cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

Больше
Рекламные посты
68 631
Подписчики
+524 часа
+2137 дней
+1 38330 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች! እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Показать все...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

99👍 28🎉 4🤩 2
Показать все...

29👍 11
ብቁ ናችሁ! ከሕይወት ትልልቅ የፍርሃት ምንጮች አንዱ “ብቁ ያለመሆን” ፍርሃት ነው፡፡ በሰዎች ለመወደድ፣ ለመፈቀር፣ ተቀባይነት ለማግኘት፣ ለማወቅ፣ ለመሰልጠን፣ እድገት ለማግኘት . . .ብቁ እንዳልሆንን የማሰብ ፍርሃት! እውነት እውነቱን እንነጋገር፡፡ አንድ ሰው እናንተን ለመቀበልና ለመውደድ የማይችል ወይም የማይፈልግ ከሆነ፣ ይህ ማለት እናንተ የዚያ ሰው አይደላችሁም ማለት ነው - አለቀ! ይህ ማለት ግን የዓለም መጨረሻ ነው ማለት አይደለም፡፡ ይህ ሰው እናንተን የመቀበልና የመውደድ ብቃቱ ወይም ፍላጎቱ የለውም ማለት ነው እንጂ እናንተ ተቀባይነት የማግኘትና የመወደድ ብቃቱና ማንነቱ የላችሁም ማለት አይደለም፡፡ እናንተን የመውደድም ሆነ የመቀበል ብቃቱና ፍላጎቱ ያለው ብዙ ሰው በዙሪያችሁ እንዳለ አስታውሱ፡፡ እነሱን ለማየትና ለመገናኘት ግን “ካልተቀበለኝና ከልወደደኝ” ብላችሁ ችክ ካላችሁት ሰው ላይ አይናችሁን ማንሳት፣ ስሜታችሁንም ማላቀቅ የግድ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ለጊዜው ከባድ ነው፣ ነገር ግን በሚልየን የሚቆጠሩ ሰዎች ችለውታልና እናንተም ትችላላችሁ! አንድ ነገር አልሆን ሲላችሁ ሁል ጊዜ እናንተ ለዚያ ነገር ብቁ ስላልሆናችሁ እንደሆነ የማሰብን የእሳቤ ንድፍ መቀየር አለባችሁ፡፡ በዚያ ምትክ ያ ሰውም ሆነ ሁኔታ ለእናንተ የማይመጥን ስለሆነ እንደቀረላችሁ ማሰብም አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜም እንዳለ አትዘንጉ፡፡ በአጭሩ፣ ለመወደድ ብቁ ናችሁ! ለማደግ ብቁ ናችሁ! ለማወቅ ብቁ ናችሁ! በዚህ ዓለም ፈጣሪ ለሰው ልጆች ደስታና ስኬት ለፈጠረው መልካም ነገር ሁሉ ብቁ ናችሁ! ሕይወት ትክክለኛውን ሰውና ስፍራ ገልጣ እስከምታቀርብላችሁ ድረስ ግን ራሳችሁን በመቀበል የድርሻችሁን መወጣት የግድ ነው፡፡ https://t.me/Dreyob
Показать все...
160👍 100🔥 7😁 2🎉 2🤩 2
በጥራት ማደግ! ሁለት አይነት እድገቶችና ትልቅነቶች አሉ፡፡ አንደኛው ውጫዊ እድገትና ትልቅነት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” ነው፡፡ 1. ውጫዊ እድገትና ትልቅነት ሰዎች በገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣ በዝና፣ በስልጣን እና በመሳሰሉት ነገሮች ሲያድጉ፣ “ውጫዊ እድገትና ትልቅነት” አገኙ እንለዋለን፡፡ ይህ እድገትና ትልቅነት ምንም እንኳን በራሱ ምንም ችግር ባይኖረውና እንዲያውም ለጥቅም የሚውል ቢሆንም ብቻውን ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ 2. “ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” ሰዎች በመልካም ስብእና፣ በጤናማ አመለካከት፣ በስሜት ብልህነት፣ በራእይ እና በጥበብ ሲያድጉ፣ “ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” አገኙ እንለዋለን፡፡ ይህ እድገትና ትልቅነት ከማንኛውም ነገር በፊት ሊቀድም የሚገባው የእድገትና የትልቅነት ዘርፍ ነው፡፡ አንድ ሰው ከላይ የተጠቀሱትን አይነት ውጫዊ እድገትንና ትልቅንን እያስመሰዘገ ውስጣዊ እድገት ሲጎድለው ከራሱ ሕይወት ጀምሮ እስከ ቤተሰቡ፣ የስራ ስምሪቱና በሃገር ደረጃ የሚያስከትለው ቀውስ ይህ ነው አይባለም፡፡ የገንዘብ አቅሙን ለማይረባ ነገርና ለሕገ-ወጥ ተግባር የሚጠቀም ማነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን? በዝናውና በታዋቂነቱ የሚኩራራውና ሰውን የሚንቀው ማን ነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን? በስልጣኑ ተጠቅሞ ሰውን የሚደቁስና እንደፈለገ የሚሆን ማን ነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን? በመጀመሪያ በውስጣችን እንደግ! ከሁሉም በፊት በጥራትና በብቃት ትልቅ እንሁን! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Показать все...
142👍 89🔥 7😱 1
Показать все...

22👍 15
Показать все...

15👍 5
ያስቸገረኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር! ተወልዶ ካደገበት ሃገሩ በተፈጠሩ ማሕበራዊ ቀውሶች ምክንያት ወደሌላ ሃገር በስደት ለመሄድ የቆረጠ አንድ ሰው ረጅም፣ አድካሚና አስፈሪ የሆነን በረሃ ለቀናት በእግሩ በመሄድ ካቋረጠ በኋላ እጅግ ደክሞና ዝሎ ነበር፡፡ በመጨረሻም በደረሰበት አንዲት ከተማ ውስጥ በተሰጠው እርዳታ ትንሽ አገገመ፡፡ የዚህን ሰው ጉዞ የሰማና ለሕብረተሰቡ ለማቅረብ የፈለገ አንድ ጋዜጠኛ አገኘውና አንድን ጥያቄ ጠየቀው፡፡ “ተጉዘህ የመጣኸው በረሃ ብዙ ሰው የማይደፍረው በረሃ ነው፡፡ ለመሆኑ በመንገድህ ላይ በጣም የጎዳህና ያስቸገረህ ውኃ ጥም ነበር? ምግብ ማጣት ነበር? አውሬ ነበር? ሽፍቶች ነበሩ? ወይስ . . . ? የዚህ ስደተኛ መልስ ለጋዜጤኛው ያልተጠበቀ ነበር፡፡ በዚህ አደገኛ በረሃ አቋርጬ ስመጣ በጣም ያስቸገሩኝ የጠቀስካቸው ትልልቅ ነገሮች አልነበሩም፡፡ ጉዞየን በጣም አድካሚና አስቸጋሪ ያደረገብኝ በእርምጃዬ ወቅት ጫማዬ ውስጥ እየገባ የሚቆረቁረኝና አላራምድ ያለኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር፡፡ የሕይወት ጉዞም እንዲሁ ነው! አብዛኛውን ጊዜ የሚያስቸግረን፣ የሚቆረቁረን፣ አላራምድ የሚለንና ከዓላማችን የሚጎትተን ችግር ትልልቁ አይደለም፡፡ በየቀኑ የሚያጋጥሙን ጥቃቅን “አሸዋዎች” ናቸው፡፡ ትንንሽ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ባህሪይ፣ ትንንሽና አናሳ ወሬን የሚያወሩ ሰዎች ሁኔታ፣ ትንንሽና ስሜትን የሚነካኩ የየቀን ገጠመኞች . . . ጉዟችንን አዳጋችና አድካሚ ያደርጉታል፡፡ “በትንንሽ” ሰዎችና ሁኔታዎች ሳትበገሩ ትልቁ የሕይወት ስእልና ዓላማችሁ ላይ በማተኮር ወደፊት መገስገስን ያወቃችሁበት ጊዜ ዋናውን የሕይወት ድል የተጎናጸፋችሁበት ጊዜ ነው፡፡ በርቱ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623
Показать все...
👍 224 86🔥 14😁 1😱 1
ከኢትዮጵያ ውጪ ለምትኖሩ በዚህ ሊንክ ግቡና ተመዝገቡ ክፍያውንም እዛው ላይ እንዴት እንደምትከፍሉ ይነግራል:: ኢትዬጽያ ለምትኖሩ ይህ ስልጠና የሚሰጥበት ሰአት ለናንተ ሌሊት ስለሚሆን ላይመች ይችላል:: https://forms.gle/NkcpF5jQwrUVVf47A
Показать все...
Dr Eyob's Vision class registration form

Fill out the form completely and submit

👍 36😱 3
Repost from Dr. Eyob Mamo
የስልጠና እድል! With Dr. Eyob Mamo ከሃገር ቤት ውጪ ለምትገኙ ሁሉ የተዘጋጀ በ Zoom የሚሰጥ የስልጠና እድል፡፡ ራእይ . . . • የተፈጠርንነትን የሕይወት ትርጉም የምናገኝበት . . . • ከተሰላቸንበት የሕይወት ዑደት የምንወጣበትና ወደ ዓላማችን አቅጣጫን የምንይዝበት . . . • ለራሳችን ብቻ ከመኖር ባሻገር በሌሎች ላይ ተጽእኖ የማምጣት መትረፍረፍ ውስጥ የምንገባበት . . . . . . ብቸኛው መንገድ! በማስወቂያ ፖስተሩ ላይ ባለው መረጃው መሰረት መመዝገብ ትችላላችሁ! አያምልጣችሁ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Показать все...
👍 54 9😱 2😁 1
Repost from Dr. Eyob Mamo
መፍራትን አትፍራው! እንደ ፍርሃት፣ ድንጋጤና ስጋት አይነት ስሜቶች ሰው ከአደጋ እንዲጠነቀቅ ከፈጣሪው የተሰጡ ስጦታዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ስሜቶች በአግባቡ ልንጠቀምባቸውና ከአደጋ ልንጠበቅባቸው ሲገባን ለአንዳንድ ሰዎች የኑሮ ዘይቤ ሆነዋል፡፡ የመውደቅ ፍርሃት፣ የመክሰር ፍርሃት፣ ያለመወደድ ፍርሃት፣ ብቻ የመቅረት ፍርሃት፣ … ጣጣችን ብዙ ነው፡፡ በፍርሃት ስንወረስ፣ ሕይወታችንን በራእይ መምራት እናቆምና ለፍርሃት ምላሽ በመስጠት መምራት እንጀምራለን፡፡ ከአንዱ ራእይ ወደሌላኛው በማለፍ ሕይወትን “ልናጠቃት” ሲገባን የመጣው ሁሉ የኑሮ ገጠመኝ የሚያጠቃን ቋሚ ኢላማዎች እንሆናለን፡፡ ቆመን ለመጣው ወይም የመጣ ለመሰለን ጥቃት ምላሽ በመስጠት ጊዜአችንን እናባክናለን፡፡ ይህ ሲሆን የቆመ ኢላማ ሆንን ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው ከአንዱ ግብ ወደሌላኛው በአላማ የምንንቀሳቀስ ሰዎች ስንሆን አይኖቻችን ከችግሩ ላይ ይነሱና መፍትሄው ላይ ማረፍ ይጀምራሉ፡፡ የፍርሃትህ ጥልቀት አእምሮህ የፈቀደለት ያህል ነው” - Unknown Source ፍርሃት በሕይወትህ ብቅ ጥልቅ ማለቱ አያስፈራህ፡፡ በዚያ ፍርሃት ምክንያት ግን መንቀሳቀስ እስኪያቅትህ ድረስ እንዳትታሰር ፍራ፡፡ ማንኛውም ሁኔታ አንተን የማስፈራራት ሙከራ የማድረግ ሙሉ መብት አለው፡፡ አንተ ካልፈቀድክለት ግን ሊያስፈራራህ አይችልም፡፡ ትፈራለህ፣ ፈሪ ግን አይደለህም፡፡ “በፍጹም አልፈራም” ብለህ ካሰብክና ከተናገርክ ከፍርሃት የተደበቅህ ሰው እንደሆንክ አመልካች ነው፡፡ በሌላ አባባል፣ የፍርሃት ስሜት እንዳይመጣ መከልከል አትችልም፣ ይህንን ስሜት ለማስተናገድ የተፈጠረ ማንነት ስላለህ፡፡ ሆኖም፣ የፍርሃትን ጥልቀትና በአንተ ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ጉዳት የመወሰን ሙሉ መብትም ሆነ ብቃት አለህ፡፡ https://t.me/Dreyob
Показать все...
👍 104 45🤩 9🔥 5🎉 3