cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ከመጽሐፍት መንደር💠

አንብብ አዕምሮህ ልክ አንደባህር ይሰፋል። ወንዞችም ለአንተ መገበር ይጀምራሉ። አንተ ወደ ሰዎች ሳይሆን ሰዎችም ወደአንተ ይመጣሉ። ማንብብ ሙሉ ሰው ያደርጋል!! አንብብ ብታነብ የሚቀርብህ ድንቁርና 🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩 🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨 🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥 ለማንኛውም አስተያየት @manbabemuluyadergal_bot

Show more
Advertising posts
3 646Subscribers
-324 hours
+47 days
+5730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የማባልጋት ባለትዳር ነበረች ። ዋና ተግባራችን ወሲብ ነው ። የምንቀጣጠረው ለወሲብ ብቻ ነው ። የምናወራው ስለ ወሲብ ነው ። አንዳችን አንዳችንን የምንፈልገው ወሲብ ሲያምረን ነው ። አጠገቤ ሆና ባሏ ደውሎ ያውቃል: "ሰውዬሽ ደወለ" ብዬ ስልኳን አቀብያት አቃለሁ ። ምንም እንዳልተፈጠረ ስታወራው እርቃኗን አትመስልም ነበር። ይገርመኛል ድድብናችን ። ነውራችን ስለተደጋገመ ተግባራችን ብልግና መሆኑ ተሰወረብን ። ቢሮዋ እሄዳለሁ፣ ቢሮዬ ትመጣለች ። ጓደኛዬ ቤት፣ እኔ ቤት፣ የሆነ ኮስመን ያለ ሰዋራ ቦታ ፣የሆነ ድብቅ ፅድት ያለ ስፍራ ፣ መኪና ውስጥ ... ብዙ ብዙ ቦታ ትመጣለች እንዋሰባለን ። የታሪካችን መነሻ እና መድረሻው ወሲብ ነው ። አንድ ቀን በደነገጠ: ተስፋ በቆረጠ ድምፅ "ባሌ አወቀብን" አለችኝ .....ደነገጥኩ ። ጠፋሁኝ ...ጠፋች ከአስራ ሰባት ቀን በኋላ ጓደኞቼ "ገኒ ሃዘን ላይ ነች፣ ሙሉ ከላይ እሰከታች ጥቁር ለብሳለች፣ ከስታለች" አሉኝ "ምን ሆነች?" አልኩ "ባሏ ሞቶባት ነው፤ ራሱን አጥፍቶ ነው የሞተው" አሉ። ስደነግጥ፣ ፊቴ ሲቀያየር ፣ እምባዬ ሲያመልጠኝ አዝኜለት ነው የመሰላቸው ። እኔ እንደገደልኩት አልጠረጠሩም ። የጥፋተኝነት ስሜት ሊገለኝ ሲል ማምለጫ መፅሃፍ ቅዱስ ገለጥኩ። "ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳል " የሚለው ከሁሉም ጎልቶ ተነበበኝ ። .. ✅️ሰው ይዞ መውደቅ ፤ ማስተካከል የማይቻል አወዳደቅ ፣ ሲያስታውሱት የሚያስነክስ አይነት አወዳደቅ፣ እነሳለሁ የማይሉት አወዳደቅ ፣ ወድቄ ነበር የማይሉት አወዳደቅ። በግዜ ምክንያት የማይደበዘዝ አወዳደቅ ... እንደዚህ አይነት መውደቅ ሲ..ያ...ስ..ጠ..ላ !! ! © Adhanom Mitiku
Show all...
👏 1
🔪🔪🔪ግድያው 🔪🔪🔪 ክፍል 3 መቼም ዝምተኛ ሰው ምንም እንደማይሰማው የሚያስበው ሁሉም ነው ከባለቤቱ ውጪ። አሁንም እውነት እውነት እየመሰለው አይደለም። እትዬ አበሩ መጥተው "አቤልዬ እኔ አፈር ልብላ ና እስኪ ግባ አፍህ ላይ እህል ቢጤ አድርግ" አሉት ቀና ብሎ አያቸው 'ከመቼው እንደዚህ ገረጡ' አለና እናቱን አያቸው ሰው ከአጠገባቸው ዞር ባለ ቁጥር ፊታቸውን እየቧጠጡ አሰቸግረው ሁለት ሰዎች ናቸው ይዘዋቸው የተቀመጡት ብሩክን ሲያየው ጭንቅላቱን ይዞ ይጮሀል ሊያረጋጉት የሚሞክሩትን ሰዎች "እኔ እኮ ሌላ ወንድም የለኝም" ይላቸዋል። ሰዎች መቼም እሱን ሳይታዘቡት አይቀሩም 'ወንድሙ ቁጭ ብሎ ብሩክ እንደዚ ሲሆን' ብለው አባቱን ግን የገረማቸው አይመስሉም ምናልባት እሳቸውም እንደሱ መሞቱን አልተቀበሉት ይሆናል ድንኳን ምናምን እያሉ ተለቅ ካሉ ሰውዬ ጋር እየተነጋገሩ ነው። ወይም ደግሞ ውስጣቸው በሀዘን እየደቀቀ ማሳየት አይችሉ ይሆናል። "እ አቤልዬ?" አሉት ለካ እስካሁን አጠገቡ ቆመዋል። እስካሁን ያዘኑት ይበቃል ደግሞ በእኔም ይዘኑ እንዴ ብሎ እሺ ብለሏቸው ተከትሏቸው ወደ ሳሎን ገባ። ዛሬ እንደዚ የእድርተኛ እና የሰፈር ሰው ሊተራመስበት ትላንትና እነሱ ብቻ ነበሩ የነበሩት ማታ ቡና ተፈልቶ ሲንጫጩ አርሰናል አሸነፈ ብሎ አየሮጠ ሄዶ ወንድሙን ሲያበሽቀው ወዲያው ማኪ መኖሯን ሲያይ አፍሮ መመለሱን አስታውሶ ፈገግ አለ።  "አቤል?" አለችው ማክዳ በለቅሶ ብዛት ያ ቀይ ፊቷ ቲማቲም መስሎ "ማኪዬ" ብሎ ሄዶ አቀፋት "ለምንድነው? እሱን ለምን? ላገባው ነበረ እኮ" ደረቱ ላይ እዬዬዋን አስነካችው። እውነት ነው ማለት ነው? ሞቷል በቃ እሺ ማኪን ለማን ጥሎ ብሩክ ብቻ እኮ ነው የማይወዳት እንጂ በፍቅራቸው የማይቀና አልነበረም። በቃ ጥሏት ሄደ? ቆይ ግን እውነትም ለምን ገደሉት? መጀመሪያ ማን ነው የገደለው? ✍nani
Show all...
👍 10
🔪🔪🔪ግድያው 🔪🔪🔪 ክፍል 2 ቅዳሜ ጠዋት ረፋድ ላይ የትልቅ ሴት ጩኸት ተሰማ። አብዛኛው ሰው ገና ከመኝታውም ሳይነቃ ስለነበረ ጩኸታቸው ሲቀሰቀሳቸው 'ለመርዶ ራሱ ረፍዷል እኮ" እያሉ እየተሯሯጡ ሲሄዱ እትዬ አስካለ ራሳቸውን ይዘው ላንቃቸው እስኪላቀቅ ያቀልጡታል "ልጄን... ልጄን... ምነው ምን አደረጋችሁ?...ጧሪዬን... ጧሪዬን ቀባሪዬን... ታሞ በተኛ ባስታመምኩ?... አሁን ከአሁን ዳነልኝ ብዬ አይን አይኑን ሳይ..." አለቃቀሳቸው የሁሉንም ሆድ አባባው የሞተው ልጃቸው በጩቤ ተወጋግቶ አልጋው ላይ በደም ተጨማልቆ አልጋው ላይ ተንጋሏል። ሰፈርተኛው ለቅሷቸውን ተቀላቅሎ ሰፈሩ ተናጋ። እትዬ አስካለ የያዛቸውን ሁሉ እጃቸውን እየመነጨቁ ሙሾ ሲያወርዱ ቆይተው አበሩ ስትመጣ "አበሩዬ ልጄን ነጠቁኝ እኮ?!...  ልጄን!!..." ብለው ተቃቅፈው ማልቀስ ጀመሩ አበሩም ተቀብላ "አስካልዬ ለኔም እኮ ልጄ ነበረ ከብሩኬ ለይቼ አላየውም ነበረ" ጓደኛሞቹ እናቶች ሌላውንም ሰው አልቅሰው አስለቀሱት በዚህ ሁሉ ወከባ ውስጥ የተረሳው አቤል ለራሱ ጥግ ላይ ድንዝዝ ብሎ ተቀምጧል "በቃ ወንድሜን ገደሉት በቃ ወንድም የለኝም ማለት ነው" እያለ ጭንቅላቱ ያቃጭልበታል የሰፈሩ ወጣቶች ፖሊስ ጠርተው የሰፈሩን ሰዎች እያረጋጉ እያለ የአበሩ ልጅ ብሩክ ደግሞ አይኑ በርበሬ መስሎ "እንደዚህ ያደረገውን ውሻ ላግኘው ብቻ" እያለ የሲሚንቶ ግርፍ የሆነውን ግንብ ሲደበድብ ሳይታወቀው እጁ በደም ተለውሶ እሱን ማረጋጋት ራሱ ሌላ ስራ ሆነ ✍nani
Show all...
👍 5 2
🔪🔪ግድያው 🔪🔪 ክፍል 1 መርማሪ ፖሊስ ሆኖ መቆየቱ ይሆናል መሰል እንደ ወታደር ሰዓት ላይ ያለው አቋም ጠንካራ ነው። አብረውት የሚሰሩትም ሰዎች ወይ ለምደውት ወይም ደግሞ ጭቅጭቁ መሯቸው ከመውጫ ሰዓታቸው በፊት ውልፍት አይሉም። አሁን ግን ሚኪያስ ከሚባለው አዲስ የሰራ ባልደረባው ጋር መስማማት አልቻሉም። ከስራ ለመውጣት ያለው ጥድፊያ ነው መሰል ሲያየው አይጥመውም "ጋሽ ብስራት ደህና እደር" ብሎ ሰዓቱን እያስተካከለ ወጣ። " 'ጋሼ' ይለኛል አያፍርም? ምን ያህል ብንበላለጥ ነው" አለ በሆዱ ገና ወጥቶ ብዙ ሳይቆይ ፅዳቷ  ስንታየሁ እየተጣደፈች መጣችና "አዬ ሚኪ ወጣ እንዴ? መውጣቱን አይቼ ላፀዳ ስገባ ቢሮው ውስጥ ወድቆ አግኝቼ ነው የአይን ጠብታ ናት መሰለኝ" ብላ ትንሽ ብልቃጥ አቀበለችው "እኔ ነገ እሰጠዋለሁ ይሄ ልበ ቢስ" ተቀበላት።ተቀብሏት ኪሱ ጨምሮት ወደ ቢሮ ተመለሰ። ሁሉንም ነገር መጨራረሱን አይቶ ቆልፎ ወጥቶ ቁልፉን ኪሱ ሲያስገባ ብልቃጡን ነካው። አውጥቶ ከኪሱ አገላብጦ ሲያየው ጠብታ አልመስል አለው። ላዩ ላይም ምንም አልተፃፈበትም። በዛውም ይሄ ተንኮለኛ ምን በኪሱ ይዞ እንደሚዞር ጉዱን ልይ ብሎ ብልቃጧን ሳምሶን (የላብራቶሪ ቴክኒሻኑ) ጋር ይዞለት ሄደ። "ሳሚዬ የኔ ምርጥ ጓደኛ" አለው ሲሸነግለው እሱም ሊወጣ በሩን ሲቆላልፍ ስለነበረ "ቸኩያለሁ ምንም እንዳትለኝ" አለ ተኮሳትሮ "ሳሚሻ ነገ ራት በእኔ ነው" ሲለው "በአንድ አፍ" ብሎ ከፍቶ አብረው ገቡ "ይቺ ነገር እይልኝ እስኪ" አልኩት "እሺ" ብሎ ተቀብሎ ማይክሮስኮፑ ላይ ጠብ አድርጎ ሲያይ ቆየና "እንዴ እንዴ ከየት አመጣሀት ባክህ" አለኝ ፈገግ ብሎ ከአጉሊ መነፅሩ ቀና ሳይል "ምነው ምንድነው?" አልኩት ሰፍ ብዬ "<truth serum> እኮ ነው" አለኝ "ምንድነው እሱ" አልኩት ሰምቼው ስለማላውቅ "ድሮ አጋቾች ለማናዘዝ የሚጠቀሙበት አሁን ተከልክሎ ቀርቷል" አለኝ ይሄ መናጢ መች አጣሁት ጭራሽ <truth serum?> ✍nani
Show all...
👍 9🔥 1
የመጀመሪያ ቀጠሮ            የመጀመሪያ ግብዣ የባጥ የቆጡን ሲያወሩ ቆዩና "ምን አይነት ሰው ነሽ?" አላት አፉ ጋር የደረሰውን ጉርሻ እየጎረሰ "ምን አይነት ሰው ነኝ መሰለህ" የጠቀለለችውን ጉርሻ ቁጭ አድርጋ ቀጠለች "በጣም ስለወደፊታቸው የሚጨነቁ አስር እና ሀያ አመት የሚያቅዱ አይነት ነበርኩ። ከዛ ድንገት የሆነ ቅፅበት ላይ ታክሲ ላይ ያየሁት ጥቅስ አባነነኝ "ዛሬ ቢሆንስ የምትሞተው" ይላል ከዛ ያስጨንቁኝ የነበሩ ነገሮች በሙሉ ዋጋ አጡብኝ በቃ የእለቱ እለት ማታ እንደሚሞት ሰው መኖር ጀመርኩ ራሴን የምከለክለው ነገር አልነበረም ሁሉንም አድርጌዋለሁ አሁን ምንም የቀረኝ የምለው ነገር የለም በቃ ለሁሉም ነገር ስሜት አጥቻለሁ ነው የምልህ። ነገሮች ቀስ ብለው እንዳይሆኑ አጣደፍኳቸው እና የሚያስደስቱኝ እና የሚያሳዝኑኝ ነገሮች ተመናመኑ አንዳንዴ ከልክ በላይ ነገሮችን መገፋፋት ዋጋቸውን ያሳጣዋል።" አለችው እና መብላቷን ቀጠለች። መልዕክቷ ግልፅ ነበረ <ላንተ የሚሆን የማቀርበው ትኩረት እና ጉጉት አይኖርም> ማለቷ ነው። እነሆ የመጀመሪያም      የመጨረሻም ቀጠሯችን ሆነ ማለት ነው።
Show all...
👍 1
😘የከንቲባው ልጅ😘 🔥ክፍል 20 . . አዘጋጅ እና አቅራቢ=- ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል ✍ . . ..ቤተሰብ ሼር ላይክ በደንብ አርጉ በፍጥነት እዲለቀቅ ♥️♥️♥️♥️ የማውቀውን አንድ ግጥም በዜማ እልላት ጀመር ። እንዲህ ብዬ ...🎤 አመሻሽ ላይ ሆኜ ፡ ሳስብሽ ሳስብሽ        በረንዳ ላይ ሆኜ ፡ አንቺኑ ስስልሽ        ስላንቺ የሚያወሳ ፡ ግጥም ስፅፍልሽ        ዕምባ ከአይኖቼ ፡ ዱብ ዱብ እያሉ        አይኔና ጉንጮቼ ፡ በዕንባ ሲሞሉ        ከሰማይ ላይ ሆና ፡ ትታዘበኛለች        እጇን በአፏ ጭና ፡ ታፈጥብኛለች        ደንገጥ አልኩኝና ፡ ዕምባዬን ጠረኩኝ        እሷም ቀስ በቀስ ፡ እኔን ቀረበችኝ       ብርሃኗ ልዩ ነው ፡ ሁሉን የሚያስረሳ       ፈዝዤ ቀረሁኝ ፡ ፎቶ እንደሚነሳ       እኔጋር ደረሰች ፡ ከዋክብት አጅቧት       መንቀጥቀጥ ጀመርኩኝ ፡ እኔም በፍርሃት       ጠጋ አለችና ፡ አይዞህ ጨረቃ ነኝ አለችኝ        አትፍራ አትሽሽ ፡ ብላ አቀፈችኝ        ኮከብ እንዳጀባት እየነገረችኝ        እንባዬን ጠራርጋ ፡ አይኖቼን እያየች         በሹክሹክታ መንፈስ ፡ ማውራት ጀመረች         አይዞህ ጠንከር በል ፡ ምንም አትሆንም         እውነት ካፈቀርቃት ፡ የትም አትሄድም        ለፍቅርክ ምስክር ፡ እሆንልሀለው        ካለችበት ሄጄ ፡ እነግርልሃለው        ያቺ ውብ ጨረቃ ፡ ቀርባ አፅናናችኝ        ለተከፋው ልቤ ደስታን ሰጠችኝ፣    "ጤዛ ሞቷን ሞታ ፡ ኮከብ ባናት ስትወጣ ፣      ድምፅ ወደኔ መጣ ፡ አለኝም ጠጣ   አንተ ድንቅ ፍጡር ጠጣ ፡ ወደኔ እስክትመጣ" ። የሚለውን ግጥም መረኩላትና ወይናችንን እየጠጣን የጨረቃን ውበት ማድነቅ ጀመርን ። አይኖቻችን ግን እሷ ላይ ለመቆየት ብዙም የፈለጉ አይመስለኝም ። ከኛ በብዙ ሺህ እጥፍ የምትርቅ ፣ ያውም የማናገኛት ጨረቃ ላይ ከማፍጠጥ ይልቅ የቅርባችን ይሻላል ብለን አይኖቻችን ውስጥ ያለውን ጨረቃ ለመፈለግ ይመስል እርስ በእርስ መፋጠጥ ጀመርን ። ብዙም ሳንቆይ ህይወት ወለላዋ ፣ ነክታኝ በስምያዋ ፣ ኑር ለዘላለም ስትል ፣ ከንፈሮቿ ነፍሴን ከአፋፍ ላይ አወጧት ፣ ባይኔ እያየሁ ወደ ጨረቃዋ አከነፏት ። መቼም የማልደርስባት ፣ ማገኛት ማይመስለኝ ፣ ያቺን እሩቅ ያለች ጨረቃ አፌን በአፏ ጎርሳ አሳየችኝ ። ከንፈሬ ከንፈሯን ፈልቅቆ ሲነካው ፣ ነፍሴ ከነፍሷ ጋር ጋብቻ የፈፀሙ ነው የሚመስለኝ ። ከንፈሯ ደግሞ ለስላሳ ነው ፤ ለዘለዓለም እንድትስመው ይገፋፋል ። መሞት ካለብኝ ልሙት ፤ ሞቴ ግን ከንፈርሽ ላይ ይሁን የሚያስብል ፣ ምሽቱ ነግቶ ፣ ወፎች እስኪንጫጩ ፣ ምድርም እስክትነቃ ድረስ ልቀቁኝ የማይል ከንፈር ። (ኧረ በህግ አምላክ ልቀቃት ...🙆) ። በስንት መከራ ከንፈራችን ተላቆ አይኖቻችን ማውራት ጀመሩ ። የከንቲባው ልጅ ከብዙ ዝምታ በዋላ "በህይወቴ አንድ የማይሰለቸኝን ነገር ልንገርህ...?" አለችኝና ቀጠለች "ካንተ ጋር #24 ሰዓት ማሳለፍ ፣ እንደውም ሰዓቱ በጣም አንሶኛል ፣ ሰዓቱም ልክ ቀናቱ #365 በሆነልኝ ። ቀናቱን ሁሉ ፣ ሳምንቱን ሙሉ ፣ ወራቱን እንዳለ ፣ ዓመታቱንም እንደዛው ካንተ ጋር በሆንኩ ። ካንተ ጋር ከሆንኩኝ ሁሉም ቀን ለኔ የፍቅር ቀናት ናቸው ። አንተኮ መውደድን የማነብብህ ደብተሬ ፣ ፍቅርን የማይብህ መስታወቴ ፣ ያለ ስጋት የምኖርብህ ሀገሬ ፣ በእስትንፋስህ የምተነፍስ ንፁህ አየሬ ነክ ። ባንተ ፍቅር እንደ ጤፍ ሺህ ቦታ ብትንትን ብልም ባንተው ፍቅር ደግሞ ይኸው እየኖርኩ ነው ። በህይወቴ ውስጥ አንተን ስላገኘሁ በጣም ደስተኛ ነኝ ። በምታደርገውና በምትለኝ ነገሮች የተለየሁ እንደሆንኩ ያክል እንዲሰማኝ ታደርጋለህ ። እናም በጣም ነው የምወድህ ፤ ሁሌም ደግሞ አደርገዋለው" ብላኝ አይኖቿን ጨፍና ከንፈሬን ድጋሜ ስትስመኝ ከውጪ በሩ ተንኳኳ ። ደንግጠን ከንፈራችን ተላቆ አይኖቻችን በሩ ላይ አረፈ ። የልብ ምታችንም ከሚንኳኳው በር በላይ ይሰማናል ። እኔ ምናልባት አቧቷ ከሆኑ ብዬ ለጥንቃቄ ወይኑንና ብርጭቆዎቹን ይዤ ወደ ቤት ውስጥ ገባሁና ኩሽና አስቀምጬ ወደ ሳሎን ተመልሼ በመስኮት የሚሆነው ነገር መከታተል ጀመርኩኝ ። የከንቲባው ልጅ ደግሞ ፈራ ተባ እያለች "ማነው ...?" ብላ ወደ በሩ አቀናች ። ከዚህ በፊት አባቷ ሲመጡ ለምልክት አስቀድመው ይደውሉ እንደ ነበር ነግራኛለች ። ታድያ ከውጪ በር ላይ ቆሞ እያንኳኳ ያለው ሰው ማነው ...? ። ህይወት ላይ ጥቃት ሊፈፅም የመጣ ሰው ከሆነ ግን እንዴት እንደሆነ ባላውቅም ሰውዬው በእጄ ሰበብ መሆኑ ነው ። (ኡ ኡ ቴ ፡ አልቀረብህም...🙆) ። አቧቷ ከሆኑ እሰየው ፡ ግን የት ነው የምደብቀው ...? ። ከውጪ ምን እንደሚል ባይሰማኝም የሷ ድምፅ ግን ይሰማል ። ብዙም ሳይቆይ በሩ ተከፈተ ። አይኔ ፣ ልቤ ፣ መላ ሰውነቴ በሩ ላይ ፈዘዋል.. ወደ ውስጥ አንድ ሰው ገባና በሩን ዘግቶ ከህይወት ጋር ጥምጥም ብለው ተቃቀፉ ። አባቷ ናቸው አልኩኝ በልቤ ። ደንግጬ ወዴት እንደ ምሄድ ግራ ገብቶኝ ወደዚያ ወደዚህ ስል አንዴ ከግድግዳ ጋር ተላተምኩና ግንባሬን እያሻሸው ወደ ከንቲባው ልጅ ክፍል ገባሁ ። ለማየትና ለመስማት እንዲያመቸኝ የክፍሉን በር ሙሉ በሙሉ አልዘጋሁም ። መብራት ግን አጥፍቻለሁ ። አባትና ልጅ ተያይዘው ወደ ውስጥ ገቡ ። ደስ የሚለው አባቷ ላለሁበት ክፍል ጀርባቸውን ሰጥተው ነው የተቀመጡት ። ህይወት ደግሞ በኔ ፊትለፊት ሶፋው ላይ ቁጭ ብላ ከፀሀይ በላይ ፈክታ በናፍቆት ወደ አባቷ እያየች ታወራለች ። "አባቢ ደና ነህ አይደል ፡ እኔኮ ተጨንቄ ስልክህ ላይ ከጠዋት ጀምሮ ስሞክር ነበር ፤ ግን አይሰራም" አለቻቸው ። አባቷም "የኔ ህይወት አመሻሹ ላይ ነው እኮ አዲስ አበባ የገባሁት ፤ እረፍት ሳልወስድ ነው በዛው በድሬ plane ወደዚህ የመጣሁት" አሏት ። "ደክሞሀል አይደል በሙቅ ውሃ እግርህን ልጠብልክ ...?" ስትላቸው "አይ ፡ ባይሆን ሻዎር ልውሰድና ብዙ የማወራሽ ነገር አለኝ" ብሏት ተነስቶ ግንባሯን ሳሟትና እኔ ወዳለሁበት ቦታ አመሩ ደንግጬ ከበሩ ጀርባ ተደበኩኝ ። ካለሁበት አጠገብ በቀኝ በኩል ያለው ክፍል ሲከፈት ይሰማኛል ። ባለፈው ለመጀመሪያ ጊዜ እዚህ ቤት ስመጣ የከንቲባው ልጅ "አባቴ ሲመጣ እዚህ ነው የሚያድረው" ያለችኝ ክፍል ነበር ። ከትንሽ ደቂቃ በዋላ ተመልሶ ተዘጋና ወደኔ እየቀረበ የሚመጣ የእግር ኮቴ እየሰማው አልፎኝ ሄደና በግራዬ በኩል ያለው ክፍል ተከፍቶ ወዲያው ተዘጋ ። በሆዴ 'አባቷ ሻዎር ገቡ ማለት ነው' ብዬ ሳልጨርስ በድጋሜ ወደኔ የሚመጣ የሰው ኮቴ ሰማሁ ። በቅስፈት ያለሁበት ክፍል መብራት ሲበራብኝ ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ... ከ 100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 21 ይለቀቃል ♥️♥️♥️♥️👍👍👍👍 ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ አንብባችሁ ስጨርሱ ላይክ ለወዳጆ ሼር ያርጉ ♥️🫶 #ከደራሲያን አለም #የቴሌግራም_ቻናል Join በማለት ራሶን በጣፋጭ ትረካዎች ዘና ያርጉ ..♥️
Show all...
♥️የከንቲባው ልጅ♥️ 🥀ክፍል 18🥀 . . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! . . ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል . . ትዝ ይለኛል ስንወጣ አጥፍተን ነበር። ህይወት ዞር ብላ በፍርሃት ታየኝ ጀመር..።    "አጥፍተን ነበር አ የሄድነው ...?" አለችኝ ። እራሴን በአዎንታ ወደላይ ወደታች ነቀነኩኝና 'አባትሽ የዚህን ቤት ቁልፍ አላቸው እንዴ ...?' አልኳት ባለፈው ሲመጡ በር ላይ ነኝ ብለው ስለደወሉላት ። "አዋ አለው ፣ ባለፈው ሲመጣ ረስቼ ነው ብሎኛል" አለችኝ ። ከእሷና ከአባቷ ውጪ ቁልፉን ማንም ከሌለው ፣ በዛላይ አባቷ እንዳሉትም ሀገር ውስጥ ከሌሉ ፣ በተጨማሪም ቢሾፍቱ እያለን ካየነው ሰውዬ ጋር ሲደማመር የሆነ ችግር እንዳለ በግልጽ ተሰማኝ ። "ይሄኔ ነው መሸሽ" አለ ያገሬ ሰው ፤ አሁን ገና ፍርሀት የሚባለው ስሜት አካሌን ወረረው ። "ሞት ላይቀር ፍርሀት ፤ አመል ላይቀር ቅጣት" ። "ፈሪ ውሃ ውስጥ ሆኖ ያልበዋል" ፤ እኛ ግን የጦርነት ቀጠና ውስጥ ሆነን ደርቀናል ። "ፈሪ ከአልጋ ላይ ወድቆ ይሞታል" ፤ እኛ ግን አልጋ ላይ የመውጣት አቅምም የለንም ። "ፈሪ የሚያባርረው ሳይኖር ይሸሻል" ፤ እኛ ግን የሚያባረን እያለ ካለንበት መንቀሳቀስ ከብዶናል ። ሞት በየሁሉም ሰው በራፍ ላይ የሚቆም ጥቁር መላክ ነው ። እኛም ቤቱን ፈትሸነው ባዶ መሆኑን ስናረጋግጥ ይህ በራፋችን ላይ የቆመው የሞት መላክ እንዳይወስደን በሩን ሁለት ጊዜ ቆለፍነው ። ተስፋና ፍርሀት ሁሌም አይነጣጠሉም ። ፍርሃት ያለ ተስፋ ፣ ተስፋም ያለ ፍርሃት አይኖርም ። ፍርሃትን የሰጠ አምላክ ፡ ተስፋንም አይነፍግም ። "ተስፋ ያልቆረጠ መነኩሴ ምናኔ ሲሄድ ሴቲቱን ይሰናበታል" አሉ አበው ። እኛም ምንም እንኳን ወደሞት እየሄደን ቢመስለን በምድር ተስፋ አልቆረጥንም ። አባቷ መጥቶ ከሆነ ብለን በሀገር ውስጥ ስልኩ ላይ ስትደውልለት "የደወሉላቸውን ደምበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም..." አለች የቴሌ ሰራተኛ ። በጣም ተጨንቀናል ። ጭንቀታችን በከንቱ ይሁን አይሁን ግን አናውቅም ። ከመተኛታችን በፊት ከጊቢ የዶርም ጓደኛዬ ደውሎልኝ ነገ ትምህርት እንደሚጀምር እና class ባልገቡት ተማሪዎች ላይ እርምጃ እንደ ሚወሰድ ነገረኝ ። ስልኩ speaker ላይ ስለነበር ያለኝን ነገር የከንቲባው ልጅም ሰምታለች ። አንድ ሶፋ ላይ ሆነን የመረቀነ የድሬ ልጅ መስለን አይናችንን አፍጥጠን እየተያየን የዕሮቡ ለሊት ለሀሙሱ ጀምበር እጁን ሰጠ ። ስንት ሰዓት እንደ ተኛን አላውቅም ። እራሳችንን እዛው ሶፋ ላይ ተቃቅፈን አገኘን ። አዲስ ነገር ካለ ብለን ቤቱንና ጊቢውን ፊትሽነው ። ሁሉንም ነገር ግን ትተነው እንደ ተኛን አገኘን ። ትንሽም ቢሆን ተረጋግተን "በቃ አንተ ወደ ጊቢ ተመለስ ፡ በኔ ምክንያት ትምህርትህን እንድታጣ አልፈልግም ። እስካሁን ድረስ ለኔ ያደረከው እራሱ ከበቂም በላይ ነው" አለችኝና ልትሸኘኝ ወደ ጊቢው ወጣን ። እኔም እቅፍ አረኳትና 'አይዞሽ እሺ ምንም አይፈጠርም ። ደግሞ ብዙም አልቆይም ፡ ፍቃድ ብቻ ጠይቄ ነው የምመልሰው እሺ' አልኳትና ስታለቅስ ላለማየት ብዬ በፍጥነት ወደ ውጪኛው በር አመራሁ ። ልክ በሩን ስከፍት "ትተኸኝ በዛው እንዳትቀርብኝ እሺ የኔ ጌታ ፣ ብቻዬን እፈራለሁ ፣ ደግሞም ማንም እንደሌለኝ ታውቃለህ አይደል...?" አለችኝ ልክ የመጀመሪያው ቀን ስንገናኝ "ትተኸኝ አትሂድ ፡ ማንም ሰው የለኝም" ባለችኝ ዜማ ። ዞር ብዬ ሳያት ፊቷ በዕምቧ እየታጠበ ነው።... በሩን አልፌ የመሄድ አቅም አልነበረኝም ። ዘጋሁትና ወደሷ ተመልሼ እቅፌ ውስጥ አስገባዋት ። ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ፤ ሁለመናዋም ይንቀጠቀጣል ። 'እሽሽሽ ፡ በቃ አታልቅሺ ፣ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ካንቺ ጋር ነኝ ። ትቼሽ የትም አልሄድም ። ሁሉንም ችግሮችሽን ላላስወግድልሽ እችላለሁ ፤ ነገር ግን ብቻሽን እንድትጋፈጪው በፍፁም አላደርግም' አልኳትና ዕምባዋን ጠራርጌ ፡ ግንባሯን ፣ አይኗን ፣ ጉንጯንና አንገቷ ስር ስሜያት ተያይዘን ወደ ቤት ተመለስን ። ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ዘንድሮ ባወጣው ህግ መሠረት የ #3 ቀን ቀሪ ከጊቢው ያሰናብታል ። የኔ ቀሪ ደግሞ ከዚያ እያለፈ ስለሆነ ትንሽ አሳስቦኝ እንጂ መጀመሪያውኑ የትምህርት ፍቅር ኖሮኝ አይደለም ወደ ጊቢ ለመመለስ የተነሳሁት ። ይሄው አሁን ትምህርቱ ላይ ፈርጄ የከንቲባው ልጅ ቤት ቀርቻለሁ ። ትውልድ ይዳን ፤ ትምህርት በኔ ይብቃ ። ሳስበው ግን ህይወት በዚሁ ሁኔታ ከቀጠለች ወደፊት ልጄን ትምህርት ቤት ወስጄ የማስተምረው አይመስለኝም ። ለነገሩ ልጄ እንደኔ ደደብ ፣ ደነዝ እና ሰነፍ የሚሆን አይመስለኝም ። በኔ ከወጣ ግን ውሃ በላው ። Campus ባይገባ ነው የሚሻለው ። ልግባ ቢል እራሱ ማን ሲያስገባው ...? ከኔጋር እየኖረ ትምህርቴን ማቄን ምናምን የሚል ከሆነ #18 ዓመት እስኪሞላው ደረስ አልጠብቅም ። ልክ ይቺን ጥያቄ ስያነሳ በሬን ከፍቼ ካለኝ ንብረት ላይ የድርሻውን ሰጥቼው አሰናብተዋለው ። (ንብረት ግን የሚኖረኝ አይመስለኝም ...🙆) ። የኔ ነገር ፡ ለራሴም ሳልሆን የልጄን ፈተፈትኩ አይደል ። (አንተ ልጅ ግን ልጅ አለህ እንዴ ...?😬) ። ምን ላርግ ፡ ከ #3 ወር በፊት የተፈተነው Applied Maths final ፈተና ትዝ ብሎኝ እኮ ነው ። On time #02:00 ሰዓት ሻርፕ (flat ...😜) ላይ class ተገኘሁና አሰላለፍ አሳምሬ አስተማሪውን ጠበቅነው ። ዛሬማ ካልደፈንኩት ከዚህ ክፍል ውስጥ ንቅንቅ አልልም ብዬ ቆረጥኩ ። በስተ ሰሜን ጎበዙ የዶርሜ ልጅ ፣ በስተ ደቡብ ከዋላዬ ስለሆነ አይመቸኝም ፣ በስተ ምስራቅ ከክፍል #1ኛ ውጤት ያለው ልጅ ፣ በስተ ምዕራብ ደግሞ ከዲፓርትመንታችን ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ልጅ ተቀምጠዋል ። Morino እራሱ አሰላለፍ እንዲህ አይችልበትም ። የተከተልኩት የጨዋታ ስልትም ፡ ትንሽ ማንበብ + ብዙ መኮረጅ = #50/50 የሚለው ነው ። ኩረጃ ላይ ብዙም ልምድ የለኝም ። እንግዲህ የኔ ጉድ ዛሬ ይታያል ። (ጉድ = Good ...😬) ፈታኙም ፈተናውን ይዞ ከተፍ አለ ። (ምናለበት አሁን ቢቀር ይሞታል ...?🙆) ። ፈተናውን ጠረጼዛ ላይ አስቀመጠና እንዲህ አለን "Continous ከ #50 ሁላችሁም ከ #40 በላይ ስላመጣችሁ አይያዝም ። ስለዚህ የዛሬው ፈተና የሚያዘው ከ #100% ነው ። #90 ጥያቄ ተዘጋጅቷል ፣ ለእያንዳንዱ ጥያቄ #3 pharagraph ትፅፋላችሁ ። ሁሉም ጥያቄ የወጣው ከተማራችሁት ውጪ ሲሆን ፤ ጥያቄዎቹ እንኳን ለእናንተ ለኛም አዲስ ናቸው ። የቀረው #10% ነጥብ ደግሞ ስማችሁን በቻይንኛ መፃፍ ይሆናል ። አሁን ፈተናውን እንጀምራለን ልክ ጀምሩ እንዳልኳችሁ pencil down እላቹዋለው ታቆማላችሁ ። ፈተናው ላይ #1 ኤክስ (❌) የገባበት ተማሪ ከጊቢው ይሰናበታል ። መልካም ፈተና ። ነጮች "ስለ ሰው ይበልጥ ባወክ ቁጥር ውሻህን ትወደዋለህ" ይላሉ ። እኔ ግን እላቹዋለው 'ስለ Maths ይበልጥ ባወክ ቁጥር አለመማርን ትወዳለህ' ።... ከከንቲባው ልጅ ጋር ቲቪ ከፍተን እያየን እያለ ስልኬ ላይ Msg ገባና አውጥቼ ሳየው... ከ 100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 19 ይለቀቃል🌹             𝗝𝗼𝗶𝗻 𝘂𝘀 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗   ♥️♥️ተቀላቀሉን ♥️♥️ https://t.me/ethio_author https://t.me/ethio_author ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን 🫶🇪🇹🇪🇹♥️❥❥__⚘_
Show all...
♥️የከንቲባው ልጅ♥️ 🥀ክፍል 19🥀 . . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! . . ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል . . ከከንቲባው ልጅ ጋር ቲቪ ከፍተን እያየን እያለ ስልኬ ላይ Msg ገባና አውጥቼ ሳየው Cost ገብቶልኝ ነው ። Non cafe ስለሆንኩኝ እንደ ተለመደው መንግስት #450 የኢትዮጵያ Dollar ባንክ account ላይ አስገብቶልኛል ። እኔ የምለው ግን ፡ መንግስት ለካ እንዲህ ቋጣሪ ነው ። cost መግባት የነበረበት በየወሩ በ #28 ነበር ። የዚህኛው ወር ግን በ #36ኛው ቀን ነው የገባው ። ቆይ ግን #450 ብር ለ #1 ወር በዚህ ኑሮ ፡ ብር ሆና ነው የምትበላው .? ያውም ከተማሪ ። እኛኮ ለምሳ እና እራት ብቻ #1200 ብር ነው የምንከፍለው ። እነሱ ግን የ #5 ሚሊዮን ብር እራት በልተው ፤ በ #450 ብር መፋቅያ ጥርሳቸውን ይፍቃሉ ። Bisrat tv እያየን ነው ። ፕሮግራሙም ስለ ሶሪያ ህፃናት ነው ። አንድ የ #7 ዓመት ህፃን እንዲህ እያለ ነው "በሽር አል አሳድ'ን (የሶርያ president) ምን አደረግነው ...? ዝምብለን እየኖርን ነበር ። ምንም ሳናደርገው ቤታችንን አፈራረሰብን ፣ ቤተሰቦቻችንን እንዳለ ገደላቸው ። ቆይ ግን ምን አድርገነው ነው ...?" ። ይሄንን ሲናገር ፊቱ እንደ ጎርፍ ዝናብ በዕምባ ተሞልቶ ነበር ። ሶሪያ ውስጥ የሞቱት ህፃናት ብቻ ከ #50,000 በላይ ናቸው ። አብዛኛዎቹ ሀገር ሰላም ብለው የትምህርት ገበታ ላይ የነበሩ ታዳጊዎች ናቸው ። በራሳቸው ጥፋት ሳይሆን በአባቶቻቸው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት ነገን ሳያዩ ዛሬን ሳይኖሩ በአጭር የተቀጩ ህፃናት ። ዛሬም ድረስ ጦርነቱ ቀጥሏል ፣ ሀገሪቷ ምድረ በዳ ሆናለች ፣ የሶሪያ ህፃናትና ህዝቦችም ስደት ላይ ናቸው ። አሸናፊ የሌለው የእርስ በእርስ ጦርነት መጨረሻው እንግዲህ ይህ ነው ። ከወር በፊት ሳቢያን ፡ ድሬዳዋ ብር ለማውጣት ባንክ ቤት ስሄድ መንገድ ላይ የሶሪያ ስደተኞች ተቀምጠው ሲለምኑ አይቼ ነበር ። ባልና ሚስት መሀላቸውን ልጃቸውን አስቀምጠው ፊትለፊት ደግሞ በአማርኛ ፊደል የተፃፈ "የሶሪያ ስደተኞች ነን ፡ እባካችሁን እርዱን" የሚል Copy ወረቀት ተቀምጦ ፣ በዚያ በኩል የሚያልፍ ሰው ደግሞ ከንፈሩን እየመጠጠላቸው ያለውን #1 ፣ #5 ፣ #10 ብር እየሰጣቸው ያልፍ ነበር ። እኔም ሳያቸው አንጀቴን ነበር የበሉኝ ። በተለይ ደግሞ መሀላቸው የተቀመጠው ፣ ምንም የማያውቀው ፣ #4 ዓመት እንኳን ያልሞላው ህፃን ልጅ እንዴት እንደ ሚያሳዝን ። anyways አያድርገውና ኢትዮጵያን ሳስባት እንደ ሶሪያ ካልሆንኩኝ ሞቼ እገኛለሁ ያለች ትመስላለች ። ሰላም ስልችት ብሏት ደም ደም ከሸተታች ሰነባብታለች ። ሰላም ሲሆን ጀርባዋን ይበላታል መሰለኝ ግደል ግደል ፣ ሰልፍ ውጣ ሰልፍ ውጣ ፣ ኮብል ኮብል ፣ አፍርስ አፍርስ ፣ ረብሽ ረብሽ ፣ ወዘተ ወዘተ ይላታል ። (ወዘተ ወዘተ እንኳን አይላትም ...😜) ። ከሶሪያ እንኳን መማር አልቻለችም ፤ የሰላም ዋጋ ምኑም አልገባትም ። ዛሬ ሁላችንም በየቤታችን ሆነን የምናየው የሶሪያ መጨረሻ የሌለው ዕልቂት ፣ መድረሻው የማይታወቅ ስደት ፣ መልስ የማያገኝ ጥያቄ ፣ ቀስ በቀስ የኛው ታሪክ ሆኖ ዓለም በየቤቱ ቁጭ ብሎ ይታዘበናል ። ልክ ዛሬ ለነዚህ ስደተኞች ከንፈር እየመጠጥን ሳንቲም እንደ ወረወርን ፤ አንድ ቀን ደግሞ ለኛም በባዕድ ሀገር ይወረወርልን ይሆናል ። ይሄ እንዳይሆን ከፈለግን ሁሉን ነገር የመንግስት ስራ ነው ማለቱን ትተን ለሰላማችን ስንል እራሳችን ፣ ቤተሰባችን ፣ ጓደኛችን ፣ ጎረቤታችን ፣ ሰፈራችን ፣ ቀበሌያችን ፣ ወረዳችን ፣ ዞናችን ፣ ክልላችን ፣ ምናምን ሳንል ለአንዲት ሀገራችን በጋራ ብንሰራ የተሻለ ብቻ ሳይሆን ተመራጭም ይሆናል ።.... የከንቲባው ልጅ በጣም ተጨንቃለች ። የአባቷ ስልክ አለመስራት ፣ ደብረ ዘይት ያየነው ሰውዬ ፣ ወደ ቤት ስንመለስ መብራቶቹ በርተው ማግኘታችን ፣ በቃ ሁሉም ነገር መጥፎ መጥፎውን እንድናስብ አርጎናል ። ከዚህም በላይ ደግሞ ያሳሰባት ነገር እኔን የሷ ችግር ውስጥ ማስገባቷ ነው ። አዚህ ቤት ውስጥ መሆን ይበልጥ ስለ ችግሩ እንድናስብ እንደሚያደርገን አውቃለሁ ። ይዣት ወጥቼ እንዳላስረሳት ፤ አባቷ እንዳሉትም ዛሬ የሚመጡ ከሆነ ከቤት እንዳያጧት ስለሰጋሁ ነው ። ለፖሊስ እንዳናመለክት ስለጉዳዩ ትተው ወደኛ እንደ ሚዞሮ ግልፅ ነው ። የሚከታተለንን ሰውዬ ትተው እኛን "እናንተ ማናችሁ ፣ ይሄ ቤት የማነው ፣ ይሄን ሁሉ ንብረትስ ከየት አመጣችሁ ...?" ከማለት አያልፉም ። ለጊዜው እንደ መፍትሔ ያየሁት ፊልም ማየቱን ነውና After የሚል ምርጥ የፍቅር ፊልም ሶፋ ላይ ሆነን እያየን ነው ። በመሀል በመሀል ሲሳሳሙ እየተሳሳምን ፣ ሲተቃቀፉ እየተቃቀፍን ፣ ሲጣሉ ደግሞ በመሃላችን ክፍተት እየፈጠርን በስተመጨረሻ ተቃቅፈን ፊልሙ አለቀ ። በፊልሙ ላይ ቅር ያለን ነገር ቢኖር ሲያልቅ ተዋንያን ሲፅፍ የኛን ስም አለመጥቀሳቸው ነበር ። እሱን እንደ ጨረስን ቁርስም ስላልበላን በጣም እርቦን ስለነበር ተያይዘን ወደ ኩሽና ገባን ። የጊቢ ተማሪ ሞያ + የቤት ልጅ ሞያ = ሞያሽ ሞያሽ ይዘርዘርልሽ ። ቁርስን መቀነስ ፣ ምሳን መሰረዝ ፣ እራትን ማሳነስ ብዙ ዕድሜ ለመኖር ዋስትና ነው ይላሉ ከቤተሰብ የተላከላቸውን ብር በአንድ ሳምንት የሚጨርሱ የጊቢ Non cafe ተማሪዎች ። በአለማችን ላይ በረሃብ የሞቱ ሰዎች ጥቂቶች ናቸው ። በተቃራኒው ግን በጥጋብ የሞቱት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ናቸው ። ስንቶቻችን ነን በምላሳችንና በጥርሳችን መቃብራችንን ስንቆፍር የምንውለው ...! ሆድ እንዳሳዩት ነው ፣ ወስፋታችንን መግታት ከብዶን ሁሉንም እችላለሁ ብለን አግበስብሰን ቁንጣን እስኪይዘን ድረስ የምንበላ ከሆነ መጨረሻችን እስኪሻለን ድረስ መፆም መሆኑን ማወቅ ይኖርብናል ። አንዳንድ ሰዎች "ስትበላ እንደልብ ፣ ስትጠጣ እንደልክህ" ይላሉ ። እኔ ግን እላችኋለሁ 'ሲርብህ ብላ ፣ ሲጠማህ ጠጣ' ። ፈላስፋው ሶቅራጥስም በዘመኑ "እኔ ለመኖር ስበላ ፣ ሌሎች ግን ለመብላት ይኖራሉ" ብሎ ነበር ። በዚህ ዘመን ግን ሀብታም ከሆነ በፈለገ ጊዜ ፣ ደሀ ከሆነ ደግሞ በአገኘ ጊዜ ሆኗል ነገሩ ። anyways ቤት ውስጥ ስጋ ነክ ነገሮችና እንጀራ ለጊዜው ስለሌሉ ቆንጆ ፓስታ ከከንቲባው ልጅ ጋር ተባብረን ሰርተን ተባብረን በልተናል ። ከሰዓታችንን ደግሞ መፅሐፍ በማንበብና ሙዚቃ በመስማት ልናሳልፈው አቅደናል ። ከአጫጭር የልቦለድ መፅሐፍት ውስጥ የአሌክስ አብርሃም "ዶክተር አሸብር" የሚለውን በጣም ስለምወደው እሱን ተራ በተራ የምንወደውን ርዕስ እየመረጥን አንዳችን ላንዳችን እያነበብን ከልባችን እየሳቅን ሳናስበው ቀኑ ለምሽት መንበርከክ ጀመረ ። በስተመጨረሻም ካሏት የግጥም መፅሐፍት ውስጥ አንዱን መርጬ በጣም የምወደውን አንድ ግጥም እንዳነብላት ጋበዘችኝ ። እኔ ግን Control ብፌው ውስጥ የሚታየኝን ወይን ከሁለት ብርጭቆ ጋር አውጥቼ ፣ እጇን ይዤ ከሳሎን ወደ ጊቢ ውስጥ ወጣን ። በረንዳ ላይ ተቀመጥንና ወይን እየጠጣን ፣ ጨረቃዋን እያየን የምወደውንና በቃሌ የማውቀውን አንድ ግጥም በዜማ እልላት ጀመር ። እንዲህ ብዬ ...🔈 ከ 100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 20 ይለቀቃል🌹   ኢትዮጵያን ይጠብቅልን 🫶🇪🇹🇪🇹♥️❥❥__⚘_
Show all...
♥️የከንቲባው ልጅ♥️ 🥀ክፍል 10🥀 . . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! . . ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል . . . የሆነ ነገር ወዳልሆነ ነገር ሊመራክ ከሆነ ፡ ማድረግ ያለብህ ከሆነ ነገር መራቅ ነው ። አልጋ ልብሱን አልብሻት ወደ አልጋዬ ተመልሼ ተኛሁ ። ጠዋት ነግቶ ከእንቅልፋችን ስንነቃ ፡ #03 ሰዓት አልፎ ነበር ። እዛው ካለንበት ሆቴል ቆንጆ ቁርስ በልተን ፡ ያለብንን የ #1 ለሊት የቤት ኪራይ ከፍለን ወደ ቡቲክ አመራን ። ውቢቷ ቢሾፍቱ ላይ ፈክተን የምናበራበትን ልብስ ገዝተን #05:30 ላይ ጉዞአችንን ወደዛው አደረግን ። ለሸገር ቅርብ ስለሆነች ብዙም ደቂቃ አልፈጀብንም ። ኩሪፍቱ ሪዞርት ከበር ላይ በክብር ተቀበሉን ። የምንቆይበት ክፍል ይዘን ፈታ ለማለት ትጥቃችንን አሟልተን ወደ መዋኛ ገንዳ አመራን ። ዋና እንደማትችል ጠጋ ብላ በጆሮዬ ነገረችኝ ። እኔም ልክ እሷ እንደነገረችኝ ፈራ ተባ እያልኩ በጆሮዋ እንደማልችል ነገርኳት ። በድንጋጤ አየችኝና "እና ምን ልናደርግ ነው የመጣነው ...? ፡ እኔ ደግሞ ምትችል መስሎኝ አንተን ተስፋ ማድረጌ" አለችኝ አኩርፋ ። ከዛን ሳኩባትና 'ስቀልድ ነው ባክሽ ፡ ዶልፊን እራሱ ጉልበቴ ስር ቁጭ ብሎ ነው የተማረው' አልኳት ። (ዶልፊን ግን ቁጭ ማለት ይችላል እንዴ ...😝) ። "ሂድ ፡ ጉረኛ" አለችኝና ትከሻዬን በፍቅር መታችኝ ። እኔ ለክባድ ብዬ ተከርብቼ ውሃው ውስጥ ገባሁ ። እሷ ግን ውሃ ነክታ አታውቅም መሠለኝ በስንት ልመና በዳዴ ገባች ። ለመዋኘት ገብቼ አሰልጣኝ ሆኜ አረፍኩ ። ያን ያክል እንኳን አላስቸገረችኝም ። ነገሮችን በቀላሉ የመያዝ ልዩ ችሎታ አላት ። ዋና የለመድኩት እንዲህ ባማረ ገንዳ ሳይሆን እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወንዝ ውስጥ ነበር ። እየዋኘሁ ፣ እያለማመድኳት ፣ እያረፍን ፣ በድጋሜ ያሁኑን step እየደገምን ከአንድ ሰዓት በላይ ቆየን ። አይን አይኔን እያየች "አስቸገርኩህ አይደል ...? ፡ በቃ የመጨረሻ አንድ ዙር አለማምደኝና ይብቃን" አለችኝ ። ሁለቱ እጆቼን ውሃው ውስጥ እንደ ምንጣፍ ዘረጋሁላት ። በሆዷና ታፋዋ እጆቼ ላይ ተኝታ በእጆቿ ደግሞ ውሃውን ወደ ዋላዋ እየገፋች ወደ ፊት ትመነጠቃለች ። እኔም ከጎኗ ሆኜ እከተላታለሁ ። እንደዛ እያደረገን የገንዳው ጫፍ ላይ ደረስን ። ከእጆቼ ላይ ወርዳ እዛው ውሃው ውስጥ በኔ ፊትለፊት ቆመችና አይን ለአይን ተጋጨን ። ውበቷ እንዴት እንደ ሚያስደነግጥ ideaw የላቹም ። አላወቁም እንጂ ሴቶቻችን የሚያምሩት በሜካፕ ሳይሆን በተፈጥሮአቸው ነው ። በዋናው ውሃ ታጥባ ኩልል ብላ ቆማ ስታየኝ ፈዘዝኩኝ ። በጣም ተቀራርበናል ። እንደውም ንፋስ በመሃላችን ለማለፍ ፈልጎ ሲታገለን ይሰማኛል ። አይኖቼ ከንፈሯ ላይ ደርቀው ቀሩ ። እሷም እንደኔው በአይኖቿ ከንፈሬ አካባቢ እየሾፈችኝ ነው ። ወደ ከንፈሬ በጣም ቀረበች ። ከንፈሯ እንኳን እሁድ ተገኝቶ ፡ እሮብንና አርብን እራሱ ያስገድፋሉ ። የሁለታችንም ስሜት እናታችን ላይ ሲወጣ ተጎራረስን ። ከንፈሯ ከከንፈሬ ፣ ትንፋሿ ከትንፋሼ ተዳመረ ። የኔን ትንፋሽ ወስዳ የሷን ለገሰችኝ ። ትንፋሿ ይሞቃል ፤ ከንፈሯ ይጣፍጣል ። ለብዙ ሴኮንዶች ከንፈር ለከንፈር ተገጣጥመን ፡ የአለምን አየር ንቀን ውስጣችን ያለውን ተለጋግሰን ዋና ገንዳው ውስጥ ከቆየን በዋላ ከንፈራችን ተላቀቀ ፡ አይናችንም ተከፈተ ። ትንሽ እንደ መተፋፈር ሆነን ከውሃው ውስጥ ወጣን ። በርዷት ነው መሠለኝ መንሰፍሰፍ ጀመረች ። አሳዘነችኝና ፎጣ አልብሻት ተሸከምኳትና ወደ ክፍላችን ጉዞ ጀመርኩኝ ። እሷን መሸከም ለኔ ብርቄም ድንቄም አይደለም ። ሶፋ ላይ በተኛችና በሰከረች ቁጥር እስከ መኝታ ክፍሏ የማድረስ የሁለት ቀን ስራ ልምድ አለኝ ። የዛሬው ግን ለየት ይላል ። አልሰከረችም ፣ አልተኛችም ፣ እራሷን አልሳተችም ፣ አይኖቿ አልተከደኑም ፣ ወዘተ ። ክፍላችንን እንደምንም በአንድ እጄ ከፍቼ ገባንና መልሼ በእግሬ ዘግቼው አልጋው ላይ ቀስ ብዬ አስተኛዋት ። አይኗን ቁልጭ ቁልጭ እያደረገች ወደላይ በስስት ታየኛለች ። እኔም ወደታች እንደዛው ። አንዲት ቃል ሳናወጣ በአይኖቻችን ብቻ እናወራለን ። ከዛን እጆቿን አንገቴ ላይ ጠምጥማ ወደራሷ ጎተተችኝና ድጋሜ ከንፈሮቻችን ህብረት ፈጠሩ ። ፎጣውን ከላዩዋ ላይ ወርውራ አልጋው ላይ ጣለችኝ ። ሁለታችንም ከዋና ገንዳው እንደ ወጣን ፡ እኔ ከላይ ራቁቴን ፡ ከስር ደግሞ በዋናው ቁምጣ ፤ እሷ ደግሞ ከላይ ጡት ማስያዣና ከስር በዋናው ፓንት ነው ያለነው ። ቅድም ከውሃው ስንወጣ በርዷት እንደዛ እንዳል ተንዘፈዘፈች ፡ አሁን ላይ ግን ገላዋ በሙሉ እንደ እሳት እየፈጀኝ ይገኛል ። አንገቷ ስር ገብቼ ስስማት ፡ አይኖቿን ጨፍና ፣ ትንፋሿን ዋጥ አድርጋ ፣ መልሳ ደግሞ በሀይል ትተነፍሳለች ። (አንገቷ ስር ከገባህ ፡ አይኗን ስትጨፍን እንዴት አየህ ...😝) ። ዛሬም እንደ በፊቱ 'ሴትና ወንድ ብቻቸውን ይሆኑ ዘንድ መልካም አይደለም' አልኩ ለራሴ ። ምን እያደረግን ነው ...? ፡ እዚህ ድረስ ለምን መጣን ...? ፡ ፈታ ማለት ምን ማለት ነው ...? ፡ አልኩኝ ለራሴ ። ከሀሳቤ ነቃሁ ፡ ከአንገቷ ምሽግ ወጣሁ ፡ ከአልጋዋ ላይ ተነሳሁ ፡ ወደ ራሴ አልጋ ሄድኩ ፡ ወደ ራሴም ተመለስኩ ። እሷም ግራ በመጋባትና በመናደድ አይነት ስሜት ከተኛችበት ቀና ብላ ታየኛለች ። የሆነ ነገር ልትለኝ ስትል በራችን ተንኳኳ ። እኔ እከፍታለሁ አልኳትና ከላይ ሸሚዝ ለብሼ ከፈትኩኝ ። አስተናጋጅ ነበር እና "የምትፈልጉት ነገር ካለ ማዘዝ ይቻላል" አለኝ በክብር እጅ እየነሳኝ ። እኔም 'ትንሽ ርቦናልና ምግብ ብናገኝ ደስ ይለናል' አልኩት ። እሱም "ከፈለጋችሁ እዚህ ፡ ፍቃዳችሁ ከሆነም ደስ የሚል ቦታ እወስዳችሁና እዛ ትበላላችሁ" አለኝ ። 'አይ ፡ ላሁኑ እዚህ እንበላለን ፤ ባይሆን ደስ የሚለውን ቦታ ማታ ትወስደናለህ' አልኩትና ሄደ ። #08 ሰዓት አልፏል ። አኩርፋኝ ቢሆንም አስተናጋጁ ያመጣልንን ምግብ እንደ ተለመደው ለራሷ ሳትበላ መጀመሪያ አጎረሰችኝ ። እኔም አጎረስኳትና ትንሽ በልተን ተውነው ። ከበላን በዋላም ሁለታችንም በአንድ ቤት ውስጥ ሆነን ሳናወራ ጀምበር እየታዘበችን ወደ ቤቷ ገባች ። ላወራት ብዬ ስነሳ በራችን ድጋሜ ተንኳኳ ። ስከፍት የቅድሙ አስተናጋጅ ነበርና ቅድም ወዳለኝ ቦታ ሊወስደን እንደ መጣ ነገረኝ ። #10 ደቂቃ ስጠን ብዬው ፡ ተመልሼ ፈራ ተባ እያልኩ ልጅቷን ቀሰቀስኳት ። 'ተነሽና ልብስሽን ቀይሪ ፡ ወደ ሆነ ቦታ እንሄዳለን' አልኳት ። አልተቃወመችኝም ፡ ልትቀይር ወደ ውስጥ ገባች ። ከሸገር የገዛነውን ልብስ አውጥቼ ለበስኩትና እሷ እስክትጨርስ መጠበቅ ጀመርኩኝ ። በዛ ውበቷ ላይ ቅድም የገዛነውን ልብስ እሷ ላይ ስስለው ፡ በቃ ጨረቃ እራሷ በአካል መጥታ የምታገኘኝ መሠለኝ ። ልጅቷ ከገባችበት ቀይራ ወጣች ።      "ደምቀሽ ስትወጪ ፡ ደምቀሽ ስትወጪ ፣       ደምቀሽ ስትወጪ ፡ ጨረቃ አፈረች"። ከ 100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 11 ይለቀቃል🌹 ━━━━━━✦✗✦━━━━━━ አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል             𝗝𝗼𝗶𝗻 𝘂𝘀 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗   ♥️♥️ተቀላቀሉን ♥️♥️ https://t.me/ethio_author https://t.me/ethio_author ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን 🫶🇪🇹🇪🇹♥️❥❥__⚘_❥
Show all...
♥️የከንቲባው ልጅ♥️ 🥀ክፍል 12🥀 . . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! . . ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል . . ,በኛ ካምፕ ውስጥ ደግሞ አንድ ታሪኩ ብቻ ነበር ያለው ፤ እሱም ምርጥ ጓደኛዬ ነበር ። ከዛን ልጆች እሱን ጠቁመዋት አገኘችው ። ስታየው እኔ እንዳልሆንኩ አወቀች ። ታሪኩ ደግሞ ከኔጋር ሲገናኝ ስሟንና ከየት እንደመጣች እየጠቆመ የተፈጠረውን ነገረኝ ። ያኔ ነበር እኔን እየፈለገች እንደሆነ የተረዳሁት ። ቀኑን አላውቅም እንጂ እንደ ማገኛት አውቅ ነበር ። ከሁለት ዓመት በዋላ ያቺን ልጅ ድጋሜ አየዋት ። ቆንጅናዋ እንዳለ ነው ፤ ኧረ እንደውም ይበልጥ ተውባ ነበር ። ተገናኘን ፣ ተቃቀፍን ፣ ለብዙ ሰዓት ቁጭ ብለን አወራን ። ሲመሽብን ስልክ ቁጥር ተለዋውጠን ተለያየን ። ከዛን ቀን አንስቶ ወደ ዱከም እስክትመለስ ድረስ በየቀኑ እንገናኝ ነበር ። ሁለታችንም እንደ በፊቱ ዝምተኛ አልነበርንም ። ስለ ብዙ ነገር አወራን ፣ ተጫወትን ፣ ብዙ ቦታ አብረን ዞርን ። በቃ ባጠቃላይ ፊልም ላይ ወይንም ልቦለድ ላይ የምታውቂውን የፍቅር ህይወት አብረን አሳለፍን ። በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የሷን ከንፈር ነበር የሳምኩት ። ወክቱ ክረምት ነበር ፤ የቴዲ አፍሮ "ኢትዮጵያ" አልበም ደግሞ በብዛት ይደመጥ ነበር ። ከሱ አልበም ውስጥ ሁለታችንም "ማራኪዬ" የሚለውን ዘፈን ከቴዲ አፍሮ በላይ ወደድነው ። ልምድ ሆኖብን ሁለታችንም ከዛን በዋላ #ማራኪዬ እያልን መጠራራት ጀመርን ። ማንም ወንድ ቢቀርባት በፍቅር የሚወድቅላት ልጅ ነበረች ። እኔም ወደኩላት ። በጣም ነበር የምንዋደደው ፤ ከምነግርሽ በላይ ። የሚገርምሽ ቀኑን ሙሉ አብረን ውለን ሰለ ማንጠጋገብ ማታ ማታ ደግሞ በስልክ txt እንፃፃፍ ነበር ። እንደውም የሆነ ቀን የተፃፃፍነውን የመልዕክት ብዛት ሳይ #5000 አልፎ ነበር ። እና ማራኪዬ ለኔ ሁሉ ነገሬ ነበረች ። የኔ አሳቢ ፣ የኔ እናት ፣ የኔ ፍቅር ፣ የኔ ረቡኒ ፣ በቃ ምን ልበልሽ ፡ እሷን ምድር ላይ ያሉ ቃላት አይገልጿትም ። በዚች ምድር ላይ እንደሷ የሚወደኝ ፤ እኔም እንደሷ የምወደው አልነበረኝም ። ፍቅርን ምድር ላይ ባሉት ነገሮች ግለፅልኝ ቢሉኝ #ማራኪዬን ነበር የምጠቁመው ። ያን ጊዜ እሷ የ #10ኛ ክፍል matric ፡ እኔ ደግሞ የ #12ኛ ክፍል entrance ፈተና ወስደን ውጤት የምንጠብቅበት ነበር ። ክረምቱን አብረን በፍቅር ዘመትን ። የመጣችሁ ክረምቱን ዘመድ ጋር ለማሳለፍ ነበርና ክረምቱ ሲገባደድ መሄጃዋ ደርሶ በእምባ ተለያየን ። ውጤት ተለቀቀ ፡ ሁለታችንም አለፍን ፡ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ደረሰኝ ። በስልክ ብቻ በየቀኑ txt እየተፃፃፍን ፡ በሳምንት እየተደዋወልን #8 ወር አለፈ ። ናፍቆታችን ገደቡን ሲያልፍ ቢሾፍቱ መጥቼ እንደማገኛት ቃል ገባሁላት ። በቃሌ መሠረትም ለፋሲካ በዓል ወደ ቤት ስመለስ አንድ ቀን ቀደም ብዬ ከድሬዳዋ ፡ ሸገር ፡ ከዛም ደብረ ዘይት እሷን ላገኛት ሄድኩኝ ። ለሶስተኛ ጊዜ ቢሾፍቱ የሄድኩት ያኔ ነበር ። #27-08-2010 ዓ.ም ። ተገናኘን ፣ በፍቅር ተቃቀፍን ። ስንተያይ እንዴት ደስ እንዳለን ideaw የለሽም ። የሆሳዕና ሳምንት ነበርና የሰራሁላትን የዘንባባ ቀለበት አደረኩላት ። ደብረ ዘይት ላይ አብረን ለ #3 ሰዓታት በፍቅር ሰከርን ። የመጀመሪያው ምሳችንን አብረን በላን ፣ ቢሾፍቱ ሀይቅ ሄደን juice እየጠጣን ተዝናናን ፣ photo ተነሳን ፣ ስለኛ ብዙ ነገር አወራን ፣ ተሳሳምን ፣ ተቃቀፍን ፣ ብቻ ያቺን ቀን በህይወቴ መቼም አልረሳትም ። ስጦታ የአንገት መስቀል አስራልኝ ልባችን እያለቀሰ ተለያየን ። እና አሁን አንገቴ ላይ የምታዪው ይህ መስቀል ማራኪዬ ያን ቀን ያደረገችልኝ ነው' አልኳትና በረጅሙ ተነፈስኩ ምንም ሳትለኝ አልጋው ውስጥ ገብታ ተኛች ። እኔም ከዛን በዋላ አልተናገርኳትም ። እንደ መሸ አልቀረም ፡ ነጋና በጠዋት ተነሳን ። ቁርስ ከበላን በዋላ "እና ደብረ ዘይትን አታስጎበኘኝም ?" አለችኝ ። 'እሺ' አልኳትና ባቦጋያ ፣ ምሳ ሰዓት ሆራ አርሰዴ ፣ ምሽት ላይ ደግሞ ቢሾፍቱ ሀይቅ ወስጃት ደስ የሚል ቀን አሳለፍን ። ትናንት ማታ በነገርኳት ታሪክ ምክንያት እንደ ከዚህ በፊቱ አትስመኝም ፣ አታቅፈኝም ፣ ሌላው ቢቀር ድንገት አይን ለአይን ስንጋጭ እራሱ አንገቷን ትደፋለች ። ወደ ኩሪፍቱ ተመልሰን እራት ከበላን በዋላ "ማታ ምንም ሳልልህ በመተኛቴ ይቅርታ ። ግን ታሪኩን እንድትጨርስልኝ እፈልጋለሁ" አለችኝ ። እኔም ካቆምኩበት ቀጠልኩላት ። 'እንዳልኩሽ ማራኪዬ ለኔ ሁሉ ነገሬ ነበረች ። ይሄን ደግሞ የፍቅር ታሪኬን ለሚጠይቀኝ ሁሉ አወራ ነበር ። የሆነ ቀን ግን ታሪኬን ከነገርኳቸው ሰዎች መሀል አንዱ "ስለሷ ስታወራ ከልክ በላይ እርግጠኛ የሆንክ ይመስለኛል ። ግን ተስፍሽ አንድ ነገር ልንገርህ ። ከራስህ ውጪ በማንም እርግጠኛ አትሁን ። ሁሉም ሰው አንተ እንደ ምታስባቸው ላይሆኑ ይችላሉ ። እንደዚህ የምልህ ክፉ ነገር አስቤ አይደለም ። ስለ ልጅቷ ከልክ በላይ የተማመንክባት ስለመሰለኝና አንድ ቀን እንዳትጎዳ ስለፈለኩኝ ነው" አለኝ ። በሱ አስተያየት ምንም አልተሸበርኩም ነበር ። እንደውም 'አንተ ማራኪዬን ስለማታውቃት ነው' አልኩት ። ከዛ በዋላ ነው እንግዲህ ጨዋታው የተጀመረው ። "ስማ ተስፍሽ ፡ እንደ ነገርከኝ ከሆነ ማራኪዬ የምትላት ልጅ ፡ አንተ ምንም ብትሆን ፣ የትም ብትሄድ ፣ ሌላው ይቅርና አንተ ብትተዋት እንኳን የማትተውክ ፣ እስከ እለተ ሞቷ ድረስ የምታፈቅርክ የተለየች ሴት ናት ። ይሄን ያክል ደግሞ በሷ እርግጠኛ ከሆንክ ለምን እኔ የምነግርህን ፈተና አታቀርብላትም ...?" አለኝና ፈተናው ምን እንደሆነ ጠየኩት ። ቀጠለና "ምን መሰለህ ፡ #3 ነገሮችን እንድታደርግ እፈልጋለሁ ። #1ኛው ፡ የልደት ቀኗ ሲደርስ ምንም አይነት txt እንዳትልክላት ፣ እንዳት ደውልላትም ። በዚህም ከሁሉ በላይ አንተን ስለ ምትጠብቅህ በጣም ታዝንብሀለች ። #2ኛው ፡ ያንተ የልደት ቀንም ሲደርስ ፡ ከሷ ለሚመጡልህ የመልካም ምኞት መግለጫ መልስ አትስጥ ። ይሄ ነገርም የንዴት መጠኗን ከፍ ያደርጋል ። #3ኛውና ወሳኙ ደግሞ ፡ ክረምት ክረምት እናንተ ጋር ሙገር እንደ ምትመጣ ነግረኸኛል ። እናም ባሁኑም ክረምት መምጣቷ ስለማይቀር ፡ ያኔ ስትገናኙ ፊት ንሳት ፣ እንደ ማትወዳት act አርግ ፣ ከሷ ጋር በመሆንህም ደስተኛ እንዳልሆንክ አስመስል ። አንተን ብላ መጥታ እንደዛ ስትሆንባት መቼም ምን እንደሚሰማት መገመት አይከብድም ። እውነት እልሀለሁ ተስፍሽ እነዚህን ሶስቱን ነገሮች ተግብረህ ፡ ማራኪክ 'እኔ አልተውህም ፣ እንደዚህ ብትሆንብኝም እወድሃለሁ' የምትልህ ከሆነ she is the best girl in the world" አለኝ ። ሶስቱን ፈተና ብሎ የነገረኝን ስሰማ መጀመሪያ ስቄበት ነበር ። እንደ ቀላል አይቼው ፣ እንደ ምታልፈውም በሙሉ ልቤ ስለተማመንኩኝ ልፈትናት ወሰንኩኝ ። ስለዚህ ጉዳይ ከኔና ከልጁ ውጪ ማንም ሰው አያውቀውም ። ደስ የሚለው ነገር የልደቷ ቀን ያኔ የነበርንበት ወር ውስጥ ነበር ። የመጀመሪያው የፈተና ቀን ደረሰ ፡ የልደቷ ቀን.. ከ 100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 13 ይለቀቃል🌹             𝗝𝗼𝗶𝗻 𝘂𝘀 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗   ♥️♥️ተቀላቀሉን ♥️♥️ https://t.me/ethio_author https://t.me/ethio_author ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን 🫶🇪🇹🇪🇹♥️❥❥__⚘_❥
Show all...