ከስነ-ፅሁፍ ዓለም
前往频道在 Telegram
✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን https://t.me/Ethiobooks ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።
显示更多📈 Telegram 频道 ከስነ-ፅሁፍ ዓለም 的分析概览
频道 ከስነ-ፅሁፍ ዓለም (@ethiobooks) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 10 311 名订阅者,在 书籍 类别中位列第 3 697,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 3 222 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 10 311 名订阅者。
根据 06 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 27,过去 24 小时变化为 7,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 9.91%。内容发布后 24 小时内通常能获得 3.00% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 1 022 次浏览,首日通常累积 309 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 7。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል!
የቻናላችን https://t.me/Ethiobooks ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ።
ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ
@firaolbm እና
@tekletsadikK ተጠቀሙ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 07 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 书籍 类别中的关键影响点。
10 311
订阅者
+724 小时
+177 天
+2730 天
数据加载中...
吸引订阅者
十月 '2610月 '26
十月 '26
+28
在0个频道中
九月 '26
+59
在1个频道中
Get PRO
八月 '26
+72
在1个频道中
Get PRO
七月 '26
+92
在0个频道中
Get PRO
六月 '26
+72
在0个频道中
Get PRO
五月 '26
+68
在0个频道中
Get PRO
四月 '26
+50
在1个频道中
Get PRO
三月 '26
+43
在0个频道中
Get PRO
二月 '26
+34
在0个频道中
Get PRO
一月 '26
+56
在0个频道中
Get PRO
十二月 '25
+36
在2个频道中
Get PRO
十一月 '25
+40
在0个频道中
Get PRO
十月 '25
+37
在0个频道中
Get PRO
九月 '25
+31
在1个频道中
Get PRO
八月 '25
+35
在1个频道中
Get PRO
七月 '25
+40
在0个频道中
Get PRO
六月 '25
+41
在0个频道中
Get PRO
五月 '25
+32
在0个频道中
Get PRO
四月 '25
+46
在2个频道中
Get PRO
三月 '25
+49
在1个频道中
Get PRO
二月 '25
+38
在0个频道中
Get PRO
一月 '25
+77
在2个频道中
Get PRO
十二月 '24
+91
在4个频道中
Get PRO
十一月 '24
+60
在1个频道中
Get PRO
十月 '24
+42
在1个频道中
Get PRO
九月 '24
+9
在1个频道中
Get PRO
八月 '24
+11
在1个频道中
Get PRO
七月 '24
+27
在1个频道中
Get PRO
六月 '24
+21
在1个频道中
Get PRO
五月 '24
+65
在0个频道中
Get PRO
四月 '24
+58
在3个频道中
Get PRO
三月 '24
+72
在0个频道中
Get PRO
二月 '24
+44
在0个频道中
Get PRO
一月 '24
+52
在0个频道中
Get PRO
十二月 '23
+49
在0个频道中
Get PRO
十一月 '23
+52
在0个频道中
Get PRO
十月 '23
+51
在0个频道中
Get PRO
九月 '23
+49
在0个频道中
Get PRO
八月 '23
+138
在0个频道中
Get PRO
七月 '23
+51
在0个频道中
Get PRO
六月 '23
+50
在0个频道中
Get PRO
五月 '23
+32
在0个频道中
Get PRO
四月 '23
+51
在0个频道中
Get PRO
三月 '23
+49
在0个频道中
Get PRO
二月 '23
+25
在0个频道中
Get PRO
一月 '23
+60
在0个频道中
Get PRO
十二月 '22
+59
在0个频道中
Get PRO
十一月 '22
+34
在0个频道中
Get PRO
十月 '22
+39
在0个频道中
Get PRO
九月 '22
+49
在0个频道中
Get PRO
八月 '22
+54
在0个频道中
Get PRO
七月 '22
+67
在0个频道中
Get PRO
六月 '22
+43
在0个频道中
Get PRO
五月 '22
+67
在0个频道中
Get PRO
四月 '22
+54
在0个频道中
Get PRO
三月 '22
+49
在0个频道中
Get PRO
二月 '22
+61
在0个频道中
Get PRO
一月 '22
+87
在0个频道中
Get PRO
十二月 '21
+118
在0个频道中
Get PRO
十一月 '21
+107
在0个频道中
Get PRO
十月 '21
+207
在0个频道中
Get PRO
九月 '21
+222
在0个频道中
Get PRO
八月 '21
+279
在0个频道中
Get PRO
七月 '21
+184
在0个频道中
Get PRO
六月 '21
+157
在0个频道中
Get PRO
五月 '21
+90
在0个频道中
Get PRO
四月 '21
+88
在0个频道中
Get PRO
三月 '21
+127
在0个频道中
Get PRO
二月 '21
+68
在0个频道中
Get PRO
一月 '21
+103
在0个频道中
Get PRO
十二月 '20
+18 991
在0个频道中
| 日期 | 订阅者增长 | 提及 | 频道 | |
| 07 十月 | +1 | |||
| 06 十月 | +7 | |||
| 05 十月 | +5 | |||
| 04 十月 | +8 | |||
| 03 十月 | +4 | |||
| 02 十月 | +2 | |||
| 01 十月 | +1 |
频道帖子
ልጅነቴና ቲቪያችን
━━ 📺 ━━
✍ መሐመድ ሰልማን
'
ድሮ የእኛ ቤት ቲቪ ክብር ነበራት። ትምህርት ካቋረጠው ታላቅ ወንድሜ ይልቅ ቲቪያችን በሰፈራችን የተሻለ ትከበር ነበር። የሰፈር ልጆች ከእኔ ጋር ጓደኛ ለመሆን ከፍተኛ ፉክክር ውስጥ ይገቡ የነበረውም በዚሁ ምክንያት ነው። ከእኔ ጋር የሚፈጥሩት ወዳጅነት በእኛ ቲቪ "120" ለማየት የይለፍ ወረቀት እንዲሆናቸው ብቻ ነበር።
"120" ድሮ እንዴት ውብ ነበር መሰላችሁ! "120" ድሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳምንታዊ ድግስ ነበር። አንዳንድ ኮበሌዎች ፍቅረኞቻቸውን፣ «እሁድ እንገናኝ፤ "120" ልጋብዝሽ» ይሉ ነበር። ቀልዴን አይደለም።
በአንዳንድ ሰፈሮች ደግሞ ልክ እንደዛሬው ፕሪምየር ሊግ የአርሴና ማንቼን ጨዋታ እናሳያለን እንደሚሉት «120 እናሳያለን፤ መግቢያ 25 ሳንቲም» የሚሉ ቤቶች ነበሩ። አንድ የሰፈርህ ልጅ «እኛ ሰፈር እኮ ጉደኛ "120" ቤት ተከፈተ» ካለህ «የኔ ሰፈር ካንተ ሰፈር ይበልጣል» እያለህ ነው ማለት ነው። ያኔ ድሮ "120" የብዙ ዜጎችን ሰንበት ውብ የማድረግ ከራማ ነበረው። ...
በተለይ የአፍሪካ ዋንጫ ሲቃረብ የሰፈሬ ልጆች ያሳዩኝ የነበረው ፍቅር የአሜሪካና የእስራኤልን ወዳጅነት ያስንቃል። ለምሳሌ ትምህርት ቤት ኳስ እየተጫወቱ እኔ ድንገት ከመጣሁ ተሽቀዳድመው ኳሷን ወደኔ ይልኳታል። ቀጥለው «እኔ ነኝ ያቀበልኩት» ብለው ይጣላሉ። ኳሷን ትንሽ አንቀርቅቤ እሰጣቸዋለሁ።
ተቧድነው እየተጫወቱ ከሆነ ደግሞ አንዱ ተጫዋች ለእኔ ሲል እንዲያርፍ ይደረግና እኔ እገባለሁ። አጥቂያቸው ያደርጉኛል። በረኛውን አልፈውም ቢሆን ጎል እኔ እንዳገባ ያቀብሉኛል። በረኛው እኔ ኳስ እየገፋሁ ከመጣሁ መርበትበት ይጀምራል። እግሩ ቄጤማ ይሆናል። ተከላካዮችም እንዲሁ።
እኔ የሞከርኩት ኳስ ፎሪ ወጥቶ ቢሆንም ዳኛው "ጎል" ብሎ ያጸድቀዋል። እንደ አንግል የምንጠቀመው ጃኬትና ሹራቦቻችንን በመሆኑ የዳኛ ውሳኔ ይግባኝ የለውም። የኔን ሙከራዎች ጎል ብሎ ካልወሰነ ከአቢዲ ፔሌ ጋር መቆራረጡ ነው። ያኔ በኛ ጊዜ አቢዲ ፔሌ "ቬጂቡም" ቅባት ሲቀባ ማየት የማይናፍቅ ልጅ አልነበረም።
የአፍሪካ ዋንጫ እንዳለቀ «ቁጩ» ጓደኞቼ ፍቅራቸው መቀዝቀዝ ይጀምራል። ከዓለምና ከአፍሪካ ዋንጫ ባሻገር የሰፈር ልጆች እኔን የሚወዱኝ ዐርብና ቅዳሜ ነው። እሁድን "120"ን እኛ ቤት ለማየት።
ሳሎናችንና ቲቪያችን
ቲቪያችን "ናሽናል" ነበረች። ልክ እንደ ቤተሰቡ አባል ነበር የምትታየው። በአንድ ወቅት "ሽሽሽሽ..." ማለት ጀምራ ቤተ ሰባችን መሀል ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጠረ። ዘመድ ሲመጣ መጀመሪያ "አሰላሙአለይኩም" ከማለቱ በፊት "ቴሌቢዥኗ በጎ ሆነች?" ይላል።
እናቴ 'አይወዱንም' ከምትላቸው ዘመዶቻችን በቀር የቲቪያችንን መበላሸት ላልነገረችው ዘመድ የለም። አንዳንድ ጠላቶቻችን ለምን ደስ ይበላቸው በሚል የቲቪያችንን መበላሸት ሚስጥር አድርጋባቸው ቆይታለች።
ያን ሰሞን ሠራተኛችን «አንቺ ጦሰኛ! ነካክተሽው ነው ቲቪው "እሽሽሽሽ" ማለት የጀመረው» ተብላ ከፍተኛ እንግልት ደረሰባት። እኔም አስር ጊዜ እንደ ጦጣ ጣርያ ላይ እየተንጠላጠልኩ የቤተሰቡን ኃዘን አንቴና በመነካካት ለማስታገስ የበኩሌን ጣርኩ። ስወርድ ልክ እንደ ዩሪ ጋጋሪን ደማቅ አቀባበል ተደረገልኝ።
ለሦስት ተከታታይ ቀናት የእንጀራ መሶባችንን እንደፈለኩ እንድጎበኘው ልዩ መብት ተሰጠኝ።
ናሽናል ቲቪያችን የሳሎናችን አድባር ነበረች። እንደ እንጀራ ሌማት ዳንቴል ለብሳ፣ እንደ ታቦት በሰው ታጅባ፣ እንደ መስጊድ ሚናራ አንቴናዋን ሽቅብ ቀስራ ሳሎናችን ላይ በክብር ስትሰየም ሁሉም የቤተ ሰብ አባል በስስት ያያት ነበር።
ቤት ውስጥ ልጆች ስንላፋ "ትወድቃላችሁ" የሚለን አልነበረም፤ «ልጆች ቲቪውን ትጥሉታላችሁ» ነበር የምንባለው። ልጅ እያለሁ ወደፊት አባቴ ከወደደኝ የሚያወርሰኝ ይህቺን እጅግ የታፈረች ቲ ቪ እንደሚሆን አስብ ነበር። በአባዬ ዘንድ ጥሩ ልጅ ለመባል እተጋ የነበረውም ለዚህ ነበር።
አሁን ግን አላህ የልጅነት ምኞቴን እንዳያሳካው በርትቼ እጸልያለሁ።
━━━━━━━━━━
📔 ፒያ ሳ - ማሕሙድ ጋ ጠብቂኝ!
🗓 መስከረም 2004 ዓ.ም.
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/Ethiobooks
| 2 | sticker.webp | 245 |
| 3 | ፓ ር ላ ማ
━•✦•━
ፓርላማ ወይም የተወካዮች ምክር ቤት የሚባለው የሕግ አውጪ ምክር ቤት ነው። ቃሉ የመጣው ከፈረንሳይኛ ቋንቋ ሲሆን ትርጉሙም መነጋገር ማለት ነው። በአብዛኛው ሚኒስትራዊ አስተዳደር በሚከተሉ ሀገሮች ይተገበራል።
በኢትዮጵያም ሕዝቦች በየአምስት ዓመቱ
የሚመርጧቸው ተወካዮቻቸው የሚገኙበት ምክር ቤት ነው። ስያሜውም «የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት» በመባል ይታወቃል።
የበርካት ሀገራት መንግሥታዊ ምክር ቤቶች "አሴምብሊ"፣ "ኮንግረስ"፣ "ፓርላማ" ... በሚሉ ስያሜዎች ይጠራሉ። ነገር ግን ለየት ያሉ ስያሜዎችን የሚጠቀሙ አገራትም አሉ። ከነዚህም በጥቂቱ የሚከተሉት አገራት ይጠቀሳሉ፦
➥ የሩሲያ ፓርላማ «ዱማ» ይባላል።
➥ የህንድ ፓርላማ «ሎክ ሰብሀ» እና «ራጅያ ሰብሀ» በሚል ስያሜ ይታወቃል።
➥ «ሀውስ ኦፍ ሎርድ» እና «ሀውስ ኦፍ ኮመን» ተብሎ የሚጠራው የብሪቲሽ ፓርላማ ነው።
➥ የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ፓርላማ «ሴኔት» እና «ኮንግረስ» ይባላል።
➥ «ሾራ» ተብሎ የሚጠራ ፓርላማ ያላት አገር አፍጋኒስታን ናት።
➥ የእስራኤል ፓርላማ መጠሪያ «ክኔሴት» ነው።
➥ የጃፓን ፓርላማ «ዳይት» ይባላል።
➥ «ትሶግዱ» የሚባል ፓርላማ ያላት አገር ቡታን ነች።
➥ የባንግላዴሽ ፓርላማ «ጄትያ ሳንሳድ» ተብሎ ይጠራል።
➥ የጀርመን ፓርላማ «ቡንደስትራ» (ታች ቤት) እና «ቡንደስታግ» (ላይ ቤት) በመባል ይታወቃል።
➥ «ፎርኬቲንግ» የዴንማርክ
➥ «ስቶርቲንግ» ደግሞ የኖርዌይ ፓርላማዎች መጠሪያ ነው።
➥ የስፔን ፓርላማ «ኮርቴስ ጄኔራሌስ»
➥ የኔፓል «ራሽትሪያ ፓንቻያት»
➥ የታይዋን «ዩዋን»
➥ የፖላንድ ፓርላማ «ሰይም»
➥ የሞንጎሊያ «ኩራል»
➥ የኦማን «ሞናርኪ»
➥ የግሪክ «ቼምበር ኦፍ ዲፒዩቲስ»
➥ የሳኡዲ አረቢያ «መጅሊስ አል ሹራ»
➥ የኡዝቤኪስታን «አሊይ መጅሊስ»
➥ የኢራን፣ የአዘርባጃን፣ የማሌዢያ እና የማልዲቭስ ፓርላማዎች ደግሞ «መጅሊስ» በመባል ይጠራሉ።
━━━━━━━━━━━
ምንጭ ➢ የዕውቀት ማኅደር
እና ➢ ድረ-ገፅ
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/Ethiobooks | 496 |
| 4 | sticker.webp | 474 |
| 5 | ዊሊያም ዊልበርፎርስ - 2 የመጨረሻው! | 698 |
| 6 | ዊሊያም ዊልበርፎርስ - 1 | 693 |
| 7 | ▶ ዊሊያም ዊልበርፎርስ
━━━━━━━━
«የባሪያዎች ጠበቃ»
@ethiobooks | 689 |
| 8 | sticker.webp | 696 |
| 9 | እሳትና ጥበብ
══✦══
✍ ሄኖክ በቀለ
'
ሰዎች እንዲህ ናቸው
°
የትዕዛዝ ዳዴ
ይጎትትህና - ስትጀምር መራመድ
እሳት ይሰጡሃል - ሸፋፍነው በአመድ
°
ከሩቅ ይሆኑና ...
ከቤትህ ቃጠሎ ...
የሚግተለተል ጢስ - ይጠባበቃሉ
ግማሹ ተቃጥሎ
ግማሹን አተረፍን - አጠፋነው ሊሉ
°
ብልጥ ከሆንክ ግን
ከምላስ 'ሚወጣ - ፍሙንም ተቀበል
ከድርጊት 'ሚመጣ - ግለቱን ተቀበል
አመዱን ገላልጠህ - ጥበብ አክልበት
ሊያቃጥሉህ ሲሹ - አንተ ብሰልበት።
═══════
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/Ethiobooks | 845 |
| 10 | sticker.webp | 751 |
| 11 | ም ላ ስ
👅 👅
👅
ምላስ ይቀባል፣ ጥርስ ይወጋል።
👅
ምስጢረኛ ምላስ የለውም።
👅
ምላስ ከጥርስ፣ እጅ ከልብስ።
👅
የተቀማጭ፣ ምላሱ ምላጭ።
👅
ምላሱ አይታጠፍም።
👅
የባለስር፣ ምላሱ አስር።
👅
ምላስ ቢጥም፣ ቀዶ ይጠቅም።
👅
መልካም ምላስ ቁጣን ታበርዳለች።
👅
ባንድ ራስ፣ ሁለት ምላስ።
👅
ምላስ ያስቀጣል፣ ስለት ይቆርጣል።
👅
ቀይ ምላሱ፣ ጥቁር ራሱ።
👅
በምላስ የተወጋ፣ ቢታከም አይድንም።
👅
ያላረፈች ምላስ፣ ሸማ ትልስ።
👅
የሰው ምላስ መንታ፣ አንዱ ለሙገሳ አንዱ ለሐሜታ።
👅
ምላስ አጥንት የለው፣ ግን አጥንት ይሰብራል።
👅 👅
ነገር በምሳሌ
@ethiobooks | 925 |
| 12 | sticker.webp | 684 |
| 13 | መልካም ምላስ ቁጣን ታበርዳለች
━━━━━✦━━━━━
✍ ከበደ ሚካኤል
'
እናቱ በጣም አድርጋ የምትወደው አንድ ልጅ ነበር። እሱም ከዐጥር ግቢያቸው ውስጥ ከሚገኙት የኮክ ዛፎች ላይ እየወጣ ፍሬውን ሲቆርጥ እናቱ ብዙ ጊዜ ታየው ነበርና ከዛፉ ላይ ወድቆ አደጋ ያገኘዋል በማለት ስለሰጋች እንዳይወጣ መላልሳ ብዙ ጊዜ ከልክላው ነበር።
አንድ ቀን ከቤት ውስጥ ሆና እንደ ልማዱ ከኮኩ ዛፍ ላይ ፍሬ ሲለቅም በመስኮት አየችው። ከቤት ሲገባ ጠርታው "ከዛፍ ላይ አትውጣ ብዬ ከልክዬህ አልነበረምን? ለምንድን ነው ዛሬ ደግሞ የወጣኸው?" ብላ ጠየቀችው።
እሱ ግን ደንግጦ "አልወጣሁም" ብሎ ካደ። እሷም በጣም ተቆጣችና "ደግሞ ከማጥፋትህ መዋሸትህ ይባስ። ባይኖቼ እያየሁህ ትክደኛለህ?" ብላ ልትመታው ተነሣች።
እሱም አሳዛኝ የሆኑትን ዐይኖቹን እያንከራተተ ለዛ ባለው አንደበቱ "እማማ እወድሀለሁ ትዪኛለሽ፣ እንደምትዪኝም እውነትም የምትወጂኝ ከሆንሽ ባይኖችሽ ካየሽው ይልቅ እኔ የምነግርሽን አብልጠሽ ማመን ይገባሻል" አላት።
ደማሙ ልጅ ይህን ማለቱ 'ስለ እኔ ፍቅር ብለሽ ያየሽውን እንዳላየሽ አድርገሽ አሳልፊው እንጂ በጥፋቴ ለምን ትሞግቺኛለሽ?' ብሎ መለማመጡ ነው።
እናቱም በዚህ ለዛ ባለው ንግግር ከቁጣዋ በርዳ በመምታት ፈንታ ልጅዋን አቅፋ ሳመችው። ዐይኖችዋም ዕንባ አቅርረው ይታዩ ነበር።
━━━━━━━━━━
📔 ታሪክና ምሳሌ - ፩ኛ መጽሐፍ
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/Ethiobooks | 860 |
| 14 | sticker.webp | 683 |
| 15 | • ጓደኛችሁ በፍቅር ዘርታችሁ •
በምስጋና የምታጭዱት ማሳችሁ ነው
━━━━━✦━━━━━
✍ ካህሊል ጅብራን
'
አንድ ወጣትም አለው፦ «ስለ ጓደኝነት ንገረን?»
እሱም እንዲህ በማለት መለሰለት፦
«ጓደኞቻችሁ ለፍላጎቶቻችሁ ምላሽ ናቸው። ጓደኛችሁ በፍቅር ዘርታችሁ በምስጋና የምታጭዱበት ማሳችሁ ነው። ገበታችሁና የምትሞቁት እሳታችሁም ነው...
«በራባችሁ ጊዜ ወደ እሱ የምትሄዱትን ያህል በሰላም ጊዜስ አትፈልጉትምን?...
«ጓደኛችሁ ከአዕምሮው ጋር ሲነጋገር በገዛ አዕምሯችሁ ውስጥ ስላለው ‹አሉታ› አትስጉ። ‹አዎንታ›ንም አትንፈጉት። ዝም ባለ ጊዜ ልባችሁ፣ ምኞቶችና ተስፋዎቻችሁ ሁሉ ቃላትን መጠቀም ሳያስፈልግ ያለ ሆታና ጭብጨባ ተወልደው በወዳጅነት የምትጋሯቸው ነገሮች ናቸውና...
«ከጓደኞቻችሁ ስትለያዩ አትዘኑ። ለተራራ ወጪ ሰው ተራራው በግልጽ የሚታየው ከሜዳው ላይ ሆኖ እንደሆነ ሁሉ፣ ከሁሉ አስበልጣችሁ በምትወዱት ሰው ውስጥ ያለው ብዙ ተወዳጅ ነገር የበለጠ ግልጽ ሆኖ የሚታያችሁ እሱ በሌለበት አይደለምን?...
«እናም በጓደኝነት ውስጥ ከመንፈስ ጽናት በስተቀር ሌላ ምንም አላኖራችሁም...
«የገዛ ራስን ምስጢር (ምኞት) ለመፍታት ከመሻት በስተቀር ሌላን የማይፈልግ ፍቅርስ ዋጋ ቢስ ነገሮችን ብቻ ለማጥመድ ወደ ባህር የተወረወረ መረብ እንጂ ፍቅር ሊሆን ይችላልን?...
«ደግሞም ለጓደኛችሁ የተቻላችሁን ያህል መልካም ሁኑለት። የልባችሁን ባህር የማዕበል ሞገድ ማወቅ ካለበት የውኃ ሙላቱን (ጎርፍንም) ጭምር ይወቅ...
«በጣዕረ ሞት (በመቀበሪያ) ጊዜያት ልትፈልጉ የሚገባችሁ የቱን ጓደኛችሁን ነው? ሁልጊዜም በፍስሃ (በሕይወት) ጊዜያት ፈልጉት። ባዶነታችሁን ሳይሆን ፍላጎታችሁን መሙላት የሚገባው እሱ አይደለምን?...
«በጓደኝነት ጣፋጭ ጊዜያት ውስጥ ሳቅና ደስታን መጋራት ይኑር። ልብ ንጋቱን (ብርሃኑን) አግኝቶ የሚታደሰውስ በጥቃቅን ነገሮች ጤዛ ውስጥ አይደለምን?»
━━━━━━━━━━
📔 የጠቢባን መንገድ
ትርጉም ➢ ሀብታሙ ተስፋዬ
📄 40 - 41
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/Ethiobooks | 985 |
| 16 | sticker.webp | 736 |
| 17 | ቅዱስ መርቆርዮስ - 2 የመጨረሻው! | 1 044 |
| 18 | ቅዱስ መርቆርዮስ - 1 | 1 061 |
| 19 | ▶ ቅዱስ መርቆርዮስ
━━━━━━
«ባለ ሁለት ሰይፉ ሰማዕት»
@ethiobooks | 1 068 |
| 20 | sticker.webp | 879 |
