cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መፅሐፍቶችን በpdf

"እንኳን ደህና መጣችሁ"Welcome! በpdf(በሶፍት ኮፒ) ለማንበብ ራሳችንን እናስለምድ! ፨ተራ ነገር በመስራት የሚባክነውን ጊዜያችንን በንባብ ላይ ስናውለው ከራሳችን አልፈን ለብዙዎች የመለወጥ ምክንያት እንሆናለን፡የንባብ ባህላችንን እናዳብር! ባለንበት ራሳችንን በእውቀት እንገንባ! ፨በዚህ ቻናል የተለያዩ መፅሐፎች፣ጠቃሚ ሀሳቦች፣አፕልኬሽኖች፣አነቃቂ ምስሎች ቀርቦላችኋል አውርደው ይጠቀሙ።

Show more
Advertising posts
2 523
Subscribers
+1424 hours
+937 days
+35730 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
Media files
760Loading...
02
በጥራት ማደግ! ሁለት አይነት እድገቶችና ትልቅነቶች አሉ፡፡ አንደኛው ውጫዊ እድገትና ትልቅነት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” ነው፡፡ 1. ውጫዊ እድገትና ትልቅነት ሰዎች በገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣ በዝና፣ በስልጣን እና በመሳሰሉት ነገሮች ሲያድጉ፣ “ውጫዊ እድገትና ትልቅነት” አገኙ እንለዋለን፡፡ ይህ እድገትና ትልቅነት ምንም እንኳን በራሱ ምንም ችግር ባይኖረውና እንዲያውም ለጥቅም የሚውል ቢሆንም ብቻውን ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ 2. “ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” ሰዎች በመልካም ስብእና፣ በጤናማ አመለካከት፣ በስሜት ብልህነት፣ በራእይ እና በጥበብ ሲያድጉ፣ “ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” አገኙ እንለዋለን፡፡ ይህ እድገትና ትልቅነት ከማንኛውም ነገር በፊት ሊቀድም የሚገባው የእድገትና የትልቅነት ዘርፍ ነው፡፡ አንድ ሰው ከላይ የተጠቀሱትን አይነት ውጫዊ እድገትንና ትልቅንን እያስመሰዘገ ውስጣዊ እድገት ሲጎድለው ከራሱ ሕይወት ጀምሮ እስከ ቤተሰቡ፣ የስራ ስምሪቱና በሃገር ደረጃ የሚያስከትለው ቀውስ ይህ ነው አይባለም፡፡ የገንዘብ አቅሙን ለማይረባ ነገርና ለሕገ-ወጥ ተግባር የሚጠቀም ማነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን? በዝናውና በታዋቂነቱ የሚኩራራውና ሰውን የሚንቀው ማን ነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን? በስልጣኑ ተጠቅሞ ሰውን የሚደቁስና እንደፈለገ የሚሆን ማን ነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን? በመጀመሪያ በውስጣችን እንደግ! ከሁሉም በፊት በጥራትና በብቃት ትልቅ እንሁን!
781Loading...
03
Elegance Unveiled: Modern Gentleman's Guide 🎩✨ 🎩✨ 1. Politeness is the truest form of sophistication. 🎩🤝 2. Chivalry is not outdated; it's timeless respect. ⚔️🕰️ 3. A gentleman's word is his bond. 🤞👨‍💼 4. Manners maketh man. 🍽️🤵 5. Hold doors open, it's a small gesture with big impact. 🚪💼 6. Cultivate a strong handshake; it speaks volumes. 🤝📈 7. Respect others' opinions, even if you disagree. 🗣️🤝 8. Stand tall, speak kindly, and dress the part. 🕴️👔 9. Offer a genuine compliment; sincerity shines. 💬🌟 10. Master the art of conversation; it's a gentleman's tool. 🗨️🎨 11. A gentleman's strength lies in his gentle touch. 💪🤲 12. Listen more than you speak; wisdom comes in silence. 👂🤐 13. Choose quality over quantity in friendships. 👬🌟 14. Apologize sincerely; it's a mark of true character. 🙏😌 15. Embrace responsibility; it's a mark of maturity. 🤔🔄 16. Gentleness is not a weakness; it's a strength. 🌼💪 17. Be punctual; it shows respect for others' time. ⏰👌 18. Treat everyone with kindness; it's a reflection of your character. 🌍💖 19. Admit mistakes gracefully; humility is attractive. 🤷‍♂️😊 20. Cultivate a sense of humor; laughter is a gentleman's ally. 😄🎭
1520Loading...
04
"ሁላችንም ሀሳብ አለን፡፡ ግን ሀሳባችን ዋጋ ያለው አይመስለንም፡፡ ሁልጊዜም ከእኛ የተለዩ፡ ከእኛ የተሻሉ "አሳቢዎች" አሉ ብለን፡ ማሰብን ለማናውቃቸው "ሌሎች" እንተወዋለን፡፡ ወይም "ማሰብ" ምሁራን የሚባሉ ሰዎች ብቻ ስራ ነው ብለን፡ ላሉብን ችግሮች አንድ መፍትሄ አምጥተው እስኪሰጡን አፍ አፋቸውን እያየን እንጠብቃለን፡፡" አለማወቅ በዶክተር ዳዊት ወንድማገኝ
1320Loading...
05
እኔ ኢትዮጵያዊያንን አላምንም! (በዓሉ ግርማ) 👉 እኔ ኢትዮጵያዊያንን አላምንም ከራሴ ጀምሮ። በጭንብል ተሸፍነን የምንኖር ህዝቦች ነን። ለሰው የምናሳየው ገፅታና እውነተኛው ባህሪያችን የተለያዩ ናቸው። እንደ ተረታችን ፣ ስነ ፅሁፋችንና ንግግራችን ባህርያችንም ሰምና ወርቅ ነው ... 👉 በዚህ ላይ ደግሞ ክፉውና በጎውን ነገር አንዱን ከሌላው ለይተን የምናይበት መለኪያ የለንም ፤ የማንኛውም ነገር መሠረታዊ መለኪያችን የግል ጥቅማችን ነው። ለዚህም ነው ተንኮል የሚበዛው፤ መተማመን የሌለው፤ የወዳጅነት ወይም የጓደኝነት ትርጉሙ የማይታወቀው ፤ ሀሜት አሉባልታና እርስ በዕርስ መበላላት የሚበዛው። ኢትዮጵያዊያን ስንባል የምናውቀው መርህ አንድ ብቻ ነው ፤ የግል ጥቅም! ከራስ በላይ ነፋስ ፤ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል... ሰውን ማመን ቀብሮ ፥ ይሉታል ከነተረቱ። የሚያሳዝን ነው... 👉 ለግል ጥቅማችን የሚበጅ ከሆነ እንዋሻለን። ስንዋሽ ህሊናችንን ቅንጣት ታህል አይቆረቁረንም። እንዴት አድርጎ ለግል ጥቅም የተገዛ ህሊና ሊቆረቁረው ይችላል? 👉 ለተንኮል አንመለስም የምንሸርበው ተንኮል ጓደኛን፤ ወዳጅን ፤ የስጋ ዘመድን አይለይም ቅናት ባህላችን ነው። 👉 ምግባር የሚባለውን ነገር በአፍ ካልሆነ በቀር በተግባር አናውቀውም። በአጠቃላይ ክፉውንና በጎውን ለይቶ የሚያይ ህሊና የለንም፤ ያስተማረንም የለም። የተማርነው ነገር ቢኖር በአደባባይ ሰው መስሎ መታየትን ነው፤ ሰው መሳይ በሸንጎ ይሉ የለም? በአደባባይ ሁሉም ጨዋ፣ ልበ ሙሉ፣ ጀግና፣ አትንኩኝ ባይ፣ ኩሩና ቅን፣ በጎ አሳቢና ታማኝ፣ አስተዋይና ትሁት ነው። በአደባባይ የምናጠልቀው ጭንብል ይህ ነው። በግል ኑሮአችን ግን ከስብቅ ፣ ከምቀኝነት ፣ ከተንኮል፣ ከቅናት ፣ ለውሸት፣ ከአሉባልታና ከሀሜት፣ ለግል ጥቅም ለመልከስከስና ለመልፈስፈስ ከፍርሃትና ከአድር ባይነት ርቀን አንገኝም። መለያ ባህርያችን ግብዝነት ነው። የግብዝነት ጭንብል አጥልቀን ነው የምንኖረው። ያለ ጭንብል እናስቀይማለን... ወይም እናምራለን፤ አይታወቅም። ያለ ጭንብል ታይተን አናውቅማ! በዓሉ ግርማ የቀይ ኮከብ ጥሪ ገፅ 234
1623Loading...
06
የሆነ ጊዜ ጓደኛዬ  እግሩን ተሰብሮ ሆስፒታል ተኝቶ ነበር ውጪ በር ላይ የተቀመጠው ወንበር ላይ  ነበርኩ ፣ ፋዘሩ እንባቸውን እየጠረጉ ከተኛበት ክፍል ሲወጡ አየኋቸው ተደናግጬ ዘው ብዬ ገባው ያቃስታል ፤  ምን ሆንክ?  አመመህ ? ስለው እያቃሰተ ስለነበረ ገላመጠኝ እያየኸኝ አይደል አይነት ፋዘር ጋ ምን አወራቹ ? እ ? "እሱ ባክህ  ...... ወንድ ልጅ አይደለህ ጠንከር በል ፣ ቀላል ነገር ነው ብሎኝ ነው ኮስተር ብሎ የወጣው" አለኝ መሃል መሃል ላይ  እያቃሰተ I think አባትነት ጨካኝ መስሎ ተሸሸጎ መባባት ነው አልኩኝ አባትነት ❤ Adhanom Mitiku
1841Loading...
07
.... " መጽሐፍት ሲበዛ ረጋ ያሉ መቼም የማይናወጡ ቋሚ ጓደኛ ናቸው ። ተደራሽነታቸው ሰፊ ፣ እጅግ ጥበበኛ ፣ በዛ ላይ ምርጥ አማካሪዎች ፣ እንዲሁም ታጋሽ የመሆን መምህር ናቸው " ( ቻርለስ ኤሎት ) ፍራንሲስ ቤከን ደግሞ እንዲህ ይለናል ፦ " አንዳንድ መጽሐፍት የሚቀመሱ ፣ አንዳንዱ ደግሞ የሚዋጡ ሲሆኑ ጥቂቶቹ ግን በሚገባ ተላምጠው ለመፈጨት ወደ ውስጣችን የሚላኩ ናቸው " 💚 እያነበብን 📖
1732Loading...
08
Media files
370Loading...
09
እውነት ተረግመናል ? ቁጥር 2 **** ለትንሽ ደቂቃ ራስህን(ንዴትህን) መቆጣጠር ካቃተህ የምትገባበት መቀመቅ ብዙ ነው። ሰሞኑን በእህታች ላይ አትላንታ ውስጥ የተፈፀመው ግድያ የስንቶችን ሕይወት ያቃውስ ይሆን ? እዚህ እኔ የምኖርበት አካባቢ አሰቃቂ የሆነ ግድያ ተፈፅሞ ነበረ ። ስለ ግድያው ከመፃፌ በፊት በብዙ የአውሮፓ ሃገራት በተለይም የስካድኔቪያን ሀገራት (ስዊዲን፣ ኖርዌይና ዴንማርክ) ክርስትናን ከመቀበላቸው በፊት ኦዲን ( Odin) በሚባል አምላክ ያምኑ ነበረ ።ኦዲን የአምላኮች ሁሉ አምላክ ነበረ። የሰው ነፍስ(ደም) ይገበርለት የነበረ ነው። በዛ ዘመን እምነታቸው መተት ተደርጎብኛል ብለው የሚያምኑ ብዙዎች ነበሩ። መተት ያደረገባቸውን ሰው ወዲያው ቢገሉት መተቱ አይለቅም ነበረ። የሚለቀው ወቅት ተጠብቆ በእጁ የሌላ ሰው ደም አስይዞ በጨረቃ ሲገደል ነበረ የሚል እምነት ነበራቸው። አንዳንዶች ደግሞ መተተኛውን ሰው ቆራርጦ መግደል መተቱን ያከሽፋል ብለው ያምኑ ነበረ። አውሮፕያውያን ክርስትናን መቀበላቸው ከአረመኔነት እንዳወጣቸው የሚያስረዱ ብዙ ፅሁፎችና ፊልሞች በአሁኑ ዘመን አሉ ።(ማወቅ የምትፈልጉ ስለ Vikings ጉግል አድርጉ) ። ወደ ዋናው ፅሁፌ ስመለስ ይህንን ዓይነት ተግባር በአሁኑ ዘመን (በሃበሻ)ይፈፀማል ብሎ ማመን ይከብዳል። ግን የፍራንክፈርት አካባቢ የአንድ ሰሞን ወሬ ነበረ ። የሚስቱን አባት ፣ የሰማኒያ ዓመት አዛውንት መተት አድርገውብኛል በማለት ገደላቸው የሚለው ወሬ እንቅልፍ ነስቶን ነበረ የከረመው ። መግደሉ አይደለም ችግሩ የተለያየውን የሰውነታቸውን አካል ቆራርጦ በፌስታል መጣሉ ነበረ አረመኔዎች ያስባለን ። ገዳዩ የጀርመን ፖሊስ ሳያጣራ አይዝምና አስከሬኑ ከተገኘ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ገዳዩ የልጃቸው የቀድሞ ባል ተይዞ አሁንም እስር ቤት ነው። ሟች ከብዙ ሰው ግንኙነት እንዳልነበራቸው ብዙዎች ያወራሉ። እንዲውም ብዙውን ጊዜያቸውን ጫካ ውስጥ ብቻቸውን ነበረ የሚያሳልፉት ይባላል። የገዳይ ከሌላ ሴት የተወለዱ ልጆች በጭንቀት በሽታ እንደሚሰቃዩ ይነገራል። ምንአልባት ገዳይን ስለ መተት ያሳሰበው ይኼ ይሆን ? የሟችን አካላት የቆራረጠበት ምክንያት መተቱን ለማክሸፍ ይሆን? ስለዚህ ጉዳይ ከገዳይ ውጭ የሚያውቅ የለም ። ግን በሰፊው የተወራው ይኼ ነበረ። አንድ በእርግጥ የማውቀው ጉዳይ ገዳይ ጥሩውን ኑሮ ትቶ እስር ቤት ውስጥ እንደሚሰቃይ ብቻ ነው።ሌላው ጊዜው ሲያልፍ እኛን አበሾችን ጫካ ውስጥ ሲያይ የሚደነግጠው ፈረንጅ ቀንሷል።(ከታች ያለው ፎቶ የኦዲን ነው) አምላክ ደህናውን ዘመን ያምጣ!
1960Loading...
10
"The Success Principles™" by Jack Canfield is a comprehensive guide to achieving success and fulfillment in various areas of life. Here are 25 key takeaways from the book : 1.  Take 100% Responsibility : 🌟 Own your life and outcomes by taking full responsibility for your actions, choices, and results. 2.  Clarify Your Vision : 🎯 Define clear goals and create a compelling vision for your ideal future. 3.  Believe in Yourself : 💪 Cultivate unshakable self-confidence and belief in your abilities. 4.  Develop a Success Mindset : 🧠 Adopt a mindset of success and abundance; think and act like a successful person. 5.  Set Clear Goals : 📅 Set specific, measurable, achievable, relevant, and time-bound (SMART) goals. 6.  Create Action Plans : 📝 Break down your goals into actionable steps and create concrete plans to achieve them. 7.  Continuous Learning : 📚 Commit to lifelong learning and personal development. 8.  Seek Feedback and Adjust : 🔄 Be open to feedback, learn from failures, and adjust your approach accordingly. 9.  Practice Persistence : 🏃‍♂️ Develop resilience and persistence to overcome obstacles and setbacks. 10.  Take Consistent Action : 🚀 Take consistent and focused action towards your goals every day. 11.  Manage Time Effectively : ⏰ Master time management and prioritize tasks based on importance and urgency. 12.  Develop Positive Habits : 🌱 Cultivate empowering habits that support your success and well-being. 13.  Surround Yourself with Positive Influences : 🤝 Surround yourself with supportive and positive people who uplift and inspire you. 14.  Practice Gratitude : 🙏 Cultivate a gratitude practice to attract more blessings and abundance into your life. 15.  Visualize Success : 🖼️ Use visualization techniques to mentally rehearse achieving your goals. 16.  Embrace Failure as Feedback : 🚫💪 View failure as a learning opportunity and stepping stone towards success. 17.  Build Resilience : 🌱 Develop emotional resilience to bounce back from challenges stronger than before. 18.  Take Calculated Risks : 🎲 Step out of your comfort zone and take calculated risks to grow and achieve more. 19.  Develop Effective Communication Skills : 🗣️ Learn to communicate assertively and persuasively to build strong relationships. 20.  Network and Build Connections : 🤝 Expand your network and build meaningful connections with others. 21.  Manage Finances Wisely : 💵 Practice financial discipline and manage your money wisely. 22.  Stay Committed to Personal Growth : 🌱 Commit to continuous personal growth and self-improvement. 23.  Celebrate Achievements : 🎉 Acknowledge and celebrate your successes along the way. 24.  Give Back and Contribute : 🤲 Make a positive impact on others and contribute to causes you believe in. 25.  Live with Purpose and Passion : 🔥 Align your actions with your values and live a purpose-driven life filled with passion and fulfillment. These principles from Jack Canfield's book provide a roadmap for achieving success, fulfillment, and personal excellence in all areas of life. Applying these principles can lead to transformative results and a more empowered, purposeful existence.
2195Loading...
11
ላብ አደር ነኝ። እንደማንኛውም የድሮ ሰው ተቀጥሮ በመስራት አምናለሁ ፤ እሞክራለሁም ። ዘመን አመጣሽ “የራስ አለቃ” ይሉት ብሂል አይዋጥልኝም ። ሰውማ አለቃ ያስፈልገዋል ። ከሰውም ደግሞ ከስልጣኔ እንዲህ ኋላ የቀረና በድህነት የሚማቅቅ እንደ እኛ አይነት ሰው በጣም አለቃ ያስፈልገዋል ። የሚገስፅ ፣ የሚቀጣ ፣ የሚያበረታታ ፣ የሚሸልም ፣ የሚያስተምር ፣ የሚመክር ፡፡ ችግሩ አለቆች ሁሉ በስፍራቸው አይደሉም። ሁሉም ሰው ደግሞ አለቃ ሊሆን አይችልም። አንዳንዶች ብቻ ለኃላፊነት ተፈጥረዋል። ስልጣኑን ይዘው ከኃላፊነቱ ገሸሽ ያሉ ብዙ ናቸው። የመምራት ክህሎት፣ የማሳወቅ ጉጉትና፣ እንደሰው የማዘን የመረዳት፣ ቀድመው ያወቁትን መንገድ ለጀማሪዎች የማሳየት ችግር ብዙ አለቆች ጋር አለ። በአጋጣሚ ይሁን አመል እንጃ አንድ መስሪያ ቤት ከ2 አመት በላይ በቋሚ ሰራተኛነት አልቆየሁም። ቶሎ ቶሎ መስሪያ ቤት መቀያየር ጥሩም ነው መጥፎም ነው። ጥሩነቱ ስራውን አካባቢውን ተላምዳችሁ በቀላሉ በደመነፍስ ስራን ለመከወን ማስቻሉ ፤ መጥፎነቱ ከባልደረቦችና ከመስሪያ ቤቱ ጋር አጉል ቤተሰባዊነት ተሰምቷችሁ በስራና የግል ሕይወት መካከል ያለችው ስስ ግድግዳ መናዷ። ለእኔ ስራ ስራ ነው! በሁለት የሙያ ዘርፍ ስራ ከጀመርኩ 9ኛ መስሪያ ቤቴን ከተቀላቀልኩ ገና 3 ወር አልሆነኝም።(አሁን ሁለት አመት አለፈኝ ) በአማካይ ከ 6ወር እስከ 2 አመታት በአንድ ቦታ ቆይቻለሁ። በስራ በነበርኩባቸው ቦታዎች ሁሉ ለቅቄ ወደ ሌላው ስገባ ... ነገ እሄዳለሁ በሚል ቸልተኝነት ያበላሸሁትና ያዝረከረኩት ስራ የለም። በሰላማዊ ትግልና በሰላማዊ መንገድ ተመራርቄ "ቸር ይግጠምሽ" ተብዬ ፍፃሜዬን አሳምሬ ነው የተለያየሁት። እጆቼን ብታዩ ሻካራና ስራ የለመዱ ናቸው። የጉልበትም የጭንቅላትም ስራ እሰራለሁ። አንድ ነፍሴን ለማሰንበት ... በግራ በቀኝ ከፊትና ከኋላ ያሉትንም ለማየት! ለስራ አለግምም፣ ሆነ ብዬ አልሰንፍም፣ በቸልተኝነት አላረፍድም ፣ በሰበብ አስባቡ ከስራ ገበታዬ አልቀርም ... ቀን ከለሌሊት ብሰራ ቅር አይለኝም። ቤቴ አምጥቼ፣ እንቅልፌን አጥቼ እሰራለሁ። የማውቀውን አሳውቃለሁ። የማላውቀውን እጠይቃለሁ። ከሚጠበቅብኝ ጊዜ እቀድማለሁ እንጂ አላዘገይም! ከስራ ልምዴ እና ከትምህርት ዝግጅቴ እኩል ሰዎች ስለኔ የሚሰጡት መልካም ምስክርነት ዋጋ እንዳለው እያደር ተገንዝቤያለሁ ። ከሁሉም በላይ ጤነኛ ነኝ። ሰላም አለኝ። ጉልበቴን አዕምሮዬንና ጊዜን አከራይቼ የማድር ለፍቶ አዳሪ ፤ ላብ አደር ነኝ። እድገት ፣ የደመወዝ ጭማሪ ፣ ያልተገባ ጥቅማጥቅም ለማግኘት ለባለቤቶችና ለአለቆች ሳጎበድድ የትም አልተገኘሁም። የሚገባውን ክብርም አልነፍግም ። በስራ ቦታ ያሉ ጥቃቅን ኢ-መደበኛ ቡድኖች ውስጥ የለሁበትም ። እነዚህ ቡድኖች በእምነት፣ በፓለቲካ አቋም፣ ባገር ልጅነት ፣ በፆታ፣ በስራ ደረጃ፣ በሰፈር ወዘተ ... የተደራጁ ሊሆኑ ይችላሉ ብዙም ትርፍ የላቸውም ! ስለዚህ የህሊና ወቀሳ የለብኝም ። ስራዬ ላዬ አተኩሬ ስለፋ ስለምውል ... "ጣሪያ ላይ በሚወድቅ ቅጠልና ፍሬ አልነቃም አስሬ" ምክንያቱም ''እኔ ባለሙያ ነኝ። የትም ብሄድ ሰርቼ ነው የማገኘው '' የሚል ልበ ሙሉነት አለኝ። ስራ ሳልንቅ ፤ ሳልማረር ሰርቼ ነው የምበላው ። ጉልበቴን አእምሮዬንና ጊዜን አከራይቼ የማድር ለፍቶ አዳሪ ላብ አደር ነኝ። ስንፍናን እጠየፋለሁ። ብዙ ነገር ልሆን እችላለሁ ። ሰነፍ ግን አይደለሁም ! “ሊሰራ የማይወድ አይብላ” መርሄ ነው ። ጤና ፣ ጉልበት ፣ ጊዜ ፣ እውቀት ኖሯችሁ የሆነሰው ትከሻ ላይ የተንጠላጠላችሁ ... ሁላችሁ ... ተነሱ ፣ ውጡ ፣ ስሩ ፣ ድከሙ እጆቻችሁን ስራ አስለምዱ ፤ አእምሯችሁ ያስብ ... ከቤት ጀምሩ የበላችሁበትን ፤ የለበሳችሁትን እጠቡ ፤ ቤት ወልውሉ ፤ ቆሻሻ ጣሉ ፤ 'ስራ ብታጡ ስፖርት ስሩ' -እንዳለው ኤርሚያስ አመልጋ ብቻ አደራ ሰው ላይ አትንጠልጠሉ...የሆነ ሰው የለፋበትን ገንዘብ ያለርህራሄ አታውድሙ! በላብ የተቦካ እንጀራ ይጥማል። ሞክሩት። እየለፋችሁ ተመጣጣኝ ክፍያ ያላገኛችሁ አይዟችሁ ልፋታችሁን ቀጥሉ! በርቱ! ጠንካራ ስራ ዛሬ ባይሆንም ውሎ አድሮ ይከፍላል። በእውነት ይከፍላል ። የእጆቻችሁን ስራ የላባችሁን ፍሬ ማንም አይነጥቃችሁም። እርግጥ ነው የሰራ ሁሉ አልበላም። ያልሰራም ጦሙን አላደረም ። እግዚአብሔር የሰጠው ሰጥቶም የባረከለት በልቷልና ! ምስጋና በሃቅ በእውነት በታማኝነት የስራ ገበታቸው ላይ ለተገኙ ጉልበታቸውን አእምሮና ጊዜአቸውን አከራይተው ለሚያድሩ ለፍቶ አዳሪ ላብ አደሮች ። #ከትውስታዬ
2260Loading...
12
ይሉኝተኛ ናት ልብ አላት አዛኝ ልብ ። በልቧ ምክንያት ኪሷ ውስጥ ብር አይበረክትም ። የመጀመርያ ቀን ስናወራ ዋልን ያን ቀን ነው ያወኳት ከዛ እለት ቀጥሎ ብዙ ቀን አገኘኋት ያኔ ያየኋት ልጅ ነች ። እናቷን አሞባት ብር አበድረኝ አለቺኝ ። ባለፈው የሰጠኋትን ስላልመለሰች እየተሳቀቀች ነበር የጠየቀቺኝ ። ብዙ ሰው ጋ ሄድኩ ። የጠየኳቸው ሰዎች እንደኔ ብር አልነበራቸውም ። ለመጀመርያ ግዜ ድህነቴ ታወቀኝ ። የለኝም አላልኳትም... ዝም ነበር ያልኳት ። የለኝም ለማለት ፅፌ ነበር አላኩላትም እንጂ ። ቸገረኝ ላለ ሰው እኔም ቸግሮኛል ብሎ ከመፃፍ አለመፃፍ ይሻላል ብዬ መሰለኝ ። ልትመረኮዝበት ያሰናዳችው ትከሻ መመርኮዣ አጥቶ መሆኑን ማወቅ ምን ያደረጋል ። ከዘጠኝ ቀን በኃላ ብዙ ብር አገኘሁ ብላ ብዙ ብር ላከችልኝ ። አንድ አንድ ልቦች ሲቸገሩ ብቻ አይደለም የሚፈልጉን ። እንዳንድ ነብሶች የዝምታችን ትርጉም ሳንነግራቸው ይገባቸዋል ። Adhanom Mitiku✍
2924Loading...
13
Media files
1560Loading...
14
Media files
3003Loading...
15
Norman Doidge's book "The Brain That Changes Itself: Stories of Personal Triumph from the Frontiers of Brain Science" explores the concept of neuroplasticity and its profound implications for understanding and treating various brain-related conditions.  Here are 25 key takeaways from the book: 1. 🧠 Neuroplasticity: The brain has the remarkable ability to reorganize itself by forming new neural connections throughout life, a concept known as neuroplasticity. 2. 🔄 Changing Brain Patterns: The book demonstrates that the brain is not fixed but rather adaptable, capable of changing its structure and function in response to experience. 3. 🕰️ Historical Perspectives: Doidge presents historical insights into the development of neuroplasticity research, highlighting the pioneers who challenged the prevailing notion of the brain's immutability. 4. 🤝 Mind-Body Connection: The book underscores the interconnectedness of the mind and body, illustrating how mental activities can influence physical brain changes. 5. 🏥 Rehabilitation Potential: Neuroplasticity offers hope for individuals with brain injuries or neurological disorders, as the brain can often recover or compensate for damaged areas. 6. 📚 Case Studies: Doidge shares compelling case studies of individuals who have overcome significant brain challenges through neuroplasticity-based therapies. 7. ⚡ Stroke Recovery: The book explores how stroke survivors can regain lost functions through targeted rehabilitation programs that leverage neuroplasticity. 8. 📖 Learning and Memory: Neuroplasticity impacts learning and memory, suggesting that continuous mental stimulation can enhance cognitive abilities. 9. 👂👁️ Sensory Adaptation: The brain can adapt to changes in sensory input, as seen in individuals who regain hearing or sight after periods of impairment. 10. 🦵 Phantom Limb Pain: Doidge discusses the phenomenon of phantom limb pain and how the brain can be rewired to alleviate such discomfort. 11. 📚 Learning Disabilities: The book examines how neuroplasticity can be harnessed to address learning disabilities like dyslexia and ADHD. 12. 😌 Emotional Regulation: The brain's plasticity extends to emotional regulation, offering insights into the treatment of mood disorders. 13. 🧠 Cognitive Therapy: Cognitive interventions can drive positive brain changes, benefiting mental health and overall well-being. 14. 🌱 Plasticity Across Lifespan: Neuroplasticity operates throughout life, influencing brain development from infancy to old age. 15. 🧩 Brain Exercises: Engaging in specific mental exercises can promote neuroplasticity and enhance cognitive resilience. 16. 🌍 Cultural Impacts: The book discusses how cultural practices and experiences can shape brain plasticity. 17. 🎵 Music and the Brain: Doidge explores how musical training can reshape brain networks and enhance cognitive functions. 18. 🧘 Meditation and Mindfulness: Practices like meditation can induce neuroplastic changes, fostering mental clarity and emotional balance. 19. 🚭 Addiction and Recovery: Neuroplasticity insights offer new approaches to understanding and treating addiction. 20. 💡 Therapeutic Innovations: The book highlights innovative therapies that leverage neuroplasticity to treat various neurological and psychological conditions. 21. 🥦 Optimizing Brain Health: Understanding neuroplasticity can guide lifestyle choices that promote brain health and resilience. 22. 🤝 Interdisciplinary Collaboration: Neuroplasticity research draws on insights from diverse fields like psychology, neuroscience, and medicine. 23. 🤔 Ethical Considerations: Doidge touches on ethical implications related to brain modification and enhancement. 24. 📢 Public Awareness: The book advocates for greater public awareness of neuroplasticity's potential and its implications for education and healthcare. 25. 🌟 Hope and Resilience: Ultimately, the book offers a message of hope, emphasizing the brain's remarkable capacity for adaptation and transformation, even in the face of significant challenges.
3741Loading...
16
Media files
3030Loading...
17
ለኢትዮጲያ ስነ ጽሁፍ መዳበር አያሌ ደራሲዎች የየበኩላቸውን ከፍተኛ ድርሻ አበርክተዋል።ለሁሉም ክብር!ግን አንዳቸውን ከሌላው የሚለያቸው የአጻጻፍ ዘዬ፡የቋንቋ ምጥቀት፡የሀሳብ ብስለት አላቸው። የአንጋፋው ሀዲስ አለማየሁ ተረታዊ አቀራረብ በፍቅር እስከ መቃብር፡በየልምዣት እንዲሁም በወንጀለኛው ዳኛ ውስጥ ተነቦ አይጠገብም። በአሉም የመጠቀ ቴክኒካዊ ብቃት እና መቼም የማይዘነጉ የሴራ አወቃቀሮች ነበሩት። ስብሀት አይነኬ ጉዳዮችን መድፈሩ፡መለያው የሆነ ቀላል አማርኛው እና ወጣ ያለው ሰብዕናው ለልቦለዶቹ ውበት ለወጣት ተከታዮቹም መብዛት አስተዋጽኦው ብዙ! ዳኛቸው ወርቁም ለቋንቋ ርቀቱና ለሀሳብ ብስለቱ ዘላለማዊ ምስክር የሆነውን አደፍርስን ትቶልን አልፏል።ዳኛቸው ፣ የአማርኛ ፈሊጣዊ አነጋገሮች፡የአማርኛ እንግሊዝኛ መዝገበ ቃላቱና የጽሁፍ ጥበብ መማሪያ የመሳሰሉ መጽሀፍትን ማዘጋጀቱ የስነ ጽሁፍን ኪነታዊ ጐን ብቻ ሳይሆን ሳይንሳዊ ባህሪውንም እንዲካነው አስችሎታል። ብርሀኑ ዘርይሁን ታሪካዊ ልብወለዶችን ለብቻው ነግሶባቸው ኖሮአል(አብነቶቹም ማዕበል የአብዮት ዋዜማ፣ የአብዮት መባቻ፣ የአብዮት ማግስት፡የታንጉት ሚስጥር፡የቴዎድሮስ ዕንባ)። የበቃ ገጣሚ እና ጸሀፊ ተውኔትስ ከሎሬት በላይ ማን አለ?! የነ ዮፍታሔ ንጉሴ፡ዮሐንስ አድማሱ፡መንግስቱ ለማን አስተዋጽኦስ ማን ይዘነጋል? ኢትዮጲያ ስነ ጽሁፍ አላት የሚለውን ለሌላኛው አለም አበክረው ያስረገጡትስ እነ ሳህለስላሴ ብርሀነማርያም በshennege's village ዳኛቸው ወርቁ በthe thirteenth sun አይደለምን? ታሪክ ጸሀፊዎችም አሉን የመጽሀፎቻቸው ተነባቢነት ልቦለዶችን የሚያስንቁ፦ተክለጻዲቅ መኩሪያ፡ጳውሎስ ኞኞ እና ምሁሩ ባህሩ ዘውዴ። አዳም ረታ ተራና የተለመዱ የሚመስሉ ጉዳዮችን በውብ ቋንቋ እና ገለፃ አበልፅጎ፣ የስነ ጽሑፍ ማማ ላይ ይሰቅላል። አለቃ ደስታ ተክለወልድ ፣ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ እና ከሳቴ ብርሀን ተሰማ፣ በቋንቋ ተጠበው ትላልቅ የአማርኛ መዝገበ ቃላት አዘጋጅተዋል። ወጣቶቻችንም አሉ፤ ከታላላቆቹ እግር ስር እየተተኩ ተስፋ የሆኑን ― አለማየሁ ገላጋይ፣ እንዳለጌታ ከበደ፣ ዘነበ ወላ፣ ኤፍሬም ስዩም፤ በእውቀቱ ስዩም። እነዚህ ሁሉ እንቁ ጠቢቦቻችን ተሰባስበው በልዩነታቸው እና በድምቀታቸው ለአማርኛ ስነ ፅሁፍ የተዋበ አንዳች ህብረ ቀለም ይሰጡታል! በመደብራችን ሀሁ መጻህፍት ሁሉንም አይነት መጽሀፍ ያገኛሉ፦ የቆዩ እና አዲስ መንፈሳዊም ሆነ አለማዊ ክላሲክም ሆነ ዘመናዊ የታሪክ፣ የፍልስፍና፣ ልብወለድ፣ የትምህርት፣ የስነልቦና፣ የሃይማኖት፣ ግለታሪክ ወዘተ አስታውሱ! በመደብራችን 10 መጻህፍት ለሚገዛ 1 መጽሀፍ በነጻ እንሰጣለን። #የሀሁ_መጽሐፍት_መደብር አድራሻ ቁ.1 አራት ኪሎ አብርሆት ጎን 2 ሜክሲኮ ደብረወርቅ ሕንጻ ስ.ቁ 0911006705/0924408461
3310Loading...
18
ዛሬ እሁድ ነው! "በአንድ ሳምንት አንድ መጽሐፍ ቻሌንጅ " የሳምንት አንድ መጽሐፍ ርዕስ: "ማዕበል ጠሪ ወፍ" ለመጀመሪያው ሳምንት የመረጥኩት መጽሐፍ የደራሲ አለማየሁ ገላጋይ "ማዕበል ጠሪ ወፍ" የተሰኘውን አዲስ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ በኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ እና በኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ ላይ አብዮት የፈጠሩ ደራሲያንን እጥር ምጥን አድርጎ በጥሩ ሁኔታ የዳሰሰበት ነው። መግቢያውን ጨምሮ በሶስት ክፍል የተከፈለው መጽሐፉ የኢትዮጵያን ሥነጽሑፍ እና በኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ ውስጥ በጉልህ ሰማቸው የሚጠሩ ሰባት ደራሲያንን ያነሳሳል። ከእነዚህ መካከል ፀጋዬ ገብረመድህን ፣ በዓሉ ግርማ ፣ ደበበ ሰይፉ ፣ ሰሎሞን ዴሬሳ ፣ ዳኛቸው ወርቁ ፣ አፈወርቅ ገ/እየሱስ ፣ገብረክርስቶስ ደስታ ይገኙበታል። ከ"ማዕበል ጠሪ ወፍ" መጽሐፍ ላይ ከብዙ በጥቂቱ ሶስት ጉዳዮችን ብቻ ልንገራችሁ ! ☑️አፈወርቅ ገብረየሱስ "ማዕበል ጠሪ ወፍ" መጽሐፍ ስለ ደራሲ አፈወርቅ ገብረየሱስ ሌላኛው ገፅ ያየሁበት መጽሐፍ ነው። ለምሳሌ ከእቴጌ ጣይቱ ጋር በወቅቱ የነበራቸውን መልካምና ክፉ ግንኙነት ከዚህ ቀደም አላውቅም ነበር። እዚህ መጽሐፍ ላይ በደንብ ተገልጿል።( ስለ አፈወርቅ ገብረየሱስ የተነገረን"ባንዳ ናቸው" ስብዕና መሠረቱ እንዴት እንደተጣለ ምክንያታዊ ሀሳብ ቀርቧል) ። በተጨማሪም ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ አማርኛ የሚባለው ቋንቋ ለሥነጽሑፍ የበቃ እንደሆነ ማረጋገጫው የዳኛቸው ወርቁ "አደፍርስ "ሳይሆን የደራሲ አፈወርቅ ገብረየሱስ "ጦቢያ" እና "አጤ ምኒልክ" የተሰኙት መጻሕፍት ናቸው በማለት ይሞግታል። ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ በገፅ 228 ስለዚሁ ጉዳይ "እንደ ስብሃት ገ/እግዚአብሔር ያሉ የወቅቱ ጀማሪ ፀሐፍት አማርኛን ትተው በእንግሊዝኛ ድርሰት ጀምረው ነበር። ስብሃት እንደሚለው "አደፍርስ" ተፅፎ ሲያነብ በእንግሊዝኛ የጀመረውን "ሌቱም አይነጋልኝ" ወደ አማርኛ አመጣው። አሁንም ቢሆን አማርኛ የበቃ- የነቃ መሆኑ ሊረጋገጥ የሚገባው በዳኛቸው "አደፍርስ" ሳይሆን በአፈወርቅ ገ/ እየሱስ "ዳግማዊ ምኒሊክ " እና "ጦቢያ" ነው ብዬ ለመከራከር እደፍራለሁ" ይላል። ☑️ሰሎሞን ደሬሳ ከሰሞኑ ጋዜጠኛ ደረጄ ሀይሌ ከገጣሚ ሰሎሞን ዴሬሳ ጋር ያደረጉትን ቃልመጠይቅ እየሰማሁ ነበር። ሰሎሞን ንግግሩ በጣም ያምራል። ገጣሚ ሰሎሞን ከግጥሞቹ ይልቅ ሲናገር በጣም ያምርበታል እያልኩ በሆዴ ሳስብ የነበረውን ጉዳይ ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ " ሰሎሞን ከግጥሙ ይልቅ ንግግሩ ይበልጥብኛል። ኮኮቤ የገጠመልኝ በዝርው ሲቀኝ ነው።በግጥሙ የሚገልጸው ጥሬ አመፁን እንጂ ሐሳቡን አይደለም። በንግግሩ ይቀኛል።በዝርው- ቅኔ ይዘርፋል።ሲገጥም ሳይሆን ስለግጥም ሲያወራ ይበልጥብኛል" በማለት ሀሳቤን ይጋራኛል። ☑️ገብረክርስቶስ ደስታ ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ "ማዕበል ጥሪ ወፍ" መጽሐፉ ላይ ገጣሚውን ገብረክርስቶስ ደስታና ግጥሙን ምን ይላል መሰላችሁ "ገብረክርስቶስ የአንጎራጓሪዎች ባህሪይ የተላበሰ ገጣሚ ይመስለኛል።ስራዎቹ ውስጥ ብልጭ ቁልጭ ያለች እውነት ብጥር ንጥር ባሉ ቃላት ይቀርባሉ።ቋንቋው ውስጥ መሸራመም ሆነ መሽኮርመም አያውቅም ።ሲናፍቅ፣ ሲያፈቅር፣ ሲደመም ፣ ሲቆዝም "እንደ እግዚሀር ሰው" የሆድን አለመደበቁ ነው የግጥሞቹ ውበት" ይላል ። ውብ አገላለጽ !። ☑️እንግዲህ ክብራንና ክቡራት እናንተ ደግሞ የዳኛቸው ወርቁ ፣ የደበበ ሰይፉ ፣ የፀጋዬ ገብረመድህን ፣ የበዓሉ ግርማን በርካታ ጉዳዮች መጽሐፉ ላይ ታገኛላችሁ አንብቡ። በነገራችን ላይ ከዓመታት በፊት ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ እና ጋዜጠኛ ማዕዛ ብሩ የእነዚህ ደራሲያን ጉዳዮችን ጨምሮ በኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ "ሸገር ካፌ" በተሰኘው ፕሮግራም ላይ ያደረጉትን ቆይታ ከዩቲዩብ ላይ ፈልጋችሁ ብትሰሙ መጽሐፉ ላይ ያልተነሱ ተጨማሪ ሀሳቦችን ልታገኙ ትችላላችሁ። "ማዕበል ጠሪ ወፍ" መጽሐፍ በ250 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ499 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል። በቀጣይ እሁድ ከምሽቱ 2:00 ላይ በሁለተኛው ሳምንት የመጽሐፍ ምርጫና ንባብ እመለሳለሁ። መልካም ንባብ። እናንተስ በዚህ ሳምንት ምን መጽሐፍ እያበባችሁ ነው?
3351Loading...
19
😁 በሬው የታለ..? ዛሬ ጓደኞቼ መስቀል ፍላወር አካባቢ የምትገኝ አንዲት ግሮሰሪ ውስጥ ተቀምጠናል የሚል ቴክስት ሲፅፉልኝ በግዜ ወደነሱ ሄድኩ። አንዳንዴ ግሮሰሪ አሪፍ ነው። ጨዋታ አለ። ትልልቅ ሰዎች ታገኛለህ ... ምናምን ብዬ አላዝግህም። it's all about cost minimization ዘመዴ ስገባ ሁሉም በግዜ ሞቅ ብሏቸዋል። በጣም የሰከረው ግን የቤቱ ባለቤት ነው። ባህሩ ይባላል። የሚያስተናግደውም እራሱ ነው። ችግሩ ከሚሸጠው ይልቅ የሚጠጣው ይበልጣል። አንዳንዴ ከስተመሩ ነው የግሮሰሪውን በር ዘግቶለት ተሸክሞ ቤቱ ሚያደርሰው። ገብቼ ቁጭ እንዳልኩ «ምን ይምጣልህ?» አለኝ በጉራጌ አክሰንት። «ጂን» አልኩ። ወዲያው ቀዝቃዛ ቢራ ይዞ መጥቶ ፊት ለፊቴ እንደሻምፓኝ ከፍቶ አስቀመጠ። መከራከር አልፈለግሁም ሐበሻ ቢራዬን እየጠጣሁ ማስታወቂው ትዝ አለኝ ... (“ኢትዮጵያዊነት መልካምነት ነው። ኢትዮጵያዊነት ክብር ነው። ኢትዮጵያዊነት ማሸነፍ ነው” ምናምን ይልሃል “ጎሽ የልጅ አዋቂ” ብለህ ሳትጨርስ ግን ....... “ሐበሻ ቢራ” ብሎ ኩም ያደርግሃል) አሁን አሁን የቢራው ፋብሪካ የጠጪው ብዛት ያስገርማል። ለነገሩ በልጅነታችን ካልጠፋ መዝሙር “አስር አረንጓዴ ጠርሙሶች በግድግዳ ላይ” የሚል ዘፈን እያዘፈኑ ያሳደጉን ለዚህ እያመቻቹን ነበር። ኢትዮጵያ ባሁን ሰአት የቢራ በርሜል ሆናለች። አንድ ሰሞን “ኢትዮጵያ ታነባለች” የሚል ሙቭመንት እንደነበር አስታውሳለሁ። አሁን “ኢትዮጵያ ትጠጣለች” ሆኗል ጉዳዩ! በርግጥ እኛ እንደነጮቹ አናካብድም። አክሱምን ያቆምነው ቁርጥ እየበላን ጠጅ እየጠጣን ነው። ፋሲለደስን የገነባነው የደብረብርሃን አረቄ ፉት እያልን ነው። ታሪካችን ውስጥ መጠጥ ትልቅ ቦታ አለው። ክፉ ቀናችንን ያለፍነው እየሰከርን ነው ዘመዴ ...ለነገሩ መፅሃፉም “ደሃ ድህነቱን ይረሳ ዘንድ ወይን ይጠጣ” ይላል። ሃሃ አይ የድሮ ደሃ። ታድሎ። የዛሬ ደሃ ዋይን ልጠጣ ቢልስ ኬት አባቱ ያመጣል? ባህሩ ይሄን ድራፍት በላይ በላዩ ይለዋል። ጥግ ላይ የተቀመጠ የፖለቲከኞች ፊት ያለው ሰውዬ «ና ሂሳብ ውሰድ» አለና መቶ ብር ከኪሱ አወጣ። ባህሩ ከቀመቀመ ማንንም አይሰማም እየተለጠጠ ሂደና መቶ ብሩን ተቀብሎ ወደላይ ቀና አርጎ በአምፖሉ ብርሃን ብሩን በትኩረት ካየው በኋላ .. «ይሄ ብር ፎርጅድ ነው» አለ። «ምን?» አለ ሰውዬው። «ፎርጅድ ብር ይዛችሁ መምጣት ጀመራችሁ ደግሞ?» ሲል ሰውየው ከመቀመጫው ተነስቶ «ምን ለማለት ፈልገህ ነው ፎርጅድ ብር ነው ምትለኝ?» «በሬው የለማ» አለው ባህሩ ብሩን በጣቶቹ ጫፍ አንጠልጥሎ። «እንዴት ነው በሬው የሌለው?» አለና ብሩን ከጁ ነጥቆ አገላብጦ ካየው በኋላ ... «ይሄ በሬ አይደል?» አለ በቁጣ። «እሱ ወይፈን ነው» አለ ባህሩ ቆፍጠን ብሉ። «በዚያ ላይ ገበሬው ራሱ ወጣት ነበር እዚህ ላይ ያለው ግን ሽማግሌ ነው» ሲል ሁላችንም ከት ከት ብለን ሳቅን .. «እና አያረጅም እንዴ? የሰው ልጅ አይደል እንዴ?» ብሎ ተከራከረ ሰውየው። አይ የፖለቲከኛ ነገር..እያልኩ እያሰብኩ ፈገግ ስል አንድ አዝማሪ እንዳባረሩት ሰው ተንደርድሮ ገብቶ ማሲንቆውን ሲገዘግዝ ብቻውን ተቀምጦ ጅኑን የሚጠጣ ኮሳሳ ሰውዬ ጮክ ብሎ «ተቀበል» አለ «እሺ» አለ አዝማሪው ፈገግ ብሎ «ዛሬም እጠጣለሁ» «ዛሬም እጠጣለሁ» አለ አዝማሪው «ነገም እጠጣለሁ» «ነገም እጠጣለሁ» አለ አዝማሪው መሰንቆውን እየገዘገዘ «ከነገወዲያም እጠጣለሁ» «ከነገወዲያም እጠጣለሁ» «ሂሳቡን ወደፊት ሰርቼ እከፍላለሁ» ሲል ባህሩ ጥግ ላይ ቆሞ እየተኮላተፈ .. "እናትህ ወልዳሃለቻ!" ካነበብኩት አካፈልኳችሁ
3780Loading...
20
Media files
3461Loading...
21
ለመኖርህ በህይወት መገኘት ብቻ ዋስትና አይሆንም። በሌሎች ኃይልን የተጎናጸፉ ባለጡንቻዎች ለመኖርህ ማረጋገጫ ካልሰጡህ በስተቀር። ድንገት አንድ ጠዋት የጦር መሣሪያ ጥይት በቤትህ ጣሪያ አናት ላይ ሲርከፈከፍ ትነቃለህ። ገና ህይወትን በመጀመሪያህ ሰዓት ይመጣና “ለዓላማዬ ተማገድልኝ” የሚል ጉልበተኛ ደጅህን ይቆረቁራል፣ እጣፈንታህን ይወስንልሃል። የዘመኔን ወጣት ምስቅልቅል ሥነ ልቡናው ፣ ፍርሃቱ፣ ተስፋ ቢስነቱ፣ የዛለ መንፈሱን ይወክላል። ህይወት ይሏት ፍዳ ተጭናበት አሳሩን ይበላል። ተራኪው በዚህኛው ክፍል የገፈቱ ቀማሽ ነው። ታድያ ይህ የማይሽር ጠባሳ ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገረ ገና ከእናታቸው ማህፀን ብቅ እንኳን ላላሉት ለመጻዒ ትውልዶች እጣፈንታቸው ዛሬ እየተሠራላቸው እንዳልሆነ ማን ደፍሮ መናገር ይችላል? — የ “ያ ትውልድ” — ከተማዋ ትታመሳለች። ብዙ ነገሮች መናድ ይጀምራሉ። ሀገሬው ሰማዩን ሲያርስ ንጉሡን ሲከስስ ይውላል። ወጣቱ ያነገባትን ተስፋ ይዞ በስሜት እየተመራ በአንድ አቅጣጫ ብቻ የለኮሳት እሳት መልሳ ራሱን ትበላዋለች። “አብዮት ልጆቿን በላች” የተባለለት የ60ዎቹ ትውልድ ገፅታ ልብ ይሏል። — ጥላ (shadow) ሲገፈፍ — አንድ ግለሰብ ለመካድ ወይም ለመጨቆን የሚሞክረውን ንቃተ ህሊና የሌለውን፣ የተጨቆነ እና ብዙውን ጊዜ የማይፈለጉትን የእራስ ገጽታዎችን ይወክላል። የግል ጥላው ልንገነዘበው ወይም መጋፈጥ የማንፈልገውን የራሳችንን ማንነቶች ያቀፈ ነው። ለምሳሌ፦ ተቀባይነት የሌላቸው ግፊቶች፣ ምኞቶች ወይም በማኅበራዊ ደረጃ የማይፈለጉ ባሕርያት ወዘተረፈ.. ጁንግ እንደሚለን እነዚህ ማንነቶች ባልተቀበልናቸውና በካድናቸው ቁጥር በእኛ ላይ ኃይል እያገኙ እና ከቁጥጥራችን እየወጡ ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶችን እስከመፈጸም ሊያደርሰን ይችላል። ስለዚህ ጥላን ማቀናጀት የጁንግ የግለሰባዊነት ፅንሰ-ሀሳብ አስፈላጊ አካል ነው - የግል እድገት እና ራስን የማወቅ ሂደት። ጥላውን በመቀበል እና በማዋሓድ ግለሰቦች የበለጠ ሙሉ፣ ትክክለኛ እና በሥነ-ልቡና የተዋሓዱ እንዲሆኑ ያስችላል —ይለናል። ማኅበረሰብ የተዋቀረበት ጠንካራ መሠረት መፈረካከስ ሲጀምር፦ ግለሰብ በደህና ጊዜ ሸሽጎ ያኖራት ነውሩ የሚፈራው እና የሚገዛለት ነገር ሲያጣ ከጓዷ ወጥቶ አደባባይ ላይ ርቃኑን ይቆማል። እንግዳ ማንነቶች ብቅ ብቅ ማለት ይጀምራሉ። ሥርአት አልበኝነት፣ ስግብግብነት፣ ሌብነት፣ ጭካኔን የመሳሰሉ የሰው ልጅ አውሬያዊ ባሕሪዎች ጥርሳቸው አግጥጠው መታየት ይጀምራሉ። ይህም ማኅበረሰባዊ መልክ ሲይዝ እኛን ይመስላል። መጽሐፏ ቆም ብለን እራሳችንን እንድናይ ትጋብዘናለች። — የሰፈሩ የተከበረ አድባር — ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል ትልቅ ቦታ የሚሰጠው እና ማንነቱን የመሠረተበት አንድ አይነኬ፣ አይመረመሬ አድባር አለው። በወለፈንዴነት የምንመላለስባትን ህይወት ትርጉም የምትለብሰው በዚህ አድባር በኩል ነው። ይኽን አድባር የወከሉት ካህኑ የተራኪው የማደጎ አባት ናቸው። የቅድስና ምሳሌ እርሳቸው ናቸው። እርሳቸው የሰፈሩ አድባር፤ የማይናዱ የሚመስሉ የማኅበረሰብ ዕሴት፤ እልፎች የተመረኮዙት ተሰባሪ የማይመስል ምርኩዝ ናቸው። በጊዜ ጉልበተኝነት ከዕለታት በአንዱ ቀን የዚህ አድባር መገለጫ እንደቅርፊት ከላዩ ላይ እየተገፈፈ ድራሹ ይጠፋል። የተጠለሉበት ቤት ምሰሶው የጊዜ ፈርጣማ ክንድ ሲያርፍበት ይዘምማል። ከዕለታት በሌላኛው ቀን ደግሞ የጊዜ አውሎ ነፋስ ጣሪያውን ገንጥሎ መጠለያ አልባ ቤተኛ ያደርገናል። በመጨረሻም ማገሩ ይወድቃል። ያ ባለግርማ በምልአት የቆመ የሚመስለው ዋርካ ዳግመኛ እንዳንጠለልበት ሆኖ ይፈርሳል። ድንገት በዙሪያችን ባዶነት ያረባል። — የመጨረሻው መጀመሪያ ነጥብ — ይሄ መጽሐፍ ከፈጠራ ልቦለድነት ከፍ ያለ ኮርኳሪ፣ መተከዣ የሚሆኑ ጥልቅ ሀሳቦችን ይዳስሳል። ሥነ ጽሑፋዊ ውበቱ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም። ሁሉም ሊያነበው የሚገባ መጽሐፍ ነው። ይህን ውብ ድርሳን ለሰጠንን ለእሱባለው አበራ ንጉሤ እጅ ነስተናል።🙏
3454Loading...
22
ፀሓይ ከጨለማዬ ምን አለሽ? — ዳሰሳ | Yodit Amanuel — “ቀለም በቀንድ (በብልቃጥ) ሳለ ጨለማ ነው፤ በተጻፈ ጊዜ ግን ብርሃን ነው። ቀለም በቀንድ ሳለ ድዳ ነው፤ በተጻፈ ጊዜ ግን መላሰኛ ነው። ቀለም በቀንድ ሳለ ጭምት ነው፤ በተጻፈ ጊዜ ግን እንደሰከረነው። ሁሉንም ይለፈልፋል።” —ከዘነብ ኢትዮጵያዊ፣ መጽሐፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ— ከመጽሐፏ ማለፊያ እግረ መንገዳችንን ጨልፈን እነሆ በረከት... ደራሲው ከዚህ በፊት ያልተሞከረ አዲስ “ማሕሌታይ” የተባለ የድርሰት አጻጻፍ ስልት እንደጻፈው በመጽሐፉ ማሳረጊያ ላይ ይነግረናል። ይህ መጽሐፍ በኢትዮጲያዊው የዜማ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ሦስት የዜማ ስልቶች ባሕርይ በግዕዝ፣ ወመቋሚያ፣ ዕዝል ወጸናጽል፣ አራራይ ወከበሮ በተወከሉ ሦስት ክፍሎች የተዋቀረ ሲሆን በዋናነት ጦርነት፣ ቀቢፀ ተስፋ፣ ፀፀት፣ ህላዌ፣ ነፃ ፍቃድ በጥልቀት ይዳስሳል። በመጀመሪያው ማለትም በ “ግዕዝ ወመቋሚያ” በተወከለው ክፍል ደራሲው የግዕዝን ዜማዊ ባሕርይ በመመሰል በዚህኛው ክፍል ጠንካራና ጠጣር ፍልስፍናዎችን ትዝብቶችን በሦስተኛ ተራኪ መደብ፣ ሁሉን አወቅ (omniscient) አንጻር ይተርክልናል። በ“ሰማይ አይታረስ፣ ንጉሥ አይከሰስ” ሁሉም ነገር ቀዝቃዛ ይመስላል። በስሜት ተካልበው ከደጃቸው ያኖሩት ባዕድ፣ ከመጡበት መንገድ የሚነፍሰው ንፋስ ከቀልብ ያልተረገጠ ዳናቸውን እያጠፋ መነሻ ቢስ አድርጓቸዋል። ከትላንት ሲያሻግሯቸው የነበሩ ድልድዮችን አፈራርሰው ዳግም በትውስታ እንዳይመለሱባቸው ሆነዋል። ትዝታቸው ደብዛው ጠፍቶ ድንገት ከየትም እንደመጡ፣ ግር በተሰኙ ሕዝቦች የተመላች ከተማ፣ ማንም በማንአለብኝነት ህመምና ጉስቁልናውን ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ባላየ ባልሰማ የሚተላለፍባት በውል ያልተቃኘን የዘመን መልክ በዚህ ባልታወቀው ሦስተኛ መደብ ተራኪ ከየጓዳው መጋረጃውን እየገለጠ ትዝብቱን ያስቃኘናል። ዐበይት ከሆኑት የፍልስፍና ዘርፎች ዲበአካላዊ (metaphysical) የሆኑ ጥያቄዎችን እያነሣ ሲብሰለሰል እናገኘዋለን። ለምሳሌ፦ በገፅ 31 ላይ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ዓለም ፈጣሪና መጋቢ አለውን? ወይስ የሰው ልጅ የመለኮት ሥራ ሳይሆን ከአጽናፈ ዓለሙ ጋር ወደ መኾን የመጣ የዐቢይ ፍንዳታ ክስተት ውጤት ነው? አምላክ የሰውን ልጅ ፈጠረ ወይስ የሰው ልጅ አምላክን?” ...በማለት የሰው ልጅ የህላዌን ወለፈንድነት (Absurdity) ለማምለጥ የሸሸገባት ድንኳኑን ህልው መሆን፣ አለመሆኗን ተያያዥ ኈልቆ መሳፍርት ጥያቄዎችን እያነሣ የሰውን ልጅ መሠረተ ምሥጢር ለመፍታት ሲበረብር ይታያል። — ነፃ ፍቃድ / free will — በነፃ ፍቃድ (Free will) እና በተወስኗዊነት (determinism) ፅንሰ ሀሳብ በፍልስፍና፣ በሥነ መለኮት እና በሥነ ልቡና ውስብስብና አከራካሪ ሲሆን። በፍልስፍናው ዘርፍ ዲበአካላዊ (metaphysics) ላይ የተመሠረተው ነገረ ህላዌ (existentialism) ሥር የሚዳሰስ እሳቤ ነው። በነጻ ፍቃድ ላይ በርካታ ቁልፍ አመለካከቶች አሉ። — ነፃ ፈቃድ — የሰው ልጅ ሙሉ በሙሉ በውጫዊ ሁኔታዎች ወይም አስቀድሞ የተወሰነ የክስተቶች ሰንሰለት ሳይወሰን በነፃነት ምርጫ እና ውሳኔ የማድረግ ፍቃድ አለው የሚለው አመለካከት። — ተወስኖአዊነትት / Determinism — የሰዎች ድርጊቶች እና ምርጫዎች ጨምሮ ሁሉም ክስተቶች የሚወሰኑት በቀደሙት ክስተቶች እና በተፈጥሮ ሕግጋት ነው የሚለው አመለካከት ነው። ምርጫችን ከቁጥጥራችን ውጪ የሆኑ ነገሮች ውጤት ተደርጎ ስለሚወሰድ የነጻ ምርጫን እና የሞራል ኃላፊነትን ይፈታተናል። ሌላኛው፦ — ተኳሃኝነት / compatibilism — ነፃ ምርጫን እና ተወስኖአዊነትን ለማስታረቅ የሚሞክር የመካከለኛ ደረጃ እይታ። ታዲያ በ“ፀሓይ ከጨለማዬ ምን አለሽ?” መጽሐፍ ላይ ከተነሡት አያሌ ጭብጦች ውስጥ ነፃ ፍቃድ አንደኛው ነው። በመጽሐፉ በገፅ 41) እንዲህ ሲል ይጠይቃል፦ “በምልዕተ ዓለሙ ውስጥ የሰው ልጆችን ዕድል ፈንታ የሚወስን ኃይል አለ? የተጻፈው ይፈጸም ዘንድ ግድ አይደለምን? ወይስ ነገረ ፍርቱና እና የአርባ ቀን ዕድልም ያረጀ ያፈጀ የአቅመቢሶች ተረት ነው?” ...ይቀጥልናም፦ “በነፃ ፍቃድ መኖር ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የመሸከም ነገር በሰው ልጅ እጅ ላይ ብቻ እንዲወድቅ ይኾናል። ኃላፊነትን በመውሰድ ውስጥ ተጠያቂነት ይከተላል። ቀናው ሲፀድቅ፣ ስሁቱ ደግሞ በሥጋውም በነፍሱም ይኮነናል። ነገር ግን በደግም፣ በክፉም ከሞት በኋላ እስከዘላለም የሚፀና ፍርድ ለመቀበል የአንድ ሰው እድሜና ህይወት በቂ ነው?” ...ብሎ በገፅ 41 ነፃ ፍቃድ፣ “እጣፈንታና የዕለት እንጀራ” ብሎ በሰየማት ንዑስ ርእስ ሥር መብሰልሰሉን ይቀጥላል። ሁለተኛው ክፍል በ“ዕዝል ወጸናጽል” ይወከላል። በዚህ ክፍል ተራኪው ከሦስተኛ መደብ ወደ አንደኛ መደብ ተራኪነት ሽግግር ያደርጋል። — ሽግግር / transcend — ይህ የተራኪውን የሰብዕና ሽግግር በአንድ ግለሰብ አንፅሮተ ዓለም ምልከታ ከመነሻ ተነሥቶ ወደ ምንምነት የሚሸጋገርበትን መሥመር ተከትሎ የተራኪውን በልጅነት ያለውን የህላዌ አረዳድ (ከነገሮች ሁሉ መለኪያነት ማዕከላዊነት) ተነሥቶ ቀስ በቀስ እየተገፈተረ ከጨዋታው ሜዳ እስከወጣበት የወጣትነት ጊዜው ያደረገውን የህይወት አረዳድ ሽግግር አስፍሮል። በህይወት ዘመናቸው በቅድስና ተመላለሱ ስለሚላቸው የተራኪው ስለ ካህኑ የማደጎ አባቱ እንዲህ ሲል ይመሰክራል፦ “ጠባያቸውና ምግባራቸው ጠንካራ ነው። ከዓለም ፍቃድ ራሳቸውን አግልለዋል። የንጽህናን ዝናር ታጥቀዋል።” (ገፅ 55) ...ሆኖም ህይወት መልኳን እየቀየረች ጀንበር እያዘቀዘቀች ስትመጣ ቀስ በቀስ እምነቱ መፈረካከስ፣ ተስፋውም መሟጠጥ ቢጀምርም በዚህ ክፍል ጭላንጭል ብርሃን ማየት የተሳነው አይመስልም። — ቀቢፀ ተስፋ — በመጽሐፉ የሚዳሰስው ሌላኛው ጭብጥ ቀቢፀ ተስፋ ነው። በህይወት መድከም እና ስለወደፊት ምስል ከሳች አንዳችም ነገር ማጣት ተስፋ ቢስነት ነው። የሁላችንም የልብ ጓዳ ቢበረበር ቢያንስ ለአንድ ጊዜ በዚህ ዓይነት ስሜት ውስጥ አልፈናል። — ኢምንትነት — በውጪው ዓለም ያለውን ትርምስ ሽሽት ወደ ውስጥ የሚደረግ ጉዞ እና በውስጣዊ ዓለም ከተንሰራፋው ጥልቅ እና አስፈሪ ጨለማ ጋር መፋጠጥ፣ በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ተራኪው ከመታዘብ እና ከመብሰክሰክ ያለፈ እዚህ ግባ የሚባል እንኳን ተሳትፎ እንደሌለው ሲረዳ የማይቀረውን የህይወት ስንክሳር ይጋፈጣል። ተራኪያችን በስተመጨረሻም የሰው ልጆች እድል ፈንታቸው በእጃቸው ላይ እንዳልሆነች ከእነርሱ ቁጥጥር ውጪ መሆኑንና ሌሎች በእነርሱ ላይ አቅም እንዳላቸው ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦ '“በድንገት ከእንስሳ በታች እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ሊያደርጉኝ የሚችሉ ሰዎች ደጃፌን በየትኛውም ቅፅበት ቢያንኳኩ ላስቆማቸው አልችልም። ኢምንት ነኝ።'” (ገፅ 109) በመጨረሻም በ “አራራይ ወከበሮ” የተወከለው የመጽሐፉ ሦስተኛ ክፍል ህልው በመሆናችን የማይቀርልን የህይወት ድለቃ ህማም ሲቃኝ፦ — ጦርነት — ዛሬ እያለፍንበት ያለውን የህይወት ምስቅልቀል በትክክልም የዚህኛውን ዘመን ትውልድ ወካይ ተደርጎ የተገለጸው አንደኛ መደብ ተራኪ የጦርነትን አሰቃቂነት ይነግረናል። በዚህ ውስጥ እልፍ የተረሣ እና ችላ የተባሉ የግለሰብ ህይወቶች ሰሚ የሌላቸውን የጣር ድምፆችን ያወጣሉ።
3485Loading...
23
Media files
3830Loading...
24
ስልጡን ሰው ደስ ይላል ። ተረጋግቶ ነው የሚያወራው ፣ አይመፃደቅም ፣ ሁሉንም አውቃለሁ አይልም ፣ሰው ያከብራል ፣ ያልገባውን ይጠይቃል ። ቀልድ ይገባዋል ፣ የግል ጉዳይህ ውስጥ ዘው ብሎ አይገባም ፣ ሃሳብ ላይ መወያየት ይችላል ፣ አመስጋኝ ነው ቅር ስላለው ጉዳይ በትህትና ይጠይቃል ። በረባው ባረባው አይሞግትም ። አብሮት ያለውን ሰው ስሜት ያጤናል ። መበሻሸቅ ውስጥ አይሳተፍም ። ስልጡን ሰው ደስ ይላል ❤ Adhanum Mitiku✍
3983Loading...
25
🔊 AWAQI weekly book recommendation Embrace Change, Seize Opportunities with "Who Moved My Cheese?" 'Who Moved My Cheese?' is your roadmap to navigating life's inevitable changes and emerging stronger than ever before. This beloved classic by Spencer Johnson offers a simple yet profound lesson - the only constant in this world is change itself. Through the whimsical tale of four characters in a maze, we're invited to reflect on our own responses to shifting circumstances. Do we freeze in fear, waiting for the "cheese" to return? Or do we boldly venture forth, exploring new paths and adapting to new realities? Whether you're facing a career crossroads, a personal challenge, or simply seeking to grow, 'Who Moved My Cheese?' will empower you to navigate change with confidence and grace. Immerse yourself in this timeless wisdom, and unlock the keys to thriving in an ever-evolving world.
240Loading...
26
(ኩኒስ ኒደርባ) አንድ ወዳጄ ያጫወተኝን እየከተብኩ ነው። በጥንት ዘመን ወደ አንዲት የገጠር መንደር ጎራ ያለ መንገደኛ በሕይወት ዘመኑ አጋጥሞት የማያውቅ እንግዳ ነገር ይታዘባል። ነገሩ እንዲህ ነው ፦ መንገደኛው ዓይኖቹን አሻግሮ ሲመለከት አንድ ገበሬ ማሳውን በማረስ ላይ ነበር። ገበሬ ማረሱ ምን ይደንቃል? ዳሩ ግን የሚያርስበትን ቀንበር ተሸክመው ሞፈሩን የሚስቡት አንድ በሬና ሌላ አንድ ሰው ተጠምደው ማየቱ ነበር ዓይኖቹ ከቦታቸው ተበልጥጠው እንዲወጡ ያደረገው። መንገደኛው ክስተቱን እንደዋዛ ሊያልፈው አልቻለም። ወደተጠመደው ሰው ጠጋ አለና ፦ «ምነው ወንድሜ እንዲህ ሆንክ ?» ሲል ልቡ በሀዘን ተሞልቶ ይጠይቀዋል። _ _ _ በባርነት ወይም በችግር ብዛት ሳቢያ ለዚህ መዳረጉን እያብሰለሰለ ትክክለኛ ምክንያቱን ለመስማት በጉጉት ተጠባበቀ። ከሰውየው የሰማው አጭር መልስ ፦ «ኩኒስ ኒደርባ » የሚል ነበር ። በኦሮምኛ ቋንቋ «ይሄም ያልፋል» እንደማለት ነው። መንገደኛው በመልሱ እየተገረመ ጉዞውን ቀጠለ። ከአመታት ቆይታ በኋላ በዛችው መንደር ሲያልፍ «ስለዛ ከበሬ ጋር ተጠምዶ ሲያርስ ስለነበረው መከረኛ ሰው ማጠያየቅ አለብኝ » ሲል አሰበ። የመንደሯ ሰዎች የሚያስደንቅ ዜና አበሰሩት። « ያ! ሰውማ ያን ሁሉ መከራ አልፎ ንጉስ ለመሆን በቃ!» _ _ _ ዜናውን ማመን አልቻለም ቤተመንግሥት ሄዶ ማግኘት እንዳለበት ወሰነ። በርግጥም ያሰው ለንግስና መብቃቱን በዓይኑ በብረቱ ማረጋገጥ ፈልጓል። ቤተመንግስቱ እልፍኝ ውስጥ በዙፋኑ ላይ ተሰይሞ የተመለከተው ሰው በርግጥም ከበሬ ጋር ተጠምዶ ሲያርስ የነበረው ሰው ሆኖ አገኘው። መንገደኛው በአክብሮት እጅ ከነሳ በኋላ ንጉሱ በአንድ ወቅት ከነበረበት አስከፊ ሁኔታ ተላቆ ለዚህ ታላቅ ክብር መብቃቱ በእጅጉ አስገራሚ መሆኑን ገለፀ። ንጉሱ ግርማ ሞገስ በተላበሰ ሁኔታ የመንገደኛውን ንግግር ካደመጠ በኋላ የሰጠው ምላሽ «ኩኒስ ኒደርባ» የሚል ነበር። «ይሄም ያልፋል» መንገደኛው ከዓመታት በፊት የሰማው አይነት መልስ በማድመጡ በመደነቅ ጉዞውን ቀጠለ። _ _ _ ከተወሰኑ አመታት በኋላ ለስራ ጉዳይ ወደዛችው ግዛት ያቀናል። ስለ ንጉሱ ማጠያየቁ አልቀረም። ንጉሱ ከዚህ አለም መሰናበቱ ተነገረው። መንገደኛው ልቡ በሀዘን ተነክቶ «ኩኒስ ኒደርባ» የሚለውን ቃሉን እያሰበ ዓይኑ እንባ አቀረረ። «ይሄም ያልፋል!… ቢያንስ መቃብሩን መጎብኘት አለብኝ» ሲል አሰበና የአካባቢውን ሰዎች ንጉሱ የተቀበረበትን የመቃብር ቦታ እንዲጠቁሙት ጠይቆ ወደዚያው አመራ። የንጉሱ መካነ መቃብር ላይ አንድ ጽሁፍ በጉልህ ተፅፎ ይታያል። በንጉሱ ኑዛዜ የተፃፈው ጽሁፍ  «ኩኒስ ኒደርባ» የሚል ነበር። መንገደኛውም «ከሞተስ በኋላ ምን ማለት ይሆን ?» በማለት እየቆዘመ መንገዱን ቀጠለ። _ _ _ _ ከጥቂት ዓመታት ቆይታ በኋላ መንገደኛው ወደዛች ግዛት ጎራ ማለቱ አልቀረም። የንጉሱ መቃብር ይታወሰውና አካባቢውን ለመቃኘት ወደ መቃብር ቦታው ያቀናል። የተመለከተው ነገር የሚያስገርም ነበር። አካባቢው ሙሉ ለሙሉ ተለውጧል። የመካነ መቃብሮቹ ፋና ሙሉ ለሙሉ ጠፍቶ በቦታቸው ሰፋፊ መንገዶች ወጥተዋል ፤ በርካታ ቤቶች ተገንብ ተዋል። መንገደኛው ባለፉት አመታት ውስጥ ያያቸው ለውጦች በህሊናው እያውጠነጠነ በዝምታ ተዋጠ። እነኚህን መንገዶችና ቤቶችም መለወጣቸው አይቀሬ እንደሆነ እርግጠኛ ሆነ። የርሱን ፈቃድ ሳይጠይቅ ምላሱ አንድ እውነታን አጉተመተመ፦ «ኩኒስ ኒደረባ » አለ ጭንቅላቱን ላይና ታች እየወዘወዘ።  «ይሄም ያልፋል!» _   ከ–ለውጥ   (ገፅ : 177)    በድሩ ሁሴን
3281Loading...
27
Media files
3421Loading...
28
ዝዋይ አራት አመት ስኖር ምንታቀለህ ብትሉኝ ከነበሩት 8 መፅሐፍት አዟሪዎች ዛሬ የቀረቱ አልፎአልፍ ብቅ ሚሉት ሁለት አዟሪዎች ሦስት መፅሐፍት ቤቶች አንዱ ወደ እስቴሽነሪ በመቀየር ላይ ያለ ሌላኛው ወደ መንፈሳዊ መፅሐፍትበማዘንበል ላይ ያለ አዳዲሰ ልበወለድ ታሪክ ታሪካዊ ስነልቦና በአማሪኛ ኦሮሚኛ ጥቂት እንግሊዘኛ የትምህርት አጋዥ መንፈሳዊ ሁሉንም ማግኝት ከፈለግን ምርጫው አንድ ብቻ ነው ዝዋይ ኑረህ ራያ መፀሐፍት መደብርን ካላወቅ አታነብም [ላኪ ወዳጅ አለህ ] ስለራያ መፅሐፍትቤትማ እነግራቹሃለው
10Loading...
29
...."ማንኛዉም ጠንካራ ሰው የጥንካሬዉ ምንጭ ያለፈበት የመከራ መንገድ ነው። ድሎት ዱለት እንጂ ጉልበት እና ጽናትን አያጠግብም። መከራ የጠንካራ ሰው አሻራ ነው። ክርስቶስን ማንም ሰው የሚያስታዉሰዉ በመስቀሉ እንጂ አሳ አበርክቶ በመቆለሉ አይደለም። ከታምራቱ ይልቅ ስቅላቱ አይረሴ አድርጎታል። በምድር ላይ ጥልቅ ሃሳብ ይዘው እንደበጋ መብረቅ ምድርን ያናወጡ ፈላስፋወችማ ከክርስቶስ በፊት ስንት አዝማን ቀድመው ነበሩ። እነሶቅራጥስ እነቡድሃ... ሰዉን ሰዉ የሚአደርገው ቁመናው ሳይሆን ፈተናው ነው።" ተልሚድ ይስማዕከ ወርቁ
3341Loading...
30
በደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ስለ መጽሐፉ የተሰጠ አድናቆት፦ ''ምንትዋብ'' ከዚህ ቀደም ሕይወት ተፈራ ከጻፈቻቸው መጻሕፍት እጅጉን የተለየ ታሪካዊ ልቦለድ ነው። ይዛ የተነሳቻት ባለታሪክም፣ታሪኩ ያጠነጠነበት ዘመንም፣ለኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ድንግል ነው። ሳይነካ ቆይቷል።የሕይወት ብዕር ፣በእቴጌ ምንትዋብ አማካኝነት፣በፈጠራ ሥራወቻችን ውስጥ ችላ ተብሎ፣ወይም ተዘግቶ የነበረውን ዘመን ከፍቶና ገርስሶ፣ቋንቋን፣ውበትን፣ጥበብን፣ፍልስፍናን እና እንደ ፎክሎር ያሉ ዕንቁወቻችን አስቆጠረን። እደግመዋለሁ፣የመካከለኛው ዘመን የታሪክ መጋረጃም በዚህ ልክ በሥነ-ጽሑፋችን ተገልጦ አያውቅም፣ንግስቶቻችንም በዚህ ልቦለድ ልክ፣እንደ ሰው በፍቅር ሲፈተኑ፣በጥበብ ረሀብ ሲናውዙ፣እንደ ሀገር መሪ ህያው ሐውልት ለማኖር ሲኳትኑ፣ሰላምን ለማዝነብ ሲባዝኑ ታይተው አያውቁም። የቀደምት ሠዓሊዎቻችንን ሕይወት እና ፍልስፍና ምን ይመስል እንደነበረም በዚህ ልክ ፈትቶ ያቀረበልን ድርሰት ማግኘትም አስቸጋሪ ነው። ደራሲዋ ትናንትናችንን ከዛሬያችን ጋር ያስተሳሰረችበት ክር ደግሞ ከምንም በላይ አበጀሽ የሚያሰኝ ነው!!! መልካም ንባብ። በሁሉም መጻሕፍት መደብሮች ይገኛል።
3820Loading...
31
በረከት በላይነህ በደጃፍ ፖድካስት ነጻ ትምህርት (Lecture) እየሰጠ አይደል እንዴ ? በረከት ከኪነጥበብ ሰውነቱ ባሻገር የብዙ እውቀት ባለቤት ሆኗል። እውቀቱ ደግሞ የዋዛ አይደለም። በእያንዳንዱ የንግግሩ ውርወራ ውስጥ የዳበረ እና ትጋትን የተሞላ የንባብ ሥርዓት ( Discipline ) ውስጥ እንደታሸ ሚያመለክት እውቀት ነው ያለው ። በራሱ ምርምር ጂኦ ፖለቲክሱን ፣ የተፈጥሮ ሀብቶች ሁኔታን ሚተነትንበት ፣ ሚያነጽርበት መንገድ በጣም ነው ደስ ሚለው። በዚህ ውይይት ብቻ ሳይገታ በመጽሐፎችም በሌሎች ቪድዮዎችም እየመጣ እንዲህ ቢያስደምመን ደስታዬ ነው። ደጃፍ ፖድካስት Dawit Tesfaye ! 🙏🏾
3762Loading...
Photo unavailableShow in Telegram
በጥራት ማደግ! ሁለት አይነት እድገቶችና ትልቅነቶች አሉ፡፡ አንደኛው ውጫዊ እድገትና ትልቅነት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” ነው፡፡ 1. ውጫዊ እድገትና ትልቅነት ሰዎች በገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣ በዝና፣ በስልጣን እና በመሳሰሉት ነገሮች ሲያድጉ፣ “ውጫዊ እድገትና ትልቅነት” አገኙ እንለዋለን፡፡ ይህ እድገትና ትልቅነት ምንም እንኳን በራሱ ምንም ችግር ባይኖረውና እንዲያውም ለጥቅም የሚውል ቢሆንም ብቻውን ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ 2. “ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” ሰዎች በመልካም ስብእና፣ በጤናማ አመለካከት፣ በስሜት ብልህነት፣ በራእይ እና በጥበብ ሲያድጉ፣ “ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” አገኙ እንለዋለን፡፡ ይህ እድገትና ትልቅነት ከማንኛውም ነገር በፊት ሊቀድም የሚገባው የእድገትና የትልቅነት ዘርፍ ነው፡፡ አንድ ሰው ከላይ የተጠቀሱትን አይነት ውጫዊ እድገትንና ትልቅንን እያስመሰዘገ ውስጣዊ እድገት ሲጎድለው ከራሱ ሕይወት ጀምሮ እስከ ቤተሰቡ፣ የስራ ስምሪቱና በሃገር ደረጃ የሚያስከትለው ቀውስ ይህ ነው አይባለም፡፡ የገንዘብ አቅሙን ለማይረባ ነገርና ለሕገ-ወጥ ተግባር የሚጠቀም ማነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን? በዝናውና በታዋቂነቱ የሚኩራራውና ሰውን የሚንቀው ማን ነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን? በስልጣኑ ተጠቅሞ ሰውን የሚደቁስና እንደፈለገ የሚሆን ማን ነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን? በመጀመሪያ በውስጣችን እንደግ! ከሁሉም በፊት በጥራትና በብቃት ትልቅ እንሁን!
Show all...
Elegance Unveiled: Modern Gentleman's Guide 🎩✨ 🎩✨ 1. Politeness is the truest form of sophistication. 🎩🤝 2. Chivalry is not outdated; it's timeless respect. ⚔️🕰️ 3. A gentleman's word is his bond. 🤞👨‍💼 4. Manners maketh man. 🍽️🤵 5. Hold doors open, it's a small gesture with big impact. 🚪💼 6. Cultivate a strong handshake; it speaks volumes. 🤝📈 7. Respect others' opinions, even if you disagree. 🗣️🤝 8. Stand tall, speak kindly, and dress the part. 🕴️👔 9. Offer a genuine compliment; sincerity shines. 💬🌟 10. Master the art of conversation; it's a gentleman's tool. 🗨️🎨 11. A gentleman's strength lies in his gentle touch. 💪🤲 12. Listen more than you speak; wisdom comes in silence. 👂🤐 13. Choose quality over quantity in friendships. 👬🌟 14. Apologize sincerely; it's a mark of true character. 🙏😌 15. Embrace responsibility; it's a mark of maturity. 🤔🔄 16. Gentleness is not a weakness; it's a strength. 🌼💪 17. Be punctual; it shows respect for others' time. ⏰👌 18. Treat everyone with kindness; it's a reflection of your character. 🌍💖 19. Admit mistakes gracefully; humility is attractive. 🤷‍♂️😊 20. Cultivate a sense of humor; laughter is a gentleman's ally. 😄🎭
Show all...
"ሁላችንም ሀሳብ አለን፡፡ ግን ሀሳባችን ዋጋ ያለው አይመስለንም፡፡ ሁልጊዜም ከእኛ የተለዩ፡ ከእኛ የተሻሉ "አሳቢዎች" አሉ ብለን፡ ማሰብን ለማናውቃቸው "ሌሎች" እንተወዋለን፡፡ ወይም "ማሰብ" ምሁራን የሚባሉ ሰዎች ብቻ ስራ ነው ብለን፡ ላሉብን ችግሮች አንድ መፍትሄ አምጥተው እስኪሰጡን አፍ አፋቸውን እያየን እንጠብቃለን፡፡" አለማወቅ በዶክተር ዳዊት ወንድማገኝ
Show all...
እኔ ኢትዮጵያዊያንን አላምንም! (በዓሉ ግርማ) 👉 እኔ ኢትዮጵያዊያንን አላምንም ከራሴ ጀምሮ። በጭንብል ተሸፍነን የምንኖር ህዝቦች ነን። ለሰው የምናሳየው ገፅታና እውነተኛው ባህሪያችን የተለያዩ ናቸው። እንደ ተረታችን ፣ ስነ ፅሁፋችንና ንግግራችን ባህርያችንም ሰምና ወርቅ ነው ... 👉 በዚህ ላይ ደግሞ ክፉውና በጎውን ነገር አንዱን ከሌላው ለይተን የምናይበት መለኪያ የለንም ፤ የማንኛውም ነገር መሠረታዊ መለኪያችን የግል ጥቅማችን ነው። ለዚህም ነው ተንኮል የሚበዛው፤ መተማመን የሌለው፤ የወዳጅነት ወይም የጓደኝነት ትርጉሙ የማይታወቀው ፤ ሀሜት አሉባልታና እርስ በዕርስ መበላላት የሚበዛው። ኢትዮጵያዊያን ስንባል የምናውቀው መርህ አንድ ብቻ ነው ፤ የግል ጥቅም! ከራስ በላይ ነፋስ ፤ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል... ሰውን ማመን ቀብሮ ፥ ይሉታል ከነተረቱ። የሚያሳዝን ነው... 👉 ለግል ጥቅማችን የሚበጅ ከሆነ እንዋሻለን። ስንዋሽ ህሊናችንን ቅንጣት ታህል አይቆረቁረንም። እንዴት አድርጎ ለግል ጥቅም የተገዛ ህሊና ሊቆረቁረው ይችላል? 👉 ለተንኮል አንመለስም የምንሸርበው ተንኮል ጓደኛን፤ ወዳጅን ፤ የስጋ ዘመድን አይለይም ቅናት ባህላችን ነው። 👉 ምግባር የሚባለውን ነገር በአፍ ካልሆነ በቀር በተግባር አናውቀውም። በአጠቃላይ ክፉውንና በጎውን ለይቶ የሚያይ ህሊና የለንም፤ ያስተማረንም የለም። የተማርነው ነገር ቢኖር በአደባባይ ሰው መስሎ መታየትን ነው፤ ሰው መሳይ በሸንጎ ይሉ የለም? በአደባባይ ሁሉም ጨዋ፣ ልበ ሙሉ፣ ጀግና፣ አትንኩኝ ባይ፣ ኩሩና ቅን፣ በጎ አሳቢና ታማኝ፣ አስተዋይና ትሁት ነው። በአደባባይ የምናጠልቀው ጭንብል ይህ ነው። በግል ኑሮአችን ግን ከስብቅ ፣ ከምቀኝነት ፣ ከተንኮል፣ ከቅናት ፣ ለውሸት፣ ከአሉባልታና ከሀሜት፣ ለግል ጥቅም ለመልከስከስና ለመልፈስፈስ ከፍርሃትና ከአድር ባይነት ርቀን አንገኝም። መለያ ባህርያችን ግብዝነት ነው። የግብዝነት ጭንብል አጥልቀን ነው የምንኖረው። ያለ ጭንብል እናስቀይማለን... ወይም እናምራለን፤ አይታወቅም። ያለ ጭንብል ታይተን አናውቅማ! በዓሉ ግርማ የቀይ ኮከብ ጥሪ ገፅ 234
Show all...
👍 1
የሆነ ጊዜ ጓደኛዬ  እግሩን ተሰብሮ ሆስፒታል ተኝቶ ነበር ውጪ በር ላይ የተቀመጠው ወንበር ላይ  ነበርኩ ፣ ፋዘሩ እንባቸውን እየጠረጉ ከተኛበት ክፍል ሲወጡ አየኋቸው ተደናግጬ ዘው ብዬ ገባው ያቃስታል ፤  ምን ሆንክ?  አመመህ ? ስለው እያቃሰተ ስለነበረ ገላመጠኝ እያየኸኝ አይደል አይነት ፋዘር ጋ ምን አወራቹ ? እ ? "እሱ ባክህ  ...... ወንድ ልጅ አይደለህ ጠንከር በል ፣ ቀላል ነገር ነው ብሎኝ ነው ኮስተር ብሎ የወጣው" አለኝ መሃል መሃል ላይ  እያቃሰተ I think አባትነት ጨካኝ መስሎ ተሸሸጎ መባባት ነው አልኩኝ አባትነት ❤ Adhanom Mitiku
Show all...
👍 4