cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

TIKVAH-MAGAZINE

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524

Show more
Advertising posts
196 364Subscribers
+5024 hours
+2367 days
+1 87830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#Update: በዲላ ከተማ ሚያዝያ 5 በጣለው ንፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ምክንያት በከተማው ሙሉ ለሙሉ ተቋርጦየነበረው የኤሌክትሪክ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል መስተካከሉ ተገልጿል።
Show all...
👏 74🤔 7😡 5 4😨 1
ዩናይትድ ኪንግደም ከ150 አመታት በፊት ከአሻንቲ የተዘረፉ 32 የወርቅ እና የብር ቅርሶችን ለጋና በውሰት መለሰች ዩናይትድ ኪንግደም ከ150 ዓመታት በፊት በብሪቲሽ እና ታዋቂ በነበሩት የአሻንቲ ህዝቦች መካከል በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ከአሻንቲ ንጉስ ፍርድ ቤት ተዘርፈው የተወሰዱ 32 የወርቅ እና የብር ቅርሶችን ለስድስት አመታት ውል በውሰት ለጋና መስጠቷ ተገለፀ። ቅርሶቹ ሊመለሱ የቻሉት የወቅቱን የአሳንቲ ንጉስ የሆኑት "ኦቱምፉኦ ኦሴይ ቱቱ 2ኛ" የብር ኢዮቤልዩ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሚቀጥለው ወር በአሻንቲ ክልል ርዕሰ መዲና በሚገኘው በማኒሺያ ቤተ መንግስት ሙዚየም ለእይታ እንዲቀርቡ ታልሞ መሆኑ ተጠቁሟል። ዩናይትድ ኪንግደም እነዚህ ቅርሶች የመለሰችው የአውሮፓና የአሜሪካ ሙዚየሞችና ተቋማት እንደ ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ቤልጂየም ባሉ ኃያላን አገሮች በቅኝ ግዛት ዘመን የዘርፏቸውን የአፍሪካ ቅርሶች እንዲመለሱ ግፊት እየተደረገባቸው ባለበት ወቅት መሆኑም ነው የተገለፀው።
Show all...
😡 19🤔 18 4😨 1
በኢትዮጵያ የ2ኛ እና 3ተኛ ክፍል ተማሪዎች ከግማሽ በላዩ ማንበብ እንደማይችሉ ጥናት አመለከተ። የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ንባብን መሠረት አድርጎ ባካሄደው ጥናት በኢትዮጵያ የሚገኙ የ2ኛ እና 3ኛ ክፍል ተማሪች #56_በመቶዎቹ ምንም ዓይነት ቃል ማንበብ እንደማይችሉ አመልክቷል። 👩‍🎓  በጥናቱ ምን ያህል ተማሪዎች ተሳተፉ? በዚህ ንባብን መሠረት ባደረገ ጥናት ከ9 ክልሎች የተወጣጡ ከ16 ሺህ በላይ ተማሪዎች በዘፈቀደ (Random sampling ) ተመልምለው ተሳትፈዋል። ተማሪዎቹ ከ401 የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የተመረጡ ናቸው። 🔍  ጥናቱ እንዴት ተካሄደ? በጥናቱ የተመለመሉት ተማሪዎቹ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የተጻፉ 50 ቃላት ቀርበውላቸው ቃላቱን ያነቡ እንደሆነ ተጠይቀዋል። በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በአፋርኛ፣ በሶማሊኛ፣ በሀዲይኛ፣ በወላይትኛ፣ በሲዳምኛ እና ቤንሻንጉል ውስጥ በሚነገረው በርታ ቋንቋ የሚማሩ ተማሪዎች በዚህ ጥናት ተሳትፈዋል። ከጥናቱ የሚጠበቀውም ፊደልን የመለየት፣ ቃላት ወይም አጭር አንቀጽ የማንበብ እና የማድመጥ እና የመረዳት ችሎታቸውን መመዘን ነው። 📕 የጥናቱ ውጤት ምን ያመለክታል? - በጥናቱ ከተሳተፉት የ2ኛ እና 3ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል 56 በመቶ የሚሆኑት አንድም ቃል ማንበብ አይችሉም። - በጥናቱ ከተሳተፉ የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ቢያንስ አንድ ቃል ማንበብ የሚችሉት 37 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው። የተቀሩት 63 በመቶዎቹ አንድም ቃል ማንብብ የማይችሉ (Zero renderers) ናቸው። - የ3ኛ ክፍል ተማሪዎች ደግሞ 55 በመቶ የሚሆኑት ከየትኛውም ፊደል ጋር እንደማይተዋወቁ ጥናቱ ጠቁሟል። - ጥናቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች እንዲስፋፉ፤ በተለምዶ ታዳጊ የሚባሉ ክልሎች ላይ ትኩረት እንዲደረግ፤ 🌍 በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመሳሳይ ጥናቶች ምን ያመለክታሉ? - በዓለም አቀፍ ደረጃ አንድ የሁለተኛ ክፍል ተማሪ በደቂቃ ቢያንስ 60፤ የ3ኛ ክፍል ተማሪ ደግሞ 90 ቃላትን እንዲያነብ ይጠበቃል። - ከላይ በተነሳው ነጥብ መሠረት በኢትዮጵያ ቋንቋዎች የሚማሩት የ2ኛ ክፍል ተማሪዎች ቢያንስ በደቂቃ 43 እንዲሁም የ3ኛ ክፍል ተማሪዎች 53 ቃላትን እንዲያነቡ ይጠበቅ ነበር። #FYI: በባለፈው ዓመት በተደረገ ጥናት የ2ኛ እና የ3ኛ ክፍል ተማሪች በድምሩ 68 በመቶ የሚሆኑት አንድም ቃል ለማንብብ መቸገራቸው ተገልጾ ነበር። መረጃው የተወሰደው ከቢቢሲ አማርኛ ነው።
Show all...
😢 27🤔 7 2😨 2😡 2🕊 1
በወር 15,000 ብር 💸💵💰💰 ማግኘት ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ 🚴‍♀️ ብስክሌት 🏍 ሞተር 🛵 E-bike ካልዎት ምን ይጠብቃሉ ከ ቢዩ ዴሊቨሪይ ጋር መስራት ይችላሉ። 💰ቢዩ ዴሊቨሪይ የምግብ አድራሽ ድርጅት ሲሆን ብስክሌት ፥ ሞተረ እና E-bike ካለው ግለሰብ ጋር አብሮ መስራት ይፈልጋል። የስራ አድራሻ ፥ አዲስ አበባ ለመመዝገብ:- ከታች ባለው ( Telegram Bot ) በመጠቀም የቀረባልችሁን ጥያቄ በመሙላት ✴️https://t.me/DriversRegistration_bot ወይም ☎️ 9533 ላይ በመደወል መመዝገብ ይችላሉ።
Show all...
4
የመስተንግዶ ባለሙያዎች የአለባበስ ኮድ መመሪያ እንዲፀድቅ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት መላኩ ተነገረ በሆቴሎች የሚሠሩ ሴት የመስተንግዶ ባለሙያዎች ከሀገሪቱ ባሕል ውጪ የሆነውን አለባበሳቸውን ለማስተካከል የሚያስችል የአለባበስ ኮድ መመሪያ ዝግጅቱ ተጠናቅቆ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት መላኩ የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ። አሁን ላይ የመስተንግዶ ባለሙያዎች በተለይም ሴቶች በአንዳንድ ሆቴሎች አማካኝነት ሥነ-ሥርዓቱን ያልጠበቀ አለባበስ እንዲለብሱ ይገደዳሉ የተባለ ሲሆን መመሪያው ፀድቆ ሥራ ላይ ሲውል በሆቴሎች የሚሠሩ የመስተንግዶ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ ዓለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአለባበስ ኮድ እንዲከተሉ ይደረጋል ተብሏል። መመሪያው በከተማዋ ካቢኔ በቅርቡ ፀድቆ ተግባራዊ እንደሚደረግ ሲገለፅ ሕጉ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣትም ጭምር ያለው በመሆኑ መመሪያውን በሚተላለፉ ላይ ቅጣት እንደሚጣል የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሣው (ዶ/ር) መግለፃቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
Show all...
👏 190 21🤔 7🕊 1
የመንግስትን እና የሀይማኖት ተቋማትን ግንኙነት በግልጽ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ መንግሥትና ሃይማኖት አንዱ በአንዳቸው ተግባርና እንቅስቃሴ ውስጥ ጣልቃ አይገቡም የሚለውን ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ መሠረት በማድረግ፣ መንግሥት ከሃይማኖት ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት በግልጽ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱ ተገለጸ፡፡ በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ያለው ድንጋጌ ሃይማኖትና መንግሥት አይደራረሱም ማለት እንዳልሆነ ሲገለጽ በጋራ የሚሠሩባቸው ጉዳዮች መኖራቸውንና ሆኖም በሕገ መንግሥቱ ያለው ድንጋጌ ጥቅል መርሆዎችን የያዘ በመሆኑ፣ ይህን ለማብራራት ሕግ በማስፈለጉ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱን ተጠቁሟል፡፡ በዚህም ባለድርሻ አካላት የተሳተፉባቸው ሦስት ጥናቶች ተካሂደው ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ከተወሰኑ ቤተ እምነቶች ጋር ውይይት የተጀመረ መሆኑን በሰላም ሚኒስቴር የሃይማኖት ጉዳዮች ዴስክ ተጠባባቂ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሀለፎም ዓባይነህ፣ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
Show all...
👏 41🤔 7😡 6 4🕊 4😨 2
የኤሌክትሪክ ኃይልን ባሉበት በመሆን መሙላት የሚያስችለው ቴክኖሎጂ በዚህ ዓመት ይጠናቀቃል ተባለ ከ900 ሺህ በላይ የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ሙሉ በሙሉ በካርድ ብቻ ባሉበት ሆነዉ የኤሌትሪክ ኃይል መሙላት የሚያችላቸዉ ቴክኖሎጂ በተያዘው ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ። ቴክኖሎጂው ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ሙሉ በሙሉ በኦላይን ወይም የካርድ ቁጥርን ከዲጅታል የክፍያ አማራጮች በመጠቀምና ግዢ በመፈፀም ወደ አገልግሎት መስጪያ ማዕከሉ መሄድ ሳይጠበቅባቸዉ ኃይል መሙላት የሚያስችላቸው መሆኑን የዘገበው ካፒታል ነው።
Show all...
👏 109 20🤔 3🕊 2😨 1
ኬንያ ከኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ የገዛችው የኤሌክትሪክ ሀይል ከባለፈው አመት በ41 በመቶ ማደጉ ተገለፀ ኬንያ ከፈረንጆቹ አዲስ አመት 2024 ጀምሮ ባሉት 3 ወራት ከኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ የገዛችው የኤሌክትሪክ ሀይል ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ41 በመቶ ማደጉን ተገለፀ። ኬንያ በተጠቀሰው ጊዜ ከኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ 408.78 Gigawatt-hour (GWh) የገዛች ሲሆን ይህም ባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገዛው የ 288.3 GWh የኤሌክትሪክ ሀይል ግዢ በ41.7 የበለጠ መሆኑ ተጠቁሟል። ለሀይል ግዢው ኬንያ ወደ 4.23 ቢሊየን የኬንያ ሽልንግ ያወጣች ሲሆን የሃይል አቅርቦቱ ርካሽ እንደሆነና ሀገሪቱ ጥገኛ የሆነችበትን የሙቀት ሀይል ማመንጫ ወጪን እየቀነስ መሆኑን ቢዝነስ ዴይሊ አስነብቧል።
Show all...
👏 13😡 3🤔 1🕊 1
#SamiTech አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!! @samcomptech በአገልግሎት አሰጣጣችንና በዕቃዎቻችን ጥራት ላይ ደንበኞቻችን ምስክሮች ናቸው። ዛሬም ብዛት እንዲሁም ጥራት ሳንቀንስ እያስተናገድን እንገኛለ! ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች፣ ወ.ዘ.ተ. አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ! የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን። የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ። @sww2844 0928442662 0940141114 https://t.me/samcomptech
Show all...
ታላቅ ቅናሽ 📣📣📣📣📣 💵 ድርጅታችን ድሪም ቢዉልደርስ በካሬ 90,000 ሲሸጥ የነበረውን ውደ 79,900 ብር ቅናሽ  አድርጓል። 🕧በ10% ቅድመ ክፍያ፣ በ9 ዙር፣ በ2 አመት ከ6 ወር ከፍለዉ የሚጨርሱት። 📍 በ CMC የተሟላ የመኖርያ መንደር ከ ለሚ ኩራ ፓርክ ፊትለፊት ⛰️በ ተንጣለለ 23,000 ካሬ ላይ ያረፉ አፓርትመንቶች፣ ከተሟላ መገልገያዎች ጋር 🛏️ባለ 1 መኝታ  79.92ካሬ  91.56ካሬ  🛏️ባለ 2 መኝታ 125.4ካሬ   127.44ካሬ  🛏️ባለ 3 መኝታ  169.92ካሬ ☎️ ለበለጠ መረጃ ይደዉሉልን 0974388888
Show all...