cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Ethio Fm 107.8

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
19 388
مشترکین
+1224 ساعت
+757 روز
+23630 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
ፈረንሳይ በዩክሬይን እያደረገችው ያለው ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ሌላ ዓለም አቀፍ ግጭት ሊቀሰቅስ እንደሚችል የሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲን አስጠነቀቁ። ፑቲን በመግለጫቸው የፈረንሳይ ቅጥር ነብሰገዳዮች ለረዥም ጊዚያት በዩክሬይን ተሰማርተው ይገኛሉ ብለዋል። ይህ ደግሞ ሌላ ዓለም አቀፋዊ ግጭት ሊቀሰቅስ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል ፕረዚደንቱ።  ፈረንሳይ በበኩሏ በዩክሬይን ያሰማራችው ምንም አይነት ቅጥር ነብሰ ገዳይ እንደሌለ አስተባብላለች ሲል የዘገበው ሮይተርስ ነው። ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ .ም
نمایش همه...
👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ከ130 በላይ ንጹሃን ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ ኢሰመኮ "ከህግ ውጭ ግድያ፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ዘረፋ፣ የጅምላ እና የታረዘሙ እስራቶች፣ አስገድዶ መድፈር፣ እገታ" ተባብሰው ቀጥለዋል ብሏል በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ከ130 በላይ ንጹሃን ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ገለጸ። ኢሰመኮ እንደገለጸው የትጥቅ ግጭት ባለባቸው በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች እንዳሁም ከግጭት አውድ ውጭ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተባብሰዋል። መረጃዎችን እና ማስረጃዎችን ለመሰበሰብ የተለያዩ አካላትን ማነጋገሩን የገለጸው ኢሰመኮ "ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋ፣ የዘፈቀደ፣ የጅምላና የተራዘመ እስራትና የተፋጠነ ፍትሕ እጦት፣ አስገድዶ መሰወር፣ እገታ፣ እና የሀገር ውስጥ መፈናቀል" እጅግ አሳሳቢ ከሚባሉት የሰብከዊ ጥሰቶች ውስጥ ቀዳሚዎቹ ናቸው ብሏል። በዚህ ሪፖርት ያካተታቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እጅግ አሳሳቢ የሆኑትን እና በምርመራ የደረሰባቸውን ብቻ ነው መሆኑን የገለጸው ኢሰመኮ በተለያዩ ምክንያቶች የዘገዩ ጉዳዮች መኖራቸውን ጠቅሷል። ኢሰመኮ በአማራ ክልል ከየካቲት 15፣2016 እስከ ግንቦት 4፣2016 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ደግሞ ከታህሳስ 15፣2016 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 8፣2016ዓ.ም ተፈጽመዋል ያላቸውን የግድያ እና የዝርፊያ ወንጀሎችን ዘርዝሯል። ኢሰመኮ እንደገለጸው በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በአማራ ክልል የተለያዩ ዞኖች በተፈጸሙ ጥቃቶች 28 ሰዎች ሲገደሉ በኦሮሚያ ክልል ደግሞ 103 ንጹሃን ሰዎች ተገድለዋል።  የተጠቀሱት ድግግሞች ቢለያይም፣ በንጹሃን ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት በማድረስ የፌደራል "መንግሰት የጸጥታ ኃይሎች፣ "ሸኔ" እና "የአማረ ታጣቂዎች መሳተፋቸውን ገልጿል። ኢሰመኮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በሶማሌ፣ በሲዳማ፣ በአፋራ በማዕከላዊ ክልሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የሰብአዊ አስፊ የሚባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ መሆናቸውን በዚህ ሪፖርቱ ጠቅሷል። በአማራ ክልል እና ኦሮሚያ ክልሎች በንጹሀን ላይ የሰብአዊ ጥሰቶች የሚፈጸሙት፣ የፌደራል መንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከታጠቁ ኃይሎች ጋር ከሚያደርጉት ግጭት ጋር በተያያዘ ነው ብሏል ኢሰመኮ። በአማራ ክልል፣ የፌደራል መንግስት የጸጥታ ኃይል ከባለው አመት ሚያዝያ ጀምሮ ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር ግጭት ውስጥ ገብቷል፤ ግጭቱ አሁንም አልቆመም። ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም
نمایش همه...
😢 5👍 2👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
አየርላንድ የፍልስጤምን የሐገርነት እውቅና ዛሬ በይፋ  ሰጠች። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁም በጋዛ ያለውን የሰብአዊ ቀውስ ለማስቆም አለምን እንዲያዳምጡ ጥሪ አቅርባለች። የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሞን ሃሪስ  ካቢኔያቸውን ሰብስበው ውሳኔውን ካጸደቁ በኋላ በሰጡት መግለጫ የአየርላንድ ውሳኔ ተስፋን የሚያንሰራራ ነው ብለውታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ሐገራቸው ነጻና ሉአላዊነቷ የተጠበቀ ሐገረ ፍልስጤም እውቅና እንደሰጡና ካቢኒያቸው ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲመሰረት መስማማቱን ይፋ አድርገዋል። በቅርቡም ስፔይንና ኖርዌይ ለነጻ ሐገረ ፍልስጤም እውቅና እንደሚሰጡ ማስታወቃቸው ይታወሳል ሲል የዘገበው አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ነው። ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም
نمایش همه...
👍 9👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
የምዕራቡ ከለብ  ቼልሲ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬሰካን   ለመሾም ተስማማ ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የሌስተር ሲቲውን አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካን በሀላፊነት ለመሾም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በሰማያዊዎቹ ቤት ለአንድ ተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ያካተተ የአምስት አመት ኮንትራት ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዚህ አመት ከአንድ አመት በኋላ ወደ ፕርሚየር ሊግ የተመለሱት ሌስተር ሲቲዎች ከቼልሲ የካሳ ክፍያ እንደሚያገኙ ተዘግቧል።
نمایش همه...
👍 7
Photo unavailableShow in Telegram
የማንችስተር  ዩናይትዱ   ግሪንውድ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሏል ! ሜሰን ግሪንውድ የላሊጋው ክለብ ሄታፌ የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጡ ይፋ ተደርጓል። ሜሰን ግሪንውድ በውድድር አመቱ ለሄታፌ ባደረጋቸው ጨዋታዎች አስር ግቦች አስቆጥሮ ስድስት ለግብ የሆኑ ኳሶች አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። የውድድር አመቱን ከማንችስተር ዩናይትድ በውሰት ለሄታፌ በመጫወት ያሳለፈው ሜሰን ግሪንውድ በቀጣይ በሄታፌ እንደማይቀጥል ማሳወቁ አይዘነጋም። በጋዲሳ መገርሳ
نمایش همه...
👍 6
"የትጥቅ ትግል አሁንም ድረስ የኢትዮጵያ ራስ ምታት ሆኗል" ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ፡፡ ግንቦት 20 ከዛሬ 33 ዓመት በፊት በዛሬው ዕለት የወታደራዊ መንግስት ደርግ መውደቅን ተከትሎ ለተከታታይ 27 ዓመታት በደማቅ ሁኔታ ሲከበር መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ ባለፉት 6 ዓመታት በዓሉን ካላንደር ይዝጋው እንጂ ከቀደሙት ግዚያት በደበዘዘ መልኩ እየታሰበ ይገኛል፡፡ የዘንድሮው ደግሞ ከቀደሙት ግዜያት በተለየ መልኩ በበርካቶች ዘንድም ሲያወዛግብ ቆይቷል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በቅርቡ ይፋ የተደረገው እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገና ያልጸደቀው "የሕዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበር ረቂቅ አዋጅ" ተከብረው በሚውሉ ብሔራዊ ባላት ውስጥ ግንቦት 20ን አለማካተቱን ተመልክቶ ነው፡፡ ጣብያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም የዛሬ 33 ዓመት እንደነበረው ሁሉ ዛሬም ከሰላማዊ ትግሎች ይልቅ ትጥቅ ትግል ተመራጭ መሆኑ ምክንያቱ ምንድነው ሲል ፖለቲከኞችን ጠይቆበታል፡፡ ከጣብያችን ጋር ቆይታ የነበራቸው የእናት ፓርቲ እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮ ከፍተኛ አመራሮች በዚህ ዙሪያ ሃሳባቸውን ሰጥተውናል፡፡ በቅድሚያ የኦፌኮ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ሙላት ገመቹ ሀገራችን ዛሬ ላይ ድረስ ላለችበት ችግር አንዱ ይህ ትጥቅ ትግል መሆኑን አንስተው፡፡ በተለይም የስልጣን ተዋረዱ ከታች ወደላይ መሆን ሲገባው ከላይ ወደ ታች መሆኑ ችግሩን አብሶታል ይላሉ፡፡ እንደ አቶ ሙላት ሁሉ የእናት ፓርቲው የህዝብ ግንኙነት እና ከፍተኛ አመራር አቶ ዳዊት ከበደ ትጥቅ ትግል እንደ ሀገር ተለማምደነዋል ሲሉ ይገልፁታል፡፡ ሰዎች ሀሳባቸውን በትጥቅ ትግል የሚያሳኩበትና ወደ መንግስት የሚመጡበትን እንደ ባህል የመቁጠር አባዜ ሊያበቃ ይገባል ብለዋል፡፡ የሀሳብ ትግል የመጫወቻ ሜዳዎች ሊመቻቹ ይገባል የሚሉት አቶ ዳዊት ይህን የማዛጋጀት የማመቻቸት ሀላፊነት ያለበት ደግሞ መንግስት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ላለፉት 33 ዓመታት ለውጥ ያላገኘው ይህ የትጥቅ ትግል ዛሬም በሀገራችን እንደ አንድ የፖለቲካዊ መፍትሄ ተደርጎ እየተወሰደ ይገኛል፡፡ እንደ ምርጫ ቦርድ ያሉና ሌሎች ነፃና ገለልተኛ መሆን የሚገባቸው ተቋማት አሁንም ነፃና ገለልተኛ አለመሆናቸውና ጠንካራ ተቋማት አለመፈጠራቸው እንደ ምክንያትም ተነስቷል፡፡ ከጣብያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት እነዚህ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችም ሀገራችን ከዚህ አዙሪት መውጣት ካለባት ሁሉም አካል ሰላማዊ ትግል መምረጥ አለበት መንግስትም የሰላማዊ ትግል ሜዳውን ማመቻት ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በአቤል ደጀኔ ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም
نمایش همه...
😢 5👍 4
#በእርግዝና ወቅት የሚደረጉ ጥንቃቄዎች በእርግዝና ወቅት እራስን ከተለያዩ ነገሮች መጠበቅ ያስፈልጋል። በእርግዝና ወቅት ከአመጋገብ ጀምሮ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም ይነገራል፡፡ ከአመጋገብ ጋር በተያያዘም ያልበሰሉ ምግቦችን መመገብ አይመከርም ይላሉ ባለሙያዎች፡፡ እንዲሁም ያለሀኪም ትእዛዛዝ ከሚገዙ እና ከሚወሰዱ መድሃኒቶች እራሳቸውን መቆጠብ እንዳለባቸው ያነሳሉ፡፡ አንድ ነፍሰጡር በእርግዝና ግዜዋ ማድርግ ስለሚገቧት ጥንቃቄዎች እና መደረግ ስለሌለባቸው ነገሮች ላይ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን የማህፀን እና ፅንስ ሀኪም ከሆኑት ዶ/ር ልንገርህ ተፈራ ጋር ጣቢችን ቆይታ አድርጓል፡፡ #በእርግዝና ወቅት መደረግ ያለባቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? - የአመጋገብ ሁኔታዋን ማስተካከል (የተመጣጠነ ምግብ መመገብ) - አተኛኘቷን ማስተካከል (በጎን በኩል መተኛት) - በእርግዝና ግዜ ሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ይመከራል ይላሉ #መደረግ የሌለባቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? - በጀርባዋ መተኛት - አልኮል መጠጦችን መጠጣት - ማጨስ - አነቃቂ ነገሮችን መውሰድ ይጠቀሱበታል በእርግዝና ወቅት ባይደረጉ ይመከራሉ የተባሉ ነገሮችን አንዲት እናት የምታደር ከሆነ በፅንሱ ላይ የአፈጣጠር ችግር ሊከሰት የሚችልበት ሁኔታ መኖሩን ባለሙያው ይናገራሉ፡፡ እንዲሁም አንዲት እናት በእርግዝና ወቅት አደጋ እንዳለ ማወቅ እና የትኛው ነገር አደጋ ነው የሚለው መለየት ያስፈልጋታል ፡፡ ይህም ማለት ብትደማ ፣የልጁ እንቅስቃሴ ቢቀንስ፣የሽርት ውሀ ቢፈስ ፣አቅም የሚያሳጣ እራስ ምታት ፣ ብዥታ እና ማንዘፍዘፍ የመሰሉ ችግሮች ቢገጥሟት እነዚህ ነገሮች በእርግዝና ወቅት አደጋ እንዳለ አመላካች የሆኑ ነገሮች ስለሆኑ በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋም መሄድ እንዳለባት ደ/ር ልንገርህ ተናግረዋል፡፡ በሐመረ ፍሬው ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም
نمایش همه...
👍 7
Photo unavailableShow in Telegram
በባህላዊ መንገድ የሚካሄደውን የማዕድን ቁፋሮ ማስቆም አልተቻለም ተባለ። በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ በባህላዊ መንገድ የሚካሄደውን የማዕድን ቁፋሮዉ ስራ ማስቆም አልተቻለም ተብሏል። የደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ የማዕድን ስራዎች ፈቃድ መስጠትና ማስተዳደር ቡድን መሪ አቶ በሪሁን አበረ ለጣቢያችን እንደተናገሩት በዞኑ ወደ ሰላሳ የሚደርሱ የተለዩ ቦታዎች እንዳሉ አንስተው ከዚህ ቀደም አደጋ የተከሰተበት ቦታ እና ሌሎቹም ባላቸው ተፈጥሮዓዊ አቀማመጥ ምክንያት ስራ እንዲያቆሙ መጠየቁን ተናግረዋል። ክረምት መምጣቱን ተከትሎ ከዚህ ቀደም የተከሰቱ መሰል አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ማህብረሰቡ ቁፋሮውን እንዲተው በደብዳቤ ብንጠይቅም እስካሁን ሊቋረጥ እንዳልቻለ አቶ በሪሁን ተናግረዋል፡፡ የአካባቢው ማህበረሰብ በቅርብ የኦፓል ማዕድን ለማውጣት በቁፋሮ ላይ እያሉ ዋሻ የተናደባቸው ሰዎች ከደረሰባቸው አሳዛኝ ገጠመኝ ሳይማር ወደ መደበኛው የኦፓል ማዕድን የማውጣት ስራ እንደተሰማራ ህገወጥ እና ስራውንም ማስቆም እንዳልተቻለ ተናግረዋል፡፡ የአካባቢው ማሕበረሰብ ከተፈጠረው አደጋ እንዲማር በደብዳቤ ለሚመለከተው አካል እንዲሁም ለጸጥታ አካላት ብናሳውቅም ቁፋሮው እንዳለቆመ እና በአካባቢው ያለው የጸጥታ ችግርም ድርጊቱን እንዳናስቆም እንቅፋት ሆኖብናልም ብለውናል። የአካባቢው ማሕበረሰብ ኑሮውን መሰረት ያደረገው ያለምንም መሳሪያ በባህላዊ መንገድ በሚደረግ የኦፓል መአድን ማውጣት ስራ ስለመሆኑ ተነስቷል። ከዚህ ቀደም የተፈጠረው አደጋም በባህላዊ መንገድ በሚደረገው ሂደት እና በጥንቃቄ ጉለት በመሆኑ ሌላ ህይወት እንዳይጠፋ አሁንም ለሚመለከታቸው አካላት በደብዳቤ እና በመሰል ዘዴዎች ቁፋሮውን ለማስቆም የሚደረገው ጥረት እንዳልተቋረጠ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ በተለምዶ ቆቅ ውሀ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የኦፓል ማዕድን ለማውጣት በቁፋሮ ላይ እያሉ ዋሻ የተናደባቸውን ሰዎች ህይወት ለማዳን ሲደረግ የነበረው ጥረት በመቋረጡ የተጎጂ ቤተሰቦች ተስፋ በመቁረጥ እርም ማውጣተኣቸው የሚታወስ ነው፡፡ በለአለም አሰፋ ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም
نمایش همه...
👍 8😢 2