en
Feedback
መጽሐፍቶችን በpdf📚

መጽሐፍቶችን በpdf📚

Open in Telegram

"እንኳን ደህና መጣችሁ"Welcome! በpdf(በሶፍት ኮፒ) ለማንበብ ራሳችንን እናስለምድ! ፨ተራ ነገር በመስራት የሚባክነውን ጊዜያችንን በንባብ ላይ ስናውለው ከራሳችን አልፈን ለብዙዎች የመለወጥ ምክንያት እንሆናለን፡የንባብ ባህላችንን እናዳብር! ባለንበት ራሳችንን በእውቀት እንገንባ! ፨በዚህ ቻናል የተለያዩ መፅሐፎች፣ጠቃሚ ሀሳቦች፣አፕልኬሽኖች፣አነቃቂ ምስሎች ቀርቦላችኋል አውርደው ይጠቀሙ።

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel መጽሐፍቶችን በpdf📚

Channel መጽሐፍቶችን በpdf📚 (@pdfffb) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 16 894 subscribers, ranking 2 129 in the Books category and 2 019 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 16 894 subscribers.

According to the latest data from 26 August, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 755 over the last 30 days and by 13 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 18.71%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 5.48% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 3 161 views. Within the first day, a publication typically gains 925 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 15.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
"እንኳን ደህና መጣችሁ"Welcome! በpdf(በሶፍት ኮፒ) ለማንበብ ራሳችንን እናስለምድ! ፨ተራ ነገር በመስራት የሚባክነውን ጊዜያችንን በንባብ ላይ ስናውለው ከራሳችን አልፈን ለብዙዎች የመለወጥ ምክንያት እንሆናለን፡የንባብ ባህላችንን እናዳብር! ባለንበት ራሳችንን በእውቀት እንገንባ! ፨በዚህ ቻናል የተለያዩ መፅሐፎች፣ጠቃሚ ሀሳቦች፣አፕልኬሽኖች፣አነቃቂ ምስሎች ቀርቦላችኋል አውርደው ይጠቀሙ።

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 27 August, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Books category.

16 894
Subscribers
+1324 hours
+1367 days
+75530 days
Posts Archive
👌🏾

Livewired David Eagleman’s Livewired: The Inside Story of the Ever-Changing Brain offers a compelling reexamination of neuroplasticity, challenging the long-standing computational metaphors that have dominated popular science. Rather than viewing the brain through the rigid lens of hardware and software, Eagleman introduces the concept of "liveware"—a biological system defined by continuous physical self-reconfiguration in response to internal demand and environmental input. The book’s central thesis centers on neural competition and adaptability. Eagleman argues that brain regions do not possess immutable, pre-designated functions. Instead, neural territory is constantly contested, where active sensory inputs preserve real estate while inactive ones are quickly overrun by neighboring functions. To ground this theory, he presents striking empirical examples, ranging from sensory substitution technologies—such as translating visual data into tactile sensations on the skin—to the rapid cortical remap that occurs when sensory organs are lost or impaired. Through these cases, the text demonstrates that the brain operates as an input-agnostic information engine capable of interpreting virtually any structured data stream it receives. Key Themes Analyzed Rejection of Hardware Metaphors: Eagleman details why static mechanical analogies fail to capture the reality of biological tissue that physically rewires its circuits, synapses, and structural connections moment by moment. Dynamic Territory Allocation: The narrative explores how neural circuits engage in an ongoing struggle for cortical space, explaining phenomena like phantom limb sensations and why dreams may serve as a defense mechanism to keep the visual cortex active at night. Sensory Augmentation & Engineering: The work bridges theoretical neuroscience and practical engineering, showing how human perception can be expanded using wearable technology that feeds non-traditional data (such as stock market trends or infrared light) directly into the nervous system. While Livewired shines in its engaging storytelling and accessible explanations of complex neuroscience, it leans heavily on optimism regarding future technological integrations, occasionally glossing over the clinical and ethical hurdles of brain-machine interfacing. Nonetheless, Eagleman succeeds in framing neuroplasticity not as a passive feature of recovery, but as the foundational rule governing human learning, perception, and evolution. It stands as a thought-provoking, beautifully articulated contribution to contemporary popular science literature. Engaged in reading always!

Feel free to open the link; it’s an AI-powered website for learning English.
+3
Feel free to open the link; it’s an AI-powered website for learning English.

🤣የበዓል ገጠመኝ! ኮንዶሚኒየም ውስጥ መኖር ችግር ነው! ሁሉም ዶሮና በጉን በሩ ላይ አስሮ ብሎካችንን ኤልፎራ አስመስሎታል። እኔም ትናንት ሚስቴ በግ ካልገዛህ እያለች ስትነተርከኝ ጥቂት ብር ይዤ በግ ልገዛ ብወጣ አንድ ቀውላላ በግ ነጋዴ ሁለት ፊታቸው ላይ ከባድ ድብርት የሚታይባቸውን ከሲታ በጎች ይዞ ቆሞ አገኘሁና ጠጋ ብዬ «ልትሸጣቸው ነው?» አልኩት «እና ሐገር ላስጎበኛቸው ነው ካገሬ ይዣቸው የወጣሁት?»አለኝ «እንደው ኩነኔ አይሆንም እነዚህን መግደል?» ስለው ፈጠን ብሎ «አንቀህ ነው እንዴ ምትገድላቸው?» አለኝ «አይ ያው በቢላም ቢሆን ...» ብዬ ሳልጨርስ «ወንድሜ ካሳዘኑህ ውሰድና በጉዲፈቻ አሳድጋቸው» አለኝ «እሺ ስንት ነች እቺ?» አልኩት ወደአንዷ እየጠ ቆምኩ «በግ ታውቃለህ ማለት ነው። በጣም አስተዋይ በግ ነች እሷ» ብሎ ጀርባዋን መታ መታ ሲያደርጋት ወደጎን ፍንግል አለችና አቧራ ዋን አራግፋ ተነሳች። «እኔ አስተውሎቷ ምን ይሰራልኛል ላስተምራት አይደለም እኮ ምወስዳት» ስለው «አስራ ስምንት ሺህ ብር ክፈል» አለኝ «አስራ ስምንት ሺህ ብርማ አታወጣም» «በርግጥ ላታወጣ ትችላለች ነገር ግን እኔ 18 ሺህ ብር ነው የሚያስፈልገኝ» «ቀንስና ልውሰድልህ» አልኩት «አይ ወዳጄ በጓን ግን አይተሃታል? ውስጠ ወይ ራ እኮ ነች። መፍዘዟን አትይ። በዚያ ላይ በእንክብካቤ ነው ያደለብኳት» «ጭራሽ ደልባ ነው እንዲህ የከሳችው?» «አዎና! በርግጥ እኔ ስብእናዋ ላይ ነው የሰራሁት። በጥሩ ስነምግባር ነው ያሳደግኋት» አለኝ ቆፍጠን ብሎ። ሳቄን ለመቆጣጠር እየሞ ከርኩ «5ሺህ ብር ትሸጥልኛለ ...?» ብዬ ሳልጨርስ«ውሰዳት!» አለኝ በደስታ ተሞልቶ። ምነው ዝም ባልኩ ብዬ በይሉኝታ አሰራ አምስት ሺ ብር ሰጥቼው በጓን ይዤ ልሄድ ስል መራመድ አቅቷት በቀስታ ስታዘግም «ቃሬዛ ቢኖርኮ ደግ ነበር» አለኝ ሰውዬው በጉን በሃዘን እየሸኘ። ተበሳጭቼ ዝም ብዬው ስሄድ «ወንድሜ እንደው ለነፍስ ትሆንሃለች መጀመሪያ የህክምና እርዳታ አርግላት» አለኝ መንገድ ላይ በጓን ያየ ሁሉ ከንፈሩን እየመጠጠ ያልፋል። አንዳንዱ እኔን እያየ አንገቱን በሃዘን ይነቀንቃል። በግ ላርድ ሳይሆን እንደአብርሃም ልጄን ልሰዋ ይዤ እየሄድኩ ነው ያስመሰሉት ። ሽምቅቅ እንዳልኩ ቤት ደረስኩ። ሚስቴ በጓን እንዳየቻት «ምንድነው ይዘህብኝ የመጣኸው?» ብላ ጮኸች። በጩኸቷ ከኔ ይልቅ የደነገጠችው በጓ ነች። አይኗን አስለምልማ መሬት ወደቀች! የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ ላደርግላት ሞከርኩ። አልነቃ ስትለኝ በአፌ ትንፋሽ ልሰጣት ሳጎነብስ ሚስቴ «በዚህ አፍህ እኔ ከንፈር ጋር ድርሽ እንደማትል እወቀው!»ስትለኝ ቀና ብዬ መጨረሻዋን ማየት ጀመርኩ ..ውይይ! አረፈች! በጣም የሚያሳዝን ሁኔታ ነው የገጠመኝ ጎበዝ። «ቆይ ግን ...የግድ ስጋዋን ለመብላት እኛ ልንገድላት ይገባል እንዴ? ያው ሞት ሞት ነው። በቢላም ሞተች በድንጋጤ ያው መሞቷ አይቀርም!» ስል ሚስቴ ሶስት ግዜ አማትባ «በል አውጥተህ ጣል» አለች። እኔ ግን ተስፋ አልቆ ረጥኩም! እቺን በግ እኮ ስጋዋን ፈልጌ ሳይሆን እንደበግ እንድትተውን ነው የገዛኋት። አክተር ደሞ አይሞትም ኦህኦህኦህኦህህ! ተመስገን! ነቅታለች ጎዶች «እልልልል ...» (አሉ እትዬ ዘርፌ የቤት እቃ (ማማሰያ ሳይቀር) እየሰረቀ ያሰለቻቸው ልጃቸው ሲታሰር) እንዲህ ነው እንጂ በግ! ዝም ብሎ መሞት አለንዴ? እኛ ሳንፈቅድላትማ አትሞታትም! አልኩ ለሚስቴ (አንዳንዴኮ እንደ አፍሪካ መሪዎች ሚያደርገኝ ነገር አለ)ሚስቴ መንቃቷን ስታይ «በል ቶሎ እረድልኝ» ብላ የአሉላ አባነጋን ሻሞላ የሚያህል ቢላ ይዛ መጣች። «አሁን ለዚች በግ ይሄን የሚያህል ቢላ መጠቀም ተመጣጣኝ እርምጃ ነው ብለሽ ታስቢያለሽ?» አልኳት «ወሬውን ተወውና ሳትሞት እረዳት» የሚል ቀጭን ትዛዝ ሰጠችኝ! ሻሞላውን ተቀብዬ ወደበጓ ስጠጋ አይኗን ከፈት አርጋ ቢላውን አየት አረገችና እንደሰው እንባዋ ባይኗ ሞልቶ ፀጥ አለችላችሁ! በቃ ሞተች!ብቻ በጣም የሚያሳዝን ጉዳይ ነው የገጠመን ወገን! ከሚስቴ ጋር ያደርኩትን አዳር አዳር አትበሉት። ለሊት ላይ ጠጋ ብዬ እያቀፍኩ «አይዞን እኛ ጤና የሚቀጥለው በዓል ምን የመሰለ ሙክት ነው ምናርደው» ስላት እንደ አለቃ ገብርሃና ገፍትራ ከግድግዳጋር አጋጨችኝ! መልካም በዓል🤙 ሁሌም ማንበብ!

ዕድሜ ለእርሶ ከጠፈረን እግር ተወርች -ካነቀፈን የዘር ደቦ፡ በየጥሻ ካስመሸገን -በመንደሩ ተተብትቦ፡ “ሰዉ “መሆን ነዉ መሻገሪያ የሚያስታርቅ ከሀያሉ፡ ሲወተዉት ልስልስ ድምፆ - ሳይሰምርልን ህያዉ
ዕድሜ ለእርሶ ከጠፈረን እግር ተወርች -ካነቀፈን የዘር ደቦ፡ በየጥሻ ካስመሸገን -በመንደሩ ተተብትቦ፡ “ሰዉ “መሆን ነዉ መሻገሪያ የሚያስታርቅ ከሀያሉ፡ ሲወተዉት ልስልስ ድምፆ - ሳይሰምርልን ህያዉ ቃሉ ፡ አለቅሳለሁ በመደቤ -እንቅልፍ የለኝም እንዳሉ፡ ሄዱ አሉ ? ላንቀላፋነዉ እኛ -ዓለም ዘመን እያለፈን ፡ እሺ ብንል ምን ነበረ ? መካሪ አባት ሳያኮርፈን ፡ ሄዱ አሉ ? አሜን ሳንል እጅ ስመን ፡ ሳንታረቅ ከእልህ ከስመን ፡ እልፍ ሳንል ጋት እርምጃ፡ ሳይሞላልን ስለት ሀጃ ፡ እንኳንስ ከደም ዕዳ ፡ ሳናወጣ ብድር ቀዳ ፡ አባት ሄደ የእልፍኝ ማገር ፡ ስመ መልካም ልበ ገር ። እንዲህም የለ መሰበር !! ፍትህ ሞተ ፣እዉነት ሞተ ፣አባት ሞተ ሲለን ጀማዉ ፡ የማጣት ብርድ ፣ ያዘን ቆፈን ፣ አጥንት ስር የሚሰማዉ ። አግኝቶናል ባደባባይ ፣ ከመለስዎ የዕንባ ጎርፉ: ባልታዘዝንዎ ይቅር በሉን _በዲናችን በሉን አፉ ። ዕድሜ ለርሶ “ዕድሜ ለርሶ “ ለሞተ ሰዉ አይባልም እንዳይሉ ፡ መጥኔዉ ለኛ ዕድሜዉ ለርሶ ተለዉጧል ብሂሉ፡ የዕምነት ትርጉም እንደዚህ ነዉ ዘር ተሻግሮ ኬላ ጥሶ፡ መከበርን አየንበት አወቅንበት ዕድሜ ለእርሶ ፣፣ በመኖርዎ የዘሩትን _በመምትዎ ደግመዉ ካሱን የረሳነዉ የተዉነዉን “ሰዉነትን “ አስታወሱን በጭንቃችን ተደርበዉ _እንደገና ሆድ አስባሱን ። ሄዱ አሉ? በህይወት የተገለጠ -ፍቅር ፍትህን አንግሶ መኖርስ በልብ ላይ -መሄድስ ልክ እንደርሶ ። ነፍሶን ይማር የተከበሩ አባታችን። “የሐገር🇪🇹መልክ” መልካም በዓል🤙

Repost from Kelemat Ads
💰 የሀገራችን ቲክቶከሮች እና ዩቲዩበሮች በወር ከ100,000 ብር በላይ እያገኙ መሆናቸውን ያውቃሉ? ስኬታቸው በተለያዩ ምክንያቶች የሚወሰን ቢሆንም፣ ጥራት ያለው ይዘት ማቅረብ ግን በጣም አስፈላጊ
💰 የሀገራችን ቲክቶከሮች እና ዩቲዩበሮች በወር ከ100,000 ብር በላይ እያገኙ መሆናቸውን ያውቃሉ? ስኬታቸው በተለያዩ ምክንያቶች የሚወሰን ቢሆንም፣ ጥራት ያለው ይዘት ማቅረብ ግን በጣም አስፈላጊ ነው። Nidan Trading ለኮንቴንት ክሪኤተሮች ስራቸውን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሳድጉ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች ይዞላችሁ ቀርቧል፦ 🎙 Wireless & Studio Mics – ጥራት ላለውና ከጩኸት የጸዳ ድምፅ 💡 Studio Lights & Softboxes – ለማንኛውም ቦታ ተስማሚ የሆነ ፕሮፌሽናል ብርሃን 🎥 DJI Gimbals – ያልተንቀጠቀጠ እና ለስላሳ የቪዲዮ ቀረጻ 📸 Camera Accessories – ለስራዎ ምቾት የሚሆኑ አስፈላጊ ተጨማሪ ዕቃዎች 🔥 አዳዲስ እቃዎች ሲገቡና ልዩ የዋጋ ቅናሾችን ቀድመው ለማግኘት የNidan Trading ቴሌግራም ቻናልን ይቀላቀሉ! @nidantradingg 👉 ቴሌግራም: @nidantradingg

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ ! 🌙 እንኳን ለነብዩ መሃመድ የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ 🎉፣ በዓሉ የመተሳሰብ ፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ 🤲✨።

ገጣሚና የዓይን ሕክምና ባለሙያዋ እፀገነት ብርሃኔ "ያልተቋጨው ቁጭት" የተሰኘ የግጥም መድበሏን ለአንባቢዎች አበረከተች። በቴፒ ከተማ ተወልዳ ያደገችው ገጣሚት እፀገነት ብርሃኔ በሙያዋ የዓይን ሕክም
ገጣሚና የዓይን ሕክምና ባለሙያዋ እፀገነት ብርሃኔ "ያልተቋጨው ቁጭት" የተሰኘ የግጥም መድበሏን ለአንባቢዎች አበረከተች።     በቴፒ ከተማ ተወልዳ ያደገችው ገጣሚት እፀገነት ብርሃኔ በሙያዋ የዓይን ሕክምና ባለሙያ (ኦፕቶሜትሪስት) ናት። በኩባ ሀገር የነበራትን የከፍተኛ ትምህርት ስኮላርሺፕ አጠናቃ ከተመለሰችበት ጊዜ አንስቶ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የዓይን ሕክምና ክፍል ውስጥ ህብረተሰቡን በቅንነት እና በታማኝነት በማገልገል ላይ ትገኛለች። ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ኦፕቶሜትሪ ባለሙያዎች ማህበር ውስጥ የስራ አስፈጻሚ አባል በመሆን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊነቷን ከመወጣቷ ባሻገር፣ በተለያዩ የቴሌቪዥን መስኮቶች በመቅረብ ስለ ዓይን ጤና ጥበቃ የማህበረሰብ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ትሰራለች። በተለያዩ ተቋማት የሚገኙ ሰራተኞች ነጻ የዓይን ምርመራ እና ሕክምና የሚያገኙበትን ሁኔታ በማመቻቸት ረገድም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክታለች። በመስሪያ ቤቷም ሆነ በማህበሩ ዘንድ በዋናነት የምትታወቀው ለህብረተሰቡ ባላት የማህበረሰብ አገልግሎት እና የበጎ ፈቃደኝነት ፍቅር ነው። ከብዙ በጥቂቱ ለህፃናት የዓይን ህክምና ምርመራ በማድረግ ነጻ መድሀኒት እና የመነጽር አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጋለች። እንዲሁም በክረምት ወራት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እና በጤና ሚኒስቴር ትብብር ጊዜያዊ የህክምና መስጫ ጣቢያዎችን በማቋቋም ሁሉን አቀፍ የጤና ምርመራዎች እንዲካሄዱ የማስተባበር እና ለታካሚዎች ነጻ መነጽር የማደል ስራን በትጋት ስታከናውን ቆይታለች። ይህች የማህበረሰብ አገልግሎት አርአያ የሆነችው ገጣሚት እፀገነት ብርሃኔ አሁን ደግሞ "ያልተቋጨው ቁጭት" የተሰኘ አዲስ የግጥም መድበሏን ለወገኖቿ አቅርባለች። ©ጌጡ ተመስገን ሁሌም ማንበብ!

ገጣሚና የዓይን ሕክምና ባለሙያዋ እፀገነት ብርሃኔ "ያልተቋጨው ቁጭት" የተሰኘ የግጥም መድበሏን ለአንባቢዎች አበረከተች። በቴፒ ከተማ ተወልዳ ያደገችው ገጣሚት እፀገነት ብርሃኔ በሙያዋ የዓይን ሕክምና ባለሙያ (ኦፕቶሜትሪስት) ናት። በኩባ ሀገር የነበራትን የከፍተኛ ትምህርት ስኮላርሺፕ አጠናቃ ከተመለሰችበት ጊዜ አንስቶ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የዓይን ሕክምና ክፍል ውስጥ ህብረተሰቡን በቅንነት እና በታማኝነት በማገልገል ላይ ትገኛለች። ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ኦፕቶሜትሪ ባለሙያዎች ማህበር ውስጥ የስራ አስፈጻሚ አባል በመሆን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊነቷን ከመወጣቷ ባሻገር፣ በተለያዩ የቴሌቪዥን መስኮቶች በመቅረብ ስለ ዓይን ጤና ጥበቃ የማህበረሰብ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ትሰራለች። በተለያዩ ተቋማት የሚገኙ ሰራተኞች ነጻ የዓይን ምርመራ እና ሕክምና የሚያገኙበትን ሁኔታ በማመቻቸት ረገድም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክታለች። በመስሪያ ቤቷም ሆነ በማህበሩ ዘንድ በዋናነት የምትታወቀው ለህብረተሰቡ ባላት የማህበረሰብ አገልግሎት እና የበጎ ፈቃደኝነት ፍቅር ነው። ከብዙ በጥቂቱ ለህፃናት የዓይን ህክምና ምርመራ በማድረግ ነጻ መድሀኒት እና የመነጽር አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጋለች። እንዲሁም በክረምት ወራት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እና በጤና ሚኒስቴር ትብብር ጊዜያዊ የህክምና መስጫ ጣቢያዎችን በማቋቋም ሁሉን አቀፍ የጤና ምርመራዎች እንዲካሄዱ የማስተባበር እና ለታካሚዎች ነጻ መነጽር የማደል ስራን በትጋት ስታከናውን ቆይታለች። ይህች የማህበረሰብ አገልግሎት አርአያ የሆነችው ገጣሚት እፀገነት ብርሃኔ አሁን ደግሞ "ያልተቋጨው ቁጭት" የተሰኘ አዲስ የግጥም መድበሏን ለወገኖቿ አቅርባለች። ©ጌጡ ተመስገን ሁሌም ማንበብ!

Repost from Kelemat Ads
እንግሊዝኛ ለመናገር ስትሞክር ቃላቱ ጠፍተውብህ ያውቃሉ? 😳 ብዙ ሰዎች እንግሊዝኛ ይገባቸዋል፤ ነገር ግን ለመናገር ሲሞክሩ በራስ መተማመን ያንሳቸዋል። ከYimaru ጋር በመለማመድ እንግሊዝኛን በል
እንግሊዝኛ ለመናገር ስትሞክር ቃላቱ ጠፍተውብህ ያውቃሉ? 😳 ብዙ ሰዎች እንግሊዝኛ ይገባቸዋል፤ ነገር ግን ለመናገር ሲሞክሩ በራስ መተማመን ያንሳቸዋል። ከYimaru ጋር በመለማመድ እንግሊዝኛን በልበ ሙሉነት መናገር ጀምር! 🎥 Free Video Lessons 💬 Free Conversation Practice 👨‍🏫 Expert Guidance & Practice Materials ዛሬ መለማመድ ጀምር፤ ነገ በራስ መተማመን ተናገር! 🚀 📲 Download the Yimaru App: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.yimaru.lms.app 📞 For help and inquiries: 0946396655 💬 Telegram: @yimarusup 📢 Telegram Channel: https://t.me/yimaru

የማይቀር ቀጠሮ 🤌🏾

ሁሉም ልክ ነኝ ካለ ማንም ልክ አይሆንም! ሁሉም ለራሱ 'ትክክል' ነው" የሚል ደካማ ፍልስፍና አብሮ አያኗኑርም፤ ኧረ ራስንም አያኖርም። ቢያንስ ለጋራ ጉዳይ የጋራ ልክ፣ የጋራ መለኪያና የጋራ ዳኝነትም መኖር አለበት። ባይፃፍም ባይደነገግም እንደሰው በጋራ ፀያፍ የሆነ ፣ በጋራ ህመም የሆነ ነገር አለኮ። ሁሉም ነገራችን በየጓዳ ልምዳችን ሆነ የሚተረጎመው። ሞት እዚህ ሌላ፣ እዛ ሌላ ሆኖ ይተረጎማል፤ ጦርነት፣ ልማት፣ ርሃብ፣ ጥጋብ፣ ውጤቱ አንድ ሆኖ ትርጉሙ የየቅል ሆነብን። በጋራ ማዘን፣ የጋራ አቋምና መርህ መያዝ ግራ ሆነብን። የሆነውን ነገር የምንኮንነውም ልክና ሰህተት የምንለውም በአድራጊው ማንነትና መለኪያ እንጅ በነገሩ ውጤት አልሆን አለ። የሾርባ ማንኪያው ዓይነት ነገር... ​ዶክተሩ ለአንድ ታካሚ መድኃኒት ያዝለታል። "በቀን አንድ የሾርባ ማንኪያ ብቻ ትወስዳለህ" ከሚል ሙያዊ ትዕዛዝ ጋር! በቀጣዩ ቀን ሰውየው ሆዱ ተነፋፍቶና እከክ በእከክ ሆኖ፣ ሽቅብ ቁልቁል እያዳፋው በቃሬዛ መጣ። ዶክተሩ ጠየቀ፦ ​"ምን ሆኖ ነው?" ​"እርስዎ ያዘዙለትን መድኃኒት ባዘዙት መሠረት ሲወስድ እንዲህ ሆነ።" ​"በስህተት አብዝቶ ወስዶ ይሆን?" ​"ኧረ በጭራሽ ዶክተር! በሾርባ ማንኪያ አሉ፣ ሳይጨምር ሳይቀንስ በሾርባ ማንኪያ ለክቶ ጠጣ፤ ይኸው እንደውም ማንኪያውንም ይዘነዋል" ብለው የድግስ ጭልፋ የሚያክል የእንጨት ማንኪያ አሳዩት። ዶክተሩ ደነገጠ። ​"ምንድነው ይሄ? በሾርባ ማንኪያ ነበር እኮ ያልኩት!" ​"ዶክተር፤ እንግዲህ እኛ ሾርባ የምንጠጣው በዚህ ነው!!" ​ፍትህ፣ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ ክብር፣ ወንጀል፣ ድህነት... እንዴት ነው ሰዋዊ ከሆነው የህሊና መለኪያ ይልቅ በየራሳችን ሰፈርና ጓዳ እሳቤ፣ በተበላሸ አስተዳደግና በመሃይምነታችን የሚለካው? የተማረውም በሚሰጠን ባዕድ መስፈሪያ ከእኛ መስፈሪያ የየቅል የሚሆነው እስከመቸ? የሚዲያው መስፈሪያ ምድር ላይ ካለው የማይቀራረበው እስከመቸ? እንዴትስ ነው በምላሳችን ጫፍ የማንቀምሰውን ኮሶ ለሌላው በጭልፋ ሙሉ የምንግተው? መቼስ ነው በደል እንደ በደል፣ ፍትህም እንደ ፍትህ በራሱ ተፈጥሯዊ መጠን የሚታየው? መቼ? ©አሌክስ አብርሃም ሁሌም ማንበብ!

Evolve_Your_Brain_The_Science_of_Changing_Your_Mind_PDFDrive_.pdf3.59 MB

LEARNING A NEW SKILL: Your Brain Literally Rewires Itself 🧠 The first time you learn something new, your brain has to build
LEARNING A NEW SKILL: Your Brain Literally Rewires Itself 🧠 The first time you learn something new, your brain has to build the pathway. Practice it again… and again… and those neural circuits can become more efficient. That’s why something that feels difficult at first can eventually feel almost automatic. You’re not just learning the skill — your brain is adapting to the practice. 🧠⚡ Discover the science of neuroplasticity and how repeated practice can change the way your brain processes and performs a skill. From learning an instrument to speaking a new language, your brain is constantly adapting. Engaged in reading always!

#ዐካኪ እና #ዘራፍ #ዐካኪ_ዘራፍ ዕድሜ ልኬን የሰማኹት ሐረግ ነው። በልጅነት “ዘራፍ፣ አቃቂ ዘራፍ” ሁሉ እንል ነበር - ከዐካኪ ይልቅ አቃቂ ለቂርቆሶች (ለጆሯችንም) ቅርብ ስለነበር። እንደው ዘራፍዬ፣ ዘራፍ ዘራፍዋ … አብሬ ዘፍኛለኹ፤ በፉጨትም ቢኾን። “ዐካኪ ምንድነው? ዘራፍስ?” ብዬ ጠይቄ ግን አላውቅም፤ ትርጉሙን የማላውቀው መስሎኝ አያውቅም። ትናንት አንድ መዝገበ ቃላት #ኤዲት እያደረግኹ አንድ አተረጓጎም አልጥም ብሎኝ፣ አማራጭ ፍለጋ የአለቃ #ደስታ_ተክለ_ወልድን መዝገበ ቃላት እያገላበጥኩ ነበር። ከቃል ቃል እየተሻገርኹ፣ “ዐካኪ” ጋ ደረስኹ። ፍችው አስገረመኝ፦ “#ዐካኪ፤ (ሐካኪ)፤ ያከከ፣ የሚያክ፤ ቧጫሪ፣ ቧጣጭ፣ ሰንዛሪ፣ ጥፍራም አውሬ።” እና “ዐካኪ ዘራፍ”ን ከቧጫሪ፣ ቧጣጭ፣ ሰንዛሪ፣ ጥፍራም አውሬ ጋራ ምን አገናኘው? “ዐካኪ ዘራፍ፤ የፉከራ ቃል፤ ዐካኪን የሚዘርፍ፣ የሚቀማ፣ ካንበሳ፣ ከድብ በግን የሚያስጥል (1ኛ ሳሙ. 17፥34-37)። ዐካኪ ‘አካኪ’ ተብሎ ቢጻፍ ግን፦ አዋኪ፣ አሸባሪ፣ በጦር ሜዳ ተከራካሪ፣ የጎበዝ ጎበዝ ማለት ነው (1ኛ ሳሙ. 17፥46-51-37)። (መጀመሪያ በተጠቀሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፣ የተናቀው ብላቴና ዳዊት በጎቹን ከአንበሳ እና ከድብ መንጋጋ ስለመንጠቁ ለሳኦል ይነግረዋል - አለቃ ደስታ ይህን ይዘው ዳዊት “ጥፍራም አውሬን የነጠቅኹ ዐካኪ ዘራፍ ነኝ” እንዳለ ይተረጉሙልናል።) የ#ከሳቴ_ብርሃን_ተሰማ መዝገበ ቃላት ደግሞ “አካኪ ዘራፍ”ን ሲፈታው እንዲህ ይላል፦ “በጥኑ ጦርነትና ባፍላ ውጊያ ላይ ዐምስት ወይም ዐሥር የኾኑ የተወረወሩ የጠላቶች ጦሮች ጋሻውን ወይም ሰውነቱን ሳይወጉት አምልጦ እነዚያ ተወርውረው የሳቱትን ጦሮች የዘረፈ አካኪ ዘራፍ ነው ይባላል።” (ኹለተኛው የአለቃ ደስታ ጥቅስ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ ዳዊት ጎልያድን በወንጭፍ ገድሎ፣ በጉልቤው ጎልያድ ሰይፍ አንገቱን ቆርጦ ይጥላል፤ ሰይፉን ዘርፎ ይሰይፈዋል፡፡ - ዳዊት እዚህም አ(ዐ)ካኪ ዘራፍ ኾኖ ይገኛል) -- [This is what we call #intertextuality in literature.] ለማንኛውም “ዐካኪ ዘራፍ” - የገዛ በጎቹን ከነጣቂ መንጋጋ የሚያድን ወይም የተሰነዘረበትን የጠላቱን/የተጻራሪውን መሣሪያ ጠላቱን ለማጥቃት የሚጠቀም ነው። ዝም ብሎ ፉከራ ወለድ፣ የስሜት ሐረግ እንዳይመስላችኹ። የጦር ቃል ብቻም እንዳይመስላችኹ። ራሳቸውን/ ምንትነታቸውን (identity)/ እሴቶቻቸውን (values)/ ልጆቻቸውን ከነጣቂ የዘመን መንጋጋ ራሱ ዘመኑ በወለደው መላ የሚያድኑትን ብርቱዎች ኹሉ ለማሞገስ የሚኾንም ቅፅል ነው። አቃቂ ዘራፍ ግን አይባልም። 😉 © ቴዎድሮስ አጥላው ሁሌም ማንበብ!

The Politics of Public–Private Partnerships and International Development: Insights from Ethiopia Publisher: Routledge (2026) Genre/Field: Critical Development Studies / Political Anthropology / Public Policy Executive Summary Emerging in response to UN Agenda 2030 and the global push to finance the Sustainable Development Goals (SDGs), The Politics of Public–Private Partnerships and International Development provides a critical, ground-level examination of how Public–Private Partnerships (PPPs) function in practice. Rather than treating PPPs as purely technocratic or neutral policy mechanisms, this volume unpacks the underlying political, ideological, and socio-economic dynamics when global policy models encounter local institutional landscapes in Ethiopia. Core Themes & Analytical Framework Deconstructing the "PPP Paradox": While international institutions and donors market PPPs under a unified, consensus-driven umbrella, the book illustrates that no single, universally accepted definition of a PPP exists. In execution, they represent a complex spectrum of arrangements with competing agendas. Bottom-Up & Anthropological Lens: Rooted in empirical fieldwork, the text examines how high-level development rhetoric translates into daily governance, questioning how power asymmetries shift between state authorities, donor agencies, and private corporations. State–Society Relations & Selective Adaptation: Through its deep focus on Ethiopia, the book analyzes how local actors selectively adopt, reframe, and internalize global policy prescriptions ("selective learning") to serve domestic political priorities, reconfiguring the boundary between the state and the market. Critical Evaluation Strengths: Contextual Depth: Moves beyond standard macroeconomic evaluations by integrating ethnographic insights and political anthropology. Interdisciplinary Rigor: Successfully bridges policy studies, critical global health, and international political economy. Nuanced Critique: Avoids binary views (pro- vs. anti-privatization) to instead explore the subtle mechanics of how public goals and private interests collide and reshape one another. Target Audience: An essential read for scholars, policy analysts, and graduate students in international development, public administration, African politics, and development anthropology. ©Editors: Jon Harald Sande Lie, Paul Beaumont, and Marit Tolo Østebø Engaged in reading always!

The_Politics_of_Public–Private_Partnerships_and_International_Development.pdf3.59 MB