💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
Open in Telegram
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Show more8 750
Subscribers
-724 hours
-357 days
-9730 days
Posts Archive
🔖ኢብኑ በጣል አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።
~
👉ሚስጥር አማና ነው። መጠበቁ ግዴታ ነው። ይህም የሙእሚኖች ባህሪ ነው። ነብዩን አስር አመት ኻድሚያለሁ። "ሚስጥሬን ጠብቅ ሙእሚን ትሆናለህ"
ብለውኛል የሚል ዘገባ ከአነስ ኢብኑ ማሊክ ተወርቷል።
📚شرح صحيح البخاري (9/64) :~ t.me/https_Asselfya
Repost from 🔷🔸|قناة الخطبــــــــاء🎙
🔸أسباب نزع البركات من الأرزاق
#خطبة الجمعة
بدار الحديث بوادي بنا- السدة
🎙للشيخ الفاضل|
أحمد بن أحمد شملان
حفظه الله تعالى
🗓 بتاريخ ٠٥ جمادى الأولى ١٤٤٨ه
┈┉┅━━•❁•━━┅┉┈
◢للمزيد| قناة الخطباء
➢https://t.me/ooooh5
ትዳር የዘገየባት ኒቃቢስት ካየህ እርሷ ወንድ ሳይሆን ያጣችው ሸሪዓዊ መስፈርቷን የሚያሟላ ሰለፊይ ባል የሚሆናትን ወንድ ነው።
አላህ ያበርታት🤲
🌸ኡክቲዬ🍒
--»አንቺ ሷሊህ ከሆንሽ ሀቅ የምጠብቂ
--»ባል አጣሁኝ ብለሽ አትጨናነቂ
--»መልካም ለመልካሞች መሆኑን እወቂ
--»ወቅቱ ቢዘገይም እንዳትበሳጪ...
--»በሶብር ጠብቂ ሷሊሁን አታጪ። ©
ቀልብ የፅድቅም የጥፋትም የእዝ ማዕከል
~
ጀነት ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተከባለች፤ ጀሀነም ደግሞ ነፍስ በምትወዳቸው ሸይጧን በሚያስውባቸው አማላይ ነገሮች፡፡ በብዙ ሁኔታዎቻችን ከአረሕማን ይልቅ ለሸይጧን የቀረብን ነን፡፡ ዐይኖቻችን፣ ጆሮዎቻችን፣ እጆቻችን፣ እግሮቻችን፣ እንዲሁም ምላሳችን ለሸይጧናዊ ተልእኮ የሰሉ ናቸው፡፡ ቀላሉን አምላካዊ ክልከላ መታገስ አቅቶን ከባባድ ሸይጧናዊ ልፋት ላይ እንተጋለን፡፡ ሁሉም የሰውነታችን ክፍሎች ለጥፋት ሲተባበሩ፣ አንዳቸው ብቻ ለሚበቁት ኸይር ግን ተባብረውም ይዝላሉ፡፡ ይሄ ሁሉ የሚሆነው እንግዲህ ማዕከሉን “ዋግ” ሲመታው ነው፡፡ ቀልብ በሺርክ፣ በቢድዐ፣ በስሜት፣ ለሙስሊሞች በምታረግዘው ክፋት፣ … ከተበከለች ታማ፣ ታውካ፣ አመርቅዛ ትሞታለች። ታዲያ ቀልብ ስትሞት ሞቷ ለኸይሩ እንጂ ለሸሩማ ኢንኩቤተር ትሆናለች - ክፉ የሸር መፈልፈያ። ብቻ ሂወቷ በኢማን ካልኩሌተር ሲሰላ ያለ ኢማን ሂወት የለምና ሞታለች - የምር ሞት! ከዚያስ? ከዚያማ ቀልብ ተበላሽታ ሌላው ሰውነት ምን ጤና ሊኖረው? የአካል እንቅስቃሴ በሙሉ ደመ-ነፍሳዊ ይሆናል። ተንቀሳቃሽ ሙት! ግድግዳ የተጠጋ እንጨት ሆኖ ሂወት እንዳለው ያስባል፡፡
ከዚህ በኋላ ዐይንም ዐይን ጆሮም ጆሮ አልሆነም፡፡ የሰማያትና የምድር አፈጣጠር፤ የሌሊትና የቀን መተካካት ለሱ ከታክሲዎች መተላፍ፣ ሽንት ቤት ደርሶ ከመመለስ ብዙም ልዩነት የለውም፡፡ ችግሩ ከማዕከሉ ነዋ!
(أَفَلَمۡ یَسِیرُوا۟ فِی ٱلۡأَرۡضِ فَتَكُونَ لَهُمۡ قُلُوبࣱ یَعۡقِلُونَ بِهَاۤ أَوۡ ءَاذَانࣱ یَسۡمَعُونَ بِهَاۖ فَإِنَّهَا لَا تَعۡمَى ٱلۡأَبۡصَـٰرُ وَلَـٰكِن تَعۡمَى ٱلۡقُلُوبُ ٱلَّتِی فِی ٱلصُّدُورِ)
"ለነርሱም በነርሱ የሚያውቁባቸው ልቦች ወይም በነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮዎች ይኖሩዋቸው ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን እነሆ ዐይኖች አይታወሩም። ግን እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ይታወራሉ፡፡" [አልሐጅ፡ 46]
በሌላ በኩል ልብ ከተስተካከለች፣ በኢማን ከተዋበች፣ በተቅዋ ካሸበረቀች መላ ሰውነት ጤና ይኖረዋል፡፡ ፊትም ኑር ይላበሳል፡፡ ዐይኖች በሐራም አይገግሙም፡፡ ጆሮዎች ለሙዚቃ አይቆሙም፡፡ ምላስም የሀሜት ማሽን አትሆንም፡፡ ከውጭ ሙስሊም ያልሆነ ገፅታ እየተስተዋለ ምላስ “ዋናው ልብ ነው” እያለች አታሽቃብጥም፡፡ ማዕከሉ ነቅቶባታላ!
ልብ ስትስተካከል እውነተኛ ማንነት ይገኛል፡፡ ከውስጥም ሙስሊም፣ ከውጭም ሙስሊም! በሐያእ የለሰለሰ፣ በውጭ ገፅታው ያልተኮፈሰ፣ በልቡ የመጠቀ፣ ከእንቶ ፈንቶ የራቀ ልዩ ስብእና! አቡበክር ሲዲቅ ረዲየላሁ ዐንሁ ከሌሎች በተለየ የላቁት በሶላትና በፆማቸው ብዛት አልነበረም፡፡ ይልቁንም ልባቸው ውስጥ በፀደቀ ነገር ነበር። ኢማን! የቀልብ ልዩ ክብር!
ባጭሩ ጥፋታችንም ልማታችንም ከልብ ጋር የተሳሰረ ነው ማለት ነው፡፡ ታዲያ እኔና እርሶ የቱጋ ነን? ሰገነት ወይስ ጫማ ተራ? ነው ወይስ መሀል ሰፋሪ? በሌላ አነጋገር ልባችን ጤነኛ ነው? በሽተኛ ነው? ወይስ ሞቷል? ለካ ይህንንም ለማወቅ ልብ ያስፈልጋል፡፡ "ባለ ልቦናዎቹ እንጂ አይገነዘቡም" አይደል ያለው ኻሊቁ?
አንተ ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው ጌታችን ሆይ! ልቦቻችንን ወደ ትእዛዝህ አዙርልን። በዲንህም ላይ አፅናን፡፡ አላሁመ ኣሚን፡፡
(ኢብኑ ሙነወር፣ 2001)
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ለራስሽ የማተገብሪውን ነገር ለሰው አትምከሪ..!
ሰው ለሌላ ሰው አርአያ ሊሆን የሚችለው ለራሱ የተግባር ሰው ሲሆን ነው...!
ለመሆን እንጅ ለመምሰል አትሞክሪ..!
ምክኒያቱም ጠንካራዋ እንስት የተግባር ሰው እንጅ የወሬ ሰው አይደለችምና...!
Repost from قناة دروس فضيلة الشيخ محمد زين بن آدم الحبشي - Sheikh MuhammedZain Adam - ሸይኽ ሙሐመድዘይን ኣደም
السلام عليكم ورحمة الله
አሁን የሪያድ ደርሳችን ይቀጥላል
ክፍል 348
ሐዲስ ቁጥር 1761
የሀይድን ጉዳይ እያስተዋልኩ ነበር… ብዙ ሴቶች በሀይድ ወቅት ራስ ምታት፣ ሆድ ቁርጠትና የጀርባ ህመም ያጋጥማቸዋል … አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት በከፍተኛ ድብርትና የስሜት መገለባበጥ ውስጥ ይመላለሳሉ ምናልባትም አንዳንዴ ማልቀስ…
ይህ ሁሉ ሲሆን ዓለም ለነርሱ ብሎ ለደቂቃ እረፍት አይሰጣቸውም … መደበኛ ትምህርቶች አይቋረጡም፣ ፈተናዎች አይዘዋወሩም፣ ስራም ለነርሱ ብሎ የተለየ ፈቃድ አይሰጥም… አላህ ሲቀር… ወዱድ ሲቀር…
እርሱ ይወዳቸዋልና እንዲንገላቱ አልፈቀደም… ልዩ የህይወት ፈቃድ ሰጣቸው … በዚያ ወቅት ሰላትን አነሳላቸው … ፆም እንዳይፆሙ ከለከላቸው… “ነብዩ እኔ ሀይድ ላይ ሆኜ እቅፌ ውስጥ ይደገፉና ቁርአን ይቀሩ ነበር።" ትላለች አዒሻ… ክብር ተመልከቱ… በነብዩ የህይወት ትምህርት ውስጥ ወንድ ልጅ በየትኛውም ሁኔታ ባለቤቱን ካላከበራት ክብር የለውም "ከናንተ ውስጥ ምርጡ… ለባለቤቱ ምርጥ የሆነው ነው" እንዲሉ … ከዚያ አንዳንዶች ይመጡና እስልምና ሴትን ልጅ በድሏል ይላሉ… ሀሻ ወከላ…
نقل
~አላህ መልካም የሻለትን ሰዉ ድኑን ያስገነዝበዋል።በተቃራኒዉ ሼር የሻበትን ሠዉድንን አያዉቅም።ዲንን ለማወቅ ችልተኛ ይሆናል።
~
. 10 ምክር ለእንስቶች .
እህቴ ጀግና ሴት ነኝ ካልሽ
1ኛ: ከሚያናግርሽ ወንድ ሁሉ ጋር አትሳቂ። አንዳንዴ መኮሳተር ጥሩ ነው። ድንበር የሌለው ፈገግታና ሳቅ ከመንገድሽ ያዘገይሻል።
2ኛ: በኢስላምሽ ጉዳይ አትደራደሪ፣ ምክንያቱም ኢስላምሽ ከህይወትሽ በላይ ውድ ነው። አንችን ከመከራ፣ ከስቃይ አውጥቶሻል። ከነ ህይወትሽ በሚቀብሩሽ ሰኣት ‘ለምን!?’ ብሎ ጠበቃ ሆኖ ለነፃነት አብቅቶሻል።
3ኛ: በእምነትሽ አትፍሪ፣ ረጋ ብለሽ ተጓዥ። ባለሽ ነገር ተብቃቂ። ኩርምት አትበይ። ከእምነትሽ ያፈነገጠ አለባበስና ፋሽን ተከታይ አትሁኚ አደራ። ኢስላምሽ ሰማያዊ እንጂ ዘመናዊ አይደለም።
4ኛ: ወደ ዝሙትና ወደ ወንጀል ከሚጋብዙ ነገሮች ሁሉ ራቂ። ‘ኢስላማዊ’ የሚለው ስም እንዳይሸውድሽ አደራ። ኢስላማዊ ፊልም፣ ኢስላማዊ ነሺዳ።
5ኛ: በቦርሳሽ ውስጥ የኮስሞቲክስ ነጋዴ ይመስል የቻይና እቃ ይዘሽ አትዙሪ። ይልቁንስ የእምነትሽን መመሪያ ቁርኣን መያዝን አትርሺ። ቦርሳሽ ውበት የሚኖራት ያኔ ነው።
6ኛ: ድንግልናሽን ጠብቂው። ለምታገቢው ብቻ አስቀምጪ። አላህ ካልፈቀደው ነገር ሁሉ ራቂ። ያኔ ደስተኛ ህይወትን ትኖሪያለሽ።
7ኛ: ሁሌም የምትሰሪውን ስራ አስተውይው። ሙስሊም እንስት የምትፈፅመውን እንጂ አትስሪ።
8ኛ: ሙስሊሟ እህቴ ሆይ! አንቺኮ ምርጥ ነሽ። ወንድ ሁሉ ይፈልግሻል። የሚያገባሽ እንዴት ታድሏል። ተፈላጊ መሆንሽን አትርሺ። ግን ለሚያገባሽ እንጂ ለሚፈልግሽ ሁሉ አትገኚ።
9ኛ: ሁሌም እምነቴ ኢስላም ነው ብለሽ ስታስቢ በሀሴት ልትረኪ ይገባል። ምክንያቱም የጀነት እጩ ተወዳዳሪ ነሽ። ውድድሩን ለማሸነፍ መዝሀበ ሰለፍን ተከተይ አደራሽን።
10ኛ: የመጨረሻው መልእክቴ - ተውሒድና ሱናን ባገኘሽው አጋጣሚ ሁሉ ለእህቶችሽ ስበኪ። ያኔ ውበትሽ ይደምቃል።©
Repost from «🔵Abu_Aisha (Awel_kasaw)»
የከሽፉ ሹቡሃት ደርስ ክፍል 12
⭕️ቀጥታ ስርጭት ⤵️⤵️⤵️
https://t.me/Abuebrahim22322?livestream=b0795afe1ea5240102
Repost from የኮምቦልቻ አህለሱና አንሷር መስጅድ official የሰለፍዬች channel
የጁመአ ኹጥባ (በኮምቦልቻ አንሷር መስጂድ) በኹጥባው ላይ የተወሱት ነጥቦች
የኹጥባው ርዕስ፦ «تزكية النفس (የነፍስ ንጽህና)»
◈ የነፍስ ንጽህና ትርጉም፦ ነፍስን ከሽርክ፣ ከቢድዓ፣ ከማዕሲያ (ከሃጢያት) እና ከመጥፎ ስነ-ምግባሮች ማጽዳት፤ እንዲሁም በኢማን፣ በታንት እና በበጎ ስነ-ምግባር ማሳደግ።
◈ እውነተኛው የነፍስ ንጽህና መንገድ፦ ሰው ውጫዊ አካሉን ብቻ ሳይሆን ልቡን፣ ሰብዕናውን እና ሃሳቡን ከኩራት፣ ከሐሰድ (ከምቀኝነት)፣ ከውሸት እና ከግልጽ/ስውር ኃጢያቶች መጠበቅ እንዳለበት።
◈ የሰው ልጅ ስኬት በልብ ንጽህና ላይ የተመሰረተ መሆኑ፦ በአኼራ ከሰዎች ንብረት እና ብዛት ይልቅ «ከሰላም ጋር ከመጣ አላህ ዘንድ የሚጠቅመው ንጹህ ልብ ያለው ሰው ብቻ ነው» የሚለው ነጥብ።
◈ የስኬት መለኪያ ገንዘብ ወይም መስተካከል አለመሆኑ፦ አላህ ዘንድ ደረጃ የሚሰጠው በውጫዊ ገጽታ፣ በሀብት ብዛት ወይም በዘር ከፍታ ሳይሆን በልብ እና በስራ ንጽህና መሆኑ።
በሸይኽ ሰይድ ሙሐመድ (አቡ ሙሐመድ አልፋቲሕ)
https://t.me/kombolcha_Ansuarmesjid_channel
Repost from 📱[ انتبه أنت مراقب ] 📲
👉በሌሊቱ ጨለማ ከአላህ ጋር ገለል
ማለት የቻለ ሰው ፊቶች በሚያበሩበት ቀን
አላህ የኑር ልብስ ያለብሰዋል ይላሉ።
ابن الجوزي | المدهش
Repost from N/a
السلام عليكم ورحمت الله وبركاته
الحمد الله
ዱኒያ ድንገህ ሳታስቡት እደምትሰናበታችሁ ሁሉ
እኔም ድንገት ሳላስበው ቻናሌን ተሰናበትኩት ሀቂቃ 1800ህዝብ
t.me/qdemiy_letwuhide
👆👆👆👆👆
ወዳጆቼን ተከታዩቼን በዚህ መልኩ አጣሁ ነገር ግን እኔ በህይወት ስላለሁ ዳግም አገኛቸዋለሁ እናም ቻናሌ ሰው አልባ ሁኗል እኔም ይሄን ቻናል ከፍቻለሁ አልሀምዱሊላህ ሼር እያረጋችሁ ተቀላቀሉ እላለሁ
t.me/qdmiyaletewhid2
🥖🥑የማበላና የማጠጣዋ ሴት!!
(እውነተኛና የተረጋገጠ ታሪክ)
ስሟ፦ ረሕማ ቢንት ኢብራሂም አል-ቍዋረዝሚይ (ረሕማ የኢብራሂም ሴት ልጅ)
የታሪኩ ምንጭ ማስተላለፍ ሰነድ፦
አል-ሓኪም እንዲህ ብለዋል፦ «አባቴ ነግሮኛል፤ አጥ-ጦህማኒ እንዲህ ሲል ሰምቻለሁ፦ "በቍዋረዝም ከተማ የማበላ፣ የማጠጣ እና ወደ መጸዳጃ ቤት የማትሄድ አንዲት ሴት አይቻለሁ።"»
የሕያ አል-ዐንበሪ እንዲህ ብለዋል፦ «አጥ-ጦህማኒ ስለዚያች የማትበላና የማትጠጣ ሴት ሁኔታ ሲያወራ ሰምቻለሁ፤ እንደዚሁም ሃያ ዓመታት በላይ (نيفاً وعشرين سنة) እንደኖረችና ይህንን በዓይኑ እንዳየ መሰከረ።»
የታሪኩ መነሻና ዝርዝር ሁኔታ፦
አዘ-ዘሀቢ እንዲህ ይላሉ፦ «ታሪኳን በ'ታሪኹል ኢስላም' መጽሐፍ ውስጥ አስፍሬያለሁ። እሷም ረሕማ ቢንት ኢብራሂም ናት። ባሏ ተገደለ፤ ሁለት ልጆችንም ትቶላት አለፈ፤ እሷም ድሃ ነበረች።
አንድ ቀን ተኝታ ባሏን ከሸሂዶች ጋር በምግብ ማዕድ ላይ ተቀምጦ አየችው፤ እሷም በወቅቱ ጾመኛ ነበረች። እንዲህም አለች፦ 'ባሌ ከእነሱ ፈቃድ ጠየቀና አንድ ቁራሽ እንጀራ ሰጠኝ፤ በላሁትም፤ ከነገሮች ሁሉ ጣዕሙ ለየት ያለና ያማረ ሆኖ አገኘሁት። ስነቃም ጠግቤ ነበር፤ ከዚያም ሁኔታው ቀጠለ።'
ይህ እውነተኛ ታሪክ ነው። በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ለሆነው ጌታ ጥራት ይገባው! ከጀነት ምግብ እንደበላች ይገመታል፤ አላህም እንዲህ ብሏል፦ {إِنَّ لَكَ أَلّا تَجوعَ فيها وَلا تَعرى} (እነሆ፤ ለአንተ በእርሷ (በጀነት) ውስጥ ከቶ አትራብም፤ አትራቆትምም) [ጣሀ - 118]።»
በታሪክ ሊቃውንት የተደረገላት ትርጉም (ማስታወሻ)፦
አል-ቀዝዊኒ በ«አሳር አል-ቢላድ» (ገጽ 234) ላይ እንዲህ ሲል ጽፎአል፦ «ረሕማ ቢንት ኢብራሂም አል-ሀዛርሲያ ለሠላሳ ዓመታት ያህል ምንም ዓይነት ምግብ አልቀመሰችም ተብላ የታወቀች ናት። አቡል ዐባስ ዒሳ አል-መርወዚ እንደተረከው ከሆነ፤ የምግብ ሽታ ሲሸታት ይከብዳት ነበር፤ ሆዷም ከጀርባዋ ጋር ተጣብቆ እንደነበር ተናግራለች። ከዚህም የተነሳ ሆዷ እንዳይጎዳባት የጥጥ ፍሬ የያዘ ከረጢት በሆዷ ላይ አስረው ነበር።
እስከ ሁለት መቶ ስልሳ ስምንተኛው (268) ዓመተ ሂጅራም ቆይታለች።» ©
[ምንጭ፦ «ሲየሩ አዕላሚን-ኑበላእ» 13 / 572]
