አትሮኖስ
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗ ║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣ ╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩ ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል። Contact @atronosebot please dont touch the leave button.😔😳😳
Больше📈 Аналитический обзор Telegram-канала አትሮኖስ
Канал አትሮኖስ (@atronosee) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 265 462 подписчиков, занимая 31 место в категории Книги и 37 место в регионе Эфиопия.
📊 Показатели аудитории и динамика
С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 265 462 подписчиков.
Согласно последним данным от 31 октября, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило -2 976, а за последние 24 часа — -507, при этом общий охват остаётся высоким.
- Статус верификации: Не верифицирован
- Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 0.06%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 0.27% реакций от общего числа подписчиков.
- Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 166 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 708 просмотров.
- Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 12.
📝 Описание и контентная политика
Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
“╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።
Contact @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳”
Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 01 ноября, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Книги.
Загружаем данные
| Дата | Привлечение подписчиков | Упоминания | Каналы | |
| 01 ноября | 0 |
| 2 | "ሰላም ነው ሲፈኔ በስራ ጉዳይ የማወራው ሰው አለ ወደዚያው ነኝ!"ብለው ፈጠን ብለው ሄዱ ሲፈን በረንዳው ላይ እንደቆመች፡ከግቢ እስኪወጡ ሸኘች እና ወደሳሎን ተመለሰች በውስጧ ብዙ ብዙ ነገር አመላለሰች የአባቷን ስራ የክንዴን ስራ የባለ ጭንብሉ ሁኔታ፡ሁሉም ነገር እንደ ትርሂት አይምሮዋ ውስጥ ተመላለሰ ምን ሆኖ ይሆን ሆስፒታል ውስጥ ግራ በመጋባት ተጨንቆ ተኝቶ ይሆን ፡የእክምናውን ወጪ ብከፍልም፡አንዳች ሳንቲም አልተውኩለትም ከሐኪም ቤት ቢያስወጡት ምን ይበላል ምንአይነት ሰው ነኝ ግን ምን አገባኝ ቅጣቱ ነው እንደውም እረድቼዋለው አይመለከተኝም እንዴዴዴዴ ትላለች በውስጧ ከራሷ ጋር እየተሟገተች፡
አቶ ይፍሩ ጓደኛቸው ይርጋን ቤታቸው ድረስ በመሄድ አገኟቸው በጣም ተናደዋል ብስጭታቸውን እንደደረሱ ነበር የዘረገፉት
"እንዴ ሰማህልኝ እኔ ሰሞኑን ሁሉ እንዴት ብለው ነው ልጁም ክንዴም ከመጋዘኑ የወጡት ምን አልባት ልጁን የላከው ሰው ይሆናል ይዞአቸው የተሰወረው እላለው፡ለካንስ እራሱ ክንዴ ነው ልጁን ይዞ ያመለጠው ይሄ ውሻ!"አሉ አዲሱ ዘበኛ የነገራቸውን አስታውሰው
"ማነገረህ ደሞ!"አሉ ይርጋ ግራ ተጋብተው
"ዘበኛው ሲሳይ!"
"ቆይ ቆይ እንዴት እንዴት ነው ነገሩ እስከዛሬ አልነገረህም ነው?!"አሉ ይርጋ በጥርጣሬ
"እህ ዝምብዬ ሳባብለው ነዋ በርግጥ አይቻለው በጓሮ በኩል ሲወጡ ነገር ግን ስለዛ በር የማውቀው ነገር አልነበረም የኛ ቤት አካል መሆኑን እንኳ ያወኩት ጊዜው ካለፈ በዋላነው ነገርግን አንድሰው ሌላውን ሰው ደግፎት ሲወጣ አይቻለውአለኝ!"
"አይገርምም እኔ አዲሱን ዘበኛ ጠርጥሬዋለው አባሪ እንዳይሆን!"አሉ ይርጋ
"እሺ አሁን ወደዋናው ጉዳይ ግባ የሱፍ እጁ አለበት ነበር ያልከኝ ምንድነው አልገባኝም ልታስደንቀኝ ነው ወይስ የሱፍ ከምር ከድቶናል ነው የምትል?!"
"አዎ አልኩህ ልጁ ባለጭንብሉ የአብዲ ጓደኛነው አሉ አይለኛ ለያዥ ያስቸገረ ዱርዬ በስርቆት የሚተዳደር እና ዘረፋውን እንዲ ያካይድ በየሱፍና በአብዲ ነው የተመረጠው ሰሞኑን የራሴን ሰው የሱፍን እንዲከታተሉ መድቤ ነበር እናም እውነቱ ይህ መሆኑን ደረሱበት!"አሉ ይርጋ በውስጣቸው ያሴሩትን አቶ የሱፍን የመጣል ተንኮላቸውን እያደሩ አቶ የሱፍ በየዋህነት የነገሯቸውን የልጄ ስራ ነው ያባለጭንብል ልጅ ያን ያህል ሰው የሚጎዳ አይደለም ገንዘብ ስላስፈለገው ብቻ ነው እንደው ለይፍሩ እንዴት እንደማስረዳው አላውቅም እስኪ አንተ አግዘኝ ብለው አማክረዋቸው ነበር አቶ የሱፍ ነገር ግን አቶ ይርጋ በዚህ አጋጣሚ አንዱን በአንዱ የመጣል ምኞታቸውን ለማሳካት ይፍሩን በየሱፍ ላይ አስነሱ አቶ ይፍሩ የበለጠ አበዱ በየሱፍ ላይም ዛቱ ብዙ ብዙ መከሩ ካቶ ይርጋ ጋር የሱፍን ለማጥፋት እገድለዋለው ይሄ ከሃዲ ..ሞት ባቶ የሱፍ ቤት ማንጃበብ ጀመረ..
======
አዳም ከቤቱ ወቶ ከቀረ አንድ ወር ሆነው እትዬ ፅጌ በልጃቸው አለመመለስ ምክንያት እንባቸው ፈሶ ፈሶ ያለቀ ይመስል በእንባቸው ፈንታ ብቻቸውን እያወሩ ወዲያ ወዲ ማለቱን ጀምረዋል በጠዋት ተነስተው የት እንደሚሄዱ ሳይናገሩ ወደ አመሻሹ ላይ ግርጥት ጉስቁል እንዳሉ ደካክመው ይመለሳሉ የቤቱን ስራ ኤዶም ሆኗል የሚሰራው አባትም በጠዋት ተነስተው፡ቤተክርስቲያን በመሄድ ልጃቸው እንዲመለስላቸው ለፈጣሪያቸው፡ልመናና ፀሎታቸውን አድርሰው፡ወደስራቸው ይሄዳሉ ኤዶም በተስፋ የወንድሙን መገኘት ያልማል ከዛም በላይ ደሞ የእናቱ ሁኔታ አሳስቦታል ወይኔ እማማ ሁሌም በኛ ምክንያት እንደ ፈንዲሻ ፍክት እንዳለች ነበር አሁን ግን ፊቷ የቀይ ጥቁር ሆኗል ሲቆይ ከዚም በላይ መሆንዋም አይቀር ይላል በጣም ፈርቷል ስለ እናቱ እማ ይበቃል ፈጣሪ ባለ ሰአት ይመጣል ብሎ ቢመክር አልሰማ ብለውታል፡ኤዶሜ ሁለታቹ እንደጆሮ ጌጥ ናቹ ለኔ ወርቆቼ ሕይወቴ ውበቴ ናቹ ለኔ በአንድ የጆሮ ጌጥ መዋብ ይቻላል?!ጎሎብኛል ኤዶሜ!አዳም ጎድሎብኛል እእእእእ ይላሉ በሰቀቀን ኤዶም ይጨነቃል የአዳም ቀልዱ ሳቁ ቤቱን ያደምቀው ነበር የኤዶም ዝምተኛነት የሚሸፈነው በአዳም ተጫዋችነት ነበር፡ አዳም አዳም የት ነህ .........?
=====
አቶ የሱፍ አቶ ይርጋን ካፌ ውስጥ ቁጭ ብለው እየጠበቁ ነው፡ ካፌው ብዙም ሰው ስላልበዛበት ተመችቷቸዋል ውስጣቸው ግን ተጨናንቋል ስለጓደኞቻቸው እምነታቸውን የበላው ይመስላቸው ይሆን ሌላ አይነት አሳብ አስቤ ያደረኩት እኔ መስያቸው ይነሱብኝ ይሆን ይርጋን እንኳ አሳምኜዋለው የሱ እዳው ገብስ ነው ችግሩ የይፍሩ ነገር ነው እንዲሁም መጀመሪያውኑ እየተጠራጠረን ነበር ጭራሽ ያ ባለ ጭንብል የልጄ የአብዲ ጓደኛ የሆነው አዳም መሆኑን ሲሰማ መቼም ሆነ ብዬ በድብቅ ላጠቃው እንዳሰብኩ ነው የሚሰማው መቼም በመጥፎ ስራ የተሳሰረ ሰው ሁሌም አይተማመን እንደው አንዴ ይርጋ ስለተፈጠረው ነገር ያስረዳልኝ እንጂ እኔም የሆነውን ነገር ለመንገር ይቀለኛል ከዛ ልጄን ስነስረሃት ማስያዝ አያቅተኝም እንደው ግን ልጁም ጠፍቷል እውነት እንዳለው ይሆንን ?እያሉ ከራሳቸው ጋር እያወሩ ሳለ አቶ ይርጋ ወደካፌው ገቡ
፡"ነዎር እንኳን ደና መጣህ ጓዴ!"አሉ የሱፍ
"በዝጌር እንኳን ደና ቆየኽኝ ጓዴ!"አሉ ይርጋ
"ስትቆይ ጊዜ ...."
"አይ እንደው ድንገት ሰው መቶ ብኝ የሆነ እቃ ፈልጎ እሱን ከመጋዘን ሳፈላልግ ነው የዘገየውት እንዴት ነህ የሰማኽው አዲስ ነገር አለ ከልጅህ አካባቢ?"አሉ ይርጋ
"ኧረ ምንም የለ ልጄ አዲስ ነገር ስለ ጓደኛው ቢሰማ ዝም የሚል ይመስልሃል ስለጓደኛው መጥፋት አሁንም ድረስ እንዳሳሰበው ነው፡ቢመጣ ማውራቱ ደስታውን ለኛ መንገሩ አይቀርም ነበር ኧረ እንዳውም እናቱ ትላንትና በየመንገዱ እያወራች ስትሄድ በመኪና ተከትያት ነበር በጣም ታሳዝናለች!!"አሉ የሱፍ ከንፈር እየመጠጡ
"ምን ይደረጋል ያልታደለች ለይፍሩ ሁሉን አጫውቼዋለው ያው ስለልጅህና ስለ ባለ ጭንብሉ ግንኙነት ያው ይፍሩ ታውቀዋለህ የዋህ ነው ትንሽ ቢናደድም ጥፋቱ ያንተ እንዳልሆነ ተረድቶ አል አታስብ፡ የበለጠ ቅዳሜ ተገናኝተን የበለጠ እንጫወታለን ብሎሃል፡ለማንኛውም ይደውልልሃል!"አሉ ይርጋ በሸፍጥ በውስጣቸው፡መቃብርህን እያስተካከለልህ ነው፡አሉ
"እሺ መቼም ጓደኛዬ እንዴት እንደማመሰግንህ አታውቅም!"አሉ የሱፍ በቅንነት ደስ እያላቸው
"ኧረባክህ አትጨነቅ የሱፍ ምንድነው ያን ያህል እሱን መፍራትህ ማነው እሱ እንዴ ጓደኞች ነን በቃ እኔ እንደው ዛሬ ብቻ አደለም ሁሌም ስመለከትህ፡ደርሰህ ይፍሩን የምታገነው ነገር አለ የዚን ያክልማ ቦታ አትስጠው !"አሉ ይርጋ ለየሱፍ የወገኑ በማስመሰል፡የተንኮል ድራቸውን እያደሩ
"አይ አይ መፍራት አደለም ጓደኛዬን ሁሌም አከብረዋለው፡ሁሌም የከዳውት እንዲመስለው ስለማልፈልግ ነው መልካም ግንኙነታችን በፀብ እንዲደመደም በጭራሽ አልፈልግም፡"አሉ የሱፍ የይርጋ አባባል እየገረማቸው
"ኧረ የምን ፀብ በል !ምን ስትል አሰብከው ፡ሁሌም ጓደኞች ነን !"አሉ ይርጋ
"እኔ የምልህ ይርጋ ግን ያ ልጅ እንደው እውነት አምልጦ ወጥቷል ነው የሚል ይፍሩ?"
"አዎን ምነው ትጠራጠራለህ !?"
"እንደው ግራ ቢገባኝ ነው!"
"ምኑ?"
"ልጁ ከጠፋ ለምን እስከዛሬ ወደቤቱ አልተመለሰም፡ብዬ ነው"
"ይፍሩ ያስወገደው ይመስልሃል?"
"ኧረ ያአላ ይቅር ይበልህ!እንዴ አያደርገውም!በዛላይ ቤተሰቡን አውቃቸዋለው ሰላምተኞቼ ናቸው፡ልጁም አዳምም የልጄ ጓደኛ ነው፡ኧረ ኧረ!!"አሉ የሱፍ ዝግንን እያላቸው
"አይ እንዳው ምን አልባት መጠርጠር አይከፋም በዛላይ እኔም ያልተዋጠልኝ ነገር አለ | 173 |
| 3 | #ባለ_ጭንብሉ
፡
፡
#ክፍል_አምስት
፡
፡
ሲፈን የዶክተሩን በር አንኳክታ ገባች ሰላም ብሎ እንድትቀመጥ ጋበዛት ሲፈን ተቀመጠች እና ዶክተሩን ምን ይሻላል በሚል አይነት ታስተውለው ጀመር
"ሲፈን ያው በቃ እንደነገርኩሽ ነው ምን ያህል እንደተጎዳ እኔም አንቺም እንዲሁ በግልፅ አይተናል ከሞት ለማትረፍ የተቻለንን ጥረት አድርገን እንዳየሺው ተሳክቶልን ሙሉ በሙሉ ጤንነቱን መልሰነዋል ነገር ግን በደብደባው ከባድነት የተነሳ የማስታወስ ችሎታውን ለጊዜው አቷል ምን አልባት ወደፊት የሚፈጠረው አይታወቅም ለጊዜው ግን ይሄንን ነው ያየነው አይዞሽ አትጨነቂ የሚፈጠረው አይታወቅም!"አለ ዶክተሩ
"ዶክተር በጣም ይከብዳል ብዙ የማታውቀው ነገረ አለ!"ብላ ደንገጥ አለች ለዶክተሩ የነገረችው በጣም ጓደኞች እንደሆኑና ምንም አይነት ቤተሰብ እንደሌለው ነው እሱም ብዙ አልተጫናትም
"ምንድነው የማላውቀው ሲፈን?"አለ ዶክተሩ
"አይ ማማለቴ እኔ በጣም እወደዋለው ሊረሳኝ አይገባም ፡"አለች
"ሲፈን ካጠገቡ ሳትርቂ ሁሌም ካገኘሽ ይላመድሻል "
"ግን "አለች ሲፈን ተወችው
"ይልቅ አሁን ሙሉ በሙሉ ስለነቃ ነይ ሄደን አብረን እንየው" ብሎ አስነስቷት አብረው ወደ ባለጭንብሉ ወጣት የተኛበት ክፍል ሄዱ ከክፍሉ ሲደርሱ ወጣቱ አዳም አልጋው ጫፍ ላይ ግራ በመጋባት ተቀምጧል፡
ዶክተሩ እንዳየው
"አሃ ነቅተሃል እንዴ?" አለው ለሰላምታ እጁን እየዘረጋለት
"አዎ ግን ምንድነው !ምን ሆኜ ነው እኔ ምንም ማስታወስ አልቻልኩም ፡ምንም ምንም !"አለ በጭንቀት ተወጥሮ
ሲፈን ጨነቃት ግራ ግብት አላት እኔ ነኝ የማውቀው ጓደኛው ብላለች ነገር ግን ስሙን እንኳ በጭራሽ አታውቀውም፡ የምታውቀውንስ እንዴት ብላ ትንገረው፡አንተ እቤታችን በውድቅት ለሊት ለመዝረፍ መጥተህ እኔንም የመድፈር ሙከራ አድርገህብኝ ነበር ከዛ ቤተሰቦቼ ያዙህ ከዛ አባቴ መጋዘን ውስጥ ቆልፎብህ ሲያስደበድብህ የማስታወስ ችሎታህን አጣህ፡ እያልኩ ነው የማቀውን የምነግረው ኧረ የማይሆነውን አለች
"አይዞህ ተረጋጋ የሆኑ ሰዎች የድብደባ ጥቃት አድርሰውብህ እሷ ናት ይዛህ የመጣችው "
"አሃ ማናቸው እና አልተያዙም በጭራሽ ምንም አላስታውስም ምንድነው ያረጉኝ ፡ "አለ አዳም በጭንቀት
"ያው ማጅራት መቺ ይሆናሉ ምንም አይነት መረጃ ከኪስህ ውስጥ አላገኘንም እንግዲ ሌቦች ቢሆኑ ነው ምንም ሳያስቀሩ የወሰዱብህ እንግዲ እሷ ስታገኝህ በደም ተጨማልቀህ እራስህን ስተህ ነበር ያው ባጋጣሚ የሁለታችሁም ጓደኛ የሆነ ሰው ነው እዛው ሰፈር አካባቢ ጠርቷት ያገኘችህና ይዛህ የመጣችው፡!!"
አለው ዶክተሩ ሲፈን የነገረችውን እያስታወሰ፡ ባለ ጭንብሉ ግራ ቢገባውም ይህችን የመሰለች ጓደኛ ስላለው አመሰገነ በቃ እሷ ስለኔ ካወቀች ቤቴ ትወስደኛለች ብሎ አሰበ መልሶ በውስጡ እንዴ ቤቴን አውቀዋለው አለ የቤቱ ስህል መጣለትና መልሶ ጠፋበት ወደ ሲፈን ተመለከተ በጣም ቆንጆ ናት የት ነው የማውቃት ጓደኝነታችን እስከምን ድረስ ይሆን፡ምንም ትዝ ሊለኝ አልቻለም
"ሲፈን ነው ስምሽ ?"
"አዎ ሲፈን ይፍሩ"
"እሺ ሲፈን ግን የት ነው የማውቅሽ?"
"ያው እንደ ማንኛውም ትውውቅ ነው የመጀመሪያ ትውውቃችን"አለች ሲፈን በገዛ እጇ አጣብቂኝ ውስጥ ገባች፡
"ማለት ?"
"ማለት ያው አንተ ነህ መተህ የተዋወከኝ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብዬ"አለች እንደመጣላት
ባለጭንብሉ አዳም ግራ ተጋባ ስለዚህም ትውስታውን ማምጣት አቃተው በጭራሽ አላስታወሰም በጣም ተናደደ አንዴት አንድ ነገር እንኳ አያስታውስም
"ዶክተር እባክህ በደንብ አክመኝ እና ከውጥረት ገላግለኝ !"አለ
"ስምህን ታስታውሳለ?"
"እእ እኔ እንጃ አላውቅም እእ"ሊመጣለት አልቻለም፡፡ዶክተሩ ሲፈንን ይዟት እራቅ በማለት "እኔ የምልሽ ምን ይሻላል ፡ቤቱን ታውቂው የለ ለምን አትወስጂውም ምን አልባት አንዳንድ ሁኔታዎች ትውስታውን ሊመልሱለት ይችላሉ !"
"እህህ እሺ ማለት አሁን ነው "ትብትብ እያለች መጀመሪያ ቤት ማዘጋጀት ነበረባት ፡"አዎ ሲፈን ከዚ በኋላ እዚ ምንም አይሰራም!!ደሞ እሱን እንጂ አንቺን አላልኩም፡እእ ማለቴ ደግመን ብብንገናኝ ደደስ ይለኛል ስለጓደኛሽም እናወራለን ስስለደረሰበት ሁኔታ ማማወቅ አለብኝ ብቻ አትርሺ ባለውለታሽ ነኝ ሻይ ቡና ብንል ችግር አለው?"አለ ዶክተር ሲፈንን ወዷታል፡ይህ ውበት በጭራሽ እንዲ ያመልጠው አልፈለገም የሲፈንና የወጣቱ ግንኙነት ቢያጠራጥረውም ሲፈንን ስለወደዳት አላስጨነቃትም እሷ በመሰላት የልጁን ጉዳይ እንድታስተካክለው ሆን ብሎ ነው የተወላት
ሲፈን ዶክተሩ ልጁን ውሰጂው ባላት መሰረት ለመውሰድ ፍቃደኛ ሆነች ግን የት ግራ ገባት ምንም አጠራጣሪ ነገር እንዳይኖር ፈልጋ ነበር እንዴት ግራ ተጋባች ቤት ይዤው ብሄድ ማሚና አባቢስ ተጨናነቀች በመጨረሻ በጣም የምትቀርባት ጓደኛዋ ላይ ተስፋ ጣለች ለጊዜው ሌሎች ውሸቶች እስክታዘጋጅ እናም ወደ ጓደኛዋ ደወለች አታነሳም ደጋግማ ደወለች በፍፁም ግራ ገባት አውቀዋለው ብላለች እሱም አንዳንድ ትውስታዎቹን ለማምጣት የምትረዳው እሷው ብቻ እንደሆነች አስቧል የገዛ ስሙን እንኳ ከሷ መስማት እንደሚፈልግ ገብቷታል፡ግን ስለሱ ምን ታውቃለች ምንም ጭንብል ለብሶ እላይዋላይ ሊሰፍር የተዘጋጀ ሰው እንደነበር ብቻነው በቃ ሌላምን ምንም !!!!! እረዥም ሰአት ቁጭ ብላ አሰበች አሰበች በመጨረሻ ውሳኔ ላይ ደረሰች ለዚ ወጣት ምንም ልነግረው የምችለው ነገር የለኝም ሕይወቱን አትርፌለታለው ከዚ ባለፈ ምን የሚያገባኝ ነገር አለ ስለምንድነው እዚ የተቀመጥኩት ብላ ተነሳች በፍጥነት መኪናዋን አስነስታ ተፈተለከች በልቧ ፈጣሪ ይርዳህ ምንም ላደርግልህ አልችልም ሲፈን ወደ ቤቷ ጉዞ ጀመረች .
========
አቶ ይፍሩ በጣም ተናደዋል፡ከሚገባው በላይ ጨስ ብለዋል፡የሚሆኑትን አተዋል እንዴት ክንዴ ባለጭንብሉን ይዞት ሸሸ ነው የሚባለው ኧረ እንዴት እንዴት ቢንቀኝ ነው ልጁን አስመልጦ እሱም የጠፋው ምን ተማምኖ እያሉ አበዱ ከወዲያ ወዲ እያሉ በቤት ውስጥ ተንጎራደዱ የልጆቻቸውን መሰብሰብ እንኳ ልብ ሳይሉ እነሱም በቀስታ ይንሾካሸካሉ፡
"ስሚ እሮዝ አባባ ቤቱን በእርምጃ እየለካው ነው እንዴ?!"
አለች ራሔል በሹክሹክታ ወደሮዛ ተጠግታ
"ኧረ እኔም ገርሞኛል እዚ ለዚ ባይመላለስ በቀጥታ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ከኮልፌ ፒያሳ ይደርስ ነበረ ፡!"አለች ሮዛም እያጋነነች
"እእህ ዳዲ ምንሼ ነው?!"አለች ሊያ ፡አባት ድንግጥ አሉ፡ሊያ የመጨረሻም ልጅ ስለሆነች ነው መሰል እንደልቧ ነው፡ንግግሯ
"ምን እእ ይቅርታ አንድ ቦታ ደርሼ ልምጣ ለእናታቹ እራት እንደምቆይ ንገሩልኝ እሺ!"ብለው ወደበሩ ሲያዘግሙ "ኧረ እንደፈራውት ዙረቱን በቀጥ ሊጀምረው ነው የስካሁኑ እቅድ ነበር ለካ !ሀሀሀሀሀ"አለች ራሔል እያሽካካች፡አባት ሳቋን ብቻ ነው የሰሙት፡ዝምብለው ወጡ ሲፈን ተከትላ በመውጣት
"ምንድነው አባቢ ችግር አለ?"አለች ባላወቀ ነገሩ ቢገባትም | 167 |
| 4 | 🚂 ሁሉም ሰው የራሱ ታሪክ አለው! ❤️
📖 አንድ አስተማሪ ታሪክ...
አንድ የ24 ዓመት ወጣት ከአባቱ ጋር በባቡር እየተጓዘ ነበር ከመስኮቱ ወደ ውጭ እየተመለከተ በታላቅ ደስታ ጮኸ
🗣️ «አባባ! ተመልከት! ዛፎቹ ወደ ኋላ እየሮጡ ነው!»
አባቱም በፍቅር ፈገግ አለ።
በአጠገባቸው የተቀመጡ አንድ ወጣት ባልና ሚስት ግን ይህን ሲመለከቱ በመገረም ተያዩ። የ24 ዓመት ወጣት እንደ ትንሽ ልጅ መደሰቱ እንግዳ መሰላቸው።
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወጣቱ እንደገና በደስታ ጮኸ
🗣️ «አባባ! ተመልከት! ደመናዎቹም ከእኛ ጋር አብረው እየሮጡ ነው!» ☁️
ባልና ሚስቱ መታገስ አቃታቸው። ወደ አዛውንቱ አባት ቀርበው
«ለምን ልጅዎን ጥሩ ዶክተር ጋር አይወስዱትም? እንደዚህ ያለ ባህሪ ለምን ያሳያል?» ብለው ጠየቁት
አዛውንቱ አባት በረጋ መንፈስ ፈገግ አሉና እንዲህ አሏቸው
💔«ዶክተር ጋር ወስጄው እኮ አሁን ነው የምንመጣው ልጄ ከተወለደ ጀምሮ ዓይነ ስውር ነበር። ዛሬ ግን ማየት የሚያስችሉትን ዓይኖች አግኝቷል»
😢 እነዚያ ባልና ሚስት የወጣቱን ባህሪ ከመፍረዳቸው በፊት ማወቅ የነበረባቸው ታሪክ ይህ ነበር!
📌 የሕይወት ትምህርት ❤️
በዚህች ዓለም ላይ የምታየው ሁሉ እውነት ሙሉ ምስል አይደለም።
እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ ታሪክ የማናውቀው ሕመም የማንረዳው ትግልና የማይታይ ስሜት አለው
❌ ከማወቅህ በፊት አትፍረድ!
❌ ከመረዳትህ በፊት አትተች!
❌ የሰውን ሁኔታ በላይ ላዩ ብቻ አይተህ የሕይወቱን ታሪክ እንደምታውቅ አታስብ!
✅ በምትችለው መጠን ሌሎችን ለመረዳት ጥረት አድርግ።
✅ በፍርድ ፈንታ ርኅራኄን፣ በትችት ፈንታ ደግነትን ምረጥ።
ምክንያቱም አንተ/ቺ የምታየው የሰውን ባህሪ ብቻ ነው፤ እሱ ግን የራሱን ታሪክ በሙሉ ያውቃል!
🔄ይህን መልዕክት ለወዳጅ ዘመደዎ ያጋሩ!
@atronosee | 530 |
| 5 | ምን እውነት ባይዘግብ
ሀሰት ቢደባልቅ፣
ኢቲቪ ታማኝ ነው
ከወንድ ልጅ ይልቅ
🔘እንደልቡ🔘 | 586 |
| 6 | ባደባባይ መሀል ሁሉን እወቁልኝ
የሜል ሰው ነበርኩኝ፣
መኖር ስጀምር ግን ያለኝን በሙሉ
መደበቅ ጀመርኩኝ
🔘አበባው🔘 | 565 |
| 7 | "ኧረ እውነቴን ነው በጓሮ አንድ ሰው ልክ እንደሰረቀሰው እየተጣደፈ ሲወጣ አይቼ ነው !"አለ መንገደኛው
"ምምን አይነት ሰው ?!"ሲፈን ሰውዬውን በድንጋጤ በጥያቄ አፋጠጠችው
"ኧረ ጎልማሳቢጤ ነው ሰውነቱ ደልደል ያለነው ጥቁር ፀጉሩ መለጥ ያለ!"አለ መንገደኛው ሰውዬውን ለመግለፅ እየሞከረ ፡
"በበየት በበኩል ነው ያያልከው?ወዴት ሄሄደ ?"ሲፈን ክንዴ ነው አለች በውስጧ ፡ወዲያው እነሱን ትታ እየከነፈች ወደጓሮው በር እሮጠች፡ ስትደርስ በጥድ የተሸፋፈነው በር እንደነበር ነው ወደዚ ከመጣች በጣም ብዙ ጊዜ ሆኗታል ምንስ ፍለጋ ትመጣለች ፡ሲፈን በሩን ገፋ ገፋ አደረገችው ብዙ አላስቸገራትም ወደውስጥ እየፈራች ገባች ሰውነቷ ሽብር ብሎባታል፡የመጋዘኑን ዙሪያ ቃኘች፡ አንዳች ነገር ተዘርሮ ያየች መሰላት፡ጨነቃት አፏ ደረቀ ለማረጋገጥ እየቀረበች እየቀረበች ሄደች ፡ሰው ነው በድንጋጤ አፋን ከፍታ ቀረች፡ባለጭንብሉ በፀጥታ ተዘርሯል፡ ሰውነቷ ተንቀጠቀጠ ቀዝቃዛ ላብ ከወደጀርባዋ ሲወርድ ተሰማት፡ ወደዋላዋ አፈገፈገች ሲሳይ ደርሶ ያዛት ፡ከዛም እሱም የወደቀውን ሰው አይቶ በድንጋጤ ክው ብሎ ወደሷ መልሶ በጥያቄ አስተዋላት ሲፈን ከሩቅ የሚመጣ ድምፅ በሚመስል
"ሞቶሃል "አለች
ሲሳይ ለቋት እየተንቀጠቀጠ ወደ ወጣቱ በመጠጋት ፊቱላይ ያለውን የሹራብ ጭንብል በማንሳት ትንፋሹን ለማዳመጥ ሞከረ ግራ ገባው መልሶ ወደአንገቱ አካባቢ እጁን ሰደደ
"ሕይወቱ አላለፈም አአለ ግግን መመፍጠን አአለብን ሐኪም ቤት መመሄድ አለበት!"አለ ሲሳይ
ዘበኛው
ሲፈን እንደባነነ ሰው ሆነች "እእውነት በበምን አወክ ?!"
"ትንሽ ጊዜ ወወታደር ቤት የቀሰምኳት ትምርት አለችኝ አሁን እሱ አደለም ዋናው ነገር መኪናሽን ይዘሻት ነይና ሐኪም ቤት እንውሰደው!"ሲፈን ደመነፍሷን እሮጠች መንገደኛው አካባቢው ሄዷል ጭር ብሏል መኪናዋን በፍጥነት ማንም ሳያያት አስነስታ መጣች እቤትም ገና አልተሰበሰቡም ጥሩ አጋጣሚ ሆነላት፡ ሲሳይ የተሰባበረውንና በደም የተጨማለቀውን የወጣቱን የከሳ ሰውነት ተሸክሞ መኪናውስጥ ማንም ሳያየው በጥንቃቄ አስገብቶ አስቀመጠው እናም ተከትሎ ሊገባ ሲል
"ቆይ ሲሳይ ይህን ጉዳይ በኔና አንተ ብቻ መሃል እንድንይዘው እፈልጋለው ማንም መስማት የለበትም አስታውስ የቤተሰቡ አካልም ሆነ ሌላ ማንም አደራ ይሄን የማደርገው ልጁን ለማዳን ነው፡ባለውለታዬ ነህ አደራ ስለዚህ አንተ ከግቢው መራቅ የለብህም ምንም እንዳልተፈጠረ ሁን አደራ እሱን ለኔ ተውልኝ ስለሁኔታው በሚስጥር አሳውቅሃለው !"ብላ ሲፈን ማረጋገጫ ሳጠብቅ የሰው ሕይወት ለማዳን መኪናዋን ይዛ ተፈተለከች ፡ብርርርርርርር ቢቢቢቢቢቢቢ ፍጥነት ሲፈን የባለ ጭንብሉ ሕይወት አደጋ ላይ ነው አባባ ....አባባ...ምንድነው ያደረከው.....ክንዴዴዴዴ...አባባባ========
ቤቱ በጠያቂ ተሞልቷል ሰው ሁሉ የየራሱን ግምት ይሰጣል አንዱ የአንዱን አሳብ ያፈርሳል አንዱ በአንዱ አሳብ ይስማማል በዛውም የራሱንም ግምት ይሰጣል አንዳንዱ ለማውራት ብቻ ብሎ እንደው እንደነገሩም አሳቡን የሚሰነዝርም አለ ብቻ የነ ኤዶም ቤት ሰሞኑን በትዬ ፅጌ ለቅሶ በመደናገጥ የሚሰበሰብ ሰው አላጣውም በቀን በማታ ልክ እንደ ሐዘን ቤት እንዴት ሆነ መልካም ዜና አለ አሁንም አልተገኘም ፖሊሶቹ ምን አሉ ምን ይሻላል አንዱ ጋር ገለው ጥለውት ይሆን ?የሴጣን ጆሮ ይደፈን ከአገር ወጥቶ ይሆን እንዴት አንድ መልእክት ሳይተው? አዬ እንደ እናት ጡት ሁለት ብቻ ሆነው ተፈጥረው አሄሄሄሄ በመሃል እትዬ ፅጌ ለቅሶ ይጀምራሉ ልጄ ልጄ እንደወጣህ ቅርት አልከው ኧረ ምን አየብኝ !ኧረ ወዴት ልፈልገው! ኧረ ምን ውስጥ አሰመጡህ ልጄ ልጄን አስራምስት ቀን ሙሉ ምንዋጠው ይባላል በሉ የበላው ጅብ አልጮህ አለ ኧረ እናንተው ምን ይሻለኛል እያሉ ያነቡታል ኤዶም የናቱን ድምፅ በሰማ ቁጥር እንባውን መቆጣጠር ያቅተዋል ወይኔ ወንድሜ ወይኔ የት ይሆን ያለኽው ከየት ላምጣህ ይላል በጭንቀት አባት ይሄ ነገር እንደቀልድ እውን ሆነ እንዴ ኧረ ዋ አዳም ምን አገኘብኝ እያሉ ያምሰለስላሉ በአዳም መጥፋት ቤተሰብ ሰፈር ጎረቤቱ ሁሉ ተጨንቆ ነው የሰነበተው....
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose | 607 |
| 8 | #ባለ_ጭንብሉ
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
ክንዴ ብረቱን መሬት ላይ በመጣል ቁና ቁና እየተነፈሰ ቁልቁል ወጣቱን እየተመለከተ እንቅስቃሴውን መጠባበቅ ጀመረ ድንገት የተፈጠረ የንዴት ስሜቱ እስኪበርድለት ትንሽ ጊዜ ወሰደበት እንዴት በልኩ በጄ ብቻ ጎሸም ባደረኩ ባዋራውት ሌባ መሆኑን እረስቶ ጭራሽ ከውሻ ይደምረኝ፡ይሄ ወፍ ዘራሽ እንዲህ ነውና ክንዴ ይሄ መደዴ አመዳም የማን አባቱ ወናፍ ነው በሉ የታባቱ ገና ልክህን ነው ማሳይህ ዱላ ቁርስ ምሳ እራትህ ያላደረኩልህ እንደው፡እኔ ክንዴ አይደለውም እያለ ዛተ ከዛም ብረቱን መልሶ አነሳው ወደ ባለጭንብሉ እግር በመክተት ቆስ ቆስ አደረገው እንቅስቃሴ የለም ወደ ሆዱ አካባቢ ነካካው የለም ክንዴ ደነገጠ ብረቱን ጣለው በርከክ ብሎ የባለጭንብሉን ፊት ከቀኝ ወደ ግራ ወዘወዘው ፀጥ እረጭ ብሏል ክንዴ ልቡ ክፉኛ በድንጋጤ መምታት ጀመረ
"አንተ ጭንብሌ አንተ !ንቃ ጭንብሌ !ኧረ ወይኔ ክንዴ !ኧረ ዋይ ጉድ ሆንኩ እንዴ !ስማማ ውሃ ውውሃ ተትፈልጋለህ! ጭንብሌ !ጭንብሌ!ጭንብሌ!ወይኔ ክንዴ ጉድ ፈላብህ ኧረ ኧረ ......." ክንዴ ሳያስበው መጮህ ጀመረ ፡ድንገት የሚመጣውን ችግር አስቦ አፉን ዘጋ ተርበተበተ ፡ቀጥ ብሎ ቆመ ግራ ተጋባ ወዴት ልሂድ ወዴት፡ለማን ልንገር፡ለአቶ ይፍሩ ልደውል፡ኧረ በጭራሽ ጠብቅ እንጂ ግደል አላሉኝ ኧረ እኔንም ያጠፉኛል ምላድርግ የሰውሰው በጄ ጠፍቷል የሰማዩም ይቅር አይለኝ እጄን ልስጥ እንዴ ክንዴ መጋዘን ውስጥ ተሽከረከረ እንዴት ብሎ ከገባበት አጣብቂኝ መውጣት እንዳለበት ግራ ገባው በመጨረሻ ፡ማምለጥ እንዳለበት ወሰነ ፡እናም በጎኑ የተኛውን ወጣት ለመጨረሻ ጊዜ ተመለከተው፡ የሹራብ ጭንብሉን ከወደቀበት በማንሳት ወደወጣቱ ቀረብ ብሎ ፊቱን ሸፈነለትና "ይቅር በለኝ !"ብሎ ዕንባ ዕንባ እያለው በጓሮ በር በኩል፡ ወጥቶ ሄደ ....ክንዴ ሄደ....ከራሱ ጋር እያወራ ሄደ ሄደ.....
=======
አቶ የሱፍ ከልጃቸው ጋር ፡በሱቃቸው ውስጥ ቁጭ ብለው ያወራሉ ወሬ አቸው ሁሉ ምክር አዘል ነው ያቶ የሱፍ፡ መግባራቸው ጥሩ ካልሆኑ ልጆች ጋር አትዋል ሁሌ ልጅነት የለም አንተነህ የኔ ንብረት ወራሽ ሌላ ማን አለኝ የመጀመሪያ ልጄ ነህ እኔ አንድ ነገር ቢገጥመኝ እናትህን እህቶችህን ጭምር አንተነህ የምትመራው፡ እኔ የምትቀርባቸው ልጆች ብዙም ደስ አይሉኝ ፡በተለይ ጀማል ከጥሩ ልጆች ጋር አላየውም እንደው አባቱ የተከበረ ሰው ነው ልጁን ግን ቀልቤ አይወደውም ፡ ምናምን ምናምን ፡አብዲ በሆዱ ይህ ምክር ግልባጭ ላንተ ቢደርስልኝ የተከበርከው አባቴ ከኔ ይልቅ ለራስህ ስነ መግባር በተጠነቀቅክ ብቻ አንተ በምትሰራው እገወጥ ስራ ወደፊት ምን እንደሚደርሰን ሳስበው፡ ይጨንቀኛል እንደው አባባ ምን ስትል ነው እነዛን እገወጦች ጓደኛ ያደረከው አንተ እራስህ አላህ እማይወደውን ስራ እየሰራህ እኔን መምከርህ ከነ ጓደኞችህ ወንጀለኛ ነህ አባባ ይላል አብዲ
"አብዱ እንደው ባለፈው መጋዘን ስለገቡት እቃዎች ከሰዎች ጋር አውርተህ ነበር ?"አሉ አቶ የሱፍ በመጠራጠር
"አላወራውም፡እኔ አባባ አንተም ሆንክ ጓደኞችህ ስለምትሰሩት የተለያየ እገወጥ ስራ አይመለከተኝም አላህን ካልፈራቹ ቀጥሉበት እሱ ይከፍላችሃል!"አለ አብዲ የአባቱ አይን ያወጣ ንግግር እያናደደው
"ምን አልክ አንተ የምን እገወጥ ነው የምትለው ፡አንተ የማትረባ ፡አቶ ይፍሩ የተከበረ ሰው ነው እድሜ ለሱ ይህን ሁሉ አብት ያፈራውት ከሱ በመሻረኬ ነው ፡ይርጋም ቢሆን!እንዴት አባክ ነው ምትናገረኝ አባትህ እኮነኝ፡ተንደላቀህ በመኖርህ ጥጋብ ፈላብህ!"አሉ አቶየሱፍ እንደመነሳት ብለው
"አሁን እየጠየኩህ ያለውት መጋዘን ሄደህ አስተካክል ያልኩህ ጊዜ ከማን አባክ ጋር ነው የሄድከው ዘበኛው ጓደኛው አብሮት ነበር ብሎኛል ይዘህው ከሄድከው ልጅ ጋር በእቃው ጉዳይ ላይ አውርተሃል?!"አሉ እጃቸውን ለዱላ እንደማዘጋጀት እያሉ
"ምንድነው ዛሬ ስላለፈ የመጋዘን እቃ ዛሬ የምጠየቀው አልገባኝም ችግር አለ ፡እገወጥ እና ጊዜው ያለፈበት መሆኑ ታወቀ ፡ምንድነው፡ስለሱ ይህን ያህል፡ ሌላ ብዙ ስራ ነበራቹ ለምን ስለሱ ብቻ!?"ቱግ አለ አብዲ
"አፈር ብላ ማንን ነው ይዘህ የሄድከው የዛኔ!"በጥፊ አላሱት
"ከ አዳም ጋር ነው የሄድኩት !" አለ አብዲ በንዴት
"ማን አባክ ነው አዳም!"
"እታች ሰፈር ያለው !"
"ማነው እሱ እታች ሰፈር ስንት ሰው አለ የማን ልጅ ነው!?"
"ምንድነው ከመጋዘን የጠፋ እቃ አለ እንዴ እንዳለ አደል እንዴ ወዲያው የተሸጠው ፡ድርሻችሁን ተካፍላችዋል ምንድነው ፡የምትለኝ ፡እሱ አብሮኝ ሄደ እንጂ ምንም የሚያውቀው ጉዳይ የለም፡ ችግር ስላለባቹ ያገኛችሁትን ከመጠርጠር ወደዋላ አትሉም!"አለ አብዲ በቁጭት
"አንተ አህያ የጠየኩህን መልስ!ማነው አዳም?!"
"የአቶ ሀይሉ ልጅ !"
"ሀይሉ ሀይሉ"አሉ አቶ የሱፍ ለማስታወስ እየሞከሩ "ሀይሉ የወይዘሮ ፅጌ ባለቤት!በቃ የትዬ ፅጌልጅ ከመንታዎቹ አንዱ ነው በጣም ጥሩ ስነ መግባር አላቸው ስትለኝ ነበር እንግዲ ባንተ አሳብ መሰረት ከነጀማል ጋር ትቼ ከመንትዮቹ ጋር ጓደኛ ሆኛለው አሁን ደስ አለህ!?"በትህቢት እና በንቀት አባቱን እያየ ተነፈሰ አብዲ
"በአላህ አንተ ምን እያልክ ነው ?!
"አሉ አቶ የሱፍ
"በቃ እንደዛ ነው እንደውም ሰሞኑን አዳም ጠፍቶ እየፈለግነው ነው የሰነበት ነው፡ እንኳን ስለናንተ መጋዘን ቁብ ሊኖረው ቀርቶ!"አለ አብዲ የአባቱ ባልሆነ ነገር እራሳቸውን ችግር ውስጥ ማስገባታቸው እያሳመመው 'እባክህ አባቴን ከገባበት ችግር አውጣው ፈጣሪዬ
አቶ የሱፍ በሰሙት ነገር ክፉኛ ደነገጡ ያ አላህ ይፍሩ አሰርኩ የሚለው ልጅ አዳም እንዳይሆን ብቻ ኧረ ጉድ ሆኛለው አብዲ አብዲ ምን አይነት የልጅ ክፉ ሰጠኽኝ በቃ ስለኛ ጓደኛ አገኘው ብሎ ልጄ ያለውን ነገር እንዳለ ዘርግፎለታል ማለት ነው ወይ ጉዴ ባለ ጭንብሉ አዳም ከሆነ ይፍሩ ለኔም አይተኛልኝ ሆነ ብዬ እንዳደረኩት ነው የሚሰማው ጉድ ፈላብኝ ፡ግን ጥርጣሬ እንጂ ላይሆንም ይችላል"ምነው አባ የፈራህ ትመስላለህ አዳም እኮ ዱርዬ አይደለም እንዴ ምንድነው ይሄን ያህል!" አለ አብዲ ቢናደድባቸውም ትካዜአቸው አሳስቦት ፡፡አቶ የሱፍ ጥሩ ስሜት አልተሰማቸውም ወደወንበራቸው ተመልሰው ሽብሽብ እንደማለት ብለው ተቀመጡ ስቅቅ ጭንቅ ጭንቅንቅ አሉ አቶ የሱፍ ፍርሃት ...ፍርሃት.....ፍርሃት......
=========
አዲሱ ዘበኛ መንገደኛው ሰው የነገረውን ወሬ ተከትሎ የግቢውን አጥር ዞረው ምንም አይነት ፍንጭ ማግኘት አልቻለም ፡ምኑ ሰካራም ነው እያለ ወደቦታው ተመለሰ ሲመለስ ሰውዬውን የጊቢው በር አካባቢ እንደቆመ አየው ኧረረረ ምን አባቱ ነው እኔን አዘናግቶ ወደውስጥ ለመግባት ይሆን እንዴ አላማው !አለመጠርጠሬ ብሎ ዱላውን እያስተካከለ ተጠጋው
"አሃ ምን አስበህ ነው በል ዱላህን ሰብሰብ አድርገው እኔ የረዳውህ መስሎኝ እንጂ !"አለው መንገደኛው እንደመሽሽ እያለ
"ምን ትረዳኛለህ ዘዴ መፍጠርህ ነው ባንተቤት ዞርበል ከዚ እወርድብሃለው !"አለ ዘበኛው እየጮኽበት በዚ መሃል ሲፈን መጣች በጣም ተደናገጠች የሰሞኑ ሁኔታ እያስፈራራት ነው ያለው ይሄ ሲጨመር ቀጥታ አያያዘችው፡ እናም ወደዘበኛው እጇን እያወናጨፈች እንዳያደርገው አስጠነቀቀች
"ምንድነው ሲሳይ ምነካህ ችግር አለ?!"ጠየቀች ሲፈን ሰውዬውን እየተከላከለችለት
"ኧረ በጓሮ ሰው ሲወጣ አየው ብሎ ሊያዘናጋኝ ሞከረ ምን እንደፈለገ አልገባኝም!"ቆጣ አለ ዘበኛው | 592 |
| 9 | ✔️የጠንቋይ ልጅ
ከልጆች ጋር ስጣላ «የጠንቋይ ልጅ» እያሉኝ እየሰደቡኝ ነው ያደኩት። አካባቢያችን ያሉ ልጆች እኛ ቤት እንዲመጡ አይፈቀድላቸውም። ወላጆቻቸው ልጆቻቸውን ከእኛ ቤት አካባቢ ያርቁ ነበር።
ልጆቻቸውን ከኛ የሚያርቁ ወላጆች እኛ ቤት ሰው አየኝ አላየኝ እያሉ ይውላሉ፤ ይንከባለላሉ። እናታችንን «በእርሶ መጀን እማማ» እያሉ ደጅ ይጠናሉ።
በድብቅ እየሰገዱ በቀን ብርሃን ማጣጣል ምን ይባላል????
ብዙ ጊዜ አይቼዋለሁ፤ «ከባሌ ጋር ሰላም ሆንን፣ ጤናዬ ተሻሻለ፣ እቅዴ ተሳካ» እያሉ ገብስማ ዶሮ እና ጥቁር በግ እጅ መንሻ የሚያመጡልን ጎረቤቶች ነፍፍፍ ናቸው፤ በአደባባይ ግን ጠንቋይ እንደሚጠየፉ ይዘበዝባሉ። ጠንቋይ ያጣጥላሉ፤ ጋብቻ ይከለክላሉ። በዚህ መጠን ከተጠየፉት ለምን እቤታችን መጥተው ይሰግዳሉ??
ይሄ ከልጅነቴ ጀምሮ የታዘብኩት ሃቅ ነው።
ቆይቶ ሲገባኝ ሴተኛ አዳሪዋን የሚያንቆሽሽ ወንድ አዳሪው ብዙ ነው ሌባ ባለስልጣንን ደምስሩ እስኪገተር አውግዞ፣ እጁ እስኪደክም ፅፎ የሞገተ በሱ ቦታ ስልጣን ሲይዝ ካወገዘው በላይ ሞላጫ ሌባ ይሆናል።
ይህ በአደባባይ የቅድስና ጭንብል አድርጎ በድብቅ የመንበርከክ በሽታ «ግብዝነት» (Hypocrisy) ይባላል!
የሰው ልጅ የራሱን ድክመትና ፍላጎት ለመሸፈን ሲል በአደባባይ ሌላውን ቀድሞ ያወግዛል። ነገር ግን ችግርና ጭንቅ ሲመጣ ያንን የማህበራዊ ሽፋን አውልቆ በድብቅ በር ላይ ይሰለፋል።
ትዝብት=እስከመቼ በድብቅ የምናደንቀውን እና የምናገዝፈውን በአደባባይ እናወግዛለን???
✍ አድሀኖም
🔄 ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ!
📌 ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ @atronosee | 812 |
| 10 | ስትሄጂ ስትርቂኝ 'በኔው አመል ማጣት
ያልኩሽ ይሄን ነበር
መቼም ትዝ አትዪኝ አትናፍቂኝ ቅንጣት፡፡
:
:
ቀናቶች አለፉ
ወራት ረገፉ
አንዲት ሴት ተዋወቅሁ ምትስቅ ያለ ድንበር
በእርሷ ሳቅ መሀል ግን
እኔ ሚናፍቀኝ ያንቺ ቁጣ ነበር ። | 896 |
| 11 | #በጣት\_መሳም
እሰይ አጎረስኳት፡ በሰበቡ ከንፈሯን ነካሁ በከንፈሬም ባይሆንልኝ፡ በጣቶቼ ጣሟ ለካሁ።
እሳት ናት ታቃጥላለች
ጣዝማ ናት ማር ማር ትላለች
ጠበል ናት ትፈውሳለች።
ፈገግ ብትል ጊዜ፡ ደግሞ እንደመሽኮርመም
ድኛለሁ ምኔን ልታመም?
ገነትን ነክቼ፡ በከንፈሯ በኩል
በዘላለም አመንኩ፡ ከባህታዊ እኩል፡፡😳 | 920 |
| 12 | "ማለቴ የዘንድሮ ልጆች ደረቆች ናቸው ለምን ጠንካራ መሆን እንዳለባቸው እንኳ ጠንቅቀው አያውቁትም ዋላ ሰበብ እንዳይሆንብህ "አሉ ይርጋ የጓደኛቸውን አይበገሬነት ቢያውቁትም እንደው ለማለት ያህል የሁለቱንም ንግግር ሲሰሙ ቆይተው አቶ የሱፍ የሃይላንድ ውሃቸውን ጥጥት አደረጉና
"እንደኔ እንደኔ ይህ ልጅ ኩርኩም ብቻ ነበር የሚያስፈልገው እንደው ልምድም ያለው ሌባ አይመስለኝም እንደው ስራ አልሆን ሲለው አሳቡን ቀይሮ በዚ ካለፈልኝ ብሎ ይመስለኛል፡" አሉ
"እሱ ግን አሁን እናንተ እንደምትሉት አይደለም ሁኔታው፡!"አሉ አቶ ይፍሩ
አሳስቧቸዋል እንዴት አድርገው ነው የሚያውጣጡት በምን መልኩ ይህን ልጅ አንድ ነገር ቢያረጉት የላከው ሰው ኖሮ የበለጠ ጉዳዩ ቢከርስ ከየት ነው የመጣብኝ ?...
===
ሲፈን ቤት ውስጥ ከናቷ ጋር ተቀምጣ ታወራለች፡ሰሞኑን ሁሉ ባለጭንብሉን ካየችበት ቀን ጀምሮ ተረብሻለች፡ ያ ሊደፍራት የታገላትን ሁኔታ ሁሉ ላለማስታወስ ጥራለች ፡ከዛ የበለጠ ግን እያሳሰባት ያለው፡ አባቷ ልጁን በትክክል እንዳሉት ለቀውት ይሆን ወይ የሚለው ነው፡አባባ የዛን ያክል ተናዶ እንዴት ነው እንደተራ ነገር በቃ አንተ ባለጌ ወደቤትህ ሂድ እንደማለት አይነት የሚሸኙት ምንም አልተዋጠላትም እናትም በዚ ጉዳይ እርግጠኛ አደሉም ግን ክፉ ነገር እሰከሚያደርሱበት ሳይሆን የሚገባውን ቅጣት ሰጥተው እንደሚለቁት ነው የተሰማቸው
"እማ ይመስልሻል፡አባባ እንዲ በቀላሉ የሚተወው ?
"የኔ ቆንጆ አባትሽን ክፉኛ መጠርጠርሽ ተገቢ አይደለም !ምን ያደርገዋል ብለሽ ነው፡እኔ አባትሽ ሲገባ አይቼዋለው ከመናደዱ በስተቀር የተለየ ነገር እንዳረገ ሰው አልነበረም፡ሲፈኔ ተይ፡በቃ እርሺ ስለዚ ነገር!"
"እማ አዎ ልጁ ችኩል ቢጤ ነበር እሱ አይካድም ፡ግን እስከሞት የሚያደርስ ቅጣት ይገባዋል፡ብሎ ውስጤ በፍፁም ሊነግረኝ አልቻለም፡እማዬ እኔ ጭንብሉን ሳወልቅበት ያየውት ፊት እንደው በድፍረት ተነሳስቶ እንጂ ልምድም ያለው አይመስለኝም!" አለች ሲፈን
"እንዴ አባትሽ ነብሰ ገዳይ መስሎ ታየሽ እንዴ!?ደሞ ሊደፍርሽ ለነበረ አንድ ዱርዬ የምን መራራት ነው ፡ምንድነው ነገርሽ ከዚ በፊት እንደሚያውቀው ሁሉ የምትሆኚው ምን አገባሽ!"የሮዛ እናት ቱግ አሉ
"እማዬ እኔ ስለማውቀው ስለማላውቀው አደለም፡ እሱ እንደ ደፋሪም አይደለም እኔነኝ በመታገሌ ለፀብ ያነሳሳውት !"አለች ሲፈን ግራ በገባው እኔታ
"እሰይ አሁን ገና ጉድ መጣ!አጥር ዘሎ ውሾች ገሎ ቤትሽ ድረስ ገብቶ በላይሽ ሊሰፍር የነበረው ለፍቅር ነበር እንዴ ሆሆሆ ምን እያልሽ ነው?"
"እማዬ እኔ በርግጥ ጥፋተኛ አይደለም እያልኩሽ አይደለም፡ልጁ ግን አጋጣሚ ሆኖ እነጂ ለኔ ብሎ አይደለም የመጣው ፡ለዘረፋ ነው በቃ!"
"እንግዲ ዘረፋው አንቺንም ያካተተ ነበር አፍኖ በርሽን ዘግቶት ነበር!"
"አዎ እማዬ አሁን ስለተፈጠረው ነገር አይደለም ፡ስለ ባለጭንብሉ ልጅ ነው በሕይወት ነው ወይ የተለቀቀው እሱን ማወቅ እፈልጋለው!"አለች ሲፈን ቁርጥ ባለ ቃል
"እሺ ይፍሩ ገድሎታል ነው አሳብሽ፡ምንድነው አንቺ ልጅ?!"ቆጣ ብለው
"እሱን አላልኩሽም፡ግን ትክክል የሆነ ነገር እየሸተተኝ አይደለም !"አለች ሲፈን ፊቷን ቅጭም አድርጋ
"እንግዲያው ይሄን ሽታ የፈጠረብሽ ያ በሽተኛ ልጅ ነውና እንፍ ብለሽ አስወግጂው፡አባትሽንም ያለ አግባብ መጠርጠርሽንም አቁሚ !"
"ምክንያት አለኝ !"
"ደሞ ምንድነው ምክንያትሽ ?"ተናደዱም ደነገጡም
"ክንዴ ከዛን ለት ጀምሮ በጭራሽ አላየውትም ፡ድንገት ስራውን ለቀቀ ተባለ ፡መቶ እንኳ አልተሰናበተንም ሲሄድም አላየነው ፡ወዲያው ወደማታ ሌላ ዘበኛ ተቀጠረ !እንደገና የዛን ለት ማታ ልብ አላልሽ እንደው እንጂ አባባ ልብሱ ደም ነበረበት እጁ እስካሁን ቆስሏል በመጠኑም ቢሆን እኔ ስገምት ልጁ አንዳች ነገር ሆኗል ክንዴ ደሞ ያውቃል ስለዚ የሱ እዚ መኖር አስፈላጊ አይደለም ለምን አይታይሽም እማ፡አባባ ልክ አይደለም ችግር ውስጥ ነው!!"አለች ሲፈን ውስጧ ያለውን እየተነፈሰች
"አንቺ ልጅ እንግዲያው ምንም ቢፈጠር አይመለከተንም፡ ማንም ሰው የሰው ቤት በውድቅት ሊት ሰብሮ ሲገባ የማባበል ግዴታም የለብንም ፡ይሄ ድፍረት ነው፡የተከበረ ቤት ነው መሪ ያለው ፡ይፍሩን የመሰለ አባወራ ያለው ምነካት ልጅቷ አጉል ሚዛናዊነትሽ አልተዋጠልኝም !"
"ኧረ እማዬ፡ይህ ልጅ እንደኛ ወላጅ ይኖረዋል
"ምን ዋጋ አለው ወላጅ ሁሉ ወላጅ ነው እንዴ ?
"እማ ከመቼ ጀምሮ ነው ጨካኝ የሆንሺው?"
ሮዛ፡ወደውስጥ ድንገት ገባች"እእ ማሚን ጨካኝ ሲፍ ማሚን?ይሄኔ ለፍራንክ ብለሽ እኮ ነው!?"አለቻት ሲፈን ደንገጥ ብላ ወሬዋን አቋረጠች ቀስ እያለም ቤቱ በቆነጃጂቶች ደመቀ አራቱም እህታማቾች እየተቀላለዱ ማሽካካት ጀመሩ ካካካካካ"....
=====
ክንዴ የመረረው ይመስላል ይህን ልጅ ሲጠብቅ ሳምንት አለፈው አቶ ይፍሩ ለማየት የቀፈፋቸው ይመስል፡ወደዚም ድርሽ አይሉ ብቻ አሳባቸውን በስልክ ማስተላለፍ ብቻ ትንሽ ምግብ ስጠው ውሃ ስጠው ጎሸም እያደረክ ማን እንደላከው አውጣጣው ፡እምቢ ካለ እንዳይሞት እንዳይሽር አድርገህ ግረፈው 'እንዴ እኔ ደከመኝ አሁንስ እኔ እራሱ እየተደበደብኩ መሰለኝ ኧረ ክንዴ እሱ በዱላ ያደገ ይመስል አይሰማው ደነዝ ኧረ ሰለቸኝ !ይላል ክንዴ እጁን እያሻሸ
"ስማ ጭንብሌ እኔ የምለው ሰው ነህ እንዴ? እንደው ምን አለበት ማን እንደላከህ ተናግረህ፡አቶ ይፍሩም ሌላ ተደብዳቢ ቢያመጡ፡አንተም ከዚ በዋላ በዱላ ብዛት መልክህ ከሚጠፋ ባይጠፋ!እኔም ሌላ ተደብዳቢ እስኪመጣ እረፍት እንድወስድ ብትረዳኝ፡ኧረ ባክህ ባክህ!!" አለ ክንዴ እንደማሾፍ እንደመናደድም ብሎ ወጣቱ ያባበጠ ፊቱ የሸፈነበትን አይኑን በስቃይ እያቁለጨለጨ
"ማንም አላከኝም አልኩ እኮ እእ ግግን አአንተ ከጌታህ የየበለጠ መጥፎ ሰው ነህ የማይገባህ እራሴ ነኘ የየራሴ አዛዥ አልኩ እኮ አንተ ባባሪያ ለለፍርፋሪ ብብለህ ነነብሴን ልልታወጣኝ ነው ከከውሾቹ ጋጋር በበገደልኩህ ሰሰው መስለኽ......"ባለጭንብሉ ተናግሮ ሳይጨርስ ክንዴ ተነስቶ በፍጥነት አቶ ይፍሩ በመቱት ብረት አናቱ ላይ ሰነዘረበት !ባለጭንብሉ ከዱላው አይለኝነት የተነሳ ከመሬቱጋር ተጋጨ ፡አይኖቹ ብዥዥዥ .....ጭልምልም መሞቴ ነው እንዴ አለ በሰመመን ውስጥ እናቱ ወይዘሮ ፅጌ ታዩት ወፍራም ቀይ ፊታቸው ሲፀይም እማማ እማማ ይቅርታ እእእአባዬ አባዬ ዳመና የጋረደው መሰለው ፀጥጥጥ ጥቁርቁር ........
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose | 879 |
| 13 | #ጭንብሉ
፡
፡
#ክፍል_ሶስት
፡
....ዘበኛው ባለ ጭንብሉን ደጋግሞ አጠገቡ እየመጣ መንቃት አለመንቃቱን ያረጋግጣል፡በእግሩም ነካ ነካ ያደርገዋል፡ወጣቱ ያለምንም ድምፅ ፀጥ እንዳለ ነው፡ዘበኛው፡ሆሆሆ እሬሳ ስጠብቅ እያመሸው ላንጋ እንዴ፡አቶ ይፍሩ ግን ግፋቸው፡ከልክ ያልፋል፡አሁን ይሄን እሬሳ ከምጠብቅ ፡እነዛን ቆነጃጂቶች፡ በሄዱበት፡እየሄድኩ ብጠብቅ፡ብሎ ለራሱ ፈገግ አለ ፡ መልሶ ወደ ወጣቱ ጠጋ ብሎ ትንፋሹን አዳመጠ አለ በሕይወት አለ ግን ባይኖር ይሻላል በድመት የተያዘች አይጥ ነው ነገሩ 'አቶ ይፍሩ እንደው መቼም ከዚ ጊቢ በሕይወት አያስወጡትም እኔም ፈርዶብኝ ቅበር መባሌ አይቀር አሄሄ እኔ ለራሴ! እያለ ዘበኛው ብቻውን ይለፈልፋል ሰአቱ ይነጉዳል ባለ ጭንብሉ እንደ ተጋደመ ነው ዘበኛው ብዙ ሲጠብቅ ስለቆየ ሰለቸው እንቅልፍ እንቅልፍ ሲለው ወደ ወጣቱ ቀረብ ብሎ እጁን ያሰረበትን ገመድ ድጋሚ አጠባበቀው እናም ፈንጠር ብሎ ተቀመጠ ብዙ ነገር አመላለሰ በሃሳቡ እንደው ይህ ልጅ ምን ፍለጋ ነው ከዚ የመጣ? ገንዘብ ፈልጎ ይሆን ወይስ ቆንጆዎቹን ኧረ እዲያ እቴ ደሞ አገር ምድሩን በሞላ ቆንጆ ምን ይሁነኝ ብሎ ነው እንደ መጋኛ በለሊት የሚመጣ አያደረገውም! እንደው ሌላስ አላማ ኖሮት ቢሆን አቶ ይፍሩ ማነው የላከህ ብለውትም አደለ ፡አሃ ምናልባት እሳቸውን ሊገድል ይሆን እንዴ' ኧረ ! ትልቅ ሰው ይገደላል !እንደው ምን አይነቱ ደፋር ነው፡እንደው ምናምኒይቱን አጭሶት ይሆን እንዴ እንዲ የጀገነው፡ ድንገት ከአሳቡ ተናጠበ
"እእ ውሃ እባካቹ ው..ሃ"አለ ባለጭንብሉ እንደመንቃት እያለ እና ሊወድቅ የደረሰ የመሰለውን ጭንቅላቱን በታሰረው እጁ ለመንካት እየጣረ
"አሃ አንተ ሞት እምቢ ነቃህ፡!"ብሎ ዘበኛው ውሃ ይዞ ተጠጋው ፡"እሺ እኔው ላጠጣህ መሰል አንተማ አቅሙን ከየት አምጥተኽው ጎበዝ ምን ልበልህ ቸገረኝ!"ብሎ እያለመጠ ውሃውን አጠጣው፡እናም እየጠጣ አቋረጠበት
"አሃ ፍጆታ የሚባል ነገር አለ ወንድሜ! አለው፡ባለጭንብሉ ቅጣቱ ከሚገባው በላይ የተጋነነ መሰለው
"አንተ የማትረባ እንቅልፍህ አልመጣም!"አለው ባለ ጭምብሉ እልህኛ ነው
"ዋላስ ከዚም በቀላሉ ለታመልጪኝ ነው አንቺ ትንኝ አታደርጊውም ግን እንደው ይሄን የለሊት ጉዞ ከየት ተማርሺው በይ!?" አለ ዘበኛው እያለመጠበት ፡ወጣቱ ይበልጥ ተበሳጨ
"አንተ የማትረባ ፡ይሄን ገመድ ከላዬላይ ፍታ ልቀቀኝ"አለ በእልህ እየተወራጨ
"ይህ የአባወራው ትህዛዝ ነው፡እናም እኔ ከሳቸው ብቻ ነው ትእዛዝ የምቀበለው አባብለህ አስተኛው ካሉኝ አስተኛሃለው ዝፈንለት ካሉ እዘፍንልሃለው ዘምርለት ቢሉም፡እዘምርልሃለው ቅበረውም ካሉ እንደዛው መቼስ ስራ አይደል!"አለ በማልመጥ
"ውሻ በበላበት ይጮሃል እንዲሉ!" አለ ባለጭንብሉ የበለጠ ሊሰድበው ቃላት እየፈላለገ
"አይጥ ድመትን ለጫወታ ትጋብዛለች ደሞ ካንተ ጋር የሚሄድ ተረት ነው፡ሀሀሀሀ እኔ የምለው፡ቀን ላይ የሆነ የጀግና ፊልም አይተህ ነበር እንዴ በለሊት ካልሲህን ቀደህ አናትህ ላይ አጥልቀህ የመጣኽው ሀሀሀሀ ሲያረጉ አይተሻል እንደው እመጣለው እንኳ አይባልም
ሀ.ሀ.ሀ..ሀ የማትረባ ዱርዬ !" ብሎ ዘበኛው በርግጫ ከቆሰለው ፊቱ ላይ መታው፡ ባለ ጭንብሉ ወደኋላው ፍንግል አለ ዘበኛው መምታቱ ያስደሰተው ይመስል ፡ደጋግሞ እረገጠው ወጣቱ ስቃዩ በረታበት በቁስሉ ላይ የሚሰነዘረው ዱላ በጣም አሳመመው ሞቱን እስኪመኝ አሳለው አቃሰተ ተሰቃየ ዱላው ቀጠለ......
====
አቶ ይፍሩ እራት ላይ አብረዋቸው የቀረቡትን አራቱንም ልጆቻቸውን በስስት እየተመለከቱ ፡ሁኔታቸውን ይከታተላሉ ፡ሮዛ 26 አመቷን ይዛለች ራሄል 23 ሲፈን 21 ሊያ 16 ይገረማል ልጆቼ አሁን ሁሉም እኩያ እስኪመስሉ ተቀራርበዋል፡አንድ ወቅት ሁሉም የሚ ያስቸግሩ እፃናት ነበሩ ዛሬ ላይ መኩሪያዬ ሆነዋል ተመስገን ምንም ነገር ስለናንተ ነው የማደርገው በዚች ምድር ላይ እስካላቹ ሁሌም የሚገባችሁን ማግኘት አለባቹ እሱን ለመስጠት ስለናንተ የማይታለፈውን ሁሉ አልፋለው እኔ እኔ ነኝ ይፍሩ አባታቹ አሉ በኩራት በውስጣቸው ያንን ውሻ ግን ማን እንደላከው ካላወኩ እንቅልፍ አይኖረኝም ፡በጭራሽ ሲፈኔን ነክቶብኝ ይሆን እንዴ እናትና ልጅ የደበቁኝ ነገር ይኖር እንዴ?አይደረግም እንደዛ አድርጎ ከሆነ ፡እንትኑን ቆርጬ አሰቃይቼ ነው ማጠፋው አይማረኝ ከማርኩት፡ሌሎቹ ልጆቼ ሰለተፈጠረው ነገር አለመስማታቸው ጥሩ ነው እንዲያ ባይሆን ኖሮ ከፊታቸው ደስታ በራቀ ነበር ስለ ጉዳዩ መስማት የለባቸውም እያሉ እያምሰለሰሉ ፡ወደሲፈን በትኩረት አዩ ዝምታ በዝቶባታል እናትየውም እንደዛው የናቲቱ እንኳ ችግር የለውም፡ልጄ እኔ ልሸማቀቅ ብለው ተቆጩ በጣም
"ሲፈኔ አንዴ ትመጪ ላናግርሽ "ብለው ተነስተው ከሳሎን ወጥተው በረንዳ ላይ ከተቀመጠው ወንበር ቁጭ አሉ ፡ሲፈን እየተጎተተች ሄዳ አጠገባቸው ተቀመጠች
"ሲፈኔ ዝምታሽ በረታብኝ እኮ ፡ምነው የደበቅሺኝ ነገር አለ ከዛን ለቱ ሁኔታ ንገሪኝ ሳደብቂ አባትሽ ነኝ!?"
"አይ አባዬ ምንም አልደበኩህም ከማስፈራራት ሌላ ነገር አላረገኝም እንደዛ ቢሆን አውጥተህ ስትለቀው ዝም የምል ይመስልሃል!ሲፈን እኮ ነኝ !"አለች በማረጋገጥ
"ሀሀሀሀ ያባቷልጅ የኔ ልዩ አንቺን ምናለ ፈጣሪ ወንድ ባደረገልኝ!"አሉ አቶ ይፍሩ
"አይ እንግዲ አባባ !አንቺን ሰው ያርግልኝ ነው የሚባለው ሰው መሆን በቂ ነው! ፆታ አያመፃድቅምም፡ አያሳፍርምም ፡የሁሉ ሰሪ እሱ ብቻ ነው፡!"አለች ሲፈን ኮስተር እንደማለት ብላ
"እሰይ የኔ አዋቂ የኔ ጀግና ልክ ነሽ !"
"አባባ የዛን ለት እውነት ባለ ጭንብሉን አውጥተህ ነው የለቀቅከው ምንም አይነት ቅጣት አላደረስክበትም ?"
"አዎ የኔልጅ ከሱ ጋር ምን አላፋኝ የፈለገው ተራ የስርቆት ጉዳይ ለመከወን ነበር ስለዚህ ጥቂት ጎሸም አደረኩትና ለቀቅኩት፡"
"ከሆነ ጥሩ ነው፡ግን ደሞ ስህተትም አለብህ የግድ ቤትህን ሰብሮ የገባን ሌባ ጎሻሽሞ መልቀቁ አልታየኝም፡ለፖሊስ ማስያዝ ነበረብህ!"አለች ሲፈን በቁጭት የአባቷ ድርጊት አልዋጥ እያላት
"እኔ በወቅቱ እሱ አልታየኝም ፡ሲፈኔ አሁን እሱን ተይውና ይልቅ እንደፊቱ ተጫዋችነትሽን አምጪው እህቶችሽ ግራ እንዳይጋቡ ደሞም መቼም እንዳይሰሙ!"
"ኧረ አባባ እነሱ መቼም አይሰሙም እንኳን ይህን አውቀው እንዲሁም ፈሪ ናቸው !"አለች ሲፈን ፈገግ ለማለት እየሞከረች፡አቶ ይፍሩ በልጃቸው፡ ሁሌም እንደተደመሙ ነው ትለያለች ሲፈን ይላሉ አስተዋይ ናት ቆንጆ ናት ፡ተወዳጅ ናት...
========
አቶ ይፍሩ ኮራ ብለው ከጓደኞቻቸው ጋር እየተገባበዙ ከአንድ ግሮሰሪ ተቀምጠዋል ወሬያቸው ሁሉ ስለ ባለ ጭንብሉ ወጣት ነበር ሁለቱም ጓደኞቻቸው ከሳቸው ጋር በሚስጥር የተሳሰሩ ናቸው ነገርግን ለመጀመሪያ ጊዜ በባለጭንብሉ ምክንያት አቶይፍሩ ጥርጣሬ ገብቷቸዋል ማነው ከሁለት አንዱ የከዳኝ ወይስ ያልጅ ተራ ሌባ ነው! ግን እንዴት ሙሰኛ አጭበርባሪ፡ሊለኝ ቻለ እያሉ በጨዋታቸው መሃል ግራ በመጋባት ያይዋቸዋል ከግንባራቸው ይነበብ ይመስል አቶ ይርጋ ሜታ ቢራቸውን ጎንጨት ብለው "አና ይፍሩ ልጁን ከቤትህ አስረህ ማቆየትህ ተገቢ ነው!"አሉ
"አሃ ማንነቱን ሳታውቅ ልቀቀው ነው የምትለኝ?"አሉ ቆጣ ብለው አቶ ይፍሩ። | 764 |
| 14 | 📢 ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች!ባለፉት ጊዚአት በቻናላችን ላይ ይወጡ የነበሩ ማስታወቅያዎች (Web Promotion) መብዛት ንባባችሁን እንደረበሸው እና ቪው (Views) እንዲቀንስ ምክንያት እንደነበር እንረዳለን። የእናንተን ሰዓት እና ንባብ ማክበር ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ስለሆነ—ያንን የማስታወቅያ ሂደት ሙሉ በሙሉ አቁመነዋል።
ከዚህ በኋላ ያለ ምንም ማስታወቂያ መረበሽ በሰከነ መንፈስ የሚወዱትን የሊቃውንት፣ የስነ-ጽሁፍ እና አስተማሪ ይዘቶች ብቻ እናደርሳችኋለን።
🔔 ይህንን አሰልቺ ማስታወቅያ ለማስቀረት ብላችሁ ቻናላችንን #Mute አድርጋችሁት ከሆነ፣ አሁን ንጹህና ጥራት ያለው ይዘት ብቻ ስለሚለቀቅበት እባክዎ #Unmute በማድረግ ቤተሰባችንን ይቀላቀሉ።
ለአስተያየታችሁና ከኛ ጋር ስለሆናችሁ እናመሰግናለን! 🙏
💥ከዚህ ቀደም የነበረው ቆይታችን ምን ይመስል ነበር?
ሐሳብዎን እና አስተያየትዎን ከታች ባለው የኮሜንት መስጫ ላይ አጋሩን! 👇
@atronosee | 821 |
| 15 | 💚 ለውብ ቀን!
ወርክሾፕ ላይ ነው የተዋወኳት፤ ከላይ እስከታች ዝንጥ ያለች፣ ግብድዬ መቀመጫ አላት። የምትቀባው Perfume ሽታው ጣፋጭ ነው። ስናወራ ብዙ የጋራ ነገር ኖረን ደስስ አለኝ፤ ደስስ አላትም።
እርግት ስክን ማለቷ እና ኮንፊደንሷ የሚስብ ነገር አላብሷታል። ወክ እያደረግን ነው፤ ከእሷ ጋር መሄድ ምቾት ይሰጣል። መንገድ ዳር ወደአለ መሸታ ቤት ገባን። ማልታ አዘዝኩ፤ ጂን አዘዘች። በትህትናም «ሲጋራ አምጭልኝ» አለች። ጂኑን ከማልታዬ ጋር አጋጨነው። እኔ ብቅሌን፣ እሷ አረቄዋን እየቀመቀምን ነው አጫጫሷ ደስ አለኝ።
«አጭስ አጭስ አለኝ፤ ጅን እዘዝ እዘዝ አለኝ» ስሜቴን ተቆጣጥሬ ገብሴን ተያያዝኩት። ስለተለያየ ነገር አወራን።
«አብረን እንደር ወይስ ሌላ ፕሮግራም አለህ ወይ?» አለቺኝ።
ደነገጥኩ! እንዳልደነገጠ ለመሆን ሞከርኩ፦
«አይ ዛሬ ምሽት አንድ አስቸኳይ ስራ አለኝ» አልኳት።
🤔 ፆታ የተቀያየርን አይነት እንግዳ ስሜት ተሰማኝ
!ነፃነቷ ረበሸኝ??
ያደኩት አባታዊ ማህበረሰብ (patriarchy society) ውስጥ ነው፤ ወንድ እየጠጣ «ከዚህ በላይ በቃህ» የምትል ቺክ…
ወሲብ እየፈለገች የምትግደረደርበት፣ ቤርጎ እየገባች «ውዴ ሌላ ቀን አይሻልም?» የምትል እንስት…
ሲጋራ ስትለኩስ «... ሳንባህን ይጎዳዋል ቅድም አጨስክ አይደል» እያለች የምትንጋተት አይነት ሴትን ማየት ነው ልምዴ።
ስለምን ወንድ ላይ ትክክል ነው ብለን የተቀበለነው ወይም ያን ያህል የማይጎረብጠን ሴት ላይ ሲሆን ይጎረባብጠናል?
አባታዊ ማህበረሰብ ውስጥ ስላደገን ይሆን??
ስህተት የግድ ከፆታ ፆታ መለኪያው መለያየት ይኖርበት ይሆን??
ነፃነቷ አፈዘዘኝ። መጉላት ለለመደ ወንድ መፍዘዝ ከባድ ነው! መገናኘት አቋረጥኩ።
🎭 ለጓደኞቼ «ፈታ ያለች፣ ነፃነቷን የተጎናፀፈች ኮንፊደንሳም ነች» ብዬ ነግሬያቸው ነበር! አሁን ግን በተቀመጥንበት ካፌ ስለሷ ሲወራ እንዲህ አልኩ፦
«ሱሴ ነች፤ በዛ ላይ ፈጣጣ!»
ያቺ ያሞገስኳት፣ ያቺ ከአቅም በላይ ያንቆለጳጰስኳትን እንስት ሳጣጥላት «በህይወቷ መንገድ እትትት ብለህ ሄደህ፣ እንደዛ አግዝፈህ ነግረኸን ዛሬ ድክመቷ ነው ብለህ ያሰብከውን ማጉላት ትክክለኛ አይደለም» ያለኝ ማንም የለም!
የሚያበላሹን የማይሞግቱን ናቸው!የሚያጨማልቁን «መላክም ሴጣንም ነች» ስንል ዝም ብለው እየሰሙን ያሉ ናቸው።
💡 ማስታወሻ፦
በዙሪያችን ያሉ ቅን ሞጋች ሰዎች ለእድገታችን ምሶሶ ናቸው።
የፍልስፍና መጀመሪያ በተለምዶ ያመንበትን በሰከነ መንገድ መመርመር ነው።
#በነገራችን ላይ በዚህ ሀሳብ ላይ የሴቶችም የወንዶችም ሀሳብ ምን ይመስላል..? አካፍሉን...
✍️ አድሀኖም
@atronosee
🔄ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ! | 859 |
| 16 | ቤቲንግ ይጫወታሉ መበላትስ ሰልችቶታል እንግዲያውንሱ በነፃ ያለምንም ክፍያ በቀን ከ 50-150 odd የሚለቀቅበት ቻናል ልጠቁማቹ ይጠቀሙበታል ቻናሉን ከስር ያሉትን በመንካት ቶሎ ይቀላቀላሉ | 112 |
| 17 | ❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️
የአንበሳ ልጅ ምን ይባላል?
ቀድመው ለመለሱ 5 ሰዎች የ500 ብር ካርድ ይሸለማሉ። | 54 |
| 18 | ማርያምን ዝም ብላችሁ join በሉ
😂😂😂ጥርሳችሁ እስኪሰበር ነው ምትስቁት ግን በዋላ ጥርሳቹ ተሰብሮ ክፈል የለም😁😁 ስሞትላቹ ተቀላቀሉት 🙏 | 129 |
| 19 | 1GB ስንት MB ነው? | 31 |
| 20 | ሁሌም ሳቅ😂😂😂 | 79 |
