ETHIO-MEREJA®
News & Media Channel® Addisababa, Ethiopia🇪🇹 ውድ የኢትዮ መረጃ ቤተሰቦች ከዚህ የቴሌግራም ቻናል ውጪ ሌላ መረጃ የምናቀርብበት ምንም አይነት የዩቲዩብ፣ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆች እንደሌለን ለማሳወቅ እንወዳለን፣ ስለሆነም በተመሳሳይ ስም በተከፈቱ ገፆች እንዳይሸወዱ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን። ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት 👉 @ethio_merejabot
Показати більше📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу ETHIO-MEREJA®
Канал ETHIO-MEREJA® (@ethio_mereja) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 98 717 підписників, посідаючи 2 649 місце в категорії Новини і ЗМІ та 328 місце у регіоні Ефіопія.
📊 Показники аудиторії та динаміка
З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 98 717 підписників.
За останніми даними від 25 вересня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на -950, а за останні 24 години на 2, загальне охоплення залишається високим.
- Статус верифікації: Не верифікований
- Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 18.57%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 8.29% реакцій від загальної кількості підписників.
- Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 18 338 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 8 185 переглядів.
- Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 45.
📝 Опис та контентна політика
Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
“News & Media Channel®
Addisababa, Ethiopia🇪🇹
ውድ የኢትዮ መረጃ ቤተሰቦች ከዚህ የቴሌግራም ቻናል ውጪ ሌላ መረጃ የምናቀርብበት ምንም አይነት የዩቲዩብ፣ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆች እንደሌለን ለማሳወቅ እንወዳለን፣ ስለሆነም በተመሳሳይ ስም በተከፈቱ ገፆች እንዳይሸወዱ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
👉 @ethio_mere...”
Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 26 вересня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Новини і ЗМІ.
Триває завантаження даних...
| Дата | Залучення підписників | Згадування | Канали | |
| 26 вересня | 0 | |||
| 25 вересня | +10 | |||
| 24 вересня | +12 | |||
| 23 вересня | +18 | |||
| 22 вересня | 0 | |||
| 21 вересня | 0 | |||
| 20 вересня | 0 | |||
| 19 вересня | 0 | |||
| 18 вересня | 0 | |||
| 17 вересня | 0 | |||
| 16 вересня | 0 | |||
| 15 вересня | 0 | |||
| 14 вересня | 0 | |||
| 13 вересня | 0 | |||
| 12 вересня | 0 | |||
| 11 вересня | 0 | |||
| 10 вересня | +11 | |||
| 09 вересня | 0 | |||
| 08 вересня | 0 | |||
| 07 вересня | 0 | |||
| 06 вересня | 0 | |||
| 05 вересня | 0 | |||
| 04 вересня | 0 | |||
| 03 вересня | 0 | |||
| 02 вересня | 0 | |||
| 01 вересня | +3 |
| 2 | 🔥 በ40/60 አከፋፈል — ቀሪውን 60% ቤቶትን ሲረከቡ ያለምንም ወለድ እና የዕቃዎች ጭማሪ በኢትዮጵያ ብር የሚከፍሉት!
📍 መገናኛ | የካ ክፍለ ከተማ (ከዲያስፖራ አደባባይ አጠገብ)
ከ8 በላይ ፕሮጀክቶችን ያስረከበው ቴምር ፕሮፐርቲስ አዲስ አስደሳች የክፈያ አማራጭ ይዞልዎ መጥቷል!
በሙሉ ክፍያ ለምትገዙ ደንበኞቻችን የ 35% ቅናሽ አዘጋጅተንላችኃል
🏢 የቤት አማራጮች:
▪️ ባለ 1 መኝታ ከ 60 ካሬ ጀምሮ
▪️ ባለ 2 መኝታ ከ 90 ካሬ ጀምሮ
▪️ ባለ 3 መኝታ ከ 118 - 154 ካሬ
በተጨማሪም
🏠ቡልጋርያ(አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት) እና ሳር ቤት ከ 1 መኝታ 68ካሬ እስከ 3 መኝታ 175ካሬ ድረስ በተለያዩ የካሬ አማራጮች
🎁 ተጨማሪ ጥቅሞች:
👉 40% ቅድመ ክፍያ ለሚከፍሉ 10% ልዩ ቅናሽ!
📲 ለበለጠ መረጃ
+251939770177
+251996856273
በ WhatsApp
WhatsApp: https://wa.me/251939770177
Telegram :@KalTemerRealEstate
https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant | 6 992 |
| 3 | ወጋገን ባንክ እያስገነባው ያለው ባለ 25 ወለል ሕንፃ የገጠመው የፀጥታ ችግር ተግዳሮት!
ከአዲስ አበባ ውጭ በርዝማኔው የመጀመርያው ይሆናል የተባለውን ባለ 25 ወለል ሕንፃ በመቀሌ እያስገነባ ያለው ወጋገን ባንክ፣ ግንባታውን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ የፀጥታ ችግር ተግዳሮት እንደሆነበት ተጠቆመ፡፡
የባንኩ አጠቃላይ የሀብት መጠን ከ111.3 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል፡፡ወጋገን ባንክ በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ ውስጥ እያስገነባው የሚገኘው ይህን ባለ 25 ወለል ሕንፃ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጠውና ወደ ሥራ የገባው ነሐሴ 2017 ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የሕንፃውን ግንባታ በሁለት ዓመት ለማጠናቀቅ የነበረ ቢሆንም፣ የግንባታ ሒደቱ ግን በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር በተፈለገው ፍጥነት ለማከናወን እንዳላስቻለው ለማወቅ ተችሏል፡፡
የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ አብዱሽ ሁሴን መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም. በተካሄደው የባንኩ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባቀረቡት ሪፖርታቸው እንደገለጹትም ‹‹አጠቃላይ የግንባታው አፈጻጸም ከ30 በመቶ በላይ የደረሰ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ሥራውን በታቀደው መሠረት እንዳይከናወን ተግዳሮት ሆኗል፤›› ብለዋል፡፡ ነገር ግን ሥራውን ለማፋጠን ቦርዱ የቅርብ ክትትል እያደረገ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡
በመቀሌ ከተማ በ3,500 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ እየተገነባ ያለው ባለ 25 ወለል (ጂ+25) ሕንፃ የግንባታ ሥራውን ለማጠናቀቅ የታቀደው በ1.5 ቢሊዮን ብር ወጪ ነው፡፡ | 6 308 |
| 4 | መቀመጫውን በአዲስ አበባ ያደረገው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ፤ የአሜሪካ ዜጎች “በማንኛውም ምክንያት” ወደ አማራ፣ ትግራይ እና አፋር ክልሎች እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።
በኢትዮጵያ ወደሚገኙ አምስት ክልሎች ከሚደረጉ ማንኛውም ጉዞዎች እንዲርቁ ከዚህ ቀደም ለዜጎቿ ማስጠንቀቂያ ሰጥታ የነበረችው ካናዳ፤ በዝርዝሩ ውስጥ የአፋር ክልል እንዲካተት አድርጋለች።
ካናዳ የአፋር ክልል የተካተተበትን አዲስ የጉዞ ማስጠንቀቂያ የሰጠችው በትላንትናው ነው። ጎረቤቷ አሜሪካ ዛሬ አርብ መስከረም 15፤ 2019 በኤምባሲዋ በኩል ባሰራጨችው የደህንነት ማንቂያ መልክት፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉ ክልሎች ስላሉ የጸጥታ ሁኔታዎች ለዜጎቿ አጭር ማብራሪያ ሰጥታለች።
ኤምባሲው በዚሁ መልዕክቱ፤ በአማራ ክልል በላሊበላ ከተማ አቅራቢያ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን የሚያመለክት መረጃ እንደደረሰው ገልጿል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከትላንት ሐሙስ መስከረም 14 ጀምሮ ወደ ላሊበላ የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን በመልዕክቱ የጠቀሰው ኤምባሲው፤ ወደ ከተማይቱ የሚደረጉ በረራዎች ዳግም መቼ እንደሚጀመሩ መረጃ እንደሌለው አመልክቷል።
የአሜሪካ ዜጎች ላሊበላን ጨምሮ ወደ አማራ ክልል ሌሎች አካባቢዎች ለማንኛውም ምክንያት እንዳይጓዙም ኤምባሲው መክሯል። ኤምባሲው ተመሳሳይ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ባስተላለፈበት በትግራይ ክልል፤ የኢንተርኔት እና የስልክ ግንኙነት መቋረጡን የሚያመለክቱ መረጃዎችን እንዳገኘም በመልዕክቱ ላይ አክሏል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር) | 7 272 |
| 5 | የ8 ዓመት ህፃንን በመደበቅ 3 ሚሊዮን ብር የጠየቀች የቤት ሰራተኛ ተያዘች
የ8 ዓመት ህፃንን በመኖሪያ ቤት ውስጥ በመደበቅ ለህፃኗ አባት 3 ሚሊዮን ብር የጠየቀች የቤት ሰራተኛ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለች።
ወንጀሉ የተፈፀመው መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም. ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ላይ በልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 8፣ ካርል አደባባይ አካባቢ በሚገኝ መኖሪያ ቤት መሆኑን የአዲስ ፖሊስ መረጃ ያመለክታል።
ፖሊስ እንደገለፀው፣ ሰናይት አየለ የተባለችው ተጠርጣሪ በቤቱ የቤት ሰራተኛ ሆና ለስምንት ወራት ያህል ስትሰራ ቆይታለች።
ተጠርጣሪዋ በዕለቱ የ8 ዓመቷን ህፃን ከቤተሰቦቿ መኖሪያ አፓርታማ ሁለተኛ ፎቅ ላይ ለኪራይ ተብሎ በተዘጋጀ ክፍል ውስጥ እንድትቀመጥ በማድረግ መደበቋን ፖሊስ ገልጿል።
ህፃኗን ከደበቀች በኋላም ለአባቷ በመደወል ልጃቸው እንደታገተች በመግለፅ፣ እንድትለቀቅ 3 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ ጠይቃለች።
የህፃኗ አባት ጉዳዩን ለፖሊስ ካሳወቁ በኋላ ፖሊስ የክትትል ስራ በማከናወን ከ24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተጠርጣሪዋን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። ህፃኗም በመልካም ጤንነት ላይ መገኘቷን ፖሊስ ገልጿል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ | 9 510 |
| 6 | #ሞተር
ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ተከለከለ።
ከዛሬ ከመስከረም 15 ቀን 2019 ጀምሮ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት በአዲስ አበባ ማሽከርከር እንደተከለከለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አሳውቋል።
"አንዳንድ ወንጀል ፈጻሚዎች ሞተር ብስክሌትን በመጠቀም የቅሚያ እና የስርቆት ወንጀል ሲፈጽሙ ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል " ብሏል። "ወንጀል ፈጻሚዎች ከቦታ ቦታ ለመዘዋወር እና የተሰረቁ እቃዎችን ለማጓጓዝ ሞተር ብስክሌትን በብዛት ይጠቀማሉ " ሲል ገልጿል።
ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የትራፊክ ደንቡን እንደማያከብሩ በተለይ ቀይ መብራትን መጣስ፣ ሌሎች ተሽከርካሪዎችን በመግጨት ማምለጥ፣ ሄልሜት ሳያደርጉ ማሽከርከር፣ የተፋፋቀ እና ለእይታ አስቸጋሪ የሆኑ የሠሌዳ ቁጥሮችን መጠቀም በአሽከርካሪዎቹ በስፋት የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶች መሆናቸውን ፖሊስ አመልክቷል።
ወንጀልን ለመከላከል እና በሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የሚፈጸምን የደንብ ጥሰት ለመቆጣጠር ከዛሬ ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ ከኮድ 4 እና ከፖሊስ ሞተር ብስክሌት ውጭ በአዲስ አበባ ከተማ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር መከልከሉን ፖሊስ አሳቋል።
ይህንን ማሳሳቢያ በሚተላለፉ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቂያ ተላልፏል።
#AddisAbabaPolice | 8 731 |
| 7 | 🏢 ካዛንቺስ ሞደርን ኮምፓውንድ
🌿 የከተማ ህይወት + አረንጓዴ ተፈጥሮ በአንድ ላይ!
በአዲስ አበባ እምብርት የሚገነባው ዘመናዊ የመኖሪያ ኮምፓውንድ።
✨ ለምን ካዛንቺስ? ✅ 60% አረንጓዴ ቦታ እና መዝናኛ
✅ ከፍተኛ ደህንነት
✅ ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤ
✅ በቋሚ ዋጋ የቤት ባለቤት የመሆን እድል
✅ 15% ቅድመ ክፍያ
🎉 እስከ 20% ቅናሽ!
🏠 የቤት አማራጮች
🛏 1 መኝታ (55m²)
💰 5,830,385 ብር
➡️ 15% ቅድመ ክፍያ: 874,557 ብር
🛏🛏 2 መኝታ (80m²)
💰 8,480,560 ብር
➡️ 15% ቅድመ ክፍያ: 1,272,084 ብር
🛏🛏🛏 3 መኝታ (95m²)
💰 10,070,665 ብር
➡️ 15% ቅድመ ክፍያ: 1,510,600 ብር
🛏🛏🛏🛏 4 መኝታ (160m²)
💰 16,961,120 ብር
➡️ 15% ቅድመ ክፍያ: 2,544,168 ብር
📲 አሁኑኑ ያግኙን!
☎️ 0928579029
💬 WhatsApp: https://wa.me/25928579029
📩 Telegram: @abel211227 | 7 955 |
| 8 | የአውሮፓ_ህብረት በኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች ጥምረት ላይ ያለውን ስጋት ሲገልጽ ተመድ ደግሞ በአፍሪካ_ቀንድ ሰፊ ግጭት ሊከሰት እንደሚችል አስጠነቀቀ
የአውሮፓ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) በትግራይ ኃይሎች እና በፌዴራል መንግሥት መካከል በድጋሚ በተቀሰቀሰው ውጊያ እንዲሁም የመቐለ፣ የአክሱም እና የሽረ አየር ማረፊያዎች በህወሓት መያዛቸውን ተከትሎ በፍጥነት እየተባባሰ ባለው የሰሜን ኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ ላይ ያላቸውን ጥልቅ ስጋት ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኤምስበርገር ህብረቱ በወታደራዊ እንቅስቃሴው መባባስ እና በትግራይ የሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎች በህወሓት መያዛቸው ጥልቅ ስጋት እንደገባው ተናግረዋል።
አምባሳደሯ በተጨማሪም ህወሓትን ጨምሮ በሰባት ተቃዋሚ እና የታጠቁ ቡድኖች መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም. ይፋ የተደረገውን «የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለህልውና» መመስረት ላይ ስጋት እንዳለ ገልጸው፣ ከወታደራዊ እርምጃ ይልቅ የፖለቲካ ውይይት እንደሚያስፈልግ በድጋሚ ተናግረዋል።
| 7 631 |
| 9 | በትግራይ ክልል የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎቶች መቋረጣቸው ተሰማ!
በትግራይ ክልል እና አዋሳኝ አካባቢዎች እየተደረገ ያለው ውጊያ ተባብሶ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት በክልሉ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ መቋረጡ ተሰምቷል።
የአገልግሎት መቋረጡ የተከሰተው ትናንት ሌሊት ከ4፡21 ጀምሮ እንደሆነ ታውቋል።ምንጮች እንደገለጹት ከሆነ የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ቢቋረጥም ለጊዜው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የስልክ አገልግሎት አሁንም እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል። ሆኖም ግን የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መዘጋቱ በክልሉ ነዋሪዎች፣ በንግዱ ማህበረሰብ እና በቤተሰብ ግንኙነቶች ላይ ከፍተኛ የመረጃ ክፍተትና ጭንቅ ፈጥሮ ይገኛል።
"ይህ የቴሌኮም አገልግሎት መቋረጥ የተከሰተው የትግራይ ኃይሎች በክልሉ የሚገኙ አየር መንገዶችን መቆጣጠራቸውንና በረራዎች መቋረጣቸውን ተከትሎ በተፈጠረው ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ውጥረት ነው" ሲል መሰረት ሚዲያ ዘግቧል።
መረጃዎቻችን ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ!
-ETHIO-MEREJA-
T.me/ethio_mereja | 8 606 |
| 10 | ኔታንያሁ በተመድ፦ «እኛ እናሸንፋለን፤ ከዚህ ውጪ ሌላ አማራጭ የለንም»
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢንያም ኔታንያሁ፣ እየጨመረ በመጣው ዓለም አቀፍ ጫና ውስጥ ሆነው የእስራኤልን አቋም ለዓለም ለማስረዳት በተባበሩት መንግሥታት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር አደረጉ።
ኔታንያሁ ወደ መድረኩ ሲወጡ የበርካታ ሀገራት ልዑካን አዳራሹን ለቀው የወጡ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ በጭብጨባ ተቀብለዋቸዋል። ከእስራኤል ልዑካን ቡድንም «አም ይስራኤል ኻይ» የሚል፣ «የእስራኤል ሕዝብ በሕይወት ይኖራል» የሚል መፈክር ተሰምቷል።
ኔታንያሁ ንግግራቸውን ሲጀምሩም አዳራሹን ለቀው ለወጡት ልዑካን «ሌሎች የሞራል ፈሪዎች ካሉ እባካችሁ አሁኑኑ ውጡ» ሲሉ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ14 ዓመታት በፊት በተመድ የኢራንን የኑክሌር ፕሮግራም ለማስጠንቀቅ የቦምብ ምስል በማሳየት ቀይ መስመር ማስመራታቸውን አስታውሰዋል።
«የኢራን አምባገነን መንግሥት አቶሚክ ቦምብ እንዳታደራጅ ለመከላከል ቃል ገብቼ ነበር፤ ያደረግኩትም በትክክል እሱን ነው» ብለዋል።
የኢራንን የኑክሌር ፕሮግራም ማፍረስ «በጣም ከባድ» ቢሆንም፣ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ካሳለፏቸው ውሳኔዎች ሁሉ ቀላሉ ውሳኔ እንደነበር ገልጸዋል።
ኔታንያሁ እስራኤል ራሷን በመከላከል አዳራሹን ለቀው የወጡትን ሀገራት ጭምር እንደታደገች ገልጸው፣ የእነዚህ ሀገራት መሪዎች በግል እንደሚያመሰግኗቸው ተናግረዋል። ይህንንም «ዓለም አቀፍ ግብዝነት» ሲሉ ገልጸውታል።
እስራኤል ከአጠቃላይ የአረብ ምድር 0.3 በመቶ ብቻ የምትሸፍን ትንሽ ሀገር መሆኗን የጠቀሱት ኔታንያሁ፣ እስራኤልን «ቅኝ ገዥ» በማለት የሚቀርብባትን ክስ አጣጥለዋል።
«ጠላቶቻችን እስራኤል ትወድቃለች ብለው አስበው ነበር፤ አልወደቅንም። ይልቁንም ተነስተን እንደ አንበሳ ተዋጋን» ብለዋል። | 8 482 |
| 11 | በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የ120 ኪሎ ሜትር የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ሊዘረጋ ነው
ኢትዮጵያና ጅቡቲን የሚያገናኝ አዲስ ድንበር ተሻጋሪ የነዳጅ ምርቶች ማስተላለፊያ መስመር ሊገነባ እንደሆነ ተገለጸ።
የኢትዮጵያን የኃይል ዋስትና ለማረጋገጥና ቀጣናዊ የንግድ ትስስርን ለማሳደግ ያለመው ይህ ስትራቴጂካዊ ፕሮጀክት፤ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በዳንጎቴ ግሩፕ የጋራ ኢንቨስትመንት የሚከናወን ነው።
ከጅቡቲዋ ዳመርጆግ እስከ ኢትዮጵያዋ ደወሌ ድረስ 120 ኪሎ ሜትር ያህል የሚዘልቀው ይህ የመሠረተ ልማት ውጥን፤ በዳመርጆግ የሚገኙትን የባሕር ላይ ነዳጅ መቀበያና ማከማቻ ተቋማት በደወሌ ከሚገኙት የሀገር ውስጥ ማከማቻና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ጋር የተቀናጀ የሎጅስቲክስ ሥርዓት ይፈጥራል።
በዚህ ሥርዓት አማካኝነት በዳመርጆግ ተርሚናል የሚረከቧቸውን የተጣሩ የነዳጅ ምርቶች በልዩ ማከማቻዎች ውስጥ ካከማቹ በኋላ፤ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት በሚሰጥ የነዳጅ ቱቦ መስመር (Pipeline) አማካኝነት ወደ ደወሌ በማጓጓዝ በሀገር ውስጥ በስፋት ማሰራጨት እንደሚቻል ተመልቷል። ፕሮጀክቱ የነዳጅ ምርቶችን ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ በተሻለ ፍጥነት፣ በታማኝነትና በአስተማማኝ ሁኔታ ለማጓጓዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሎ ይጠበቃል። | 8 578 |
| 12 | 🔥 በ40/60 አከፋፈል — ቀሪውን 60% ቤቶትን ሲረከቡ ያለምንም ወለድ እና የዕቃዎች ጭማሪ በኢትዮጵያ ብር የሚከፍሉት!
📍 መገናኛ | የካ ክፍለ ከተማ (ከዲያስፖራ አደባባይ አጠገብ)
ከ8 በላይ ፕሮጀክቶችን ያስረከበው ቴምር ፕሮፐርቲስ አዲስ አስደሳች የክፈያ አማራጭ ይዞልዎ መጥቷል!
በሙሉ ክፍያ ለምትገዙ ደንበኞቻችን የ 35% ቅናሽ አዘጋጅተንላችኃል
🏢 የቤት አማራጮች:
▪️ ባለ 1 መኝታ ከ 60 ካሬ ጀምሮ
▪️ ባለ 2 መኝታ ከ 90 ካሬ ጀምሮ
▪️ ባለ 3 መኝታ ከ 118 - 154 ካሬ
በተጨማሪም
🏠ቡልጋርያ(አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት) እና ሳር ቤት ከ 1 መኝታ 68ካሬ እስከ 3 መኝታ 175ካሬ ድረስ በተለያዩ የካሬ አማራጮች
🎁 ተጨማሪ ጥቅሞች:
👉 40% ቅድመ ክፍያ ለሚከፍሉ 10% ልዩ ቅናሽ!
📲 ለበለጠ መረጃ
+251939770177
+251996856273
በ WhatsApp
WhatsApp: https://wa.me/251939770177
Telegram :@KalTemerRealEstate
https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant | 9 192 |
| 13 | በኤልኒኖ ምክንያት ሊከሰት የሚችለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሰብል ላይ ብክነት እንዳያስከትል ጥንቃቄ ያስፈልጋል ተባለ
በሰሜንና በምዕራብ የአገሪቱ ክፍሎች የበጋው ወቅት የደረሱ ሰብሎች የሚሰበሰቡበት በመሆኑ፤በኤልኒኖ ምክንያት ሊከሰት የሚችለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሰብል ላይ ብክነት እንዳያስከትል ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡
በየኢትዮጵያ ሜትሮዎሎጂ ኢንስቲትዩት የግብርና ሜትሮዎሎጂ ባለሙያዉ አቶ ይመራ አሰፋ እንደገለፁት፤አርሶ አደሮች ማሳቸውን በየጊዜው በመከታተል የደረሱ ሰብሎችን በፍጥነት እንዲሰበስቡና ወደ ጎተራ እንዲያስገቡ፣ የዘገዩ ሰብሎች ካሉ ደግሞ ዝናቡን ለምርታማነት እንዲጠቀሙበት ምክረ ሃሳብ ሰጥተዋል።
ባለሙያዉ በመጪው የበጋ ወቅት የሚጠበቀው የአየር ጸባይ ለግብርናው ዘርፍ ሁለገብ ተፅዕኖ እንዳለው ገልጸው፤አርሶና አርብቶ አደሩ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርግ አሳስበዋል።
የኢንስቲትዩቱ የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎች በየክልሉ ላሉ የግብርና ቢሮዎችና ባለሙያዎች እየተላለፉ መሆኑ ተቋሙ እየገለፀ ይገኛል። | 9 881 |
| 14 | 🏢 ካዛንቺስ ሞደርን ኮምፓውንድ
🌿 የከተማ ህይወት + አረንጓዴ ተፈጥሮ በአንድ ላይ!
በአዲስ አበባ እምብርት የሚገነባው ዘመናዊ የመኖሪያ ኮምፓውንድ።
✨ ለምን ካዛንቺስ? ✅ 60% አረንጓዴ ቦታ እና መዝናኛ
✅ ከፍተኛ ደህንነት
✅ ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤ
✅ በቋሚ ዋጋ የቤት ባለቤት የመሆን እድል
✅ 15% ቅድመ ክፍያ
🎉 እስከ 20% ቅናሽ!
🏠 የቤት አማራጮች
🛏 1 መኝታ (55m²)
💰 5,830,385 ብር
➡️ 15% ቅድመ ክፍያ: 874,557 ብር
🛏🛏 2 መኝታ (80m²)
💰 8,480,560 ብር
➡️ 15% ቅድመ ክፍያ: 1,272,084 ብር
🛏🛏🛏 3 መኝታ (95m²)
💰 10,070,665 ብር
➡️ 15% ቅድመ ክፍያ: 1,510,600 ብር
🛏🛏🛏🛏 4 መኝታ (160m²)
💰 16,961,120 ብር
➡️ 15% ቅድመ ክፍያ: 2,544,168 ብር
📲 አሁኑኑ ያግኙን!
☎️ 0928579029
💬 WhatsApp: https://wa.me/25928579029
📩 Telegram: @abel211227 | 9 246 |
| 15 | አሜሪካ ለሱዳኑ መሪ ጄነራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሃን ቪዛ ከለከለች
አሜሪካ የሱዳን ወታደራዊ መሪ ጄነራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሃን ወደ ግዛቷ ለመግባት ያቀረቡትን የቪዛ ጥያቄ ውድቅ ማድረጓ ተነገረ።
የፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው አሜሪካ የሱዳኑ መሪ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ባለው በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ነበር የአሜሪካን ቪዛ የጠየቁት።
አሜሪካ የቪዛ ክልከላውን በተመለከተ በይፋ የሰጠችው ማብራሪያ የሌለ ሲሆን፣ አንድ ምንጭ ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት ቪዛውን የምትሰጠው "አል ቡርሃን ለሦስት ወራት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነትን ሲቀበሉ" እንደሆነ ገልጿል።
ነገር ግን ከፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጋር በደም አፋሳሽ ጦርነት ውስጥ የሚገኘው በአል ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ኃይል እንዲህ ዓይነቱ ፋታ ተቀናቃኙ መልሶ እንዲደራጅ እና ጥቃቱን እንዲቀጥል ዕድል ይሰጣል በሚል ተቃውሞታል።
የቪዛ ክልከላውን በተመለከተ የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤እርምጃው ድርጅቱን እንዳሳሰበው እና ዋና ፀሐፊው አሜሪካን እንደ አስተናጋጅ አገር ያለባትን ግዴታ በመፈጸም አል-ቡርሃን በአካል እንዲሳተፉ ቪዛውን እንድትሰጥ እያሳሰቡ መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጽህፈት ቤት ጉዳዩ እንደተሰማ ወዲያውኑ ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር መነጋገር እንደጀመረ እና ውይይቱም መቀጠሉን ገልጸዋል።
ጄነራል አል ቡርሃን የአገራት መሪዎች በሚሳተፉበት በዓመታዊው የመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በመገኘት ንግግር ለማድረግ ፕሮግራም ተይዞላቸው ነበር። | 8 712 |
| 16 | ተማሪ ኦብሴ እና እናቷ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት ተበረከተላቸው
በቅርቡ በሁለት ሴቶች ቤቷ ድረስ በተፈጸመባት አሰቃቂ የድብደባ ጥቃት ሳቢያ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን እና የብዙሃኑን ህዝብ ቁጣ ቀስቅሶ የነበረው አሳዛኝ ድርጊት ሰለባ የሆነችው ተማሪ ኦብሴ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት ስጦታ ተደረገላት።
ዛሬ ይፋ በተደረገው አዲስ የቪዲዮ መረጃ መሰረት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተማሪ ኦብሴ እና ለእናቷ የመኖሪያ ቤቱን ቁልፍ ያስረከቡ ሲሆን፥ አጠቃላይ የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም ተገልጿል። | 8 827 |
| 17 | አሜሪካ በህወሓት ላይ ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጠች!
ተጨማሪ ኃይለኛ ማዕቀቦችን እንደምትጥልም አሳስባለች!
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ ዛሬ ባወጡት መግለጫ የህወሓት አመራሮች የጀመሩትን አዲስ እና መጠነ ሰፊ ጥቃት አጥብቀው ኮንነዋል። አምባሳደሩ የቡድኑን እርምጃ "ማሸነፍ የማይቻልበት እና ለህዝብ ምንም የማይፈይድ አደገኛ ውሳኔ" ሲሉ አጣጥለውታል።
በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አደራዳሪነት በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር የተጀመረውን የሰላም ውይይት ወደ ጎን በመተው ህወሓት ዳግም ወደ ጦርነት ማምራቱ አሜሪካን ክፉኛ አሳዝኗል። ይህንኑ ተከትሎም ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ከዚህ እብደት እና የጥፋት ጦርነት እራሳቸውን እንዲያርቁ እና ከስህተቱ እንዲማሩ አምባሳደሩ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል።
በ2026 ዓመት መጀመሪያ ላይ በህወሓት አመራሮች ላይ ማዕቀብ መጣሏን ያስታወሰችው አሜሪካ፣ ኢትዮጵያን ወደ ተሳሳተ አዘቅት በሚገፉ ተጨማሪ አመራሮች ላይም ኃይለኛ ማዕቀብ ለመጣል የሚያስችል ሙሉ አቅምና መሳሪያ እንዳላት አስጠንቅቃለች። ምንም እንኳን አሜሪካ ይህን የቅጣት በትር ለማሳረፍ ዝግጁ መሆኗን ብታሳውቅም፣ አሁንም ቢሆን ከጥፋቱ ለመመለስ ትክክለኛው መንገድ ምክንያታዊ የሆነ የፖለቲካ ውይይት ማድረግ ብቻ መሆኑን አምባሳደር ማሲንጋ በአፅንዖት አሳስበዋል። | 10 502 |
| 18 | የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሰብሳቢ በሰሜን ኢትዮጵያ በአፋጣኝ ውጥረቱ እንዲቀንስ ጥሪ አቀረቡ!
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን (AUC) ሰብሳቢ ማህሙድ አሊ ዩሱፍ በሰሜን ኢትዮጵያ እንደገና የተባባሰውን ውጥረትና የወታደራዊ እርምጃ በከፍተኛ ስጋት መመልከታቸውን ገለጹ።
ሰብሳቢው በተለይ መቀሌ፣ አክሱምና ሽሬ አየር ማረፊያዎች በትግራይ ኃይሎች መያዛቸውና የፌዴራል ሠራተኞች መታሰራቸው እና የሲቪል የአየር በረራዎች መስተጓጎላቸው ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረ ጠቁመዋል።
በተጨማሪም በደቡብ ትግራይና በአፋር ክልል የግጭት ሁኔታዎች እየተባባሱ መሆናቸውን እና አዳዲስ የፖለቲካና የወታደራዊ ትብብሮች መፈጠራቸው ሁኔታውን የበለጠ ሊያባብስ እንደሚችል ገልጸዋል።
(ሙሉ መግለጫው ተያይዟል) | 10 234 |
| 19 | 🔥 በ40/60 አከፋፈል — ቀሪውን 60% ቤቶትን ሲረከቡ ያለምንም ወለድ እና የዕቃዎች ጭማሪ በኢትዮጵያ ብር የሚከፍሉት!
📍 መገናኛ | የካ ክፍለ ከተማ (ከዲያስፖራ አደባባይ አጠገብ)
ከ8 በላይ ፕሮጀክቶችን ያስረከበው ቴምር ፕሮፐርቲስ አዲስ አስደሳች የክፈያ አማራጭ ይዞልዎ መጥቷል!
በሙሉ ክፍያ ለምትገዙ ደንበኞቻችን የ 35% ቅናሽ አዘጋጅተንላችኃል
🏢 የቤት አማራጮች:
▪️ ባለ 1 መኝታ ከ 60 ካሬ ጀምሮ
▪️ ባለ 2 መኝታ ከ 90 ካሬ ጀምሮ
▪️ ባለ 3 መኝታ ከ 118 - 154 ካሬ
በተጨማሪም
🏠ቡልጋርያ(አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት) እና ሳር ቤት ከ 1 መኝታ 68ካሬ እስከ 3 መኝታ 175ካሬ ድረስ በተለያዩ የካሬ አማራጮች
🎁 ተጨማሪ ጥቅሞች:
👉 40% ቅድመ ክፍያ ለሚከፍሉ 10% ልዩ ቅናሽ!
📲 ለበለጠ መረጃ
+251939770177
+251996856273
በ WhatsApp
WhatsApp: https://wa.me/251939770177
Telegram :@KalTemerRealEstate
https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant | 9 971 |
| 20 | አንጋፋው ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ፣ በተለይም በወርቃማው የሙዚቃ ዘመን ከ60 በላይ የማይረሱና ተወዳጅ የሙዚቃ ሥራዎችን ያበረከተው አንጋፋው ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ድምፃዊው በአዲስ አበባ አራት ኪሎ ፊት በር በሚባለው አካባቢ ተወልዶ ያደገ ሲሆን፣ ከሙዚቃ ጋር የነበረው ጥልቅ ፍቅርና ከአንጋፋው ድምፃዊ ጥላሁን ገሰሰ ጋር የነበረው ቅርበት ወደ ሙዚቃው ዓለም እንዲገባ ካደረጉት ዋና ምክንያቶች መካከል መሆናቸው ተገልጿል።
ግርማ ነጋሽ የሙዚቃ ሥራውን የጀመረው በፖሊስ ሰራዊት ኦርኬስትራ ባንድ ውስጥ በመቀጠር ነበር። በኋላም በብሔራዊ ቲያትር ቤት በመቀጠር በድምፃዊነት ሙያውን አጠናክሮ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የራሱን አሻራ ማሳረፍ ችሏል።
ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ በመድረክ ላይ ካቀረባቸውና ከፍተኛ ተወዳጅነት ካተረፉት ሥራዎቹ መካከል “የኔ ሐሳብ” እና “ምነው ተለየሽኝ — መስከረም ሳይጠባ” የተሰኙት ይጠቀሳሉ።
እነዚህ ሥራዎች ከ60 ዓመታት በላይ ታሪክ ቢኖራቸውም፣ እስከዛሬ ድረስ በሙዚቃ አድማጮች ዘንድ ተወዳጅነታቸውን የጠበቁ ሥራዎች መሆናቸው ተገልጿል።
እ.ኤ.አ. በ2011 በአዲስ አበባ ከታዋቂው Either/Orchestra የጃዝ ባንድ ጋር በመሆን “የኔ ሐሳብ” የተሰኘውን ታሪካዊ ሥራውን በመድረክ ላይ እንደገና በማቅረብ ተሳትፏል።
የአንጋፋው ድምፃዊ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገልጿል። ግርማ ነጋሽ የሦስት ወንዶችና የአንድ ሴት ልጅ አባት ነበር። | 11 531 |
