uz
Feedback
Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

Kanalga Telegram’da o‘tish

Ethiopian Enterprise Developmen (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

Ko'proq ko'rsatish
9 841
Obunachilar
+924 soatlar
+397 kun
+12230 kun

Ma'lumot yuklanmoqda...

Taglar buluti
Ma'lumot yo'q
Muammo bormi? Iltimos, sahifani yangilang yoki bizning qo'llab-quvvatlash boshqaruvchimizga murojaat qiling>.
Kirish va chiqish esdaliklari
---
---
---
---
---
---
Obunachilarni jalb qilish
Sen '26
Sentabr '26
+189
1 kanalda
Avgust '26
+227
0 kanalda
Get PRO
Iyul '26
+251
0 kanalda
Get PRO
Iyun '26
+184
0 kanalda
Get PRO
May '26
+219
1 kanalda
Get PRO
Aprel '26
+145
0 kanalda
Get PRO
Mart '26
+67
0 kanalda
Get PRO
Fevral '26
+93
0 kanalda
Get PRO
Yanvar '26
+94
0 kanalda
Get PRO
Dekabr '25
+92
1 kanalda
Get PRO
Noyabr '25
+111
0 kanalda
Get PRO
Oktabr '25
+156
0 kanalda
Get PRO
Sentabr '25
+102
0 kanalda
Get PRO
Avgust '25
+153
0 kanalda
Get PRO
Iyul '25
+124
1 kanalda
Get PRO
Iyun '25
+98
0 kanalda
Get PRO
May '25
+143
0 kanalda
Get PRO
Aprel '25
+155
0 kanalda
Get PRO
Mart '25
+193
0 kanalda
Get PRO
Fevral '25
+136
0 kanalda
Get PRO
Yanvar '25
+242
0 kanalda
Get PRO
Dekabr '24
+420
0 kanalda
Get PRO
Noyabr '24
+346
0 kanalda
Get PRO
Oktabr '24
+443
0 kanalda
Get PRO
Sentabr '24
+462
0 kanalda
Get PRO
Avgust '24
+837
0 kanalda
Get PRO
Iyul '24
+830
0 kanalda
Get PRO
Iyun '24
+642
0 kanalda
Get PRO
May '24
+839
0 kanalda
Get PRO
Aprel '24
+813
1 kanalda
Get PRO
Mart '24
+896
0 kanalda
Get PRO
Fevral '24
+595
0 kanalda
Get PRO
Yanvar '24
+514
1 kanalda
Get PRO
Dekabr '23
+391
1 kanalda
Get PRO
Noyabr '23
+45
1 kanalda
Get PRO
Oktabr '23
+43
0 kanalda
Get PRO
Sentabr '23
+23
0 kanalda
Get PRO
Avgust '23
+29
0 kanalda
Get PRO
Iyul '23
+19
0 kanalda
Get PRO
Iyun '23
+27
0 kanalda
Get PRO
May '23
+59
0 kanalda
Get PRO
Aprel '23
+32
0 kanalda
Get PRO
Mart '23
+67
0 kanalda
Get PRO
Fevral '23
+83
0 kanalda
Get PRO
Yanvar '23
+253
0 kanalda
Get PRO
Dekabr '22
+324
0 kanalda
Get PRO
Noyabr '22
+190
0 kanalda
Get PRO
Oktabr '22
+88
0 kanalda
Get PRO
Sentabr '22
+52
0 kanalda
Get PRO
Avgust '22
+80
0 kanalda
Get PRO
Iyul '22
+276
0 kanalda
Get PRO
Iyun '22
+207
0 kanalda
Get PRO
May '22
+125
0 kanalda
Get PRO
Aprel '22
+63
0 kanalda
Get PRO
Mart '22
+551
0 kanalda
Sana
Obunachilarni jalb qilish
Esdaliklar
Kanallar
27 Sentabr0
26 Sentabr+13
25 Sentabr+4
24 Sentabr+7
23 Sentabr+18
22 Sentabr+4
21 Sentabr+8
20 Sentabr+7
19 Sentabr+8
18 Sentabr+7
17 Sentabr+9
16 Sentabr+11
15 Sentabr+5
14 Sentabr+4
13 Sentabr+2
12 Sentabr+4
11 Sentabr+2
10 Sentabr+5
09 Sentabr+7
08 Sentabr+7
07 Sentabr+3
06 Sentabr+6
05 Sentabr+8
04 Sentabr+5
03 Sentabr+13
02 Sentabr+7
01 Sentabr+15
Kanal postlari
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፤ እንኳን ለ2019 ዓ.ም የመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ! #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት! ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡ https
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፤ እንኳን ለ2019 ዓ.ም የመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ! #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት! ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡ https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

2
#የአምራች_ስነ_ልቦና (ክፍል 20) - #ቢ ኤም ኤፍ የባህል እና ዘመናዊ ልብስ ዲዛይን ማምረቻ (ማርስ ዲዛይን) ===========///////============== በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ ገ
#የአምራች_ስነ_ልቦና (ክፍል 20) - #ቢ ኤም ኤፍ የባህል እና ዘመናዊ ልብስ ዲዛይን ማምረቻ (ማርስ ዲዛይን) ===========///////==============   በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ የሚገኘው ቢ ኤም ኤፍ የባህል እና ዘመናዊ ልብስ ዲዛይን ማምረቻ (ማርስ ዲዛይን) አምራች ኢንተርፕራይዝ በሀገር ባህልና ዘመናዊ አልባሳት ምርቱ በዘርፉ አዲስ ተስፋና አርአያነቱን እያስመሰከረ ይገኛል፡፡   ሙሉ መረጃውን በቅርብ ቀናት ይጠብቁን!   ​#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!   ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡   https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
542
3
የማርስ ዲዛይን የስኬት ጉዞ፡ ከአንድ ማሽን እስከ ሰፊ የኤክስፖርት እቅድ EED - መስከረም 15/2019 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ የሚገኘው የቢ ኤም ኤፍ (BMF) የባህልና ዘመናዊ ልብስ ዲዛይን ማምረቻ (ማርስ ዲዛይን) አምራች ኢንተርፕራይዝ፣ በዘርፉ አዲስ ተስፋና አርአያነቱን እያስመሰከረ ይገኛል:፡ ኢንተርፕራይዙ በ2002 ዓ.ም በ15 ሺህ ብር አነስተኛ መነሻ ካፒታልና በአንድ ማሽን ስራውን የጀመረ ቢሆንም፣ ባሳየው የትጋትና የቁርጠኝነት ጉዞ ምርቶቹን በአይነትና በመጠን በማሳደግ ካፒታሉን ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ማድረስ ችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ማርስ ዲዛይን ከ80 በላይ ዘመናዊ ማሽኖችንና 10 የሽመና ባለሙያዎችን በማደራጀት፣ ለ17 ቋሚና ለ10 ጊዚያዊ ሰራተኞች አስተማማኝ የስራ ዕድል ፈጥሯል፡፡ የኢንተርፕራይዙ መስራችና ስራ አስኪያጅ ዲዛይነር ማርስዓለም ሁሴን እንደገለጹት፣ ድርጅቱ ከዋናው ማምረቻ በተጨማሪ በቤታቸው ሆነው የጥልፍ፣ የዳንቴልና የመቋጨት ስራዎችን ለሚሰሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የገቢ ምንጭ መሆን ችሏል፡፡ በተለይም ህፃናት ልጅ ላላቸው ሴቶች ቅድሚያ የመቀጠር ዕድል በመስጠትና ለአካል ጉዳተኞች የስራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡ ድርጅቱ የወንዶችና የሴቶች ልዩ ልዩ አልባሳትን፣ የሀገር ባህል ሽፎኖችንና ጋቢዎችን፣ የመጋረጃና የሶፋ ጨርቆችን እንዲሁም ልዩ ልዩ የእጅ ስራዎችን እያመረተ ለገበያ ያቀርባል፡፡ በሀገራችን የሚከበሩ በዓላት በሀገር ባህል አልባሳት የሚደምቁ በመሆናቸው የተፈጠረውን ሰፊ የገበያ ዕድል በመጠቀምና በተለያዩ የጨረታ ስራዎች ላይ በመሳተፍ ውጤታማ መሆን የቻለ ሲሆን፣ ለዚህ ስኬቱም ከተለያዩ ተቋማት የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡ ለዚህ የስኬት ደረጃ መድረስ በመንግስት በኩል የተመቻቹት የስራ ማስኬጃ ብድር፣ የማምረቻ ቦታ፣ የማሽን አቅርቦት፣ የክህሎት ስልጠናዎች እንዲሁም የገበያና የግብዓት ትስስር ድጋፎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበራቸው፡፡ በተለይም በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ እና በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በተመቻቸለት የኢ-ኮሜርስ ገበያ ድጋፍ የፖስት ገበያ ተጠቃሚ ለመሆን ችሏል፡፡ ይህም ምርቶቹን ወደ ውጭ ከመላክ ባለፈ በሚመቻቹ የውጭ ገበያ ዕድሎች ላይ በመሳተፍ የሀገርን ምርት ለማስተዋወቅና የተሻለ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት አስችሎታል፡፡ በአሁኑ ወቅት የስራው ስፋት እየጨመረ በመምጣቱ በገላን ክፍለ ከተማ አስተዳደር ተጨማሪ የማስፋፊያ ቦታ በማግኘት የግንባታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ አዲሱ ማስፋፊያ በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር ምርትን በስፋት በማምረት ከሀገር ውስጥ ፍላጎት ባሻገር ለውጭ ገበያ ኤክስፖርት የማድረግ ሰፊ እቅድ ይዟል፡፡ በመጨረሻም የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ሰፊ የስራ ዕድል የሚፈጥርና የሀገርን ኢኮኖሚ የሚያጠናክር በመሆኑ፣ በተለይም ሴቶች በዘርፉ በስፋት በመሰማራትና ሀብት በማፍራት ራሳቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውን ብሎም ሀገራቸውን መለወጥ እንዳለባቸው ዲዛይነር ማርስዓለም ይመክራሉ፡፡ #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት! ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡ https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
583
4
+6
Matn yo'q...
516
5
ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው ሀገራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ ​EED መስከረም 14/2019 ዓ.ም (አዳማ) ​የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከመላው ኢትዮጵያ ለተወጣጡ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው ሀገራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ። ​ስልጠናው አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪ ሆነው በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ሽግግር፣ በተኪ ምርት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና በኤክስፖርት እድገት ላይ ጉልህ ሚና እንዲጫወቱ ለማስቻል ያለመ ነው:: ​በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት በልማት መ/ቤቱ የዋና ዳይሬክተር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማው ፈረደ እንደገለጹት፤ መድረኩ በተዘጋጁ የአሰራር ስርዓቶችና የድጋፍ ማዕቀፎች ላይ አመራሩና ባለሙያው የጠለቀ እውቀትና ክህሎት እንዲጨብጥ ማስቻሉን ተናግረዋል። አቶ ግርማው አክለውም የስልጠናው መካሄድ የዘርፉን የአሰራር ስርዓትና የድጋፍ ማዕቀፎች የተሳለጡና ወጥ በሆነ መልኩ ለመተግበር የሚያስችል የጋራ ግንዛቤ የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል። ​ሰልጣኞች በስልጠናው የቀሰሙትን እውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመለወጥ የሌሎች ባለሙያዎችንና የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች አቅም እንዲገነቡና ውጤታማ ድጋፍ እንዲሰጡ አሳስበዋል። ​በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ የታቀዱትን የዘርፉን ልማት ግቦች በሚፈለገው ፍጥነትና ጥራት ለማስፈጸም የሁሉም አካላት የጋራ ቅንጅትና ቁርጠኝነት አስፈላጊ መሆኑ አመላክተዋል። ​የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት፤ በስልጠናው ያገኙት ግንዛቤና ክህሎት በየደረጃው የሚታዩ የአሰራር ማነቆዎችን ለመፍታትና ለኢንተርፕራይዞቹ ወጥ የሆነ ድጋፍ ለመስጠት ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጥርላቸው ገልጸው፣ ወደ ሥራ ቦታቸው ሲመለሱ ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር ለመለወጥ ቁርጠኛ ሆነው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። ​#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት! ​ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡ https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
612
6
ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው ሀገራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ+9
ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው ሀገራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ
569
7
https://youtu.be/Zo-ZzehCZMU #የአምራች_ስነ_ልቦና (ክፍል አስራ_ዘጠኝ) - #ቱምሃ_የንጽህና_እቃዎች አምራች ===========///////============== ​#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት! ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡ https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
715
8
+4
Matn yo'q...
825
9
ተኪ ምርቶች፤ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ EED መስከረም 12/2019 ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስና የሀገር ውስጥ ምርትን በበቂ ሁኔታ ለማሳደግ ተኪ ምርቶች ላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች የመተካት ሥራ እየተጠናከረ መምጣቱ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በእጅጉ ጠቃሚ ነው፡፡ የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገት ዋና ማሳያ የምርት እድገት መሆኑን በውል በመገንዘብ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በርካታ ተግባራትን በልዩ ትኩረት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ በራሷ አቅም የምታመርታቸውን ምርቶች ለራሷና ለዓለም በማቅረብ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች። ለአብነትም በግብርናው ዘርፍ ስንዴ እንዲሁም በመድኃኒትና ሌሎች መሰረታዊ ምርቶች ራሷን ለመቻል በርካታ ተግባራትን እያከናወነች ነው፡፡ ተኪ ምርቶች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት የውጭ ምንዛሪ አቅምን ከማሳደግ ባለፈ ሰፊ የስራ እድል በመፍጠርና ዜጎች ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት እንዲችሉ እያደረገ ይገኛል። በ2018  በጀት ዓመት ብቻ በተኪ ምርት 5 ነጥብ 96 ቢሊየን ዶላር ማዳን የተቻለ ሲሆን፤ ለ448 ሺህ 717 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡ ኢትዮጵያ ለገቢ ምርቶች የምታወጣውን ወጪ ለመቀነስ ተኪ ምርቶችን በብዛት፣ በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ሲሆን፤ ይህም ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት እንዲመዘገብ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ96 እስከ 100 የሚጠጉ ስትራቴጂያዊ ተኪ ምርቶችን በመለየት በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ እየሰራች ነው፡፡ በተጨማሪም የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ከግብርና፣ ንግድና ኢንቨስትመንት ጋር ጠንካራ ትስስር ፈጥሮ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ እየተሰራ ነው፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ ሀብቷን በአግባቡ በመጠቀም ሰፊ የሰው ኃይል አቅሟን በማቀናጀትና በጠንካራ አመራር ወደፊት በመጓዝ ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ የነገዋ የበለጸገች ኢትዮጵያ ጠንካራ መሰረት ዛሬ እየተጣለ ይገኛል። ምንጭ: FBC #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!   ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጻችንን ይጎብኙ፦ 👉 https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopmentlease
727
10
የምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስፋት የአሠራር ሥርዓት   EED መስከረም 12/2018 ዓ.ም   የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከመላው ሀገሪቱ ለተውጣጡ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች የሚሰጠውን ሀገራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናክሮ ቀጥሏል። በስልጠና ውሎውም “የምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስፋት የአሠራር ሥርዓት” ቀርቦ ሰፊ ስልጠናና ውይይት ተካሂዶበታል።   ምርጥ ተሞክሮ ማለት የሚፈለገውን ውጤት በዘላቂነት ለማስመዝገብ እንዲያስችል በጥናትና በልምድ የተረጋገጠ ውጤታማ የአሠራር ስርዓት ነው።   አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች በሀገሪቱ የመዋቅራዊ ኢኮኖሚ ሽግግር ውስጥ የሚኖራቸውን ከፍተኛ አበርክቶ በዘላቂነት ለማስቀጠል፣ ውጤታማ የሆኑ የመንግስት ድጋፍ አሰጣጥና የኢንተርፕራይዝ አሰራር ስርዓቶችን መለየት፣ መቀመርና ማስፋት ከፍተኛ ሀገራዊ ፋይዳ አለው። ይህንን ታሳቢ በማድረግም የምርጥ ተሞክሮ ልየታ፣ ቅመራና ማስፋት የአሰራር ስርዓት ተዘጋጅቷል።   👉የአሠራር ስርዓቱ ዋና ዓላማ ውጤታማነቱ በጥናት የተረጋገጠ የመንግስት ድጋፍ አሠጣጥን እና የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን አሰራር ለመለየት፣ ለመሰነድና ለማስፋት የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት ነው። ይህም ለዘላቂ የኢንተርፕራይዝ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት መሻሻል ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።   👉የምርጥ ተሞክሮ ዋነኛ ጥቅሞች ምርታማነትን ማሳደግ፡ የኢንተርፕራይዞችን ልዩ ውጤታማነትና አፈጻጻም ማጎልበት፣   ዕውቀትና በራስ መተማመንን ማዳበር፡ የባለሙያዎችንና የአመራሩን የፈጠራና የችግር መፍታት አቅም ማደራጀት፣   የአሰራር ሥርዓትን ማስተካከል: ሂደቶችን በማቃለል ውጤታማ አሰራርን መተግበር፣   👉የምርጥ ተሞክሮ ትግበራ ሂደት ማቀድና ልየታ (Planning & Identification) ቡድን ማቋቋም (Team Formation) መረጃ መሰብሰብ (Data Collection) መሰነድ (Documentation) ማስፋት (Scaling & Dissemination)   👉ምርጥ ተሞክሮን ለመለየት የሚያገለግሉ መስፈርቶች ውጤታማነትና ስኬታማነት፦ የታለመውን ግብ በግልጽ ማሳካቱ የተረጋገጠ፣ ተዛማጅነት፦ ከዘርፉ ስትራቴጂካዊ ግቦች ጋር የተጣጣመ፣ ዘላቂነትና የመስፋት አቅም፦ በሌሎች አካባቢዎችና ኢንተርፕራይዞች በቀላሉ ሊደገም የሚችል፣ የባለድርሻ አካላትና የተጠቃሚዎች ተሳትፎ፦ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ፣ የአመራር ቁርጠኝነት፦ ትግበራውን ለመደገፍ የሚያስችል አስተዳደራዊ ዝግጁነት ያለው፣   #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!   ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጻችንን ይጎብኙ፦ 👉 https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopmentlease
740
11
የምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስፋት የአሠራር ሥርዓት ስልጠና+3
የምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስፋት የአሠራር ሥርዓት  ስልጠና
761
12
https://youtu.be/CYM_GAFFTiw?si=f0VXUVTad-FeDdZ8 #የአምራች_ስነ_ልቦና (ክፍል አስራ_ዘጠኝ) - #ቱምሃ_ሳሙና ===========///////==============   ቱምሃ ሳሙና በ5 አባላት (አቶ ዘመኑ፣ ታከለና ጓደኞቻቸው) ሽርክና ማህበር በ2010 ዓ.ም ፈሳሽ ሳሙና በማምረት ወደ ስራ የገባ መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ነው፡፡   የኢንተርፕራይዙ መስራች አባልና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘመኑ መለሠ "ቱምሃ ሳሙና" ስራውን ለመጀመር በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በኩል የተገኘው የሙያ ስልጠናና ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበረው ገልፀዋል፡፡ በተለይም በተቋሙ የተገኘው የሙያ ክህሎት ስልጠና አባላቱ ከተለያየ የስራ ዘርፍ የመጡ በመሆናቸው ስራውን ለመጀመር መሰረት እንደሆናቸው የገለፁት አቶ ዘመኑ፤ ከሙያ ስልጠና በተጨማሪ ከምርት አመራረት እስከ ገበያ አጠቃቀምና ተወዳዳሪነት ድረስ በተቋሙ የተደረገላቸው ድጋፍ ትልቅ አቅም እንደሆናቸው ተናግረዋል፡፡ ይህም ኢንተርፕራይዙ ጥራት ያላቸውን የጽዳትና የዲተርጀንት ምርቶች በስፋት እንዲያመርትና በዘርፉ ውጤታማ እንዲሆን ያስቻለው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን በቅርብ ቀናት ይጠብቁን!   ​#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!   ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡   https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
744
13
ስርዓተ-ፆታና አካታችነት በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ   EED መስከረም 11/2018 ዓ.ም   የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከመላው ሀገሪቱ ለተውጣጡ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች የሚሰጠው ሀገራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና ቀጥሎ ውሏል። በኢንዱስትሪው ዕድገትና ውጤታማነት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው «ስርዓተ-ፆታና አካታችነት» (Gender and Inclusivity) ርዕስ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።   ስርዓተ-ፆታ (Gender) በወንዶችና በሴቶች መካከል ያሉ ማህበራዊ ሚናዎችንና ግንኙነቶችን የሚያመለክት ሲሆን፤ በማህበረሰብ ደረጃ የተቀመጡ አመለካከቶች፣ ልምዶችና ተግባራት በሁለቱም ፆታዎች እንዲተገበሩ የሚጠበቁበትን ሂደት ያጠቃልላል።   በስልጠናው የተዳሰሱ የስርዓተ-ፆታ የግንዛቤ ደረጃዎች (Levels of Gender Awareness)፦ የስርዓተ-ፆታ ግንዛቤ እጦት (Gender Blind)፦ በወንዶችና ሴቶች መካከል ያሉ ልዩነቶችንና ፍላጎቶችን ያላገናዘበ አሰራር፤ ስርዓተ-ፆታ ተኮር (Gender Sensitive)፦ በወንዶችና ሴቶች መካከል ልዩነቶች መኖራቸውን መገንዘብና መረዳት፤ ለስርዓተ-ፆታ ጉዳይ ምላሽ ሰጪ (Gender Responsive)፦ የተለዩ ፍላጎቶችንና ክፍተቶችን ለመድፈን በተግባር የተደገፈ ምላሽ መስጠት፤ ስርዓተ-ፆታዊ ለውጥ (Gender Transformative)፦ አድሏዊ አሰራሮችንና አመለካከቶችን በመቀየር ዘላቂ እኩልነትን ማረጋገጥ።   አካታችነት (Inclusivity) ምንድን ነው? አካታችነት ማለት ሴቶችን፣ ህፃናትን፣ ወጣቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ አረጋውያንን እና ሌሎች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በፖለቲካና በባህል ዘርፎች እኩልና ፍትሐዊ ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድረግ ነው፡፡ ይህም የነገሩን ሁኔታ፣ ፍላጎትና ልምድ በፖሊሲዎች፣ በህጎች፣ በስትራቴጂዎች፣ በፕሮግራሞች፣ በእቅዶችና በሪፖርት እንዲሁም በክትትልና ግምገማ ሂደቶች ውስጥ ታሳቢ ማድረግን ይጠይቃል።   በስራ ቦታ የሚተገበሩ የማካተት ደረጃዎች፦ በፖሊሲ፣ ህግና ስትራቴጂ ደረጃ ከሁኔታዎች ትንተና ጀምሮ እስከ ግብ፣ የትኩረት አቅጣጫና የክትትል ስርዓት ውስጥ ማካተት፤ በፕሮግራሞች፣ ፕሮጀክቶችና እቅድ ደረጃ ከቅድመ ቀረጻ ጀምሮ እስከ ትግበራና ግምገማ ድረስ ያሉ ሂደቶችን አካታች ማድረግ፤ በተቋም ደረጃ ተቋሙ የተቋቋመባቸውን ዋና ዋና ዓላማዎች ለማሳካት በሚዘረጋቸው አስተዳደራዊ ዘርፎችና ተግባራት ውስጥ ማካተት።   የማካተት ስልቶችና አፈፃፀም ሂደቶች (Key Implementation Steps) የፍላጎትና ሁኔታ መረጃ ስብስብና ትንተና በፆታ፣ በእድሜ እና ከአካል ጉዳተኝነት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን በመተንተን ፍላጎቶችን በግልፅ መለየት፤   አካታች ዓላማ፣ ግብና አመላካች መቀረጽ ፍላጎትንና ከባቢያዊ ሁኔታዎችን ያገናዘቡ ኢላማዎችና የማስፈጸሚያ ስልቶችን ማዘጋጀት፤   በጀት መመደብና መተግበር ለተቀመጡት አካታች ተግባራት አስፈላጊውን በጀት መመደብና ወደ ተግባር መተርጎም፤   ክትትልና ግምገማ በእቅዱ መሰረት የተከናወኑ ስራዎችን በመገምገም ያመጡትን አዎንታዊ ፋይዳ ማረጋገጥ።   #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!   #EthiopianEnterpriseDevelopment #EED #GenderAndInclusivity #CapacityBuilding #MSME #Manufacturing #Ethiopia   ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡   👉 https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
575
14
+4
Matn yo'q...
660
15
የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አሰጣጥ EED መስከረም 11/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከመላው ሀገሪቱ ለተውጣጡ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች የሚሰጠው ሀገራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና ቀጥሎ ውሏል። የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያተኮረ ውይይትና ስልጠና ተሰጥቷል። ከዚህ ቀደም የነበረውን አሰራር በማሻሻልና የአለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን በማካተት፣ ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ፍላጎትና ደረጃ የሚመጥን ግልፅ ስትራቴጅውን መነሻ ያደረገ የማስፈጸሚያ ማንዋል ተዘጋጅቷል። 👥 የማንዋሉ ተጠቃሚዎች ·👉ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች: በዕድገት ተኮር ንዑስ ዘርፎች የተሰማሩ ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች (እንደ ዕድገት ደረጃቸው በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ ያገኛሉ)። 👉አስፈጻሚና ባለድርሻ አካላት በየደረጃው የሚገኙ የዘርፉ ልማት አስፈጻሚዎች፣ ድጋፍ ሰጪ ተቋማትና አመራሮች የተጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጡ ያስችላቸዋል። 📌 የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዋና ዋና ዓላማዎች ⚙️ለጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ግልፅና ደረጃውን የጠበቀ የአገልግሎት ስርዓት መዘርጋት፣ ⚙️የኢንተርፕራይዞችን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የገበያ ተወዳዳሪነታቸውን ማረጋገጥ፣ ⚙️የስልጠና፣ የምክር፣ የቴክኖሎጂ፣ የግብይት እና የጥራት ማሻሻያ ድጋፎችን በተሟላ መልኩ ማቅረብ ⚙️ የአገልግሎት አሰጣጥ ዋና ዋና ስልቶች · የክላስተር እና ኢንተርፕራይዝ ተኮር ኤክስቴንሽን አገልግሎት · የከፍተኛ ትምህርት፣ የቲቪኢቲ (TVET) እና የምርምር ተቋማት ትስስር ·  ዲጂታላይዜሽን እና የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ · የግል ዘርፉን ተሳትፎ ማረጋገጥ 🔄 የአፈፃፀም ቅደም-ተከተል (Steps) 1.   የመረጃ ዝግጅትና አገልግሎቱን ማስተዋወቅ 2.   ጥያቄ መቀበል፣ የነባራዊ ሁኔታ ትንተና ማካሄድና ውል መፈራረም 3.   የድርጊት መርሃ-ግብር በማዘጋጀት አገልግሎቱን መስጠት 4.   ክትትል፣ ግምገማ፣ ግብረ-መልስ እና ተሞክሮዎችን ማስፋት #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!   ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡   https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
1 490
16
የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አሰጣጥ ስልጠና+2
የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አሰጣጥ ስልጠና
511
17
የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍን የግብዓት አቅርቦትና የኢንዱስትሪ ትስስር ማጎልበት ለምን አስፈለገ? EED መስከረም 11/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከመላው ሀገሪቱ ለተውጣጡ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች የሚሰጠው ሀገራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደቀጠለ ነው። የአምራች ኢንዱስትሪ ትስስር ስትራቴጂ መሰረት በማድረግ በተለይም በአምራች ዘርፉ የሚስተዋሉ የግብዓት አቅርቦት ማነቆዎችን መፍታት እና የኢንዱስትሪ ትስስር ማጠናከር ላይ ሰፊ ስልጠናና ውይይት ተደርጓል።   ትኩረት የተሰጣቸው የኢንዱስትሪ ትስስር ዓይነቶች፦ · የኋልዮሽ ትስስር (Backward Linkage) አምራች ኢንተርፕራይዞች ለምርት ሂደታቸው የሚሆኑ ጥሬ ዕቃዎችንና ግብዓቶችን ከሀገር ውስጥ አቅራቢዎችና አርሶ አደሮች ጋር በመተሳሰር የሚያገኙበት አሰራር፤ ·የፊትዮሽ ትስስር (Forward Linkage) ኢንተርፕራይዞች ያመረቷቸውን ምርቶች ለሚያከፋፍሉ፣ ለሚሸጡ ወይም ተጨማሪ እሴት ለሚጨምሩ ሌሎች ድርጅቶች የሚያቀርቡበት የገበያ ትስስር፤ ·የጎንዮሽ ትስስር (Horizontal Linkage) በዘርፉ ያሉ አምራቾች የግብይት ወጪዎችን ለመቀነስ፣ ሀብቶችን በጋራ ለመጠቀምና የምርት ጥራትን ለማሳደግ የሚያደርጉት የጋራ ትብብር፤ ·አቀበታዊ ትስስር (Vertical Linkage) በእሴት ሰንሰለቱ ውስጥ ባሉ አምራቾች መካከል ቀልጣፋ ግብይት በመፍጠር ተወዳዳሪነትን የሚያሳድግ ትስስር። በግብዓት አቅርቦት ዙሪያ የተለዩ ዋና ዋና ማነቆዎች: ·ለኢንተርፕራይዞች የሚሆኑ ግብዓቶች በዋጋ፣ በጥራት እና በሚፈልጉት መጠንና ጊዜ አለመገኘት፤ ·ግብዓት ከአገር ውስጥ በሚገዛበት ወቅት ህጋዊ ደረሰኝ አለማግኘትና የታክስ ክፍያ ችግሮች፤ ·የደላሎች መበራከትና አላስፈላጊ የገበያ ሰንሰለት መዘርጋት፤ ·የኢንዱስትሪዎች ግብዓት ልማት ድርጅት አቅርቦት ውስን መሆን · የብድር ዋስትና መመዘኛዎችን ለማሟላት መቸገር የተቀመጡ ስትራቴጂካዊ መፍትሔዎች 👉የሀገር ውስጥ ምርትን ማጠናከር የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ በስፋት ማምረት እና በተኪ ምርት ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የማበረታቻ ስርዓት መዘርጋት፣ 👉ቀጥታ ትስስርና የኮንትራት ፋርሚንግ አርሶ አደሮችን በክላስተር በማደራጀት ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር ማስተሳሰር፣ የኮንትራት ፋርሚንግ ስርዓት መዘርጋት እና ደላሎችን ከገበያ ማስወጣት፣ 👉በግብርናው ዘርፍ ኢንቨስት ማድረግ ባለሀብቶች በግብርናው ዘርፍ ኢንቨስት በማድረግ ለኢንዱስትሪዎች የጥሬ ዕቃ አቅርቦት እንዲያረጋግጡ ማድረግ፣ 👉የወጪና የትራንስፖርት ማቃለል በኬላዎች የሚጠየቁ አላስፈላጊ ወጪዎችን መቆጣጠርና የግብዓት እንቅስቃሴን ማሳለጥ፣ 👉የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠናዎች ለኢንተርፕራይዞች ዘመናዊ የግብዓት አቅርቦት ትስስር ክህሎት ስልጠናዎችን መስጠት እና ጥራት ያለው ምርት እንዲያመርቱ ድጋፍ ማድረግ #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!   ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡   https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
624
18
+3
Matn yo'q...
685
19
ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች መሰጠት የጀመረው ሀገራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና+9
ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች መሰጠት የጀመረው ሀገራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና
931
20
በ2018 በጀት ዓመት በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች 270 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል!   ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች ሀገራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ EED መስከረም 9/2019 ዓ.ም  (አዳማ) የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት አዲስ በተቋቋሙና በተጠናከሩ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች 270 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን አስታወቀ::   ይህ የተገለጸው ከመላው ኢትዮጵያ ለተወጣጡ 160 ለሚሆኑ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት በተጀመረበት ወቀት ነው። የልማት መስሪያ ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታህ የሱፍ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ተቋሙ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 526/2015 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪ ሆነው በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ሽግግር፣ በተኪ ምርት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና በኤክስፖርት እድገት ላይ ጉልህ ሚና እንዲጫወቱ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል። በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 4 ሺህ 233 አዳዲስ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች መቋቋማቸውንና በዚህም ለ270,546 ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን ገልጸዋል::   ከዚህም በተጨማሪ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት በተሰራው ስራ 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር የሚያወጡ ምርቶችን መተካት መቻሉንና ወደውጭ በተላኩ ምርቶች 36 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ዶላር መገኘቱን ተናግረዋል::   ም/ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም  የዘርፉን ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የሚሰጡ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን፣ የእድገት ሽግግር፣ የቴክኖሎጂ ልማት፣ የጥራት አስተዳደርና የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ስራዎችና ድጋፎች የተሳለጡና ወጥ መሆን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ሰልጣኞች ከስልጠናው የሚያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር በመለወጥ በየአካባቢያቸው ለሚገኙ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች አቅም የሚገነባና ውጤታማ ድጋፍ እንዲሰጡ ም/ዋና ዳይሬክተሩ አደራ ብለዋል:: #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!   ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡   https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
748