cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethio telecom

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Show more
Advertising posts
345 947
Subscribers
+17024 hours
+1527 days
-5 49030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Show all...
በስኬት የተሞላው የኢትዮ ቴሌኮም 2016 በጀት ዓመት አፈጻጸም! | Ethio telecom Annual Performance of 2023/24 E.F.Y.

የደንበኞቻችን ብዛት 78.3 ሚሊዮን በማድረስ የእቅዳችንን 100.4% ያሳካ ሲሆን 93.7 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት የእቅዳችንን 103.6% አሳክተናል። ለበለጠ፡

https://bit.ly/3VWyKnZ

#ዲጂታልኢትዮጵያንእውንበማድረግላይ Our subscriber base has reach 78.3 million customers, surpassing our target by 100.4%. Moreover, our total revenue for the budget year becomes 93.7 billion birr, surpassing our plan by an outstanding 103.6%. For more:

https://bit.ly/3XYjKJc

#Realizing_Digital_Ethiopia #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #Annualperformance #Ethiotelecom #telebirr

👍 78 20👏 7😁 5
Show all...
በስኬት የተሞላው የኢትዮ ቴሌኮም የ2016 በጀት ዓመት አፈጻም! | Ethio telecom's Remarkable Performance of 2023/24 E.F.Y.

የደንበኞቻችን ብዛት 78.3 ሚሊዮን በማድረስ የእቅዳችንን 100.4% ያሳካ ሲሆን 93.7 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት የእቅዳችንን 103.6% አሳክተናል። ለበለጠ፡

https://bit.ly/3VWyKnZ

#ዲጂታልኢትዮጵያንእውንበማድረግላይ Our subscriber base has reach 78.3 million customers, surpassing our target by 100.4%. Moreover, our total revenue for the budget year becomes 93.7 billion birr, surpassing our plan by an outstanding 103.6%. For more:

https://bit.ly/3XYjKJc

#Realizing_Digital_Ethiopia #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #Annualperformance #Ethiotelecom #telebirr

👍 11😁 2🤩 1🙏 1
01:02
Video unavailableShow in Telegram
ስለአብሮነትዎ ምስጋና በቴሌብር ሱፐርአፕ ያዘጋጀነውን ልዩ የዕድል ጨዋታ እንዴት መሳተፍ እንደሚችሉ በቀላሉ ይመልከቱ!
Show all...
lucky draw 3.mp483.15 MB
👍 97 21🙏 21😡 16🥰 5🤩 4😢 3😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
ስለአብሮነትዎ ምስጋና በቴሌብር ሱፐርአፕ ያዘጋጀነው ልዩ የዕድል ጨዋታ ብዙዎችን በሽልማት እያንበሸበሸ ነው! አሸናፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ!! ሽልማቱ ገና አልተነካም እስከ ሐምሌ 09/2016 ዓ.ም ይቆያል፤ የአየር አዓት በመሙላት፣ ጥቅል በመግዛት፣ በቴሌብር ግብይት በመፈጸም እና ገንዘብ እየተላላኩ በቴሌብር ሱፐርአፕ http://onelink.to/fpgu4m ላይ የዕድል ጨዋታ ይሳተፉ!! አሁንም የ250 ሺህ ብር ሽልማቶች፣ ቅንጡ አይፎን 15 ፕሮ ማክስ ስልኮች፣ ዜድ.ቲ.ኢ A34 ስልኮች እንዲሁም 500 ሺህ የሚደርሱ የዳታ ጥቅል እና የገንዘብ ሽልማቶች እርስዎን ይጠብቃሉ! ለበለጠ መረጃ፡ https://youtu.be/MiyUul6AxzI ይጎብኙ! #Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #SmartAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
Show all...
👍 120🙏 39 34😁 10👏 6🤩 2😡 2😢 1💔 1
Photo unavailableShow in Telegram
እነሆ 500,000 ተጨማሪ የምስጋና ስጦታ፤ በቴሌብር የዕድል ጨዋታ! በበጀት ዓመቱ በነበረን አስደናቂ ስኬቶች ስለአብሮነትዎ ምስጋና እስከ 250 ሺህ የሚደርስ ኢ-ገንዘብ፣ አይፎን 15 ፕሮማክስ፣ ስማርት ስልክ፣ የዳታ ጥቅልና ኢ-ገንዘብ የሚያሸልሙ 500,000 ስጦታዎችን በቴሌብር ሱፐርአፕ አሰናድተናል! ቴሌብር ሱፐርአፕን ከ http://onelink.to/fpgu4m ይጫኑ! በየቀኑ አየር ሰዓት ለመሙላት፣ ጥቅል ለመግዛት፣ ለግብይትና ገንዘብ ለማስተላለፍ እየተጠቀሙ ከሐምሌ 5 እስከ 9 ለአምስት ቀናት የሚቆየውን የዕድል ጨዋታ ይሞክሩ! ለተጨማሪ መረጃ youtube.com/@ethio_telecom ይከተሉ፡፡ ስለ አብሮነትዎ ከልብ እናመሰግናለን! #Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #SmartAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
Show all...
👍 281 80🙏 33😁 15🎉 13👌 11🥰 8🤩 6❤‍🔥 4
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!! በ2016 በጀት ዓመት 93.7 ቢሊዮን ብር ገቢ በማግኘት የዕቅዳችንን 103.6% ማሳካታችንን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው! እርስዎም የስኬታችን ተካፋይ እንዲሆኑ ከነገ ሐምሌ 5- 7/ 2016 ዓ.ም ለ3 ቀናት የሚቆይ 1 ጊ.ባ ዳታ፣ 25 ደቂቃ የድምጽ እና 50 አጭር መልዕክት የምስጋና ስጦታ አበርክተንልዎታል፡፡ እንዲሁም በቴሌብር ሱፐርአፕ http://onelink.to/fpgu4m የዕድል ጨዋታ ከተጨማሪ አጓጊ ስጦታዎች ጋር ይጠብቁን! ስለ አብሮነትዎ ከልብ እናመሰግናለን! #Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #SmartAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
Show all...
🙏 145👍 79 28😁 18🥴 7🤩 1
ኩባንያችን በ2016 በጀት ዓመት የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን ተደራሽና አካታች በማድረግ የማህበረሰባችን ቁልፍ ችግሮች የሚፈቱ እንዲሁም የሀገራችንን ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የሚያፋጥኑ በርካታ ተግባራት በማከናወን ስኬቶችን ተጎናጽፏል፡፡ በበጀት ዓመቱ የቴሌብር ደንበኞቻችንን ብዛት 47.55 ሚሊዮን በማድረስ የእቅዳችንን 107.8% ያሳካን ሲሆን ኩባንያችን ከዳሸን ባንክ እና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር እያቀረበ በሚገኘው የማይክሮ ብድር፣ የማይክሮ ቁጠባ እና ኦቨር ድራፍት አገልግሎቶች ለ2.9 ሚሊየን ደንበኞች 9.35 ቢሊዮን ብር የብድር አገልግሎት አቅርቧል፡፡ በተጨማሪም በቴሌብር አማካይነት 1.3 ሚሊየን ደንበኞች 9.72 ቢሊዮን ብር መቆጠብ የቻሉ ሲሆን አገልግሎቱ ከጀመረበት ከነሐሴ 2014 ዓ.ም ጀምሮ 5.3 ሚሊየን ደንበኞች 12.88 ቢሊዮን ብር የብድር አገልግሎት እንዲሁም 2.1 ሚሊየን ደንበኞች ደግሞ 13.35 ቢሊዮን ብር መቆጠብ ችለዋል፡፡ በቴሌብር የገንዘብ ዝውውርን ዲጂታላይዝ በማድረግ በበጀት አመቱ 1.81 ትሪሊዮን የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ የተዘዋወረ ሲሆን አገልግሎቱ ከተጀመረ ጀምሮ በኢኮኖሚው ውስጥ 2.55 ትሪሊየን የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ማንቀሳቀስ ተችሏል፡፡ ውድ የኩባንያችን ቤተሰቦች፣ ክቡራን ደንበኞቻችን እና የሥራ አጋሮቻችን በቴሌብር የስኬት ጉዞ አብሮነታችሁ ስላልተለየን ከልብ እናመሰግናለን! ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/3VWyKnZ ይጠቀሙ፡፡ #ዲጂታል_ኢትዮጵያን _እውን_በማድረግ_ላይ #telebirr #Ethiotelecom #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #ECA #HOPR #HoF
Show all...
👍 122 39👏 6🤔 4😢 4🤣 2🤪 1
እንኳን ደስ ያላችሁ! እንኳን ደስ አለን! ኩባንያችን የ2016 በጀት ዓመት እቅዱን በላቀ ስኬት ማጠናቀቁን ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው! ባጠናቀቅነው የ2016 በጀት ዓመት የሀገራችንን ሁለንተናዊ እድገት የሚያፋጥኑ፣ የማህበረሰባችንን ቁልፍ ችግሮች የሚፈቱ እና ህይወት የሚያዘምኑ፣ የደንበኞችን የቴሌኮም አጠቃቀምና ተሞክሯቸውን የሚያሻሽሉ፣ የድርጅት ደንበኞችን ውጤታማነት የሚያሳድጉ እንዲሁም በአጠቃላይ የሀገራችንን ተወዳዳሪነት የሚጨምሩ በርካታ ምርትና አገልግሎቶች አቅርበናል፡፡ በውጤቱም የቴሌኮም ደንበኞቻችንን ቁጥር ከአምና ተመሳሳይ ወቅት በ8.9% በማሳደግ 78.3 ሚሊዮን አድርሰን የእቅዳችንን 100.4% አሳክተናል፡፡ እንዲሁም በጀት ዓመቱ አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢያችንን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት በ21.7% ወይም በ16.7 ቢሊዮን ብር በማሳደግ 93.7 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት የእቅዳችንን 103.6% አሳክተናል፡፡ የውጭ ምንዛሪ የማመንጨት አቅማችንን በማስፋት ከአምናው በ20.7 በመቶ አሳድገን አጠቃላይ 198.02 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በማስገባት የእቅዳችንን 117.5% አሳክተናል፡፡ ውድ የኩባንያችን ቤተሰቦች፣ ደንበኞቻችን እና የሥራ አጋሮቻችን በስኬታችን ጉዞ አብሮነታችሁ ስላልተለየን ከልብ እናመሰግናለን! ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/3VWyKnZ ይጠቀሙ፡፡ #ዲጂታል_ኢትዮጵያን_እውን_በማድረግ_ላይ #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
Show all...
161👍 147👏 27😡 20🍾 9🥰 6😢 3🥴 3🤣 1
Photo unavailableShow in Telegram
በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ምዝገባ በአገልግሎት ማዕከሎቻችን እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ምዝገባ ካልፈጸሙ በአካል ቀርበው በነጻ ይመዝገቡ! በአቅራቢያዎ የሚገኘውን የምዝገባ ማዕከል ለማወቅ በቴሌብር ሱፐርአፕ ውስጥ የተካተተውን አቅጣጫ ጠቋሚ መተግበሪያ http://onelink.to/fpgu4m በነጻ ይጠቀሙ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ https://bit.ly/3REY68C ይጎብኙ! #DigitalID #Fayda #Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
Show all...
👍 75 28
በቴሌብር ኢንጌጅ እንደልብ በነጻ ያውጉ!! ቴሌብር ሱፐርአፕ http://onelink.to/fpgu4m ላይ ያገኙታል፡፡ youtube.com/watch?v=-YqT-yr17tE #Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #Engage #DigitalAfrica #SmartAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
Show all...
በቴሌብር ሱፐርአፕ #ኢንጌጅ እንደልብ በነጻ ያውጉ | telebirr SuperApp #Engage

👍 66 14😢 2
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.