cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

DW Amharic

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

نمایش بیشتر
Advertising posts
42 066مشترکین
+3924 ساعت
+2807 روز
+1 41930 روز
آرشیو پست ها
نمایش همه...
የሚያዚያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. አርዕሰተ ዜና የአፍሪቃ ሕብረት «የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው» በሚል የተሰራጨው መረጃ «የተሳሳተ» ነው ሲል የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ አስታወቀ። የሶማሊያ መንግሥት ራሽን በመስረቅ የተጠረጠሩ በዩናይትድ ስቴትስ የሰለጠኑ የልዩ ኮማንዶ አባላት ማገዱንና ማሰሩን አስታወቀ። በጋዛ ሰርጥ አስቸኳይ ፣ቅድመ ሁኔታ የሌለውና ዘላቂ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ቻይና ጥሪ አቀረበች። የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ በጋዛ የተኩስ አቁም ላይ እንዲደረስ በጸጥታው ምክር ቤት የሚደረገውን ጥረት ማደናቀፍ እንዲቆምም ጠይቃለች። https://p.dw.com/p/4fEoL?maca=amh-RED-Telegram-dwcom 👉🏾 @dwamharicbot
نمایش همه...
የሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ዋና ዋናዎች፤ የሰላም ሚኒስትር ደኤታ የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ በዛሬ ዕለት የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው። ታንዛኒያ ውስጥ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የ155 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አስታወቁ። እስያ ውስጥ ደግሞ በሙቀት ማዕበል ሰዎች እየሞቱ ነው። ቱርክና ግሪክ ከሰሃራ በመጣ አቧራ አየራቸው ታፍኗል። ማዕከላዊ ናይጀሪያ ውስጥ ከባድ ዝናብ በአንድ እስር ቤት ላይ ጉዳት ማድረሱን ተከትሎ 120 የሚሆኑ እስረኞች ማምለጣቸው ተሰማ። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኢትዮጵያም ሆነ በመላው ዓለም የወባ በሽታ ስርጭት በእጅጉ መስፋፋቱ እና የሚያደርሰው ጉዳትም እየከፋ መምጣቱ ተገለጸ። ዝርዝሩን ያድምጡ ያንብቡ https://p.dw.com/p/4fC8H?maca=amh-RED-Telegram-dwcom 👉🏾 @dwamharicbot
نمایش همه...
የተላለፈበትን የሞት ቅጣት ይግባኝ መጠየቅ ይችላል ተብሏል። ከጎርጎርሳዊው 2022 እስከ 2023 በኢራን ለተፈጠረው አለመረጋጋት ቱማጂ ሳሌህ ተሳትፎ አለው ሲል የኢራን አብዮታዊ ፍርድ የሞት ቅጣት ማስተላለፉን ጠ,በቃው አሚር ራይሲያን ሻራቅ ለተሰኘው የሀገሪቱ ተነባቢ ጋዜጣ ነግረዋል። ሳሌህ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሳለች ከተገደለችው የ22 ዓመቷ ኩርድ ኢራናዊት ጉዳይ ጋር በተያያዘ በመላው ሀገሪቱ አመጽ ከተቀሰቀሰ በኋላ በጥቅምት ወር 2022 ነበር በቁጥጥር ስር የዋለው ። ራፐሩ በትጥቅ በታገዘ አመጽ እና መንግሥት ላይ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ማሰራጨት የሚለው ከቀረቡበት ክሶች መካከል አንዱ ነው። በወቅቱ የስድስት ዓመት እስራት ከተላለፈበት በኋላ ተለቆ የነበረው ሙዚቀኛው መንግስትን በሀሰት በመወንጀል ተከሶ በጥቂት ቀናት ውስጥ ዘብጥያ ወርዷል። በሙዚቀናው ላይ የሞት ፍርድ መተላለፉ ከተሰማ በኋላ በቀድሞው ትዊተር በአሁኑ አጠራሩ X «# ቱማጂ ይለቀቅ» የሚሉ መረጃዎች በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ። የራፐሩ ጠበቃም የሞት ቅጣቱ እንዳይፈጸም ይግባኝ እንደሚጠይቁ አስታዉቀዋል።
نمایش همه...
የተወደዳችሁ የዶቹ ቬለ አድማጮች እና ተከታታዮች የሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ስርጭታችን ከጥቂት ጊዜ በኋላ በፌስቡክ በቀጥታ ይደመጣል። ለዕለቱ ከተጠናቀሩ ዘገባዎች መካከል፤ በአሸባሪነት የተከሰሱ ሰዎች የፍርድ ቤት ዉሎ፣ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለታጣቂዎች ያቀረበዉ ጥሪና ተግዳሮቱ ፣ የዎላይታ ዞን መምህራን የስራ ማቆም እና የትምህር ቤቶች መዘጋት ፣ የንጹህ ውሃ አቅርቦት ችግር በድሬዳዋ እንዲሁም የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ሽታየን ማየር የአንድነት ጥሪ ይገኙበታል። ሳምንታዊው የባህል ዝግጅታችን ደግሞ የኢትዮጵያዊቷን ገጣሚ በሳኡዲ አረቢያ ያስተዋውቃል። የዓለም ዜናን ጨምሮ ሁሉንም በሰዓቱ ተገንታችሁ እንድትከታተሉን ከወዲሁ የአክብሮት ግብዣችን ይድረሳችሁ። የዶቼ ቬለን የየዕለቱን የዜና እና የዜና መጽሔት ጥንቅሮች ከዩቲዩብ ቻናላችን ማግኘት እንደምትችሉ እናስታውሳችሁ። ትክክለኛው የዶይቼ ቬለ የዩቲዩብ ቻናል ከታች ያለው ሲሆን እስከዛሬ ሰብስክራብ ያላደረጋችሁ በማድረግ በዩቲዩብም ቤተሰባችን ሁኑ። ለሌሎችም ማጋራት አትርሱ። እናመሰግናለን። https://www.youtube.com/@dwamharic/videos
نمایش همه...
በጦርነት ወስጥ ባሉ ህጻናት ላይ የሚከሰት የስነልቦና ቀውስ ከአስርት አመታት ለተሻገረ ጊዜ አብሮ ሊቆይ እንደሚችል የአንድ ዓለማቀፍ የግብረ ሰናይ ድርጅት ጥናት አመለከተ ። ጥናቱ እንደሚለው በጦርነቶች ከፍተኛ ተጋላጭ እና ተጎጂዎች ህጻናት ናቸው። 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በማክበር ላይ የሚገኘው SOS የህጻናት መንደር እንዳለው ከምንጊዜውም ይልቅ በጦርነት እና ግጭቶች ውስጥ የሚገኙ ህጻናት ትኩረት ሊያገኙ ይገባል። በኦስትሪያ የህክምና ተማሪዎች በጎርጎርሳውያኑ 1949 የተመሰረተው SOS የህጻናት መንደር የጋዛ ሰርጧን የራፋህ ከተማን ጨምሮ በመላው ዓለም ከ130 በላይ ሃገራት ውስጥ እየሰራ ይገኛል። መንደሩ ያኔ ሲመሰረት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠው የነበሩ ህጻናትን ማገዝ ዓላማው አድርጎ ነበር ያሉት የመንደሩ ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈጻሚ አንጄላ ሮዛሌስ በህጻናት ላይ እየደረሰ ነው ያሉትን በደል በማስታወስ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህም ቢሆን ዓለም «እዚያው በስፍራዋ ቀርታለች » ብለዋል። ህጻናት ቤተሰቦቻቸውን በሞት ማጣት ፣ የተመጣጠነ ምግብ አለማግኘት ፣ከትምህርታቸው መስተጓጎልን ጨምሮ የሚደርሱባቸው በደሎች ለዓመታት ከአዕምሯቸው ሊፋቁ የማይችሉ መጥፎ ጠባሳዎችን ጥሎባቸው እንደሚያልፍ ነው የተመላከተው። ዩክሬን ሱዳን እና ሄይቲን ጨምሮ ግጭት ጦርነቶች ባሉባቸው ሃገራት የህጻናት መንደሮች ያሉት SOS ፤ህጻናትን ተጋላች የሚያደርገው ግጭት ጦርነት ከመቀዛቀዝ ይልቅ እየተባባሰ መሄዱ ያሳስበኛልም ብሏል።
نمایش همه...
በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ ተከሳሾች የፍርድ ቤት ዉሎ አራት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን ጨምሮ በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ በሽብር ወንጀል ክስ ከቀረበባቸው 51 ተከሳሾች መካከል 23ቱ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። የዛሬው ችሎት "ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾች ላይ የመሠረተውን ክስ እንዲያሻሻል እና ያልቀረቡ ተከሳሾች ላይ በጋዜጣ የተደረገውን ጥሪ ውጤት ይዞ እንዲቀርብ" የተሰጠውን ትእዛዝ ለማድመጥ የተሰየመ ነበር። ተከሰሾች "በክሳችን ውስጥ የተገለፀውን የሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት ጉዳት በስም ዝርዝር" በመግለጽ ዐቃቤ ሕግ ያቅርብ" በሚል ያቀረቡት ጥያቄ "ምስክሮችን ለጉዳት የሚዳርግ ነው" በሚል ዐቃቤ ሕግ አቤቱታ ማቅረቡን የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ ዘግቧል። ግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት ይህንን እና ችሎት ያልቀረቡ በጋዜጣ ጥሪ የተደረገላቸው ተከሳሾችን ጉዳይ ለማድመጥና ትእዛዝ ለመስጠት ለግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ . ም ቀጠሮ ሰጥቷል።
نمایش همه...
... በመላው ዓለም በበሽታው ከተጠቁት ውስጥ 70 በመቶ በ12 ሃገራት ውስጥ መከሰቱን ያመለከተው መረጃው ህንድን አንዷ አድርጓታል። የተቀሩት 11 ሃገራት አፍሪካ ውስጥ ያሉ ሃገራት ናቸው ። በ2022 አፍሪካ ውስጥ በወባ ምክንያት ከተከሰተው 580 ሺ ሞት ውስጥ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች በሆኑ ህጻናት ላይ የተከሰተው ሞት ከ80 በመቶ በላይ ይሸፍናል። የወባ በሽታን ለመከላከል የተደረገው ትግል ከፍተኛ የበሽታው ስርጭት ባለባቸው አካባቢዎች መሻሻል ማሳየቱን ዘገባዎች ያመለክታሉ ። የበሽታው መመርመሪያ መሳሪያዎች ፤ የክትባት ስርጭት እና ጸረ ወባ የአልጋ አጎበር ስርጭት መጨመር በሽታውን ለመከላከል ማገዙም ነው የተገለጠው ። ነገር ግን ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በዓለምአቀፍ ደረጃ ተከስቶ የነበረው የኮሮና ወረርሽኝ ያስከተለው የእንቅስቃሴ መስተጓጎል የወባ በሽታ ስርጭትን ለመግታት ይደረጉ የነበሩ ጥረቶችን አዳክሞታል ነው የተባለው። የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተለው መዘዝ ደግሞ ሌላ አሳሳቢ ችግር ይዞ መጥቷል። ከአሁን ቀደም ወባ ደርሶባቸው በማያውቅ በአፍሪካ ትልቁ ተራራ ኪሊማንጃሮን ጨምሮ በምስራቃዊ ኢትዮጵያ ተራራማ አካባቢዎች ጭምር መታየቱን ዘገባው ጠቁሟል። አዲሱን ክስተት መንግስታት እና ዓለማቀፍ ድርጅቶች በአንክሮ እንዲመለከቱት እና የጥንቃቄ እርምጃዎች እንዲወስዱም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
نمایش همه...
ዛሬ የዓለም የወባ ቀን ነው፤ በዓለም የወባ ቀን የአየር ንብረት ለውጥ ከአሁን ቀደም ወባ ድርሽ ብሎ በማያውቅባቸው አካባቢዎች ጭምር እንዲከሰት ማድረጉ ተሰምቷል። ባለፈው የጎርጎርሳውያኑ 2023 ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በአካባቢው ሊተላለፍ የሚችል ወባ መከሰቱን ተከትሎ የአየር ንብረት ለውጥ ከአንዳንድ አካባቢዎች የጠፉ በሽታዎች ጭምር ዳግም እንዲቀሰቀሱ አልያም እንዲሰራጩ ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ተዘግቧል። አፍሪቃ ውስጥ በከፍተኛ ገዳይነቱ የሚጠቀሰው የወባ በሽታ አሁንም ድረስ ለሚሊዮኖች በበኅታው መጠቃት አልያም ህልፈት መዳረግ ምክንያት መሆኑ መቀጠሉ ዕለቱ ሲዘከር የወጣ መረጃ አመልክቷል። በጎርጎርሳውያኑ 2019 በመላው ዓለም በ85 ሃገራት ውስጥ ከነበሩት 233 ሚሊዮን የወባ በሽታ ተጠቂዎች ቁጥር በ2022 ወደ 249 ሚሊዮን ማደጉን የዓለም ጤና ስርጅት መረጃ ያመለክታል። በወባ በሽታ የሚፈጠረውን የሞት መጠን ደግሞ በተመሳሳይ ዓመት ከነበረው 576 ሺ ወደ 608 ሺ አድጓል።...
نمایش همه...
በ59 ሃገራት የሚገኙ ከ282 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለከፋ ረሃብ መጋለጣቸውን የመንግስታት ድርጅት ሪፖርት አመለከተ ። የዓለማቀፉ ድርጅት ሪፖርት እንዳለው በአስከፊ ጦርነት ውስጥ የምትገኘው የጋዛ ሰርጥ በርካታ ቁጥር ያለው ተጋላጮችን በመያዝ ትመራለች። ከጎርጎርሳውያኑ 2022 ወዲህ 24 ሚሊዮን ተጨማሪ ሰዎች ለከፋ የምግብ እጥረት እና ለረሃብ መጋለጣቸውን ያመለከተው መረጃው ከጋዛ ጦርነት በተጨማሪ የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ሚሊዮኖች እርዳታ ጠባቂ አልያም በረሃብ አፋፍ ላይ ያሉ ናቸው ብሏል። በየዓለም የምግብ እርሻ ፕሮግራም ሪፖርት እንደሚያሳየው በአምስት ሃገራት ውስጥ የሚገኙ እና ቁጥራቸው ከ705 ሺ በላይ የሆኑ ሰዎች ደረጃ አምስት ወይም ለከፋ ረሃብ የተጋለጡ ናቸው ። ከእነዚህ ውስጥ 80 በመቶውን ቁጥር የሚሸፍነው በጋዛው ጦርነት አስከፊውን ጊዜ በማሳለፍ ላይ የሚገኙት ፍልስጥኤማውያን ናቸው ። ደቡብ ሱዳን ፣ ቡርኪና ፋሶ ፣ ሶማሊያ እና ማሊ እያንዳንዳቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ለረሃብ የተጋለጡ ዜጎች እና ስደተኞች በመያዝ ይከተላሉ። በሀገራቱ እና በአካባቢያቸው እየተደረጉ ያሉ ግጭቶች እና ጦርነቶች እስካልቆሙ ድረስ ችግሩ እየከፋ ሊሄድ እንደሚችል ዓለማቀፉ ድርጅት አሳስቧል። ከዚህ በተጨማሪ በያዝነው የጎርጎርሳውያኑ 2024 መጀመሪያ ላይ ኤል ኒኖ ያስከተለው የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰበት ወቅት እንደነበር ያስታወሰው ድርጅቱ የጎርፍ መጥለቅለቅን ጨምሮ በአንዳንድ የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት የዝናብ እጥረትን በማስከተል ችግሩን ከድጡ ወደ ማጡ እንዳያደርገው ያሰጋኛል ብሏል። መንግስታት እና ለጋሾች በረሃብ ምክንያት «የጅምላ የሰውን ልጅ ውድቀት ለመታደግ» ርብርብ እንዲደረግ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ ጥሪ አቅርበዋል።
نمایش همه...
በመዲናይቱ አዲስ አበባም ሆነ በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል ባሉ ትልል ከተሞች የሚገነቡ ህንጻዎች በቁጥርም ሆነ በመጠን እጅጉን እየጨመሩ መምጣታቸው ይታያል። በሀገሪቱ ለመኖሪያም ሆነ ለተለያዩ ግልጋሎቶች የሚውሉ የህንጻ ግንባታዎች ከምንግዜውም ይልቅ እየጨመሩ መምጣታቸውን ተከትሎ ከግንባታ እና ተያያዝ እንeቅስቃሴዎች ጋር ተያይዞ በሚከሰቱ የደህንነት ችግሮች የበርካታ ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ እና የንብረት ውድመት ሲከተልም ይታያል ፤ ይሰማል። ከሰሞኑ እንኳ አዲስ አበባ ውስጥ ለግንባታ የተከማቸ አፈርና ድንጋይ አንድ ቤት ላይ ተደርምሶ የሁለት ቤተሰብ አባላት የሆኑ የሰባት ሰዎችን ህይወት ነጥቋል። የህንጻ ግንባታ ጥራታቸውን ባለመጠበቅ የሚገጥሙ መደረመስን ጨምሮ ለበርካታ ሰዎች ህልፈት እና የንብረት ውድመት ምክንያት የሆኑ ጉዳዮች በተለያዩ ጊዜያት ተዘግበዋል። ከህንጻ ግንባታ ጋር ተያይዘው ለሚከሰቱ አደጋዎች በግንባታ ወቅት የሚደርስ አደጋን ለመከላከል የወጡ ህጎች አለመተግበራቸው በምክንያትነት ከሚቀርቡ ጉዳዮች አንዱ ሲሆን ግንባታዎችን በርካሽ ግብአት እና የሰው ኃይል ለመገንባት የሚደረጉ ጥረቶች ደግሞ ደረጃቸውን የጠበቁ ህንጻዎች እንዳይገነቡ ከማድረግ አልፎ ለከፋ የሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራም ሲዳርግ እየታየ ነው። አሁን አሁን ደግሞ በመንግስትም ይሁን በግል በአጠቃላይ ሀገሪቱ የግንባታ ፍላጎት እጅጉን እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ በመስኩ ተገቢው ክትትል እና ቁጥጥር ካልተደረገ ችግሩ አሳሳቢ ሆኖ እንደሚቀጥል መገመት አያዳግትም ። ለመሆኑ በየአካባቢያችሁ የሚከናወኑ ግንባታዎች ምን ያህል ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው ? የግንባታ ደህንነት ባለመጠበቁ የገጠማችሁ ችግር ይኖር ይሆን ? ዘላቂ መፍትሄውስ ምን ይሁን ትላላችሁ ፤ ሃሳባችሁን አካፍሉን ፤ ተወያዩበትም።
نمایش همه...
-አዲስ አበባ ዉስጥ የሁለት ቤተሰብ አባላት በሚኖሩበት ቤት ላይ ዛሬ ማለዳ የተናደ ድንጋይና አፈር 7 ሰዎች ገደለ።የከተማይቱ ባለስልጣናትና የሟች ጎረቤቶች እንዳሉት የድጋይና አፈሩ ናዳ ከፍተኛ በመሆኑ ሰዎችን ማዳን አልተቻለም። -ኬንያን ያጥለቀለቀዉ ጎርፍ የርዕሰ ከተማ ናይሮቢ አዉራ መንገዶችን የደራሽ ወንዝ መዉረጃ አድርጓቸዉ አረፈደ።ጎርፍ ሰሞኑን ኬንያ ዉስጥ 32፣ ታንዛኒ 58 ሰዎች ሲገድል ቡሩንዲ ዉስጥ ከ100 ሺሕ በላይ ሕዝብ አፈናቅሏል። -ዓለም ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ፍፃሜ ወዲሕ የምትመራበት ሕግና ሥርዓት ከጥፋት አፋፍ ላይ መድረሱን አምንስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት እንደሚለዉ በመላዉ ዓለም የሚፈፀመዉ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየከፋ፤ ጥሰቱን ለማስቆም የሚደረገዉ ጥረት እየተዳከመ ነዉ። https://p.dw.com/p/4f9Lk?maca=amh-RED-Telegram-dwcom @dwamharicbot
نمایش همه...
የፕላስቲክ ቆሻሻን ወደ ጥበብ የለወጠው የናይጀሪያ ቤተመዘክር/ሙዚየም/
نمایش همه...
የተወደዳችሁ የዶቹ ቬለ አድማጮች እና ተከታታዮች የሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ስርጭታችን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በፌስቡክ በቀጥታ ይደመጣል። ለዕለቱ ከተጠናቀሩ ዘገባዎች መካከል፤ በትግራይ እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በሚገኙ ከተሞች በተነሳው ግጭት ከተፈናቀሉት መካከል በዋጃ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ወገኖች ስለሚገኙበት ሁኔታ፤ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ለመዋሀድ ንግግር ጀመረ ስለመባሉ የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት የሰላም ጥሪ ተስፋው እና ስጋቱ ፣ በአሜሪካን የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች፣ በትግራዩ ጦርነት ለተጎዱ የእርዳታ ማሰባሰቢያ መርኅ ግብር ይገኙበታል። ኢትዮጵያ የቡና መገኛ ሀገር መሆኗን ስላረጋገጠው አዲስ የዘረመል ጥናትም የሚያስቃኝ ጥንቅር አለን። የዓለም ዜናን ጨምሮ ሁሉንም በሰዓቱ ተገንታችሁ እንድትከታተሉን ከወዲሁ የአክብሮት ግብዣችን ይድረሳችሁ። የዶቼ ቬለን የየዕለቱን የዜና እና የዜና መጽሔት ጥንቅሮች ከዩቲዩብ ቻናላችን ማግኘት እንደምትችሉ እናስታውሳችሁ። ትክክለኛው የዶይቼ ቬለ የዩቲዩብ ቻናል ከታች ያለው ሲሆን እስከዛሬ ሰብስክራብ ያላደረጋችሁ በማድረግ በዩቲዩብም ቤተሰብ እንሁን። ለሌሎችም ማጋራት አትርሱ። እናመሰግናለን። https://www.youtube.com/@dwamharic/videos
نمایش همه...
... ለልማት በሚለው እቅድም ከአራት ኪሎ ጥይት ቤት ጀምሮ እስከ ፒያሳ ድረስ ነዋሪዎቹ እንደሚነሱ ተነግሯቸዋል ነው ያሉት። በተለይ በቀበሌ ቤት ነዋሪዎች ቤቶች እየተሰጣቸው ቤቶቹ እየፈረሱ እንደሆነም አመልክተዋል። የእሳቸውን ጨምሮም ከራስ አምባ ሆቴል ፊት ለፊት በታችኛው በኩል ያሉ አካባቢዎች የግል ቤቶች ግምትና ልዋጭ መሬት ለማዘጋጀት በሚል እስካሁን እንዳልፈረሱም ተናግረዋል። በዚህ መሀልም ላልተወሰነ ጊዜ በሚል ፈረሳው መቆሙን፤ ከመንግሥት አካላት ጋር በተደረገው ውይይትም ተማሪዎች የዚህን ወቅት ትምህርታቸውን እስኪያጠናቅቁ በሚል ለጊዜው ማፍረሱ እንደቆመ እንደተነገረም ነው ለዶቼ ቬለ የገለጹት። ሆኖም ግን ነዋሪዎች ከዛሬ ነገ ሊነሱ እንደሚችሉ በመስጋት ዕቃቸውን ሸክፈው በመጠባበቅ ላይ እንዳሉም አመልክተዋል። በተመሳሳይ በሰሜን ማዘጋጃና በሰሜን ሆቴን አካባቢ ነዋሪዎች እንደሚነሱ እንደተነገራቸው ለመረጃው ቅርብ እንደሆኑ የገለጹ የአካባቢው ነዋሪ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። እንደ መረጃ ምንጩ፤ ከፋሲል ትምህርት ቤት ጀርባ፣ በሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ እስከ ቀለበት መንገድ ድረስ ነዋሪዎች አካባቢው ፈራሽ መሆኑ እንደተነገራቸውም መረጃ እንዳላቸው ገልጸዋል። የቀድሞ ሰፈሮች መፈራረስ የነዋሪዎቹን ማኅበራዊ ግንኙነትና መስተጋብር ክፉኛ እንደጎዳው የሚናገሩ እንዳሉ ሁሉ ልማቱ ውሎ አድሮ ለሁሉም የሚጠቅም ሊሆን እንደሚችል የሚሞግቱ አሉ። እርስዎስ ምን ይላሉ?
نمایش همه...
በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች «ለልማት» በሚል ቤቶችን የማፍረሱና ነዋሪዎችንም የማንሳቱ ሥራ ቀጥሏል። «የኮሪደር ልማት» በተሰኘው ፕሮጀክት ከፒያሳ አንስቶ እስከ የካ ሾላ አካባቢ ድረስ እንደሚያካልል ያመለከቱት አንድ የከተማዋ ነዋሪ የእሳቸውን ጨምሮ የሚፈርሱ ቤቶች ለባለቤቶቹ እንደተነገራቸው ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። ይፈርሳል ተብሎ የፈረሳው ሥራ የተጀመረው ከፒያሳ መብራት ኃይል አንስቶ እስከ የካ ሾላ ገበያ ድረስ የሚያካልል መሆኑን የገለጹት የመረጃ ምንጩ ከሳምንታት በፊት በተለምዶ ሺህ ሰማንያ በመባል በሚታወቀው አካባቢ ነዋሪ እንደነበሩ ነው የነገሩን። አሁን አካባቢያቸው የብስክሌት እና የእግረኛ መሄጃን ጨምሮ መንገድ ለማስፋት በሚል ቤታቸው እንደሚፈርስ ስለተነገራቸው ለቅቀው ወደ ሠኀሊተ ምሕረት አካባቢ ተከራይተው ለመኖር መገደዳቸውንም ገልጸዋል። በዚሁ በኮሪደር ልማት በተባለው ፕሮጀክትም የቤቶች ፈረሳ መጀመሩን፤ የራስ አምባ ሆቴልን ጨምሮም እስከ ድልድዩ ድረስ አጥራቸው የፈረሰና የሚፈርስ ቤቶች መኖራቸውንም ዘርዝረዋል። ...
نمایش همه...
... ሌላኛው የአላማጣ ከተማ ተፈናቃይ መሆናቸውን ለዶቼ ቬለ የተናገሩት ሚሊየን ኪሮስ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪም ቤት ንብረቱን ትቶ የተሰደደው ገሚሱ ቆቦ ከተማ፤ ቀሪው ደግሞ ዋጃ መጠለያ ውስጥ ተበትኖ ይገኛል ነው ያሉት። ኅብረተሰቡ ለመፈናቀል የተዳረገውም አካባቢያቸው በህወሃት ታጣቂዎች በመከበቡ ዝርፊያ፤ ድብደባና ግድያም ስላለ ለሕይወታቸው በመስጋት መሆኑንም ተናግረዋል። እሳቸውም እንዲሁ ከተወሰነ እርዳታ በቀር የተፈናቀለው ኅብረተሰብ ያገኘው ሰብአዊ እርዳታ አለመኖሩን ነው ያመለከቱት። ካለፉት ሁለት ዓመታት አንስቶ እስከ አሁን ግጭቱ እስከተከሰተበት ጊዜ ድረስ የአላማጣ ከንቲባ ሆነው የቆዩት የራያ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኃይሉ አበራ፤ ኅብረተሰቡ ከስድስት ወረዳዎች መፈናቀሉን ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። ለተፈናቃዩ ኅብረተሰብ እህል ማቅረብ ባለመቻሉ እራሱ የከተማው አስተዳደር ለተወሰኑ ቀናት ዳቦ እየገዛ ለመመገብ መሞከሩን ሆኖም ከአቅም በላይ እንደሆነ ነው የተናገሩት። የተመድ ሁኔታውን አስመልክቶ ባወጣው ዘገባ በሺህዎች የሚቆጠሩት ሴቶች እና ሕጻናትን ጨምሮ ለተፈናቀለው ኅብረተሰብ መጠነ ሰፊ የሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልግ አመልክቷል።
نمایش همه...
በሰሜን ኢትዮጵያ በአወዛጋቢ አካባቢዎች በተከሰተው ግጭት የተፈናቀሉት ወገኖች ከ50 ሺህ በላይ መድረሳቸውን የተመድ አመለከተ። በአላማጣ ከተማ፣ በራያ አላማጣ፣ ዛታ እና ኦፍላ አካባቢ ከሚያዝያ አምስት እና ስድስት ጀምሮ በተከሰተው ግጭት ምክንያት ነዋሪዎቹ አካባቢያቸውን ጥለው ለመፈናቀል መዳረጋቸውን ነው ድርጅቱ ይፋ ባደረገው መረጃ ያስታወቀው። ዶቼ ቬለ ካነጋገራቸው ከእነዚህ ወገኖች አንዷ ከአላማጣ ከተማ ተፈናቅለው ዋጃ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙት እናት፤ አራት ልጆቻቸውን እና እህታቸውን ይዘው መሰደዳቸውን ተናግረዋል። እንደእሳቸው አገላለጽም «ተኩስ ሳይሰማ የህወሃት ታጣቂዎች ከሚኖሩበት አንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በመድረሳቸው» ምንም ነገር ሳይዙ ቤት ንብረታቸውን ጥለው በእግር ለመሰደድ ተዳርገዋል። እሳቸውም ሆኑ ሌሎች ተፈናቃዮች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተሰደው መጠለያ ውስጥ ቢሰባሰቡም እስካሁን ያገኙት የምግብም ሆነ አልባሳት እርዳታ እንደሌለም አመልክተዋል። ...
نمایش همه...
የኬንያ የተለያዩ ግዛቶች ውስጥ የጎርፍ መጥለቅለቅ እንቅስቃሴዎችን እንደገደበ እየተነገረ ነው። በዋና ከተማ ናይሮቢ ጎዳናዎች በጎርፍ በመዋጣቸው የኤኮኖሚ መናኸሪያ የሆነችውን ከተማ የአስቸኳይ ጊዜ የአደጋ ቀጣና እንዳስመሰላት የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። የመሠረተ ልማቶች መቋረጥ፤ የነዋሪዎች መፈናቀልና የንብረት ውድመት ከባድ የኤኮኖሚ ኪሳራ እንዳስከተለ ነው ነዋሪዎች በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ባጋሯቸው ቪዲዮና ፎቶዎች አማካኝነት የገለጹት። የኬንያ ቀይ መስቀል ይፋ ባደረገው መሠረት እስካሁን በሀገሪቱ በጎርፍ አደጋው ምክንያት የ38 ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል። ከ11 ሺህ በላይ ሰዎችም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። የኬንያ ቀይ መስቀል በመላ ሀገሪቱ ከጎርፍ አደጋ 180 ሰዎችን ማትረፍ መቻሉንም አስታውቋል። የድርጅቱ ሀላፊ ቬናንት ናዲጊላ፤ ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ የወረደው ዝናብ ኬንያ ውስጥ መጠለያን ጨምሮ የሰብአዊ እርዳታ ፈላጊዎችን እየፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል። የኬንያ መንግሥት ከባዱን ዝናብ ተከትሎ የጎርፍ አደጋ ማስጠንቀቂያ አውጇል።
نمایش همه...