cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

Ethiopian Enterprise Developmen (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

Show more
Advertising posts
5 483
Subscribers
+2124 hours
+1837 days
+73730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
አዲስ ዘመን በዚህ ሳምንት
Show all...
👍 7
ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚገኙ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚደገፉበት ፕሮግራም በአውሮፓ ህብረትና አጋሮቹ ይፋ ተደረገ .............. EED ግንቦት 7/2016ዓ.ም የአውሮፓ ህብረት እና አጋሮቹ ግጭት ተከስቶባቸው አካባቢዎችን ኢኮኖሚ ወደነበረበት ለመመለስ እንዲሁም አነስተኛ እና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን መልሶ ማቋቋም የሚያሰችላቸውን ፕሮግራም ይፋ አድርገዋል። ፕሮግራሙ በሰሜን ኢትዮጵያ ከግጭት በኋላ ያሉ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን በተሻለ የፋይናንስ አቅርቦት ለመደገፍ ዓላማ ያደረገ ነው፡፡ ይህም በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸውን አምራች ኢንተርፕራይዞችና በአግሮፕሮሰሲንግ ዘርፍ ላይ የተሰማሩትን በመደገፍ ወደ ምርትና ምርታማነትን ለመመለሰ ያለመ ነው፡፡ ድጋፉ የአውሮፓ ህብረት ፣ ኔዘርላንድስ እና ጀርመን ቀጣይነት ባለው መልኩ ወሳኝ በሆኑ ዘርፎች እያደረጉ ያሉትን አጋርነት ያሳያል ያሉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን ሙሀመድ ድጋፉ በተለይ በሴቶችና ወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ላይ ልዩ ጠቀሜታ አለው ሲሉ አክለዋል። በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ በበኩላቸው ግጭት በነበሩባቸው አካባቢዎች የሚገኙ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን መደገፍ ማህበራዊ ትስስርን በማጠናከር፣ ኢኮኖሚ እንዲያገግም በማድረግና ሰላምን በማስፈን ረገድ ትልቅ ሚና አለው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
Show all...
👍 11 2
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሚሰጠው የሊዝ ፋይናንስ የብድር አገልግሎት የሥልጠና ሰርተፍኬት እንደ ቅድመ ሁኔታ የሚታይበት አሠራሩን አሻሻለ፡፡ EED ግንቦት 06/2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጠውን ልዩ ስልጠና በሂደት በስራ ላይ ሆነው እንደሚወስዱ ታሳቢ ተደርጎ ወደ ስራ መግባት የሚቻልበት አሰራር መዘርጋቱን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው አስታወቁ። ፕሬዝደንቱ የአነስተኛ እና መካከለኛ የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾችን የግንዛቤ አድማስ ለማስፋት ባንኩ ሥልጠናዎችን በማመቻቸት እና በቀጥታ እንዲሳተፉ በማድረግ በርካታ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሠው ይህ አሰራር እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህ በፊት በአራተኛ ዙር ባንኩ የሚሰጠውን ሥልጠና ለመውሰድ ተመዝግበው በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ስልጠና ያልወሰዱ እና ስልጠናውን ለመውሰድ ምዝገባ ያላከናወኑ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ባንኩ በአጭር ጊዜ ስልጠናውን እንዲሰጣቸው ወይም በልዩ ሁኔታ የሚስተናገዱበት ሁኔታ እንዲመቻችላቸው በተደጋጋሚ ለዋናው መ/ቤት፣ ለዲስትሪክቶችና  ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የቀረቡትን ጥያቄዎች ተቀብሎ ምላሽ መስጠት በማስፈለጉ ማሻሻያውን ማድረግ ማስፈለጉን ነው ዶ/ር ዮሐንስ የገለፁት፡፡ በመሆኑም ባንኩ አሁን ባለው የሊዝ ፋይናንሲንግ አሠራር ቅድመ-ሁኔታ መሰረት ስልጠና ባለመውሰዳቸው ምክንያት የካፒታል እቃ ዱቤ ግዢ ተጠቃሚ ያልሆኑትን ኢንተርፕራይዞች በልዩ ሁኔታ ማስተናገድ እንዲቻል ባንኩ በቀጣይ በሚያመቻቸው የሥልጠና መርሃ-ግብር የሚሰለጥኑ መሆኑ ታሳቢ ሆኖ፤ የማምረቻ ቦታ በግላቸው፣ ከመንግስት ወይም ከግል በኪራይ ስለማግኘታቸው ማስረጃ እንዲያቀርቡ በማድረግ እንዲሁም የተሟላ መሰረተ ልማት እንደ አግባብነቱ የተሟላላቸው ስለመሆኑ፣ የሥራ ማስኬጃ 20% መዋጮ ማዋጣት የሚችሉ ስለመሆኑ፤ እንዲሁም ሌሎች በሊዝ ፋይናንሲንግ ቅድመ-ሁኔታዎችን ስለማሟላታቸው በአግባቡ ተረጋግጦ በመደበኛው የሊዝ ፋይናንሲንግና በቅርቡ በፀደቀው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት አማራጭ እንዲስተናገዱ መፈቀዱን ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።
Show all...
👍 10
"በበጀት አመቱ 9 ወራት ከ10.8 ሚልየን ቶን በላይ ግብዓት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ቀርቧል" የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እንደቀጠለ ነው EED ግንቦት 06/2016 ዓ.ም የኢንዱስትሪ ሚኒሰቴር ባለፉት 9 ወራት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ከ10.8 ሚልየን ቶን በላይ ግብዓትን ማቅረቡን የተቋሙ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን አባይ አስታወቁ። የሚኒስቴሩን የ9 ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት አቶ ጥላሁን በተጨማሪም በ9 ወራት ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት በተሠራው ስራ 1.96 ቢልየን ዶላር ዋጋ ያላቸውን ምርቶች በሀገር ውስጥ በማምረት መተካት መቻሉን ገልፀዋል። ስራ አስፈፃሚው በዚሁ ሪፖርታቸው ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ለስራ ማስኬጃና ለማሽነሪ ሊዝ አገልግሎት የዋለ 44.22 ቢልየን ብር ብድር መቅረቡን አስታውቀዋል። ከዚህ ውስጥም 4.9 ቢልየን ብሩ ለአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች የቀረበ ነው ብለዋል። አቶ ጥላሁን አያይዘውም የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም አጠቃቀም ከማሻሻል አንፃር በተከናወነ ሠፊ እንቅስቃሴ ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ማምረት አቅማችን 56.04 መድረሱን ገልፀው በዘርፍ ደረጃ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም 64.8 በመቶ ማድረስ ሲቻል የቆዳ 58.9፣ የማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ ኢንጂነሪንግ 40.1፣ የምግብና መጠጥ 62፣ እንዲሁም የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓት አምራቾች ደግሞ 54.3 በመቶ መድረሱን አብራርተዋል። #ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት
Show all...
👍 3
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልሰ አብዲሳ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት ‼️ በዓለም የሰላም ሎሬት ጠቅላይ ሚንስትራችን ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳብ አመንጪት ከተጀመረው የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ወዲህ የታየው የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ መነቃቃት አበረታች ነው። ክልላችንም የማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪውን እንደአንድ የትኩረት አቅጣጫ ወስዶና በዘርፉ ያሉትን ተግዳሮቶችና እድሎች ለይቶ መንቀሳቀሱ ለተጀመረው ንቅናቄ ጉልበት እንዲሆነው እያስቻለ ነው። የክልላችን የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የኢንቨስትመንት ንቅናቄ ግልፅ ስትራቴጂና ግብ ያለው ነው። በዚሁ መሠረት ብዙ የስራ እድሎችን በመፍጠር፣ የውጭ ምንዛሪ በማሳደግ፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ በመተካት (Import substitution)፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን (FDI) በመሳብ እንዲሁም የአገር ውስጥ አምራቾችን በማበረታታት ረገድ ሰፊ ስራ በመከወን ላይ እንገኛለን፤ አበረታች ውጤቶችም ተመዝግቧል። ንቅናቄው እንደክልል ካስገኛቸው ዋና ዋና ውጤቶች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው:- የተለያዩ የምክክር መድረኮችን በመፍጠር  የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ባለድርሻ አካላትን ቅንጅታዊ አሰራር ለማጠናከር ተችሏል። በዘርፉም የሚስተዋሉ የፋይናንስ፣ የመሠረተ ልማት፣ የግንባታና የምርት ግብአቶች መነቆዎች ትርጉም ባለው መልኩ መቀነስ ተችሏል። በውጤቱም ብዙ ኢንዱስትሪዎች በተነቃቃ አካኋን ወደ ምርት ተመልሰዋል። በዚህ የስኬት ጉዞ፣ ከምንም በላይ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ምርታማነት ጨምሯል፤ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ መተካት መተካት እየሰፋ ሄዷል። በሌላ በኩል ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የስራ እድል መፍጠር የተቻለ ሲሆን፣ ስለዘርፉ ያለው ግንዛቤም መሻሻል አሳይቷል። ይኸም የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ድርሻውን እንዲያሳድግ አስችሎታል። ይህ ማለት ግን የዘርፉ ጉዞ በሚፈለገው ፍጥነት ላይ ደርሰናል ማለት አይደለም። በመሆኑም በቀጣይ የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄን በመጠቀም በነባር የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ዙሪያ ያሚስተዋሉ ያልተቀረፉ ማነቆዎችን ለይተን ለመፍታት እንዲሁም ለአዳዲስ ኢንቨስትመንቶች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የምንሰራ ይሆናል። ግንቦት 6 ቀን 2016 ዓም
Show all...
👍 2
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተጠሪ ተቋማትና የክልል የዘርፉ አስፈፃሚዎች የ9 ወራት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተጀመረ EED ግንቦት 06/2016 ዓ.ም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልል የዘርፉ አስፈፃሚዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ በካይዘን የልህቀት ማዕከል በመካሄድ ላይ ነው። የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በመድረኩ  እንደገለፁት ባለፉት 9 ወራት በአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም አጠቃቀም፣ በአዳዲስ ኢንቨስትመንት ማስፋት፣ በኢንዱስትሪ ሽግግርና ጥናትና ምርምር ስራዎች ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የዘርፉ ሞተር በማድረግ ዘርፉን ለማነቃቃት በታቀደው መሠረት የተሠሩ ስራዎች ውጤታማ ነበሩ ያሉት ሚኒስትሩ በዚህም የአምራች ኢንዱስትሪ ዋነኛው ሀገራዊ የርብርብ ማዕከል እንዲሆን አስችሏል ሲሉ ገልፀዎል።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላሳየው የላቀ ተሳትፎ ሽልማት ተበረከተለት EED ግንቦት 06/2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በ2016 የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በአምራች ኢንተርፕራይዞች ተሳትፎና ስኬታማ እንቅስቃሴ ላሳየው የላቀ ተሳትፎ ሽልማት ተበረከተለት። በኤክስፖ መዝጊያ ላይ በተካሄደው የምስጋና መድረክ ሽልማቱን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ ከየኢፌድሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እጅ ተቀብለዋል። በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖው የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመረጡ 79 አምራች ኢንተርፕራይዞችና የማህበራትን ያሳተፈ ሲሆን አምራቾቹ ሀገራዊ የማምረት አቅምንና የምርት ስብጥርን በማሳየት ረገድ ከፍተኛ መነቃቃትን የፈጠሩ እንደነበሩ በርካታ የኤክስፖው ተሳታፊዎች መስክረዋል። #ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት
Show all...
👍 6
"የአምራች ኢንዱስትሪውን በመደገፍ ኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግሩን ዕውን ለማድረግ በመንግስት በኩሉ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክው ይቀጥላሉ" አቶ ተመስገን ጥሩነህ ======== EED ግንቦት 05/2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2016 ማጠቃላያ መርሃ ግብር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩንህ፣ ጥሪ ያተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፣ የአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተካሄደ። በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ የንቅናቄው ዋና አላማ የአምራች ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እንደሀገር ያሉንን የልማት እድሎች መጠቀምና የዘርፉን ተግዳሮቶች በቅንጅት መፍታት ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንዚህን አላማዎች በመያዝ በዘርፉ ኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት በመንግስት በኩል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል። ንቅናቄው መንግስት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት ለለውጡ ማሳያ ነው፤ ሆኖም እንደ ሀገር ኪለው የመልማት ፍላጎትና አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ማነቆ አኳያ ቀጣይነት ያለው ክትትልና ድጋፍ አስፈላጊ ነው ሲሉም አክልዋል።          የቀጣይ አቅጣጫዎችን በተመለከተም ንቅናቄውን በማጎልበት ሊያሳካቸው ያስቀመጣቸውን አላማዎች በአግባቡ በመተግበር ተጨባጭ ውጤቶችን ማረጋገጥ፣ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አምቅ አጠቃቀም ተግዳሮቶችን በዘላቂነት መፍታት፣ የአምራች ኢንዱሰትሪውን የሀገር ውስጥ የገበያ ድርሻ በተኪ ምርት ማሳደግ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል። #ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት
Show all...
👍 5