cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን https://t.me/Ethiobooks ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
11 453
المشتركون
-224 ساعات
-167 أيام
-4530 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

‹ገድ› እና 13 ቁጥር ━━━✦━━━ በተለምዶ 13 ቁጥር የገደቢስነት ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ እምነት የተጀመረው የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት ገደማ ሲሆን አስራ ሁለቱ ሐዋርያት እና ኢየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻውን የጌታ ራት ለመብላት በማዕድ ዙሪያ ተቀምጠው ሳለ ቁጥራቸው 13 እንደነበር እና በነጋታው ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ራሱን እንዳጠፋ፣ ክርስቶስም ተይዞ ስቅላት እንደተፈረደበት ከሚገልፀው ታሪክ ጋር ተያይዞ የመጣ ነው። ይህ ስሜት የአስራ ሦስትን ገደቢስነት በሰዎች አዕምሮ ውስጥ አሰረጸ። ➥ 13 ቁጥርን አጥብቆ የመፍራት ስነ-ልቦናዊ አባዜ ‹ትሪስካ ዴካ ፎቢያ› ይባላል። ➥ በብዙ አገሮች ሆቴሎች ውስጥ 13 ቁጥር አልጋ የለም። በአያሌ አይሮፕላኖች ውስጥም 13 ቁጥር መቀመጫ የለም። በአንዳንድ ቦታዎች 13 ቁጥር በሎተሪ ቲኬት ውስጥ አይካተትም። ➥ በትላልቅ ሆስፒታሎችም እንደሚታየው 13 ቁጥር አልጋ እንዳይኖር ይደረጋል። በህሙማን ላይ ስነ-ልቦናዊ ጫና እንዳይፈጥር በመስጋት ብዙ የኦፕሬሽን ክፍሎች 13 የሚል መለያ ቁጥር እንዳይኖራቸው ተደርጓል። ➥ በአንዳንድ አገሮች 13 እና አርብ ሲገጥም አያድርስ ፍርሃት ያመጣል። በዚህም ምክንያት የወሩ አስራ ሦስተኛ ቀን አርብ ላይ ከዋለ በተለይ የግል ድርጅት ያላቸው ባለሀብቶች ወደ ሥራቸው አይገቡም። በዚህም በብዙ ሚልዮን ዶላር የሚቆጠር ኪሳራ ይደርሳል። ➥ በአስራ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን ካፒቴን ጂም ፍሪይዴይ የተባለ መርከበኛ በዕለተ አርብ በወሩ አስራ ሦስተኛው ቀን ‹HMS Friday› የተባለች መርከብ ይዞ ጉዞውን ቀጠለ። አሳዛኙ ገጠመኝ ግን መርከቡም መርከበኛውም በዚያው እንደወጡ መቅረታቸው ነው። እስከ አሁን ድረስ የመርከቢቷ ደብዛ አልተገኘም። ➥ አሜሪካኖች ጨረቃ ላይ በመንኩራኩር ለመድረስ አስር ጊዜ ሙከራ አድርገው ሳይሳካላቸው ቀረና በአስራ አንደኛው ሙከራ አፖሎ 11 በተባለች መንኩራኩር የሰው ልጅ ጨረቃ ላይ ሊወጣ ችሏል። ቀጥሎ አፖሎ 12 ተላከች፤ አሁንም ተሳካ። ➥ በማስቀጠል አፖሎ 13 ተላከች ነገር ግን ሙከራው ሳይሳካ ቀረ። አፖሎ 14 የተባለች መንኩራኩር ስትላክ ሙከራው በሚገባ ግቡን መታ። እንደዚህ ዓይነት ከ13 ቁጥር ጋር የተያያዙ በርካታ ምሳሌዎችን ማቅረብ ይቻላል። ➥ ለአንዱ ‹ገደ-ቢስ› ቁጥር ለሌላው የእድል ቁጥር ሊሆን ይችላል። ጣልያን ውስጥ በአንዳንድ ስፍራዎች 13 ቁጥር ተወዳጅ ቁጥር ነው። እንዲሁም ለግራኞች ‹ገድ› አለው ተብሎ የሚታመንበት ቁጥር 13 ነው። ━━━━━━━━ 📔 የዕውቀት ማኅደር ✍ በዶክተር ኬ.ኬ. 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks
إظهار الكل...
ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን

https://t.me/Ethiobooks

ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።

👍 4🤔 3
ገዴ /ገድ ገድዬ/ ══ 🐦‍⬛️ ══ ✍ ካሕሳይ ገ/እግዚአብሔር ' ገዴ ልዩ ባህርይና አኗኗር ካላቸው የአሞራ ዓይነቶች አንዱ ነው። መልኩ ከሆዱ (ከደረቱ) በኩል በጣም ነጭ ሆኖ ጀርባው ጥቁር ነው። በመሆኑም ከሩቅ ሲያዩት ከስር ነጭ ኩታ ለብሶ ከላይ ጥቁር ካባ የደረበ ካህን (ቄስ) ይመስላል። ገዴ በትግራይ፣ በዋግ ሕምራና በከፊል ሰሜን ጎንደር ገድ ገድዬ እየተባለ ይጠራል። ገዴ የደስታ፣ የምስራች፣ የመልካም ነገር ተምሳሌት ተደርጎ ስለሚታመንበት በትግራይ «ገዴ ገድየ ሐጎስ» ብለው የሚጠሩትም አሉ። ሰዎች በመንገድ ሲሄዱ ገዴ ነጭ ደረቱን ወደ እነርሱ አቅጣጫ አዙሮ ቁጭ ብሎ ካጋጠማቸው ያሰብነው ሁሉ ይሳካል፣ መልካም ነገር ያጋጥመናል ብለው ያምናሉ፣ ‹ገድ አውለኝ› ብለውም ጉዞአቸውን በደስታ ይቀጥላሉ። በአንጻሩ ጀርባውን ወደ እነርሱ አዙሮ ካገኙት የፍርድ ቤት ቀጠሮም ቢኖርባቸው ይመለሳሉ እንጂ ቅጣትንና እስራትን ፈርተው አይሄዱም። ገዴ ሲጮኽም ሆነ ሲበላ አይታይም። ይሁንና አንድ ታዋቂ ሰው የሚሞት ከሆነ ማታ በሟቹ ቤት አጠገብ ከበሩ በስተግራ አቅጣጫ ካለው ዛፍ ላይ ሆኖ የተለየ የመርዶ ድምፅ ያሰማል። ሰዎች ይህንን ስለሚያውቁም የታመመ ሰው ካለ ለቀብሩ የሚያስፈልገውን ቅድመ ዝግጅት ያደርጋሉ። የታመመ ሰው ከሌለም «ገዴ ጮኻለች ማን ይሞት ይሆን?» እያሉ ይጨነቃሉ። ገዴ (ገድ ገድዬ) ሌላም አስገራሚ ባሕርያት አሉት። ሴት ገዴ እንቁላሏን የምትጥለው ሰው ከማይኖርበት ቦታ ራቅ ካለ ሥፍራና ከሰዋራ ቦታ ነው። በመሆኑም የገዴ እንቁላል ማግኘት ከባሕር ወለል ድረስ ዋኝቶ እንቊ የማውጣት ያህል ከባድ ነው። በአጋጣሚ ከተገኘ ግን ዋጋው እጅግ ውድ ነው። የጥንት አባቶች በገዴ እንቁላል የተለያዩ ተአምራዊ ተግባራትን ያከናውኑ እንደነበር ይነገራል። ... ሌላው የገዴ አስገራሚ ባሕርይ በተፈለገውና በየጊዜው አለመታየቱ ነው። ከዚህም በላይ የፈለገው አነጣጣሪ ተኳሽ ከቅርብ ርቀትም ቢሆን በጥይት ተኩሶ መምታት አይቻለውም። ገዴ ባገኘው ዛፍ ላይም አይቀመጥም። ገዴ ከዓመት እስከ ዓመት ቅጠላቸው እንደለመለመ በሚቆዩ እንደ ወይራ፣ ዶቅማ፣ ማቅማ በመሳሰሉ ዛፎች ወይም ቋሚ አለት ላይ ነው የሚያርፈው። ━━━━━━━━ 📔 ኅብረ - ብዕር አንደኛ መጽሐፍ 📄 152 - 154 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks
إظهار الكل...
ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን

https://t.me/Ethiobooks

ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።

👍 7
ሄንሪ ኪሲንጀር - 2 የመጨረሻው!
إظهار الكل...
🤔 3
ሄንሪ ኪሲንጀር - 1
إظهار الكل...
🤔 3
▶ ሄ ን ሪ ኪ ሲ ን ጀ ር ━━━━━━━ «ዕድሜያማው ዲፕሎማት» @ethiobooks
إظهار الكل...
አ ት ረ ሳ ም ══✦══ ✍ ሜሮን ጌትነት ' ረስቻታለሁ የለኝም ትዝታ አላስታውሳትም ጠዋትና ማታ ትለኛለህ አሉ ላገኘኸው ሁሉ ምንም ብንራራቅ ባንሆን እንደ ድሮ ያሳለፍነው ጊዜ አይቀርም ተቀብሮ አውቃለሁ አትረሳም መች አጣሁት እኔ ለኒያ ጎረቤትህ ይስጥልኝ እንጂ ዕድሜ ሞክሼ ልጃቸውን በማዕረግ ካልዳሩ ወይ ቤት ካልቀየሩ አትረሳኝም ከቶ ጠዋትና ማታ ስሜን እየጠሩ። ═══════ 📔 ዙ ረ ት 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks
إظهار الكل...
ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን

https://t.me/Ethiobooks

ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።

👍 11😁 1