ar
Feedback
DW Amharic

DW Amharic

الذهاب إلى القناة على Telegram

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام DW Amharic

تُعد قناة DW Amharic (@dw_amharic) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 54 769 مشتركاً، محتلاً المرتبة 4 795 في فئة الأخبار والوسائط والمرتبة 575 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 54 769 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 08 يوليو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار -58، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -6، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: موثّقة (مؤكدة رسمياً من تيليجرام)
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 7.88‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 5.49‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 4 314 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 3 006 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 0.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 09 يوليو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الأخبار والوسائط.

54 769
المشتركون
-624 ساعات
+47 أيام
-5830 أيام
أرشيف المشاركات

ኢቦላ፣ ከሞት ያመለጡት ተስፋን ይሰብካሉ፣ የገዳዩ በሽታ ሥርጭት ግን አልተገታም ምሥራቂዉ ኮንጎ አልፎ አልፎ የሚታይ ተስፋ ብልጭ ብሏል።በኢቦላ ተሕዋሲ ሥርጭት ከፉኛ የተጎዳችዉ ቤኒ ከተማ ከተሕዋሲ መፈወሷ የተረጋገጠ የመጀሪያዋ ሰዉ ተመዝግቦባታል።በሽታዉ ግን አሁንም እየተዛመተ ነዉ።የጤና ባለሙያዎችም ከተሕዋሲዉ ጋር ብቻ ሳይሆን ከፍርሐት፣ከተሳሳተ መረጃና ከጊዜ ጋር እየታገሉ ነዉ።ከኢቦላ የዳነችዉ የቤኒ ነዋሪ ማሕበረሰቡ ተስፋ እንዳይቆርጥ ትመክራለች።እሷ መዳንዋ የተረጋገጠዉ በሽታዉን ለመከላከል ባለሙያዎች በሚረባረቡበት ወቅት ነዉ።(ቪዲዮዉን ይመልከቱ)

የቀጥታ ስርጭት ማስታወቂያ የረቡዕ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ስርጭታችን የዓለም ዜና ይቀድማል። ዜናውን በሚከተለው የዜና መጽሔት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለዋጋ ንረት የሰጡት ማብራሪያ ና የ
የቀጥታ ስርጭት ማስታወቂያ የረቡዕ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ስርጭታችን የዓለም ዜና ይቀድማል። ዜናውን በሚከተለው የዜና መጽሔት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለዋጋ ንረት የሰጡት ማብራሪያ ና የሕዝብ አስተያየት፤ ትግራይ ክልል ይካሄዳል የተባለው የወጣቶች የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላና ይህን በመቃወም በቅርቡ ይካሄዳል የተባለው ሰልፍ፤ የኢትዮጵያን ኤኮኖሚ በሚመለከት የባለሙያዎች እይታ፤ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤና የሕዝቡ አስተያየት እንዲሁም ባገረሸው የኢራን አሜሪካ ጦርነት ምክንያት የነዳጅ ዘይት ዋጋ ዳግም ማሻቀቡን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን ተካተዋል። ሳምንታዊው የኤኮኖሚው ዓለም ኢትዮጵያ 5.5 ቢሊዮን ዶላር ካገኘችበት የወርቅ ገበያ ብሔራዊ ባንክ እንዲወጣ አይኤምኤፍ የሚገፋው ለምንድነው? በማለት ይጠይቃል። ሳይንስ እና ቴክኒዎሎጂ ደግሞ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በሕግ እንዲመራ መጠየቁን ይዳስሳል። ዝግጅቶቹን ለመከታተል ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ ቀጠሮአችሁ ከዶቼቬለ ጋር ይሁን

የትራምፕ ወቀሳና ዛቻ በኔቶ ጉባኤ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት በምህጻሩ ኔቶ ጉባኤ ዛሬ በአንካራ ቱርክ ተጀምሯል። በጉባኤ ላይ የተገኙት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ
የትራምፕ ወቀሳና ዛቻ በኔቶ ጉባኤ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት በምህጻሩ ኔቶ ጉባኤ ዛሬ በአንካራ ቱርክ ተጀምሯል። በጉባኤ ላይ የተገኙት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደቀደሙት ጊዜያት ሁሉ የኔቶ አባል ሀገራትን ሲወቅሱ፣ በስፔይን ላይ ሲዝቱ፤ ግሪንላንድንም ሲያስፈራሩ ተሰምተዋል። ጉባኤው ከመጀመሩ አስቀድሞ ትራምፕ ከኔቶ ዋና ጸሀፊ ማርክ ሩተ ጋር በተነጋገሩበት ወቅት በኔቶ ደስተኛ አለመሆናቸውን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። በግሪንላንድ ጉዳይ እንዲሁም ቁጥር አንድ የሽብር ደጋፊ ባሏት በኢራን ጉዳይ ሊረዱን ባለመፈለጋቸው በኔቶ ደስተኛ አይደለንም ብለዋል። ስፔይንን አስፈሪ የኔቶ አባል ሲሉ የተቹት ትራምፕ ከአሁን በኋላ ከስፔን ጋር ምንም ዓይነት የንግድ ግንኙነት አይኖረንምም ብለዋል። ትራምፕ ዛሬ ከስፔን ጋር አገራቸው የነበራትን የንግድ ግንኙነት እንደምታቋረጥ ዝተዋል። ትራምፕ አሁንም ቢሆን የኔቶ አባል የሆነችውን የዴንማርክን ግዛት ግሪንላንድ የመጠቅለል ፍላጎታቸውን ከመናገር አልተቆጠቡም። ግሪንላንድ ለኛ በጣም አስፈላጊ ስትሆን ለዴንማርክ ግን አስፈላጊ አይደለችም ያሉት ትራምፕ አሁንም እንደሚፈልጓት አጽንኦት ሰጥተዋል። «እኛ የምንፈልጋት ለዩናይትድ ስቴትስ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ጥበቃ ለማድረግ ነው» በማለት ትራምፕ «ግሪንላንድን መያዝ እኛን ይረዳናል ለዴንማርክ ግን የሚፈይደው አይኖርም» ሲሉም ሞግተዋል። የኔቶ ዋና ፀሀፊ ማርክ ሩተ እየጨመረ በመጣው የዩናይትድ ስቴትስ ግሪንላንድን የመጠቅለል ፍላጎት ላይ ለመነጋገር ሁለቱ ሀገራት ስምምነት ላይ እንዲደርሱ አሳስበዋል። ይሁንና የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜተ ፍሬድሪክሰን በበኩላቸው ግሪንላንድ «ለሽያጭ እንደማትቀርብ» ኮፕንሀገን ግልጽ አድርጋለች ብለዋል።

የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት በጀት 2.34 ትሪሊየን ብር በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀደቀ የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትናንቱ 30ኛው መደበኛ ጉባኤው ለፌደራል መንግስት የ
የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት በጀት 2.34 ትሪሊየን ብር በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀደቀ የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትናንቱ 30ኛው መደበኛ ጉባኤው ለፌደራል መንግስት የ2019 በጀት 2.34 ትሪሊየን ብር አጽድቋል። በሙሉ ድምጽ ከጸደቀው በጀት 1.49 ትሪሊዮን ብሩ ከታክስ ገቢ የሚሰበሰብ ፣ ቀሪው 93.7 ቢሊዮን ብር ከልማት አጋሮች በሚገኝ ብድርና ድጋፍ እንዲሁም 320 ቢሊዮን ብር ከሀገር ውስጥ በሚገኝ ብድር የሚሸፈን መሆኑ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢን ጠቅሶ ምክር ቤቱ በድረ ገጽ ላይ አስታውቋል። እንደ ሰብሳቢው በበጀት ድልድሉ 30 በመቶው ለትምህርት፣ ለመንገድ፣ ለጤና፣ ለግብርና፣ ለኃይል አቅርቦት ማስፋፊያ እና ለከተማ ልማት የተመደበ ነው። ለክልሎች የበጀት ድጋፍ ደግሞ 187.3 ቢሊዮን ብር ወይም 15.1 በመቶ ተመድቧል። ይህም በምክር ቤቱ ድረ ገጽ ላይ እንደተጠቀሰው ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ28.4 ቢሊዮን ብር ወይም 17.8 በመቶ ጭማሪ ያሳያል። ትናንት በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስለጸደቀው 2.34 ትሪሊየን ብር የፌዴራል መንግስት የ2019 ዓም በጀት ምን አስተያየት አላችሁ ? ጻፉልን ፎቶ፦ ከኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

ዳንጎቴኬንያ ላሙ ወደብ ነዳጅ ዘይት ማጣሪያ ሊገነቡ ነው ናይጀሪያዊው ቱጃር አሊኮ ዳንጎቴ በኬንያው የላሙ ወደብ በቀን 700 ሺህ በርሜል የሚያመርት የነዳጅ ማጣሪያ ለመገንባት ማቀዳቸው ተረጋገጠ ።
ዳንጎቴኬንያ ላሙ ወደብ ነዳጅ ዘይት ማጣሪያ ሊገነቡ ነው ናይጀሪያዊው ቱጃር አሊኮ ዳንጎቴ በኬንያው የላሙ ወደብ በቀን 700 ሺህ በርሜል የሚያመርት የነዳጅ ማጣሪያ ለመገንባት ማቀዳቸው ተረጋገጠ ። አንድ የዳንጎቴ ኩባንያ ከፍተኛ ባለሥልጣንን ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዛሬ እንደዘገበው እስካሁን በፕሮጀክቱ ላይ የነበረው ጥርጣሪ እልባት አግኝቷል። የድርጅቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ኤድዊን ዴቫኩማር እንደተናገሩት ከምሥራቅ አፍሪቃ ሀገራት ትልቅ ኤኮኖሚ በምታንቀሳቅሰው በኬንያ የሚገነባው የነዳጅ ማጣሪያ ወደ 30 ወራት የሚጠጋ ጊዜ ይወስዳል። የፕሮጀክቱን ቦታ በተመለከተ ከታንዛንያ እና ከኬንያዋ የሞምባሳ ወደብ ጋር በተያያዘ ሚስጥራዊና አወዛጋቢ ጉዳዮች እንደነበሩ ዴቫኩማር አስታውሰዋል። የዳንጎቴ ቢሮ ባወጣው መግለጫ ፕሮጀክቱ ወደ ላሙ ስለተዛወረበት ምክንያት ዳንጎቴ ከታንዛንያዋ ፕሬዝዳንት ሳምያ ሱሁሉ ሀሰን ጋር ተነጋግረው ነበር። ታንዛንያም በላሙ ውረታ እንድትሳተፍም ጋብዘውም ነበር።

የማክሰኞ ሰኔ 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና አርዕስተ ዜና *የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትን በተመለከተ የሚሻሻል እንጂ «ያለውን የሚያጎድል» ነገር ይፈጠራል ብለው እንደማያስቡ ተናገሩ ። «በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ለኢትዮጵያ ጠቃሚ ሐሳቦች ካሉ እንዳሉ ይቀጥላሉ ብዬ አስባለሁ» ሲሉም አክለዋል ። *የኬንያ ፖሊስ በመዲናይቱ ናይሮቢ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረውን «ሳባ ሳባ ዴይ» የተሰኘ የመታሰቢያ ሰልፍ ከለከለ ። የመታሰቢያ ሰልፉ እንዳይከናወን ለማከላከል በዋና ከተማዪቱ ፖሊስ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በከባዱ የታጠቁ የፀጥታ አካላትን ማሰማራቱን የፈረንሣይ ዜና አገልግሎት (AFP) ዘግቧል ። በጎረቤት ታንዛኒያም ዛሬ ሰልፉ እንዳይካሄድ በርካታ ፖሊሶች ተሰማርተው እንደነበር ተገልጧል ። *የፈረንሣይ ፕሬዚደንት ኤማኑዌል ማክሮ ሶሪያን በሚጎበኙበት ወቅት በተከሰቱ ሁለት ተከታታይ ፍንዳታዎች 18 ሰዎች ቆሰሉ ። ከቆሰሉት መካከል አራቱ ፖሊሶች መኾናቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ የዜና ምንጭ ዘግቧል ። ሙሉ ዜናውን በድምጽ እና በጽሑፍ በማገናኛው በኩል መከታተል ይቻላል https://pepurl.com/p/5Gj3f?maca=amh-RED-Telegram-dwcom