fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

መጽሐፍቶችን በpdf📚

መጽሐፍቶችን በpdf📚

رفتن به کانال در Telegram

"እንኳን ደህና መጣችሁ"Welcome! በpdf(በሶፍት ኮፒ) ለማንበብ ራሳችንን እናስለምድ! ፨ተራ ነገር በመስራት የሚባክነውን ጊዜያችንን በንባብ ላይ ስናውለው ከራሳችን አልፈን ለብዙዎች የመለወጥ ምክንያት እንሆናለን፡የንባብ ባህላችንን እናዳብር! ባለንበት ራሳችንን በእውቀት እንገንባ! ፨በዚህ ቻናል የተለያዩ መፅሐፎች፣ጠቃሚ ሀሳቦች፣አፕልኬሽኖች፣አነቃቂ ምስሎች ቀርቦላችኋል አውርደው ይጠቀሙ።

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام መጽሐፍቶችን በpdf📚

کانال መጽሐፍቶችን በpdf📚 (@pdfffb) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 18 139 مشترک است و جایگاه 2 024 را در دسته کتب و رتبه 1 999 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 18 139 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 26 اکتبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 598 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 15 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 17.72% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 5.11% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 3 208 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 926 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 20 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
“"እንኳን ደህና መጣችሁ"Welcome! በpdf(በሶፍት ኮፒ) ለማንበብ ራሳችንን እናስለምድ! ፨ተራ ነገር በመስራት የሚባክነውን ጊዜያችንን በንባብ ላይ ስናውለው ከራሳችን አልፈን ለብዙዎች የመለወጥ ምክንያት እንሆናለን፡የንባብ ባህላችንን እናዳብር! ባለንበት ራሳችንን በእውቀት እንገንባ! ፨በዚህ ቻናል የተለያዩ መፅሐፎች፣ጠቃሚ ሀሳቦች፣አፕልኬሽኖች፣አነቃቂ ምስሎች ቀርቦላችኋል አውርደው ይጠቀሙ።”

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 28 اکتبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته کتب تبدیل کرده‌اند.

18 139
مشترکین
+1524 ساعت
+1437 روز
+59830 روز
آرشیو پست ها
ያገር መዓዛ ምሽት! አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት! የ62ኛ ምሽት እንግዳችን፤ በኢትዮጵያ የሬዲዮ ጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ የማይፋቅ አሻራዋን ያኖረች፤ በቃል ጥበቧ ትውልድን ያነጋገረች፤ የሰዎችን የሕይወት
ያገር መዓዛ ምሽት! አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት! የ62ኛ ምሽት እንግዳችን፤ በኢትዮጵያ የሬዲዮ ጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ የማይፋቅ አሻራዋን ያኖረች፤ በቃል ጥበቧ ትውልድን ያነጋገረች፤ የሰዎችን የሕይወት ታሪክ በጥበብ የምትፈታ፤ አንጋፋዋ የሚዲያ ባለሟል መዓዛ ብሩ ናት! ያገር መዓዛ ምሽት! ለዓመታት ብዙ ሺዎችን ስታነጋግር፣ የታሪክ ጓዳቸውን ስትበረብር፤ የሕይወት መንገዳቸውን ስትፈትሽ የኖረችው ልሳነ-ርቱዋ መዓዛ ብሩ በዚህ ታሪካዊ ምሽት የእርሷን የራሷን ታሪክ ታወጋናለች! ጠያቂዋ ትጠየቃለች! እንግዳ አክባሪዋ ትከበራለች! ከሕይወት ጉዞዋ፤ ከሙያዊ ፍልስፍናዋ፤ ከ"ጨዋታ" እስከ "ሸገር" ተረማምዳ ካለፈቻቸውና ካሳለፈቻቸው የሚዲያ ሙያዊ ጉዞዋ፤ ከማይረሱ የስቱዲዮ ትዝታዎቿ፤ ከድልና ከፈተና የሕይወት አጋጣሚዎቿ ያለስስት ጠልቀን እየቀዳን እንጎነጭ ዘንድ ልቧን፣ አእምሮዋን፣ መንፈሷን፣...ግልጽ አድርጋ በልዩ እመቤታዊ ትህትና ትቀርብልናለች፡፡ እኛም ከአየር ሞገድ እመቤቲቱ ፍቅር የተሞላበት ደግ ልቧ ጠልቀን በነጻነት እንዋኛለን፡፡ ያለገደብ እናወጋታለን፡፡ በፍቅር እናዳምጣታለን! የጥበብ ማዕዳችን ሰፊ፤ ገበታችንም ሙሉ ነው! ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ሂስና ዳንስ እንደተለመደው ዓይነት በዓይነት ተዘጋጅተውላችኋል። 📅 ረቡዕ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 ዓ.ም. 🕠 11:30 ሰዓት 📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ አንድ ምሽት፣ ብዙ ታሪኮች! አንድ መድረክ፣ ሺህ ስሜቶች! ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

The more that you read, the more things you will know. The more that you learn, the more places you'll go. Dr. Seuss

Anna Karenina Leo Tolstoy’s Anna Karenina, first published in book form in 1878, stands as a supreme monument of realist fiction and psychological depth. Famously summarized by its opening line—"All happy families are alike; each unhappy family is unhappy in its own way"—the novel explores the inescapable consequences of individual choices against the rigid architecture of 19th-century Russian high society. Narrative Architecture and Dual Plotlines The novel’s structural brilliance lies in its dual plot, which juxtaposes the tragic trajectory of Anna Arkadyevna Karenina with the philosophical and domestic search for meaning undertaken by Konstantin Levin. The Tragic Arc: Anna’s affair with the dashing cavalry officer Count Alexei Vronsky shatters her social standing. Tolstoy traces the psychological erosion of Anna’s character, driven not merely by societal condemnation, but by her own consuming jealousy, isolation, and guilt over abandoning her son. The Thematic Counterpoint: Levin serves as Tolstoy’s semi-autobiographical mouthpiece. Through Levin’s struggles with agrarian reform, existential despair, and spiritual awakening, Tolstoy examines the values of labor, faith, and sincerity against the hollow materialism of St. Petersburg and Moscow aristocrats. Characterization and Psychological Realism Tolstoy pioneered a granular, shifting interiority that renders his characters with startling human contradiction. Anna is neither a simple villain nor a pure victim; she is vibrant, intelligent, and trapped by a society that demands absolute hypocrisy. Similarly, figures like Karenin (her rigid, emotionally stunted husband) and Oblonsky (her charming, unrepentant brother) are rendered with profound empathy and clinical psychological precision, refusing easy moral categorization. Themes and Motifs Society vs. Individual Authenticity: The novel interrogates the hypocrisy of aristocratic institutions, contrasting the artificiality of urban salons with the grounded, cyclical rhythms of rural life. Love and Destruction: Tolstoy contrasts various manifestations of love—destructive passion, companionate marriage, dutiful affection, and spiritual grace—evaluating how each shapes human fulfillment. Faith and Mortality: Particularly through Levin, the novel grapples with nihilism and the desperate human need for an ethical framework that transcends death. Literary Legacy Anna Karenina remains a masterclass in narrative pacing, thematic coherence, and philosophical inquiry. By uniting sweeping social critique with microscopic psychological observation, Tolstoy created a work that transcends its historical era, remaining a definitive exploration of human desire, conscience, and consequence. Engaged in reading, always.

Engaged in reading, always.📖✨

እኔኮ የማደንቃቸውም የምቃወማቸውም ፖለቲከኞች አሉ። የሚሰማኝን ልፅፍ ጣቴን ኪቦርድ ላይ ሳሳርፍ ግን " ነገ ጧት ከእንቅልፌ ስነሳ ቦታ ተቀያይረው ቢጠብቁኝስ" የሚል ስጋት ውል ይልብኛል። አውቃለሁ ፖለቲካ የፅድቅ መንገድ አይደለም ፤ ጥቅምን አመዛዝኖ ለአገርና ሕዝብ ይበጃል ላሉት ጉዳይ አቋምን መቀየር የተለመደ ነው። ግን ሲጀመር አቋም የሚባል ነገር ያለው ስንቱ ነው? ለምሳሌ አሁን ቀይ ባህር ወይ ሞት ከሚሉት 80 በመቶወቹ ተሟሙተው ኤርትራን የሸኙ፣ ኤርትራ ለምን ተገነጠለች ያሉትን ያሰሩ ያሰቃዮ ያሰደዱና ያስገደሉም ናቸው። እሽ ተፀፅተው ነው እንዳንል አሁንም ዶ/ር ዐብይ ነገ በቲቪ ብቅ ብሎ "ቀይ ባህር አያስፈልገንም" ቢል እነዚሁ ሰወች "እንኳን ቀይ ባህር ቀይ ወጥ ራሱ አያስፈልገንም" ከማለት አይመለሱም። ጉዳዮ ወደብ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም አይደለም፤ እነዚህ ሰወች አገር ነው የሚፈልጉት ወይስ ስልጣንና ጥቅም? ይሄ ሁሉ ወጣት የሚጫረሰው በእነሱ ስህተት ነው አሁንም ስህተት ያሉትን ለማረም ሌላ ትውልድ መገበር አለበት። ፖለቲከኞቻችንኮ እንደሚያሳዮት ባህሪ እንኳን ሰው የራሳቸው ጥላ አምኖ አይከተላቸውም። እንደሰወቹ የሚቀያየር የአገር ጥቅም ሳይሆን ሰወች እየተቀያየሩ የሚያስቀጥሉት ዘላቂ አገራዊ ጥቅም የትኛው ነው?

‎ቅዳሜ ጠዋት ከ4:00 ጀምሮ 📅 ‎ ‎ዋልያ መጻሕፍት እና የሐሳብ መድረክ 📚 ‎ ‎የአእምሮ ጤና እና የዕለት ተዕለት ሕይወታችን 🧠 ‎============================ ‎ ‎ዋልያ መጻሕፍት "የአእምሮ ጤና እና የዕለት ተዕለት ሕይወታችን" በሚል ርእስ በአእምሮ ጤና ምንነት፣ መንሥኤና መፍትሔ ላይ ትኩረት ያደረገ፣ የኅብረተሰቡን የአእምሮ ጤና ግንዛቤ የሚያሳድጉ እንዲሁም ለውጥ ለማምጣት የሚያግዙ ተሞክሮዎች የሚቀርቡበት ልዩ ሳይንሳዊ ፕሮግራም አዘጋጅቷል። ‎ ‎የዕለቱ ተጋባዥ እንግዶቻችን በአእምሮ ጤና ላይ የላቀ ዕውቀትና ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎች የሆኑት:- 👩‍⚕️ ‎ ‎ዶ/ር ዮናስ ባህረ ጥበብ ‎============== ‎ሳይካትሪስት እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሕክምና ትምህርት ክፍል መምህር ‎ ‎ ‎ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ ‎=============== ‎ሳይካትሪስት እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሕክምና ትምህርት ክፍል መምህር እንዲሁም በዩኒቨርስቲው የአእምሮ ሕክምና ክፍል ውስጥ የሡሥ  ሕክምና ሰብ-ስፔሻሊስት ‎ ‎ ‎ለፓነል ዲስከሽን የተመረጠው መጽሐፍ 📖 ‎ ‎የአእምሮ ጤና መዛባቶች፤ ምንነቶች፣ መንሥኤዎችና መፍትሔዎች። ‎ ‎ቦታ ‎ ‎📍 4 ኪሎ፣ ኢክላስ ሕንጻ፣ ዋልያ መጻሕፍት አዳራሽ ‎ ‎ቀን እና ሰዓት ‎ ‎📅 ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. ‎ ‎🕣 ጠዋት 4፡00 ጀምሮ ‎ ‎ ‎"ያነበበ ይነበባል" ‎ዋልያ መጻሕፍት

📚✨ የመጽሐፍ ፊርማ ዝግጅት በጃዕፈር መጻሕፍት ! ✍️ በEBS ቴሌቪዥን ቴክኖሎጂ ነክ በሆኑ ዝግጅቱ የምታውቁት የቴክኖሎጂ ባለሙያና የ " ግርምተ ሳይቴክ " መጽሐፍ አዘጋጅ ሰለሞን ሙሉጌታ ካሳ ሰሞኑም " አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ " የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃቱ ይታወቃል ! ይህንንም በማስመልከት ሰለሞን ሙሉጌታ ካሳ የፊታችን ቅዳሜ 14 በጃዕፈር መጻሕፍት በመገኘት የፊርማ ዝግጅት ያደርጋል 📖 የሚወዱትን መጽሐፍ ከደራሲው ፊርማ ጋር ለማግኘት ደራሲውን በአካል ለመገናኘትና በዚህ ልዩ የንባብ ዝግጅት ለመሳተፍ ቅዳሜ በ 14 እንዳይቀሩ ! 📅 ቀን፦ የፊታችን ቅዳሜ 14 📍 ቦታ፦ ጃዕፈር መጻሕፍት 📚 ይህን ልዩ አጋጣሚ እንዳያመልጥዎ፤ ከእኛ ጋር ይሁኑ!

አንጀቴን ያራሰው ምላሽ! የሆነ ነገር ላይ አይቼው ነው። ​ወጣቱ አውቶብስ ውስጥ ወንበር ይዞ ሲጓዝ አንዲት ባልቴት ቆማ ይመለከትና ተነስቶ ያስቀምጣታል። ባልቴቷ ከማመስገን ይልቅ በቀጥታ ወደ ጥያቄ ገባች። ​«ስንት ዓመትህ ነው?» «ሃያ ስምንት።» «እና በዚህ ዕድሜህ በአውቶብስ ትጋፋለህ? የኔ ልጅ በሃያ አምስት ዓመቱ ተፍ ተፍ ብሎ ምን የመሰለ መኪና ገዝቶ ይንፈላሰሳል፤ አትስነፍ፣ ነቃ በል እንጂ!» ​ወጣቱ ፈገግ ብሎ... «አልሰነፍኩም... እኔም ሌት ከቀን ሰርቼ መኪና ገዝቻለሁ።» «የታለ?» «እናቴ በስተርጅና አውቶብስ ላይ እንዳትጋፋ ሰጥቻት ነው።» ሁሌም ማንበብ!

፩. የመጽሐፉ መሠረታዊ መረጃዎች የመጽሐፉ ርዕስ፦ እኛና አብዮቱ ደራሲ፦ ሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ አሳታሚ፦ ፀሐይ አሳታሚና አከፋፋይ ድርጅት ፪. የስነ-ጽሑፋዊና የታሪክ ይዘት ማብራሪያ «እኛና አብዮቱ» በኢትዮጵያ ዘመናዊ የታሪክ እና የፖለቲካ ስነ-ጽሑፍ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የትዝታ/የታሪክ ማስታወሻ (Memoirs) መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ የተጻፈው በደርግ መንግሥት ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት በሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ ነው። ሀ) የትረካው ጭብጥ እና ትኩረት የደርግ አመሠራረትና የሥልጣን ጉዞ፦ መጽሐፉ የ1966ቱን የኢትዮጵያ አብዮት መፈንዳት፣ የደርግ (የወታደራዊ አስተዳደር) አደረጃጀት፣ እንዴት እንደተቋቋመ እና ወደ ሥልጣን እንደመጣ ከውስጥ አዋቂ እይታ አንጻር ያቀርባል። የውስጥ ሽኩቻዎችና የፖለቲካ ውሳኔዎች፦ በደርግ አባላት መካከል የነበሩትን ውጥረቶች፣ የነበረውን የአመራር ሂደት፣ የሻምበል መንግሥቱ ኃይለማሪያምን ወደ ከፍተኛ ሥልጣን መውጣት እንዲሁም በወቅቱ የተወሰዱ ዋና ዋና የፖለቲካ እና ወታደራዊ ውሳኔዎችን በዝርዝር ይተነትናል። የወቅቱ ሁነቶች፦ በሀገሪቱ የነበረውን «ቀይ ሽብር» እና «ነጭ ሽብር»፣ የኤርትራና የትግራይ አማፂያንን ትግል፣ የሶማሊያን ወረራ እና የውጭ ሀገራት (ለአብነት ያህል የሶቪየት ህብረት እና ኩባ) ጋር የነበረውን ግንኙነት ያብራራል። ለ) የስነ-ጽሑፍ ዘStyle እና የአጻጻፍ ስልት የግል ማስታወሻና የታሪክ ሰነድ (Autobiographical History)፦ ደራሲው የድርጊቱ አካልና ዋና ተሳታፊ ስለነበሩ ትረካው በቀጥታ እይታ (First-person narrative) የቀረበ ነው። ሰነዶችን ማጣቀስ፦ ደራሲው የራሳቸውን ትዝታ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ታሪካዊ ሰነዶችን፣ የስብሰባ ቃለ-ጉባኤዎችንና የጽሑፍ ማስረጃዎችን በመጠቀም ትረካውን ለማጠናከር ሞክረዋል። ቋንቋና አቀራረብ፦ የአጻጻፍ ስልቱ ግልጽ፣ ቀጥተኛና የዚያን ዘመን የፖለቲካና የወታደራዊ ቃላትንና መግለጫዎችን በስፋት የሚጠቀም ነው። ፫. የመጽሐፉ ፋይዳና የታሪክ እሴት የውስጥ እይታ (Insider Account)፦ በኢትዮጵያ አብዮት ዘመን ከፍተኛ ሥልጣን ላይ ከነበሩት ጥቂት ግለሰቦች አንዱ የጻፉት በመሆኑ፣ በታሪክ ተመራማሪዎችና አንባቢያን ዘንድ የወቅቱን ወታደራዊ መንግሥት አሰራር ለመረዳት እንደ አስፈላጊ የታሪክ ምንጭ ይወሰዳል። ለታሪክ ክርክሮች የሚሰጠው ምላሽ፦ ከደርግ ውድቀት በኋላ የተጻፈ በመሆኑ፣ ደራሲው የደርግን አስተዳደር ድክመቶችና ጥንካሬዎች ለመገምገም፣ እንዲሁም ይደርስባቸው ለነበሩ ትችቶች የራሳቸውን ምላሽ ለማስቀመጥ ሞክረዋል። በአጠቃላይ «እኛና አብዮቱ» የ20ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ታሪክ፣ የአብዮቱን ሂደትና የደርግን አስተዳደር ለመረዳት የሚረዳ ትልቅ ስነ-ጽሑፋዊና ታሪካዊ ሀብት ነው። ሁሌም ማንበብ!

🫴🏽📖

ሰው ጤነኛ የሚባለው ከላይ ፈጣሪን ሲፈራ፡ ከጎን ሰውን ሲያፍር ፡ ከውስጥ ህሊናውን ሲያዳምጥ ነው። ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሀጂ ኡመር እንድሪስ
ሰው ጤነኛ የሚባለው ከላይ ፈጣሪን ሲፈራ፡ ከጎን ሰውን ሲያፍር ፡ ከውስጥ ህሊናውን ሲያዳምጥ ነው።
 ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሀጂ ኡመር እንድሪስ

The Practice of Conceptual History In The Practice of Conceptual History, German historian and theorist Reinhart Koselleck presents a transformative approach to understanding how history is shaped, experienced, and written. At its core, the text investigates Begriffsgeschichte (conceptual history)—the study of how political and social concepts are not static labels for objects or events, but dynamic indicators and catalysts of historical change. Rather than viewing history as a simple chronological sequence of events, Koselleck argues that historical consciousness rests upon complex structures of time, space, and language. Key Thematic Pillars 1. Words vs. Concepts Koselleck draws a crucial distinction between ordinary words and historical concepts: Words can have unambiguous, singular meanings. Concepts aggregate a multiplicity of historical experiences, conflicts, expectations, and political claims into a single term (e.g., state, revolution, democracy, freedom). Concepts are both indicators of historical change (reflecting social transformations) and factors in change (shaping how individuals act and conceive their future). 2. The Sattelzeit (Threshold Period, c. 1750–1850) A central thesis of Koselleck’s work is the concept of the Sattelzeit—the "saddle period" spanning the late 18th to the mid-19th century. During this era of political revolution and industrialization, language underwent a fundamental shift: Classical concepts were temporalized, democratized, and ideologized. Concepts shifted from describing static states of being to reflecting movement, process, and future-oriented goals (e.g., the concept of progress or history as a singular, grand process rather than a collection of stories). 3. Space of Experience and Horizon of Expectation Koselleck introduces two fundamental anthropological categories to explain how humans experience historical time: Space of Experience (Erfahrungsraum): The accumulated past that shapes present reality, memories, and institutional structures. Horizon of Expectation (Erwartungshorizont): The future possibilities, hopes, anxieties, and goals that drive human action. In traditional societies, experience and expectation were closely aligned; the past dictated what the future would hold. Modernity, however, is defined by a widening gap between experience and expectation: the future is increasingly perceived as unknown, open, and capable of being actively shaped or "made" through political and social action. 4. Sedimented Layers of Time (Zeitschichten) Borrowing a metaphor from geology, Koselleck challenges linear views of historical progression. He posits that historical time exists in multiple, overlapping layers—short-term events, medium-term structural trends, and long-term anthropological realities. These distinct temporalities operate simultaneously, giving historical periods their complex, layered quality. Significance to Historiography and Theory Bridging Social History and Linguistics: Koselleck refuses to treat language as a mere mirror of social reality or social history as independent of language. Instead, conceptual history acts as the crucial intersection where social structures and linguistic representations continually inform each other. Understanding Modernity: The volume provides a theoretical framework for diagnosing modernity. Modern political debates are shown to be fundamentally ideological struggles over who controls the meaning of key concepts that define human agency, historical direction, and societal goals. Engaged in reading always!

👌🏾

«ፍቅርና ጦርነት አጀማመሩ እንጂ አጨራረሱ አይታወቅም!» — (አሌክስ አብርሃም) ​ትራምፕ ጥላው እንኳን የሚያስፈራ የጦር መርከብ አስጠግተው «ኢራንን ተሰናበቷት» ሲሉ ዓለም ኢራንን እንደገና እናያታለን አላለም ነበር፤ ኢራን አለች፣ መኖር ብቻ... የአለም ጉሮሮ ላይ እንደ አሳ እሾህ ተሰክታ አትዋጥ አትተፋ። ​ሩስያ በኪሎ ሜትሮች በሚግተለተል ባቡር ታንክ ጭና ወደ ዩክሬን ስትገሰግስ «ያ ኮሜዲያን አለቀለት፣ ቻው ዩክሬን» ተባለ፤ አራት ዓመት ይኸው የአለማችን ዘግናኝ ጦርነት ሆኖ ቀጥሏል። ​ወደኋላ አፍጋኒስታንን ተመልከቱ በሶቪየት ህብረት፣ በኋላም በአሜሪካ ያልዘነበባት፣ ያልተሞከረባት ዘመናዊ መሣሪያ አልነበረም፤ (ከኒውክሌር መልስ ) በመጨረሻ «የኢምፓየሮች መቃብር» ተብላ አረፈችው። እነዚያ የዋህ መሳይ ያልሰለጠኑ የሚባሉት ሕዝቦች እነዚህን ግዙፍ አገራት ከአገራቸው ለማስወጣት ለአመታት ተዋጉ ብዙ ወጣት ሴትና ህፃናት ገበሩ። በ20ኛው ክፍለ ዘመን የሶቪየት ህብረትን፣ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ የአሜሪካንና የኔቶን (የ32 አገራት ጦር ስብስብ) ጦር ሁሉንም አስወጡ። ያወጣጡስ ክፋት። ​ትላንት ፋኖ ጋር ጦርነት ሲጀመር በሳምንታት ነገሮች ልክ ይገባሉ ተብሎ ነበር፤ ከአራት ዓመት በኋላ የገባንበትን ተመልከቱ! ሕወሓት ጋር ጦርነት ይኸው አሁንም ቀጥሏል፤ ኦነግ ጠፋ፣ ተበተነ ከተባልን ስንት ዓመቱ!? ​ቬትናም፣ የየመን ሁቲዎች ወዘተ... ወደኋላም ወደፊትም ታሪክ የሚነግረን ተመሳሳይ ነው። አሁን ኤርትራና ኢትዮጵያ መሃል የሚደረገው ዛቻና ፉከራ ምኑም የማያምር ነው፣ ጦርነት ከተጀመረም መቼም የማያልቅ እልቂት የሚያስከትል ትልቅ ስህተት ነው የሚሆነው። ጥፋቱ የማነው አይደለም ጥያቄው፤ ማን ያሸንፋል አይደለም ጉዳዮ... የአገራት የጦር ግዝፈትም ይሁን ደካማነት ለጦርነት ፍጻሜ ዋስትና አይሆንም።
ጥይትና ወታደር ያልቃል፤ ጥላቻ ቂምና የአገር ፍቅር ስሜት ዘላለም ያዋጋል
ማንም አገሬ አጥፍታለች አይልም። ምክንያት ኖረ አልኖረ መሪወች ጦርነት ካወጁ ሕዝብ ተቧድኖ መተላለቁ አይቀርም። ይሄ አቧራውን አራግፎ ለትንታኔ የተነሳ አሙቁልኝ ሁሉ ነገ እንዴት እጁን ታጥቦ ዞር እንደሚል በአሥር ዓመት አሥር ጊዜ አይተናል። በወዲያም በወዲህም ያላችሁ እባካችሁ ተረጋጉ። የኛዎቹ ኢሳያስ የሚባለውን ሰውዬ ማስወገድ ሰላም የሚያመጣ ከመሰላችሁ ከታሪክ ተማሩ፤ ጋዳፊ ተገደለ በየመንደሩ ጋዳፊ ማረን የሚያስብል የጎበዝ አለቃ ተፈጠረ፣ ሳዳም ተገደለ በየመንደሩ ብዙ ወሮበላ ተፈጠረ፤ አንባገነን መሪዎችን መግደልም ይሁን ማስወገድ ታሽጎ የኖረውን የጂኒን ጠርሙዝ መክፈት ነው።)) እንቢ ካላችሁ ፈጣሪ ለንፁሃን ይራራ! ©አሌክስ አብርሃም ሁሌም ማንበብ!

Do not use your energy to Worry. Use your energy to Believe, to create, to learn, to Think and grow. 🌱 Professor Richard Feynman

✨
✨

ሁላችንም ቅምጥ አለን! ​ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምናያቸው "የባህል ልብሶቻችን" ለሥራ ፈትና ለቦዘኔ የሚሆኑ፣ ለምንም የማይመቹ የጨርቅና ጌጣጌጥ ክምር ሆነዋል። በተለይ አሁን አሁን የምናያቸው የሴቶች "የባህል አልባሳት" ለሚስት እንኳን አይሆኑም፤ ሚስት ልጆች አሏት፣ ቤት አላት፣ ሥራ አላት፣ ክብር አላት። እነዚህኞቹ ታስቦባቸው "ለቅምጥ ሴቶች" የተሠሩ ዓይነት ናቸው። ቅምጥ የሚለው ቃል የሆነ ሰው ያስቀመጣት ሴት፣ ተቀምጣ ያስቀመጣትን ከመጠበቅና የወሲብ ፍላጎቱን ከማሟላት ያለፈ ምንም ሰብዓዊ ኃላፊነት የሌላት፣ ምንም የማትሠራ ሕያው አሻንጉሊት ማለት ነው። ​በነገራችን ላይ ቅምጦችን አንድ ወንድ ብቻ አይደለም የሚያስቀምጣቸው፤ በማስታወቂያ ስም ድርጅቶች ያስቀምጧቸዋል (ፕሮፌሽናል የማስታወቂያ ሠራተኞችን አይመለከትም፣ካሉ!)፣ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ያስቀምጧቸዋል፣ መንፈሳዊ ቅምጦች አሉ፣ የፖለቲካ ቅመጦች፣ የብሔር ቅምጦች... ሕዝብ ራሱ ቅምጥ ያስቀምጣል! ምንም የማትጠቅም ሴት የሕዝቡን ድብቅ የወሲብ ፍላጎት በእይታ እያሟላች ሶሻል ሚዲያ ላይ ልብስ እየቀየረች ትቀመጣለች። ሕዝቡ እንድታወራ ከፈለገ በኢንተርቪው ስም ያስወራታል (ምንትስ ተወለድኩ፣ በዚያ ወጣሁ ወረድኩ...)፣ ደንሺ ካላት ትደንሳለች፣ ሳቂ ስትባል ትገለፍጣለች፣ ሕዝቡ ከተቆጣት ቄስ፣ ፓስተር ይዛ አልቅሳ ሕዝቡ እግር ላይ ትወድቃለች፤ ይቅር ይላትና ላይክ ይሰጣታል። በሐሳቡ ይተኛታል። ​በዚህኛው ዘመን አናውቀውም እንጂ ሁላችንም ቅምጦች አሉን፣ ወይም ራሳችን ቅምጦች ነን። ሶሻል ሚዲያው በየቀኑ አዳዲስ ቅምጦችን እያመጣ እንደቆሻሻ ይደፋልናል። ልጅነታቸውን ካልጨረሱ እስከባለትዳር! ላይክ እስካደረግን ድረስ እንደፈለግን የምናቀረሽባቸው። ወደ ባህል ልብሱ ስንመጣ የጋራዥ ቱታ በባህል ልብስ ቢሠራ የሚል ሐሳብ አለኝ😀 ትንሽ ባህላችንን ወደስራ ያሰራጨው ጠገዋል። ለዚህ ኮተት ሴቶቹ የሚከፍሉትን ዋጋ ስትመለከቱ ያስደነግጣችኋል። የባህል ልብስና ቅምጥ ምን አገናኘው? የባህል ልብስ በብዛት በሚሸጥባቸው እንደ አሸንዳ ወይም በቅርቡ ለተፈጠሩ የብሔር ብሔረሰብ በዓላት ላይ የሚፎገሉ ሴቶችን እዚያው ጠይቁ። ግን ለምንድነው በተለይ ሴቶች የባህል ልብስ ላይ የሚጋደሉት? ሰው ያውም ሴት ለምና የባህል ልብስ እንዴት ትለብሳለች? ከወንዶቹ በላይ ባህ ላቸውን ስለሚያከብሩ?😀 የባህሉን ተውት፤ ሽፎን የሚባል አምስት እርምጃ ሲራመዱ ላብ ላብ ለሚጠረንን አስቀያሚ ልብስ እንዴት እንደሚጋደሉ! ሁሌም ማንበብ!

In addition to substantive theory, the encyclopedia offers thorough methodological guidance. It covers quantitative and demog
In addition to substantive theory, the encyclopedia offers thorough methodological guidance. It covers quantitative and demographic techniques such as standardization, as well as qualitative research methodologies ranging from positivist-oriented science to interpretive narrative and autoethnographic approaches. It also explores qualitative modeling frameworks—including logic, Boolean algebra, and event sequence analysis—alongside assessments of quality of life and quasi-experimental research designs. Overall, the Macmillan Encyclopedia of Sociology serves as an essential, richly documented compendium reflecting both the historical foundations and the contemporary pluralism of sociological inquiry. Engaged in reading always📖✨