EB Media
رفتن به کانال در Telegram
👉መዝናኛ 👉ዜና 🗣 Our YouTube Channel https://youtube.com/@ebmedia123?si=3Zgov2sCJcx1Qla4
نمایش بیشتر2 520
مشترکین
+624 ساعت
+2757 روز
+24930 روز
آرشیو پست ها
2 520
🚨 መቀሌና አካባቢዋ የኔትወርክ መቋረጥ ተመዘገበ
በመቀሌ ከተማና አካባቢዋ የኢትዮ ቴሌኮም የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት በተለያዩ አካባቢዎች መቋረጡ ተሰምቷል።
እንደ አካባቢው መረጃ፣ ችግሩ በከተማዋ ሁሉም አካባቢ ሳይሆን በተለያዩ ስፍራዎች የታየ ሲሆን፣ የሳፋሪኮም አገልግሎት ግን እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
እስካሁን ችግሩን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ይፋዊ ማብራሪያ አልተሰጠም።
2 520
ጀነራል ታደሰ ወረደ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። የቤተሰብ ምንጮች ጀነራሉ ለሻብያ ተላልፈው ሊሰጡ ይችላሉ በሚል ስጋት ውስጥ ወድቀዋል።
📲 ለተጨማሪ መረጃዎች፦
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
2 520
+7
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ዛሬ በጅቡቲ ተገኝተው፣ ከጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ እና ከዳንጎቴ ግሩፕ መስራች አሊኮ ዳንጎቴ ጋር በመሆን ጅቡቲ ዳመርጆግን ከኢትዮጵያ ደወሌ የሚያገናኝ አዲስ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ፕሮጀክትን ይፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ በሁለቱም ጫፎች የሚገነቡ የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናሎችን ያካተተ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በዳንጎቴ ግሩፕ ትብብር እንደሚተገበር አመልክተዋል።
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ ፕሮጀክቱ የነዳጅ ማጓጓዣ ወጪንና መዘግየትን በመቀነስ የኢትዮጵያን የኃይል ዋስትና ለማጠናከር እንዲሁም በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል ያለውን የንግድ መስመር የበለጠ ፈጣንና ዘላቂ ለማድረግ ያግዛል።
ፕሮጀክቱ ከነዳጅ ማጓጓዣ መሠረተ ልማት ባለፈ፣ የአፍሪካውያንን ኢንቨስትመንትና የጋራ ልማት ለማሳደግ የታለመ ሰፊ ኢንቨስትመንት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ/ም
2 520
latest update
የላሊበላ ኤርፖርት በረራዎችን ዛሬ ሰረዘ፤ በኤርፖርቱ ቅርብ ርቀት የፋኖ ሃይሎችና የመከላከያ ሰራዊት ውጊያ ላይ ናቸው። more to follow
2 520
በወልቃይት አቅጣጫ አዲስ ውጊያ‼️
በተከዜ ወንዝ አቅጣጫ በምዕራብ ግንባር አዲስ ከባድ ውጊያ መቀስቀሱ ተገለጸ።
በሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ (ራያ ዋግኽምራ አፋር ሰሜን ወሎ)እየተደረገ ካለው ውጊያ ባሻገር፣ ዛሬ በምዕራብ ግንባር በተከዜ ወንዝ አቅጣጫ አዲስና ከባድ ውጊያ መቀስቀሱን ከግንባር የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል።
ከሌሊት ጀምሮ በአየር እና በድሮን የታገዘ ድብደባ ሲደረግበት በነበረው በዚህ ግንባር፣ በአሁኑ ሰዓት ከወልቃይት ወደ ትግራይ በሚወስደው መስመር በተከዜ ወንዝ በኩል በሁለት አቅጣጫዎች ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል።
የመረጃ ምንጮች እንደጠቆሙት ውጊያው እየተካሄደባቸው ያሉት ሁለቱ ግንባሮች፦
* የጸሊሞይ ግንባር፦ በዋናው ድልድይ በኩል በወልቃይት እና በትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች፣ እና
* የጓል ተከዜ ግንባር፦ በተከዜ ወንዝ ዳርቻዎች ናቸው።
በእነዚህ ግንባሮች እየተካሄደ ባለው ከባድ ውጊያ እስካሁን ድረስ የደረሰው የሰው እና የንብረት ጉዳት አልታወቀም።
2 520
🥺 “በልጅነቴ ወላጆቼ ሞተዋል” — ቢኒያም ሽብሬ
“እኔም የአርባምንጭ ልጅ ነኝ። በልጅነቴ ወላጆቼን አጥቻለሁ። አርባምንጭን በተደጋጋሚ ጎብኝቻለሁ። አሁንም በድጋሚ እንድመጣ ስለጋበዘኝ ማስተር አገረሰላምን አመሰግናለሁ። የአርባምንጭ ነዋሪዎችም ላደረጉልን ደማቅ አቀባበል ከልብ አመሰግናለሁ።” ❤️
#EthioFightNight #BinyamShibre #Arbaminch #VisitGamo
2 520
🏠❤️ ኦብሴና እናቷ የመኖሪያ ቤት ተሰጣቸው!
የኦብሴን አሳዛኝ ጉዳይ ተከትሎ በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ የነበሩት ኦብሴና እናቷ ወይዘሮ ማሜ ባርሴሳ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የመኖሪያ ቤት ስጦታ አበረከቱላቸው።
ይህ ለእናትና ልጅ አዲስ የሕይወት ምዕራፍ፣ የተስፋና የመረጋጋት መጀመሪያ ሆኗል። ❤️
🙏 እንኳን ደስ አላችሁ! አዲሱ ቤታችሁ የሰላም፣ የደስታና የተስፋ ቤት ይሁንላችሁ።
2 520
"ጦርነት የሞቀ ቤት ቁጭ ብሎ ሰበር
ዜና እንደማንጋጋት ቀላል አይደለም"
ጦርነት አስቀያሚ ነው። እግዚአብሔር ሰላሙን ያውርድልን።
ጦርነትን አልደግፍም። ጦርነትን አላውቀውም። ጥሩ የሚባል ጦርነት ግን የለም። መጥፎ የሚባል ሰላምም አላውቅም። በተለይ የርስበርስ ጦርነት የወጣቱን ነፍስ ይበላል። አገር ይበላል። ተስፋን ይበላል። በቀላሉ ስልክህን እየጠነቆልክ ቀነደሸው፣ ለበለበው፣ ሸኘው....እንደምትለው ቀላል አይደለም። ጦርነትን እንደ እግር ኳስ ለመመልከት የምትቋምጡ ፈጣሪ ልባችሁን ያብራላችሁ።
ጦርነት የሞቀ ቤት ቁጭ ብሎ ሰበር ዜና እንደማንጋጋት ቀላል አይደለም። በዚህም በዚያም ከሚወድቁ ዜጎቻችን ጀርባ ህልም አለ፤ ቤተሰብ አለ፤ ደረሰልኝ የሚል እናትና አባት አለ። በጦርነቱ ከሚወድቀው ሰው ጀርባ አሳዛኝ ታሪክ አለ።
እና እባካችሁ ለሰላም ዕድል ስጡ!! ብዙ ሰው አልቆ ወደ ጠረጴዛ ከምትሄዱ፤ ክቡሩ ሰው ሳይወድቅ ለንግግር ተዘጋጁ። አባቶች ጩሁ። የሃይማኖት አባቶች በዚያም በዚህም ለመገዳደል የቆሙ ኃይሎችን መሃል ገብታችሁ መጀመሪያ እኛን ግደሉ በሉ።
እንደ ግለሰብ ያለኝ አቅም ይኼ ብቻ ነው።
ጌታ ያስበን
Daniel Tefera
2 520
🕊️🇪🇹 የሰላም ጥሪ — ኢትዮጵያ ለሁላችንም!
“የጦርነት ጉሰማ ይብቃ! ሰላም ለኢትዮጵያ እና ለህዝቦቿ!”
የተለያዩ አመለካከትና ጥያቄዎች ሊኖሩን ይችላሉ፤ ነገር ግን ልዩነታችንን በጦርነት ሳይሆን በውይይት፣ በመቻቻልና በሰላማዊ መንገድ እንፍታ።
ኢትዮጵያዊ የሆንን ሁላችን የሰላም ድምፃችንን እናንሳ። የትኛውም ክልል፣ የትኛውም ማህበረሰብ፣ የትኛውም ወገን በጦርነት እንዳይጎዳ በጋራ እንስራ።
የድሃ ልጅ ደም አይፍሰስ፤ እናቶች አይልቀሱ፤ ሀገር አትውደም።
🤝 ልዩነታችንን በውይይት
🤝 ችግሮቻችንን በመግባባት
🤝 ወደፊትን በሰላም እንገንባ።
አንድ ሀገር፣ የተለያዩ ህዝቦች፣ አንድ የሰላም ጥሪ። 🇪🇹🕊️
ሰላም ለኢትዮጵያ!
ሰላም ለህዝባችን!
ሼር ሼር ሼር
📲 ለተጨማሪ መረጃዎች፦
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
2 520
😳 “16 ዓመታት ምግብና ውኃ አልወሰድኩም” — ሙሉወርቅ አምባው
በ10 ዓመቷ የምግብ ፍላጎቷ ከተዘጋ በኋላ፣ ላለፉት 16 ዓመታት ምንም ምግብና ውኃ ሳትወስድ እንደኖረች የምትናገረው ሙሉወርቅ አምባው ታሪኳ ብዙዎችን አስደንቋል።
እርሷ የመጨረሻ የተመገበችው ምስር ወጥ በእንጀራ እንደነበር ትናገራለች። በኢትዮጵያና በውጭ ሀገራት ሕክምናዊ ምርመራዎችንም እንዳደረገች ታስረዳለች።
የታሪኳ በስፋት የታወቀው የጉዞ ቪዲዮ አዘጋጁ ድሩ ቢንስኪ ወዳለችበት ሄዶ የዕለት ተዕለት ሕይወቷን ካሳየ በኋላ ነው።
⚠️ ሆኖም 16 ዓመታት ያለ ምግብና ውኃ መኖሯን የሚያረጋግጥ በሳይንሳዊ ቁጥጥር የተደረገ የሕክምና ማስረጃ እስካሁን አልቀረበም።
#Ethiopia #MuluworqAmbaw #EBMedia
2 520
ከአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ
ከውልደት እስከ እርጅናው፣ ከደደቢት በረሃ እሰከ አራት ኪሎ ሽፍትነትና የህዝቦች እልቂት የማይለየው የህወሓት አዛውንቶች ክበብ ከትናንት ሌሊት ጀምሮ በአፋር ህዝብ ላይ መጠነ-ሰፊ ጦርነት ከፍተው አድረዋል።
ህወሓት ለግማሽ ክፍለ-ዘመን በጦርነትና በትውልድ ደም አፍሳሽነት አድጎና ተመንድጎ፣ በምድር ላይ ያለ-ምንም ለውጥ በደም ቁማር ጃጅቶ መኖር የሚፈልግ የቀጠናው ጠንቅ የሆነ ወሮበላ ቡድን ነው።
የኢትዮጵያን መፍረስ ከሚፈልጉ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር የክህደት ሽርክና የገባው የህወሓት ተላላኪ ቡድን ከዛሬ ሌሊት ጀምሮ በአፋር ክልል ኪልበቲ ረሱ ዞን በአብአላ፣ በመጋሌ፣ በወሰማና በሌሎች አካባቢዎች ላይ ሀገር ሰላም ብሎ በተኙት ንጹሐን ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል።
የቡድኑ እኩይ ዓላማው በመጀመሪያ ትግራይን ትውልድ አልባ ማድረግ ስሆን፣ ቀጥሎም ጎረቤት ክልሎችን በመውረር ለዘላለሙ በህዝቦች መካከል የማያበራ ቁርሾና ቅራኔ መፍጠር ነው። ፍላጎቱም በኢትዮጵያ ጠንካራ ሀገረ-መንግሥት እንዳይኖር በማድረግ፣ ሀገራችን ሁሌም ለጠላቶቿ የተንበርካኪነት ሚናን የምትወጣ ሀገር ሁና ማየት ነው።
ከትናንት ጥፋቱ የማይማር ለጥፋትና ለእልቂት የተደራጀው የህወሓት ተላላኪ ቡድን ለፈጸመው ወረራ መራር ምላሽ የሚያገኝ ይሆናል።
ይህ ዘራፊና ነቀርሳ ቡድን የትግራይን ህዝብም ሆነ የኢትዮጵያ ዋነኛ ጠላት ነው። ከአሁኑ ሰአት ጀምሮ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋነኛ ተግባሩ የህዝቦቹን ደህንነት እና ሰላም መጠበቅ ስለሆነ፣ ከሌሎች ወዳጅ ሀይሎች ጋር በመሆን አጸፋዊው ራስን የመከላከል እርምጃ የሚወስድ ይሆናል።
Afar Communication Bureau
2 520
ሰበር መረጃ
የአፋር ክልል መንግስት፤ የህወሓትና ከአጋሮቹ የሚደረገውን ጥቃት እከላከላለሁ ሲል መግለጫ አውጥሏል። በአፋር ግንባር፤ የትብብሩ ሃይሎች ወሳኝ ቦታዎችን ይዘዋል።
2 520
🚨 ጌታቸው ረዳ በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መግለጫ ሰጡ
አቶ ጌታቸው ረዳ በማህበራዊ ሚዲያ ባጋሩት ጽሁፍ፣ የህወሃት አመራሮች በአፋርና አማራ ክልሎች በሚገኙ የመንግስት ይዞታዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጸዋል ሲሉ ጠቅሰዋል።
እንዲሁም በትግራይ የነበሩ አየር ማረፊያዎች በኃይል መያዛቸውንና በዚህም ምክንያት ወደ ክልሉ የሚደረጉ በረራዎች መቋረጣቸውን ገልጸዋል።
በመግለጫቸውም የህወሃት የፖለቲካና ወታደራዊ አመራር እርምጃው ኃላፊነት የጎደለው መሆኑን ተናግረዋል።
📌 ይህ መግለጫ በወቅታዊው የትግራይ ሁኔታ ላይ ምን ያስባሉ? አስተያየታችሁን በኮሜንት አጋሩ።
📲 ለተጨማሪ መረጃዎች፦
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
https://t.me/EBMedia123
2 520
አንጋፋው ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ ከዚህ አለም በሞት ተለየ፡፡
ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ ትናንት ምሽት 1 ሰዓት ገደማ በመኖሪያ ቤቱ በተመላላሽ ነርሶች የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ሳለ በ83 አመቱ ከዚህ አለም በሞት መለየቱን ቤተሰቦቹ ነግረውናል፡፡
ግርማ ነጋሽ ምነው ተለየሺኝ ፣ የኔ ሀሳብ ፣ እንገናኛለን ፣ አልበቃኝም ገና እና በሌሎች ተወዳጅ ዘፈኖቹ ይታወቃል፡፡
የድምፃዊው ቤተሰቦች ዛሬ ለሸገር እንደተናገሩት ግርማ ነጋሽ በአዲስ አበባ ከተማ ፊት በር አካባቢ በ1936 ዓ.ም የተለወደ ሲሆን በፖሊስ ኦኬስትራ በቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ በአሁኑ ብሔራዊ ቲአትር ለበርካታ አመታት በሙዚቃ ስራው አገልግሏል፡፡
ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ የ3 ወንዶችና የ1 ሴት ልጅ አባት የነበረ ሲሆን የቀብር ስነ ስርዓቱም ነገ ከቀኑ በ8 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ይፈፀማል ተብሏል፡፡
#ሽገርኤፍኤም
2 520
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ፣ አክሱም እና ሽረ ከተሞች በዛሬው ዕለት ሊያደርጋቸው የነበራቸውን በረራዎች ሰረዘ
መስከረም፥ 13/2018 ዓ.ም (E-24NA)፦ II በመቐለ ከተማ የሚገኘውን የአሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን የትግራይ ኃይሎች መቆጣጠራቸውን ምንጮች አስታወቁ።
ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ እና ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ ዛሬ ረቡዕ መስከረም 13፤ 2019 ሊደረጉ ታቅደው የነበሩ በረራዎች ስድስት ነበሩ። እነዚህ በረራዎች መሰረዛቸውን በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኃላፊነት ደረጃ የሚሰሩ ምንጭ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል።
በመቐለ ከተማ የሚገኙ ሶስት ነዋሪዎችም ዛሬ ጠዋት ወደ ከተማው የመጣ አውሮፕላን እንደሌለ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
ሌላ የከተማው ነዋሪ በበኩላቸው በመቐለ ከተማ “አብርሃ ካስትል” አካባቢ ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የትኬት መሸጫ ቢሮ ዛሬ ጠዋት በሄዱበት ወቅት፤ “ለጊዜው በረራ ተቋርጧል። በቀጣይ እናሳውቃለን” መባላቸውን ተናግረዋል።
2 520
አዲሱ መንግሥት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ይመሰረታል - አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
****
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መጠናቀቅን ተከትሎ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የመንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡
አፈ-ጉባኤው በመልዕክታቸው 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ 10 ሺህ 438 ዕጩዎች እንዲሁም ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተሳተፉበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ባለው ሁኔታ በስኬት መጠናቀቁን አብራርተዋል፡፡
በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የፌዴራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑንና ተጠሪነቱም ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነ ያስታወሱት አፈ-ጉባኤው፤ የምክር ቤቱ የሥራ ዘመንም በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እንደሚጀምር በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 መደንገጉን አንስተዋል፡፡
እንደዚሁም በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 56 መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ጥምር ድርጅቶች የፌዴራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል እንደሚያደራጅና እንደሚመራ ጠቅሰዋል፡፡
በዚህም መሠረት መስከረም 25 ቀን የመንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡
ለሥነ-ሥርዓቱ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የጠቆሙት አፈ-ጉባኤው፤ በሕዝብ የተመረጠው አዲሱ መንግሥት ቀጣዩን አምስት ዓመታት ሀገርና ሕዝብ የመምራት ኃላፊነት እንደሚረከብ አረጋግጠዋል፡፡
መጪው ዘመን የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የብልፅግና እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል፡፡
