉም ሰው ልዩና የማይነጻጸር ነው። ማንም ሰው እራሱን እንጂ ሌላውን መሆን አይችልም፡፡ እራሱን በማያቋርጥ ሁኔታ ከሌላው ጋር የሚያነጻጽር ሰው ከራሱ በቀር ሁሉም ሰው ደስተኛ ይመስለዋል። በጎረቤቱ ግቢ ውስጥ ያለው ሳር እሱ ጋ ካለው በተሻለ እረንጓዴ እንደሆነ ያስባል፡፡ የጎረቤቱ ሚስት ውብ እንደሆነች በማሰብ እራሱን በቅናት ያንጨረጭራል። ጎረቤቱ ግን ይህን ጊዜ እንዴት ከሚስቱ ማምለጥ እንደሚችል እያሰበ ይሆናል። ሁሉም ሰው በሌላኛው ላይ ቀናተኛ ነው፡፡ በቅናት የተነሳ ይህንን የመሰለ ገሃነም መፍጠር ችለናል፡፡ አዛውንቱ ገበሬ ወንዙ ያስከተለውን ጉዳት ለስለስ ባለ ሁኔታ ሲቃኙ ቆዩና «ሂራም» ብለው ጎረቤታቸውን ጠሩት፡፡ ከጎረቤታቸው ያለው ገበሬ እንደደረሰም «ጅረቱ አሳማዎችህን ለቃቅሞ ወስዶዋቸዋል” አሉት፡፡ ጎረቤትየው የቶምሰንን አሳማዎችስ?›› ኣዛውንቱ ‹‹እነሱም በጅረቱ ተወስደዋል፡፡›› ጎረቤትየው «የላርሰንስ?›› አዛውንቱ ««እርሱም እንደዛው» ጎረቤትየው ««አፎይ» ሲል - በረዥሙ ተነፈሰና «እንግዲያውስ ያሰብኩትን ያህል መጥፎ አይደለማ፡፡» ሁሉም ሰው ችግር ውስጥ ከሆነ ጥሩ ስሜት ይፈጠራል። እያንዳንዱ ሰው ያለውን እያጣ ከሆነ ጥሩ ስሜት ይፈጠራል፡፡ ሁሉም ሰው ስኬታማና ደስተኛ ከሆነ ግን ጎምዛዛ የሆነ ስሜት ይፈጠራል። ለምንድን ነው ሌላኛውን የመመልከት ስሜት ውስጥ ሊሰርጽ የቻለው? ምክንያቱም የራሳችሁን ውስጣዊ ቡራኬ እንዲጎመራ አላደረጋችሁትም፡፡ ውስጠታዊው ህልውናችሁ እንዲያብብ አላደረጋችሁትም፡፡ ስለዚህ ውስጣችሁን ስትመለከቱት ባዶነት ይሰማችሁና የእያንዳንዱን ሰው ውጫዊ ገጽታ መመልከት ትጀምራላችሁ። የእራሱን ውስጣዊ ገጽታና የሌላውን ውጫዊ ገፅታ የሚመለከት ሰው ከፍተኛ ቅናት ይፈጠርበታል፡፡ ምክንያቱም የሁሉም ሰው ውጫዊ ገጽታ በፈገግታ የደመቀ ነው፡፡ ሁሉም ከውጭ የሚያሳየው ፈገግታ ከውስጡ የሚካሄደውን ነገር እንዳይታይ ይጋርድለታል፡፡ የሁሉም ሰው ውጫዊ ፈገግታ ውስጠቱ ባዶ እንደሆነ ለሚያስብ ሰው ስቃይን ይፈጥራል፡፡ አንድ በሱፊዎች ዘንድ የሚነገር ታሪክ አለ፡፡ አንድ በስቃይ የተሞላ ህይወትን የሚመራ ሰው ነበር:: ሰውዬው ወደ አምላኩ በሚጸልይበት ወቅት ሁሉ «ሁሉም ሰው ደስተኛ ሆኖ ለምን እኔ ብቻ እሰቃያለሁ? ለምን እኔ ብቻ?» ይል ነበር፡፡ አንድ ቀን ጥልቅ በሆነ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ ለአምላኩ ጸለየ፡፡ ‹‹አምላኬ የማንኛውንም ሰው ስቃይ ብትስጠኝ ልቀበል ዝግጁ ነኝ፡፡ እባክህ! እባክህ ጌታዬ የእኔን ግን ውሰድልኝ፡፡ ከዚህ በላይ ልሸከመው አልችልም›› ሲል ተማጸነ፡፡ ጸሎቱን ጨርሶ እንደተኛ ውብ የሆነ ህልም አየ። በህልሙ ውስጥ አምላክ ሰማይ ላይ ተከሰተና እንዲህ ሲል ተናገረ። ‹‹ስቃያችሁን ሁሉ ወደ ቤተ መቅደሱ አምጡ፡፡» እያንዳንዱ ሰው የየራሱ ስቃይ የታከተው ስለነበር በተለያዩ ወቅቶች <<የማንኛውንም ሰው ስቃይ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ፡፡ የእኔን ግን ውሰድልኝ። ከዚህ በላይ መሸከም አልችልም››  ብሎ ይጸልይ ነበር። እንደተባለው ሁሉም ሰው ስቃዩን በቦርሳ አጭቆ ወደ ቤተ መቅደሱ አመራ፡፡ ባለታሪኩን ጨምሮ ሁሉም ሰው ጸሎቱ አምላኩ ዘንድ ተቀባይነት ስላገኘ በስፍራው ላይ ከፍተኛ የደስታ ስሜት ነገሰ፡፡ ሁሉም ሰው ከቤተ መቅደሱ ሲደርስ አምላክ እንዲህ ሲል እወጀ፡፡ ‹‹ቦርሳችሁን ከግድግዳው ስር አስቀምጡት ሁሉም ሰው ቦርሳውን አስቀምጦ ከጨረሰ በኋላ አምላክ እንዲህ ሲል በድጋሚ አወጀ፡፡ «አሁን መምረጥ ትችላላችሁ። ማንኛውም ሰው የፈለገውን ቦርሳ መውሰድ ይችላል፡፡›› በጣም አስገራሚው ነገር ቀን ከሌት ሲጸልይ የነበረው ሰውዬ ሌላ ሰው ቦርሳውን እንዳያነሳበት እየተጣደፈ ወደ ቦርሳው ሮጠ። ሁሉም ሰው እንደ ሰውዬው የየራሱን ስቃይ ያጨቀበትን ቦርሳ ፍለጋ ተራወጠ፡፡ እያንዳንዱ ሰው የየራሱን ስቃይ በድጋሚ ለመሸከም ዝግጁ ነበር፡፡ ምንድን ነበር የተከሰተው? በህይወታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ አንዳቸው የሌላቸውን ችግር ስቃይና መከራ ተመለከቱ፡፡ አንዳውም እራሳቸው ከያዙት ቦርሳዎች የሚበላልጡ የሌሎችን ሰዎች በስቃይ የታጨቁ ትልልቅ ቦርሳዎች እንዳሉ ተገነዘቡ፡፡ በተጨማሪ ሁሉም ሰው ከራሱ ስቃይና መከራ ጋር ተላምዷል። የራሱን ስቃይ ማባበልና መቻል ይችላል፡፡ የሌላውን ሰው የመከራ ቦርሳ ቢወስድ ግን ከቦርሳው ውስጥ ያለው አዲስ አይነት መከራ ምን አይነት እንደሆነ አያውቅም፡፡ ምናልባት የባሰም ሊሆን ይችላል፡፡ አላሚው ሰው ከእንቅልፉ ሲነቃ በድጋሚ ጸለየ፡፡ <<አምላኬ ስላሳየኸኝ ህልም አመሰግናለሁ፡፡ ከዚህ በኋላ እንዲህ አይነቱን ጥያቄ ደግሜ አልጠይቅህም፡፡ የሰጠኸኝን ነገር ሁሉ የሰጠኸኝ ለበጎ ነው። ለዛም ነው የሰጠኸኝ፡፡» የቅናት ስሜት ካለባችሁ በማያቋርጥ ስቃይ ውስጥ ትወድቃላችሁ። የምትቀኑ ከሆነ ሀሰተኛ ትሆናላችሁ፡፡ ማስመሰል ትጀምራላችሁ፡፡ ያልሆናችሁትን መስላችሁ ለመታየት ትሞክራላችሁ፡፡ የሆነ ሰው ጋር ኖሮ እናንተ ጋር የጎደለ ነገር ካለና ነገርዬውን ማግኘት የማትችሉ ከሆነ ከሰው ላለማነስ ብላችሁ የረከሱ ተተኪ ነገሮችን ማበጀት ትጀምራላችሁ። ለቀናተኛ ሰው ህይወት ሲኦል ትሆንበታለች። ስለዚህ ቀናተኛነታችሁ ይጠፋ ዘንድ እራሳችሁን ከሌላው ጋር ማነጻጸር አቁሙ። ይህን ስታደርጉ ያልሆናችሁትን መስላችሁ ለመታየት የምታደርጉትን ጥረትና ሌላውን ለማስመሰል የምታደርጉትን ሙከራ ታቆማላችሁ፡፡ ይኼ ሁሉ ሂደት የተሳመረ የሚሆነው ግን ውስጣዊውን ሀብታችሁን ማሳደግ ስትችሉ ነው። ለማደግ ጣሩ። ይበልጥ እውነተኛ ግለሰብ ለመሆን ሞክሩ። እራሳችሁን አፍቅሩ። ለእራሳችሁ ክብር ስጡ። ይህ ሲሆን የገነት በሮች ክፍት ይሆኑላችኋል። በእርግጥ ወደ በሮቹ ተመልክታችሁ ስለማታውቁ ነው እንጂ እስካሁንም በሮቹ ክፍት ነበሩ። @Zephilosophy @Zephilosophy
Show all...
ውስጣዊ ምሕንድስና (Inner Engineering) Sadhuguru ለመሆኑ አብዛኛው የሰው ልጅ ምንድነው የሚሰራው? ይበላል፣ ይተኛል፣ ይዋለድና ይሞታል፡፡ ብዙ ነገሮች ልትሰራ እንደምትችል ታምን ይሆናል፤ ግን የመሞቻህ ቅጽበት ሲደርስ ወደ ኋላ መለስ ብለህ ትመለከትና ስትሰራ የነበርካቸው ነገሮች በሙሉ የመኖር ሂደትህን ማወሳሰብ እንደነበረ ትረዳለህ፡፡ የሰው ልጅ እያንዳንዱ ትል፣ ነፍሳት፣ ውሻ፣ ድመትና ወፍ ሊያደርጉት የቻሉትን ቀላል የሕይወት ሂደት ማድረግ አልቻለም፡፡ የሰው ልጅ በሕይወቱ መጨረሻ በዙሪያው ባሉት ነገሮች ሁሉ የተጎዳ ይሆናል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ፣ ብዙ ሰዎች እድሜያቸው ሲገፋ ጥበበኛ አይሆኑም- የቆሰሉ እንጂ፡፡ እኛ በለውጥ ሂደት ውስጥ ነን፡፡ ምክንያቱም ይህ የሕይወት ተፈጥሮ ነው። ሁሉም ነገር ቀጣይነት ያለው የለውጥ ሂደት ነው፤ · እኛስ? በፕላኔታችን ላይ ያለ ነገር ሁሉ በለውጥ ሂደት ውስጥ ነው፡፡ አንተስ የለውጥ ሂደት ነህ? ይህ ትልቅ ጥያቄ ነው፤ ለዚህ ጥያቄ መልስህ አዎን የሚል ከሆነ፣ ምንም ችግር የለም፡፡ ከዚህም ከዚያም ጋር የምትቀላቅልና በየቀኑ ለምን እንደተቀላቀልክ አሳማኝ ምክንያት እየፈለግክ  ያለህ በራሱ የማይንቀሳቀስ ውሃ ከሆንክ፣ ተስፋ የለህም፡፡ በዚህች ፕላኔት ላይ ጊዜ የምታባክን ነህ፡፡ ጊዜ ማባከን ሲባል ሕይወትን ማባከን ማለት ነው፣ ምክንያቱም ሕይወትህ ጊዜ ነው፡፡ ሌላ ፍጥረት፣ ቅን ካልሆነ ሰው ይልቅ በደስታ ሊዘል ይችላል፡፡ አንተ ከሌሎች ፍጥረታት በበለጠ የተሻለ ነገር መስራት የማትችል ከሆነ፣ እጅግ ውድ ሕይወት መሆንህ ምንም ጥቅም የለውም፡፡ በጫካ ውስጥ ምንም አይነት ወጥ ቤት የለም፣ በውስጡ የሚኖሩት ግን በሚገባ ይመገባሉ። ዝሆንም ጫማ አድርጎ ሲራመድ አትመለከትም፤ እኛ ግን ለመብላት፣ ለመተኛት ለመራመድ፣ ከጫማ እስከ ልብሶች እንዲሁም እስከ ቤቶች ድረስ በሁሉም መንገድ እጅግ ብዙ ዝግጅቶች የሚያስፈልጉን እጅግ ውድ የሆንን ሕይወት ነን፡፡ ስለዚህ በዚህ ሁሉ ወጪ፣ ሌሎች ፍጥረታት ሊሰሩት ከሚችሉት የተሻለ ነገር መስራት ይገባናል።የመኖራችን ትርጉም በልቶ ከማደር የተሻለ ምክንያት ሊኖረው ይገባል። በእውነት ደህንነት ተሰምቶህ የሚያውቀው የተደሰትክ ጊዜ ነው፡፡ በአካልህ ላይ ህመም ቢኖር እንኳን ደስተኛ ከሆንክ ደህና እንደሆንክ ይሰማሃል። ደህንነት ማለት በመሰረታዊነት በሕይወት ውስጥ የተወሰነ ደረጃ ደስተኛ መሆን፣ ሐሴት ማድረግ ማለት ነው፡፡ ደስተኛ ሆነህ መኖር የምትፈልግ ከሆነ፣ በውስጥም ይሁን በውጪ አኗኗርህን፣ አካባቢህንና ራስህን በምታስተዳድርበት መጠን የተወሰነ ይሆናል፡፡ በመሰረታዊነት ሕይወት አስተዳደር ነው፡፡ አካልህን፣ አእምሮህን፣ ስሜትህንና ሁኔታዎችህን እንዴት መጠበቅ እንዳለብህ የማታውቅ ከሆነ፤ ሕይወትህ፣ ቤትህ፣ አካባቢህ፣ በዓለም ላይ  ያለ ህዝብ አጠቃላይ የሕይወትህ ጥራት የሚወሰነው ነገሮችን በራስህ ማስተዳደር በምትችልበት መጠን ነው፡፡ በአጠቃላይ ስለ አስተዳደር ስንነጋገር የምናስበው በአጠቃላይ ስለ ሕይወት ሳይሆን፣ ከኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች አንጻር ሆኗል ዛሬ በብዙ መንገዶች ሌሎቹ የሕይወት ገጽታዎች ወደ ጥግ ተገፍተው ፕላኔቷ ያለችበት ህግ ኢኮኖሚክስ መሆኑ የሚያሳዝን ነው፡፡ የሚገዛው ኢኮኖሚክስ ሲሆን፣ የምናስበው ኢኮኖሚክስ ብቻ ሲሆን፣ በብዙ  መንገዶች ያልታረምንና ደስታ የራቀን እንሆናለን፡፡ በሕይወታቸው ያልተሳካላቸው ሰዎች በውድቀታቸው እየተሰቃዩ ሲሆን፣ በሕይወታቸው ስኬታማ የሆኑ ሰዎች ደግሞ በስኬታቸው እየተሰቃዩ ነው፡፡ ውድቀት በቀላሉ የሚመጣ በመሆኑ በውድቀትህ መሰቃየት ምንም አይደለም፡፡ እየተሰቃየህ ያለኸው በስኬትህ ከሆነ ግን፣ ስኬት በቀላሉ የሚመጣ ነገር ባለመሆኑ ያ አሳዛኝ ነገር ነው፡፡ ስትሰራው _ የነበረው ነገር፣ ስትናፍቀው የነበረ ነገር፣ በሕይወትህ ውስጥ ልትፈጥረው ትፈልገው የነበረ ነገር፣ በተከሰተ ጊዜ፤ በዚያ መሰቃየት ከጀመርክ፣ ያ በሕይወት ውስጥ እውነተኛው አሳዛኝ ነገር ነው። በምድር ላይ ያሉ በጣም ብዙ ስኬታማ ሰዎች በስኬቶቻቸው እየተሰቃዩ ነው። በስኬታቸው እየተሰቃዩ ነው ሲባል፣ የአምስት አመት ልጅ ሳለህ ምን ያህል ደስተኛ ነበርክ፣ ዛሬስ ምን ያህል ደስተኛ ነህ? በሀያ አራት ሰዓታት ጊዜ ውስጥስ ለምን ያህል ጊዜ ደስተኛ ሆነሃል? በሕይወትህ ውስጥ ደስተኛ ካልሆንክና የምታደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ደስታን ማሳደድ ከሆነ መጥፎ አስተዳዳሪ ነህ ማለት ነው፡፡ በሕይወትህ ውስጥ የምታደርጋቸውን ነገሮች ሁሉ፣ የምታደርገው ያ ነገር ደስታህ እንደሆነ ስለምታምን ነው፡፡ ራስህን ታስተምራለህ፣ ሙያህን ታሻሽላለህ፣ ቤተሰብ ትገነባለህ፣ ምኞቶችህን ትከተላለህ፣ ብዙ ነገሮችን ትሰራለህ... ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች ማሳካት ደስታ እንደሚያመጣልህ ስለምታምን ነው፡፡ ያንን ሁሉ ካደረግክ በኋላ ደስታህ ከመብዛት ይልቅ ከቀነሰ አንተ የራስህ መጥፎ አስተዳዳሪ ነህ ማለት ነው፡፡ የራሱን አካል፣ የራሱን አእምሮ፣ የራሱን ስሜት፣የራሱን ኃያል እንዴት ማስተዳደር እንዳለበት የማያውቅ ሰው፣ ውጪያዊ ነገሮችን በሚያስተዳድርበት ጊዜ የሚያስተዳድረው በአጋጣሚ እንጂ እርሱ እንደሚፈልገው ሆነ ብሎ አይደለም፡፡ ምክንያቱም አእምሮህን፣ ኃያልህን፣ ውስጣዊ ነገሮችህን እንዴት ማስተዳደር እንደምትችል ካላወቅክ፣ ውጪያዊ ነገሮችን ማስተዳደርህ በአጋጣሚ መሆኑ አይቀርም፡፡ ነገሮችን በአጋጣሚ በምታስተዳድርበት የምትኖረውም በአጋጣሚ ይሆናል፡፡ በአጋጣሚ ስትኖር ደግሞ ድንገት ሊከሰት እንደሚችል አደጋ ነህ ማለት ነው፡፡ ሊሆን እንደሚችል አደጋ ከተከሰትክ ደግሞ፣ሁልጊዜ ጭንቀት ውስጥ መሆን የተለመደ የሕይወትህ ክፍል ይሆናል፡፡ ከዚያ ሰዎች በዓለም ላይ ምንም ነገር ብታገኝ ጭንቀታም መሆንህ የማይቀር ይሆናል፡፡ መንገድ ውጣና ምን ያህል ደስተኛ ፊቶች እንደምታገኝ ተመልከት፡፡ በጣም ጥቂት ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ውጪያዊ እንጂ ውስጣዊ አስተዳደር ስለሌለን ነው፡፡ የምንፈልገውን በመፍጠር ሂደት ውስጥ የሕይወታችን ምንጭ የሆነችውን ይህቺን ፕላኔት እያጠፋናት ነው፡፡ ደስታችንን በማሳደድ ውስጥ ይህቺን ፕላኔት እንደ ደመራ እያጋየናት ነው፡፡ ግን አሁንም አልረካንም፤ ሰዎች ምድር ላይ መኖር ከጀመሩበት ከብዙ መቶ አመታት በፊት ከነበርነው የበለጠ ደስተኛም አልሆንንም፡፡ ስለዚህ የሆነ ቦታ ላይ ውስጣዊ ነገሮቻችንን ችላ ብለናል፡፡ ታዲያ ወደ ውስጣችን ለመመለስ ምን ያስፈልገናል? @Zephilosophy @Zephilosophy
Show all...
...✍ ካለፈው የቀጠለ እናም ኑሯችን ለእግዚአብሔር የተሰጠ ነው፤ የምንኖረው ለእግዚአብሔር ነው፤ የምንታገለው ለእግዚአብሔር ነው፤ የምንሰዋው ለራሳችን አይደለም፣ ለእግዚአብሔር ነው፤ የምንዋለደው ለእግዚአብሔር ነው፡፡ እናም የዓለም ታሪክ የእግዚአብሔር ታሪክ ነው:: ሰዎች ታሪክ የላቸውም፡፡ እግዚአብሔር በህብረተሰቡ ኋላቀር አመለካከት ውስጥ ታስሯል። ኋላቀር አመለካከታቸው ሰዎችን ከዕውቀት፣ ከነፃነት፣ ከእውነት፣ ከፍትህ፣ ከፍቅር፣ ከታማኝነት.... ወዘተ አስሯቸዋል:: የሰዎች እኩይ _ ሐሳብና ኋላቀር አመለካከት ሁልጊዜ ሁለተኛ ደረጃ ደመነፍሳዊ ባሕርያቸውን እንደተጫነው ነው፡፡ እናም እግዚአብሔር በሰዎች ኋላቀር አመለካከትና እኩይ ሐሳብ ታስሯል። ዘረኝነት፣ አክራሪነት፣ ጨቋኝነት፣ አድሏዊነት ፣ እምባገነንነት፣ ጦረኝነት፣ ጥላቻ፣ ብቀላ፣ ሴሰኝነት፣ ምቀኝነት፣ የመሳሰሉት እኩይ ክስተቶች ሁልጊዜ እግዚአብሔር በሰዎች ውስጥ የሚታሰርባቸው ማህበራዊ ክስተቶች ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ዋና ፍላጎት ከዚህ እስር ወጥቶ በዓለሙ ላይ ሁሉ መናኘት ነው:: የፈረንሳይ አብዮት፣ የአሜሪካ የነፃነት አዋጅ፣ የእንግሊዙ የኢንዱስትሪ አብዮት፣ የአፍሪካውያን የነፃነት እንቅስቃሴ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰቱት የእርስበርስ ጦርነቶችና አመጾች (ዐፄ ኃሥላሴ ላይ፣ የኢህአዴግ ትግል፣ የሚያዚያ 30ው 1997 ዓ.ም የቅንጅት ሰልፍ፣ ጥናትና ምርምሮች፣ ፈላስፎች ከህብረተሰቡ ጋር የሚገጥሙት ትግል፣ ዲሞክራሲያዊ ምርጫዎች...) ሁሉ እግዚአብሔር ከታሰረበት ኅህብረተሰብ ውስጥ በአሸናፊነት ለመውጣት የተደረገና የሚደረግ ታሪክ ነው፡፡ ‹‹የሕዝብ አቤቱታ የእግዚአብሔር ድምፅ ነው› እንደሚባለው፣ ሁልጊዜ የሕዝብ አመፆችና ፍላጎቶች ሲከሽፉና ሲዳፈኑ እግዚአብሔር ከዚያ ኅህብረተሰብ ውስጥ በአሸናፊነት ለመውጣት ያደረገው ትግል የመክሸፉ ምልክት ነው፤ ወይም ደግሞ ዲያሌክቲክሱ በበቂ ሁኔታ ያለመብሰሉ _ ምልክት ነው፡፡ እናም ሁልጊዜ ሕዝብ ሲያምፅ እግዚአብሔር ከታሰረበት ማህበራዊ ክስተቶች ውስጥ ነፃ ለመውጣት እየታገለ ነው። ኑሯችን ሁሉ እግዚአብሔርን ከእስር የማውጣት ትግል ነው፡፡ ከኋላ ቀር አመለካከቶች ተላቀን በሁለተኛ ደረጃ ደመነፍሳዊ ባሕርያችን ግነት ስንኖር ያን ጊዜ እግዚአብሔርም ከእስር ነፃ ይወጣል፤ በዓለሙ ላይም ይገናል፡፡ እግዚአብሔር ከእስር ወጥቶ በአሸናፊነት በአንድ ኅህብረተሰብ ውስጥ ሲነግስ እዚያ ኅህብረተስብ ውስጥ ዕውቀት ይመጥቃል፤ ነፃነት፣ሰላም፣ እውነተኛነት፣ ፍትሃዊነት፣ ፍቅር፣ እኩልነት፣ ሰብዓዊነት፣ ተፈጥሯዊነት፣ የህግ የበላይነት ይነግሳል፡፡ ሁሉም ሰው እንደ ክርስቶስ ይሄንን ተልዕኮ አንግቦ ነው የሚወለደው:: ሁላችንም በዓለም ላይ እግዚአብሔርን ከእስር አውጥቶ ለማንገስ ነው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ሶፍትዌር እንደነበረው ሁሉ እኛም እንዲሁ ነን፤ እግዚአብሔርን በዓለሙ ላይ ሁሉ ለማንገስ እግዚአብሔር ባሕርያቱን እኛ ላይ ፕሮግራምድ አድርጎ ወደ ምድር ላከን፡፡ ከዚህ ተልዕኮ እንዳናፈገፍግም እግዚአብሔር ባሕርያቱን ባሕርያችን አደረገው፡፡ አምላክ ሰው ሆነ፣ ሰውም አምላክ ሆነ፡፡ እንግዲህ ሰው ማነው? ካላችሁኝ «ሰው ደመነፍሳዊ ባሕሪውን ነው» እላችኋለሁ፡፡ ኮምፒውተር እንዴት ዓይነት ነው? ካልን ሶፍትዌር ፕሮግራሙን ይመስላል እንባላለን፡፡ ሰውም ማንን ይመስላል? ካላችሁኝ ‹‹ደመነፍሳዊ ፕሮግራሙን ይመስላል› እላችኋለሁ፡፡ የሶፍትዌር ፕሮግራሙ ዓይነት የኮምፒውተሩን የአገልግሎት ዓይነት እንደሚወስነው ሁሉ የሰዎች የደመ ነፍሳዊ ባሕሪ ዓይነትም የሰዎችን ባሕሪ፣ አስተሳሰብና ከዓለም ጋር ያላቸውን ትውውቅ (ጥገኝነት) ይወስነዋል፡፡ በመሆኑም የሰዎችን ደመነፍሳዊ ፕሮግራም በመቀየር ብቻ ወይም የተወሰኑትን ፕሮግራሞች በማስተካከል ብቻ ሰውን አሁን ከሚኖረው የአኗኗር ዘይቤ ፈጽሞ መለወጥ ይቻላል፡፡ ሰውን አውሬ ማድረግ ይቻላል፤ ሰውን መልአክ ማድረግ ይቻላል፤ የራስ ወዳድነት ባሕሪውን መቀነስ ይቻላል፤ ፆታዊ ፍላጎቱን መለወጥ ይቻላል፤ እሬት እንዲጣፍጠው፣ ስኳር ደግሞ እንዲመረው ማድረግ ይቻላል፣ ሳርና ቅጠላ ቅጠል ተመጋቢ ብቻ እንዲሆን ማድረግ ይቻላል፤ እንደ X-ray በጣም አጫጭር የሆኑ ሞገዶችን ማየት እንዲችል ማድረግ ይቻላል፡፡ ሁለመናችን ደመነፍሳዊ ባሕርያችን ላይ የተወሰነ ነው፡፡ አሁን ያለን ተፈጥሯዊ ባሕሪ፣ አስተሳሰብ፣ ፍላጎት... ወዘተ ሁሉ አሁን ካለን የደመነፍሳዊ ባሕሪ ዓይነት የሚነሳ ነው፡፡ የሰዎችን ደመነፍሳዊ ፕሮግራም በመለወጥ የሰዎችን አጠቃላይ የኑሮ ዘይቤ መለወጥ የሚቻል ቢሆንም እግዚአብሔር ግን የፈቀደው አሁን ባለን ደመነፍሳዊ ባሕሪ አሁን ያለነውን ዓይነት ሰዎች እንድንኖር ነው፡፡ ፈላስፋውና የሂሳብ ሊቁ ላይብኒዝ፣ «ይህ ዓለም፣ ሊኖሩ ከሚችሉት እልፍ አእላፍ ዓለማት ውስጥ እግዚአብሔር የፈቀደውና ለእኛ የተሻለው ነው፤›› እንዳለው፡፡ ምናልባት ወደፊት መጽሐፍ ቅዱስ ከሚነግረን የፍርድ ቀን በኋላ እግዚአብሔር የሚወዳቸውን ሰዎች የሚያኖርበት አዲስ ዓለም አሁን ያለውን ደመነፍሳዊ ሶፍትዌር ፕሮግራማቸውን በመለወጥ ሊሆን ይችላል። ደመነፍሳዊ ፕሮግራማችንን በመለወጥ ብቻ አሁን የምንኖርባትን ዓለም መንግሥተ ሰማያት ማድረግ ይቻላል፡፡ ከፍርዱ ቀን በኋላ የሚሆነውም ይኼው ይመስለኛል፡፡ @Zephilosophy @Zephilosophy
Show all...
.... ✍ ካለፈው የቀጠለ ይሄንን የባህሪ ህግ ነው እኔ የሁለተኛ ደረጃ ደመነፍሳዊ ባሕሪ የምለው:: ጠቢቡ ዘርዓ ያዕቆብም ‹‹ህገ ልቦና›› ይለዋል፤ ‹‹የእኔ ቅዱስ መጽሀፍ ተፈጥሮዬ ላይ ያልው ህገ ልቦና ነው፤›› ይላል ዘርዓያዕቆብ፡፡ ይህ ህገ ልቦና ወይም ደመነፍሳዊ ባሕሪ ከመጀመሪያው ቀጥሎ የተጫነብን (load) ፕሮግራም ስለሆነ ስሙን የሁለተኛ ደረጃ ደመነፍሳዊ ባሕሪ እንበለው፡፡ ትርጉሙም፡ «ሰው፣ መንፈሳዊ (ነፍሳዊ) ሕልውናውን ጠብቆ ለመቆየት ሲል እግዚአብሔር ላይ ያለውን ጥገኝነት የሚረዳበት በሰውና በእግዚአብሔር (በነባራዊ ሐሳቦች መካከል ያለ ስውር ትውውቅ (divine program) ነው::» ይሄኛው ሶፍትዌር ፕሮግራም በሰው አእምሮ ውስጥ ብቻ የሚገኝ ነው፡፡ እንስሳት ያላቸው የመጀመሪያ ደረጃ ደመነፍሳዊ ባሕሪ ብቻ ነው፡፡ ሰው ግን ሁለቱም ደመነፍሳዊ ባሕሪዎች አሉት፡፡ ኮምፒዩተር ላይ የምናገኘው መረጃ ሁሉ ሶፍትዌር ፕሮግራሙ ላይ ያለውን የመረጃ ጥንቅር ብቻ ነው፡፡ ፕሮግራምድ ከተደረገው ነገር ውጭ የምናቀብለውን መረጃ ኮምፒዩተሩ አያውቀውም፡፡ ደመነፍሳዊ ባሕሪም ተመሳሳይ ነገር ነው፡፡ ሰው ከውጭ (ከአካባቢው) የሚፈልገው ደመነፍሳዊ ባሕሪው ላይ ፕሮግራምድ የተደረገለትን መረጃ ብቻ ነው፡፡ የተለያዩ የሞገድ ርዝመቶች (wave lengths) አንዱን ብርሃን፣ አንዱን ድምጽ፣ ሌላውን ሙቀት፣ አንዱን ቀይ፣ ሌላውን ነጭ፣ አንዱን ሰማያዊ፣ ሌላውን አረንጓዴ... እያደረገ አእምሮ የሚተረጉመው በውስጡ ካለው ደመነፍሳዊ ፕሮግራም በመነሳት ነው፡፡ የሰዎችን የዓይን መልዕክትና አካላዊ እንቅስቃሴያቸውን ተመልክተን ይሄ የፍቅር ነው፣ ይሄኛው ደግሞ የጥላቻ፣ ይሄ የመደሰት ነው፣ ይሄኛው ደግሞ የመከፋት፣ ይሄ ወሲብ ቀስቃሽ ነው፤ ይሄኛው ደግሞ ውበት ነው፤ ይሄኛው ደግነት ነው፤ ይሄኛው ራስ ወዳድነት ነው ወዘተ... የምንለው አሁንም ደመነፍሳዊ ባሕርያችን ላይ ያለውን ፕሮግራም መነሻ አድርገን ነው፡፡ ደመነፍሳዊ ባህሪ ማለት በህይወትና የህይወትን ህልውና በሚወስኑ ክስተቶች መካከል ያለ ስውር ተፈጥሯዊ ትውውቅ ነው በሚለው ትርጉም የጀመርነውን ሃሳብ እንቀጥል፡፡ ባለሙያዎች በተለይም ደግሞ ሳይኮሎጂስቶችና ሶሲዮሎጂስቶች ግን ሰው ለአካባቢያዊ ክስተቶች የሚሰጠው ትርጉም ከልምድ የተገኘ ነው ይላሉ፡፡ ሆኖም ግን ለልምዶቻችን ራሱ የተለየ ትርጉም የምንሰጠው አሁንም ደመነፍሳዊ ፕሮግራማችንን መሠረት አድርገን ነው፡፡ ጀርመናዊው ታዋቂ ፈላስፋ Kant ይሄንን ሁኔታ The apriori conditions of experience ይለዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ ፕሮግራሞች ያሉት የመጀመሪያ ደረጃ ደመነፍሳዊ ባሕሪ ውስጥ ነው፡፡ ሁለተኛ ደረጃ ደመነፍሳዊ ባሕሪ ደግሞ በተለያዩ ነባራዊ እሴቶች (ፍቅር፣ እውነት፣ ፍትህ፣ነፃነት፣ታማኝነት፣ እኩልነት፣ ሰብዓዊነት ወዘተ...) ፕሮግራምድ የተደረገ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰው ላይ ያለው ፈቃድ ወይም ፍላጎት ያለው እዚኽኛው ደመነፍሳዊ ባሕሪ ውስጥ ነው፡፡ በመሆኑም ሰው ለፍቅር፣ ለእውነት፣ ለፍትህ፣ ለነፃነት ፣ ለታማኝነት ፣ ለመረዳዳት፣ ለዕውቀት፣ ለሰብዓዊነት፣ ለእኩልነት.. ወዘተ ያለው ፍላጎት (ዝንባሌ) በሙሉ ከዚህኛው ፕሮግራም የሚያፈተልክ ነው፡፡ እነዚህ እሴቶች በሙሉ የእግዚአብሔር መገለጫ ባሕርያቶች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር የሚገለጸው ባሉት ባሕርያት ነው፡፡ እነዚህም ባሕሪዎቹ ከላይ የዘረዘርናቸው ነባራዊ እሴቶች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ሰዎች ላይ ያለው ዋነኛ ፍላጎት የእሱ መገለጫ የሆኑ ባሕሪዎቹን በዓለም ላይ ሁሉ (የሰው ልጅ በሄዱበት ጥግ ሁሉ) ማንገስ ነው፡፡ ሄግል እንዳለው individuals are the means by which God actualizes His Reason (Will) in the world. ተጨማሪ ሐሳብ ከዚሁ ፈላስፋ እንውሰድ፣ «የእግዚአብሔር ዋነኛ ዓላማ የራሱን ንቃተ ኅህሊና ማወቅ ነው፡፡ ዕውቀት ደግሞ የአዋቂና የታዋቂ ግንኙነትን ስለሚፈልግ እግዚአብሔር ራሱን ወደ ተቃራኒው ማለትም ወደ ተፈጥሮ (እኛ ይሄንን ተፈጥሮ የሰዎች የተንሸዋረረ ንቃተ ኅሊናና ሰይጣን እንበለው) ቀየረ፣ እንግዲህ አሁን ለትግል የሚሆኑ ሁለት ተቃራኒ ኅልውናዎች ተፈጥረዋል፤ በአንድ በኩል የሰዎች ልማዳዊ አስተሳሰብ ላይ የተጫነው የተንሸዋረረ ንቃተ ህሊናና ሰይጣን አለ፣ በሌላ በኩል ደግሞ እግዚአብሔር አለ፡፡ እነዚህ ሁለት ህልውናዎች አንደኛው በሌላኛው ላይ የበላይነትን ለማግኘት ሁልጊዜ በትግል ላይ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ፍላጎት በዚህ  ‌ ትግል (Dialectic) ውስጥ በአሸናፊነት መውጣትና በዓለም ላይ ሁሉ መንገስ ነው፡፡ እናም ሰዎች በሁለተኛ ደረጃ ደመነፍሳዊ ባሕርያችን ፕሮግራምድ የተደረግነው የእግዚአብሔርን ባህሪዎች ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የምንመሳሰለውም በሁለተኛ ደረጃ ደመነፍሳዊ ባሕሪያችን ነው፡፡ በዚህ ባህሪያችን ከእግዚአብሔር ሰማያዊ ግዛት ውስጥ የተወሰነ መለኮታዊ ድርሻ አለን፡፡ እንግዲህ ሰው ሥጋ ብቻ አይደለም፡፡ ከሥጋም በላይ እንጂ፡፡ ማርክሲስቶች እንደሚሉት ሰው ቁስ አካላዊ ብቻ አይደለም፤ መንፈሳዊ ሕልውናም አለው እንጂ፡፡ ዳርዊናውያን እንደሚሉት ሰው እንስሳ ብቻ አይደለም፤ መለኮታዊም እንጂ፡፡ ሰው ሁል ጊዜ ደመነፍሳዊ ባሕሪው ውስጥ ፕሮግራምድ ያልተደረገውን ነገር ከውጭ አይፈልግምና፤ በሁለተኛ ደረጃ ደመነፍሳዊ ባሕሪው ግፊት ሰው ሁል ጊዜ የእግዚአብሔር ባሕርያት በዓለም ላይ በበላይነት እንዲነግሱ ይታገላል፡፡ ልክ ባል የሚስቱ እንደሆነው ሁሉ፤እናትም የልጇ እንደሆነችው ሁሉ እኛም የእግዚአብሔር ነን፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ደመነፍሳዊ ባሕሪያችን በኩል ለተፈጥሮ እንደተሰጠን ሁሉ፣ በሁለተኛ ደረጃ ደመነፍሳዊ ባሕሪያችን በኩል ደግሞ ለእግዚአብሔር ተሰጥተናል፤እናም ሰዎች የእግዚአብሔር ወታደሮች ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ባሕርያትን በዓለም ላይ ሁሉ ለማንገስ እንታገላለን፤ እንዋጋለን፡፡ ትግሉና መስዋዕትነቱ ከባሕርያችን አፈትልኮ የሚወጣ ቢሆንም ዓላማው ግን እግዚአብሔርን በዓለም ላይ ማንገሥ ነው፡፡ አንድ ሰው ሲዋሽ ሰምተህ አንዳች ነገር ከውስጥህ ነሽጦህ ሽንጥህን ገትረህ ለእውነት ስትሟገት፣ ሙግትህ ለህሊናህ ቢመስልህም እየታገልክ ያለኸው ግን እግዚአብሔርን ለማንገሥ ነው፡፡ ምክንያቱም ‹‹እውነት› የእግዚአብሔር ባሕሪ ነው:: በታሪክ ሕዝቦች ጭቆናን ለማስወገድ፣ ነፃነትን፣ እኩልነትንና ፍትህን ለማንገስ ያደረጉት ትግልና የከፈሉት መስዋዕትነት ሁሉ እግዚአብሔርን በዓለም ላይ ለማንገስ የከፈሉት መስዋዕትነት ነው:: ፍርድ ቤቶች፣እስር ቤቶች፣ ፖሊስ ጣቢያዎች፣ የዕርዳታታድርጅቶች፣ የስብዓዊ ተቋማት፣ የሃይማኖት ማዕከላት፣ የጥናትና ምርምር ተቋማት... ወዘተ ሁሉ በምድር ላይ የእግዚአብሔር ጠበቃዎች ናቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ባሕርያት በዓለም ላይ ለማንገስ በምድር ላይ የሚታገሉ ተቋማት ናቸው፡፡         ✍ይቀጥላል✍ @Zephilosophy @Zephilosophy
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.