cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን https://t.me/Ethiobooks ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።

Show more
Advertising posts
11 476
Subscribers
-224 hours
-67 days
-5830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የጅራፍ ንቅሳት ══ ❖ ══ ✍ ኤፍሬም ስዩም ' ከጀርባህ ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት፣ እኛን የመውደድህ የዘላለም እትራት፤ የፋሪስ የሳዶቅ ያለማመን ደባ፣ የጲላጦስ ግርፊያ የሄሮድስ ካባ፣ ከፊትህ የወጣው የደም ጎርፍ እና እንባ፤ ላንተ ስቃይ ናቸው ለእኛ ግን ደስታ፣ መከራህ ነውና የመዳን አለኝታ፤ የመዳን አለኝታ። ጅራፍ እና ቡጢ ምራቅና ሀሞት፣ ለዐይን ደስ የማይል የስቃይ ደም ግባት፣ በደም የተረጩ ቅዱሳት አልባሳት፣ እኚህ ናቸው ውበት የጌታ ደም ግባት፣ የመዳን አለኝታ የዘላለም እትራት። ውዴን ያላያችሁ እኔ ልንገራችሁ፣ ፍቅሩን ላሳያችሁ ድምፁን ላሰማችሁ፤ ምራቅ ተቀብቷል፣ ቡጢ ተቀብሏል፣ ሀጥያት ተሸክሟል፣ በቁንዳላው መሀል የደም ጎርፍ ይፈሳል፣ የፍቅር ንጉሥ ነው የእሾህ አክሊል ደፍቷል። ውዴን ያላያችሁ፣ ድምፁን ላሰማችሁ፣ ፍቅሩን ልንገራችሁ፤ ዐይኑ ፍቅር ያለቅሳል፣ ጎኑ ደም ይረጫል፣ ጽህሙ ተነጭቷል፣ ልብሱ ሜዳ ወድቋል፣ በቃሉም ቅዱስ ነው ይቅርታን ይሰዋል፣ ከፍቅር ትከሻው የዓለም ደዌን አዝሏል። ከጀርባው ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት፣ እኛን የመውደዱ የዘላለም እትራት፤ ለርሱ ስቃይ ናቸው ለእኛ ግን ደስታ፣ መከራው ነውና የመዳን አለኝታ። ይህ ሁሉ ቢሆንም፣ ይህ ሁሉ ቢሆንም፤ የሰው ልጆች ድፍረት ክብሩን አይቀንስም፣ ስለ ሰው መድከሙም ኃይሉን አያወርድም። ስሙ እግዚአብሔር ነው፣ ስሙ ይቅርታ ነው፣ ስሙ መሐሪ ነው። የፈረሱን ብርታት ብቃቴ ነው የሚል፣ ብዛቱን ተማምኖ የሚታበይ ልዑል፣ በሱ ስም ይወድቃል በስሙ ይጣላል። ስሙ ሁሉን ቻይ ነው ሁሉንም አድራጊ፣ ታላቁን የሚጥል ለታናሽ ተዋጊ። ውዴን ያላያችሁ፣ ድምፁን ያልሰማችሁ፣ እኔ ልንገራችሁ፤ ከጀርባው ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት፣ እኛን የመውደዱ የዘላለም እትራት፤ ለርሱ ስቃይ ናቸው ለእኛ ግን ደስታ፣ መከራው ነውና የመዳን አለኝታ። እናም ጌታችን ሆይ፥ ያመኑት ይጽናኑ የወጉህም ይዩህ፣ በደም የተረጩ ልብሶችህን ለብሰህ፣ አሜን! ጌታችን ሆይ ናልን ተመልሰህ!!! ════════ 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks
Show all...
ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን

https://t.me/Ethiobooks

ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።

👍 6🙏 1
👍 1🙏 1
ጉ ል ባ ን ═ ✦ ═ ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው። በጸሎተ ሐሙስ በቤት ውስጥ ከሚፈጸሙ ተግባራት አንዱ ጉልባን ማዘጋጀት ነው። ጉልባን እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ሲወጡ በችኮላ መጓዛቸውን የምናስታውስበት ከእስራኤላውያን የመጣ ትውፊታዊ ሥርዓት ነው። በአገራችን ኢትዮጵያ አብዛኞቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ይህ ሥርዓት ዛሬም በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ ይከበራል።፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከባርነት በወጡ ጊዜ አቡክተው፣ ጋግረው መብላት አለመቻላቸውን ያስታውሰናል። በወቅቱ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መመገብ፣ ንፍሮ ቀቅለው ስንቅ መያዝ የመንገድ ተግባራቸው ነበር። ይህን ታሪክ ለማሰብም በሰሙነ ሕማማት በተለይም በጸሎተ ሐሙስ ቂጣና ጉልባን ይዘጋጃል። በጸሎተ ሐሙስ የሚዘጋጀው ጉልባንና ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል። ይኸውም ጨው ውኃ እንደሚያስጠማ ዅሉ፣ ጌታችንም በመከራው ወቅት ውኃ መጠማቱን ለማስታወስ ነው። ━━━━━━━━ ምንጭ፦ ዊኪፒዲያ 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks
Show all...
👍 6
የመጻሕፍት ዓይነቶች ═══ 📓 ═══ 📚 አልማናክ ➪ ዓመታዊ የዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊና አገራዊ የመረጃ መድብል 📚 አንቶሎጂ ➪ የአንድ ደራሲ ሙሉ ሥራዎች ተጠቃለው የተዘጋጁበት ጥራዝ 📚 አትላስ ➪ መጽሐፈ ካርታ 📚 ቢብሎግራፊ ➪ የዋቢ መጻሕፍት ዝርዝር 📚 ባዮግራፊ ➪ የሕይወት ታሪክ 📚 አውቶ-ባዮግራፊ ➪ ግለ-ታሪክ 📚 ክሮኖሎጂ ➪ ዜና መዋዕል፤ በቀን፣ በሳምንት፣ በወር፣ በዓመት ቅደም ተከተል የተጻፉ ክስተቶች 📚 ዲክሽነሪ ➪ መዝገበ ቃላት (በተመሳሳይ ቋንቋ) 📚 ዲክሽነሪ ኦፍ ኮቴሽን ➪ መዝገበ ጥቅስ 📚 ዳይሬክተሪ ➪ መዝገበ አድራሻ 📚 ኢንሳይክሎፒዲያ ➪ ዓውደ-ጥበብ፤ ከ'ኤ' እስከ 'ዜድ' ያለውን ሁሉ ትንታኔ ያጠቃለለ ባህረ-ዕውቀት 📚 ጋዜተር ➪ የቦታ፣ የከተሞች፣ የአገራት ዝርዝር መግለጫ 📚 ግሎሰሪ ➪ የቴክኒክ ቃላት ፍቺ መጽሐፍ 📚 ላንግዊጅ ዲክሽነሪ (የሙያ) ➪ አስተርጓሚ መዝገበ ቃላት (ከአንዱ ወደ ሌላው ቋንቋ) 📚 ሞኖግራፍ ➪ በአንድ ርዕስ ወይም አጀንዳ ላይ ብቻ ያተኮረ መጽሐፍ 📚 ኖቭል ➪ ረዥም ልብ-ወለድ ታሪክ 📚 ኖቬሌ ➪ አጭር ልብ-ወለድ ታሪክ 📚 ፍሬዝ ቡክ ➪ አዲስ ቋንቋ መልመጃ ትንሽ መጽሐፍ 📚 ሪፈረንስ ➪ የዕውቀት እና መረጃ ማበልጸጊያና የመረጃ ማጣቀሻ መጽሐፍ 📚 ቴክስት ቡክ ➪ መማሪያ መጽሐፍ 📚 'ሁ ኢዝ ሁ' ዲክሽነሪ ➪ የበርካታ ሰዎች ሕይወት ታሪክ አጠር አጠር አድርጎ የያዘ ዓውደ-ሰብ 📚 ይር ቡክ ➪ ዓመታዊ መጽሐፍ 📗 📒 📕 📘 📗 📒 📕 ምንጭ ➢ የዕውቀት ማኅደር 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks
Show all...
ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን

https://t.me/Ethiobooks

ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።

👍 11
የእይታ ክፍተት ══✦══ ለአርባ ዓመታት በሰላም ይኖሩ የነበሩት ባልና ሚስት ካለልክ መጨቃጨቅ ከጀመሩ ወደ አንድ ዓመት ሆኗቸዋል። አለመስማማቱ የጀመረው ባል ሚስትን፣ «ለምጠይቅሽ ጥያቄዎች መልስ አትስጪኝም፣ እኔን የማናገር ፍላጎት ስለሌለሽ መዝጋት ጀምረሻል» በማለት መበሳጨት ጀምሮ ነበር። ለብዙ ዓመታት በፍቅርና በመስማማት ይኖሩ የነበሩ እነዚህ ባልና ሚስት በድንገት እንደዚህ ዓይነት አለመግባባት ሲፈጠርባቸው ጉዳዩ ለወዳጆቻቸው ሁሉ ግራ አጋብቷል። ባልም እንዲሁ ምን እንደሚያደርግ እርግጠኛ አልነበረም። ምክንያቱም የሚስቱን ሁኔታ ሲያጤነው ምንም አልተለወጠችም። ያየው ለውጥ ለሚጠይቀው ጥያቄ መልስ አለመስጠቷ ላይ ብቻ ነው። በተለያየ መልኩ ካስተዋላት በኋላ ግን፣ "በቃ ጆሮዋ እየደከመ መጥቶ ነው" ብሎ ደምድሟል። እርግጠኛ መሆን ግን ፈልጓል። አንድ ቀን ባልየው የሥነ-ልቦና አዋቂ ለሆነው ለአማካሪው ስለ ችግሩ ሊያማክረው ወደ ቢሮው ሄደ። ትውውቃቸው የረዥም ዘመን ስለነበር የሞቀ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ተቀምጠው ማውራት ጀመሩ። ባልየው፣ «ሥራ የሚበዛብህ ሰው እንደሆንክ አውቃለሁ። ሌሎችም ሰዎች ሊያማክሩህ ይጠብቁሃል። ወደ ሃሳቤ ልግባ፤ ባጭሩ ሚስቴ ማድመጥ አቁማለች። እየናቀችኝ ይመስለኝ ነበር፣ አሁን ግን ሳስበው ጆሮዋ መስማት ሳያቆም አይቀርም።» ብሎ ከሚስቱ ጋር ስላለው ችግርና እንዴት ለሚጠይቀው ጥያቄ መልስ መስጠት እንዳቆመች፣ በሁኔታውም ስሜቱ እየተጎዳ እንደሆነ ተረከለት። ይህ የብዙ ዓመታት ልምድ ያለው አማካሪ ገና ታሪኩን በመስማት ላይ እያለ ችግሩ በአንድ ጊዜ ገባው። ምክሩ አጭርና ግልጽ ነበር። «ዛሬ ወደ ቤት ስትገባ ከ20 ሜትር ርቀት ላይ ሆነህ አንድ ጥያቄ ጠይቃት፣ ካልሰማችህ ከ15፣ ከዚያም ከ10፣ ከዚያም ከ5 ሜትር እያልክ በምን ርቀት ላይ ስትሆን መልስ እንደምትሰጥህ አጣራ።» አለው። ሰውየው ወደ ቤቱ ሄዶ የተባለውን አደረገ። ከ20 ሜትር ርቀት ላይ ሆኖ «ዛሬ ራት ምንድን ነው?» ብሎ ጠየቀ፣ መልስ አላገኘም። ይህንኑ ጥያቄ ከ15 እና ከ10 ሜትር ርቀቶች ላይ ሆኖ ሲጠይቅ አሁንም መልስ አላገኘም። ከ5 ሜትር ርቀት ላይ ሆኖ ለአራተኛ ጊዜ፣ «ዛሬ ራት ምንድን ነው?» ብሎ ገና ከመጠየቁ መልሱን በፍጥነት አገኘ። «ሦስት ጊዜ ነገርኩህ፣ አሁን ለአራተኛ ጊዜ ነው የምነግርህ፣ ለራት የተዘጋጀው መኮሮኒ ነው።» ብላ መለሰችለት። ለካስ አልሰማ ያለው ጆሮ የባል እንጂ የሚስት አልነበረም። ባልየው ይህ እውነታ ከገባው በኋላ ወደ አማካሪው ለመመለስ ሙከራ አላደረገም። >>> ━━━━━━━ 📔 እ ይ ታ ✍ በዶ/ር ኢዮብ ማሞ 📄 37 - 38 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks
Show all...
ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን

https://t.me/Ethiobooks

ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።

👍 13😁 4🙏 2
ሱልጣን ሀሰናል ቦልካህ - 2 የመጨረሻው!
Show all...
👍 3
ሱልጣን ሀሰናል ቦልካህ - 1
Show all...
👍 3
▶️ ሱልጣን ሀሰናል ቦልካህ ━━━━━━━━ «ወርቅ የሰገደላቸው ንጉሥ» @ethiobooks
Show all...