cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ETHIO-MEREJA®

Addisababa, Ethiopia🇪🇹 News & Media Company® . USA : Washington . . . ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!! 👉 @ethio_merejabot

إظهار المزيد
Advertising posts
132 279المشتركون
-2024 hour
-2017 يوم
-36830 يوم

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

አየር መንገዱ ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ማዕከላትን ወደ ሥራ ሊያስገባ መሆኑን ገለጸ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጨማሪ ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ማዕከላትን ወደ ሥራ ሊያስገባ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው ገለጹ፡፡ የአፍሪካ አቪዬሽን የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ተቋማት ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን ትላንት በአዲስ_አበባ ተከፍቷል፡፡ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ተጨማሪ ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ማዕከላትን አገልግሎት ያስጀምራል፡፡ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን አካል ክፍሎች ጥገና ኮምፕሌክስና መለዋወጫዎች ማዕከል እየገነባች ነው ያሉት አቶ መስፍን፤ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ወደ አገልግሎት ለማስገባት እየተሠራ ነው ብለዋል። የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገናው አየር መንገዱን ጨምሮ በአፍሪካ በተለይም በመካከለኛው ምሥራቅ ለሚገኙ አየር መንገዶች አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ የአየር ፍሬም፣ ሞተርና አካል ጥገናን ጨምሮ የምሕንድስና የቁሳቁስ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ማስረዳታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
إظهار الكل...
👍 14🥰 2👎 1
ዜና፡ አቶ ታዬ ደንደአ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍ እና የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት' ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ በጸጥታ ሀይሎች ታህሳስ 2 ቀን በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደኣ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት” ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው። በክሱ ላይ ፤ “ተከሳሹ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ሲሰሩ የሀገርን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደጎን በመተው  ፀረሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በስማቸው በተከፈተ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ነበር” የሚል ተካቷል፡፡ አቶ ታዬ ደንደኣ በቁጥጥር ስር ሲውሉ በራሳቸው እና በቤተሰባቸው ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደደረሰባቸው ገልጸው አቤቱታ በቃል አቅርበዋል። ምርመራው ታሕሳስ 24 ማለቁንና ዘግይቶ ክስ መቅረቡንም ተቃውመዋል። ዐቃቤ ሕግ ሌሎች ምርመራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ገልጾ መልስ ሰጥቷል ሲል ፋና ዘግቧል።ፍርድ ቤቱም በአያያዝ ላይ ያቀረቡትን የመብት ጥያቄ በሚመለከት በጽሑፍ በዝርዝር ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጾ፤ ዋስትናውን በሚመለከት መርምሮ ብይን ለመስጠትም ለሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
إظهار الكل...
😁 57👍 51👎 26 4🥰 3🤔 1😱 1
በኢትዮጵያ በተቋረጡ እና በቆሙ የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይ የ35 ቢሊዮን ብር ካሳ በተቋራጮች ተጠየቀ የ #ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር “በፀጥታ ችግር” ምክንያት በተቋረጡ እና በቆሙ የመንገዶች ፕሮጀክቶች ላይ 34.95 ቢሊዮን ብር ካሳ በተቋራጮች መጠየቁን አስታወቀ። አስተዳደሩ እስከ 2016 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ድረስ “በፀጥታ ችግር” ምክንያት “ሙሉ በሙሉ የኮንትራት ውላቸው የተቋረጠ” 31 የመንገድ ፕሮጀክቶች መኖራቸውንም ይፋ አድርጓል። ከእነዚህ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል 19ኙ የሚገኙት የፋኖ ታጣቂዎች እና የፌደራል መንግሥቱ ግጭት ውስጥ በገቡበት የአማራ ክልል ነው። ለሁለት ዓመታት ያህል ጦርነት በተካሄደበት የትግራይ ክልል ደግሞ 11 የመንገድ ፕሮጀክቶች ውላቸው ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በሚንቀሳቀስበት የኦሮሚያ ክልል ደግሞ 19 የመንገድ ፕሮጀክቶች በጊዜያዊነት ቆመዋል ብሏል። በፀጥታ ችግር በተቋረጡ እና በቆሙ ፕሮጀክቶች ላይ የአገር ውስጥ፣ የውጭ አገር የሥራ ተቋራጮች በድምሩ 34.95 ቢሊዮን ብር ካሳ ጠይቀዋል።ከዚህ ውስጥ 87 በመቶ ወይም 30.5 ቢሊዮን ብር ካሳ የጠየቁት የአገር ውስጥ ሥራ ተቋራጮች ናቸው።
إظهار الكل...
👍 63🤔 5😁 4 3🥰 3🤯 3👏 1
“ሕጋዊ ያልሆኑ አስተዳደሮችን ለማፍረስ ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር ጭምር እየሠራን ነው” - አቶ ጌታቸው ረዳ #የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ “ሕጋዊ ያልሆኑ አስተዳደሮችን ለማፍረስ ከፌደራል መንግሥቱ እና ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር ጭምር እየሠራን ነው” ሲሉ ገለጹ አቶ ጌታቸው ረዳ ትናንት ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከ'ቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ' ጋር በነበራቸው ቆይታ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ በፕሪቶርያ ከስምምነት መደረሱን አስታውሰው “ምዕራብ ትግራይ፣ ሰሜን ምዕራብ ትግራይ እና ደቡብ ትግራይ ያሉ ሕገ-ወጥ አስተዳደሮች ፈርስው” ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የደኅንነት ማረጋገጫ መስጠን ይጨምራል ብለዋል። ይህን ስምምነት ተግባራዊ ማድረግ ረዥም ጊዜ ወስዷል የሚሉት አቶ ጌታቸው፤ ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ረዥም ጊዜ መውሰድ ባይኖርበትም “ከፌደራል መንግሥቱ ጋር አብረን እየሠራን ነው። ከአማራ ክልል ጋርም ቢሆን በተወሰነ ደረጃ አብረን እየሠራን ነው” ብለዋል። ባለፉት ሳምንታት በአማራ እና ትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተው የሰላም መደፍረስ ያጋጠመው በሁለቱ ክልሎች ባሉ “የሚሊሻ አባላት” የነበረ እንጂ መደበኛ ኃይሎች የተሳተፉበት ግጭት አልተካሄደም ብለዋል። የተከሰተውን ሁኔታ ሲያስረዱም፤ “በአማራ ክልል የነበሩ ሚሊሻዎች የተለያዩ አስጊ እንቅስቃሴያዎችን ሲያደርጉ ነበር። በእኛ በኩል ያሉ የሚሊሻ አባላት ምላሽ ሰጥተዋል” ብለዋል። ይህን ተከትሎ የአማራ ክልል ያወጣው መግለጫ “መሬት ላይ ያለውን እውነታ ያላገናዘበ” ነው ያሉት አቶ ጌታቸው፤ የፌደራል መንግሥቱ እና ህወሓት የደረሱት የሰላም ስምምነት ተፈጻሚ እንዳይሆን እያደረገ ያለው ሕጋዊ ያልሆነ የአማራ አስተዳደር ነው ብለዋል።
إظهار الكل...
👎 103👍 79👏 4 3🥰 3🤯 3🔥 1😁 1
በአዲስ_አበባ የመኖሪያ ህንጻ ተደርምሶ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ በመዲናይቱ አዲስ አበባ፣ አዲስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12፣ ልዩ ስሙ ጠሮ መስጂድ በተባለው ቦታ የመኖሪያ ህንጻ ተደርምሶ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ። የመንግስት መገናኛ ብዙሃ የወረዳውን ስራ አስፈፃሚ አይዳ አወልን ጠቅሶ እንደዘገበው አደጋው የተከሰተው የግለሰብ መኖሪያ ቤት ተደርምሶ በጀርባ በሚገኝ ሌላ መኖሪያ ቤት ላይ በማረፉ ነው፡፡ አደጋው የደረሰው ትናንት ምሽት 5 ሰአት ላይ ነው። ዜናው ስለ ተጎጂዎች፣ ስለ አደጋው መንስኤ እና ሌሎች ጉዳቶች ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።
إظهار الكل...
የካናዳ መንግሥት በኢትዮጵያ የፀጥታ ችግር አለባቸው ባላቸው የተለያዩ አካባቢዎች ጉዞ እንዳያደርጉ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። በዚህም በትግራይ፣ በአማራ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በሲዳማ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች መንቀሳቀስ እንደሌለባቸው አስታውቋል። ከኤርትራ ድንበር 10 ኪሎ ሜትር፣ ከሶማሊያና ኬኒያ የሚያዋስኑ ድንበሮች 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ዙሪያ ዜጎች እንዳይንቀሳቀሱ ሲል የጉዞ መረጃዎችን በሚሰጥበት ድረገፅ አስፍሯል።
إظهار الكل...
❇️ Lark Air Humidifier with LED Light        💯 High Quality 🌼 በኤሌክትሪክ የሚሰራ 🌼 ለቤት መልካም መዓዛን የሚሰጥ 🚩Water Tank Capacity: 330ml 🚩Operating power: 2.5W 🚩 Spray Volume 30-50ml/H 🚩Purify the air & Beautify the Environment 🔅Three-level ambient light 🔅Silent humidification 🔅Two levels of fog 🔅Adjustable speed   💦 ዋጋ፦ ✅ 1,600 ብር    ☎️ 0901882392    ☎️ 0931448106
إظهار الكل...
👍 14 1
ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክር መድረክ እንዲመጡ ጥሪ ቀረበ ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክሩ መድረኮች እንዲመጡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ፡፡ የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ሥላሴ፤ ግጭት ሕይወትና ንብረትን ያጠፋል እንጂ ችግርን አይፈታም ሲሉ ገልጸው፤ “ታሪካዊ አጋጣሚ” በሆነው ሀገራዊ ምክክር በመሳተፍ ሐሳብን በማቅረብ መግባባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ ኮሚሽነሯ አሁንም ታጣቂዎቹ ወደ ምክክሩ እንዲመጡ በመጠየቅ ሲመጡም ጥበቃ እንደሚደረግላቸው አረጋግጠዋል፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን ጨምሮ ሌሎች የሲቪክ ድርጅቶች በሀገራዊ ምክክሩ ከመሳተፍ እራሳቸውን አግልለዋል። የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ስራ አስፈጻሚ ኪሚቴ አባል የሆኑት ሱልጣን ቃሲም በቅርቡ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ባደረጉት ቆይታ ፓርቲያቸው የኮሚሽኑ ምስራታ ሂደት እና እያከናወነው ያለው ስራ ላይ ቅሬታ እንዳላቸው አስረድተዋል።
إظهار الكل...
👎 90👍 60 8😁 8
ከአበባ የተሰራው የመጀመሪያው አልማዝ!! ቻይና በዓለም የመጀመሪያ የሆነውን ከአበባ የተሰራ አልማዝ አበረከተች። አልማዝ በተፈጥሮ ከሚገኙ እጅግ ውድ ማዕድናት መካከል አንዱ ነው፡፡ በተፈጥሮ ከሚገኙ ነገሮችም እጅግ ጠንካራው ነው፡፡ ይሁን እንጂ የቻይና ሳይንቲስቶች ፔኦኒ ከተሰኘ ቀይ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ በላብራቶሪ ውሰጥ ይህን በተፈጥሮ የሚገኝ ውድ ማዕድን መስራት መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡ ይህ አልማዝ ሎያንግ ታይም ፕሮሚስ የተሰኘ በቻይና ሎያንግ ከተማ ውሰጥ የሚገኝ ድርጅት የሰራው ሲሆን አልማዙን ከአበባው በሚገኝ የካርቦን ንጥረነገሮች በመጠቀም እንደተሰራ ገልጸዋል፡፡ አልማዙ ከከተማው የፔኦኒ አባባ ማእከል በተገኙ አበቦች የተሰራ ሲሆን ድርጅቱ የተሰራውን 3 ካራት አልማዝ መልሶ ለአበባ ማእከሉ አበርክቷል፡፡የአምራች ድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አልማዙ 41 ሺሕ ዶላር የሚጠጋ ዋጋ እንዳለው ጠቅሰው አልማዙን ለማምረት ባዮ ጄኒክ ካርቦን ኤክስትራክሽን የተሰኘ ከፍተኛ ሙቀትና ግፊት የሚጠቀም ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀሙ ገልጸዋል፡፡ ይህ በቴክኖሎጂ በመታገዝ የሚሰራ አልማዝ በተፈጥሮ ከሚገኘው አልማዝ ጋር በአካልና በኬሚካል ስሪታቸው አንድ አይነት ሲሆኑ የሚለዩትም በዋጋቸውና ለመሰራት በሚፈጁበት ጊዜ ነው ተብሏል፡፡ ሰው ሰራሽ አልማዞቹ በወራት የሚፈጠሩ ሲሆን በተፈጥሮ የሚገኝ አልማዝ ግን ለመፈጠር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዓመታትን ይፈጃሉ፡፡ በተጨማሪም በላብራቶሪ ውስጥ የሚሰሩት አልማዞች ዋጋቸው በተፈጥሮ ከሚገኙት አነስ ያለ ነው መባሉን ከብሪዚ ስክሮል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
إظهار الكل...
👍 42 4🥰 2
መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የሰባት ሀገራት ኤምባሲዎች በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ውጥረት አሳስቦናል ሲሉ ገለጹ የካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ጃፓን፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካ በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ እና አማራ ክልል መካከል “አጨቃጫቂ ቦታዎች” ሲሉ በገለጿቸው የደቡብ ትግራይ አከባቢዎች የተፈጠረው ውጥረት አስግቶናል ሲሉ ገለጹ። ሁሉም አካላት ትጥቅ የማስፈታት፣ ተዋጊዎችን የመበተን እና መልሶ የማቋቋም እንዲሁም ተፈናቃዮችን በሰላማዊ መንገድ ወደ ቀያቸው የመመለስ ጥረት እንዲያፋጥኑ ጠይቀዋል። ሁኔታዎች እንዲረጋጉ እና ንጹሃንን ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ጠይቀዋል። በኢትዮጵያ የሚታየው ውስብስብ የፖለቲካ እና የጸጥታ ቀውስ መፍትሔ ሊያገኝ የሚችለው እና ዘላቂ ሰላም የሚሰፍነው ሁሉን አቀፍ ንግግር በባለድርሻ አካላት መካከል ሲደረግ ብቻ ነው ሲሉ አሳስበዋል።
إظهار الكل...
👍 49👎 13 7🤔 2