cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ወግ ብቻ

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13@wegoch @Words19@seiloch@zefenbicha Creator @leul_mekonnen1

Больше
Рекламные посты
19 495
Подписчики
-324 часа
-107 дней
-3330 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ልገድልላት ስነሳ ትሞታለች!? (ዘማርቆስ) እርሜን ከቤቴ ስወጣ የሚያበሳጨኝ አላጣም...ከታክሲ ስወርድ ጠብቀው በልመና ልቤን ከሚጠቡኝ ህፃናት አንስቶ ከተማው ሁለመናው ይደብረኛል።ዱካኩን ለማስታገስ የጀበና ቡና ልከደም ብዬ ወደ ሙሉ ጠጋ ስል ያለወትሮዋ የሴት አቀማመጧን ዘንግታ መሀል ለመሃል የተተረተረ ቀይ የውስጥ ሱሪዋን በነፃ ታስጎበኘን ጀመር።ቀይ ውስጥ ሱሪዋን አልፎ ሌላ የሆነ ቀይ ነገር...ዙሪያውን የጠቆረ... "ሙሉ!" አለ አስመላሽ ከሰጠመችበት የሀሳብ ውቅያኖስ መንጥቆ በሚያወጣ መንጠቆ ድምፅ...ዘወር አለች...ዘወር ብቻ...ከኪሱ ድፍን ሁለት መቶ ብር አውጥቶ "ደኅነኛ ፓንት ግዥበት" ብሎ ወደ ረከቦቱ ወረወረው።እመር ብላ ተነሳችና የተጣደውን ጀበናዋን ከመቅፅበት አቀባብላ ሙሉውን ቡና አስመላሽ ግንባር ላይ ቀዳችው። የሙሉ ጀበና ከግርማው ቅንጣት ሳይተርፈው...ከድምፁ ለትውስታ ጥቂት ሳይቀረው...እንደ አንዳንዱ ሰው ልብ በሰከንድ ንክትክት አለ። ማነው ሰው ሸክላ ነው ያለው?ሸክላ ሸክላን ይሰብራል? አስመላሽስ ምን አፉን አስከፈተው?ብሩን ከሰጣት እሷ መግዛቱ አይጠፋት...ይሄ የሰው ግም! የሆነው ሆኖ አስመላሽ ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ሙሉ ምርር እያላት እንዲህ አለችኝ... "እንደው በሆነልኝና ፍሬውን ቆርጨ ለውሻ በሰጠሁት ይኸ ቁርባ!" "ኧረ ስለወንድ ልጅ!" አልኩ ቅፍፍ ብሎኝ። "ምናባቱ!እየዞረ መልከፍከፉ ነው የሚቀርበት ይኸ አንከሊስ!" "ቆይ ምንድነው ያደረገሽ?ቅድም የተናገረው ብቻ ነው እንዲህ ያበሳጨሽ?" አልኳት "አይደለም" "ታዲያ?" "ኧረ ጉዱ ብዙ ነው ግዝሽ" "ግዴለም ልስማው" "በሜዳ አረገዝኩ ግዝሽ" ስትለኝ ማማተብ ቀረሽ ድንጋጤ ልቤን ሰነጠቀው...ሙሉ ናታ...ሙሉ'ኮ ሙሉ ናት!ሰርቶ መከበርን፣ለሰው መኖርን፣ተደርጎላት አይደለም አድርጋ ማመስገንን፣በዚህ ጩኸታም ከተማ ዝምምም ብሎ መኖርን የተማርንባት መጽሐፋችን!ሙሉም ሳታገባ ታረግዛለች?ማናባቱ ነው ሙሉን ያለ ወግ ለመተኛት የሚደፍረው?መጽሐፋችንን በቆሻሻ እጁ የገለጠብን ማነው? "ወድጄ አይደለም'ኮ" ስትለኝ "ተይ ሙሉ...መቸስ ተደፍሬ ነው አትይኝም" አልኳት "ስማኝ እስቲ ግዝሽ..." "ምንድነው?" "አስመላሽ...ጉዴን ያዘብኝ" "የምን ጉድ?" "አንድ ቀን መጥቶ የማያውቀውን 'ሰላም ልበልሽ ብዬ ነው' ብሎ ቤት መጣ...ከጓሮ ገላየን እየታጠብኩ ስለነበር 'ግባና ጠብቀኝ እየታጠብኩ ሁኘ ነው' አልኩት" "እእእእሺ..." "ለካስ እሱ ገብቶ የተቀመጠ መስሎ ተደብቆ ሲቀርፀኝ ነበር" "ገላሽን ስትታጠቢ?" "ኋላስ!ከዛልህ በነጋታው ካሴት ሲልክልኝ ዘፈን መስሎኝ እመየ ባለችበት ካሴቱን ከፈትኩት በቲቪ" "ከዛስ?" "ከዛ ደውዬ ምን እንደሚፈልግ ስጠይቀው በአጭር ትዕዛዝ 'ማንንም ሳታስከትይ ቤቴ ነይ' አለኝ...ሄድኩ...'በፈለኩ ሰዓት የማላገኝሽ ከሆነ ያየሽውን ካሴት አባዝቼ ሻሞ ብየ ነው የምበትነው...በፌስቡክ ሁላ ነው የምለቅብሽ' አለና 'ተጣጥበሽ ወደ ማታ ተመለሽ' ብሎ አባረረኝ" "ይሄ ብስባሽ!ቆይ ማዘር ምን አሉ?" "ያለኝን ስነግራት 'ለዚህ ሙርጥ ፊት እግርሽን ከምትከፍች ሙሉ ጎጃም እርቃንሽን አይቶሽ ይግረመው...ሰው ተደብቆ የቀረጠሽ እንጅ አንች ራስሽን ቀርጠሽ አትለቂው...ወሬ አንድ ሰሞን ነው' አለችኝ" "እእእሺ..." "አልሰማኋትም...'ወሬ አንድ ሰሞን ነው' ብሎ ነገር የለም ግዝሽ...ገላን ያህል ነገር በየሰው ቤት በካሴት አስቀምጬ...በየስልኩ ተይዤ የሞት ሞት ከምሞት የአስመላሽ መጫወቻ ብሆን ይሻለኛል ብዬ ተጣጥቤ ሄድኩለት"አለችኝ አንገቷን ደፍታ።የምለው ጠፋኝ...አስመላሽ ያንን ሊነኩት ቀርቶ ሊያዩት የሚያሳሳውን ገላዋን በገላዋ አጥምዶ መያዙ አበገነኝ።በዚያ እርሙጥሟጥ ከንፈሩ ውብ ከንፈሮቿን ሲጎርስ(ዘንዶ በጎረሰው!)...ያንን በቆሎ ለሳምንት የተዘፈዘፈበት ውኋ የሚያስንቅ ትንፋሹን ሲያጥናት...ለወትሮው በልበ ሙሉነት የምትቀስራቸው ጡቶቿን ቀን አኮማትሯቸው... በነዚያ አስቀያሚ ጣቶቹ ወገቧን ሲዞረው...መሰበሯን እያየ ጭኗን ፈልቅቆ ሲገናኛት ...አስመላሽ አስመለሰኝ...ከወፍራም አንጀቴ አንስቶ ነው የተመለሰው...ይሄ የሰው ሩብ! "መቼ ነው?"አልኳት ቅስሜ የሷን ያህልም ባይሆን ተሰብሮ "አይ ግዛቸው...ጊዜው ምን ይረባሃል?" "ግዴለም ንገሪኝ" "ሶስት ወር አለፈው"...ኩምሽሽ አልኩ። "መጀመሪያ ሰሞን ኮንዶም እንጠቀም ነበር" "እእእሺ" "ሁለት ሶስቴ ከተገናኘን በኋላ ግን ከዚህ ወዲያ ኮንዶም አልፈልግም ብሎ ድርቅ አለ" "ያንት ያለህ!ሙሉ ተመርምራችኋል ግን?" "እኔ ተመርምሬ ነበር ከበቀደም...ግን እንመርመር ስለው...'ያንች ድህነት ቫይረስ ሆኖ ካልጨረሰን የኔውስ አይጎዳንም' ብሎ አሾፈብኝ" አለችና ተገፍቶ የመጣ እንባዋን በመዳፏ አበሰችው።ለካ "አይዞሽ"ም ጭካኔ ይጠይቃልና! "አስገድዶ..."አልጨረሰችውም "ደፈረሽ?" "አዎ...ያውም እየሰደበኝ...እየረገመኝ...እየተፋብኝ..." "እገለዋለሁ ይሄን የውሻ ልጅ!"አልኩና አፈፍ ብዬ ስነሳ እጄን ይዛ ቁጭ አረገችኝ...ጉልበታም ናት። "የሙት ልጅ እንድወልድ አትፍረድብኝ" አለችኝ። "በቁሙ ሞቷል'ኮ" "የካደውን ማመኛ እድሜ ይስጠው" "አይገርምሽም ቢሰጠው ራሱ እነጥቀዋለሁ"ብዬ ጥያት ስፈተለክ እየሮጠች ትከተለኝ ጀመር።አስመላሽን እንዴት ከምድረ ገፅ እንደማጠፋው እያሰብኩ ስለነበር መከተሏ ግድ አልሰጠኝም።ብቻ የሆነ ቅፅበት ላይ ድብልቅልቁ የወጣ ድምፅ ታክሲ ውስጥ በተቀመጥኩበት ጆሮዬን ሰርፆ ሲገባ ታወቀኝ።አቤት አንዳንዱ ሞት ፍጥነቱ!አሁን ሳናግራት አልነበር?በስንት የተነዳ መኪና ነው ስስ ነፍሷን ከአየር ላይ የቀለበብኝ?አስመላሽ በቡና የተጠበሰ ፊቱን አሳሽጎ...ፍንክቱን አስጠግኖ ለቀብር ተሰየመ...ተያየን...ተግባባን...አፈቅራት እንደነበር ያውቃልና በኔ ላይ ድል አድራጊነት ይሰማው...ወይ ሀዘን አላውቅም...ብቻ ጠጋ ብሎ "ማናችን ነን የገደልናት" አለኝ። ዘማርቆስ 02/09/16 @wegoch @wegoch @paappii
Показать все...
6👍 4👏 3🤔 3😱 2🤬 2
ሲምሉ ሁሉንም ቃላት እርግጥ አድርገው 'ማርያምን' እያሉ ነው ። እማማ እቴነሽ ነው የምንላቸው ። ወፍራም ናቸው ሽንሽን ቀሚስ ነው የሚያደርጉት፣ ወገባቸው ላይ መቀነት አይጠፋም ። ቀይ ናቸው አንገታቸው ላይ ንቅሳት አለ ። ባለሙያ ናቸው ። ሰላምተኛ ናቸው ። በየድግስ ቤቱ ወጥ ይሰራሉ ። አይሞላላቸውም ታላቅ ወንድሜን መዳኒት ግዛልኝ ሲሉ አስታውሳለሁ ። አንድ ቀን ልጃቸው ታስሮ ነበረ ከወር እስር በኃላ ለመፈታት የገንዘብ ዋስ ሲባል ነጠላ አንጥፈው ሲለምኑ ጎረቤት ሲያስቸግሩ አስታውሳለሁ እማማ እቴነሽ ሃለፎም የሚባሉ ጎረቤት ነበሩአቸው ። በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ተባረሩ። ሙሉ ግቢያቸውን ለእማማ እቴነሽ በአደራ አስረክበው ኤርትራ ገቡ ። በቅርቡ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መሃል እርቅ ሲደረግ እማማ ሃለፎም መጡ ። የሃያ አንድ አመት ያከራየሁት ኪራይ ብለው በየወሩ ያፃፉትን መዝገቡ ጋር አስደምረው ሰጧቸው ለሳቸው አደራ ማለት በልጅ ፍቅር ፣ በጤና መታወክ ፣በድህነት፣ የግዜ ብዛት የማይፈትነው ፣ ቢፈትነውም የማያሸንፈው ነበር ። ከዛ ግዜ በኃላ የአደራ ስሙ እና ትርጉሙ እማማ እቴነሽን ይመስለኛል:: By Adhanom Mitiku @wegoch @wegoch @paappii
Показать все...
58👍 9🔥 4
የሙሉ ጊዜ ደራሲት (ማዕዶት ዘማርቆስ) የሰው ልጅ ያለስራ ይኖር ዘንድ ይቻለዋልን?የሰማይ አእዋፋትስ በክንፎቻቸው ዛብረው ይበሉትን ከሰበሰቡ ይልቁንም ከነሱ በላይ የሆነው ሰው እጆቹን ለስራ እንዲዘረጋ አታውቁም? ግን የሰው ልጅ አያ መሌን የመሰለ ሰው በዙሪያው እያለ እንዴት ሰርቶ መብላት ይቻለዋል?እሳቸው ጡረተኛ ሆኑና እኛ የምንሰራው ሁሉ ውጉዝ ነው ማለት ነው?ወይስ ከሳቸው ጋር ላለመጎራበጥ የግድ ዘመቻ ሄደን ቀኝ ጆሮአችን ስር መመታት አለብን?እኔን የሚገርመኝ ከግራ ጆሯቸው አንዲት ነገር አለማምለጧ! ለአያ መሌ የዘመኑ ሰው የሚሰራው ስራ ሁሉ ከፈጣሪ ያጣላል።ነጋዴው ሁሉ በውሸት እየማለ ያተርፋል...የመንግስት ሰራተኛው ሁሉ ድሀውን ያጉላላል...ሹፌሩ ሁሉ ሴሰኛ ነው...ሀኪሙ ሁሉ አዋቂ መስሎ አላዋቂ ነው...የጀበና ቡና የምትሸጢቱ ሁሉ ሸሌ ናት...ከደሙ የፀዳው ቀኝ ጆሮውን ተመቶ ቤት የተቀመጠ ጡረተኛ ወታደር ብቻ ነው። እሳቸው ቤት ተከራይቼ የገባሁት ይሁዳ ጌታውን ስሞ የሸጠ ቀን ይመስለኛል።እስከ ትንሳኤ መታገስ አቅቶኝ ዘመኔ ሁሉ ረቡዕ ሆነብኝ።ብቸኛዋ ተማራሪ እኔ አለመሆኔ ነው እስከዛሬም ያቆየኝ።ዘካርያስ እና ከማል የተከራየኋትን ጠባብ አንዲት ክፍል ቤት ተጎራብተው የሚኖሩ ምርጥ ወዳጆቼ ናቸው።ዘካርያስ አንድ የብስኩት ፋብሪካ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ ላብ አደር ባለትዳር ነው።ከማል ደግሞ የኮምፒውተር ባለሙያ ወንደላጤ...እኔ መሃል ያለሁቱ ጊዜ ደግሞ ያው ጊዜ ነኝ...ደራሲ ነኝ እላለሁ። "የሙሉ ጊዜ ስራሽ ምንድነው?"ሲሉኝ ደሜ ቱግ ብሎ "ደራሲ!"እላለሁ።"ማለ...ቴ ጎን ለጎን የምትሰሪው ሌላ ስራ የለም?"ይለኛል ሌላው።'ጎንህ ይነደልና ድርሰት ስራ አይደለም?'ልል ያምረኝና መልሼ 'መተው ነገሬን ከተተው' ብዬ ዝም እላለሁ። ታች አምና ለገና መታወቂያዬን ላሳድስ ሄጄ አዳሽ ተብየው "ስራ..."ሲለኝ "ደራሲ!" አልኩት ጡት አልባ ደረቴን ነፋ አድርጌ። "ሌላ የምትሰሪው ተጨማሪ ስራ የለም?" "ድርሰት ስራ አይደለም እንዴ?" "አ...ይ ጎን ለጎን የምትሰሪው ካለ ብዬ ነው" "እእእእእ....ጎን ለጎን ማለትህ ነው?" "እ..." "ሸማኔ!" "ኧ?" "ጎን ለጎን እሸምናለሁ...'ቢዝነስ ካርድ' ልስጥህ?" "አ...ይ አመሰግናለሁ"አለና ጤነኝነቴን እየተጠራጠረ በድብንድብ ፊቱ ገላምጦኝ መዝገቤ ላይ ማህተሙን አሳረፈ።ይሄ የሸማኔ ልጅ!I love ሸማኔ! ከአከራዬ ከአያ መሌ ጋርም የገጠመኝ ይኸው ነው።ቤታቸውን አይቼው ወድጄው ዋጋ ሁላ ተስማምተን ስናበቃ መታወቂያዬን ተቀብለው እየተንተባተቡ አነበቡና "ስራሽ ድርስ ነው የሚለው?ነፍሰጡር ነሽ?"አሉኝ 'ችቦ አይሞላም' ወገቤን በግርታ እየቃኙ።ደራሽ በጠረጋቸው! "አይ...ደራሲ ነው የሚለው...ግጥሞችና ታሪኮችን እፅፋለሁ...ፀሃፊ ነኝ" "ፅፈሽስ?" "አሳትሜ እሸጠዋለሁ"...አልተዋጠላቸውም... "አልፎ አልፎ ደግሞ መድረኮች ላይ እየተከፈለኝ ፅሁፎቼን አቀርባለሁ"...ክፉም ደግም ሳይናገሩ መታወቂያዬን ሰጡኝና ጎበጥ ጎበጥ እያሉ ወደቤታቸው ገቡ። በነጋታው ጧት ለማኝ እንትን ሳይል መጡና በሬን ቆፈቆፉ።ቤቴ በወረቀት እንደተዝረከረከ እየተጨናበስኩ ተነስቼ ከፈትኩላቸው።ዙሪያዬን በ 'የማነሽ መተታም' አስተያየት ቃኙና "የስራ ቦታሽን ብትጠቁሚኝ ብየ ነው"አሉኝ።ለምንም እንዴትም ሳልል ለሳምንት ቀጠሮ ሰጥቻቸው ከወር አንዴ ወደምሳተፍበት የጥበብ ምሽት VIP አድርጌ ወሰድኳቸው። ጓዶቼ የዛን ቀን የነካቸውን እንጃ ፋሲካ ፋሲካ የሚል ግጥም አብዝተው ነበር።መድረኩ እንደተከፈተ ለወትሮው ሽለላና ቀረርቶ ከአፉ የማይጠፋው ያሬድ "ጡትሽን ያየሁ 'ለት" የሚል ሁለት ገፅ ግጥም አነበበ።አናውቀውምና ነው?!የናቱን ጡት እንኳ 6 ወር አልጠባም'ኮ!እንደው ደርሶ ወግ ይድረሰኝ የሚል ሰው ያበሽቀኛል!ቀጥላ ለሌላው ጊዜ "ኢትዮጵያ" የሚለውን ቃል በጥብጠው የጋቷት የምትመስለው ዙፋን "ድንግል ምናባቱ" የሚል መነባነብ አቀረበች።ቀጥሎ ቢንያም ድምፁን በሚችለው ልክ አሳምሮ "ያዝ እጇን...ዝጋ ደጇን...ሳም ጉንጯን..."ብሎ ወረደ።ይሄ እርጉም አዝማሪ!ባለፈው ወር'ኮ "አጥንቴም ይከስከስ" ሲል ነበር።ወይኔ!በየመሃሉ አያ መሌን ሳያቸው መዳፋቸው ላይ አገጫቸውን ተክለው በሌላኛው እጃቸው በከዘራቸው ወለሉን እየቀበቀቡ በሆዳቸው 'ወይ ወላድ!' ሲሉ ሰማኋቸው።የኔን "ቀበቶውን ፈታሁት" የሚለውን ወግ ቢሰሙ እመር ብለው ተነስተው በቁንጥጫ እንደሚያልመዘምዙኝ ያለ ነቢይ ፍንትው ብሎ ታየኝና ቀስ ብዬ ይዣቸው ወጣሁ።መሽቶ ስለነበር ብለው ይሁን የሚሰድቡኝ ግራ ገብቷቸው ይሁን እንጃ ማታውን ምንም አላሉኝም። ጧት ወረቀቶቼን ሰብስቤ ልወጣ ስል በረንዳቸው ላይ ተፎልለው "ጊዜወርቅ" አሉኝ። "አያ መሌ ደኅና አደሩ?" "አይለቅበት ለመድሃኔዔለም!...ምነው ማታ መድረኩ ላይ ሳላይሽ?" "ው...ውይ አያ መሌ የፃፍኩትን'ኮ ረስቸው ሄጄ..." "ነው?" "እ...እንደው ዝንጉ ነኝ ሲፈጥረኝ" አልኳቸው።ቅማል የበላቸው ይመስል ጉያቸው ስር ከቁፋሮ መለስ ያለ ዘመቻ አካሄዱና አንድ ሲዲ አውጥተው "ይኸንንስ አልረሳሽውም?"አሉኝ።እማይበጃችሁ ይድረቅና ድርርርርቅ ብዬ ቀረሁ!ያ ሰላቢ እያሱ ለፅሁፍሽ ይረዳሻል ብሎ የዛሬ ሳምንት የሰጠኝ የፈረንሳይ ፊልም ነው።ሌላው ይቅር...ምናለ አይቼው ቢሆን?በቃ የምናቤ እስረኛ ሊያረጉኝ ነው።ቢበዛ french kiss ቢኖረው ነው...ባስ ካለ ቢላፉና ቢተሻሹ ነው...እንደው ይሉኝታ ካጡ እሱ ቀሚሷን ቢገልብ ነው (ያንንም ለብሳ ከሆነ)...እኔን ከቤት ማስባረር ከፈለገች እግሯን ልትከፍተው ትችላለች...አናቷ ይከፈት! "ጊዜወርቅ" ብለው ከምናቤ መንጥቀው አላቀቁኝ። "አይከፈትም!"አልኩ በደመነፍስ ። "ምኑ?" "እ...ድንበራችን ለጠላት አይከፈትም!" "ሆሆሆይ!...በይ እንኪ ከጥራጊው ጋር አውጥተሽ ጥለሽው እመቤት ናት አግኝታ ያስገባችው የጠቀመ እንደሁ ብላ..."ሲሉኝ ቅዱስ ሚካኤል ከገነት የጠራኝ ነው የመሰለኝ።ተቀብያቸው ልሄድ አልኩና ...ያው የነገር ማግኔት አይደለሁ?ዘወር ብዬ "አያ መሌ..."አልኳቸው። "አቤት" "የማታውን ወደዱት?" "እኒያ ሁላ እንዳንች ደራሲ ናቸው? "አ...አዎ ፀሃፊዎች ናቸው" " 'የጡቷ ስር ሙቀት እንደሳት እንደሳት ክኒና ግዙልኝ ገደለኝ ትኩሳት' ያለውም?" ያሬድ ውጋት ይረድህ! ሰው እንዴት በግራ ጆሮው ሰምቶ እንዲህ ይሸመድዳል በጣድቁ? "እ...አዎ ነው"አልኩ ምንተ ሀፍረቴን። "እህምምምም...'እሳት ነው ብላቸው ቅቤ እየቀቡኝ እስተነ ድንግሌ ንስሃ አስገቡኝ' ያለችቱም?"አሉኝ። አይ ዙፋን!ዙፋንሽን አፈር ይነቅንቀው!እግራቸው ስር የተቀመጠችዋን ድመት አይቼ 'ይቺ ድመት 'ሚያው' ሳትል ሶስት ጊዜ ልካዳት ይሆን?'ብዬ ባስብም በፍርድ ቀን ታስጠይቀኛለችና
Показать все...
👍 15 6👏 2🔥 1
"አ...አዎ..." አልኩ። "እዚህ ግቢ አይናቸውን እንዳላይ አደራ" አሉኝ ማስጠንቀቂያም ልመናም በሚመስል ቃና።ኧረ እንኳን አይናቸው ሊታይ ስልካቸውም አይመለስም። ዋል አደር ስንል ግን ማን ወሬውን እንደሚያቀብላቸው እንጃ "ደሞ ትናንት እዛ እመድረኩ ላይ ወጠሽ 'መንግስትን እንገልብጥ' ብለሻል አሉ"... "ዛሬ ደሞ ያች የበቀደሚቱ ጋለሞታ 'አባይን ተሻግሮ አባይ አለ ወይ እንደ እህል እንደ ውሃ እ*ስ ይጦ'ማል ወይ' አለች አሉ"... "ሰልስትና 'ለታ ደሞ ያ አዝማሪ 'ጉራ ብቻ' ብሎ ዘፍኖ ከንቲባው እኔን ነው ብሎ ይፎገላል አሉ"... አሉ...አሉ...አሉ...አሉ...ምርርርርርርርርር ሲለኝ ጨርቄን ማቄን ሳልል ልወጣ ያምረኝና...ትዝዝዝ ሲለኝ ለካ ከዘካርያስ ፍቅር ይዞኛል።ያች አራስ ሚስቱ ደግሞ ምናባቷ ነው ሳህኔን የማትመልሰው? . . . . . ማዕዶት ዘማርቆስ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. @wegoch @wegoch @paappii
Показать все...
17👏 9👍 4👎 4🔥 2
ማህተብ ፈቶ ቀለበት ማሰር የለም! 'አጅሬ' የምለው...'ጊዜዬ' የሚለኝ አንድ ጌታን የተቀበለ የከንፈር ወዳጅ ነበረኝ።አብሮነታችን ዕድሜ ላይኖረው...ማህተቤን ላልፈታ...ማህተብ ላያስር ነገር...ከማይካደው እውነታ በላይ ብዙ ነገሩ ገዝቶኝ አብሬው መጓዝ ጀመርኩ።ተገኝቼ 'ማላውቅበት ቦታ ከሱ ጋር ተገኘሁ...ስጋ እየፆምኩ ስጋ የበላ እሱን ለመሳም አልግደረደርም ነበር።አንገቱ እስኪዥጎረጎር መጥጬው 'ከጠየቁህ ጊዜ ናት በል' ስል ግዳይ የጣልኩ ይመስለኝ ነበር።ያውም በሁዳዴ...ያውም በአቢዩ! ያወቅሁትኝ ሰሞን የሴት ግሳንግሴን ገፍፌ ጥዬ...እኔው ደዋይ...እኔው መልዕክት ላኪ...እኔው አጥብቆ ጠያቂ እየሆንኩ በእናትነት እና በሚስትነት መሃል የሚቀላውጥ ማንነቴን ጋትኩት።ሰከረ...ስካሩ ዕድሜ ገዛ። በሱ ካስተናገድኳቸው እብደቶቼ ሁሉ የማልረሳው የlipstickኬን ነገር ነው።አንድ ዕለት አክስቴን ልጎበኝ በሄድኩበት lipstickኬ ማለቁ ትዝ ብሎኝ የአክስቴን ልጅ ግዥልኝ ብዬ መላክ...ዘምናኒት ጁስ ጁስ የሚል lipstick ገዝታ መምጣት...ልቀባው ወደ አፌ ሳስጠጋው የጠረኑ ማማር...ተቀብቼ ስቀምሰው የጣዕሙ ነገር...ቴዲ "ሳሙኝ ሳሙኝ የሚል ከንፈር..."ያለው አምለሰት ይኸን መሳይ ተቀብታ ብትጠጋው ነው ብዬ እንድደመድም አደረገኝ። 'ቴዲ አንጋጦ ባየው ከንፈር እንዲህ አጉል ከሆነ አጅሬ ቁልቁል አይቶኝማ እንደምን አይስት!'የሚል ሔዋናዊ ሀሳብ ብልጭ አለብኝና ያንን እንጆሪ እንጆሪ የሚል lipstick አልጋዬ ላይ አስቀምጬ ኩሽና ገባሁ።ከኩሽና ስመለስ እማይበጃችሁ ይድረቅና ድርርርርርቅ ብዬ ቀረሁ...አንድ ከየት እንደመጣ የማላውቀው(በኋላ ሳጣራ የአክስቴ ሰራተኛ ልጅ) በግምት 3 አመት የሚሆነው ህፃን lipstickኬን ይዞ ይመጠምጣል።በድንጋጤ ነጥቄ ስመለከተው እንኳን የሚቀባ የሚታይ የለውም።ህፃኑን አየሁት...የጠባውን ያጣጥማል...'ደሜ ፈላ' ብል ደሜ ራሱ ይታዘበኛል...ተንተከተከ...ተፈናጥሮ ሰው እስኪጠብስ! የሆነ ስላችሁ የጨረሳችሁት ሁነት...በምናባችሁ እንዳማረ ተጀምሮ እንዳማረ የሚጠናቀቅ ሁነት...ሊሆን እንደማይችል ስታውቁት ልባችሁ ይወርድ የለ?እኔ ሁለመናዬ ነው የወረደው...ከእንጥሌ ጀምሮ... ልጁን በልቤ ረገምኩት... 'ከንፈርክን ስማ 'እንደ ወንድሜ ነው 'ማይህ ' ትበልህ'...'አልጋ አስይዛ ፔሬድ ላይ ነኝ ትበልህ!'... 'ፔሬዱ ሲሄድ 'ትንሽ ነው' ትበልህ' ብዬው ሳበቃ "ቤቢ አሜን በል" አልኩት። "አሜን"...ኤታባቱ! እናም እኔ ወለተ ማርያም...የአብማይቱ ማርያም ልጅ...የማርቆሷ ሎጋ...ጠላታችሁን የሎስ ያክንፈውና አስተካክሎ 'ነገ' እንኳን ማለት ከማይችል ደቡቤ ጋር ከነፍኩ።ዘረኛ ነበርኩ...እልልልም ያልኩ ዘረኛ!ወንድ ጎጃሜ ካልሆነ ወንድ የማይመስለኝ!'ሲያናድደኝ የምሰድበው ስድብ እንኳን ካልገባው ምን ላደርገው ነው?' ብዬ የምራቀቂቱ... ''መቼ ይመችሃል?'' ስለው "ነጌ" "እንዴት አርገህ አበጃጀኸው?" ስለው "እንደዚህ እንደዚህ 'አርግቼ' " "እኔ ኦርቶዶክስ...አንተ ጴንጤ...በምን ስሌት አብረን እንሁን?"ስለው " 'እምነት...ተስፋ...ፍቅር እነዚህ ሶስቱ ፀንተው ይኖራሉ፤ከሁሉም ግን ፍቅር ይበልጣል' ነው መፅሐፍ ቅዱስ 'የምለው' " ከሚለኝ አንድ ተላሰስ ጋር...ወደቅሁ። መላመዳችን ሲበረታ...ቅርርባችን ልክ ሲያጣ ጥያቄዎቻችንን ሽሽት ገባን።መሄድ ብቻ!እስከሆነ ቀይ መስመር ድረስ...በድፍረት ጥያቄዎቻችንን ስር ድረስ የማንጠያየቀው የማይቀረውን መለያየት ያራቅን መስሎን ነበር።ጠንካራ አማኝም ባልሆን ፈሪ ነኝ...ነፍስ አባቴ ዘንድ ስከንፍ ሄጄ 'መናፍቅ ወድጄ ልቤ ጠፋ' አልኳቸው። "ወለቴ" "ኧይ አባ" "እምን ድረስ ቀረብሽው?" "ሲሉኝ?" "ተመተቃቀፍ አለፋችሁ?" ሲሉኝ መሽኮርመም "ወለቴ...አደራሽን አረከሰኝ እንዳትይኝ" "ይፍቱኝ አባ" "አዪዪዪዪዪ....አይ ወለቴ...ምነው?ህጉን ስታውቂው?" አሉኝ...የምፈታበት መፅሐፍ ተነበበ...ለሶስት ተከታታይ ቀናት ጠመቁኝ። ህጉ 'ከአህዛብ አትጠጉ' ይላል...እንኳን አንሶላ መጋፈፍ...ማዕድ መካፈልን ያወግዛል...ግን ከህግ በላይ የሚገዛ፣ከውግዘት በላይ የሚያስር መሳሳብ ሲመጣስ?ምኔንም መሰሰት እስካልችል ከተሸነፍኩስ?አጅሬ አንዴ የሆነ መጣጥፍ ሲያነብልኝ "ሰው ከፍቅር የሚቆራረጠው ሰጥቶ መቀበልን ሲሻ ነው...የፍቅር ምክንያቱም ውጤቱም መስጠት ነው...ስለፍቅር የሚደረጉ ዝቅታዎች ሁሉ ከየትኛውም ከፍታ ይልቃሉ...ፍቅር ውስጥ መቀበልን የሚሻ እሱ ቀሽም ነው..." ብሎኝ ነበር።ያለስስት ስለሰጠሁት ሁሉ ደስተኛ ነኝ...አይደፈርን ደፍሬ፣አይተላለፉትን ተላልፌም...ይናፍቀኛል። በስተ መጨረሻ...ተመርቆ ከጊቢ ሊወጣ ሳምንት ሲቀረው "ተጠመቅና ከመሄድህ በፊት እንጋባ" ብዬ እስከምመረቅ ያሉትን ሶስት አመታት በዕምነት ልጠብቀው መዘጋጀቴን ነገርኩት...'ያዲያቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም' እንዲሉ "አንቺ ወደኔ እንዳትመጪ ምንድነው 'ሚያግድሽ? ቤተሰብ ነው?''አለኝ።እርግጥ ነው ቤተሰቦቼ የሚያማልደውን እየሱስ እየመገቡ አላሳደጉኝም...ከነሱ በላይ ግን...ነጌ ምጤ ሲመጣ ማን ሊያዋልደኝ?ማን ጭንቄን ሊያረግብ?የሱ ቀበቶ በቂ አልነበረምና ልቤን ዳር እስከዳር እየከረሰሰኝ...ዘለዓለም የሚመስል ፅልመት እየወረሰኝ...ሸኘሁት...ማህተብ ፈቶ ቀለበት ማሰር የለም። ዘማርቆስ 29/08/16 By @gize_yayeh @wegoch @wegoch @paappii
Показать все...
89👍 43👎 8👏 2🤔 2
"ብቻዬን ስላልተውከኝ አመሰግናለሁ።" ቴክስት ገባልኝ ማሂ ናት "ብቻዬን ስላልተውከኝ አመሰግናለሁ " የሚለው ብቻ በጉልህ ታየኝ ። በቀደም "አብረኸኝ ሁን በጣም ...በጣም ከፍቶኛል" ብላኝ ያለሁበትን ጠቆምኳት ያለሁበት መጣች ። እየጠጣን፣ ትንሽ ፈገግ ቁዝምም እያለች፣ ነፍ ነገር እየቀደድን እየተጫወትን አመሸን ። ወደ ቤቷ መሄድ እንደማትፈልግ ገባኝ ፣ ራይድ ደወልኩ፣ መነሻ እና መድረሻ ተናገርኩ ቤቴ ወሰደን ። ቆሎ ከኮመዲኖ፣ ከፍሪጅ ቢራ አቀርብኩላት ። ቆሎ እየቆረጠምን፣ ቢራ እየጠጣን ቢጃማ አውጥቼ ሰጠኋት እና ሱቅ እቃ ገዝቼ መጣው ብዬ ወጣሁ። ትንሽ የማልገዛውን እቃ እየጠየኩ ቆይቼ ተመለስኩ ቢጃማዬን ለብሳ ቆየችኝ ። ቢጃማዬን ገላዋን አስገብታበት አሳምራዋለች ። መሞናደሏን ቢጃማዬ አሳበቀባት ። አይኗ፣ ሁኔታዋ፣ አወራሯ ሁሉ ነገሯ መሞናደሏን ከልሎታል ። ሰው ስሜትን ሳያነብ ስሜታዊ ከሆነ ምኑ ጋር ነው ስውነቱ ? ትንሽ እንደተጨዋወትን የአልጋዬን አንሶላ ገልጠን ገባን ። አቀፍኳት ሳቅፋት ሰውነቷን ኩምትር እንዳደረገች ነበር ። መሳቀቋ ገብቶኛል፤ ግን እንዳልገባኝ ሆኜ ግንባሯን ሳምኩት። አሳሳሜ 'አትሳቀቂ ይሄው ትከሻዬ' የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ነበር ግንባሯን በታላቅነት በአለሁልሽ ነው የሳምኳት። መልዕክቴ በትክክል ይድረስ አይደረሳት አላወኩም ። ሲያጉረመርም የነበረው ዶፍ ዝናብ ዘነበ አቀፍኳት ፣ በረዳት ወይ አመነችኝ መሰል በደንብ ጥግት ብላብኝ ታቀፈች ። "ለምንድን ነው የምወደው ነገር ሳፈጥበት ገሸሽ የሚለው ?፣ የምጠላው ሳይቀር እኮ መውደድ ስጀምር ጥላ ያጠላበታል ። እያጡ ማዘን እኮ ደከመኝ። እንደ እናቶች ተረግሜ ፣ተደግሞብኝ ወይ ደግሞ አይነጥላ ይሆን? ለማለት ጫፍ ላይ እየደረስኩ ነው። " በለሆሳስ ስታወራ በጨለማው ውስጥ ኩልል ያለ እንባ ያፈሰሰች መስሎኛል ። ይሄን የቅሬታ ድምፅ ከእንባ ውጪ መተንፈስ የሚቻል አልመሰለኝም ። "አይዞሽ ሁሉም በግዜው ይስተካከላል። ሳንካ የሆነብሽ ሁሉ ወደ ጥሩ ይለወጣል ። ትላንት የከበደን ስንት ነገር ቀሎልን የለ?" የበለጠ አቀፍኳት ፤ ደረቴ ላይ ተኛች ። የሆነች ነፍስ አምናኝ የተጠለለችብኝ መሰለኝ ። ሙሉ ሰው የሆንኩ መሰለኝ ። ስጋዬን ችላ ማለት የምችል አይነት ስሜት ተሰማኝ ደረቴ ላይ እንደተኛች በደስታ ፈገግ አልኩ ። እንዳቀፍኳት እንደታቀፈችኝ ለሊት ላይ ነቃሁ፣ አየኋት እንቅልፍ ውስጥ ጭልጥ ብላለች። አምናኝ ባዶ ክፍል ራሷን ገላዬ ላይ ጥላ ተኝታለች ። ደስስ እንዳለኝ ተኛሁ። ጠዋት ቁርስ በላን እና ሄደች። አስራ እንድ ሰአት ከሃያ ቴክስት ላከችልኝ : "ብቻዬን ስላልተውከኝ አመሰግናለሁ። መሄጃ አጥቼ መሄጃ ስለሆንከኝ አመሰግናለሁ።" ቴክስቱን እንዳየሁት አለቀስኩ ። ለመዋሰብ ታግያት ቢሆን ኖሮ እንዴት ነበር የሚሰማት? ብዬ አሰብኩ። አባቴ እግሩ በተቆረጠበት ሰዓት ፣ ስራ በተባረረበት ሰዓት፣ ንብረቱን በተቀማበት ሰዓት፣ የዘመዶቹን የጓደኞቹን የብዙ ሰው ስም እየጠራ "ብቻዬን ተውኝ: ብቻዬን ተውኝ" ብቻውን መተውን እየተናዘዘ በዛው አእምሮ እንደታወከ ስላስታወሰቺኝ ይሆን ብቻ መተው ማለት ትርጉሙ ገብቶኝ ይሆን ? ከብዙ ግዜ በኃላ ቃሉን ስለሰማሁት ይሆን? የአባቴ ሁኔታ አይኔ ላይ ስለመጣብኝ ይሆን? ብቻዬን ስላልተውከኝ አመሰግናለሁ የሚለው 'message' አስለቀሰኝ ። ጌታዬን ወደ ሰማይ አንጋጥጬ አመሰገንኩት ። "መሸሸጊያ ያጣች ድክም ያላትን ነፍስ : በኔ ምክንያት የበለጠ እንዳታዝን ስላደረከኝ አመሰግናለሁ ጌታዬ።" By Adhanom Mitiku @wegoch @wegoch @paappii
Показать все...
94👍 24🔥 2👏 1
ፍቅር እና ቁጥር ስንግባባ ሰሞን እኔ መላመድን ለማምለጥ የምባትል ባተሌ ነበርኩ። የተጣመርኩት ባይኖርም ራሴን ብቻዬን እወደዋለሁ። የማልደራደርበት ማንነት ነበረኝ። ሌሎችን የማደንቅበትና የማከብርበት የማንነት መለኪያያዎችም ነበሩኝ። እሱ ---- አላውቅም የሱን ፍላጎት........ ብቻ አላጣደፈኝም። የተለየ ፍላጎት እንዳለውም ሊያሳየኝ አልተፍጨረጨረም። የሰው ፍላጎት እና ሀሳብ ሲጫንብኝ እንደማልወድ ገብቶታል። ማባበሉ አጥንቶ የቀመረበት ነበር። ጆሮዬ ከአንዴም ሁለቴ ከድቶኛል እና በተቆለጳጰሰ የፍቅር ዓረፍተ ነገር የሚደነግጥ ልብ እንደሌለኝ አውቋል። ቀስ በቀስ ለፍፅምና የተጠጋ እሱነቱን ነው የጋተኝ። በገንዘብ ተተምነው ውድ የሆኑ ስጦታዎች እየገዛ አይደለም ያቀበጠኝ፤ በአንድ አንጎል የምናስብ እስኪመስለኝ ድረስ የሚያስፈልገኝን እና ለልቤ የቀረቡ ስጦታዎችን ነበር የሰጠኝ። ውደጂኝ አላለኝም። እንድወደው ምንም አስተዋፅኦ እንዳላደረገ ዓይነት፣ .....የቀን ተቀን እሱነቱን እየኖረ እንደሆነ ዓይነት ፣....... እኔን ለመማረክ የጨመረው ምናምኒት ትጋት እንደሌለ ፣.......... ለሃጬ እስኪዝረበረብ በሱሱ ለመተብተቤ ያበረከተው ምንም እንደሌለ ሁላ ......ከደሙ ነፃ ነኝ...... እኔ የእለት ተእለት እኔነቴን ነው የኖርኩት ዓይነት እጁን ተለቀለቀ። የሰው ልጅ አዘቦታዊ ማንነት እንዴት እንዲህ እንከን አልባ ይሆናል ብዬ አልጠየቅኩም። በየእለቱ እየገለጠ ያስነበበኝን የማንነቱን ምሰሶዎች ሰብስቤ እሱ ነው ያልኩትን እሱን በልቤ ገነባሁ ፣ በአዕምሮዬ ሳልኩ። ለዚህ ማንነት እጅ ሰጠሁ። እዚህ ጊዜ ላይ ፍቅሩን ፣ ጊዜውን ፣ ጆሮውን ፣ ልቡን ፣ ገላውን ፣ትኩረቱን ያልሰጠኝ የለም። 100% እሱነቱን ያለስስት ነበር የሰጠኝ። እስክበስል ማገዶ እንደምፈጅ ገብቶታል። አልተጣደፈም። ከሞከኩኝ ኋላ እስክበሰብስ እንደምታሽ ገብቶታል። ሱሴ የሆነ ጊዜ ላይ ....... ያለእርሱ ትንፋሽ እንደሚያጥረኝ የገባው ሰዓት ላይ ....... የሂሳብ ቀመሩን ይጫወት ጀመረ። ቀስ በቀስ ከመቶ እሱነቱ ይገምሰው ገባ። ፍቅሩንም ጊዜውንም ጆሮውኑም ልቡንም ገላውንም ትኩረቱንም በግማሽ ቦደሰው። 50% !! ልቤ የምትደገፈው ምርኩዝ ስታስስ የነጠቀኝን ትንሽ ይጨምርበታል። 75%!! ........ ጨዋታው ይሄ ነው። 100 እንደነበር ይጠፋኛል። ካጣሁት ግማሽ ይልቅ የተጨመረልኝ እሩብ ያስቦርቀኛል። ልቤ መልሳ እሱን ማምለኳን ትቀጥላለች። መልሶ ከ75% ወደ 25% ሲወርድብኝ የአየር ቧንቧዬ የጠበበ ያህል ደረቴን ያፍነኛል። መልሶ 25% እሱን ይጨምርልኛል። ግማሽ እሱነቱን እንደነሳኝ አላላዝንም። የጨመረልኝ ያስደንሰኛል። አንድ ቀን ገላውን ለሌላ ሴት አዋሰብኝ። እዚህ ጊዜ ላይ ከሙሉ እሱነቱ 5% ፐርሰንቱን እንኳን አልሰጠኝም። በብዙ ትዕግስት እና ጥበብ ውስጤ የገነባው እሱነቱ ግን አሁንም አልተገመሰም። ወይም በቀላሉ እንዳይፈርስ አድርጎ ከዓለት ገንብቶታል። ወይም ማመን አልፈልግም። ፍንክች አይልም። አልካደኝም። በእንባ ታጅቦ ይቅርታ ጠየቀኝ። ይቅርታውን በአግቢኝ ጥያቄ እና ቀለበት አጀበው። የምለው ገባችሁ? ከአምስት 25% ነዳው አይደል? ያደረገውን ሳይሆን ያደረገልኝን እያሰብኩ ተፍለቀለቅኩ። ስለሚወደኝ አይደል አዳራሽ ሙሉ ህዝብ ጠርቶ ፕሮፖዝ ያደረገኝ? ሶስት ቀን የት እንዳለ እንኳን ሳይነግረኝ ዘግቶኝ ይከርምና በአራተኛው ቀን ለእናቴ ከክርስታል የተሰራ የአበባ ማስቀመጫ ገዝቶ ከች ይላል። ሶስቱን ቀን ረስቼ ለእናቴ ላሳያት ፍቅር እሸነፋለሁ። እሱ ከሚያሳየኝ የዘቀጠ ማንነት ይልቅ በልቤ ያነገስኩት ማነነት ላይ ሙጭጭ አልኩ። በሂሳብ ቀመሩ ተወናበድኩ። የእሱን ስዕል ከልቤ ከማፍረሴ ብዙ ቀን ቀድሞ እኔ ፈረስኩ። የእሱን እውነተኛ ማንነት አምኜ ከመቀበሌ ከብዙ ቀናት ቀድሞ የራሴ ማንነት ጠፋኝ። መላመድን ላመልጠው የምሸመጥጥ አትሌት አልነበርኩ? እሱ ከልቤም ከህይወቴም ሲወጣ ለመሮጥም ለማምለጥም ለማሰብም የተረፈ አቅም አልነበረኝም. ** ** ***** By meri feleke @wegoch @wegoch @paappii
Показать все...
60👍 25😢 15🥰 5👎 2
"በቃኝ" ሳይሆን "በቃችሁ" ይበላችሁ! (አሌክስ አብርሃም) የቤተክርስቲያኗ መሪ ብስጭት ብለው ቢሯቸው ክስ ይዘው የተሰበሰቡትን ሴቶች እያናገሩ ነው! "ተው ብየ ነበር...ዘፋኙ ዘፈን በቃኝ ብሎ ሲመጣ ገና በሩን ሲያልፍ ማይክ እየሰጣችሁ ዘምር ስትሉ .... አርቲስቱ ሲመጣ ገና ከበር ተቀብላችሁ መንፈሳዊ ድራማ ስራ ስትሉ ተው አላልኩም? አካውንታቱ ገና ሲገባ ገንዘብ ያዝ ስትሉ ኧረ ይረጋጋ ትንሽ መንፈሳዊ ነገሩ ይጠንክር ቆይ አላልኩም ? አላልኩም ወይ እህቶቸ ? እናተ ምናላችሁኝ? ቤቱን በእልልታ እያቃጠላችሁ ምናለበት አላችሁኝ! ሰው በቃኝ ብሎ ቢወስንም በውሳኔ ብቻ ፈተና አይገታም! ይማሩ ይደጉ አልኩ! እና አሁን አገልጋይ ባሎቻችንን በዝሙት ጣለቻቸው የምትሏት እህታችን "ሴተኛ አዳሪነት በቃኝ" ስላለች ብቻ የወንድሞች አዳር ፆሎት ላይ ሻይ ታፍላ ብላችሁ መደባችኋት፤ ይሄንንም ተው ብየ ነበር! አሁን ምን አድርግ ነው የምትሉኝ? "ይሄ በቀላሉ የሚታይ አይደለም እንከሳለን" አለች አንዷ በቅርብ የዓለም ነገር በቃኝ ብላ የተቀላቀለች ሴት! መሪው ጠየቁ " እህቴ ወደዚህ ቤ/ክ ከመምጣትሽ በፊት ስራሽ ምን ነበር ?" "በሴቶች ጉዳይ ቢሮ ጠበቃ" አያችሁ ... በቃችሁ ካላለን በስተቀር በቃኝ ስላልን ከዓለም ጋር ያስተሳሰረን እትብት አይቆረጥም! ሰው ይወስናል ውሳኔ የሚጠናው እለት እለት በሚገነባው መንፈሳዊ ማንነት ላይ ነው! አሁን ጨርሻለሁ " ሁሉም በቁጣና በእልህ በየአፉቸው ተንጫጩ! በር ላይ የቆመው ቆፍጣና ጠባቂ ድንገት በሩን በርግዶ ገባና "የምን ብጥብጥና ሽብር ነው? እርምጃ ሳልወስድ በፊት ሁላችሁም ውጡ" አለ በቁጣ! በቅርቡ ወደምእመኑ የተቀላቀለ ፌዴራል ፖሊስ ነበር! ገና ከመግባቱ ጥበቃ አድርገውት! @wegoch @wegoch @paappii
Показать все...
😁 72👍 48👏 9 6🤔 4
የማባልጋት ባለትዳር ነበረች ። ዋና ተግባራችን ወሲብ ነው ። የምንቀጣጠረው ለወሲብ ብቻ ነው ። የምናወራው ስለ ወሲብ ነው ። አንዳችን አንዳችንን የምንፈልገው ወሲብ ሲያምረን ነው ። አጠገቤ ሆና ባሏ ደውሎ ያውቃል: "ሰውዬሽ ደወለ" ብዬ ስልኳን አቀብያት አቃለሁ ። ምንም እንዳልተፈጠረ ስታወራው እርቃኗን አትመስልም ነበር። ይገርመኛል ድድብናችን ። ነውራችን ስለተደጋገመ ተግባራችን ብልግና መሆኑ ተሰወረብን ። ቢሮዋ እሄዳለሁ፣ ቢሮዬ ትመጣለች ። ጓደኛዬ ቤት፣ እኔ ቤት፣ የሆነ ኮስመን ያለ ሰዋራ ቦታ ፣የሆነ ድብቅ ፅድት ያለ ስፍራ ፣ መኪና ውስጥ ... ብዙ ብዙ ቦታ ትመጣለች እንዋሰባለን ። የታሪካችን መነሻ እና መድረሻው ወሲብ ነው ። አንድ ቀን በደነገጠ: ተስፋ በቆረጠ ድምፅ "ባሌ አወቀብን" አለችኝ .....ደነገጥኩ ። ጠፋሁኝ ...ጠፋች ከአስራ ሰባት ቀን በኋላ ጓደኞቼ "ገኒ ሃዘን ላይ ነች፣ ሙሉ ከላይ እሰከታች ጥቁር ለብሳለች፣ ከስታለች" አሉኝ "ምን ሆነች?" አልኩ "ባሏ ሞቶባት ነው፤ ራሱን አጥፍቶ ነው የሞተው" አሉ። ስደነግጥ፣ ፊቴ ሲቀያየር ፣ እምባዬ ሲያመልጠኝ አዝኜለት ነው የመሰላቸው ። እኔ እንደገደልኩት አልጠረጠሩም ። የጥፋተኝነት ስሜት ሊገለኝ ሲል ማምለጫ መፅሃፍ ቅዱስ ገለጥኩ። "ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳል " የሚለው ከሁሉም ጎልቶ ተነበበኝ ። .. ሰው ይዞ መውደቅ ፤ ማስተካከል የማይቻል አወዳደቅ ፣ ሲያስታውሱት የሚያስነክስ አይነት አወዳደቅ፣ እነሳለሁ የማይሉት አወዳደቅ ፣ ወድቄ ነበር የማይሉት አወዳደቅ። በግዜ ምክንያት የማይደበዘዝ አወዳደቅ ... እንደዚህ አይነት መውደቅ ሲ..ያ...ስ..ጠ..ላ !! ! By Adhanom Mitiku @wegoch @wegoch @paappii
Показать все...
😢 44👍 25 8👎 6😱 1
ኒላ ዘ መንፈስ 4 (አሌክስ አብርሃም) በክፍል ሶስት ትረካችን ኢትዮጵያዊቷ ፊደል እና በሂውማን ሄር ሰበብ በውስጧ የገባችው ኒላ የተባለች የሙት መንፈስ (የፀጉሩ ባለቤት ነኝ የምትል) ከብዙ ስድድብና አለመግባባት በኋላ ቀስ በቀስ እርስ በእርስ ማውራት እንደጀመሩ፤ ፊደል ነገሩ በቁጣና በሐይል የማይሆን ስለመሰላት በውስጧ ተቀምጣ እንደ አለቃ የምታዛትን ነጭናጫዋን ኒላን በፀባይ ለመያዝ እንደወሰነች አይተናል። ይባስ ብሎ ኒላ ገና በቀናት እድሜ ስለፊደልና መሰሎቿ ኢትዮጵያዊያን ባህሪ እየጠቀሰች ፊደልን መምከርና መውቀስ ጀምራለች! ቆሻሻ እንደማትወድ በመግለፅ የፊደልን ቤት አስፀድታታለች! ኒላ መንፈስ ናት፤ ከሁለት ዓመት በፊት ህንድ ውስጥ በ24 ዓመቷ በባቡር አደጋ የሞተች ሴት መንፈስ! ከሞቷ በፊት እጅግ የምትወደውና የምትሳሳለት ፀጉሯ «ሂውማን ሄር» ተብሎ ወደኢትዯጵያ ተላከ ! ፊደል የተባለች ታዋቂ ተዋናይት ገዝታ ተጠቀመችበት፤ በዛው ቅፅበት የኒላ መንፈስ በፀጉሩ በኩል የፊደልን ሰውነት ተጋርቶ መኖር ጀመረ! አሁን ፊደል ማለት አንዲት ሴት ግን በውስጧ ሁለተኛ መንፈስ የሚኖርባት ግራ የተጋባች ሴት ሆናለች! ቀጣዩን እነሆ! * * ** * «አንች ህንዳዊ ነሽ ፣ እንደነገርሽኝ ኢትዮጵያን ካወቅሻት ገና የተወሰኑ ቀናት ቢሆንሽ ነው! ግን ስለእኔም ይሁን ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ልክ እዚህ ተወልዶ እንዳደገ ሰው ትናገሪያለሽ ! የምትይውን ነገር ሁሉ እንዴት አወቅሽው? » አለች ፊደል የኒላን ቁጣና ዘለፋ የተቀላቀለበት ምክር በዝምታ ስታዳምጥ ከቆየች በኋላ! «ስለመንፈስ ምንም አታውቂም? ይሄ የሚበዛው ክፍሉ በማይረባ ዝባዝንኬ የተሞላ አዕምሮሽ ለእኔ እንደኮምፒውተር ወይም እንደስልክ ነው አሰራሩ! መንፈስ ሁኘ ውስጥሽ ስገባ ከህፃንነትሽ ጀምሮ እስከአሁን የተጠራቀመ ትዝታሽ ችሎታሽ ፣ባህሪሽ፣ ስሜትሽ ሁሉም ነገር አንች የምታውቂውና የምታስታውሸው ሁሉ እኔ «ሜሞሪ» ላይ ተጭኗል። ግን የምጠቀመው የምፈልገውን ሲሆን የምጠቀመውም በእኔ በራሴ መንገድ ብቻ ነው! የራሴ ህልውና አለኝ ፣የራሴ አስተሳሰብና ስሜት አለኝ፣ የራሴ ችሎታና አረዳድ አለኝ፣ የሌለኝ አካል ብቻ ነው! አካሌ እዛ ህንድ ተቃጥሎ አመዱ ወንዝ ላይ ተበትኗል! ከእንግዲህ እነዛ ውብ የሰውነት ክፍሎቸ ዳግም አይመለሱም! ያ ውብ ፈገግታየ የለም ፣ ስለዚህ ፈገግታሽን እጋራለሁ፣ እነዛ ውብ እግሮቸ እና እጆቸ የሉም ስለዚህ የአንችን እግርና እጅ እጋራለሁ ፣ ከንፈሮቸ የሉም የአንችን ከንፈሮች እጋራለሁ. . . ለዛ ነው እንደአሳማ የሚያገሳና እንደውሻ የሚናከስ ትንፋሹ ጋን ጋን የሚሸት ወንድ እንዲስምሽ የማልፈልው! ሁለታችንም ያልተስማማንበት ወንድ አጠገብሽ አይደርስም! ምክንያቱም ሰውነትሽ ሰውነቴ ነው! ሂሂሂሂሂ ስንት ነገር አለ! የተረፈኝ ብቸኛ መታሰቢያ ይሄ አንች አናት ላይ የተቀመጠው ፀጉሬ ብቻ ነው! ይሄ ፀጉር ሁሉ ነገሬ ምድር ላይ የቀረኝ ብቸኛ መታሰቢያ ነው። ጓደኞቸ የምወዳቸው ቤተሰቦቸና ነፍሴን የምሰጥለት ፍቅረኛየ ሁሉም ተረት ናቸው አሁን!ለዘላለም አብረውኝ አይኖሩም! ህይዎት እንዴት አጭር ናት? " አለች ባዘነ ድምፅ! «ፀጉርሽ እንዴት ተረፈ ግን?» በቤተሰቦቸ እምነት ሴት ልጅ በህይዎት ዘመኗ ሁለት ጊዜ ፀጉሯን ለምናመልክበት ቤተ መቅደስ ትሰጣለች፣ ልክ እንደስዕለት ነው! አንድ ከማግባቷ በፊት፣ ትዳሯ እንዲባረክ (ይሄ በፍላጎት የሚደረግ ነው) ሁለተኛው በወጣትነቷ ከሞተች! እንደገና ስትፈጠር በመልካም ሰው ወይም እንስሳ እንድትፈጠር! እኔ ግን አንች ውስጥ ተፈጠርኩ ሂሂሂ! ምናልባት ያኔ ፀጉሬን ስቆረጥ ቅር ስላለኝ አምላካችን አዝኖብኝ ይሆናል። ልክ እናተ አስራት መባ ስጦታ እንደምትሉት ነው! በበሃላችን ፀጉር የመጨረሻው የሴት ልጅ ክብር አንዲት ሴት ለምታመልከው ጣኦት ፀጉሯን መስጠቷ ክብሯን ኩራትና ፀጋዋን ሁሉ ለአምላኳ የመስጠት ጥልቅ መንፈሳዊ ትርጉም አለው! ወይም ከቸገራት ፀጉሯን ሸጣ ኑሮዋን ልትደጉም ትችላለች! ማንም ሴት ቸግሯት ፀጉሯን ስትሸጥ ደስ ብሏት አትሄድም ከእንባ ጋር ነው! «ቤተመቅደሱ ፀጉሩ ምን ያደርግለታል?» አለች ፊደል ቤተመቅደሱ ፀጉሩን ሰብስቦ ሂውማን ሄር ለሚያዘጋጁ ካምፓኒዎች ይሸጠዋል ! ካምፓኒዎቹ አዘጋጅተው ወደመላው ዓለም ይሸጡታል! የእኔም ፀጉር በዚሁ መንገድ ነው የሚመጣው! እኔ የመጀመሪያውን ፀጉሬን በሰጠሁበት ቀን ስድስት ሺ ሴቶች ሰጥተዋል። ወደሁለት ቶን ፀጉር ማለት ነው! ሁለት መቶ ኩንታል ማለት ነው! ይሄ አንዲት ትንሽ ከተማ ላይ ብቻ ነው፤ በመላው ህንድደግሞ ብዙ ሚሊየን ኩንታል ይሆናል! አሁን የገረመኝ ከዛ ሁሉ ጉድ ፀጉር ስንት አገር እያለ እንዲህ አይነት ከአመት አመት ፀሐይና አቧራ የማይለየው፣ ዜጎቹም ግራ የተጋቡበት አገር መንቃቴ ! ይባስ ብሎ እንደአንች አይነት በዚህ ዕድሜዋ እንደ 11 ዓመት ልጅ የምታስብ ሴት ውስጥ መኖሬ . . .» አለች። ፊደል ፈገግ አለችና «ግንኮ በዕድሜ እበልጥሻለሁ ለምን አታከብሪኝም ኒላ?» «እሱማ አገራችሁም በዕድሜ ስንቱን አገር ትቀድማለች ? ግን አሁንም ገና ትላንት እንደተመሰረተ አገር እንደተወዛገበች እንደተደናበረች ነው! ጉራ ብቻ! ገና ጡጦ ላይ እኮናችሁ! የሶስት ሽ ዓመት ሚሚ ! » ፊደል ዝም አለች! አገር ጅኒ ጃንካ ይደክማታል። ፊደል ቀኑን ሙሉ ከተማ ወጥታ ልብስና አስቤዛ ስትገዛ ውላ ተመለሰች! ኒላ ልብስ ታመራርጣት ነበር። በአንዳንድ ምርጫቸው ስለማይጋቡ መጨቃጨቃቸው አልቀረም! ፊደልን ከሩቅ የሚያይዋት ሰዎች «ለየላት» ይላሉ! በተቻላት መጠን ዝም ለማለት ብትሞክርም የኒላ ጭቅጭቅ ዝም የሚኣስብል አልነበረም። እንደውም በአንድ ቀሚስ ከለር ምርጫ ስላልተግባቡ ወደቤት ሲመለሱ ተኮራርፈው ነበር። ፊደል ሻዎር ወስዳ ራት በልታ ወደምኝታዋ ስትሄድ ኒላ ድንገት ወሬ ጀመረች «እኔ የምልሽ ፊደል . . .ለምን የፌስ ቡክ አካውንት አትከፍችም ?» "አለኝ ምን ያደርግልኛል! " ለአንች ማን አለሽ ? እና ለማን ነው ? ለእኔ ! እንዴ ጭራሽ ? ምን ችግር አለው? በስሜ ክፈችልኝ ጓደኞቸን አገሬን ቤተሰቦቸን ማየት እፈልጋለሁ! የድሮ አካውንቴን ባስብ ባስብ ማስታወስ አልቻልኩም! ይመስለኛል የእኔን ሜሞሪ ፕሮሰስ የሚያደርገው የአንች አዕምሮ ማስታወስ ላይ ትንሽ ደከም ያለ ነው መሰል ሂሂሂ ! እና ፌስቡክ አካውንት ያለው መንፈስ ልትሆኝ? አለች ፊደል ነቆራዋን እንዳልሰማ አልፋ! በነገሩ ግርምት ተፈጥሮባት ነበር። አዎ! ክፈችልኝ! በዛውም የፍቅረኛየን የእኔን የድሮ የጓደኞቸን ፎቶ አሳይሻለሁ! ፊደል ጉጉትና ፍርሃት ተቀላቀለባት ! ግን ጉጉቷ አሸነፋት! ይች ከሁለት አመት በፊት ሞትኩ የምትል ሴት ምን ትመስል ይሆን? እውነት ናት አንደሰው ምድር ላይ ኑራ ነበር? ጓጓች ! «ከፈለግሽ ምን ቸገረኝ» አለችና ወደማንበቢያ ጠረጴዛዋ ሄደች! ውስጧ ግን የሆነ የጅል ስራ እንደምትሰራ እየነገራት ነበር። ላፕቶፗን ከፈተችና «እሽ በምን ስም ልክፈትልሽ? » ኒላ N I L A ፊደል ስሙን አስገባች ! ድንገት ግን ኒላ በሳቅ ፍርስ አለች ! ሂሂሂሂሂ ሂሂሂሂሂሂ ካካካካካኣ ምን ያስቅሻል?
Показать все...
👍 26 9🤔 1