ከስነ-ፅሁፍ ዓለም
✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን https://t.me/Ethiobooks ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።
Больше📈 Аналитический обзор Telegram-канала ከስነ-ፅሁፍ ዓለም
Канал ከስነ-ፅሁፍ ዓለም (@ethiobooks) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 10 297 подписчиков, занимая 3 708 место в категории Книги и 3 225 место в регионе Эфиопия.
📊 Показатели аудитории и динамика
С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 10 297 подписчиков.
Согласно последним данным от 02 октября, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 8, а за последние 24 часа — 2, при этом общий охват остаётся высоким.
- Статус верификации: Не верифицирован
- Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 11.05%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 3.06% реакций от общего числа подписчиков.
- Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 1 137 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 315 просмотров.
- Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 8.
📝 Описание и контентная политика
Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
“✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል!
የቻናላችን https://t.me/Ethiobooks ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ።
ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ
@firaolbm እና
@tekletsadikK ተጠቀሙ።”
Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 03 октября, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Книги.
Загрузка данных...
| Дата | Привлечение подписчиков | Упоминания | Каналы | |
| 03 октября | +4 | |||
| 02 октября | +2 | |||
| 01 октября | +1 |
| 2 | sticker.webp | 273 |
| 3 | ም ላ ስ
👅 👅
👅
ምላስ ይቀባል፣ ጥርስ ይወጋል።
👅
ምስጢረኛ ምላስ የለውም።
👅
ምላስ ከጥርስ፣ እጅ ከልብስ።
👅
የተቀማጭ፣ ምላሱ ምላጭ።
👅
ምላሱ አይታጠፍም።
👅
የባለስር፣ ምላሱ አስር።
👅
ምላስ ቢጥም፣ ቀዶ ይጠቅም።
👅
መልካም ምላስ ቁጣን ታበርዳለች።
👅
ባንድ ራስ፣ ሁለት ምላስ።
👅
ምላስ ያስቀጣል፣ ስለት ይቆርጣል።
👅
ቀይ ምላሱ፣ ጥቁር ራሱ።
👅
በምላስ የተወጋ፣ ቢታከም አይድንም።
👅
ያላረፈች ምላስ፣ ሸማ ትልስ።
👅
የሰው ምላስ መንታ፣ አንዱ ለሙገሳ አንዱ ለሐሜታ።
👅
ምላስ አጥንት የለው፣ ግን አጥንት ይሰብራል።
👅 👅
ነገር በምሳሌ
@ethiobooks | 490 |
| 4 | sticker.webp | 440 |
| 5 | መልካም ምላስ ቁጣን ታበርዳለች
━━━━━✦━━━━━
✍ ከበደ ሚካኤል
'
እናቱ በጣም አድርጋ የምትወደው አንድ ልጅ ነበር። እሱም ከዐጥር ግቢያቸው ውስጥ ከሚገኙት የኮክ ዛፎች ላይ እየወጣ ፍሬውን ሲቆርጥ እናቱ ብዙ ጊዜ ታየው ነበርና ከዛፉ ላይ ወድቆ አደጋ ያገኘዋል በማለት ስለሰጋች እንዳይወጣ መላልሳ ብዙ ጊዜ ከልክላው ነበር።
አንድ ቀን ከቤት ውስጥ ሆና እንደ ልማዱ ከኮኩ ዛፍ ላይ ፍሬ ሲለቅም በመስኮት አየችው። ከቤት ሲገባ ጠርታው "ከዛፍ ላይ አትውጣ ብዬ ከልክዬህ አልነበረምን? ለምንድን ነው ዛሬ ደግሞ የወጣኸው?" ብላ ጠየቀችው።
እሱ ግን ደንግጦ "አልወጣሁም" ብሎ ካደ። እሷም በጣም ተቆጣችና "ደግሞ ከማጥፋትህ መዋሸትህ ይባስ። ባይኖቼ እያየሁህ ትክደኛለህ?" ብላ ልትመታው ተነሣች።
እሱም አሳዛኝ የሆኑትን ዐይኖቹን እያንከራተተ ለዛ ባለው አንደበቱ "እማማ እወድሀለሁ ትዪኛለሽ፣ እንደምትዪኝም እውነትም የምትወጂኝ ከሆንሽ ባይኖችሽ ካየሽው ይልቅ እኔ የምነግርሽን አብልጠሽ ማመን ይገባሻል" አላት።
ደማሙ ልጅ ይህን ማለቱ 'ስለ እኔ ፍቅር ብለሽ ያየሽውን እንዳላየሽ አድርገሽ አሳልፊው እንጂ በጥፋቴ ለምን ትሞግቺኛለሽ?' ብሎ መለማመጡ ነው።
እናቱም በዚህ ለዛ ባለው ንግግር ከቁጣዋ በርዳ በመምታት ፈንታ ልጅዋን አቅፋ ሳመችው። ዐይኖችዋም ዕንባ አቅርረው ይታዩ ነበር።
━━━━━━━━━━
📔 ታሪክና ምሳሌ - ፩ኛ መጽሐፍ
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/Ethiobooks | 607 |
| 6 | sticker.webp | 507 |
| 7 | • ጓደኛችሁ በፍቅር ዘርታችሁ •
በምስጋና የምታጭዱት ማሳችሁ ነው
━━━━━✦━━━━━
✍ ካህሊል ጅብራን
'
አንድ ወጣትም አለው፦ «ስለ ጓደኝነት ንገረን?»
እሱም እንዲህ በማለት መለሰለት፦
«ጓደኞቻችሁ ለፍላጎቶቻችሁ ምላሽ ናቸው። ጓደኛችሁ በፍቅር ዘርታችሁ በምስጋና የምታጭዱበት ማሳችሁ ነው። ገበታችሁና የምትሞቁት እሳታችሁም ነው...
«በራባችሁ ጊዜ ወደ እሱ የምትሄዱትን ያህል በሰላም ጊዜስ አትፈልጉትምን?...
«ጓደኛችሁ ከአዕምሮው ጋር ሲነጋገር በገዛ አዕምሯችሁ ውስጥ ስላለው ‹አሉታ› አትስጉ። ‹አዎንታ›ንም አትንፈጉት። ዝም ባለ ጊዜ ልባችሁ፣ ምኞቶችና ተስፋዎቻችሁ ሁሉ ቃላትን መጠቀም ሳያስፈልግ ያለ ሆታና ጭብጨባ ተወልደው በወዳጅነት የምትጋሯቸው ነገሮች ናቸውና...
«ከጓደኞቻችሁ ስትለያዩ አትዘኑ። ለተራራ ወጪ ሰው ተራራው በግልጽ የሚታየው ከሜዳው ላይ ሆኖ እንደሆነ ሁሉ፣ ከሁሉ አስበልጣችሁ በምትወዱት ሰው ውስጥ ያለው ብዙ ተወዳጅ ነገር የበለጠ ግልጽ ሆኖ የሚታያችሁ እሱ በሌለበት አይደለምን?...
«እናም በጓደኝነት ውስጥ ከመንፈስ ጽናት በስተቀር ሌላ ምንም አላኖራችሁም...
«የገዛ ራስን ምስጢር (ምኞት) ለመፍታት ከመሻት በስተቀር ሌላን የማይፈልግ ፍቅርስ ዋጋ ቢስ ነገሮችን ብቻ ለማጥመድ ወደ ባህር የተወረወረ መረብ እንጂ ፍቅር ሊሆን ይችላልን?...
«ደግሞም ለጓደኛችሁ የተቻላችሁን ያህል መልካም ሁኑለት። የልባችሁን ባህር የማዕበል ሞገድ ማወቅ ካለበት የውኃ ሙላቱን (ጎርፍንም) ጭምር ይወቅ...
«በጣዕረ ሞት (በመቀበሪያ) ጊዜያት ልትፈልጉ የሚገባችሁ የቱን ጓደኛችሁን ነው? ሁልጊዜም በፍስሃ (በሕይወት) ጊዜያት ፈልጉት። ባዶነታችሁን ሳይሆን ፍላጎታችሁን መሙላት የሚገባው እሱ አይደለምን?...
«በጓደኝነት ጣፋጭ ጊዜያት ውስጥ ሳቅና ደስታን መጋራት ይኑር። ልብ ንጋቱን (ብርሃኑን) አግኝቶ የሚታደሰውስ በጥቃቅን ነገሮች ጤዛ ውስጥ አይደለምን?»
━━━━━━━━━━
📔 የጠቢባን መንገድ
ትርጉም ➢ ሀብታሙ ተስፋዬ
📄 40 - 41
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/Ethiobooks | 703 |
| 8 | sticker.webp | 577 |
| 9 | ቅዱስ መርቆርዮስ - 2 የመጨረሻው! | 824 |
| 10 | ቅዱስ መርቆርዮስ - 1 | 812 |
| 11 | ▶ ቅዱስ መርቆርዮስ
━━━━━━
«ባለ ሁለት ሰይፉ ሰማዕት»
@ethiobooks | 828 |
| 12 | sticker.webp | 706 |
| 13 | በራ፤ የመስቀል ደመራ
═══ ❖ ═══
✍ ጸጋዬ ገብረ መድኅን
'
የአደይ ችቦ እየፋመ ፥ እየጋመ
ኢዮሃ እያስገመገመ እየተመመ
የመስቀል ደመራ
በራ።
በራ የአዲስ ዘመን ችቦ
በመስከረም ሰብል አብቦ
ከዋክብቱን ፈነጠቀ
ርችቱን አንፀባረቀ
ተኳለ አዲስ ደመቀ
መስኩን በቀለም አዝርዕት፥ በጥበብ አጥለቀለቀ
ሸለቆው ተንቆጠቆጠ ፥ ተራራው አሸበረቀ
ኢዮሃ ኢዮሃ አበባዬ! ምድር ሕይወት አፈለቀ።
ነጋ ፥ የአዲስ ዘመን ችቦ
ፈካ ፥ ፀደይ አረብቦ
ሌሊቱ እንደ ጎህ ቀደደ ፥ ጨለማው እንደ ቀን ጠራ
እንደ ውቅያኖስ ዕፅዋት ፥ እንደ ጠፈር ኮከብ ደራ
ምድር ስጋጃ ለበሰ ፥ የጌጥ አልባሳት ተቀባ
ሰማይ በእልልታ አስተጋባ
ኢ ዮ ሃ መስከረም ጠባ።
ነጋ ፥ የአዲስ ዘመን ችቦ ፥ ምድር ሕይወት አፈለቀች
የምስራች አዝርዕቷን ፥ አዲስ ቡቃያ ወለደች
የአደይ አበባን ለገሠች
ለአዲስ ዘመን አዲስ ብርሃን ፥ አዲስ መስከረም ገበየች።
ነጋ ፥ የአዲስ ዘመን ችቦ
ፈካ ፥ ፀደይ አረብቦ
በራ፣
የመስቀል ደመራ።
═════════
🗓 መስከረም ፲፱፻፷፫
መስቀል አደባባይ
📖 📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/Ethiobooks | 846 |
| 14 | sticker.webp | 622 |
| 15 | የአጼ መስቀል የደመራ በዓል
1922 ዓመተ ምሕረት
━━━━ ❖ ━━━━
የአጼ መስቀል በዓል መስከረም 10 ቀን 1922 ዓ.ም. ዓርብ በግርማዊት ንግሥት ዘውዲቱና በግርማዊ ንጉሥ ተፈሪ ፊት በቤተ መንግሥት ተከበረ። ሊቀ ጳጳሳቱ፣ እጨጌው፣ ሚኒስትሮች፣ መኳንንት የዲፕሎማቲክም ሰዎች በበዓሉ ላይ ነበሩ።
የምራቱ ተረኞች የጽርሐ አርያም ካህናት ባለፈው ወር በአየር እየበረረ የመጣውን የአውሮፕላን ታሪክ ለመጥቀስ ሲሉ
"ወረሰየ ደመና ወከየዶ ዘየሐውር በክንፈ ነፋስ ዘርየስዬሙ ለመላእክቲሁ መንፈስ።"
የሚለውን ምስባክ አሰበኩ። የዘመኑን ታሪክ በተመሳሳይ ጥቅስ ማቅረብም የተለመደ ነገር ነበር።
ከዚህም በኋላ ተቀጸሊ ጽጌ አስካለ ማርያም ሐጼጌ "እቴጌ አስካለ ማርያም ሆይ፣ አበባን ተቀዳጂ" እያሉ እንደ ተለመደው አሸብሽበውና ሊቀ ጳጳሱ አሳርገው የበዓሉ ፍጻሜ ሆነ። አስካለ ማርያም የንግሥት ዘውዲቱ የክርስትና ስም ነው። ሁልጊዜም ተቀጸል ጽጌ ሲባል የሚጠራው ይህ ስም ነበር።
የደመራ በዓልም መስከረም 16 ቀን 1922 ኀሙስ በ9 ሰዓት በአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ በአደባባዩ ላይ በወታደር ሰልፍ ተከበረ።
በዚህ ጊዜ ሦስት አውሮፕላኖች በአየር ላይ እያንዣበቡ የመገለባበጥ ትርእይት ስላሳዩ ሕዝቡ ብርቅ ነገር ሆኖበት ሽቅብ ሽቅብ ተመለከተ። ደግሞም የወረቀት አበባና የወረቀት ጽሑፍ ለሕዝቡ በተኑለት። ከግጥሙ ቃል የማስታውሰውን በሚከተለው እገልጻለሁ፦
የመስቀሉ በዓል ምንኛ ገነነ፣
ከአምና ዘንድሮ የበለጠ ሆነ።
ንግሥትና ንጉሥ በዙፋን ሆነው፣
ጀግናው ተሰልፎ መኳንንት ከበው።
በግራና በቀኝ በራስጌ በግርጌ፣
አምስት ጳጳሳት ስድስተኛ እጨጌ።
ደግሞም ተንዣበበ በስተላይ ባየር፣
ተጓደኞቹ ጋር የተፈሪ ንስር፣
አበባ ሊነዛ በዓሉን ሊያከብር።
በዘንድሮው መስቀል በዛሬው በዓል፣
እጅግ ደስ ይበለን እልል እንበል።
ብርሃንን እንልበስ ሰላምን እንውደድ፣
ንስረ ተፈሪ ነው በጨለማ እንሂድ።
በአየር ላይ ሆኖ አበባን ሲዘራ፣
ከተከታዮቹ ከመላእክት ጋራ፣
እንቁጣጣሽ ይላል የተፈሪ አሞራ።
ሰልፉም እንደተፈጸመ ግርማዊ ንጉሥ በሠራዊት ታጅበው ወደ ግቢያቸው ተመለሱ።
━━━━━━━━━━
📔 የሐያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ
✍ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ
📄 376 - 377
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/Ethiobooks | 912 |
| 16 | sticker.webp | 711 |
| 17 | 💬
❝ትናንሽ እቅዶች አታውጡ። ትናንሽ እቅዶች የሰዎችን የልብ ምት የሚያጣድፍ አስማት የላቸውም። ትላልቅ እቅዶችን በመንደፍ በተስፋና በሥራ ተንጠራርታችሁ አልሙ።❞
ዳንኤል ኤች. በርንሃም
💬
❝መጥፎ እድሎች ወይም ኪሳራዎች ሁልጊዜ በተከፈተላቸው በር ይገባሉ።❞
ሞንታኝ
💬
❝ከአሳማ ጋር ትግል መግጠም እንደሌለብኝ የተማርኩት ከረዥም ጊዜ በፊት ነበር። እንደዚያ ካደረጋችሁ ትቆሽሻላችሁ፤ በዚያ ላይ አሳማ ትግል ይወዳል።❞
ሳይረስ ቺንግ
💬
❝ገነት ማለት ሁልጊዜ ፍቅር ያለበት ቦታ ነው።❞
ኤመርሰን
💬
❝ስኬታማ የመሆን ልባዊ ፍላጎት ካለን ተሸናፊዎች የማይደፍሯቸውን ሥራዎች መሥራትን መድፈር ይኖርብናል።❞
ያልታወቀ
💬
❝ቁም ነገሩ ከየት እንደመጣህ አይደለም፤ ዋናው ቁም ነገር ወደ የት እንደምትሄድ ማወቅህ ነው።❞
ብሪያን ትሬሲ
💬
❝እውነተኛ ዕውቀት ከትክክለኛ ልምድ ይፈልቃል።❞
ቶልስቶይ
💬
❝የማንም ሰው 'ጂኒየስነት' ምን ያህል ብታበራ እንኳ ያለ ከባድ ሥራ፣ ያለ ዕድል እና ያለ ጠቋሚ ባልንጀራ ከጋን መብራትነቷ ልትወጣ አትችልም።❞
ፕሊኒ
💬 💬
ጥቅሶች
@ethiobooks | 1 032 |
| 18 | sticker.webp | 781 |
| 19 | ሞሪንጋ ለደም ግፊት
━━━✦━━━
የደም ግፊት በመላው ዓለም ግንባር ቀደም የጤና ችግር እየሆነ መጥቷል። ይኽ ችግር ቀድሞ ባደጉ አገሮች ውስጥ የሕመሞች ቁንጮ ሆኖ የከረመ ሲሆን ከቅርብ አስርት ዓመታት ወዲህ ደግሞ በማደግ ላይ ላሉ አገራት ትልቅ ራስ ምታት እየሆነ ይገኛል።
የደም ግፊት ጤናን የሚያመሰቃቅል፣ አኗኗርንና አመጋገብን የሚያመሰቃቅል፤ ለልብ፣ ለኩላሊትና ለአንጎል አደጋዎች የሚያጋልጥ ገዳይ በሽታ ነው።
"የደም ግፊት" በኬሚካላዊ ቋንቋ ሲተነተን በደማችን ውስጥ ሶዲየም የተባለው ከጨው ውስጥ የሚገኘው ንጥረ ነገር ከሚፈለገው መጠን በላይ መጨመር ማለት ነው። በደማችን ውስጥ የፖታሺየም ንጥረ ነገር መቀነስ በተቃራኒው የሶዲየም ንጥረ ነገርን መጨመር ያስከትላል።
ስለዚህ ፖታሺየም በብዛት ያላቸውን ምግቦች መውሰድ በተዘዋዋሪ የደም ግፊትን ለመቀነስ ይረዳል። ታዋቂውና ስመጥር የሆነው የፖታሺየም መገኛ የሚባለው የፍራፍሬ ዓይነት ሙዝ ነው።
ሞሪንጋ ደግሞ ከሙዝ በ15 እጥፍ የሚበልጥ የፖታሺየም ክምችት (ይዘት) አለው። በዚህ ትንታኔ መሰረት ሞሪንጋን በመመገብ የደማችንን የፖታሺየም መጠን በበቂ ሁኔታ ከፍ ማድረግ፤ ቀጥሎም የደማችንን የሶዲየም መጠን ዝቅ ማድረግ ይቻላል። የደማችንን የሶዲየም መጠን መቀነስ ሲባል በሌላ አገላለፅ የደም ግፊትን መቀነስ ማለት ነው።
ስለዚህ ሞሪንጋን በየዕለቱ በመጠቀም የደም ግፊትንና የደም ዝውውር ሥርዓትን አስተማማኝ በሆነ መልኩ ማስተካከል ይቻላል።
በከፍተኛ የደም ግፊት ለሚሰቃዩ ሰዎች ጨው (ሶዲየም) ተጨማሪ የስቃይ ምንጭ ብቻ ሳይሆን የሞት መንስኤም ነው። ይልቁን ጠቃሚ የሚባሉት ንጥረ ነገሮች ፖታሺየም፣ ዚንክ፣ ካልሺየም፣ ማግኒዥየም እና ቫይታሚን ኤ ናቸው።
ሞሪንጋ እነዚህን ለደም ግፊት ህሙማን ጠቃሚ የሚባሉትን ንጥረ ነገሮች ሙሉ በሙሉ አለው። ለምሳሌ ሞሪንጋ ከፍተኛ የፖታሺየም ይዘት አለው። አስቀድመን እንዳነበብነው ከፍተኛ ፖታሺየም ያለው ምግብ መመገብ ማለት በደም ውስጥ ያለውን የፖታሺየም ማዕድን መጠን እንደሚጨምር ግልፅ ነው።
በደም ውስጥ ያለው የፖታሺየም መጠን ሲጨምር በኩላሊት ውስጥ የሶዲየምን መጣራትና የሶዲየምን በሽንት ውስጥ የመወገድ ሂደት ያፋጥናል። ይህ የሁለቱ ንጥረ ነገሮች የመተካካት ሂደት ነው። የሶዲየም ስፍራ በፖታሺየም ይተካል። ሶዲየም በሽንት ይወገዳል። ስለዚህ በደም ውስጥ ያለው የሶዲየም መጠን ይቀንሳል። ይህ ደግሞ የደም ግፊትን ዝቅ ያደርገዋል።
ልክ እንደ ፖታሺየም በተለያዩ ትንታኔዎች ምክንያት ይሁን እንጂ ዚንክ፣ ማግኒዥየም፣ ካልሲየም እና ቫይታሚን የደም ግፊትን የመቀነስ ጠቀሜታ አላቸው።
━━━━━━━━
📔 ማርና ሞሪንጋ
✍ ዶክተር ኬ.ኬ.
📄 133 - 134
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/Ethiobooks | 1 196 |
| 20 | sticker.webp | 916 |
