ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈

ETHIO-MEREJA®

ETHIO-MEREJA®

前往频道在 Telegram

News & Media Channel® Addisababa, Ethiopia🇪🇹 ውድ የኢትዮ መረጃ ቤተሰቦች ከዚህ የቴሌግራም ቻናል ውጪ ሌላ መረጃ የምናቀርብበት ምንም አይነት የዩቲዩብ፣ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆች እንደሌለን ለማሳወቅ እንወዳለን፣ ስለሆነም በተመሳሳይ ስም በተከፈቱ ገፆች እንዳይሸወዱ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን። ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት 👉 @ethio_merejabot

显示更多

📈 Telegram 频道 ETHIO-MEREJA® 的分析概览

频道 ETHIO-MEREJA® (@ethio_mereja) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 98 485 名订阅者,在 新闻与媒体 类别中位列第 2 665,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 324 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 98 485 名订阅者。

根据 11 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -504,过去 24 小时变化为 0,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 13.51%。内容发布后 24 小时内通常能获得 9.90% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 13 326 次浏览,首日通常累积 9 762 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 33。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“News & Media Channel® Addisababa, Ethiopia🇪🇹 ውድ የኢትዮ መረጃ ቤተሰቦች ከዚህ የቴሌግራም ቻናል ውጪ ሌላ መረጃ የምናቀርብበት ምንም አይነት የዩቲዩብ፣ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆች እንደሌለን ለማሳወቅ እንወዳለን፣ ስለሆነም በተመሳሳይ ስም በተከፈቱ ገፆች እንዳይሸወዱ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን። ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት 👉 @ethio_mere...”

凭借高频更新(最新数据采集于 12 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 新闻与媒体 类别中的关键影响点。

98 485
订阅者
无数据24 小时
-517 天
-50430 天

数据加载中...

吸引订阅者
10月 '26
十月 '26
+39
在3个频道中
九月 '26
+85
在6个频道中
Get PRO
八月 '26
+27
在3个频道中
Get PRO
七月 '26
+6
在4个频道中
Get PRO
六月 '26
+8
在5个频道中
Get PRO
五月 '260
在2个频道中
Get PRO
四月 '26
+10
在6个频道中
Get PRO
三月 '26
+127
在7个频道中
Get PRO
二月 '26
+16
在4个频道中
Get PRO
一月 '26
+15
在8个频道中
Get PRO
十二月 '25
+3
在5个频道中
Get PRO
十一月 '25
+33
在8个频道中
Get PRO
十月 '25
+35
在8个频道中
Get PRO
九月 '25
+65
在4个频道中
Get PRO
八月 '25
+23
在3个频道中
Get PRO
七月 '25
+4
在5个频道中
Get PRO
六月 '25
+49
在8个频道中
Get PRO
五月 '25
+35
在7个频道中
Get PRO
四月 '25
+7
在7个频道中
Get PRO
三月 '25
+26
在3个频道中
Get PRO
二月 '25
+3
在11个频道中
Get PRO
一月 '25
+71
在7个频道中
Get PRO
十二月 '24
+196
在7个频道中
Get PRO
十一月 '24
+183
在10个频道中
Get PRO
十月 '24
+464
在9个频道中
Get PRO
九月 '24
+557
在10个频道中
Get PRO
八月 '24
+594
在14个频道中
Get PRO
七月 '24
+221
在8个频道中
Get PRO
六月 '24
+39
在9个频道中
Get PRO
五月 '24
+248
在10个频道中
Get PRO
四月 '24
+495
在10个频道中
Get PRO
三月 '24
+808
在12个频道中
Get PRO
二月 '24
+449
在9个频道中
Get PRO
一月 '24
+427
在13个频道中
Get PRO
十二月 '23
+249
在8个频道中
Get PRO
十一月 '23
+245
在11个频道中
Get PRO
十月 '23
+987
在19个频道中
Get PRO
九月 '23
+233
在0个频道中
Get PRO
八月 '23
+435
在0个频道中
Get PRO
七月 '23
+582
在0个频道中
Get PRO
六月 '23
+410
在0个频道中
Get PRO
五月 '23
+327
在0个频道中
Get PRO
四月 '23
+578
在0个频道中
Get PRO
三月 '23
+123
在0个频道中
Get PRO
二月 '23
+1 206
在0个频道中
Get PRO
一月 '23
+2 730
在0个频道中
Get PRO
十二月 '22
+261
在0个频道中
Get PRO
十一月 '22
+333
在0个频道中
Get PRO
十月 '22
+381
在0个频道中
Get PRO
九月 '22
+809
在0个频道中
Get PRO
八月 '22
+1 206
在0个频道中
Get PRO
七月 '22
+403
在0个频道中
Get PRO
六月 '22
+288
在0个频道中
Get PRO
五月 '22
+329
在0个频道中
Get PRO
四月 '22
+160
在0个频道中
Get PRO
三月 '22
+2 643
在0个频道中
Get PRO
二月 '22
+101
在0个频道中
Get PRO
一月 '22
+649
在0个频道中
Get PRO
十二月 '21
+598
在0个频道中
Get PRO
十一月 '21
+2 509
在0个频道中
Get PRO
十月 '21
+2 433
在0个频道中
Get PRO
九月 '21
+1 050
在0个频道中
Get PRO
八月 '21
+2 889
在0个频道中
Get PRO
七月 '21
+3 399
在0个频道中
Get PRO
六月 '21
+1 218
在0个频道中
Get PRO
五月 '21
+1 229
在0个频道中
Get PRO
四月 '21
+1 659
在0个频道中
Get PRO
三月 '21
+1 269
在0个频道中
Get PRO
二月 '21
+1 388
在0个频道中
Get PRO
一月 '21
+2 540
在0个频道中
Get PRO
十二月 '20
+253 170
在0个频道中
日期
订阅者增长
提及
频道
11 十月0
10 十月+6
09 十月+1
08 十月+2
07 十月+16
06 十月+3
05 十月0
04 十月+5
03 十月+4
02 十月+2
01 十月0
频道帖子
ኦነግ፣ መንግሥት የባሕር በር ለማግኘት የሚያደርገውን ጥረት በቅንነት እመለከተዋለሁ ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አቋሙን ገለጠ። የአገሪቱ የሕዝብ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረና ኢኮኖሚዋም እያደገ መሄ
ኦነግ፣ መንግሥት የባሕር በር ለማግኘት የሚያደርገውን ጥረት በቅንነት እመለከተዋለሁ ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አቋሙን ገለጠ። የአገሪቱ የሕዝብ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረና ኢኮኖሚዋም እያደገ መሄዱን የገለጠው ኦነግ፣ ለዚህ ደሞ የባሕር በር ማግኘት አማራጭ የለውም ብሏል። ሁሉም የኦሮሞ የፖለቲካ ኃይሎች የሀሳብ ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው ለኦሮሞ ሕዝብ ጥቅምና ደኅንነት በጋር የሚሠሩበት ጊዜው አሁን ነው ሲል ኦነግ ጥሪ ያደረገ ሲሆን፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚደረጉ ጦርነቶች ምንጊዜም የኦሮሚያን ሀብት "ለመበዝበዝ" ያለሙ እና በዚሁ አካባቢ የሚደረጉ ወታደራዊ ጥምረቶችም "ኦሮሞንና ኦሮሞነትን ለማጥፋት" ያለሙ ናቸው ሲል አቋሙን አስታውቋል።

2
የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጄነራል ታደሠ ወረደን ጨምሮ በትግራይ ኃይሎች በቁም እስር ላይ የነበሩ አምስት የቀድሞ የፖለቲካና ወታደራዊ አመራሮች መፈታታቸውን ተሰምቷል። ጄነራል
የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጄነራል ታደሠ ወረደን ጨምሮ በትግራይ ኃይሎች በቁም እስር ላይ የነበሩ አምስት የቀድሞ የፖለቲካና ወታደራዊ አመራሮች መፈታታቸውን ተሰምቷል። ጄነራል ታደሠ፣ የቀድሞው የትግራይ ኃይሎች የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ኢሳያስ ታደሠ እና ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር አብርሃ በመንግሥት ሠራዊት እጅ እንደሚገኙ ተረድተናል። የትግራይ ኃይሎች የመረጃና ደኅንነት ኃላፊ የነበሩት ኮሎኔል ተወልደ እምበብ ስለመለቀቃቸው ግን ለጊዜው ማረጋገጥ አልቻልንም። በሌላ ዜና፣ የትግራይ የሰላም ኃይል እንትጮ አካባቢ አምስት የትግራይ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ለመንግሥት ኃይሎች እጅ መስጠታቸውን ዛሬ አስታውቋል። እጃቸውን የሠጡት ወታደራዊ አዛዦች፣ ኮሎኔል ብርሃነ ገብረኣናንያ፣ ኮሎኔል ወልዳይ ማውጫ፣ ኮሎኔል ገብረማርያም ተኽሉ፣ ኮሎኔል መሓሪ ይፍጠር እና ኮሎኔል ገብረሃዋርያ ደስታ መኾናቸውን ቡድኑ ገልጧል።
2 721
3
🎯ቤት የመግዣው ጊዜ አሁን ነው ከህንፃ ባሻገር እምነትን የገነባው ቴምር ሪልስቴት 👉አፓርትመንትን ብቻ ሳይሆን ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ከበቂ መኪና ማቆሚያ ሊፍት የከርሰ ምድር ውሀ Garbage Sh
🎯ቤት የመግዣው ጊዜ አሁን  ነው   ከህንፃ ባሻገር እምነትን የገነባው ቴምር ሪልስቴት 👉አፓርትመንትን ብቻ ሳይሆን ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ከበቂ መኪና ማቆሚያ ሊፍት የከርሰ ምድር ውሀ Garbage Shooter ,Generator ፕሮግራም ሲኖር የሚዘጋችበት ቴራስ እንዲሁም የኤሌክትሪክ መኪና ጃርች ማድረጊያን ጨምሮ      🎯 በሳር ቤት አደባባይ 👉ባለ 3 መኝታ 134ካሬ፣ 151ካሬ ፣ 162ካሬ  ፣175ካሬ 👉 ባለ 2 መኝታ 132 ካሬ አማራጭ 👉 ባለ 1 መኝታ 73ካሬ ፣ 93 ካሬ አማራጭ      🎯መገናኛ(የካ ክፍለ ከተማ ጀርባ) 👉ባለ 2 መኝታ ከ90ካሬ እስከ 105ካሬ 👉ባለ 3 መኝታ ከ118ካሬ እስከ 145ካሬ 👉Penthouse 210ካሬ እስከ 352ካሬ           🎯ቡልጋርያ(አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት) 👉ባለ 1 መኝታ 68ካሬ እስከ 72ካሬ 👉ባለ 2 መኝታ 81ካሬ እስከ 101ካሬ 👉ባለ 3 መኝታ 142ካሬ * ቅድመ ክፍያ 20% ከፍለው ቀሪው እስኪረከቡ በ3 አመት * 30%-35% ልዩ እና  ታላቅ ቅናሽ #በአዲስ አበባ ቁልፍ በሆኑ አካባቢዎች ላይ ከምቹ አከፍፈል ከወለድ እና ከግንባታ እቃዎች ጭማሪ ነፃ በሆነ ዋጋ እንካቹ እያልን ነው  ለበለጠ መረጃ    +251939770177    +251996856273 📱 WhatsApp: https://wa.me/251939770177 💬 Telegram: @KalTemerRealEstate | https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant
5 095
4
#ሞተር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሞተርሳይክል እንቅስቃሴ ላልተወሰነ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ እንዲታገድ መደረጉን ተከትሎ፣ በሞተር ጥሪና ዲሊቨሪ ስራ ላይ የተሰማሩና ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተዳድሩ በርካ+1
#ሞተር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሞተርሳይክል እንቅስቃሴ ላልተወሰነ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ እንዲታገድ መደረጉን ተከትሎ፣ በሞተር ጥሪና ዲሊቨሪ ስራ ላይ የተሰማሩና ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተዳድሩ በርካታ ወጣቶች ለከፍተኛ የኢኮኖሚና የመኖር አደጋ መጋለጣቸው አስታወቁ። በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ድምፃቸውን ያሰሙ ወጣቶችና ይዘት ፈጣሪዎች እንደገለጹት፣ የከተማዋን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅና ህግ ማስከበር አስፈላጊ ቢሆንም፣ ጥፋተኞችን ለይቶ ከመቀጣት ይልቅ ሁሉንም ሞተረኞች በጅምላ ማገድ ተገቢ አይደለም። አብዛኞቹ ወጣቶች ከጠዋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በብርድና በዝናብ ሳይበገሩ ህጋዊ በሆነ መንገድ በላባቸው ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ፣ የቤት ኪራይ የሚከፍሉና የዕለት ጉርሳቸውን የሚሸፍኑ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ይህ በጅምላ የተጣለ እግድ የበርካታ አባወራዎችን ህይወት ጨለምተኛ የሚያደርግና ለከፍተኛ እንግልት የሚዳርግ በመሆኑ፣ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት የህጋዊ ሰራተኞችንና የህገወጦችን ልዩነት ለይተው መፍትሔ እንዲያበጁ ጥሪ ቀርቧል።
6 846
5
የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት እና አጋሩ የትግራይ የሰላም ኃይል ስልታዊቷን የአድዋ ከተማ ተቆጣጠሩ። ወታደሮቹ የአድዋ ከተማን ሲቆጣጠሩ ከትግራይ ኃይሎች መከላከል እንዳልገጠማቸው ነዋሪዎችን ጠቅሶ የ
የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት እና አጋሩ የትግራይ የሰላም ኃይል ስልታዊቷን የአድዋ ከተማ ተቆጣጠሩ። ወታደሮቹ የአድዋ ከተማን ሲቆጣጠሩ ከትግራይ ኃይሎች መከላከል እንዳልገጠማቸው ነዋሪዎችን ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። ከኤርትራ ድንበር በ40 ኪሎሜትር ገደማ ርቀት ላይ የምትገኘው የዓድዋ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለጹት የመከላከያ ሰራዊት እና አጋሩ ትናንት እሑድ ወደ ከተማዋ ገብተዋል።አቶ አፈወርቂ የተባሉ የከተማዋን ነዋሪ ጠቅሶ የዜና ምንጩ እንዳለው የትግራይ ኃይሎች ከተማዋን ለቀው የወጡት ባለፈው ቅዳሜ ነበር። በታጣቂዎቹ መውጣት እና የፌዴራል ኃይሎች መግባት መካከል በተፈጠረ ክፍተት የአድዋ ሆስፒታልን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ተቋማት መዘረፋቸውን የአይን ምስክሮች ተናግረዋል። ሌላ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የከተማዋ ነዋሪ በበኩላቸው የመንግሥት ወታደሮች ወደ ከተማዋ ቢገቡም ገና መረጋጋት ባለፈጠሩ ያስከተለው ስጋት መንገዶች ባዶ እንዲሆኑ ማድረጉን ተናግረዋል። ባለፈው መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ/ም በአድዋ ከተማ ውስጥ በሚገኝ አንድ ሆቴል ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ጉዳት ደርሶ እንደነበር ACLED የተባለ የግጭት ተከታታይ ቡድን አስታውቆ ነበር ። በወቅቱ በሆቴሉ ውስጥ የህወሓት ባለስልጣናት ስለመኖራቸው ግን አልተረጋገጠም።
7 651
6
በጅቡቲ አቅራቢያ አንድ ጀልባ ተገልብጦ ቢያንስ የ109 ስደተኞች አስከሬን ሲገኝ፣ 80 ኢትዮጵያዊያን ደግሞ በህይወት ተረፉ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ ዛሬ እንደገለፀው በጅቡ
በጅቡቲ አቅራቢያ አንድ ጀልባ ተገልብጦ ቢያንስ የ109 ስደተኞች አስከሬን ሲገኝ፣ 80 ኢትዮጵያዊያን ደግሞ በህይወት ተረፉ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ ዛሬ እንደገለፀው በጅቡቲ ባህር ጠረፍ አካባቢ በተገለበጠው ጀልባ 15 ህፃናትን ጨምሮ 109 ቢያንስ ስደተኞች ህይወታቸው ሲያልፍ ወደ116 በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ አልታወቀም፡፡ ጀልባው የተገለበጠው ሀሙስ እለት ለአርብ አጥቢያ ለሊት ላይ ነው፡፡ ከአደጋው በህይወት የተረፉ በሰጡት መግለጫ ጀልባው ከጅቡቲ ተነስቶ ወደየመን እየተጓዘ እንደነበር ገልፀው 350 ሰዎችን አሳፍሮ እንደበርም አስታውቀዋል፡፡ የተገለበጠውም ከጅቡቲ ኦቦክ ከተማ በስተሰሜን አቅጣጫ ላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የአለም ስደተኞች ኤጀንሲ ወይንም አይኦኤም የጅቡቲ ተወካዩ አሌክሳንደር ኮሳይክ ሲናገሩ ‹‹የሰዎች ህይወት ማለፉ እጅግ አሳዛኝ አሳዛኝ ነው፡፡ በአደጋው ውድ ህይወታቸውን ስላጡትና የት እንደገቡ ስለማይታወቁት እነዚህ ስደተኞች ቤተሰቦቻቸው ምንም መረጃ የሌላቸው መሆኑ ያሳስበናል›› ካሉ በኋላ የድርጅታቸው ሰራተኞች በስፍራው ደርሰው አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ይህ አሳዛኝ ክስተት ስደተኞች ወደየመንና ከዚያም ወደሌሎች የባህረ ሰላጤው አገራት ለመድረስ የባብኤል መንደብን ሰርጥ ለማቋረጥ በሚሞክሩበት ወቅት የሚገጥማቸውን አደጋ እንደሚያሳይም አስረድተዋል፡፡ አይኦኤም እንዳለው ከተገኙት 109 አስከሬኖች ውስጥ 52ቱ ወንዶች፣ 42ቱ ሴቶችና 15 ህፃናት(9 ሴትና 6 ወንዶች) ናቸው፡፡ እስካሁን ባለው መረጃ 80 ሰዎች በህይወት ተርፈው የተገኙ ሲሆን ሁሉም የተረፉት ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውንም አስታውቋል፡፡ የሟቾቹንና የጠፉትን ሰዎች ዜግነት በተመለከተ እስካሁን የተባለ ነገር የለም፡፡
10 678
7
🎯ቤት የመግዣው ጊዜ አሁን ነው ከህንፃ ባሻገር እምነትን የገነባው ቴምር ሪልስቴት 👉አፓርትመንትን ብቻ ሳይሆን ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ከበቂ መኪና ማቆሚያ ሊፍት የከርሰ ምድር ውሀ Garbage Sh
🎯ቤት የመግዣው ጊዜ አሁን  ነው   ከህንፃ ባሻገር እምነትን የገነባው ቴምር ሪልስቴት 👉አፓርትመንትን ብቻ ሳይሆን ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ከበቂ መኪና ማቆሚያ ሊፍት የከርሰ ምድር ውሀ Garbage Shooter ,Generator ፕሮግራም ሲኖር የሚዘጋችበት ቴራስ እንዲሁም የኤሌክትሪክ መኪና ጃርች ማድረጊያን ጨምሮ      🎯 በሳር ቤት አደባባይ 👉ባለ 3 መኝታ 134ካሬ፣ 151ካሬ ፣ 162ካሬ  ፣175ካሬ 👉 ባለ 2 መኝታ 132 ካሬ አማራጭ 👉 ባለ 1 መኝታ 73ካሬ ፣ 93 ካሬ አማራጭ      🎯መገናኛ(የካ ክፍለ ከተማ ጀርባ) 👉ባለ 2 መኝታ ከ90ካሬ እስከ 105ካሬ 👉ባለ 3 መኝታ ከ118ካሬ እስከ 145ካሬ 👉Penthouse 210ካሬ እስከ 352ካሬ           🎯ቡልጋርያ(አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት) 👉ባለ 1 መኝታ 68ካሬ እስከ 72ካሬ 👉ባለ 2 መኝታ 81ካሬ እስከ 101ካሬ 👉ባለ 3 መኝታ 142ካሬ * ቅድመ ክፍያ 20% ከፍለው ቀሪው እስኪረከቡ በ3 አመት * 30%-35% ልዩ እና  ታላቅ ቅናሽ #በአዲስ አበባ ቁልፍ በሆኑ አካባቢዎች ላይ ከምቹ አከፍፈል ከወለድ እና ከግንባታ እቃዎች ጭማሪ ነፃ በሆነ ዋጋ እንካቹ እያልን ነው  ለበለጠ መረጃ    +251939770177    +251996856273 📱 WhatsApp: https://wa.me/251939770177 💬 Telegram: @KalTemerRealEstate | https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant
10 577
8
ትግራይ መቀሌ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ዛሬ ጀምሯል። ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ለሁለት ሳምንት ያህል ተቋርጦ ዛሬ መልሶ በጀመረው የኢትዮ+4
ትግራይ መቀሌ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ዛሬ ጀምሯል። ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ለሁለት ሳምንት ያህል ተቋርጦ ዛሬ መልሶ በጀመረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያው በረራ፦ ➠ አቶ ጌታቸው ረዳ ➠ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ➠ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ➠ የትግራይ የሰላም ኃይል አዛዥ ጀነራል ወዲ አንጥሩ ➠ የትግራይ ሰላም ኃይል አመራር ሜጀር ጃነራል ዘውዱ ኪሮስ ➠ ኮሎኔል ወዲ አባተ  ... እንደነበሩበት ተነግሯል። የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በጫናና በኃይል ከኃላፊነታቸው እንዲነሱና ትግራይን ለቀው እንዲወጡ ከተደረጉ ከ19 ወራት በኋላ ነው መቐለ የተመለሱት። ዛሬ ጥዋት ላይ መቐለ፣ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርሱ በከተማዋ ወጣቶች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ቡድኑ በዛሬ ቆይታው ከኤርትራ በ35 ኪ/ ሜ ርቀት በምትገኘው ዓዲግራት ከተማ ገብቶ ከነዋሪዎች ጋር ይነጋገራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተሰምቷል።
12 023
9
አዲግራት ‼️ ዛሬ የመከላከያ ሠራዊቱ አዲግራት ከተማን ሲቆጣጠር የከተማው ነዋሪዎችና የአካባቢው ህብረተሰብ ለሠራዊቱ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። የአዲግራት ከተማ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊት ያ+3
አዲግራት ‼️ ዛሬ የመከላከያ ሠራዊቱ አዲግራት ከተማን ሲቆጣጠር የከተማው ነዋሪዎችና የአካባቢው ህብረተሰብ ለሠራዊቱ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። የአዲግራት ከተማ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊት ያደረጉት አቀባበል በፎቶ።
13 048
10
በ 1% ቴምር ሪልስቴት የሱቅ ባለቤት መሆን እንዴት እንደምትችሉ ? 👉ሳይቶቹ የሚገኙት በሳር ቤት አደባባይ የንግድ ሱቅ በ ቡልጋርያ(አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት) የንግድ ሱቅ እና ቢሮ እና በገላን(
በ 1% ቴምር ሪልስቴት የሱቅ ባለቤት መሆን እንዴት እንደምትችሉ ? 👉ሳይቶቹ የሚገኙት በሳር ቤት አደባባይ የንግድ ሱቅ በ ቡልጋርያ(አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት) የንግድ ሱቅ እና ቢሮ እና በገላን(ኮንደሚኒየም ፊት ለፊት) የንግድ ሱቅ እንደየ ካሬቸው እንደሚገኙበት floor እና እንደሚገኙበት ሳይት ዋጋቸው ይለያያል ለምሳሌ ሳር ቤት አደባባይ 1ኛ Floor ላይ ያለውን ሱቅ ውስጥ ሙሉ ክፍያ 3,800,000ብር የሆነውን እንስራው 👉ሙሉ ክፍያ 3,800,000ብር 25% ቅድመ ክፍያ 950,000ብር አሁን ይከፈል እና 👉24% በወር 1% (38,000ብር) በ 2 አመት ይከፈላል እና 👉ቀሪውን 51% 10% Structure ሰራ ሲጠናቀቅ 10% Ceramic ስራ ሲጠናቀቅ 10% Aluminium ስራ ሲጠናቀቅ ቀሪውን 21% የንግድ ሱቁን ሲረከቡ የሚከፈል ነው የሚሆነው 📞 +251939770177 📞 +251996856273 #TemerProperties #RealEstateEthiopia #AddisAbaba #LuxuryLiving #HomeInvestment #ቴምርሪልስቴት
12 420
11
በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ወደ ተሀድሶ ማዕከላት እንዲያስገቡ ጥሪ ቀረበ በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን በአቅራቢያቸው ወደተዘጋጁ የተሃድሶ ማዕከላት እን
በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ወደ ተሀድሶ ማዕከላት እንዲያስገቡ ጥሪ ቀረበ በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን በአቅራቢያቸው ወደተዘጋጁ የተሃድሶ ማዕከላት እንዲስገቡ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል፡፡ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ብ/ጄ ደርቤ  መኩሪያው እንዳሉት፤ በደቡባዊ ዞን ያሉ የቀድሞ ተዋጊዎችም ይሁን አመራሮች በማይጨው ከተማ እና መኾኒ ከተማ በመሰብሰብ ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ፡፡ በደቡብ ምስራቅ ዞን መቐለን ጨምሮ ያሉ የታጠቁ ኃይሎችም መቐለ ከተማ በሚገኘው የሰሜን እዝ ጠቅላይ መምሪያ እንዲሁም በምስራቃዊ ዞን ዓዲግራት አካባቢ ያሉ ዓዲግራት እና ውቅሮ ከተማ ላይ ወደ ተዘጋጁ ማዕከላት ሪፖርት እንዲያደርጉ ገልጸዋል። በማዕከላዊ ዞን አክሱም፣ ዓድዋ፣ አቢያዲን ጨምሮ ዓድዋ፣ አክሱም እና አቢያዲ ከተማ ላይ በመሰባሰብ ሪፖርት እንዲያደርጉ ተጠይቋል። በሰሜን ምዕራብ ዞን ያሉ ታጣቂዎች ደግሞ ሽረ ከተማ ላይ በሚገኘው የቀድሞው ማዕከላዊ እዝ ጠቅላይ መምሪያ ላይ ሪፖርት እንዲያደርጉ ተጠቁሟል፡፡ እነዚህን ታጣቂዎች ለመቀበል የመከላከያ ሰራዊቱ ዝግጁ ሆኖ እየጠበቀ እንደሚገኝም የተገለጸ ሲሆን፤ ወደማዕከላቱ የሚመጡ ታጣቂዎች ዓለም አቀፍ መርህን በተከተለ መንገድ እንደሚስተናገዱ ኮሚሽኑ አመልክቷል። በመሆኑም ታጣቂዎቹ ወደተዘጋጁ ማዕከላት በመምጣትና ትጥቃቸውን በማስረከብ አስፈላጊውን የተሃድሶ ሂደት እንዲፈፅሙ ጥሪ ቀርቧል።
12 721
12
በትላንትናው ዕለት በተመሰረተው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ካቢኔ ውስጥ ሳይካተቱ የቀሩት የቀድሞዋ የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ፤ በአፋር ክልል መንግስት ሹመት ተሰጣቸው። የመጀመሪያዋ ሴት
በትላንትናው ዕለት በተመሰረተው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ካቢኔ ውስጥ ሳይካተቱ የቀሩት የቀድሞዋ የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ፤ በአፋር ክልል መንግስት ሹመት ተሰጣቸው። የመጀመሪያዋ ሴት የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር የነበሩት አይሻ፤ የአፋር ክልል የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽንን በኃላፊነት እንዲመሩ በዛሬው ዕለት መሾማቸውን የክልሉ መንግስት አስታውቋል። አራት የፌደራል መስሪያ ቤቶችን በሚኒስትርነት የመሩት አይሻ፤ ወደ ተወለዱበት አፋር ክልል የመለሳቸውን ኃላፊነት የሰጧቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ናቸው። አይሻ በሚኒስትርነት ከመሾማቸው አስቀድሞ የአፋር ክልል የአደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ቢሮ ኃላፊ ነበሩ። የምህንድስና ባለሙያዋ አይሻ የመጀመሪያውን የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትርነትን ያገኙት በ2008 ዓ.ም. ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ስልጣን በያዙ በጥቂት ወራት ልዩነት ካቢኔያቸውን ሲያዋቅሩ ሹመት ከተሰጣቸው 10 ሴቶች አንዷ የነበሩት አይሻ፤ የመከላከያ ሚኒስትርነቱን ከአቶ ሞቱማ መቃሳ ተረክበዋል። ሆኖም ሚኒስትሯ በዚህ የኃላፊነት ቦታቸው የሰሩት አንድ ዓመት ለማይሞላ ጊዜ ነበር። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ለማ መገርሳ በሚያዝያ 2011 ዓ.ም. የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው ሲሾሙ፤ እርሳቸው ወደ ከተማ ልማት እና የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ተዘዋውረዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
13 262
13
ትግራይ ፣ ሽሬ❗️ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ የሰላም ሃይል በመሆን ሽሬ ከተማን ተቆጣጥሯል። የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ የሰላም ሃይል በመሆን ሽሬ ከተማን የተቆጣጠረ ሲሆን ወደ ከተማ+2
ትግራይ ፣ ሽሬ❗️ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ የሰላም ሃይል በመሆን ሽሬ ከተማን ተቆጣጥሯል። የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ የሰላም ሃይል በመሆን ሽሬ ከተማን የተቆጣጠረ ሲሆን ወደ ከተማው ሲገቡ በህዝቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
12 993
14
ተመድ ለኤርትራ ወረራ ምላሽ ይስጥ ስትል ኢትዮጵያ ጠየቀች ጎረቤት ኤርትራን በወራሪነት የከሰሰችው ኢትዮጵያ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግልፅና በመርህ ላይ የተመሰረተ ምላሽ እንዲሰጥ ጠየቀች። ከ
ተመድ ለኤርትራ ወረራ ምላሽ ይስጥ ስትል ኢትዮጵያ ጠየቀች ጎረቤት ኤርትራን በወራሪነት የከሰሰችው ኢትዮጵያ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግልፅና በመርህ ላይ የተመሰረተ ምላሽ እንዲሰጥ ጠየቀች። ከድርጅቱ ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ ጋር የተወያዩት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ፣ ሀገራቸው፣ በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት ሉዓላዊነቷንና የግዛት አንድነቷን የመከለከል መብት እንዳላት መናገራቸውንም ጽሕፈት ቤታቸው አስታውቋል። የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል ሦስት ዞኖች በኩል ድንበር ተሻግረው ወደ ትግራይ ክልል እንደገቡ የገለጹት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ ራሷን የመከላከል ተፈጥሯዊ መብቷን እንደምትጠቀም ለጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት አባላት አስታውቀዋል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወታደሮቹ ከ30-60 ኪሎ ሜትር ወደ ኢትዮጵያ ግዛት እንደገቡ ጠቅሰዋል። የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የባሕር በር ይገባኛል ጥያቄን ካነሳበት ጊዜ ጀምሮ የወረራ ቅስቀሳ ሲያካሂድ ቆይቷል በማለት ከሰዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ግብፅ፣ ሱዳንና ኤርትራ ታጣቂዎችን ይረዳሉ በማለት ሲወነጅል ቆይቷል። ሰሞኑን ደግሞ፣ የኤርትራ ወታደሮች ድንበር ጥሰው ገብተዋል፣ ግልፅ ወረራም ፈጽመዋል በማለት ከሷል።
11 876
15
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ ከተማ በጊዜያዊነት አቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ ከተማ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን የሚያደርገ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ ከተማ በጊዜያዊነት አቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ የኢትዮጵያ አየር መንገድ  ወደ መቀሌ ከተማ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚጀምር መሆኑን አስታወቀ። አየር መንገዱ ደንበኞቹ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ በመሄድ ወይም ወደ ጥሪ ማዕከሉ በመደወል የጉዞ ምዝገባ ማስያዝ እንደሚችሉ ገልጿል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትግራይ ክልል ባለው “ወቅታዊ ሁኔታ” ምክንያት ከመስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ መቀሌ፣ አክሱምና ሽሬ የሚያደርጋቸውን በረራዎች ለጊዜው ማቋረጡ ይታወቃል።
12 241
16
በ 1% ቴምር ሪልስቴት የሱቅ ባለቤት መሆን እንዴት እንደምትችሉ ? 👉ሳይቶቹ የሚገኙት በሳር ቤት አደባባይ የንግድ ሱቅ በ ቡልጋርያ(አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት) የንግድ ሱቅ እና ቢሮ እና በገላን(
በ 1% ቴምር ሪልስቴት የሱቅ ባለቤት መሆን እንዴት እንደምትችሉ ? 👉ሳይቶቹ የሚገኙት በሳር ቤት አደባባይ የንግድ ሱቅ በ ቡልጋርያ(አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት) የንግድ ሱቅ እና ቢሮ እና በገላን(ኮንደሚኒየም ፊት ለፊት) የንግድ ሱቅ እንደየ ካሬቸው እንደሚገኙበት floor እና እንደሚገኙበት ሳይት ዋጋቸው ይለያያል ለምሳሌ ሳር ቤት አደባባይ 1ኛ Floor ላይ ያለውን ሱቅ ውስጥ ሙሉ ክፍያ 3,800,000ብር የሆነውን እንስራው 👉ሙሉ ክፍያ 3,800,000ብር 25% ቅድመ ክፍያ 950,000ብር አሁን ይከፈል እና 👉24% በወር 1% (38,000ብር) በ 2 አመት ይከፈላል እና 👉ቀሪውን 51% 10% Structure ሰራ ሲጠናቀቅ 10% Ceramic ስራ ሲጠናቀቅ 10% Aluminium ስራ ሲጠናቀቅ ቀሪውን 21% የንግድ ሱቁን ሲረከቡ የሚከፈል ነው የሚሆነው 📞 +251939770177 📞 +251996856273 #TemerProperties #RealEstateEthiopia #AddisAbaba #LuxuryLiving #HomeInvestment #ቴምርሪልስቴት
12 999
17
ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ ፈቼ የሚወስደው መንገድ ለሁለት ቀናት ይዘጋል! በአዲስ አበባ ከጎሮ አደባባይ በኮዬ ፈቼ በኩል ወደ ቱሉ ድምቱ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለሁለት ቀናት ዝግ እንደሚሆን የአ
ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ ፈቼ የሚወስደው መንገድ ለሁለት ቀናት ይዘጋል! በአዲስ አበባ ከጎሮ አደባባይ በኮዬ ፈቼ በኩል ወደ ቱሉ ድምቱ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለሁለት ቀናት ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ። በመንገዱ ላይ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር መሠረተ ልማት ሥራ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የመሬት ውስጥ የሚቀበሩ መሠረተ ልማቶችን ለመዘርጋት የዋናው አስፋልት መንገድ ክፍል ተቋርጧል። በመሆኑም ከዛሬ መስከረም 28 እስከ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ ፈቼ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች በጎሮ–ቦሌ ኤርፖርት መንገድ አቅጣጫ በመጓዝ በቡልቡላ በኩል ወደ ኮዬ ፈቼና አካባቢው ሊጓዙ ይገባል ተብሏል። እንዲሁም ከኮዬ ፈቼ ወደ ጎሮ አደባባይ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች ከኮዬ ፈቼ አደባባይ በቡልቡላ በኩል ወደ ጎሮ አደባባይ የሚወስደውን የቦሌ ኤርፖርት–ጎሮ አዲስ መንገድን ጨምሮ ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ባለሥልጣኑ አሳስቧል።
14 502
18
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)ዛሬ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. የካቢኔ አባላትን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው አሾሙ። በዚህ መሠረት ➠አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚ+1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)ዛሬ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. የካቢኔ አባላትን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው አሾሙ። በዚህ መሠረት ➠አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ➠ጌዲዎን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ➠አቶ አዲሱ አረጋ ግብርና ሚኒስትር፣ ➠ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) የገንዘብ ሚኒስትር፣ ➠አቶ መሐመድ ኢድሪስ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር፣ ➠ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ትምህርት ሚኒስትር፣ ➠ወ/ሮ ሃና አርዓያ ሥላሴ የፍትሕ ሚኒስትር፣ ➠ወ/ሮ ያስሚን ውሀብረቢ የንግድና ቀጣና ትብብር ሚኒስትር፣ ➠ዶ/ር ፍሥሐ ይታገሱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር፣ ➠ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር፣ ➠መቅደስ ዳባ (ዶ/ር) የጤና ሚኒስትር፣ ➠አቶ አወሉ አብዲ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር፣ ➠ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሤ የገቢዎች ሚኒስትር፣ ➠አቶ በረከት ፍሥሐ ጽዮን የብሔራዊ ስትራቴጂክ ሚኒስትር፣ ➠ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር፣ ➠ወ/ሮ ዓለም ፀሐይ ጳውሎስ የማዕድን ሚኒስትር፣ ➠አቶ ሳዳት ማሻህ የሎጀስቲክስ ሚኒስትር፣ ➠ወ/ሮ ሻዊት ሻንካ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ➠አቶ ሙሳ አደም የሰላም ሚኒስትር፣ ➠ወ/ሮ ፍሬሕይወት ታምሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር፣ ➠መሀመድ አብዱራህማን (ኢንጂነር) የከተማ መሠረተ ልማት ሚኒስትር፣ ➠ሱልጣን ወሌ (ዶ/ር-ኢንጂነር) የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር፣ ➠አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡ መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ!       -ETHIO-MEREJA-      T.me/ethio_mereja
15 235
19
አሜሪካ በኢትዮጵያ «ወታደራዊ ተቋማት ላይ የረጅም ርቀት ጥቃቶች ሊሰነዘሩ ይችላሉ» ስትል የደህንነት ማስጠንቀቂያ አወጣች አሜሪካ በአዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል፣ በተያዘው የፈረንጆቹ ጥቅምት
አሜሪካ በኢትዮጵያ «ወታደራዊ ተቋማት ላይ የረጅም ርቀት ጥቃቶች ሊሰነዘሩ ይችላሉ» ስትል የደህንነት ማስጠንቀቂያ አወጣች   አሜሪካ በአዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል፣ በተያዘው የፈረንጆቹ ጥቅምት ወር «በኢትዮጵያ ወታደራዊ ተቋማት» ላይ የረጅም ርቀት ጥቃቶች ሊሰነዘሩ ይችላሉ በሚል በኢትዮጵያ የሚኖሩ ዜጎቿ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የደህንነት ማስጠንቀቂያ አስተላለፈች።   አሜሪካ ረቡዕ ምሽት ባወጣችው መግለጫ «በጥቅምት ወር [እ.አ.አ.] በኢትዮጵያ ወታደራዊ ተቋማት ላይ የረጅም ርቀት ጥቃቶች ሊሰነዘሩ እንደሚችሉ የሚጠቁሙ ዘገባዎች ደርሰውኛል» ብላለች። አሜሪካ አክላም ዜጎቿ «አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉና»  ባለሥልጣናት የሚሰጡትን መመሪያ እንዲከተሉ አሳስባለች።   አሜሪካ ማምሻውን ባወጣችው የደህንነት ማስጠንቀቂያ በተጨማሪም ዜጎቿ «በማንኛውም ምክንያት» ወደ አማራ ክልል (ላሊበላን ጨምሮ)፣ ወደ ትግራይ ክልል ወይም ወደ ዓፋር ክልል ከማንኛውም ዓይነት ጉዞ እንዲቆጠቡ መክራለች። ቀደም ሲል በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎቿ ደህንነታቸው የተጠበቀ ከሆነ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ፣ ካልሆነ ደግሞ ሁኔታዎች እስኪሻሻሉ ድረስ ባሉበት ቦታ እንዲጠለሉ አሳስባለች።   መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ!       -ETHIO-MEREJA-      T.me/ethio_mereja
15 582
20
የኤርትራ ጦር ሠራዊት በትግራይ ክልል ወደ ምትገኘው የአዲግራት ከተማ መግባቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። ዶቸ ቬለ ያነጋገራቸው ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ወታደሮቹ ወደ መቐለ በመጓዝ ላይ ይገኛሉ። በት
የኤርትራ ጦር ሠራዊት በትግራይ ክልል ወደ ምትገኘው የአዲግራት ከተማ መግባቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። ዶቸ ቬለ ያነጋገራቸው ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ወታደሮቹ ወደ መቐለ በመጓዝ ላይ ይገኛሉ።  በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ የሚገኙ የመረጃ ምንጭ  የኤርትራ ወታደሮች “በበርካታ ከባድ ተሽከርካሪዎች ተጭነው ወደ ደቡብ አቅጣጫ” እየተጓዙ መሆናቸውን በአዲግራት ከሚገኙ ነዋሪዎች መስማታቸውን ገልጸዋል።  የአዲግራት ከተማ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መሆኗንም ገልጸዋል። ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር 40 በ40 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በምትገኘው አዲግራት የኤርትራ ወታደሮች እንደገቡ በተመሳሳይ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።  ወታደሮቹ ከአዲግራት በደቡባዊ አቅጣጫ ወደ መቐለ በመጓዝ ላይ እንደሚገኙ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት የመረጃ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
16 437