cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ETHIO-MEREJA®

Addisababa, Ethiopia🇪🇹 News & Media Company® . USA : Washington . . . ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!! 👉 @ethio_merejabot

Show more
Advertising posts
132 679Subscribers
+2524 hours
-127 days
+530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ቪዲዮ🎥"የአዲስ አበባ ከተማ የመንገድ ኮሪደር የአስፋልት ማንጠፍ፣ የእግረኛ መንገድ ንጣፍ ዝርጋታ፣ መንገዱን ተከትሎ የሚሰሩ የአረጓዴ ልማት ስራዎች በሁለት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው" - ወ/ሮ አዳነች አቤቤ (የአ/አ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ) በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው የመንገድ ኮሪደር ልማት ስራ አሁን ያለበት ደረጃ ፕሮጅክቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የሚያስችል ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡ በተለይም የአስፋልት ማንጠፍ፣ የእግረኛ መንገድ ንጣፍ ዝርጋታ፣ መንገዱን ተከትሎ የሚሰሩ የአረጓዴ ልማት ስራዎች በሁለት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ የልማት ኮሪደር ስራዎቹ በ5ኮሪደሮች ተለይተው ግንባታቸው በመፋጠን ላይ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን የልማት ኮሪደር ስራዎቹ 6 ክ/ከተሞችን ያካልላሉ ተብሏል። የልማት ኮሪደር ስራው በዋነኛነት:- -መንገዶችን የማስፋፋት ስራ -ወጥና ዘመናዊ የመብራት ዝርጋታ - የአረንጏዴ ልማት ስራዎች - ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት - ሰፋፉና ምቹ የእግረኛ መንገዶች - የብስክሌት መንገድ - ያረጁ ህንጻዎች ጥገና እና ማስዋብ ያካትታል። በልማት ምክንያት ሲኖሩ ከነበሩበት መንደር የተነሱ ነዋሪዎችን በተመለከተ:- -በመንግስት መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ሲኖሩ ለነበሩ ነዋሪዎች ጽዱ እና ለመኖር ምቹ የሆኑ የመኖሪያ ቤቶች ተገንብተው ለነዋሪዎች ተላልፈዋል -የንግድና የመስሪያ ቦታ ለነበራቸው ነዋሪዎች በተገቢ ቦታ የተሻለ የንግድ ቦታ ተሰጥቷል ተብሏል። -የግል ይዞታ ለነበራቸው ነዋሪዎች ካሳና ምትክ ቦታ እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን በራሳቸው በኩል ያሉ መስፈርቶች አጠናቅቀው ለሚመጡ ነዋሪዎች በሚመጡበት ጊዜ የሚስተናገዱ ይሆናል ተብሏል::(ምንጭ፣አዲስ-አበባ ከተማ አስተዳደር)       T.me/ethio_mereja
Show all...
👎 42👍 23 2🥰 2🔥 1
"የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በድጋሚ የሚያገረሽበት ዕድል ዝግ ነው" - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በድጋሚ የሚያገረሽበት ዕድል ዝግ ነው በማለት ትናንት ከቻይናው ሲጂቲኤን ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። ያለፈው ጦርነት የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት አልነበረም ያሉት ጌታቸው ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደርና የትግራይ ሕዝብ ድጋሚ ጦርነት እንዳያገረሽ የተቻላቸውን ጥረት ኹሉ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። ጌታቸው ይህን ያሉት ፣ በአላማጣ አቅራቢያ በትግራይ ኃይሎች እና ባካባቢው ሚሊሻዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ በተደረገ ማግስት ነው መባሉን ዳጉ ጆርናል ከዋዜማ ዘገባ ተመልክቷል። አቶ ጌታቸዉ ይህንን ይበሉ እንጂ አብን፣ ሕወሃት ለአዲስ ዙር ጦርነት ቅስቀሳ እያደረገ ነው ሲል ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ከሷል። ፓርቲው፣ በግጭት ማቆም ስምምነቱ መሠረት የሕወሃት ተዋጊዎች ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ሳይፈቱና መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ክልል ጸጥታ ለማስከበር ሳይሠማራ ሕወሃት ለሌላ ዙር ጦርነት ፕሮፓጋንዳ በመለፈፍ ተጠምዷል ብሏል። የፌደራሉና የአማራ ክልል መንግሥታት የሕወሃትን የጠባጫሪነት ቅስቀሳ በትኩረት እንዲከታተሉና በአማራ ክልል የሚካሄደው ግጭት "በንግግር" እና "ድርድር" እንዲፈታም አብን ጠይቋል። የአማራ ሕዝብ ሕወሃት ሊያደርስበት የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል በአንድነት እንዲቆም የጠየቀው ፓርቲው፣ የትግራይ ሕዝብም ራሱን ከሕወሃት ቀንበር እንዲያላቅቅ ጥሪ አድርጓል።
Show all...
👍 22👎 7 2
"የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በድጋሚ የሚያገረሽበት ዕድል ዝግ ነው" - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በድጋሚ የሚያገረሽበት ዕድል ዝግ ነው በማለት ትናንት ከቻይናው ሲጂቲኤን ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። ያለፈው ጦርነት የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት አልነበረም ያሉት ጌታቸው ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደርና የትግራይ ሕዝብ ድጋሚ ጦርነት እንዳያገረሽ የተቻላቸውን ጥረት ኹሉ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። ጌታቸው ይህን ያሉት ፣ በአላማጣ አቅራቢያ በትግራይ ኃይሎች እና ባካባቢው ሚሊሻዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ በተደረገ ማግስት ነው መባሉን ዳጉ ጆርናል ከዋዜማ ዘገባ ተመልክቷል። አቶ ጌታቸዉ ይህንን ይበሉ እንጂ አብን፣ ሕወሃት ለአዲስ ዙር ጦርነት ቅስቀሳ እያደረገ ነው ሲል ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ከሷል። ፓርቲው፣ በግጭት ማቆም ስምምነቱ መሠረት የሕወሃት ተዋጊዎች ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ሳይፈቱና መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ክልል ጸጥታ ለማስከበር ሳይሠማራ ሕወሃት ለሌላ ዙር ጦርነት ፕሮፓጋንዳ በመለፈፍ ተጠምዷል ብሏል። የፌደራሉና የአማራ ክልል መንግሥታት የሕወሃትን የጠባጫሪነት ቅስቀሳ በትኩረት እንዲከታተሉና በአማራ ክልል የሚካሄደው ግጭት "በንግግር" እና "ድርድር" እንዲፈታም አብን ጠይቋል። የአማራ ሕዝብ ሕወሃት ሊያደርስበት የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል በአንድነት እንዲቆም የጠየቀው ፓርቲው፣ የትግራይ ሕዝብም ራሱን ከሕወሃት ቀንበር እንዲያላቅቅ ጥሪ አድርጓል።
Show all...
በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰሩ የጉምሩክ ሰራተኞች እንደአዲስ ሊዋቀሩ ነው ተባለ በቅርብ ጊዜያት በርካታ ቅሬታዎችን ያስተናገደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉምሩክ የስራ ክፍል፤ ሰራተኞች በአዲስ መልክ እንደሚደራጁ የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ። አዲስ ማለዳ ከብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ ባገኘችው መረጃ  የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በ2016 ስምንት ወራት ውስጥ 49 የጉምሩክ ሰራተኞች እና ከፍተኛ አመራሮች  ላይ አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።   ኮሚሽኑ በሰራተኝኞቹ ላይ የሚቀርቡትን ቅሬታዎች ለመቅረፍ "ረጅም ጊዜ" የወሰደ ጥናት መካሄዱ ታውቋል። በጥናቱ መሰረት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የሚሰሩ የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞን ለመቀየር፣ ለማሸጋሸግ እና በድጋሚ ለማዋቀር ዝግጅት ተደርጓል ተብሏል።
Show all...
👍 48👎 8 3😍 1
THE MOST PRIVATE GROUP №1 ❌ They are robbing Crypto Exchanges for Millions of dollars! Yesterday profit = 50,000$+ 👉 https://t.me/+5YRwSjrwkCIwNDE1 👉 https://t.me/+5YRwSjrwkCIwNDE1 👉 https://t.me/+5YRwSjrwkCIwNDE1 Go fast! Only the first 1000 subs will be accepted! 👀🚀
Show all...
👍 6 1
የአማራ ክልል መንግስት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሀገሪቱን ና ሁለቱን ክልሎች ወደ ቀውስ ከሚያስገቡ ተግባራቶቹ እንዲቆጠብ አስጠነቀቀ። የአማራ ክልል መንግስት ዛሬ ባወጣው መግለጫ “የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትናንትናው እለት ማለትም መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም የራያ አላማጣ ወረዳ ቀበሌዎችን በመያዝ ነዋሪዎችን በመግደልና በማሰቃየት ላይ ይገኛል” ሲል ከሷል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫው፤ የአማራ ክልል መንግስት “የትግራይ መሬቶችን የግዛቱ አካል በማድረግ” በክልሉ ካርታ ላይ አስፍሯል፤ የትግራይ ክልል መሬቶች የሰፈሩበትን ካርታ በትምህርት ካሪኩለሙ በማካተት እያስተማረበት እንደሚገኝ ተረድቻለሁ” ማለቱ ይታወሳል። የአማራ ክልል መንግስት ይህንን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ፤ “የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ በተሳሳተ ካርታ ወደ አማራ ክልል ተካተዋል ያላቸውን አካባቢ ሕዝቦች ታሪካዊ እውነታን፣ ተጨባጭ ማስረጃዎችን እና ነባራዊ ሐቅን የካደ፣ አሳሳችና የጠብ አጫሪነት ፍላጎትን የተሸከመ መግለጫ ነው” ብሎታል። “የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአማራ ክልል የተማሪዎች የመማሪያ መጻሕፍ ውስጥ የተሳሳተ ካርታ ተሰርቷል ሲል ባወጣው መግለጫ ሊያመላክታቸው የተፈለጉት አካባቢዎች ካለፉት 30 ዓመታት በፊት ጀምሮ የወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎችን ሲያቀርቡባቸው በነበሩ ቦታዎች ናቸው” ብሏል የአማራ ክልል በመግለጫው። “ህወሓት የሠሜን ዕዝ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን አሰቃቂ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የማንነትና የአስተዳደር ጥያቄዎቹ ለዘመናት የታፈኑበት ሕዝብ ከማዕከላዊው መንግስት ጎን ተሰልፎ የበኩሉን አስተዋጽዖ ከማበርከቱ ባሻገር በሂደቱ ህወሓት በኃይል ተገፍፎባቸው የነበረውን የማንነትና ጥያቄና ራስን በራስ የማስተዳደር ነጻነት የተቀዳጁበት ሁኔታ ተፈጥሯል” ብሏል የአማራ ክልል መንግስት። የአማራ ክልል በመግለጫው “የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከመማሪያ መጽሃፍ ካርታ ጋር በተያያዘ በአማራ ክልል ላይ ጥቃት ከመፈጸም የማይመለስ መሆኑን የሚገልጽ የጠብ አጫሪ መግለጫ ማውጣቱ ካለፉት ድርብርብ ውድቀቶች ትምህርት አለመውሰድን ከማሳየት የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም” ብሏል። የተፈጠሩ ችግሮችን በህግ አግባብ እንዲፈታ እተደረገ ያለውን ጥረት የአማራ ክልል መንግስት የራሱን ድርሻ እየተወጣ ባለበት ሁኔታ በህዝብ መጎሳቆልና በወጣቶች እልቂት ትምህርት አለመወሰዱና የተለመደ ትንኮሳ በማድረግ ላይ መሆኑ እንዳሳዘነውም ገልጿል። የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ለሀገሪቱ ቋሚ ቀውስ ምንጭ ከሚያደርጉት ተግባራት እንዲታቀብ፣ ሀገራችንንና ሁለቱን ክልሎች ወደ ቀውስ ከሚያስገቡ ተግባራት እንዲቆጠብም የአማራ ክልል መንግስትአስጠንቅቋል።እንዲሁም ጊዚያዊ አስተዳደሩ ከለመደው አጓጉል የካርታ ፖለቲካ ጨዋታ እንዲወጣና የህዝብን ፍላጎት ማዕከል ባደረጉ ውይይቶች ላይ እንዲያተኩር መክሯል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ የአማራ ክልል በመማሪያ መጽሐፍት ላይ ያውጣው የተሳሳተ ካርታ ላይ በአስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያደርግ በመግለጫው አስተጠንቅቆ ነበር።ይህ የማይሆን ከሆነ ግን “ይህን ተከትሎ ለሚመጣው ነገር ሁሉ ሃላፊነቱን የሚወስደው የአማራ ክልል መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን” ብሏል።
Show all...
👍 76 22👎 8🥰 2👏 1
የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት “ዲሞግራፊ ለመቀየር” የሚካሄድ አይደለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተባበሉ!! በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የመንገድ እና አካባቢ ልማት ፕሮጀክት፤ “ዲሞግራፊ ለመቀየር” አሊያም “ኦሮሞዎችን ወደ ከተማ ለመመለስ ነው” የሚሉ ወገኖችን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተችተዋል። አዲስ አበባ ውስጥ “ከበቂ በላይ” የኦሮሞ እና የሌሎች ብሔር ተወላጆች መኖራቸውን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “የሌለ ሰው ኖሮ፤ ሰው ለማምጣት የምንቸገርበት አይደለም” ሲሉም አስተባብለዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህን ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራን ከሚያስፈጽሙ አመራሮች እና የስራ ኃላፊዎች ጋር ትላንት ረቡዕ መጋቢት 18፤ 2016 ባደረጉት ውይይት ነው። እርሳቸው የሚመሩት መንግስት ከዚህ ቀደም ባከናወናቸው የግንባታ ስራዎች “ብዙ ስሞታዎች ነበሩ” ያሉት አብይ፤ ለዚህም የምኒልክ ቤተ መንግስት እና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እድሳትን በምሳሌነት አንስተዋል።  “ይሄ ግቢ ሲቀየር ሀገራዊ ፖለቲካ ነበር። የእዚህን ግቢ እድሳትን እና ዩኒቲ ፓርክን ለመቃወም ሰዎች በጣም ብዙ ደክመዋል። በኋላ [የአዲስ አበባ ከተማ] ማዘጋጃ ቤት ሲጠናቀቅ፤ ‘ለምን ተሰራ’ ተብሎ ብዙ ተብሏል። አሁንም ብዙ አሉባልታዎች፤ ብዙ ወሬዎች ይሰማሉ። ‘ዲሞግራፊ ለመቀየር ነው’፤ ‘ኦሮሞዎች ለመመለስ ነው’ [የሚሉ] የተለያዩ ስሞች ይሰጣሉ” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። አብይ መንግስታቸው የአዲስ አበባ ከተማን “ዲሞግራፊ” የመቀየር እቅድ እንደሌለው ያስረዱት፤ የትውልድ ስፍራቸው የሆነችውን የበሻሻ ከተማ በምሳሌነት በመጥቀስ ነው። “ ‘ዲሞግራፊ መቀየር’ የሚባል ነገር የሚመጣው፤ በሻሻ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ቋሚ ሰዎች የነበሩ ሆነው፤ ሰዎች ከጅማ፣ ከአጋሮ ከመጡ፤ በሻሻ እንዲገቡ እና እንዲቀላቀሉ ሲፈለግ የሚሰራ ስራ ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህንን ከአዲስ አበባ ከተማ ሁኔታ ጋር አነጻጽረዋል።  “አዲስ አበባ ውስጥ፤ ከበቂ በላይ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ፣ ከበቂ በላይ ሁሉም አለበት። የሁለት፣ ሶስት ሚሊዮን ከተማ እኮ አምስት፣ ስድስት [ሚሊዮን] ገባ። የሌለ ሰው ኖሮ፤ ሰው ለማምጣት የምንቸገርበት አይደለም። አዲስ አበባስ የማን ከተማ ሆና ነው፤ ማን ዲሞግራፊ የሚሰቃይባት? አይገባኝም” ሲሉም ተደምጠዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። የአዲስ አበባ የመንገድ ኮሪደር ልማት ዓላማ ከተማይቱ “ የሁሉም እና ውብ” እንድትሆን ማድረግ መሆኑን የጠቀሱት አብይ፤ ከ“ዲሞግራፊ መቀየር” ጋር ተያይዞ የሚሰሙ አስተያየቶችን “ወሬ እና አሉባልታ” ሲሉ አጣጥለዋቸዋል። “ይሄ ወሬ እና አሉባልታ የሚፈርሰው፤ በተግባር ሰርተን ስናሳይ ነው። ከተግባር ውጭ ይህንን ወሬ ሊያፈርስ የሚችል የለም” ያሉት አብይ፤ ፕሮጀክቱ “ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ” የሚተገበር ከሆነ “ሰው ለመገንዘብ አይቸገርም” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። የአዲስ አበባን “አጠቃላይ የመንገድ ሽፋን እና ዘመናዊነት እንዲሁም የትራንስፖርት ፍሰት ወደ ላቀ ደረጃ ሊያሳድግ የሚችል” የተባለለት “የመንገድ ኮሪደር ልማት”፤ በከተማዋ ካቢኔ የጸደቀው ከአንድ ወር በፊት የካቲት 15፤ 2016 ነበር። በዚህ ፕሮጀክት እንዲለሙ ዕቅድ የተያዘላቸው የመንገድ ኮሪደሮች፤ ዓለም አቀፍ “የስማርት ሲቲ” ስታንዳርድን በማሟላት የአዲስ አበባ ከተማን ደረጃ “ከፍ የሚያደርጉ ናቸው” ሲል የከተማይቱ አስተዳደር ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ አይዘነጋም። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)  
Show all...
👎 69👍 45 2🥰 1
👍 4 2
Do you enjoy reading this channel? Perhaps you have thought about placing ads on it? To do this, follow three simple steps: 1) Sign up: https://telega.io/c/ethio_mereja 2) Top up the balance in a convenient way 3) Create an advertising post If the topic of your post fits our channel, we will publish it with pleasure.
Show all...
👍 4🥰 2
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!