Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)
📈 Análisis del canal de Telegram Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)
El canal Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት) (@ethiopianenterprisedevelopment) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 10 010 suscriptores, ocupando la posición 7 180 en la categoría Negocios y el puesto 3 420 en la región Etiopía.
📊 Métricas de audiencia y dinámica
Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 10 010 suscriptores.
Según los últimos datos del 06 noviembre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 116, y en las últimas 24 horas de 6, conservando un alto alcance.
- Estado de verificación: No verificado
- Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 9.46%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 4.69% de reacciones respecto al total de suscriptores.
- Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 947 visualizaciones. En el primer día suele acumular 469 visualizaciones.
- Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 2.
📝 Descripción y política de contenido
El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“Ethiopian Enterprise Developmen (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)”
Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 07 noviembre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Negocios.
Cargando datos
| Fecha | Crecimiento de Suscriptores | Menciones | Canales | |
| 06 noviembre | +6 | |||
| 05 noviembre | +3 | |||
| 04 noviembre | +8 | |||
| 03 noviembre | +7 | |||
| 02 noviembre | +2 | |||
| 01 noviembre | +5 |
| 2 | ምርታማነትና ተወዳዳሪነት፡ ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች የዕድገት ቁልፍ!
=======//////==========
የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ ሰፊ የስራ ዕድል የሚፈጥር ከመሆኑም በላይ ለሀገራችን ኢኮኖሚ የላቀ ድርሻ አለው።
በዚህ ፈጣንና ተወዳዳሪ የገበያ አለም ውስጥ በዘርፉ ዘላቂ ስኬት ለማስመዝገብ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ወሳኝ ናቸው።
ብዙ ጊዜ ስለ ማኑፋክቸሪንግ ተወዳዳሪነት ስናስብ ወደ አእምሮአችን የሚመጣው ትልልቅ ማሽኖችን መግዛት ወይም ከፍተኛ ካፒታል ማፍሰስ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በሀገራችን እውነታ የአነስተኛና መካከለኛ አምራቾች ውጤታማነት የሚጀምረው ካለን ሀብት ላይ አላስፈላጊ ብክነትን በማስወገድ ነው። እንዲሁም የምርታማነት ሚስጥሩ ሁልጊዜ አዲስ ማሽን መግዛት ሳይሆን፣ በእጃችን ያለውን ማሽን፣ ጊዜ እና ጥሬ ዕቃ በካይዘን እና በዘመናዊ የጥራት አሰራሮች ማደራጀት መቻል ነው።
አንድ አነስተኛ አምራች በየቀኑ በስራ ቦታው የሚያደርጋቸው ትንሽ የሚመስሉ ማሻሻያዎች በወሩ መጨረሻ ትልቅ የገቢ ልዩነት ያመጣሉ። የማምረቻ ቦታን በጥንቃቄ ማደራጀት፣ የጥራት ጉድለቶችን ገና ከጅምሩ መግታት፣ የሰራተኞችን የስራ ፍሰት ማስተካከል እና በዲጂታል የገበያ አማራጮች ምርትን በቀጥታ ማቅረብ ያለ ተጨማሪ ወጪ ከፍተኛ ተወዳዳሪነትን ያስገኛል።
እውነተኛ ተወዳዳሪነት የሚገነባው በደረጃ እና በጥራት በሚመረቱ ሀገር በቀል ምርቶች ነው። ዛሬ በፋብሪካችን የምናደርጋት አንዲት የጥራት ማሻሻያ ነገ የሀገር ውስጥ ገበያን ሙሉ በሙሉ ለመሸፈንና ወደ ውጭ ገበያ ለመሸጋገር መሰረት ይሆናል!
#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!
ለተጨማሪ መረጃ፡
https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment | 567 |
| 3 | ደሴ አሰፌ የእንስሳት መኖ ፋብሪካ በ61 ሚሊዮን ብር ካፒታል ወደ ማምረት ገባ
EED ጥቅምት 24/ 2019 ዓ.ም
በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ የተቋቋመው ደሴ አሰፌ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ወደ ማምረት መግባቱ ተገለፀ።
የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን በማጠናከርና የሀገር ውስጥ ምርትን በመተካት ረገድ ትልቅ ድርሻ ያለው ይህ ኢንዱስትሪ አጠቃላይ የካፒታል መጠኑን 61 ሚሊዮን ብር ያደረሰ ሲሆን፣ በላቀ የኢንዱስትሪ ማቀነባበር ሂደት ጥራታቸውን የጠበቁ የዶሮ መኖ፣ ለወተት ላሞችና ለእንስሳት ማደለቢያ የሚሆኑ የምግብ አይነቶችን አምርቶ ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛል።
ፋብሪካው ወደ ማኑፋክቸሪንግ ምርት ስራ በመግባቱ በቀጥታ ለ37 በላይ ዜጎች አዲስ የኢንዱስትሪ ስራ እድል የፈጠረ ሲሆን፣ የአካባቢውን የግብርና ተረፈ-ምርቶች በኢንዱስትሪ ግብአትነት በመቀየር በግብርና እና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ መካከል ጠንካራ የገበያና የምርት ትስስር እንዲፈጠር አድርጓል።
የቴክኖሎጂ አጠቃቀሙንና የማምረት አቅሙን በማሳደግ የሀገር ውስጥ አግሮ-ፕሮሰሲንግ ማኑፋክቸሪንግ እድገትን ለማፋጠን፣ የምርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና የምርት አቅሙን በማስፋፋት ለተጨማሪ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር አቅዶ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
ምንጭ: የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ (https://www.facebook.com/share/p/19fF6VFgZQ/)
#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!
ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡
https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment | 774 |
| 4 | የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በግንባታ ላይ የሚገኘውን የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች የልህቀትና የኢንኩቤሽን ማዕከል ጎበኙ
EED — ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዶ/ር ፍስሃ ይታገሱ፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች እና ከፍተኛ አመራሮች የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት እያስገነባ የሚገኘውን የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች የልህቀትና የኢንኩቤሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!
ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡
https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment | 815 |
| 5 | https://www.facebook.com/share/p/1ZRUs1NhSg/ | 857 |
| 6 | #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!
ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡
https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment | 1 116 |
| 7 | Sin texto... | 1 617 |
| 8 | የጨፋ ዱቄት ፋብሪካ፡ ከፈተናዎች ወደ ዘላቂ የምርት እድገትና የሥራ እድል ፈጠራ
=====//////=======
በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በከሚሴ ከተማ የሚገኘው የጨፋ ዱቄት ፋብሪካ ያጋጠሙትን ዘመናት የተሻገሩ የሥራ አመራርና የገበያ ፈተናዎች በመቋቋም፣ የውስጥ አደረጃጀቱን በማስተካከል ዳግም ወደ ምርት ሥራ ተመልሷል። ፋብሪካው በአሁኑ ወቅት በሙሉ አቅሙ ማምረት ባይችልም፣ ለ22 ዜጎች የሥራ እድል በመፍጠር የገበያ ተሳትፎውን ማጠናከር ጀምሯል።
የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ ወጣት አባስ አሚሩ መሀመድ እንዳረጋገጡት፣ ፋብሪካው በ2006 ዓ.ም. በተሰጠው 3,400 ካሬ ሜትር የመሬት ይዞታ ላይ በ3 ሚሊዮን ብር ካፒታል የማሽን ግዥ በመፈጸም ነበር የምርት ሥራውን የጀመረው።
በወቅቱ “ፈውዝ ዱቄት ፋብሪካ” በሚል ስያሜ ወደ ሥራ የገባው ይህ ተቋም፣ በሂደት ከውጭ ሀገር የሚገቡ የዱቄት ምርቶች በዝቅተኛ ዋጋ ወደ አገር ውስጥ መጎረፋቸውን ተከትሎ በገበያ ተወዳዳሪነቱ ላይ ከፍተኛ ጫና አጋጥሞታል። ይኸው የገበያ መዛባት ለከፍተኛ ኪሳራ ዳርጎት ለአጭር ጊዜ ሥራውን ለማቋረጥ ተገዶ ነበር።
የሥራ አመራር ለውጥና ዳግም መነሳት
ፋብሪካው ከቀደመው ውድቀት ትምህርት በመውሰድና አዲስ የአመራር አደረጃጀት በመዘርጋት በ2016/17 ዓ.ም. “ጨፋ ዱቄት ፋብሪካ” በሚል አዲስ ስያሜ ዳግም ወደ ምርት ገብቷል።
ይህ አዎንታዊ ማገገም ውጤታማ የሥራ አመራር፣ ተገቢ የምርት አደረጃጀትና የገበያ ተሳትፎ ለአንድ አምራች ተቋም መነሳት ያላቸውን ፋይዳ የሚያሳይ ተግባራዊ ተሞክሮ ሆኗል።
የሥራ እድል ፈጠራና ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦ
ፋብሪካው ዳግም ሥራ በመጀመሩ በአሁኑ ወቅት ለ16 ቋሚና ለ6 ጊዜያዊ ሠራተኞች፣ በድምሩ ለ22 ዜጎች የገቢ ምንጭ መፍጠር ችሏል።
ይህ የሥራ እድል ፈጠራ የግል ኢንቨስትመንት ለዜጎች የገቢ ምንጭ በመፍጠር፣ የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በማጠናከርና የምርት ዘርፉን በማሳደግ ረገድ ያለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያመለክታል።
የፋይናንስ እጥረት፡ ዋነኛው የምርት አቅም ማነቆ
ተቋሙ በገበያ ውስጥ ያለውን ተሳትፎ ለማስቀጠል ቢጥርም፣ የካፒታልና የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት በሙሉ አቅሙ እንዳያመርት ትልቅ ማነቆ ሆኖበታል።
የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ ወጣት አባስ አሚሩ መሀመድ እንደገለጹት፣ በተለይም ለምርት የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎችን በበቂ መጠን ለመግዛት የፋይናንስ እጥረቱ ዋና እንቅፋት ሆኖባቸዋል።
ሥራ አስኪያጁ አክለውም የፋብሪካው የገበያ ፍላጎት አስተማማኝ መሆኑን ጠቁመው፣ ከባንኮች የሸሪዓ መርህን የተከተለ (ከወለድ ነፃ) የፋይናንስ አቅርቦት ማግኘት ከተቻለ ግብዓቶችን በበቂ ሁኔታ በመግዛት በሙሉ አቅም ማምረት እንደሚችሉ አስረድተዋል።
የዘርፉ አመራሮች ድጋፍ አስፈላጊነት
ፋብሪካው ያለበትን የካፒታል ችግር ፈትቶ አቅሙን ያደገ ዘላቂ ተቋም እንዲሆን በየደረጃው ያሉ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት አመራሮችና ባለሙያዎች የቅርብ ድጋፍ ሊያደርጉለት እንደሚገባ ጥሪ አቀርቧል።
ይህ ድጋፍ ፋብሪካውን ከተስማሚ የፋይናንስ አቅርቦትና ከባንኮች ጋር ማገናኘት፣ በምርት ሂደቱ የሚያጋጥሙ አስተዳደራዊና ሙያዊ ማነቆዎችን መፍታት፣ እንዲሁም የአካባቢውን የምርት አቅም በማሳደግ የገበያ መረጋጋት መፍጠርን ያካተተ መሆን አለበት።
በአጠቃላይ፣ የጨፋ ዱቄት ፋብሪካ ጉዞ ሀገር በቀል አምራች ተቋማት የሚገጥሟቸውን ፈተናዎችና ተገቢው ተቋማዊ ድጋፍ ከተደረገላቸው ዳግም የማንሰራራት አቅማቸውን ያሳየ ነው። የፋብሪካውን የምርት አቅም ማሳደግ የሥራ እድልን ከማስፋቱም በላይ የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለማጠናከር የጎላ ድርሻ ይኖረዋል።
ምንጭ: አማራ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ (https://www.facebook.com/share/19cAV1HfiP/)
#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!
ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡
https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment | 1 153 |
| 9 | Sin texto... | 1 213 |
| 10 | "የመንግስት ድጋፍ አቅማችንን እንድናሳድግ አስችሎናል!" — ኒው ኤግልስ ጋርመንት
EED ጥቅምት 17/2019 ዓ.ም
መንግስት ለኢንዱስትሪው ዘርፍ የሰጠው ትኩረትና ድጋፍ አምራቾች አቅማቸውን አሳድገው የብዙዎችን ህይወት እንዲደግፉ ማስቻሉን የኒው ኤግልስ ጋርመንት ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍጹም እንግዳ ገልፀዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ በ5 ሺህ ብር መነሻ ካፒታል የተቋቋመው «ኒው ኤግልስ ጋርመንት» ካፒታሉን 25 ሚሊዮን ብር ማድረሱንና የ85 ዜጎችን የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል።
ድርጅቱ በ2011 ዓ.ም «ሀይለየሱስ፣ ፍፁምና ጓደኞቻቸው» የህትመትና ማስታወቂያ (ኒው ኤግልስ ጋርመንት) በሚል ስም በ5 ሺህ ብር መነሻ ካፒታል እና በ50 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ሥራውን የጀመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የሀገር ውስጥ ምርትን በመተካት ረገድ አርአያነት ያለው የስኬት ጉዞ እያስመዘገበ ይገኛል።
የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍጹም እንግዳ እንደገለጹት፤ ድርጅታቸው በጅምር ወቅት የነበረበትን የፋይናንስ እጥረት በሊዝ ፋይናንስ የአገልግሎት ብድር የ6 ማሽኖች ድጋፍ በማግኘት አልፎታል። በወቅቱ የ3 ዜጎችን የሥራ ዕድል በመፍጠር የተነሳው ድርጅቱ፣ በአሁኑ ወቅት በመንግስት በተመቻቸለት የ400 ካሬ ሜትር መስሪያ ቦታ ላይ በመንቀሳቀስ የካፒታል መጠኑን 25 ሚሊዮን ብር ማድረስ ችሏል።
በዚህም የ85 ዜጎችን የሥራ ዕድል መፍጠር የቻለ ሲሆን፤ ልዩ ልዩ የአልባሳት ምርቶችን በጥራት በማምረት ለጅምላ አከፋፋዮች፣ ለግል ድርጅቶች እንዲሁም ለመንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት እያቀረበ ይገኛል።
ሥራ አስኪያጁ አክለውም፤ መንግስት ለኢንዱስትሪው ዘርፍ፣ በተለይም ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ጥራት ባላቸው የሀገር ውስጥ ምርቶች ለሚተኩና ወደ ውጭ ለሚልኩ አምራቾች የሰጠው ልዩ ትኩረትና ድጋፍ ይበልጥ ምርታማ እንዲሆኑ እንደረዳቸው ገልጸዋል።
በጉዟቸው ወቅት ያጋጥማቸው የነበረው የመብራት መቆራረጥ ችግር በኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ትኩረት አግኝቶ መፍትሔ ማኘቱን ያስታወሱት አቶ ፍጹም፤ የተፈጠረላቸው የገበያ ትስስርና የተዘጋጁት ባዛሮች ምርትን ከመሸጥ ባለፈ የደንበኞችን የምርት ፍላጎት በትክክል ለመለየትና ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለማቅረብ እንዳስቻላቸው ጠቁመዋል።
በቀጣይም የሀገር ውስጥ ገበያን ሙሉ በሙሉ ከመሸፈን ባሻገር የምርት ጥራትና ተወዳዳሪነት ላይ አተኩሮ በመሥራት ምርቶቹን ወደ ውጭ ሀገር ለመላክ ማቀዱን ድርጅቱ አስታውቋል።
የመስሪያ ቦታዎችን በማመቻቸት፣ ባዛርና ኤግዚቢሽኖችን በማዘጋጀት እንዲሁም የገበያ ትስስር በመፍጠር እየተደረገ ያለው አጠቃላይ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
ምንጭ: አዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ (https://www.facebook.com/share/p/1CPV8pppuj/)
#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!
ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡
https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment | 796 |
| 11 | Sin texto... | 771 |
| 12 | የውጭ ምንዛሬ ቋት፡ የኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን
ጥቅምት 16፣ 2019 ዓ.ም
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ጥገኛ ከመሆን ወደ ተዋቀረ የሀገር ውስጥ ምርት፣ ተወዳዳሪ የውጭ ንግድ እና ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጠራ በመሸጋገር የኢኮኖሚዋ ማዕከል እየሆነ መጥቷል።
በፖሊሲ እና በተቋማት አሠራር ማሻሻያዎች፣ እንደ «ኢትዮጵያ ታምርት» ባሉ ማዕቀፎች እየተመራ የሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ገጽታ ዕድገት አሳይቷል።
በኢትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ እና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ግንባር ቀደም ከሆኑት ምርቶች መካከል ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም የምግብና መጠጥ ምርቶች ይጠቀሳሉ።
በቅርብ ዓመታት በተለይም «ኢትዮጵያ ታምርት» ንቅናቄ እና በኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት የዘርፉ የወጪ ንግድ አፈጻጸም እያደገ የመጣ ሲሆን ባለፈው በጀት ዓመት ብቻ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው 607 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬ አስገኝቷል፡፡
ይህም የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ያከናወናቸውን ውጤታማ ሥራዎች እና ያስመዘገባቸውን ተጨባጭ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውጤቶች፤ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት፣ የውጭ ምንዛሬ ገቢን በማሳደግ እንዲሁም የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ያለውን ሚና ያሳያል፡፡
የሀገሪቱ ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ስትራቴጂ የውጭ ምንዛሬ ክምችትን ለማሳደግ ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎችን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ በሀገር ውስጥ አማራጮች መተካት ነው። ይህም የግብርና፣ የግንባታ፣ ሕክምና እንዲሁም ሌሎች ግብዓቶችን፣ ጨርቃጨርቅን እና የፍጆታ ዕቃዎችን ጭምር በሀገር ውስጥ አምራቾች የማምረት አቅም ፈጥሯል።
በሀገር ውስጥ በቅድሚያ መመረት የሚገባቸውን እና በውጭ ምርቶች ላይ ጥገኛ የሆኑ ዕቃዎችን በመለየት ክፍተቶችን መሙላት የሚያስችል አሠራር በመዘርጋቱ የሀገር ውስጥ ማምረቻ ኢንዱስትሪዎች በቢሊየኖች የሚቆጠር ዶላር ግምት ያላቸውን ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት ችለዋል።
በመዋቅራዊ ለውጦች እና የግል አጋርነቶች በተለያዩ የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች የሚመረቱ ምርቶች የውጭ ምርት ምትክ መሆን መቻላቸው እንዲሁም በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ዕቃዎች ከፍተኛ የገበያ ድርሻ መያዛቸው የምርት መጠን ማደጉን ብቻ ሳይሆን ሸማቾች በኢትዮጵያ ምርቶች ጥራት እና ጥንካሬ ላይ ያላቸው እምነት እየጨመረ መምጣቱን ያሳያል።
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎችን ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር ማቀናጀት ለዘላቂ ማክሮኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ወሳኝ ከመሆኑ ባሻገር የኢንዱስትሪ ዘርፉ የማኑፋክቸሪንግ ኤክስፖርት ገቢውን በማሳደግ በዓለም አቀፍ ገበያዎች ላይ ያላውን ተሳትፎ በዘላቂነት እያሳደገ ይገኛል።
ሀገሪቱ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን እና ኤክስፖርት ማቀነባበሪያ ማዕከላትን በመደገፍ ጥሬ ዕቃዎችን ብቻ ወደ ውጭ ከመላክ ይልቅ የግብርና ምርቶችን፣ ሌጦ እና ቆዳዎችን፣ እንዲሁም ማዕድናትን በሀገር ውስጥ በማቀነባበር የተሻለ ትርፍ ማስገኘት እንዲያስችል እሴት የመፍጠር አቅሟን እያሻሻለች ትገኛለች።
የማኑፋክቸሪንግ ደረጃዎች ከዓለም አቀፍ መመዘኛዎች ጋር በመጣጣማቸው፣ በኢትዮጵያ የተሠሩ አልባሳት፣ የግብርና ማቀነባበሪያ ምርቶች፣ እንዲሁም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በዓለም አቀፍ ገበያዎች ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አስችለዋል፡፡
በኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲሁም አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ለሀገሪቱ አምራች ኃይል ተግባራዊ የሥልጠና መድረክ በመሆን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው።
የግብርና-ኢንዱስትሪ ትስስር አነስተኛ አርሶ አደሮችን በቀጥታ ከኢንዱስትሪ እሴት ሰንሰለቶች ጋር በማገናኘት ለግብርና ጥሬ ዕቃዎች የተረጋጋ ገበያ ዋስትና ይሰጣል እንዲሁም ገቢን ያሳድጋል።
ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት፣ የኤክስፖርት አድማስን በማስፋፋት፣ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ገቢን በማስገኘት እንዲሁም ለሺዎች ሥራ ዕድል በመፍጠር የኢንዱስትሪ ዘርፉ በኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ራስን የመቻል እና የዘላቂ ብልጽግና ጉዞ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
#FMC
#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!
ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡
https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment | 709 |
| 13 | https://www.youtube.com/@ethiopiaenterprise
ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን እና ስራ ፈጠራን ይደግፋሉ? በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ተሰማርተዋል? ወይንስ ለመሰማራት አስበዋል?
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የዩቲዩብ ቻናልን በመቀላቀል የሀገራችንን አነስተኛ እና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች የስኬት ጉዞ ይከታተሉ!
ቻናላችንን Subscribe በማድረግ፡
· «የአምራች ሥነ-ልቦና» ፕሮግራሞችን እና የኢንተርፕራይዞችን የልምድ ልውውጥ ያገኛሉ
· አዳዲስ የቴክኖሎጂ፣ የፈጠራ እና የሙያ ዕውቀቶችን ይሸምታሉ!
· የሀገር ውስጥ አምራቾችን የስኬት ታሪክ በመመልከት ለራስዎ ተነሳሽነት ይፈጥራሉ!
· የሀገር ውስጥ ምርቶችን ያስተዋውቃሉ፤ አዳዲስ የገበያ እና የንግድ ትስስሮችን ይፈጥራሉ!
አሁኑኑ የዩቲዩብ ገጻችንን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
https://www.youtube.com/@ethiopiaenterprise
#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!
ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡
https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment | 1 086 |
| 14 | ኩል ፕላስ ፕላስቲክ ፋብሪካ፡ ከኬሚስትሪ ሳይንስ ምሩቅነት እስከ 80 ሚሊዮን ብር የኢንቨስትመንት ስኬት
=========////======
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኬሚስትሪ ሳይንስ ምሩቅ የሆነችው ሰላማዊት ቶማስ፣ በሻሸመኔ ከተማ በ80 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባውን "ኩል ፕላስ" የተሰኘ የፕላስቲክ ቧንቧ ማምረቻ ፋብሪካ እውን በማድረግ ወደ ሥራ ማስገባት ችላለች።
በሙያዋ በኬሚስትነት የሥራ ዓለምን የተቀላቀለችው ሰላማዊት፣ በትምህርቷና በአጭር ጊዜ የቅጥር ሥራዋ ያገኘችውን ልምድ መነሻ በማድረግ ለአካባቢውና ለሀገር የሚበጅ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ለመንደፍ በቅታለች።
ጥራት ያለው ለመጠጥ ውሃ፣ ለአግሮ ኢንዱስትሪ እና ለእርሻ መስኖ ሥራዎች የሚውል የፕላስቲክ ቧንቧ በብዛት የሚያመርት ፋብሪካ የመትከል ህልሟ እውን እንዲሆን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ያዘጋጀው የሥልጠና ፕሮግራም ትልቅ ዕድል ፈጥሮላታል።
ሰላማዊት በሥልጠናው ተሳትፋ የንግድ ሐሳብ ማፍለቅን፣ የፋይናንስ ምንጭ አያያዝና አስተዳደር ክህሎቶችን ከተገበየች በኋላ ያቀረበችው የፕሮጀክት እቅድ በባንኩ ተቀባይነት አግኝቶ መጽደቁ ተገልጻል።
በዚህም መሠረት ሥራ የጀመረው ኩል ፕላስ ፕላስቲክ ፋብሪካ በሰዓት 500 ኪሎ ግራም የፕላስቲክ ቱቦ የማምረት አቅም ያለው ሲሆን፣ በቀን ስምንት ሰዓት ብቻ እንኳን ቢሰራ በዓመት እስከ 1 ሺህ 200 ቶን ምርት ለገበያ ማቅረብ ያስችለዋል። ይህ ምርት ሀገሪቱ ከዚህ ቀደም ከውጭ የምታስገባውን መሰል ምርት በከፍተኛ ሁኔታ የሚተካና በዘርፉ የቴክኖሎጂ ሽግግር ያመጣ መሆኑ ተጠቅሷል።
በተጨማሪም ፋብሪካው ለ43 ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ ተረፈ ምርቱን መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውል ቴክኖሎጂ የሚጠቀም በመሆኑ ለአካባቢ ጥበቃም የበኩሉን ሚና እየተወጣ ይገኛል።
ኢንቨስተሯ ሰላማዊት ቶማስ «ድሮም ከሀገር ለሀገር ነው» በማለት መልእክቷን ያላተመች ሲሆን፣ ያለ ኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሥልጠናና የፋይናንስ ድጋፍ ይህን ታሪክ መጻፍ አዳጋች ይሆን እንደነበር አብራርታለች።
ምንጭ: የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት
#ለተጨማሪ_መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ!
https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment | 865 |
| 15 | Sin texto... | 889 |
| 16 | Sin texto... | 1 376 |
| 17 | የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የ2019 በጀት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የመደበኛ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ
EED ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም
የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ማኔጅመንት አባላት የ2019 በጀት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የመደበኛ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ አካሂደዋል፡፡
ውይይቱ በዋናነት በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የመደበኛ ስራዎች አፈጻጸም፣ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ ተጠሪ ተቋማት እና ክልልና ከተማ አስተዳደር የ2019 በጀት ዓመት የድጋፍና ክትትል ቼክሊስት እንዲሁም በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ አጀንዳውን አድርጓል፡፡
በውይይቱ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርን ጨምሮ የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ረቂቅ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም የበጀት ዓመቱ የሱፐርቪዥን ቼክሊስት ለአስተያየት ቀርቦ ጥልቅ ውይይት ተካሄዶበታል፡፡
በ2019 በጀት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከአምራች ኢንዱስትሪ ወጪ ምርቶች 118 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ እንደተገኘ ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ21.4 በመቶ ዕድገት እንዳለው ፣ ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካትም ከ1.3 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉ በሪፖርት ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከፕሮጀክት አፈጻጸም፣ ከመሰረተ ልማትና ፋይናንስ አቅርቦት፣ ከጥናትና ምርምር ስራዎች አንጻር የተሻለ አፈጻጸም እንዳለ የቀረቡ ሪፖርቶች አመላክተዋል፡፡
የበጀቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች የሚከናወንበት ቢሆንም በርካታ መደበኛ ስራዎችም እንደተሰሩ ሪፖርቱ አመላካች ነው ያሉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ (ዶ/ር) ለአብነትም ከኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከካፒታል ፕሮጀክት አፈጻጸም እና ሌሎችም አንጻር የተነሱት ተጠቃሽ ቢሆኑም አነስተኛ አፈጻጸም ባላቸው ግቦች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን እያጋጠሙት ያለውን ማነቆዎች በመፍታት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ያለውን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ግለቱን አስጠብቆ ማሰቀጠል ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በመረጃ ጥራት ፣ ታአማኒነት እና ወቅታዊነት፣ በአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በኮፕ-32 የተፈረሙ ውሳኔዎችን ተግባራዊ ማድረግ፣ በተቋማዊ ቅንጅት፣ በዲጂታላይዜሽን፣ በብሔራዊ አቅም ግንባታ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳይ ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት
#ለተጨማሪ_መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ!
https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment | 832 |
| 18 | Sin texto... | 11 |
| 19 | የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ለአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር ድጋፍ አደረገ
EED ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ለአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ፡፡
ተቋሙ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች እንዲቋቋሙ፣ እንዲያድጉና ተወዳዳሪ ሆነው እንዲጠናከሩ ከሚያደርገው ዋና ሀገራዊ ተልእኮው ጎን ለጎን፣ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት በኩልም የነቃ ተሳትፎ ሲያደርግ መቆየቱን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ትዕግስት ድጋፌ ገልጸዋል፡፡
ወ/ሮ ትዕግስት አክለውም እንደተናገሩት፤ የኢንተርፕራይዞች እድገትና ጥንካሬ ትርጉም የሚኖረው ማህበረሰቡን በሚጠቅሙና በሚደግፉ ስራዎች ሲታጀብ በመሆኑ፣ ልማት መሥሪያ ቤቱ ከተለያዩ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ጋር በመተባበር ድጋፍ ለሚሹ፣ ለችግር ለተጋለጡና አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
በዛሬው ዕለትም ከልማት መ/ቤቱ እና ከተለያዩ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች የተቀናጀ አስተዋጽኦ የተገኙትን ልዩ ልዩ ድጋፎች ለድርጅቱ ኃላፊዎች አስረክበዋል፡፡
ኢንተርፕራይዞች በአምራችነታቸውና በኢኮኖሚ ግንባታ ከሚያደርጉት አስተዋጽኦ ባሻገር፣ ማህበራዊ ችግሮችን በመቅረፍና አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ረገድ የሚያሳዩትን በጎ ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት
#ለተጨማሪ_መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ!
https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment | 925 |
| 20 | ዶ/ር አዲሱ ፈቃዱ የፋኦ (FAO) ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸነፉ
EED ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም
የሉሲ እንሰት መስራችና የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪው ዶክተር አዲሱ ፈቃዱ፣ በግብርና ምርምር እና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ የተባበሩት መንግሥታት የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) የስኬት ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል። ዶ/ር አዲሱ ሽልማታቸውን በጣሊያን ሮም በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው የዓለም የምግብ ቀን ሥነ-ሥርዓት ላይ ተረክበዋል።
ተመራማሪው ሽልማቱን ያገኙት በእንሰት ሰብል አመራረትና ማቀነባበር ላይ ባደረጉት የፈጠራ ጥናት ነው። ጥናታቸው የቆጮ ዝግጅትን በማዘመን ያለ አንዳች ግሉተን (Gluten-Free) በዱቄትና በኩኪስ መልክ ጥራቱን ጠብቆ እንዲዘጋጅ ያስቻለ ሲሆን፣ ይህም ለስኳር ታካሚዎችና ለጤና ተስማሚ በመሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የገበያ ተቀባይነት አግኝቷል።
ዶ/ር አዲሱ የምርምር ውጤታቸውን ወደ ተግባር በመቀየር በ440 ሺህ ብር ካፒታል የጀመሩት "ሉሲ እንሰት" ማኑፋክቸሪንግ፣ በአሁኑ ወቅት ካፒታሉን ወደ 16 ሚሊዮን ብር በማሳደግ ከ130 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጥሯል። በተጨማሪም ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሴቶችን ከባድ የሥራ ጫና ከመቀነስ ባለፈ ከ16 በላይ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን አግኝተዋል።
ዶ/ር አዲሱ አክለውም ወጣቶች ከቅጥር ይልቅ በዙሪያቸው ያሉትን ጸጋዎች በመለየት የራሳቸውን ሥራ በመፍጠር ለሀገራቸው እድገት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ መክረዋል።
#ኢትዮጵያ ታምርት፤ እኛም እንሸምት!
🔗ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይከተሉ፦
https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment | 960 |
