cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

TIKVAH-MAGAZINE

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
196 389
المشتركون
+10124 ساعات
+687 أيام
+1 50330 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ልጆች 13 ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ ስማርት ስልኮችን ባይጠቀሙ ሲል በፈረንሳይ የተሰራ ጥናት አመለከተ። በተለያየ የእድሜ ደረጃ ላይ ያሉ ህፃናት እና ታዳጊዎች ስማርት ስልኮችን በመጠቀም የተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾችን ሲጠቀሙ አለፍ ሊልም በነዚህ የትስስር ገጾች ላይ ተሳትፎ ሲያደርጉ ይስተዋላል። የስማርት ስልክ አጠቃቀም ጥንቃቄ የሚያስፈልገው እንደሆነ ቢነገርም ሀገራችን ኢትዮጵያ ጨምሮ ስማርት ስልኮች ላይ የሚገኙት የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህፃናትና ታዳጊዎችን ለሱስ ከመዳረግ ባለፈ በልጆች ላይ ስነልቦናዊ ጉዳት እያስከተለ ስለመሆኑ ይነገራል። ጉዳዩን አስመልክቶ በፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ማክሮን ሀሳብ አመንጪነት ታዳጊ ልጆችን ከአደጋ ለመጠበቅ ኒውሮሎጂስት እና የዘርፉ ባለሙያዎች የስልክ ስክሪን አጠቃቀም መመሪያዎችን ለመንግስት እንዲጠቁሙ  በማሰብ 3 ወራትን የፈጀ ጥናት ተሰርቷል። በጥናቱም ልጆች 13 አመት እስኪሞላቸው ድረስ ስማርት ስልኮችን እንዲጠቀሙ መፈቀድ እንደሌለበትና እንደ #ቲክቶክ፣ #ኢንስታግራም እና #ስናፕቻት የመሳሰሉ ማህበራዊ ሚዲያዎችን እስከ 18 አመት ድረስ መጠቀም እንደሌለባቸው ጥናቱ አመልክቷል። ጥናቱም ከ3 አመት በታች ያሉ ህጻናት የቴሌቪዥን ስክሪኖች ጨምሮ ለስልኮች ተጋላጭ መሆን እንደሌለባቸው የጠቆመ ሲሆን አንድ ህፃን 11 ዓመት ሳይሞላው ስልክ ሊኖረው እንደማይገባና ይህ ካልሆነ ህፃናት በልጅነታቸው ስሜታቸውን ከመግለፅ እና ነገሮችን ከመረዳት አኳያ ሊያዳብሯቸው የሚገባቸውን ችሎታዎች ሊጎዳ እንደሚችል ተገልጿል። የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ማክሮን ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በጥር ወር ህፃናትን ላይ ጉዳት እየዳረገ ስለሚገኘው የስማርት ስልክ እንዲሁም የስክሪን አጠቃቀም " እገዳዎች ወይም ገደቦች " ሊኖሩ ይችላሉ ማለታቸውም ነው የተነገረው። ይህ ጥናት በኢትዮጵያ ካለው የህፃናትና ታዳጊዎች ስማርት ስልክ አጠቀም አንፃር እንዴት ይታያል?
إظهار الكل...
👏 114 18🕊 9🤔 6😨 6😡 1
"የዓለም ባንክ የአፍሪካ ሀገራትን መዋቅራዊ ችግሮች ከመደገፍ ለሴሚናር ገንዘብ ማውጣት ይቀለዋል" የዩጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የዩጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የዓለም ባንክ ድሃ የአፍሪካ ሀገራት ለዕድገታቸው እንቅፋት የሆኑ የእርሻ፣ ትራንስፖርትና መሰል መዋቅራዊ ችግሮችን እንዲፈቱ ብድር ከመስጠት ይልቅ ለሚዘጋጁት ‘ሴሚናሮች’ ብድር ቅድሚያ ይሰጣል ሲሉ ወቀሳ ሰነዘሩ። ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት በኬኔያ በተካሄደው የአለም አቀፍ ልማት ማህበር የአፍሪካ ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ነው። " አለም ባንክ ሰዎች ተቀምጠው ለሚመገቡት ሴሚናሮች  ብድር ለመስጠት ፈጣን ናቸው። ነው ነገር ግን የመስኖ እና የመሠረተ ልማት ልማትን አይደግፉም " ሲሉ ወቅሰዋል። ፕሬዝዳንቱ አፍሪካ ዘላቂ ልማት (Sustainable underdevelopment) አያስፈልጋትም አፍሪካ የምትፈልገው ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ (Socio-Economic Transformation) ነው ያሉ ሲሆን ዘላቂ ልማትን የሚባለውን ፅንሰ ሀሳብ እድገት የሌለው ሲሉ ገልጸውታል። "አንድ ሴት በዚህ ዓመት ካረገዘች በሚቀጥሉት ሦስት እና አራት ዓመታት እርጉዝ አትሆንም፥ ይህ ፈጽሞ አይፈጠርም ተፈጥሯዊው እድገት ለወራት ታረግዛለች ልጁ ያድጋል፤ ይወለዳል፤ ይጎለምሳል። የሆነ ምዕራፍ ላይ እርግዝናው (Quantitative) ወደ ልጅነት ይቀየራል (Qualitative) እነዚህን ቃላት በዶክመንታችሁ አስተካክሏቸው።" ሲሉ ገልጸዋል። ፕሬዚደንት ሙሴቬኒ አክለውም፥ አፍሪቃ የጥሬ ዕቃዎቿን ወደ ውጭ መላክ እንድታቆም የጠየቁ ሲሆን ጥሬ እቃ ላይ እሴት ሳይጨመር መላክ በአፍሪካዊያን ሀብት ሌሎችን ማበልጸግ እንደሆነ የቡና እና የማዕድን ሀብትን በምሳሌ አንስተው አስረድተዋል። "ኡጋንዳ ሀብታም ሀገር ብትሆንም አብዛኞቹ ዜጎቿ ለዕለት ጉርስ እንጂ ለኪስ የሚሆን ገንዘብ ከሚያገኙበትን ሥርዓት ( Money Economy) ውጪ ናቸው። ይህንን ለመቅረፍ ገንዘብ የሚሰጠኝ የለም ምክንያቱም ሁሉም ገንዘብ ለአቅም ማጎልበቻ (Capacity Building ) ነው። እኛ ግን በራሳችን ፈንድ እየሰራን ነው" ሲሉ ተናግረዋል። በአፍሪካ የግሉ ዘርፍ እየተደገፈ ባለመሆኑ እድገት እየተመዘገበ እንዳልሆነ የገለፁት ሙሴቬኒ የግሉ ዘርፍ እንዲበረታታ በቅድሚያ በአነስተኛ ዋጋ ማምረት መቻል ለዚህም ደግሞ  የመንገድ የኤሌክትሪክ ሀይል ያስፈልጋል ሲሉ ጠቅሰው የዓለም ባንክ ለእነዚህ ነገሮች ፈንድ ያደረገበትን ኦዲት ያድርግ ሲሉ ጠቅሰዋል። (📹 28 MB)
إظهار الكل...
👏 202 21😨 4🕊 2😡 2
እንኳን አደረሳችሁ! ካሉበት ሆነው ለሚወዱት ቤተሰቦ/ወዳጆ ለትንሳዔ እንዲሁም ለዳግመ ትንሳዔ በዓላት ሙሉ #ሥጦታ ከሙሉ #ደስታ ጋር ይላኩ! ድርጅታችን በ #Platinum , #Golden, #Silver አማራጭ #የበግ ሙክትን ጨምሮ በዓል በዓል የሚሉ ሥጦታዎችን ለሚወዱት ሰው #ባለበት #በተመጣጣኝ ዋጋ ይላኩ። እንደ እናንተው ሆነን እናደርሳለን! ይደውሉ - 0911359234 (WhatsApp NO.) or 0954882764 ሙሉ ፖኬጁን ይመልከቱ 👉 t.me/bluebellgiftstore 😮 #ለቤተሰቦቻችን_ብቻ: ባለፈው ዓመት ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ስጦታ የላኩ እንዲህ ተደስተዋል 👉https://t.me/bluebellgiftstore/627
إظهار الكل...
4
ከታላቁ ህዳሴ ግድብ በቀን እስከ 250 ኪሎ ግራም የሚደርስ ዓሳ እየተገኘ ነው ተባለ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከዚህ ቀደም ታጥቀው ይንቀሳቀሱ የነበሩና ሌሎች ወጣቶች በ2 ማኅበር ተደራጅተው በጀመሩት የዓሳ ማስገር ስራ ከህዳሴ ግድብ በቀን እስከ 250 ኪሎ ግራም የሚደርስ ዓሳ እየተገኘ መሆኑ ተገለፀ። የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሐይቅ ግድቡ ውሀ መያዝ ከጀመረ ወዲህ በተለይም ለዓሳ ምርት ምቹ መሆኑ ሲገር በ8 ወራት ውስጥ 1729 ቶን ዓሳ ምርት ከህዳሴ ግድብ መገኘቱን ዶይቼ ቨለ በዘገባው አመልክቷል። ወጣቶቹ የተደራጁበት ማህበርም 56 የሚደርሱ ወጣቶችን ያቀፈ ሲሆን በግደቡ ዳርቻ በሚሰሩት የዓሳ ማስገር ስራ በቀን ከ2 እስከ 3 ኩንታል ዓሳ እንደሚኝና በአካባቢው የዓሳ ማስገር ስራውን በማህበሰረብ አቀም ለማድረግና ለማሻሻል ዘመናዊ ጅልባዎች ያስፈልጋሉ ተብሏል።
إظهار الكل...
👏 266🤔 40 33🕊 11😡 6😢 1
#CholeraUpdate በኢትዮጵያ ባለፈው ወር ከአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ የኮሌራ ታማሚዎች ቁጥር እንደተመዘገበ ተነገረ በአፍሪካ ባለፈው መጋቢት ወር በኮሌራ በሽታ ከተያዙ 14,441 አዲስ የኮሌራ ታማሚዎች መሃከል ከአህጉሪቱ ከፍተኛ ታማሚዎች የተመዘገቡባት ኢትዮጵያ መሆኗን የአለም ጤና ድርጅት ሪፖርት አመልክቷል። በተጠቀሰው ወር በኢትዮጵያ 4009 ሰዎች በኮሌራ መያዛቸው ተነግሯል። በኮሌራ ከተያዙት ሰዎች ውስጥም 24 ሰዎች መሞታቸው ተጠቁሟል። በኢትዮጵያ ባለፉት 3 ወራት 9,429 ሰዎች በኮሌራ ተይዘው 111 ሰዎች መሞታቸውንም ሪፖርቱ አመልክቷል። በአፍሪካ ከጃንዋሪ 1 ቀን 2023 እስከ ማርች 31 ቀን 2024 በጠቅላላው በ18 ሀገራት 271,119 ሰዎች በኮሌራ በሽታ ሲያዙ በተጠቀሰው ጊዜ በኢትዮጵያ 39,892 ሰዎች በበሽታው ተይዘው 524 ሰዎች መሞታቸውም ነው የተገለፀው።
إظهار الكل...
😢 23 5🤔 1
#እንድታውቁት ነገ ረቡዕ ሚያዚያ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በአለም አቀፍ ደረጃ የሠራተኞች ቀን የሚከበርበት ቢሆንም፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዋናው መስሪያ ቤት እስከ አገልግሎት መስጫ ማዕከሎቹ ድረስ በሚገኙ ሁሉም ቢሮዎች ሁሉንም አገልግሎቶቹን እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።
إظهار الكل...
👏 81🤔 14 10😡 8😨 4
በ2023 አምስት ምርጥ እንግሊዝኛ ተናጋሪ የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው? "ኢዱኬሽን ፈርስት" የተባለ ዓለማቀፍ የትምህርት ተቋም እድሜአቸው ከ 18 - 20 የሆኑ 2.1 ሚሊዮን ወጣቶችን ከ113 ሀገራት የእንጊሊዘኛ ቋንቋ ችሎታቸውን በመገምገም የሀገራትን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪ ብቃት ደረጃ አውጥቷል። ተቋሙ የቋንቋውን ተናጋሪዎች ብቃት በጣም የላቀ፣ ከፍተኛ፣ መካከለኛ፣ ዝቅተኛ እና በጣም ዝቅተኛ በሚሉ አምስት የብቃት ደረጃዎች በመክፈል ነው ሪፖርቱን ይፋ ያደረገው። በሪፖርቱ መሰረትም ከ1ኛ እስከ 5ኛ የተቀመጡ የአፍሪካ ሀገራት በቅደም ተከተል፦ 🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ 🇰🇪 ኬንያ 🇳🇬 ናይጄሪያ 🇬🇭 ጋና 🇺🇬 ኡዳንዳ መሆን ችለዋል። ከአፍሪካ በቋንቋ ተናጋሪነት ብቃት የመጀመሪያ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ደቡብ አፍሪካ  "#በጣም_የላቀ" በተባለው ከፍተኛ የእንግሊዘኛ ብቃት ያላችው ሀገራት ምድብ ውስጥ ተካትታለች። 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ኬንያ እንዲሁም 3ኛዋ ናይጄሪያ "#ከፍተኛ" በተባለው እንዲሁም  ዩጋንዳ እና ጋና "#መካከለኛ" በተባለው የቋንቋ ተናጋሪነት ምድብ ተመድበዋል። ሀገራችን #ኢትዮጵያ🇪🇹 #ዝቅተኛ የእንጊሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪነት ምድብ ውስጥ ከታንዛኒያ፣ ሞሮኮ፣ አልጄሪያ፣ ማዳጋስካር፣ ማላዊ፣ ግብፅ ጋር መመደቧ በሪፖርቱ ተመላክቷል። ኔዘርላንድስ፣ ሲንጋፖር፣ ኦስትሪያ፣ ዴንማርክ እና ኖርዌይ ከአለም ከ1 እስከ 5 ያለውን የኢንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪነት ብቃት ደረጃ መያዝ ችለዋል።
إظهار الكل...
👏 68🤔 19 4😢 3🕊 3😡 3
እንኳን አደረሳችሁ! ካሉበት ሆነው ለሚወዱት ቤተሰቦ/ወዳጆ ለትንሳዔ እንዲሁም ለዳግመ ትንሳዔ በዓላት ሙሉ #ሥጦታ ከሙሉ #ደስታ ጋር ይላኩ! ድርጅታችን በ #Platinum , #Golden, #Silver አማራጭ #የበግ ሙክትን ጨምሮ በዓል በዓል የሚሉ ሥጦታዎችን ለሚወዱት ሰው #ባለበት #በተመጣጣኝ ዋጋ ይላኩ። እንደ እናንተው ሆነን እናደርሳለን! ይደውሉ - 0911359234 (WhatsApp NO.) or 0954882764 ሙሉ ፖኬጁን ይመልከቱ 👉 t.me/bluebellgiftstore 😮 #ለቤተሰቦቻችን_ብቻ: ባለፈው ዓመት ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ስጦታ የላኩ እንዲህ ተደስተዋል 👉https://t.me/bluebellgiftstore/627
إظهار الكل...
5
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በቤሩት አል ሃሪሪ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ምን ገጠመው? የሊባኖስ አቬዬሽን ባለስልጣን “ቴል አቪቭ” የተሰኘ መለያ ያለበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ቤይሩት ሲደርስ ተቃውሞ ማሰማቱን የሀገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የሀገሪቱ ሲቪል አቬዬሽን ባለስልጣን ቤይሩት ያረፈው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 787-9 አውሮፕላን ወደ አዲስ አበባ ከመመለሱ በፊት ምልክቱን እንዲሸፍን አድርጓል። በተጨማሪም፥ አውሮፕላኖች በቤይሩት ከመድረሳቸው በፊት ሊባኖስ "ጠላቴ ናት" ከምትላት እስራኤል ጋር የተያያዘ ምንም አርማ እንደሌለ ማረጋገጥ እንዳለበት አሳስቧል። ሊባኖስ ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ኖሯት የማያውቅ ሲሆን እንደ ጠላት ሀገር የሚተያዩ ናቸው። ሁለቱ ሀገራት በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመሀከለኛው ምስራቅ ባለው ግጭትና የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን የሆነው 'ሒዝቦላ' ጋር በሚያደርጉት ውጊያ ቀጠናው እና ሁለቱ ሀገራት የተካረረ ውጥረት ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል። አየር መንገዱ አዳዲስ አውሮፕላን ሲያስገባ አውሮፕላኖቹ የመጀመሪያ በረራ ያደረጉበት የመጀመሪያው ከተማ ስም በውጨኛው ክፍል ላይ ይጻፋል። ይህም የአየር መንገዱ ልምድ ነው። በዚህ መሰረትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ4 አመት በፊት ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኑን ወደ መስመር ሲያስገባ ቅድሚያ የበረረበትን የከተማ ስያሜ ' ቴል አቪቭ ' የሚል የሚል ስያሜ ሰጥቶት ነበር።
إظهار الكل...
👏 152🤔 43 34😡 30🕊 8😨 3😢 1
መንግሥት የሪል ስቴት ንብረት ታክስና የተሽከርካሪ ዝውውር ታክስ ለመጣል ማቀዱ ተነገረ መንግሥት የአገሪቱን የታክስ ገቢ ለማሳደግ የሪል ስቴት ንብረት ታክስና የሞተር ተሽከርካሪ ዝውውር ታክስ ለመጣል ማቀዱን ሪፖርተር ዘግቧል። ሁለቱን አዲስ ዓይነት ታክሶች ከዘንድሮ ጀምሮ እስከሚቀጥለው ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ለመጣል መታቀዱም ተጠቁሟል። በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች በሙሉ እንደየ ሞተር አቅማቸው የመንገድ ፈንድ ክፍያ በየዓመቱ ይከፍላሉ። አሁን የታቀደው የተሽከርካሪ ዝውውር ታክስ ከመንገድ ፈንድ ክፍያ በተጨማሪነት የሚጣል ሲሆን ይህ ታክስ በአገሪቱ ውስጥ ባሉ ሁሉም ተሽከርካሪዎች ላይ የሚተገበር እንደሆነም ተገልጿል። ሌላው የሪል ስቴት ንብረት ታክስ በ2025 ተግባራዊ እንደሚደረግ ሲጠቆም ታክሱ የሚጣለው፣ በአልሚዎች ላይ ይሁን በሪል ስቴት አልሚዎች፣ ወይም የተገነቡ ቤቶችን በሚገዙ ነዋሪዎች በግልፅ አልታወቀም። ነገር ግን የሪል ስቴት ታክስ በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች እንዲሰበሰብ ታቅዶ በመረቀቅ ላይ ከሚገኘው የንብረት ታክስ በተጨማሪ፣ የታቀደ አዲስ የታክስ ዓይነት መሆኑን ተነግሯል። @TikvahethMagazine
إظهار الكل...