cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

TIKVAH-MAGAZINE

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524

Ko'proq ko'rsatish
Advertising posts
196 204Obunachilar
-2524 soatlar
-1187 kunlar
+1 36130 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Обуначиларнинг ўсиш даражаси

Ma'lumot yuklanmoqda...

በጎፋ ዞን ቡልቂ ከተማ የ16 አመት ታዳጊ የደፈሩ 2 ግለሰቦችና ታዳጊዋ እንድትደፈር ያደረገች ሴት በፅኑ እስራት ተቀጡ በጎፋ ዞን በቡልቂ ከተማ አስተዳደር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሱ 2 ግለሰቦችና ታዳጊዋ እንድትደፈር በማመቻቸት በአባሪነት የተከሰሰች አንዲት ሴት በጽኑ እሥራት መቀጣታቸውን የከተማው ኮሚኒኬሽን አሳውቋል። 1ኛ ተከሣሽ የሆነው አቶ በቃኃኝ ባቤና እና 2ኛ ተከሣሽ አቶ አበራ ሚኖታ የተባሉት ግለሰቦች የ16 ዓመቷን ታዳጊ በመድፈር ክስ ሲቀርብባቸው 3ኛ ተከሣሽ የሆነችው ወ/ሮ ብርቱኳን ከበደ ደግሞ በራሷ ምግብ ቤት በዕቃ አጣቢነት ቀጥራ የምታሠራትን ይህቺን ታዳጊ ሰራተኛ ያለፍቃዷ 1ኛ ተከሣሽ እንዲደፍራት በማመቻቸት መከሰሷ ተገልጿል። የከተማው ፖሊስ የተፈፀመውን ወንጀል መነሻ በማድረግ ምርመራ አድርጎ ያጠናቀቀውን የምርመራ መዝገብ ለከተማው ዓቃቤ ሕግ አቅርቦ ዐቃቤ ሕግም የምርመራ መዝገቡን ከመረመረ በኋላ ፍርድ ቤቱ 1ኛ እና 2ኛ ተከሣሾች ተበዳይን ያለፍላጎቷ አስገድደው ስለመድፈራቸው እና 3ኛ ተከሣሽም ተበዳይ በ1ኛ ተከሣሽ ያለፍላጎቷ እንድትደፈር ምቹ ሁኔታ መፍጠሯን በማስረጃ አረጋግጧል። በዚህም የቡልቂ ከተማ አስተዳደር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተከሣሾቹን ማቅለያ እና የዐቃቤ ሕግን ማክበጃ ሀሳቦችን ከመረመረ በኋላ #1ኛ ተከሣሽ አቶ በቃኻኝ ባቤና በ9 ዓመት ጽኑ እሥራት፤ #2ኛ ተከሣሽ አቶ አበራ ምኖታ በ7 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት፤ #3ኛ ተከሣሽ የሆነችው ወ/ሮ ብርቱኳን ከበደ በ6 ዓመት ጽኑ እሥራት እንድትቀጣ ወስኗል። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
😡 220👏 51 15😢 9😨 9
" በቀጣይ የበልግ ዝናብ ወቅት በሶማሌ ክልል ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች እንዲሁም በሌሎች ክልሎች በመቶ ሺ የሚገመቱ ሰዎች በጎርፍ ሊጠቁ ይችላሉ " OCHA በኢትዮጵያ በሶማሌ፣ ደቡብ፣ ኦሮሚያ፣ አፋርን ጨምሮ ሌሎችም ክልሎች እስከ ግንቦት ባለው የበልግ የዝናብ ወቅት ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሰዎች በጎርፍ ሊጠቁ እና ሊፈናቀሉ እደሚችሉ የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። በሪፖርቱ መሰረት፦ - በ #ሶማሌክልል፡- በአፍዴር፣ ሊባን፣ ቆራሄ፣ ኤረር፣ ዳዋ፣ ጃራራ፣ ኖጎብ እና ሸበሌ ዞኖች ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በጎርፍ በጎርፍ ሊጠቁ ይችላሉ ተብሎ የተገመተ ሲሆን ወደ 773,000 የሚጠጉ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ይጠበቃል። - በ #ደቡብ፦ 145,000 የሚጠጉ ሰዎች በጎርፍ ሊጠቁ የሚችሉ ሲሆኑ 64,000 ሰዎች ቀደም ሲል በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በመካከለኛው ኢትዮጵያ ክልል፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በሲዳማ ክልሎች ተፈናቅለዋል። - በ #ኦሮሚያክልል፦ 421,000 የሚገመቱ ሰዎች በጎርፍ ይጠቃሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን በቦረና፣ ጉጂ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ ሀረርጌ እና ምስራቅ ሀረርጌ ወደ 104,000 የሚጠጉ ሰዎች ተፈናቅለዋል። በ #አፋርክልል፦ 83,000 የሚጠጉ ሰዎች ለጎርፍ አደጋ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ሲሆን 61,000 ሰዎች በተለያዩ ዞኖች ይፈናቀላሉ ተብሎ ይገመታል። በ #አማራክልል ፦ ከሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ እና ከኦሮሞ ልዩ ዞን የተፈናቀሉ 3,000 ግለሰቦችን ጨምሮ ወደ 45,000 የሚጠጉ ሰዎች የጎርፍ ተጠቂ ይሆናሉ ተብሎም ተጠቁሟል። በ #ትግራይክልል፦ 4,000 የሚገመቱ ሰዎች የጎርፍ ተጠቂ ይሆናሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን 1,000 ሰዎች በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች ሊፈናቀሉ  ይችላሉ። የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከሰብአዊ የእርዳታ ድርጅቶች ጋር በመሆን ከመጋቢት እስከ ግንቦት የጎርፍ አደጋን ለመከላከል በአፋር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ ሶማሌ እና የደቡብ ክልሎች የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን በመለየት የቅድመ ዝግጅት ስራ የሰራ ሲሆን የገንዘብ እጥረት ግን የእርዳታ አቅርቦቱን እየገደበ መሆኑ ተገልጿል። ፎቶ፦ ፋይል @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
😢 25 5🕊 3😨 2🤔 1
ደስ ይበላችሁ! ካሉበት ሆነው ለሚወዱት ቤተሰቦ/ወዳጆ ለትንሳዔ እንዲሁም ለዳግመ ትንሳዔ በዓላት ሙሉ #ሥጦታ ከሙሉ #ደስታ ጋር ይላኩ! ድርጅታችን በ #Platinum , #Golden, #Silver አማራጭ #የበግ ሙክትን ጨምሮ በዓል በዓል የሚሉ ሥጦታዎችን ለሚወዱት ሰው #ባለበት #በተመጣጣኝ ዋጋ ይላኩ። እንደ እናንተው ሆነን እናደርሳለን! ይደውሉ - 0911359234 (WhatsApp NO.) or 0954882764 ሙሉ ፖኬጁን ይመልከቱ 👉 t.me/bluebellgiftstore 😮 #ለቤተሰቦቻችን_ብቻ: ባለፈው ዓመት ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ስጦታ የላኩ እንዲህ ተደስተዋል 👉https://t.me/bluebellgiftstore/627
Hammasini ko'rsatish...
👏 2
ሳፋሪኮም በ3 ዓመታት ውስጥ የኔትዎርክ ማማዎችን በሦስት እጥፍ ለማሳደግ እቅድ እንዳለው ገለፀ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 3 አመታት ከ1.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት በማድረግ በመላ ሀገሪቱ የኔትወርክ ተደራሽነቱን ለማስፋት የሚያንቀሳቅሳቸውን የቴሌኮም ማማዎች በሶስት እጥፍ ለማሳደግ እቅድ እንዳለው ገለፀ። ኩባንያው በፀጥታ ችግር ምክንያት በሚፈለገው ልክ ተደራሽቱን ማስፋት እንዳልቻለ ሲገልፅ በአሁኑ ወቅት 2,500 የኔትዎርክ ማማዎችን የሚያንቀሳቅስ ሲሆን 1,000 ያህሉን ከኢትዮ ቴሌኮም የተከራየው መሆኑን የኩባንያው  ዋና ስራ አስፈፃሚ ዊም ቫንሄሌፑቴ ለሪፖርተር ተናግረዋል። ሳፋሪኮም በአዲስ አበባ እና በሌሎች 26 የከተማ አካባቢዎች ተደራሽ መሆኑን የገለፁት ሀላፊው ነገር ግን ኩባንያው በመላው ሀገሪቱ አገልግሎቱን ለማዳረስ እስከ 7ሺ የኔትዎርክ ማማ የሚያስፈልገው መሆኑን አንስተዋል። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
👏 54 8😨 1
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊና ቁሳዊ ሀብቶች ላይ ያተኰረ ኢንሳይክሎፔዲያ ሊዘጋጅ ነው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊና ቁሳዊ ሀብቶች እንዲሁም አስተምህሮዎች ላይ ያተኰረ መዝገበ አእምሮ (ኢንሳይክሎፔዲያ) በማኅበረ ቅዱሳን አማካይነት ሊዘጋጅ መሆኑ ተገልጿል። የመዝገበ አእምሮ (ኢንሳይክሎፒዲያ) ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ለማዘጋጀት እንዲቻል በተለያዩ የሙያ መስኮች የተሰማሩ ምሁራን ዕውቀታቸውንና ልምዳቸውን ማካፈል የሚችሉበት መድረክ በዛሬው እለት በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል። የሚዘጋጀው መዝገበ አእምሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ፣ ጥንታዊና ሐዋርያዊ አስተምህሮ ፣ ዶግማ ፣ ቀኖና እና ትውፊት እንዲሁም የጳጳሳትን ፣ የሊቃውንትን ፣ የትልልቅ ገዳማትንና አድባራትን ታሪክ ወዘተ. የሚያካትት ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት በዘገባው አመልክቷል። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
242👏 31🤔 8😡 5
#Update: በኬንያ በጣለው ከባድ ዝናብ የሟቾች ቁጥር 70 መድረሱ ተነገረ በኬንያ በጣለው ከባድ ዝናብ እና የጎርፍ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ የኬንያውያን ዜጎች ቁጥር  70 መድረሱን የኬንያ የመንግሥት ቃል አቀባይ አይዛክ ሙዋራ በትላንትናው እለት በናይሮቢ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። የጎርፉ አደጋ ከኬንያ 47 ክልሎች 23ቱን ያጠቃ ሲሆን ሰብአዊ ጉዳቱን እንዳባባሰው ተገልጿል። የሀገሪቱ የሚቲዎሮሎጂ ዲፓርትመንት በሚቀጥሉት 3 ቀናትም በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች መካከለኛ እና ከባድ ዝናብ እንደሚቀጥል ትንበያውን አስቀምጧል። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
😢 24 4🕊 2😨 1
#cloudbridge. #traininginstitute ክላውድ በሪጂ ማሰልጠኛ ተቋም ፤ለስልጠና ፍላጊዎች በሙሉ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽ እውቀት አቅም ግንባታ ነፃ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቆ እናንተን በጉጉት  ይጠብቃል:: ስልጠና ሚሰጥባችው ዘረፎች መካከል፡ 1,Web development 2,Interior design የስልጠና ቦታ ሲቲ ሞል 6ኛ ፎቅ, መገናኛ ድልድይ,wow burger ያለበት፣Megenagna siti Mall 6th, Addis Ababa, Ethiopia ለተጨማሪ መረጃ 094-228-0000 092-083-8483 ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸው ፈጥነው በአካል መተው ይመዝገቡ።          ለአንድ ቀን ሚቆይ ነፃ ስልጠና!               Register online https://cloudbridgeacademy.com/registration Telegram :https://t.me/cbmtraininginstitute
Hammasini ko'rsatish...
#SamiTech አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!! @samcomptech በአገልግሎት አሰጣጣችንና በዕቃዎቻችን ጥራት ላይ ደንበኞቻችን ምስክሮች ናቸው። ዛሬም ብዛት እንዲሁም ጥራት ሳንቀንስ እያስተናገድን እንገኛለ! ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች፣ ወ.ዘ.ተ. አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ! የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን። የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ። @sww2844 0928442662 0940141114 https://t.me/samcomptech
Hammasini ko'rsatish...
2👏 1
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን የዞን አምስት ውድድርን እንድታዘጋጅ ተመረጠች ኢትዮጵያ ከ10 ሃገራት እና ከ350 በላይ ልዑካን ቡድን የሚሳተፉበት በዓለም አቀፍ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን የሚዘጋጀው ዞን አምስት የምስራቅ አፍሪካ እጅ ኳስ ዋንጫ እንድታዘጋጅ መመረጧን የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል። የምስራቅ አፍሪካ ዞን አምስት ሃገራት ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ጂቡቲ እና ቡሩንዲ ሲሆኑ ውድድሩ ከግንቦት 03 - 11/2016 ዓ.ም ከ18 ዓመት በታች እና ከ20 ዓመት በታች የብሄራዊ ቡድን የሚሳተፉበት የእጅ ኳስ ውድድር መሆኑ ተገልጿል። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
👏 43 6🤔 4😡 3😨 2
" በአዲስ አበባ ከሚገኙ 77 ሺ ስደተኛ ዜጎች 72 በመቶዎቹ ሴቶች እና ህጻናት ናቸው " ሪፖርት በአዲስ አበባ ከ28 ሀገራት የተውጣጡ 77,653 ስደተኞች የሚኖሩ መሆኑን እና ከነዚህም ውስጥ 71 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸውን የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ከስደተኞች እና ተመላሾች ጋር በመተባበር ባወጡት ሪፖርት አመልክቷል። ሪፖርቱ በመዲናዋ ከሚገኙ 92 በመቶ የሚሆኑት ስደተኞች የኤርትራ ዜጎች ሲሆኑ ቁጥራቸውም 71,588 መሆኑን ጠቅሷል። የየመን ዜጎች 2,466 (3%) ሶማሊያ 1,140 (1%) እንዲሁም ደቡብ ሱዳን 720 ስደተኞች በመዲናዋ እንደሚገኙም በሪፖርቱ ተመላክቷል። ከአጠቃላይ ስደተኞች 35,365 ወይም 46 በመቶ የሚሆኑት ስደተኞች በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፤ 22,657 ወይም 29 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በቦሌ ክፍለ ከተማ፤ እንዲሁም 8162 ወይም 11 በመቶዎቹ በየካ ክፍለ ከተማ የሚገኙ መሆናቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል። በሪፖርቱ መሰረት፦ - ለአደጋ የተጋለጡ ሴቶች 11,938 ሲሆኑ በተመሳሳይ የህፃናቱ ቁጥር 2,838 ነው። -  ከ0-17 አመት እድሜ ያላቸው ህጻናትና ታዳጊዎች 30 በመቶ ናቸው። - ከባድ የጤና እክል ያለባቸው 1,336 ሴቶች እና 2,545 ወንዶች አሉ። - አካል ጉዳተኞች 607 ወንድ፣ 2,438 ሴቶች ሆነው ተመዝግበዋል። - ነጠላ ወላጅ ቤተሰቦች ወንድና ሴት በድምሩ 3,224 መሆናቸውም ተመላክቷል። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...