cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

ይህ የኖህቶኤል ሀሳቦች የሚንፀባረቁበት ቻናል ነው። የምትስማሙባቸውን ለወዳጆ ሼር ያድርጉላቸው።🙏 @Noahtoael በማንበብ ብቁ እና ጤናማ እውቀት ያላቸውን ትውልድ እናፍራ! በዚህም ቻናል.! ፦አጫጭር አዝናኝ እና አስተማሪ ታሪኮች ፦ተከታታይ ታሪኮች ፦ትረካዎች ፦ግጥም እና ስነፅሁፎች .......ያገኛሉ!

Show more
Advertising posts
2 576Subscribers
+124 hours
-37 days
-1330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Love is the whisper of the heart, the gentle embrace of souls entwined. It's the warmth of a smile shared in a crowded room, and the silent understanding in a glance. Love is the language of the universe, spoken in countless ways yet understood by all. @Noahtoaels_idea
Show all...
2
Seni seviyorum❤️
Show all...
4🤔 2
የሆነ ጊዜ ነበር ከልቤ ስስቅ የነበረበት፣ ግን ሌላ ጊዜም ነበር በጣም ሳለቅስ የነበረበት፣ ከዛም ሳልፍ ግን በህይወት ላይ ለማዘንም ለመደሰትም ጊዜ እንዳለዉ ያመንኩበት፥ የሆነ ጊዜ ነበር ለህይወት መጓጓት የጀመርኩበት፣ ግን ሌላ ጊዜም ነበር ሁኔታዎች ማያልፉ መስሎኝ የተጨነኩበት፣ ከዛም ሳልፍ ግን ሁሉም እንደሚያልፍ ያየሁበት፣ ህይወቴ ዉስጥ ለተፈጠሩት ነገሮች ትርጉም መስጠት የጀመርኩበት የሆነ ጊዜ ነበር ተስፋ የቆረጥኩበት፣ ግን ሌላ ጊዜም ነበር ከእንቅልፍ መንቃቴ ተአምር እንደሆነ የተረዳሁበት፣ ከዛም ሳልፍ ግን የሆነ ቀን እንደምሞት ያወኩበት ሁላችንም ይሄን ህይወትን እየኖርን ያለነዉ ለመጀመሪያ ጊዜ ነዉ፣ ራሳቹ ላይ አትክበዱ ፣ ለራሳቹ ሌላ እድል ስጡ፣ የህይወትን ሌላ ጎን ለማየት አትስነፉ፥
Show all...
9👍 1
እስኪ ዛሬ ያጋጠመኝን አንድ ታሪክ ልንገራችሁ፣ ፈጣሪ እንዳልጠፋ ልጅ ሰጠኝ ስላለቺኝ አንዲት ልጅ፡ . የሆስፒታል Ward ዉስጥ ያገኘዋት አንዲት ልጅ ነዉ እንዲ ያለቺኝ . ህይወት ምን እንዳስተማረኝ ልንገርሽማ ስትለኝ፣ ጆሮዬን ሰጠዋት . ታውቂያለሽ ፈጣሪን በጣም አስከፍቼዋለሁ ብዙ ጊዜ ሳጠፋ ቆይቻለሁ፣ እሱ ግን ሁሌም አብሮኝ ነበር አልራቀኝም ከቁጣ የራቀና ምህረቱም የበዛ ነዉ፣ ብዙ ልክ ያልነበሩ ነገሮች በህይወቴ ላይ ሰርቻለሁ፣ ለክፋቴ ምላሽ ሳይሰጠኝ ብዙ መንገድ ተጉዣለሁ፣ በዛ ብቀጥል ኖሮ ግን እጠፋ ነበረ፥ . ከዛ ወደ ሆዷ ጎንበስ እንዳለች ፈገግ ብላ ፈጣሪ ግን እንዳልጠፋ ብሎ ልጅ ሰጠኝ አለቺኝ፣ አያቹ ምን አይነት አምላክ እንደሆነ፡ እኛ ሰዎች ሩቅ ሆነን የሰዎችን ህይወት እያየን የእጇን ነው የሰጣት እያልን ከንፈር ለመምጠጥ እንቸኩላለን ፣ እነሱ ግን ፈጣሪ እንዳልጠፋ ይሄን ሰጠኝ ይላሉ፣ ሌላን ሳይነቅፉ መኖር ታላቅ ብቃት ነው፣ የሌሎችን ስህተት አውጥቶ ሰውን ማሳነስ ራሳቸውን የማግዘፊያ አማራጭ ላደረጉ ሰዎች ግን በጣም ቀላል ነው፥ . ፈጣሪ እንደ ሰው አይደለም፣ ሁሌም የስህተት መጨረሻም መውደቅ አይሆንም፣ አንድ አንዴ በሰራናቸዉ ስህተቶች ውስጥ በረከት ይኖራል፣ እስቲ ህይወታቹን ቃኙት በየትኛዉ ጥፋታቹ በረከት አፍሳቹሀል ከምንስ ተመልሳቹሀል?
Show all...
👍 9 3
Repost from እንማር
ከዮቶር መፅሀፍ የተወሰዱ ሀሳቦች... -ሰላም ካላቸው ወይ ያሰቡበት ላይ ደርሰዋል ወይ የሚሄዱበት የላቸውም -ነፍሳችንና ስጋችን የሚያዜሙት ዜማ ህብረት ከሌለው ውበትም ሆነ መልዕክት ሊኖረው አይችልም -ብዙ ሰዎች የራሳቸው ማንነት ላይ ከማተኮር ይልቅ የሌሎች ሰዎች ሰዎች ማንነት ላይ በማተኮር እድሜያቸውን ያባክናሉ -አብረን ያፈካነው ቀን እኮ ነው አንቺን የገለፀሽ። እነዚህ ሰዎች የዚ ቀን ፀሀይ ሲያበራሽ ነው የተመለከቱሽ። እንደኔ በጨለማ ውስጥ አብረውሽ ሊጓዙ የሚችሉ አይነት አይደሉም -ጀግና ጥሩም ሆነ መጥፎ ያው ጀግና ነው -እውነትን እየተረዳህ በመጣህ ቁጥር ስቃይ ከውስጥህ ይሟታል ብላ ነፍሴ ሹክ አለቺኝ -ምንም ብወደው ልኖርበት የማልፈቅደው ቤት ውስጥ እየተላተምኩ እየተፈጠፈጥኩ ከምኖር ልኖርበት የምፈቀደውን ሌላ ቤት መስራት ይጠበቅብኛል -ከንቱ ፍራቻ ብለን የጠራነው የሰው ልጅ ደመ ነብሱን ከማዳመጥ ስለቦዘነ በራሱ ላይ የፈጠረው የፍራቻ ስሜት ነው -ካለሁበት ተነስቼ አንድ እርምጃ ወደፊት በተራመድኩ ቁጥር የጨለማው ግድግዳም ወደኋላ አንድ እርምጃ ይሸሻል -ፍራቻዬን በድርጊት አሸንፌዋለሁ -እናንተ ወጣቶች የቁሳዊው አለም ሰዎች ናችሁ እኛ ሽማግሌዎቹ ደግሞ የመንፈሳዊው አለም ሰዎች ነን -በእናንተ ውስጥ እርካታና ሰላም ጠፍቷል። ብዙ ትሮጣላችሁ እንጂ የእርካታን ደጅ አትረግጡም -የሰው ልጅ አስቀድሞ በነፍሱ በሰውነቱ እና በማንነቱ  ላይ ቀድሞ ካልሰለጠነ ምኑን ነው ሰለጠነ የምንለው? ቁሳቁሱን ነው? -በመንፈስ ስትሰለጥን በማንነትህ ላይ ስልጣን ይኖርሀል -ሀይልና ገንዘብን ቅድሚያ ባደረገ ግስጋሴ ውስጥ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻ ይነግሳል -ሰዎችን ጥገኛ የማያደርግ ምስጢራዊ እገዛ መልካም ነው -ሁሉም ነገር በለውጥ ውስጥ የሚያልፈው እኮ በፍቅር ሳቢያ ነው -እጅህ ላይ ያሉትን ተአምራት ሳትጠቀም ሌላ ተአምር ከሰማይ ለምን መጠበቅ ያስፈልግሀል -የሰው ልጅ እምነት እርግጠኝነት ይጎድለዋል -የአንድ እቃ ወይም ጉዳይ ዋጋ የሚለካው ባረፈበት ሰው ማንነት ላይ ነው -ሀሳባችን በራሱ የህወታችንን ጉዟችንን የሚቀርፅ ሀይል ነው -ራሳችንን በሌላኛው ሰው ቦታ ላይ አድርጎ ማሰብ ጉድለትን ማረሚያ መንገድ ነው -ፍቅር ነፍስን ከነፍስ ከማቆራኘት አቅም እንዳለው አታውቂም? -በገፍ ታፍሶ የተሰጠሽን ፍሬ ሳስተሽ ስለማትጠቀሚበት የምታባክኚው ይበዛል። ተቆጥቦና ተቆጥሮ የተሰጠሽ ፍሬ ግን ውድ ነው። -ህይወት በጣም ትገርማለች በdestiny ላይ የቱጋር እንኳን ስህተት እንደፈፀምክ ሳይገባህ እንዲሁ ፊትህ ያገኘኸውን ብቻ ዝም ብለህ ትኖራለህ
Show all...
👍 4
የተሻለውን እወቅ አንድ ወቅት እንደዚህ ሆነ አንዲት ወፍ እና አንዲት ንብ እየተጫወቱ ሳለ ወፊት ብዙ ግዜ በሃሳቧ የሚመላለሰውን አንድ ጥያቄ ለታታሪዋ ንብ ጠየቀቻት "አንቺ! በብዙ ልፋት እና መከራ ጥረሽ ግረሽ የምትሰሪውን ማር ሰዎች ያለ ምንም ድካም ወስደው ሲጠቀሙበት አታዝኚም ወይ?" አለቻት። ንቧም ስትመለስ "በፍፁም አላዝንም ምክንያቱ ሹም ሰዎች የሰራሁትን ማር ሊወስዱት ይችላሉ እንጂ በውስጤ ያለውን የማሩን አሰራር ጥበብ ማንም ከእኔ ውስጥ ሊወስደው አይችልም።" አሳ እንዴት እንደሚጠመድ ሳይነግሯቼ ሐይቅ ውስጥ አሳ እንዳለ እና አሳ ማስገሪያው ሰተዋችሁ ቢሄዱ ለእናንተ ጥቅም የለውም ስለዚህ የሻለውን እወቁ!! ኖህቶኤል ነኝ ለወዳጆ ሼር ያርጉ https://t.me/Noahtoaels_Idea
Show all...
3
አንዳንዴ ደሞ ገና በጠዋት ስትነሳ ሰው ይናፍቅሀል...ጓደኞችህ ጋር ትደውላለህ...ታወራለህ....አንዳንዶቹ ጋር መልዕክት ትልካለህ...ደህንነታቸውን ትጠይቃለህ....አሁንም ውስጥህን ቅር ቅር ይለዋል....አንድ የቀረህ ሰው አለ ብሎ ውስጥህ ይጮህብሀል....በእርግጥም የናፈቀህን ሰው ያኔ ትለያለህ.... ስልክህን ታነሳለህ....መልሰህ ታስቀምጣለህ....ድብርት ከነ ሙሉ ቤተሰቡ እንግድነት ይመጣል...ትበሳጫለህ....ዛሬን ተኝተህ ማለፍ ያምርሀል....ከዛ ፈተና እንዳለብህ ትዝ ይልሀል....አልያም ስራ መቅረት አትችልም....ጭንቅላትህ እንደተወጠረ ሰላም አውለኝ ብለህ ትወጣለህ...ላትልም ትችላለህ.....ብቻ እንደዛ....እንደነገሩ ትውላለህ....እንደ እኔ ከሆንክ በየመሀሉ ታለቅሳለህ....ራስህን ብቻህን ባገኘህበት ቅፅበት ሁሉ....ወይም ከራስህ ጋር ታወራለህ....ምኑም ስላልገባህ መጠየቅም ስለማትችል.....ደሞ ማንንም መውቀስም ስለማትችል.... እነርሱም ያሉበትን ሁኔታ ፈቅደው እና ወደው ስላላመጡት እና ከቁጥጥራቸው በላይ ስለሆነ....ራሳቸውን እያጡ ስለሆነ....መናገር እንኳን የማይችሉት ነገር ስለሆነ....ስለደከማቸው....እንዲ መሆኑን እነርሱም ስለማይፈልጉት... ማን ይወቀሳል.... ጊዜ ጌታ ሆነ....እንደተለመደው እስቲ ቶሎ እለፍ እንለው ይሆናል እንጂ ምን ይባላል..... ✍Shewit https://t.me/shewitdorka
Show all...
ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

ለአስተያየታችሁ @Shedorka

👍 3 2🔥 1😢 1