cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

Ethiopian Enterprise Developmen (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
5 884
مشترکین
+2524 ساعت
+2407 روز
+78530 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

نمایش همه...
👍 2
“የአፋር ክልል የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ሊዝ አክሲዮን ማሕበርን ለማቋቋም ያሳየው ተነሳሽነት ለክልሉ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዕድገት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው” አቶ አብዱልፈታ የሱፍ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋ/ ዳይሬክተር EED ግንቦት 21 2016 ዓ.ም በአፋር ክልል በም/ ርዕስ መስተዳደር የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ክቡር አቶ አሊ መሐመድ የሚመራ ቡድን ከኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከፍተኛ አመራሮች ጋር የሊዝ ፋይናንስ አክሲዮን ማሕበርን ለማቋቋም የሚያስችል ውይይት አደረገ። የካፒታል ዕቃ ሊዝ ፋይናንስ አክሲዮን ማሕበራት የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ያሉባቸውን የማሽነሪና የቴክኖሎጂ ችግር ለመቅረፍ በብድር መልክ ለማቅረብ የተቋቋሙ ሲሆን ይህም በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማነቱ በግልፅ የታየ ሆኗል፡፡ ነገር ግን አክሲዮን ማሕበራቱ በ4 ክልሎችና በ1 ከተማ አስተዳደር ብቻ የተቋቋሙ በመሆኑ ሁሉም ክልሎች በተመሳሳይ ደረጃ ከዘርፉ ተጠቃሚ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ የአፋር ክልልም ይህ አክሲዮን ማሕበር ካልተቋቋመባቸው ክልሎች አንዱ እንደመሆኑ ለአምራች ኢንተርፕራይዞች በተሟላ መልኩ የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ ተስኖት ቆቷል፡፡ ይህን ክፍተት የተረዳው ክልሉም በክልሉ ከፍተኛ ሃላፊዎች የሚመራ ቡድን አቋቁሞ በክልሎች ያለውን የአክሲዮን ማሕበራቱን አፈፃጸም ሲገመግምና ሲያጠና ቆይቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር አክሲዮን ማሕበሩን ለማቋቋም በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙርያ ለመምከር ቡድኑ በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ተገኝቶ ውይይት አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፉ በመድረኩ እንደተናገሩት በካፒታል ዕቃ ሊዝ ፋይናንስ ተጠቃሚ የሆኑ ክልሎችና አምራች ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ ስራ እየሰሩ እንደሆነ ጠቁመው በተመሳሳይ መልኩ የማይጠቀሙ ክልሎች ደግሞ ዝቅተኛ አፈፃፃም እንዳላቸው ም/ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል። አቶ አብዱልፈታ አክለውም መንግስት ለአምራች ኢንተርፕራይዞች የሚሰጠውን ድጋፎች በወጥነት በመስጠት በሁሉም ክልሎች ያሉ ኢንተርፕራይዞች ተቀራራቢ ውጤት እንዲያመጡ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሊዝ ፋይናንስ አቅራቢዎች ኢንተርፕራይዞችን እየወለዱ የሚያሳድጉ ተቋማት እንደመሆናቸው ከዚህ ቀደም ያልተቋቋሙባቸው ክልሎች እንዲያቋቁሙ ምክረሀሳብ በማቅረብና አስፈላጊውን ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን የተናገሩት ም/ ዋና ዳይሬክተሩ የአፋር ክልል የሊዝ ፋይናንስን ለማቋቋም ላሳዩት ተነሳሽነት አመስግነዋል። በክልሉም የሊዝ ፋይናንስ እንዲቋቋምና ያሉ አምራች ኢንተርፕራይዞች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የልማት መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደረጉ አቶ አብዱልፈታ ተናግረዋል።
نمایش همه...
👍 4🤷‍♂ 1 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
በአንድ ጊዜ ቻርጅ ለ1 አመት የሚያገለግል ድምፅ አልባ ጄኔሬተር የፈጠረው የወለጋው ፌዴሳ ሹማ ‹ ግንቦት 21/ 2016 ዓ.ም ፌዴሳ ሹማ ተወልዶ ያደገው በቄለም ወለጋ ሲሆን፣ በከተማው ውስጥ በኤሌክትሪክ ጥገና ሙያው ይታወቃል፡፡ ይህን የኤሌክትሪክ ጥገና ሥራውን የመብራት መጥፋት እና መቆራረጥ ብዙ ጊዜ አስተጓጉሎበታል። "ችግር ብልሃትን ይወልዳል" እንዲሉ ወጣቱ ሥራውን በተደጋጋሚ ላስተጓጎለበት ችግር መላ መዘየድ እንዳለበት አሰበ፤ አስቦም ወደ ተግባር ገባ። ከብዙ ጥረት በኋላ አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ እስከ አንድ ዓመት ድረስ አገልግሎት መስጠት የሚችል ቴክኖሎጂ እውን አደረገ። ወጣት ፌዴሳ ሹማ በኃይል አማራጭ ዘርፍ አብዮት ይፈጥራል ተብሎ የታመነበት መሣሪያ የፈጠራ ባለቤት ነው፡፡ ቴክኖሎጂው የመብራት አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ ለሞባይል፣ ለቴሌቭዥን፣ ለፍሪጅ እና የትኛውንም ዓይነት የኤሌክትሮኒክስ መጠቀሚያዎችን ቻርጅ የሚያደርግ፣ የሚያንቀሳቅስ እና በገመድ እና ገመድ አልባ ቴክኖሎጂ መጠቀም እንዲቻል ተደርጎ የተሠራ ነው። አንዴ የያዘውን ኃይል ደጋግሞ እያደሰ (recycling) ራሱን ቻርጅ ከማድረግ አልፎ ለረዥም ጊዜ ኃይል ማመንጨት የሚችለው ይህ ቴክኖሎጂ በሀገራችን ብቻ ሣይሆን ምን አልባትም በዓለማችን ላይ በኃይል አማራጭ ዘርፍ አብዮት መፍጠር እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል። ከ300 ዋት ጀምሮ እንደ ተጠቃሚው አቅም እና ፍላጎት የሚዘጋጀው ይህ ድምፅ አልባ ጄኔሬተር አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ነው ወጣቱ ያረጋገጠው።
نمایش همه...
2
አምራች ኢንተርፕራይዞች የሽግግር ስትራቴጂ ኢንተርፕራይዞች የደረጃ እድገትን መሰረት ያደረገ ሽግግር እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው EED ግንቦት 20 /2016 ዓ.ም (ባህርዳር) የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች የደረጃ ሽግግር ስትራቴጂ ላይ ለአማራ ክልል የዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡ ስልጠናውን የሰጡት በዘርፉ ዙሪያ  ልምድ ያላቸው አቶ ቤዛወርቅ ከተማ ስትራቴጂው የኢንተርፕራይዞችን እድገት መሰረት ያደረጉ ድጋፎችን በመስጠት ኢንተርፕራይዞች የደረጃ ሽግግር እንዲያደርጉ በማስቻል ኤክስፖርትን ማስፋትና ተኪ ምርትን ማበራከት የሚያስችል መሆኑን በገለፃቸው አብራርተዋል። ስትራቴጂው በዘርፉ የተሻለ ልምድ ያላቸውን የህንድ፣ የቬትናምና የኬንያ ሀገሮችን ተሞክሮ ያካተተ መሆኑን ያብራሩት አቶ ቤዛወርቅ እነዚህ ሀገራት የዘርፉን ልማት  በክላስተር ልማት፣ በፋይናንስ አቅርቦት፣ በሰለጠነ የሰው ሃይል አቅርቦትና በገበያ ትስስር ትኩረት ሰጥተው የሚደግፉና ሌሎች ማበረታቻዎችን የሚያቀርቡ መሆናቸውንም አመላክተዋል። ስትራቴጂው እንዲተገበር የዘርፉ አስፈፃሚ አካል አውቆና ተገንዝቦ በአግባቡ መተግበርና መምራት እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል። በዚህም በ10 ዓመቱ በዘርፉ የተያዘውን የ5 ሺህ ተወዳዳሪና ውጤታማ ኢንተርፕራይዞች ሽግግር ማሳካት የሚቻል መሆኑ በስልጠናው ግንዛቤ ተወስዷል። #ኢትዮጵያ_ታምርት   #እኛም_እንሸምት
نمایش همه...
👍 7 2👏 1
በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ልማት ፍኖተ ካርታ ላይ ለአማራ ክልል የዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ EED ግንቦት 19 /2016 ዓ.ም (ባህርዳር) የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ለአማራ ክልል የዘርፍ በአመራርና ባለሙያዎች በ10 ዓመቱ የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዝ ልማት ፍኖተ ካርታ ላይ ስልጠና ሰጠ፡፡ ስልጠናውን የሰጡት በዘርፉ ልምድ ያላቸው አቶ ቤዛወርቅ ከተማ የ 10 ዓመቱ የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ልማት ፍኖተ ካርታ አምራች ኢንተርፕራይዞችን በፋይናንስና በመሰረተ ልማት፣ በስልጠና፣ በገበያ ትስስርና መሰል ድጋፎች በመደገፍ ተወዳዳሪና ውጤታማ ኢንተርፕራይዞች እንዲፈጠሩና ዘርፉ ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ያለውን ድርሻ እንዲወጣ የሚያስችል መሆኑን በገለፃቸው አስረድተዋል። 10 አመቱ ፍኖተ ካርታ እንዲተገበር የዘርፉ አስፈፃሚና ድጋፍ ሰጪ አካላት ተቀናጅቶና ተቀራርቦ መስራትን ይጠይቃል ያሉት አቶ ቤዛወርቅ ፍኖተ ካርታው በቀጣይ 10 ዓመት 62 ሺህ አዲስ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን መፍጠር ፤ 2 ነጥብ 16 ሚሊየን አዳዲስ የስራ እድል መፍጠር ፤ 468 ሚሊየን ዶላር ከወጪ ንግድ ማግኘት ፤ 5 ሺህ ኢንተርፕራይዞችን የደረጃ ሽግግር እንዲደርጉ አሁን ያለውን 50 ፐርሰንት አማካይ የማምረት አቅም አጠቃቀም ወደ 85 ማድረስ የሚያስችል መሆኑንም አመላካተዋል። #ኢትዮጵያ_ታምርት ፣ #እኛም_እንሸምት
نمایش همه...
👍 6 2
ለአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች በሚሰጥ የመንግስት የድጋፍ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከቻይና የተቀመረ ምርጥ ተሞክሮን ለትግራይ የዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች በስልጠና ኢንዲስፋፋ አደረገ EED ግንቦት 19/2016  (መቐለ) ለሶስተኛ ቀን በቀጠለው ለትግራይ የዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች የሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና በውጤታማ የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርራይዞች ድጋፍ አሰጣጥ ዙሪያ ከቻይና የተቀመረ ምርጥ ተሞክሮን ለትግራይ የዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች ለማስፋት ስልጠና በመስጠት ቀጥሏል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አቅም ግንባታ ባለሙያ አቶ መኮንን ሞላ ስልጠናውን ሲሰጡ እንደገለፁት ቻይና በአለም ካሉ ሀገራት በኢኮኖሚዋ ሁለተኛ ደረጃ የያዘችው ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርቷ 60% የሚሆነው በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ምርት ነው፡፡ ይህም ዘርፉን ለመምራት የምትጠቀምበት ፖሊሲ ውጤታማ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ በቻይና የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማትን ከብሄራዊና ከማህበራዊ ስትራቴጂክ ልማት ጋር ተሰናስሎ ታቅዷል፡፡ በተጨማሪም ወደ ዘርፉ መቀላቀል ፍላጎት ላላቸው የግል ባለሀብቶች ብድር ያለ ወለድ በማመቻቸትና ሌሎች መሰረተልማቶችን በማመቻቸት መልካም የኢንቨስትመንት ከባቢን መፍጠር ችለዋል፡፡ ቻይና አንድ ምርት ለአንድ ከተማ የሚል ፖሊሲ ትከተላለች፡፡ ይህ ማለት እያንዳንዱ ከተማ ያለውን ፀጋ በመለየት ከገበያ ፣ከሰው ሀብት እና ከሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ጋር በማስተሳሰር ትኩረቱን በአንድ ምርት ላይ ብቻ  ያደረገ ከተማ መፍጠር ማለት ነው፡፡ አንድ ምርት ለአንድ ከተማ ፅንሰ-ሀሳብ ተመሳሳይ ምርት የሚያመርቱ ኢንተርፕራይዞች በአንድ ከተማ ተሰባስበው ስለሚገኙ ለምርት የሚያስፈልጋቸውን መሰረተ ልማትና ግብዓት አንድላይ ለማቅረብ ከማስቻሉም ባሻገር በምርት ሂደት ለሚያጋጥሙ ችግሮችን በቶሎ ለመቅረፍ ያስችላል፡፡ በዚህ ረገድ የቻይናዋ ጉዋንዢንግ በኬብል ምርት፣ ሻንጊዝ በሲልኪ(በሃር) ምርት እንዲሁም ይኢ-ዉ በጅምላ ንግድ የሚታወቁ ከተሞች ናቸው፡፡ ቻይና ለአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች የምትሰጠውን የብድር አቅርቦት የወለድ ምጣኔው በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ በተጨማሪም በየከተማው ብዙ ቅርንጫፍ ያላቸውና በልዩ ሁኔታ ኤክስፖርትን የሚደግፉ  እንደ የቻየይና ኤክስፖርት ኢምፖርት ባንክ (Exim bank) ፣ የቻይና ኤክስፖርት ብድር ኢንሹራንስ ህብረት (Sinosure) ፣ የቻይና ልማት ባንክ እንዲሁም የቻይና ግብርና ልማት ባንክ የመሳሰሉ ተቋማት አሏቸው፡፡            የቻይና መንግስት ከአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ለሚፈፀም ግዢ ቅድሚያ ከመስጠቱም ባሻገር  ለዘርፉ የገበያ አስተዳደር ISO9001 ጥራት ደረጃን የሚያሟላ የተለየ የግብይት ስርዓት በመዘርጋቱ አምራች ኢንተርፕራይዞች የተፈጠረላቸውን የገበያ ዕድል በመጠቀም በአጭር ግዜ ምርትና ምርታማነትን ማሻሻል ችለዋል፡፡  ቻይና "የለም" የሚባል ነገር የለም ፡፡ የትኛውንም አይነት ምርት በሚፈለገው መጠንና ጥራት ማቅረብ የሚችል የላቀ የስራ ባህል ያላቸው ህዝቦቿ ለእድገቷ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል፡፡ የቻይና ዜጎች በስራ ባህላቸው ብቻ ሳይሆን የሀገራቸውን ምርት ብቻ በመጠቀምም በአለም ተወዳዳሪ የሌላቸው ሀገር ወዳድ ህዝቦች ናቸው፡፡ በመጨረሻም ከትግራይ ክልል የተውጣጡ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች የክልሉን ተሞክሮ በማቅረብ ከቻይና ተሞክሮ ያገኙትን ዕውቀት ለቀጣይ ስራቸው ግብአት በማድረግ እንደሚጠቀሙበት ገልፀዋል፡፡ #ኢትዮጵያ_ታምርት ፣ #እኛም_እንሸምት
نمایش همه...
👍 7
ለአስፈፃሚው አካል የሚሰጡ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች አምራች ኢንተርፕራይዞችን በውጤታማነት ለመደገፍ ትልቅ አቅም እንደሚሆን ተመላከተ EED ግንቦት 19/2016 ዓ.ም (ባህርዳር) የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን በውጤታማነት መደገፍ በሚያስችሉ ስትራቴጂክ ሰነዶች ዙሪያ ለአማራ ክልል የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች በባህርዳርና በኮምቦልቻ ከተሞች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡ በባህርዳር ከተማ እየተሰጠ ያለውን ስልጠና ያስጀመሩት የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ምክትል ሃላፊ ተወካይ አቶ ካሳሁን ታዬ ስልጠናውን ሲያስጀምሩ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አምራች ዘርፉ ውጤታማ እንዲሆን ከክልሉ ጋር ተቀራርቦ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፤ በዚህ ስልጠናም ዘርፉን በውጤታማነት መደገፍ በሚያስችሉ በልዩ ልዩ ስትራቴጂክ ሰነዶች ላይ ኢንተርፕራይዞችን ለሚደግፉ አመራሮችና ባለሙያዎች አዘጋጅቷል ብለዋል። ለአስፈፃሚው አካል የሚሰጡ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች አምራች ኢንተርፕራይዞችን በውጤታማነት ለመደገፍ ትልቅ አቅም አለው ያሉት አቶ ካሳሁን ስልጠናው ተቀራራቢ እውቀትና ግንዛቤ ይዞ ኢንተርፕራይዞችን ለመደገፍ የሚያስችል በመሆኑ ሰልጣኞች ስልጠናበተገቢው ሁኔታ በመከታተል ወደታች ማውረድ እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። ዛሬው ዕለት ለአማራ ክልል የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች መሰጠት የጀመረው ስልጠና የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ ፍኖተ ካርታ፣ የሽግግር ስትራቴጂ፣ የማምረት አቅም አጠቃቀምና በጥራት ስራ አመራር ላይ ትኩረት ያደረጉ መሆናቸው ተገልጿል። #ኢትዮጵያ_ታምርት   #እኛም_እንሸምት
نمایش همه...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
"ለብድር ካቀረብኩት 43.5 ቢሊዮን ብር ውስጥ 26 በመቶ የሚሆነውን ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሠጥቻለሁ" ኦሮሚያ ባንክ EED ግንቦት 18/2016 ዓ.ም ከተመሰረተ 15 ዓመታት ያስቆጠረው ኦሮሚያ ባንክ ለብድር ካቀረበዉ 43.5 ቢሊዮን ብር ዉስጥ 11.3 ቢልየን ብሩን ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ማሠራጨቱን አስታወቀ። ቀሪው የብድር አቅርቦት ለከፍተኛ ተበዳሪዎች ማቅረቡን የገለፀዉ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተፈሪ መኮንን ይህም የብድር አቅርቦት በአማካይ አንድ ተበዳሪ 5 ሚሊዮን ብድር መውሰዱን ተናግረዋል። የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተፈሪ መኮንን ጨምረዉ እንደተናገሩት የባንኩ የተበላሸ የብድር መጠኑ ከ1.6 በመቶ እስከ 2 በመቶ የሚደርስ እንደሆነ ገልፀዋል ። አሁን ላይ ቅርንጫፎችን ከመክፈት ወደ ዲጂታል የባንክ አገልግሎት ፊቱን ያዞረዉ ባንኩ "ኦሮ ዲጂታል" በተሰኘው አገልግሎት ቴሌግራምን ጨምሮ በ7 አማራጮች አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
نمایش همه...
👍 12