cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

Ethiopian Enterprise Developmen (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

Більше
Рекламні дописи
6 124
Підписники
+2224 години
+1747 днів
+82630 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

"90 በመቶ የሐገራችን አምራቾች በአነስተኛና መካከለኛ ደረጃ የሚገኙ እንደመሆናቸው ዘርፉን በልዩ ሁኔታ መደገፋችንን እንቀጥላለን" አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ፤ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ሚኒስቴር ዴኤታ EED ሠኔ 04/2016 ዓ.ም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ለውይይት ቀርቧል። በዉይይት መድረኩ ንግግር ያደረጉት የኢንደስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ እንደገለፁት በ2017 በጀት አመት ለአምራች አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል። አምራች ኢንተርፕራይዞች ሀገራችን ካሏት ኢንዱስትሪዎች 90 በመቶ ያህሉን ድርሻ ቢይዙም በመስሪያ ቦታ አቅርቦት፣ በፋይናንስ፣ በግብዓትና ገበያ ትስስር አሁንም ከፍተኛ ድጋፍ ይፈልጋሉ ያሉት ሚኒስትሩ ይህን ሁኔታ በውጤታማነት ለመቀየር በቀጣይ በጀት ዓመትም ዘርፉን በልዩ ሁኔታ መደገፋችንን እንቀጥላለን ብለዋል። በመድረኩ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የ2017 በጀት ዓመትን ዕቅድ ያቀረቡት የተቋሙ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማው ፈረደ እንደገለፁት በቀጣዩ በጀት አመት ከ5,300 በላይ አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች ይፈጠራሉ፤ 810 ኢንተርፕራይዞችም የደረጃ ሽግግር ያደርጋሉ። በቀጣዩ በጀት አመት በተጨማሪም ለ18,631 የዘርፉ አስፈፃሚዎች ስልጠና ለመስጠት መታቀዱን የገለፁት አቶ ግርማ 3.2 ቢልየን ብር ብድር ለስራ ማስኬጃ እንዲሁም 4.3 ቢልየን ብር ግምት ያለው ማሽነሪንም በካፒታል ዕቃ ሊዝ ፋይናንስ፤ በድምሩ ከ7.5 ቢልየን ብር ዘላይ በብድር ለማሠራጨት ታቅዷል ብለዋል። የፅ/ቤት ኃላፊው አያይዘውም በ2017 ከአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች 39.2 ሚልየን ዶላርን ከኤክስፖርት ለማግኘት መታቀዱን ገልጸዋል።
Показати все...
👍 9
"በ2017 በጀት ዓመት የማምረት አቅም አጠቃቀማችንን በማሻሻል 2.7 ቢልየን ብር ዋጋ ያላቸውን ምርቶች በሐገር ውስጥ እንተካለን" አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ EED ሠኔ 4/2016 ዓ.ም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማትና የክልል የዘርፉ አስፈፃሚዎች ጋር በመሆን ያዘጋጀውን የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ይፋ አደረገ። በአዳማ ከተማ የተካሄደውን የዕቅድ መግባቢያ መድረክ በንግግር የከፈቱት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አት ታረቀኝ ቡሉልታ እንደገለፁት የ2016 በጀት ዓመት በተለይም ከዋና ዋና እቅዶች አንፃር ጠንካራ አፈፃፀምና መነቃቃት የተፈጠረበት እንደነበር ጠቅሠው ይህንኑ ውጤታማነት በላቀ ደረጃ ለመፈፀም የሚያስችል የ2017 በጀት አመት እቅድ መዘጋጀቱን ገልፀዋል። በ2017 በጀት አመት የማምረት አቅም አጠቃቀማችንን ወደ67% ለማድረስ አቅደናል ያሉት ሚኒስትሩ የኤክስፖርት አቅማችንን አሟጦ በመጠቀምም 517 ሚልየን ዶላር ለማግኘት ታስቧል ብለዋል። ተኪ ምርትን ከማስፋት አንፃር 2.7 ቢልየን ብር ግምት ያላቸውን ምርቶች በሐገር ውስጥ ለመተካት መታቀዱን ገልፀዋል። አቶ ታረቀኝ በዚሁ ንግግራቸው የተዘጋጁ ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን ወደመሬት በማውረድ፣ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን በማስፋትና የብሔራዊ ስትሪንግ ኮሚቴውን አቅም በመጠቀም ዕቅዶችን በላቀ ተነሳሽነትና ውጤታማነት ለመፈፀም መታሠቡንም አብራርተዋል።
Показати все...
👍 7
የአምራች ኢንተርፕራይዝ ዘርፉን ለሚቀላቀሉና ስራቸውን ማስፋት ለሚፈልጉ አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚያግዙ 21 የቢዝነስ ሰነዶች ተዘጋጅተው ለክልልና ከተማ አስተዳደሮች ተሸጋገሩ EED ግንቦት 30/2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ለክልልና ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት በቢዝነስ ፕላን፣ ምርት ፕሮፋይልና ማሽን ስፔስፊኬሽን አዘገጃጃት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰልጠና ሰጠ። ተቋሙ ሀገር በቀል የሆኑ አምራች ኢንተርፕራይዞች እንዲበራከቱና አዳዲስ እንዲቋቋሙ በሚያደርገው ክትትልና ድጋፍ የቢዝነስ ዕቅድ፣ የምርት ፕሮፋይልና ማሽን ስፔስፍኬሽን አዘገጃጀት ላይ ውስንነቶች እንዳሉ በመረዳት ይህንን ለመቅርፍ ይረዳሉ ያላቸውን 21 የቢዝነስ ሰነዶችን አዘጋጅቶ ለሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደሮች እንደየነባሪዊ ሁኔታቸው አገልግሎት ላይ እንዲያውሉት አሸጋግሯል። የቢዝነስ ሰነዶቹ በአግሮ ፕሮሲንግ፣ ኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓት፣ ጌጣጌጥና ማዕድን፣ ብረታብረትና እንጨት እንዲሁም ቆዳና ጨርቃጨርቅ ዘርፎች ላይ ያተኮሩ ናቸው።
Показати все...
👍 5 2🔥 2
"እንደሀገር ያለውን ለአምራች ኢንተርፕራይዝ ልማት የተመቸ ሁኔታ በመጠቀም ሀገራዊ ኢኮኖሚን ለማሳደግና ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍልን ዕውን ለማድረግ መጠቀም ይገባናል" አቶ አብዱልፈታ የሱፍ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር EED ግንቦት 30/2016 ዓ.ም እንደሀገር ያለውን የአምራች ኢንተርፕራይዝ ልማት በተቀናጀና በወጥነት ለመደገፍ የሚያስችሉ ሠነዶች ተዘጋጅተው ለዘርፉ የክልልና አስተዳደር አስፈጻሚ አካላት ተሸጋገሩ። የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እንደገለፁት ሠነዶቹ በዋናነት በተለያዩ ክልሎችና አስተዳደሮች በሠነድ ዝግጅትና አፈፃፀም የሚታዩ ችግሮችን በመቅረፍ ወጥነት ያለውን አሠራር ለመዘርጋት የሚያስችሉ ናቸው። እንደአቶ አብዱልፈታ ገለፃ ሠነዶቹ የአዋጪነት ጥናትን፣ የምርት ፕሮጀክት ፕሮፋይልንና በማሽን ስፔሲፊኬሽን አዘገጃጀት ዙሪያ ያሉ የእውቀት ውስንነቶችንና የወጥነት ችግሮችን ለመፍታት ይረዳሉ። ሀገራችን ለአምራች ኢንተርፕራይዝ ልማት በገበያ፣ በተፈጥሮ ሀብትና በተቋማዊ አቅምና አደረጃጀት የተመቸ ሁኔታ ያላት እንደመሆኑ እነዚህን አቅሞች በተቀናጀ መልኩ በመጠቀም ሀገራዊ ኢኮኖሚን ለማሳደግና ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍልን ዕውን ለማድረግ መጠቀም ይገባናል ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ለዚህም ተቋማቸው አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል። በመድረኩ ከሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የዘርፉ አስፈፃሚዎች የተገኙ ሲሆን በሠነዶቹ ዙሪያም ስልጠና ተሠጥቷል።
Показати все...
👍 9
በአምራች ኢንተርፕራይዝ ልማቱ የሚከናወኑ ስራዎችን የሚዲያ አካላት መደገፍ እንዳለባቸው ተገለፀ EED ግንቦት 29/2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በአምራች ኢንተርፕራይዝ ልማት ዙሪያ ለሚዲያ አካላት እየሠጠ የሚገኘው ስልጠና እንደቀጠለ ነው። በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ የህ/ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸናፊ መለሠ በአምራች ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ የሚዲያ ሚና በሚል ርዕስ ለሚዲያ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል። አቶ አሸናፊ በገለፃቸው የሚዲያ አካላት በአምራች ዘርፉ ላይ ያሉ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በማሳየት፣ ዘርፉ በሀገራችን ለማደግ ያለውን ምቹ ሁኔታ በማስተዋወቅና የተሻለ ተሞክሮ ያላቸውን ጠንካራ ኢንተርፕራይዞችና ስራ ፈጣሪዎችን ልምድ በማስተዋወቅና በማስፋት ያላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። የአምራች ኢንተርፕራይዝ ልማት ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ግንባታ፣ ለማህበራዊ አኗኗር ወይቤ መሻሻልና ጤናማ የሐብት ክፍፍል ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው የገለፁት ስራ አስፈፃሚው ዘርፉ ላይ የሚሰራውን ስራ የሚዲያ አካላት በተጨባጭ መረጃ በማስደገፍ ማሳየት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የመጡ የቢዝነስ ጋዜጠኞች ተሳትፈዋል።
Показати все...
👍 5
የሚዲያ አካላት በዘርፉ ያለውን መልካም አጋጣሚ እና የመበልፀግ ፀጋ ለህብረተሰቡ የማሳወቅ ትልቅ ሀላፊነት እንዳለባቸው ተጠቆመ EED ግንቦት 29/ 2016 ዓ.ም በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች አለም አቀፍ ተሞክሮ እና በሀገራዊ የዘርፉ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ለሚዲያ ባለሙያዎች ስልጠና ተሠጠ፡፡ ስልጠናውን የሠጡት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዻውሎስ በርጋ እንዳብራሩት በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ያለው አለም አቀፍ ተሞክሮ ሲታይ 33 በመቶ  የሚሆነው የሀገር ውስጥ ገቢ ይሸፍናሉ፣ በአለም 20 በመቶ የሚሆነው የፈጠራ ሀሳብ የሚመነጨውም ከአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሲሆን በተጨማሪም አጠቃላይ በአለም ላይ ከሚደረጉ የንግድ ልውውጦች ውስጥ 90 በመቶ  በመያዝ በኢኮኖሚ ውስጥ ከተፈጠሩ የስራ እድሎች ለ50 በመቶ ለሚሆኑ ዜጎች ስራ መፍጠር የቻለ ዘርፍ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ በሀገራችን የአምራች ዘርፉን ለማበረታታት ልዩ ልዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ዻውሎስ ባለፉት 5 ዓመታት የዘርፉ ልማት በውጤታማ ስኬት ውስጥ እየተጓዘ ስለመገኘቱ አብራርተዋል። አቶ ጳውሎስ አያይዘውም በ10 አመቱ የልማት ዕቅድ በዘርፉ 62 ሺህ አዲስ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች በመፍጠር አሁን ካለው 30 በመቶ የሀገር ውስጥ የገበያ ድርሻ ወደ 60 በመቶ ማሳደግ፤ 2 ነጥብ 16 ሚሊየን አዳዲስ የስራ እድል መፍጠር ፤ 468 ሚሊየን ዶላር ከወጪ ንግድ ማግኘትና አሁን ያለውን 50 በመቶ አማካይ የማምረት አቅም አጠቃቀም ወደ85 ለማድረስ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል። አቶ ጳውሎስ አክለውም የሚዲያ አካላት በዘርፉ ያለውን መልካም አጋጣሚ እና የመበልፀግ ፀጋ ለህብረተሰቡ በማሳወቁ ረገድ ትልቅ ሀላፊነት እንዳለባቸው ገልፀዋል።
Показати все...
👍 7
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተደራሽነት ወሰኑን ለማስፋትና የተቀናጀ መረጃ ተደራሽ ለማድረግ የኮሙዩኒኬሽን ክላስተር ሟቋቋም እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ EED ግንቦት 29/2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ተልዕኮዎች፣ በአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ፣ የዘርፉ ዓለም አቀፉ ተሞክሮና በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዋና ዋና ተልዕኮዎች ዙሪያ ለሚዲያ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በአዳማ ከተማ እየተሰጠ ነው፡፡ በስልጠናው የተሳተፉት የሚዲያ ባለሙያዎች እንደተናገሩት በአምራች ዘርፍ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና ያሉ ምቹ ሁኔታዎች እንዲሁም ዓለም አቀፍ የዘርፉ ተሞክሮ ላይ ለሚዲያ አካላት ግንዛቤ መፈጠሩ የሚበረታታ መሆኑን ገልፀዋል። የአምራች ዘርፉን ለማነቃቃት የተጀመረው "የኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ በርካታ ውጤቶችን አስመዝግቧል ያሉት የሚዲያ ባለሙያዎች  የደተራሽነት ወሰኑን ከማስፉትና የተደራጀ መረጃ ወጥነት ባለው መልኩ ለዜጎች ተደራሽ ከማድረግ አንፃር የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ክላስተር ማቋቋም እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። የአገር ውስጥ አምራች ኢንተርፕራይዞችን  የሚያመርቷቸውን ምርቶች ከማስተዋወቅ አንፃር በኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በኩል ክፍተት እንዳለ የተናገሩት የሚዲያ ባለሙያዎች በተመሳሳይ መልኩ የሚዲያ ባለሙያዎች በዘርፉ ያሉ እንቅስቃሴዎችን በስፋት የዘገባ ሽፋን ከመስጠት አንጻር ውስንነት እንዳለ አመላክተዋል። ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችና ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግና ዘርፉን የሚመሩና የሚደግፉ አካላት የሚስተዋሉ ችግሮችንም ጥናትን መሰረት ባደረገ መልኩ መፍታት እንደሚጠበቅባቸው የሚዲያ ባለሙያዎች ተናግረዋል።    የተሰጠውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መነሻ በማድረግ የሚዲያ ባለሙያዎች የሀገር ውሰጥ አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚያመርቷቸውን ምርቶችና ያሉ ምቹ ሁኔታዎች በማስተዋወቅ  ባለሀብቶች የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን እንዲቀላቀሉ በቢዝነስ ዘገባቸው በስፋት መስራት እንደሚያስፈልግ ተገልጻል። የሀገርወሰጥ አምራቾች የማምረት አቅም ላይ ያሉ ዕውነታወች ለማህበረሰቡ ግንዛቤ በመፉጠር ዜጎች የሀገር ውስጥ ምርቶች የመግዛት ባህልን እንዲያጎለብቱ በማድረግ ሂደት ውስጥ የጋዜጠኞች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ በመድረኩ ተነስቷል። በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የመጡ ጋዜጠኞች ተሳትፈዋል።
Показати все...
👍 5👏 2
Перейти до архіву дописів