EB Media
رفتن به کانال در Telegram
👉መዝናኛ 👉ዜና 🗣 Our YouTube Channel https://youtube.com/@ebmedia123?si=3Zgov2sCJcx1Qla4
نمایش بیشتر1 785
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+347 روز
+28630 روز
در حال بارگیری داده...
کانالهای مشابه
ابر برچسبها
هیچ دادهای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
ژوئیه '26
ژوئیه '26
+61
در 0 کانالها
ژوئن '26
+346
در 0 کانالها
Get PRO
مه '26
+109
در 0 کانالها
Get PRO
آوریل '26
+202
در 0 کانالها
Get PRO
مارس '26
+39
در 0 کانالها
Get PRO
فوریه '26
+9
در 0 کانالها
Get PRO
ژانویه '26
+31
در 0 کانالها
Get PRO
دسامبر '25
+33
در 0 کانالها
Get PRO
نوامبر '25
+30
در 0 کانالها
Get PRO
اکتبر '25
+88
در 0 کانالها
Get PRO
سپتامبر '25
+121
در 0 کانالها
Get PRO
اوت '25
+167
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئیه '25
+79
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئن '25
+20
در 0 کانالها
Get PRO
مه '25
+35
در 0 کانالها
Get PRO
آوریل '25
+83
در 0 کانالها
Get PRO
مارس '25
+183
در 0 کانالها
Get PRO
فوریه '25
+217
در 0 کانالها
Get PRO
ژانویه '25
+341
در 0 کانالها
Get PRO
دسامبر '24
+161
در 0 کانالها
Get PRO
نوامبر '24
+220
در 0 کانالها
Get PRO
اکتبر '24
+197
در 0 کانالها
Get PRO
سپتامبر '240
در 0 کانالها
Get PRO
اوت '240
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئیه '240
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئن '240
در 0 کانالها
Get PRO
مه '240
در 0 کانالها
Get PRO
آوریل '240
در 0 کانالها
Get PRO
مارس '240
در 0 کانالها
Get PRO
فوریه '240
در 0 کانالها
Get PRO
ژانویه '240
در 0 کانالها
Get PRO
دسامبر '230
در 0 کانالها
Get PRO
نوامبر '23
+1
در 0 کانالها
Get PRO
اکتبر '23
+274
در 0 کانالها
| تاریخ | رشد مشترکین | اشارات | کانالها | |
| 08 ژوئیه | +5 | |||
| 07 ژوئیه | +3 | |||
| 06 ژوئیه | +47 | |||
| 05 ژوئیه | 0 | |||
| 04 ژوئیه | +2 | |||
| 03 ژوئیه | +1 | |||
| 02 ژوئیه | +2 | |||
| 01 ژوئیه | +1 |
پستهای کانال
መረጃ‼️
ዩክሬን ለራሺያ ሲዋጉ የነበሩ ኢትዮጵያውያንን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገች‼️
የዩክሬይን የስለላ ተቋም በሩሲያ ጦርነት ‹‹ተሰልፈዋል›› ያላቸውን 34 ኢትዮጵያዊያን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ፡፡
በዩክሬይን መንግስት የስለላ ተቋም ስር የሚንቀሳቀሰው ‹‹አይ ወንት ቱ ሊቭ›› የተሰኘው ፕሮጀክት ዛሬ በሩሲያ ጦርነት ውስጥ እየተሳተፉ ነው ያላቸውን 34 ኢትዮጵያዊያን ስም ይፋ አድርጓል፡፡ ፕሮጀክቱ ይህንን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ‹‹የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጄ ላቭሮቭ ወደኢትዮጵያ የገቡት በአፍሪካ የሚያደርጉት ጉብኝት አንዱ አካል አድርገው ነው፡፡ ይህ ጉብኝታቸው ደግሞ ሩሲያ በዩክሬይን ላይ በምታደርገው ጦርነት የአፍሪካ ዜጎችን ማሰለፏ ከፍተኛ ተቃውሞ መቀስቀሱን ተከትሎ ነው›› ብሏል፡፡
ሚኒስትሩ አዲስ አበባ መግባታቸውን ምክንያት በማድረግም ለሩሲያ ተሰልፈው የሚዋጉ 34 ኢትዮጵያዊያንን ስም ይፋ ለማድረግ መወሰኑን የጠቀሰው ፕሮጀክቱ ከእነዚህ መካከል ቢያንስ 3ቱ መሞታቸውን አስታውቋል፡፡ ፕሮጀክቱ እንደገለፀው እነዚህ ኢትዮጵያዊያን ለሩሲያ ጦር ሀይል የፈረሙት በተለያየ ጊዜ ነው፡፡ እ.ኤ.አ ዲሴምበር 24 ቀን 2024 አ.ም 8ቱ ኮንትራት መፈረማቸውን ጠቅሶ፣ ሴፕቴምበር 1 ቀን 2025 ደግሞ 10ሩ እንዲሁም ኦክቶበር 30 ቀን 2025 በተመሳሳይ 9 ሰዎች ኮንትራት መፈፀማቸውን አስረድቷል፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያዊያን ኮንትራቱን የፈረሙት በቀጥታ ከሩሲያ ጦር ሀይል ጋር ሳይሆን በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች አማካኝነት እንደሆነ አስታውቋል፡፡
አዩዘሀበሻ
=====================
💎⬇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
| 2 | ወርቅ በመዳብ!
(✍️ጋዜጠኛ መላኩ ብርሃኑ እንደፃፈው)
በ1977 አካባቢ የተቀረጸውና ለህዝብ የደረሰው "ሰርጌ ትዝታው" ዘፈን የአስቴር ማስተር ፒስ ነበር ብል አላጋንንም።
ቴክኖሎጂ እንደዛሬው ባልረቀቀበት በዚያ ዘመን እንኳን ዘፈኑ ሲጀምር በ'ችርስ' ከሚጋጭ ብርጭቆ የሚወጣ ድምጽ ከሳቅና ውካታ ጋር ተዳምሮበት የተሰራው ሳውንድ ኢፌክት አድማጩን ፌሽታ ስሜት ውስጥ የሚከት ነበር። ከነዚያ ደስተኛ ሰዎች ሳቅ ጋር አብሮ በአጃቢነት የሚመጣው ትሮምቦን ይሁን ምን በውል ያልለየሁት ሳክስፎን ደግሞ ለሙዚቃው ልዩ የሆነ ውበት ሰጥቶታል።
ይህ ዘፈን ያላገባ ሁሉ የሚወዘወዝበት ፣ ትዝታውና 'ቫይቡ' ዘመን አይሽሬ የሆነ ፣ በትናንቱም በዛሬው ትውልድ የሚወደድ የትዝታችን አንድ አካል ነበር። ዘፈኑ በራሱ የሚያወራው የሰርግ ትዝታ ሆኖ ሳለ አሁን ትዝታ አልባ ችክችካ ሆኖ ሲመጣ በጣም ነው ደስ የማይለው። የዘፈኑን ግጥም የጻፈው ነፍስ ሄር ያየህይራድ አላምረው ቢሰማ ራሱ በዚህ ነገር እጅግ የሚያዝን ይመስለኛል።
ይህ 'ችክችካ' ና ድለቃ ለሰርግ ቤት ከታፊዎች ይጠቅም ካልሆነ በቀር በሙዚቃው 'ሙድ' ወደኋላ በትዝታ መሄድ ለለመደ ጆሮ ምንም ዋጋ የለውም!
"ቆይ ግን ዘንድሮ ስንቱን ነገር ተነጥቀን እንችለዋለን?" ነበር ያለኝ አንድ ሁነኛ ወዳጄ ይህንን ዘፈን ሰምቶ :: እውነቱን ነው... የህይወታችን ትዝታ ሆነው እንፅናናባቸው የነበሩ ነገሮች ሁሉ እየጠፉብን ባዶ ልንቀር እኮ ነው ጐበዝ? ቤታችንን፣ ሰፈራችንን፣ አሁን ደግሞ ሙዚቃችንን . . . ምን ቀረን ግን?
ቆይ እስኪ አንድ ሙዚቃ ብዙ ዓመት ቆይቶ የህዝብ ሀብትና ትዝታ ከሆነ በኋላ መነካካትን የሚከለክል ህግ ግን መኖር የለበትም ?
ሜርድ!
አስቴር ወርቁን በመዳብ ለወጠችው! | 109 |
| 3 | የካሜራ ባለሙያውን ቤተሰብ እንደግፍ!
#Ethiopia | በእንጅባራ ከተማ በሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በደረሰ አሳዛኝ የመኪና አደጋ ህይወቱን ያጣው የካሜራ ባለሙያ ሳሙኤል (ሳሚ) ስርዓተ ቀብር በትውልድ ቦታው ተፈጽሟል።
ሳሙኤል የሁለት ልጆች አባት ሲሆን፣ ታናሽ ልጁ ገና በወራት ዕድሜ ላይ ይገኛል። ባለቤቱም ቋሚ የገቢ ምንጭ ባለመኖሯ፣ ልጆቿን ለማሳደግ የባለቤቷን የፎቶ ስራ ማስቀጠል እንደሚያስፈልጋት ተገልጿል።
አደጋው በደረሰበት ወቅት ይጠቀምበት የነበረው ካሜራ ከጥቅም ውጭ በመሆኑ፣ የእንጅባራ ፎቶ ቤቶች ባለሙያዎችና የስራ ባልደረቦቹ ለባለቤቱ አዲስ ካሜራ ለመግዛት የድጋፍ ዘመቻ ጀምረዋል።
በመሆኑም ወንድማችንን በመዘከር እና ቤተሰቡን በመደገፍ የአቅማችንን ያህል እንድንሳተፍ ጥሪ ቀርቧል።
ለድጋፍ፦
- የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር፡ 1000175765445
- የሂሳቡ ባለቤት፡ ማእዛ ይርጋ ረዳ
- በአካል ለመርዳት የባለቤቱ ስልክ፡ 0930648504
ለወንድማችን ሳሙኤል ነፍስ ይማር፤ ለቤተሰቡም ፈጣሪ መጽናናትን ይስጥ።
📲 ተጨማሪ ወቅታዊ ዜናዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
👉 https://t.me/EBMedia123 | 170 |
| 4 | በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆነ
ቀን፦ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም.
በአዲስ አበባ ከተማ ለ2019 በጀት ዓመት የሚተገበረው የግል መኖሪያ ቤቶች ኪራይ ዓመታዊ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ መጽደቁንና የአከራይ-ተከራይ አዲስ የውል እድሳት ምዝገባ ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤቶች በይፋ መጀመሩን የከተማዋ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።
ይህ የዋጋ ማስተካከያ ውሳኔ በከተማዋ ሰፊ ሳይንሳዊ ጥናት ተካሂዶ የነዋሪውን እውነተኛ የመክፈል አቅም ባገናዘበ መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በኪራይ ገበያው ላይ የሚስተዋሉ ህገ-ወጥና ዘፈቀዳዊ አሰራሮችን በዘላቂነት ለመግታትና የዜጎችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ ታስቦ የተወሰነ መሆኑ ተገልጿል።
አዲሱ አሰራር በአንድ በኩል አከራዮች ወቅቱንና የኢኮኖሚ ሁኔታውን ያገናዘበ ፍትሐዊ ገቢ እንዲያገኙ የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ተከራዮች ከገቢያቸው ጋር የተመጣጠነ ኪራይ በመክፈል ከተደጋጋሚ መፈናቀልና ከስነ-ልቦና ስጋት ድነው የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ ያደርጋል። ይህ እርምጃ በከተማዋ ያለውን የኑሮ ውድነት ጫና በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ ረገድ የጎላ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና መልካም አስተዳደር ፋይዳዎች እንዳሉት ቢሮው አረጋግጧል።
📲 ተጨማሪ ወቅታዊ ዜናዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👉 https://t.me/EBMedia123 | 176 |
| 5 | https://youtu.be/e2mRB3Rk1p8 | 167 |
| 6 | አስቴር አወቀ ~"የሰርጌ ትዝታው" 💔 😭
በመጀመሪያ መነካት የሌለበት ኦርጅናሉ ቅርስ የነበረ "Masterpiece " የሆነ ስራሽ ነበረ...ግን ምን ዋጋ አለው አፈረስሽው ያውም ራስሽ!🙄
~ኦርጅናሉ የቀድሞው "የሰርጌ ትዝታው" የሚለው ዘፈን ቅንብሩ ብቻውን ከኢንትሮ ጀምሮ ወደ ትዝታ ፤ ወዳለፈው የሰርግ ቀን ይዞ ይነጉዳል ምስል እየከሰተ ...ምስጋና ለአቀናባሪዎች ለመኮነን ባንድና ለጥላዬ ገብሬ!
~ታዲያ የቀድሞው የግጥሙ ሀሳቡ ከቅንብሩ ጋር የተስማማና አብሮ ዘፈኑም it is all about 'የሰርግ Memory' ነበር!.....ያገቡ ሰዎች ሲሰሙት ደስ የሚል ትዝታ ይመጣባቸዋል የሰርግ ቀናቸውን በማስታወሱ....ያላገቡ ሰዎች ደግሞ ሲሰሙት የወደፊት ሰርጋቸው እንዴት ሊሆን እንደሚችል እያሰቡ ጥሩ ምስል ይፈጥራሉ በአዕምሯቸው!
~የአሁኑ አቀናባሪሽ (ቢናንዲ) ግን የግጥሙን መልዕክት ሳይረዳ "ደልቂ ደልቂ" ነገር አደረገብሽ.... ቅንብሩ አይደለም ትዝታ ሊጭር ይቅርና በጣም ነው የሚረብሸው... ሲመስለኝ ይሄ አቀነባሪ የሰራልሽ ለዲጄ አስቦ እንጂ ሙዚቃውን ተረድቶ አይደለም!...የሰርጌ ትዝታው ራሱ Nostalgic የሆነ ሙዚቃ ነበር እሱ ግን ሲፈልግ ደመቅ ያለ የጴንጤ መዝሙር vibe አንዳንዴ ደግሞ ዲጄ የሚከፍተው ማስጨፈሪያ ሙዚቃ አስመስሎ ትዝታ መሆኑን ስቶ የዛሬ ማስጨፈሪያ የጊልዶ ካሳ ነገር አደረገው!😭
~በእርግጠኝነት አስቴር ይሄን ሙዚቃ እንደ ድሮው አበጋዙ ሺዎታ ጋር ለመስራት ብታስቢ ወይ "ይቅር ተይ አንስራው" ይልሻል ወይ ደግሞ ቢሰራው እንኳን እንደዚህ አያበላሽውም እሱ...ምክንያቱም ሙዚቃን ያውቃል ሀሳቡን ይረዳል እጅግ ጎበዝ ነውም እና!
~እንደ ሀሳብ "የሰርጌ ትዝታው"ን ድጋሚ ያቀነባርከው ሰውየ ግን ከእንግዲህ ደግመህ ሙዚቃ ባትሰራስ Man....ከገባህ በዚህ ልክ ነው ያናደድከኝ!🙄
~በነገራችን ላይ ሙዚቃውን በኔ ልክ የሰማው ሰውና የሚወደው ሰው ሀሳቤን ይረዳኛል እንዴት እንደተበላሸም ይገበዋል....በደምብ ያልሰማችሁት ሰዎች ግን እኔ "Negative" ነገር እያወራሁ ይመስላቹሀል ስለ አስቴር አትሳሳቱ እኔ አስቴርን በጣም ነው የምወዳት!🙌
~ከአስቴር ሙዚቃ "የተረታሁለት፣ ሙናዬ፣ ካቡ፣ የአይኔ መንከራተት፣ አካል ሰው፣ ለመድክ ወይ ፣ ያለ ስሜ ፣ ይቅር ማመኔ ፣ ፍቅር ፍቅርና የሰርጌ ትዝታው" ሁልጊዜ የምሰማቸው በጣም የምወድላት ስራዎቿ ናቸው አይደለም ድጋሚ መሰራትና ይቅርና አስቴር ራሱ መድረክ ላይ እንድትዘፍናቸው አልፈልግም...የሚበላሹ ስለሚመስለኝ!😭
~አስቴር አወቀ ከአበጋዝ ጋር ሙዚቃ መስራት ማቆምሽ ብዙ ነገር እያጎደለብሽ ነው ...ኧረ የሆነ ሰው ይምከርሽ በሚካኤል!🙏
@Jah Mc እደጻፈው | 198 |
| 7 | بدون متن... | 166 |
| 8 | 🎶 አስቱ ተመለሰች! ❤️
ትዝታችንን እና ልጅነታችንን የሚያስታውሱ ዜማዎች እንደገና ተመልሰዋል። አስቱ በአዲስ አልበም ከአድናቂዎቿ ጋር ተገናኝታለች። እርስዎ አዲሱን አልበም ሰምታችኋል? የወደዳችሁትን ዘፈን በኮመንት አጋሩ! 🎵👇 | 218 |
| 9 | https://youtu.be/MZgLTvtb4bg?si=Mm8jaOeSH9ylX0IG | 216 |
| 10 | ተአምራዊው ምሽት
አርጀንቲና አፈር ልሳ ተነስታ ባለቀ ሰአት ባስቆጠረቻቸው 3 ጎሎች ግብጽን 3 ለ 2 እየመራቻት ነው።
ጨዋታው ሊጠናቀቅጨ 2 ደቂቃ ቀርቷል | 211 |
| 11 | ድምጻዊ ሣሞን«የዘመን ምልክት» አልበሙን ይፋ አደረገ!
በኢትዮጵያ የዘመናዊ ሙዚቃ ዓለም ውስጥ ከዝና ይልቅ ለጥበብ ጥራት ቅድሚያ በመስጠት የሚታወቀው ድምጻዊ ሣሞን ዜማስ፣ በሙዚቃ አፍቃሪያን ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን «የዘመን ምልክት» የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ አልበሙን በይፋ ለሕዝብ አስተዋወቀ።
ይህ አልበም ድምጻዊው ለሙዚቃ ያለው ጥልቅ ተሰጥኦ እና ለጥራት የማይደራደር አቋም ማሳያ ተደርጎ የተወሰደ ነው።
በውስጡ 13 በብቃት እና በጥንቃቄ የተሰሩ የሙዚቃ ስራዎችን የያዘ ነው።
የአሁኑን ትውልድ ስሜት፣ ፍቅር፣ ስብራት፣ ተስፋ እና ራስን ፍለጋ በአንድ ላይ አቀናጅቶ የያዘው ይህ የጥበብ መዝገብ፣ ከሙዚቃ ቅንብር እስከ ግጥም ድረስ የትውልዱን የውስጥ ውጊያና ስኬት የሚያንጸባርቁ የጥበብ ፍሬዎችን አካቷል።
የአልበሙን መውጣት ለየት የሚያደርገው፣ ድምጻዊው ለደጋፊዎቹ ያዘጋጃቸው ሁለት ዋና ዋና የሙዚቃ ክሊፖች በአንድ ጊዜ ይፋ መደረጋቸው ነው። በተለይም የአልበሙ መጠሪያ የሆነው «የዘመን ምልክት» እና ተወዳጅነት ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቀው «ንገርዋት» የተሰኙት የሙዚቃ ስራዎች በምስል እና በድምፅ ታጅበው የሙዚቃ ወዳጆችን እይታ ተጋብዘዋል።
ይህንን የትውልድ አሻራ የሚያሳርፍ የሙዚቃ ስራ ለሁሉም አድማጮች ተደራሽ እንዲሆን የተደረገ ሲሆን፣ ሙሉውን የአልበም ይዘት እና አዳዲስ ክሊፖቹን በድምጻዊ ሣሞን ዜማስ ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናል መከታተል ይቻላል።
በተጨማሪም በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የሙዚቃ አፍቃሪያን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚታወቁ የሙዚቃ ማዳመጫ ፕላትፎርሞች አማካይነት በማንኛውም ሰዓት እና ቦታ አልበሙን ማዳመጥ ይችላሉ ተብሏል።
ሣሞን ዜማስ «የዘመን ምልክት» የጥበብ ስራ ብቻ ሳይሆን፣ ለትውልዱ የማይደበዝዝ አሻራ ለማሳረፍ የያዘው ታላቅ የጥበብ አዋጅ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ አድማጮች ይህንን የጥበብ ጉዞ አብረው እንዲጋሩ እና በየሙዚቃ መድረኮቹ በመታደም የልባቸው አካል እንዲያደርጉት ጥሪ ቀርቧል። | 236 |
| 12 | بدون متن... | 212 |
| 13 | بدون متن... | 1 |
| 14 | ሰርጌይ ላቭሮቭ በድንገት አዲስ አበባ ገቡ‼️
በኢትዮጵያ የሩሲያ ኢምባሲ ባወጣው መግለጫ ሚንስትሩ በአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት በማድረግ ላይ ሲሆኑ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል።ላቭሮቭ የጀሙሩትን የአፍሪካ ጉብኝት ኢትዮጵያን የመጀመሪያቸው ሀገር አድርገዋል። | 238 |
| 15 | ''ብልጽግና ፓርቲ ''በስልጣን ላይ ያለ መንግስት ለሁለት የስልጣን ዘመን ብቻ እንዲቆይ አንፈልግም''
ይህንንም ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በአጀንዳነት ማቅረቡን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አረጋገጡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጣዩ የመንግስት ምስረታ ወቅትም የበዓለ ሲመት ክብረ በዓል እንደማይኖርም ገልጸዋል።
አብይ ይህን ያሉት፤ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 30፤ 2018 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከፓርላማ አባላት ለቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው። በዚሁ የፓርላማ ስብሰባ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፕሬዝዳንትነት የሚመሩት ብልጽግና ፓርቲ ምርጫን በተመለከተ ያሳለፈው ውሳኔ እና በሀገራዊ ምክክር ላይ ያቀረበው አጀንዳ ይገኝበታል።
ከአንድ ሳምንት በኋላ መካሄድ በሚጀምረው ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ ላይ ብልጽግና ፓርቲ ለውይይት ካቀረባቸው አጀንዳዎች መካከል የስልጣን ገደብ አንዱ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ፓርቲው “በስልጣን ላይ ያለ መንግስት ቢበዛ ለሁለት የስልጣን ዘመን ብቻ መቆየት አለበት” የሚል አጀንዳ ማቅረቡን የገለጹት አብይ፤ ይህ በአፍሪካ አህጉር ያልተለመደ እንደሆነ አመልክተዋል።
ሀሳብዎን ያካፍሉን? | 220 |
| 16 | ስለ ኤልሳቤጥ ደስታ መግለጫ " ከቪዚት ከምባታ"
በፎቶግራፍ አንሺ ምስክር ከበደ አማካኝነት ማኅበራዊ ሚዲያውን ያጥለቀለቀው የኤልሳቤጥ ደስታ ምስል አሁን ላይ ሕይወቷን ሙሉ በሙሉ ሊቀይር የሚችል ታላቅ የሥራ ዕድል ይዞላት መጥቷል።
በአሁኑ ወቅት ከተለያዩ ታዋቂ ዓለም አቀፍ የሞዴሊንግ ድርጅቶች እና ታላላቅ ብራንዶች የሥራ ጥያቄዎችና መልዕክቶች እየደረሱን ይገኛሉ።
ይህ አጋጣሚ ኤልሳቤጥ ተፈጥሮ የለገሳትን ልዩ ውበት ለዓለም መድረክ በማሳየት የተሻለና የተቀየረ የሕይወት መስመር እንድትፈጥር ትልቅ በር የከፈተላት ሲሆን፣ ራሷን ከመጥቀም ባለፈም የኢትዮጵያዊነትን ውበት በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ በኩራት እንድታስተዋውቅና ሀገሯን እንድታስጠራ መንገድ የሚጠርግ ነው።
እኛም በ«ቪዚት ከምባታ» በኩል ማኅበራዊ ሚዲያው የፈጠረላትን ይህንን ታላቅ ዕድል ሳታባክን በአግባቡ እንድትጠቀምበት እና አስፈላጊውን የባለሙያ ድጋፍ ሁሉ እንድታገኝ ከጎኗ በመሆን የምንችለውን ሁሉ እንደምናደርግ እያረጋገጥን፣ አዳዲስ መረጃዎችን ተከታትለን የምናሳውቃችሁ ይሆናል።
Via ቪዚት ከምባታ Visit Kambata | 205 |
| 17 | "የቤት ኪራይ ከአብዛኛው ዜጎቻችን ወርሃዊ ገቢ በላይ ሆኗል። በአሁኑ ወቅት በሀገራችን መካከለኛ የሚባል የህብረተሰብ መደብ ጠፍቶ ጥቂት እጅግ የበለፀጉ እና አብዛኛው በድህነት የሚማቅቅ ሁለት መደቦች ሆነዋል " ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) | 201 |
| 18 | 🚨 ሰበር!
“ኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ ብዙ ቢኖርም ሰራተኛ ማግኘት ከባድ ሆኗል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።
ወላጆች ወጣቶችን ከከተማ ውጪ ያሉ የሥራ ዕድሎችን እንዲሞክሩ አሳሰቡ፤ በሀገር ውስጥም ጊዜን በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው ገለጹ።
📲 ተጨማሪ ወቅታዊ ዜናዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👉 https://t.me/EBMedia123 | 192 |
| 19 | 🚨 ሰበር መረጃ
የድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ምክትል ማናጀር የሆነችው ማሕሌት (ሃና) ሰለሞን ከወራት እስር በኋላ በዋስ መለቀቋ ተነግሯል። መረጃው እንደሚያሳየው፣ ፍርድ ቤቱ የጠየቀው የዋስትና ገንዘብ በቴዲ አፍሮ በኩል ተከፍሏል።
📲 ተጨማሪ ወቅታዊ ዜናዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👉 https://t.me/EBMedia123 | 225 |
| 20 | https://youtu.be/hqiprV6n8Lg | 219 |
