cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

YeneTube

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Show more
Advertising posts
130 425Subscribers
+624 hours
+457 days
+1 68730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"ታማሚው ስለማይድን የተሰበሰበውን ብር ሰይጣን አሳስቶን አጠፋነው. . ." ይህንን ያለው 9,000 ሰው ተሰብስቦ በሚመለከተው የቲክቶክ ሽምግልና ላይ ነው። ከሞተር ወድቆ ከወገብ በታች ለማይንቀሳቀሰው አለሙ ቢጫ የተባለ ታማሚ ግለሰብ የተለያዩ ታዋቂ ቲክቶከሮች የእርዳታ ገንዘብ ቢሰበስቡም ለታማሚው ብር ሳይደርስ ቀርቶ ታማሚው ባቀረበው ተማፅኖ ብሩን የሰበሰቡት ቲክቶከሮች የተወሰነ ብር ቢመልሱም ዋነኛው ወጣት ግን 350,000 ሺህ ብር አካባቢ ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆነም። ለዚህም የቀረበው ምክንያት " ታማሚው ስለማይድን ብሩን አጥፍቼዋለሁ . . . ቲክቶክ አካውንቴን ሸጬ እከፍላለሁ" ብሏል። Via: ስንታየሁ ኃይሉ @Yenetube @Fikerassefa
Show all...
😭 65👍 13👀 7 3😁 3
Show all...
YeneTube

Boost this channel to help it unlock additional features.

👍 1
የቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች ይታያሉ ያሏቸው፤ “የማያቋርጡ እና ኃይለኛ ውጥረቶች” እንደሚያሳስቧቸው ገለጹ። በኢንዱስትሪ የበለጸጉት ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ይፈጸማሉ የሚባሉ “የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እና በደሎች ሪፖርቶች”፣ “ብርቱ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ” እና “የምግብ ዋስትና እጦት መስፋፋት” እንዳሰጋቸውም አስታውቀዋል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በኢትዮጵያ ጉዳይ ስጋታቸውን ያንጸባረቁት፤ በጣልያኗ ካፕሪ ደሴት ያካሄዱትን ስብሰባ ሲያጠናቅቁ ዛሬ አርብ ምሽት ባወጡት መግለጫ ነው። ሚኒስትሮቹ በዚሁ መግለጫቸው፤ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል በተፈረመው ግጭት የማቆም ስምምነት አተገባበር ረገድ የተወሰዱ እርምጃዎችን በበጎ እንደሚቀበሉ ገልጸዋል። በሰብዓዊ መብቶች እና በሲቪል ሰዎች ጥበቃ፣ ውጥረቶችን ለመፍታት በሚደረግ ፖለቲካዊ ውይይት፣ በዕርቅ፣ በብሔራዊ ውይይት፣ የሽግግር ፍትህ እና በግጭት ወቅት ወንጀል የፈጸሙ ተጠያቂ ለማድረግ፤ ተጨማሪ እና ዘላቂ እርምጃዎች ተግባራዊ እንዲደረጉ አበረታተዋል። በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በመካሄድ ላይ በሚገኙ ግጭቶች የሚሳተፉ ወገኖች፤ በንግግር ሰላም ለማውረድ ተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንዲኖራቸውም ጥሪ አቅርበዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ) @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
👍 22👎 10 3😁 1
በአዲስ አበባ 32 ሺህ አባወራዎች ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ናቸው ተባለ፡፡ የክረምት ወር መግባቱን ተከትሎ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች 32 ሺሕ አባወራዎችና ለጎርፍ አደጋ የተጋለጡ መሆናቸውን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።በአሁኑ ሰዓት በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች በጥናት ተለይተው ታውቀዋልም ብሏል፡፡ የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ስጋት ቅነሳ ምክትል ኮሚሽነር ይክፈለው ወ/መስቀል እንደተናገሩት አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ፣ ልደታ፣ ቂርቆስና አራዳ ክፍለ ከተሞች በተደጋጋሚ ጎርፍ የሚያጠቃቸውና በከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች ናቸው ብለዋል፡፡ በመዲናዋ በወንዝ ዳር የሚኖሩ በርካታ ዜጎች መኖራቸውን የገለጹት ምክትል ኮሚሽነር ይክፈለው ዜጎችን ከአካባቢው በማንሳት ወደ ሌሎች አካባቢዎች ማዛወር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡መሥሪያ ቤታቸው ሰባት ከሚሆኑ ባለድርሻ መስራቤቶች አካላት ጋር በመሆን ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከል አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ በማድረግ ላይ መሆኑንም ተናግረዋል። ኮሚሽነሩ ለጎርፍ አደጋ መባባስ ምክንያት ናቸው ያሏቸውን ችግሮች ሲገልጹ፣ በተለያዩ ምክንያቶች ተቆፋፍረው ክፍት የተተዉ ጉድጓዶች፣ የውሃ መውረጃ ቦዮች፣ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችና ወንዞች ላይ ተረፈ ምርቶችንና ቆሻሻዎችን መጣል በዋነኝነት ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡እነዚህ ችግሮች በሁሉም አካባቢ በመለየት አሁን ላይ የስራ ክፍፍል ተደርጎ ቅድመ ዝግጅት ስራ እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ [Ethio FM] @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
👍 27 5😭 3🔥 1
በቦኮሃራም የታገተችው ናይጄሪያዊት ተማሪ ከ10 ዓመት በኋላ ሦስት ልጆችን ወልዳ ነጻ ወጣች! ከአስር ዓመት በፊት በቦኮሃራም ታጣቂዎች ታግተው ከነበሩ ሴቶች መካከል አንዷ የሦስት ልጆች እናት ሆና በናይጄሪያ መንግሥት ወታደሮች ነጻ ወጣች።በአውሮፓውያኑ ሚያዝያ 2014 ቦርኖ ከምትባለው ከተማ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች 276 ተማሪ ሴቶችን ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤታቸው አፍነው መውሰዳቸው ይታወሳል። እነዚህ የቺቦክ ትምህርት ቤት ሴት ልጆች መታገት መላው ዓለምን አስደንግጦ በወቅቱ የአሜሪካ ቀዳማዊ እመቤት የነበሩትን ሚሼል ኦባማን ጨምሮ ዓለም አቀፍ የማስለቀቅ ዘመቻ እንዲጀመር ምክንያት ሆኖ ነበር። ታፍነው ተወስደው ከነበሩት 280 ከሚጠጉት ልጃገረዶች መካከል አስካሁን ድረስ 100 የሚሆኑት በታጣቂዎቹ ቁጥጥር ስር ናቸው ወይም የደረሱበት አልታወቀም።ትናንት ሐሙስ ደግሞ የናይጄሪያ ሠራዊት ከአስር ዓመት በፊት ከታፈኑት ተማሪዎች መካከል አንዷን ከሦስት ልጆቿ ጋር ከታጣቂዎቹ ነጻ ማውታቱን አስታውቋል። ታጋቿ ሦስት ልጆቿ በተጨማሪም የአምስት ወራት ነፍሰ ጡር መሆኗን ሠራዊቱ ገልጿ።በቦኮ ሃራም ቡድን ታፍነው ከተወሰዱ ሴት ተማሪዎች መካከል አስካሁን ከ180 በላይ የሚሆኑት በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ውስጥ ከምትገኘው ቦርኖ ግዛት የቡድኑ መደበቂያ ሳምቢሳ ጫካ በፀጥታ ኃይሎች ነጻ ወጥተዋል ወይም ከቡድኑ አምልጠዋል።አስካሁን ከቡድኑ ነጻ ከወጡ ልጃገረዶች መካከል አንዳንዶቹ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ ማርገዛቸው ወይም ልጅ መውለዳቸው ተዘግቧል። የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች ጠልፈው የሚወስዷቸውን ተማሪዎች በወሲብ ባርነት ስር ያቆይዋቸዋል የሚሉ ዘገባዎች በተደጋጋሚ ሲወጡ መቆየታቸው ይታዋል።ወደ ቤታቸው ከተመለሱት መካከልም የተወሰኑት የናይጄሪያ ባለሥልጣናት የሚያስፈልጋቸውን እንክብካቤ እና ድጋፍ እንዳላደረጉላቸው በመግለጽ መንግሥትን ይታቻሉ።በናይጄሪያ ውስጥ አሁንም የጅምላ አፈና ተማሪዎችን እና ወላጆችን የሚያሳስብ ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
👍 35😭 27 4😁 4👀 3
👍 1
🎉አስደሳች ዜና ለወላጆች🎉          📚Ace Tutors📚     በማንኛውም የት/ት ደረጃ ለሚገኙ ልጆችዎ ብቁ የሆኑ አስጠኚዎች አዘጋጅተናል - ለብሄራዊ እና ለት/ቤት ፈተና እናዘጋጃለን - ብቁ በሆኑ ወንድ እና ሴት አስጠኚዎች - ለሁሉም የት/ት ደረጃ ከ Kg - 12ተኛ ክፍል ለበለጠ መረጃ ☎️በ0943909174 ይደውሉ @acetutorshr @acetutorshr
Show all...
👍 1 1
ወደ ህንድ በትሬኒንግ አማካኝነት ይጓዙ። - Training to India - Work experience 0 years and plus - Both trip tickets is full covered Room and food covered - Daily payment call us on 0946488251 ወይም 0919492435 ይደውሉ
Show all...
👍 3
ኔስትሊ በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት በሚልካቸው የወተት ምርቶቹ ላይ ስኳር እንደሚጨምር ተሰማ! የስዊዘርላንዱ የምግብና መጠጥ አምራች ኩባንያ ኔስትሊ ወደ አፍሪካ፣ እስያ እና ደቡብ አሜሪካ በሚልካቸው የጨቅላ ህጻናት ወተት እና ሌሎች ምርቶቹ ላይ ስኳር እና ማር እንደሚጨምር "ፐብሊክ አይ" የተሰኘ ስዊዘርላንድ ውስጥ የሚገኝ የምርመራ ትቋም አጋልጧል። ቡድኑ ከላይ ወደተጠቀሱት ክፍለ አህጉራት የሚላኩ የኒዶ(Nido) እና ሴሪላክ(Cerelac) ምርቶችን ቤልጄም ወደሚገኝ ላብራቶሪ ልከው ያስመረመሩ ሲሆን በውስጡ በአለም የጤና ድርጅት መመሪያ መሰረት አለቅጥ መወፈርን እና ተያያዝ በሽታዎችን ለመከላከል ለጨቅላ ህጻናት የተከለከለ የስኳር መጠንን ይዞ መገኘቱ ተዘግቧል። በአንጻሩ ኩባንያው ለአውሮፓ ደንምበኞቹ የሚልከው ስኳር የሌለበት እንደሆነ የዘ ጋርዲያን ዘገባ ያመለክታል። ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ በሴሪላክ ምርት ላይ የሚጨመረው ስኳር መጠን ከፍተኛ ከሆነባቸው ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ያመለክታል።የመረጃው ይፋ መሆንን ተከትሎ የአለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎች የተቹት ሲሆን እስካሁን ኩባንያው ያለው ነገር የለም። @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
👍 46😭 31 8👀 2
ኔስትሊ በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት በሚልካቸው የወተት ምርቶቹ ላይ ስኳር እንደሚጨምር ተሰማ! የስዊዘርላንዱ የምግብና መጠጥ አምራች ኩባንያ ኔስትሊ ወደ አፍሪካ፣ እስያ እና ደቡብ አሜሪካ በሚልካቸው የጨቅላ ህጻናት ወተት እና ሌሎች ምርቶቹ ላይ ስኳር እና ማር እንደሚጨምር "ፐብሊክ አይ" የተሰኘ ስዊዘርላንድ ውስጥ የሚገኝ የምርመራ ትቋም አጋልጧል። ቡድኑ ከላይ ወደተጠቀሱት ክፍለ አህጉራት የሚላኩ የኒዶ(Nido) እና ሴሪላክ(Cerelac) ምርቶችን ቤልጄም ወደሚገኝ ላብራቶሪ ልከው ያስመረመሩ ሲሆን በውስጡ በአለም የጤና ድርጅት መመሪያ መሰረት አለቅጥ መወፈርን እና ተያያዝ በሽታዎችን ለመከላከል ለጨቅላ ህጻናት የተከለከለ የስኳር መጠንን ይዞ መገኘቱ ተዘግቧል። በአንጻሩ ኩባንያው ለአውሮፓ ደንምበኞቹ የሚልከው ስኳር የሌለበት እንደሆነ የዘ ጋርዲያን ዘገባ ያመለክታል። ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ በሴሪላክ ምርት ላይ የሚጨመረው ስኳር መጠን ከፍተኛ ከሆነባቸው ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ያመለክታል።የመረጃው ይፋ መሆንን ተከትሎ የአለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎች የተቹት ሲሆን እስካሁን ኩባንያው ያለው ነገር የለም። @YeneTube @FikerAssefa
Show all...