cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Ethio telecom

The first Telecom operator in Ethiopia https://t.me/EthiotelecomChatBot

Больше
Рекламные сообщения
386 906Подписчики
-1024 часы
+1 4457 дней
+8 08930 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

መጋቢትን ለባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት! በዚህ ወር በማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን በሚቀላቀሉ አዲስ ተከታዮች (Followers) ብዛት ልክ 30 ብር እንዲሁም በሚጋሩ ልጥፎች (Share) ልክ 10 ብር ለባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት እንለግሳለን! እርስዎም ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይከተሉ፤ ፖስቶቻችንን ያጋሩ፤ ለወገን ድጋፍ ይተባበሩ! ቴሌግራም፡ https://t.me/ethio_telecom ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/ethiotelecom ኢንስታግራም ፡https://www.instagram.com/ethiotelecom/ ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/ethio-telecom ዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/c/EthiotelecomETH ቲክቶክ፡ http://www.tiktok.com/@ethio_telecom?lang=en ዘላቂ የጋራ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለወገን ብሩህ ተስፋ! #MatchingFundForSustainableFuture #Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
Показать все...
👍 12🙏 3🥴 2 1
ኩባንያችን በመጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ጉዞን ለመቃኘት በተዘጋጀው ሀገራዊ ጉባኤ ላይ ከታዳሚዎቹ በዲጂታል መንገድ ግብዓት የሚሰበሰብበት የዲጂታል ፖርታል ማዘጋጀቱን መግለጹ ይታወሳል። ፖርታሉ የዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽኑን ለማፋጠን በቀጣይ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው አስፈላጊ እርምጃዎች ዜጎች በቀላሉ ካሉበት ሆነው አስተያየት ለመስጠት እንዲችሉ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን እርስዎም ማስፈንጠሪያውን https://bit.ly/49eSBn1 በመጠቀም ወይም QR Code ስካን በማድረግ ግብዓትዎን እንዲሰጡን በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ጉባኤ ላይ በመገኘት ገንቢ አስተያየታችሁን ለሰጣችሁን ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ የግሉ ዘርፍ አጋሮች፣ ወጣት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እና መላው ታዳሚዎች ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን። #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica
Показать все...
በትላንትናው ዕለት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተካሄደው የሀገራችንን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚቃኝ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ሀገር አቀፍ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ክቡር አቶ ማሞ ምህረቱ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ፣ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ጀነራል ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ እና በትምህርት ሚኒስቴር የአይ.ሲ.ቲ እና ዲጂታል ትምህርት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ዘላለም አሰፋ የፓነል ውይይት አካሂደዋል፡፡ በፓነሉ የሀገራችንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚቃኙ የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን የኩባንያችን ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ እንደ ቴሌኮም፣ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ዳታ ሴንተር፣ ክላውድ ያሉ ዲጂታል መሰረተ ልማቶች እንዲሁም እንደ ዲጂታል መታወቂያ፣ ዲጂታል ክፍያ ስርዓቶች ያሉ አስቻይ ሲስተሞች የዲጂታል ኢትዮጵያ ራዕይን ዕውን ለማድረግ ቁልፍ ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ “ዲጂታል ኢትዮጵያን መገንባት ጉዞ ነው” በማለት የተናገሩት ዋና ስራ አስፈጻሚያችን "በየምዕራፉ የምናሳካቸው ፍሬዎች አሉ" በማለት በኃይል አቅርቦት እና በቴሌኮም ተደራሽነት ዙሪያ የተሰሩት የማስፋፊያ ስራዎችን አብራርተው በንፅፅር የታዩ እድገቶች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል። #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica
Показать все...
👍 16😡 3😁 2 1
በትላንትናው ዕለት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተካሄደው የሀገራችንን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚቃኝ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ሀገር አቀፍ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ክቡር አቶ ማሞ ምህረቱ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ፣ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ጀነራል ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ እና በትምህርት ሚኒስቴር የአይ.ሲ.ቲ እና ዲጂታል ትምህርት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ዘላለም አሰፋ የፓነል ውይይት አካሂደዋል፡፡ በፓነሉ የሀገራችንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚቃኙ የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን የኩባንያችን ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ እንደ ቴሌኮም፣ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ዳታ ሴንተር፣ ክላውድ ያሉ ዲጂታል መሰረተ ልማቶች እንዲሁም እንደ ዲጂታል መታወቂያ፣ ዲጂታል ክፍያ ስርዓቶች ያሉ አስቻይ ሲስተሞች የዲጂታል ኢትዮጵያ ራዕይን ዕውን ለማድረግ ቁልፍ ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ እነዚህን ቁልፍ መሰረተ ልማቶች በመገንባትና በማስፋፋት አንጻራዊ እድገት የተመዘገበ ሲሆን ሆኖም መገንባት ብቻ በቂ አለመሆኑን እና መሰረተ ልማቶቹን ጥቅም ላይ በማዋል ዲጂታል ኢኮኖሚን ከመገንባት አንጻር የዲጂታል መታወቂያ ትግበራ መጀመሩ፣ ፖሊሲዎችን በማሻሻል የዲጂታል ክፍያ ስርአት መዘርጋቱ እንዲሁም የኢንተርኔት ዋጋ ተመጣጣኝ መደረጉ አስቻይ ሁኔታ በመፍጠር ከፍተኛ ስኬትን እንዲመዘገብ ማስቻሉን ገልጸዋል፡፡ “ዲጂታል ኢትዮጵያን መገንባት ጉዞ ነው” በማለት የተናገሩት ዋና ስራ አስፈጻሚያችን "በየምዕራፉ የምናሳካቸው ፍሬዎች አሉ" በማለት በኃይል አቅርቦት እና በቴሌኮም ተደራሽነት ዙሪያ የተሰሩት የማስፋፊያ ስራዎችን አብራርተው በንፅፅር የታዩ እድገቶች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል። መሰረተ ልማቶች ላይ የጀመርናቸውን ስራዎች አጠናክረን መቀጠል እና አካታች ማድረግ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ የሚጠይቅ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ ፓነሊስቶቹ በውይይቱ ወቅት የዲጂታል ገንዘብ አገልግሎት በሀገራችን በፋይናንስ ዘርፉ ላይ ፈጣን ለውጥ እያመጣ መሆኑ፣ እንደ ሀገር ለአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ትኩረት በመስጠት የኢትዮጵያን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማፋጠን አበረታች ጅማሮ ላይ እንደምንገኝ፣ ከሳይበር ጥቃት የነጻ፣ አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተረጋገጠ የሳይበር ስነምህዳር ለመገንባት እና ተጋላጭነትን ለመቀነስ እንዲሁም የዲጂታል ትምህርትን በትምህርት ካሪኩለም ውስጥ በማካተት ዘመኑን የዋጀ ትውልድ ለመፍጠር የሚያስችል ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡ #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ኩባንያችን በቅርቡ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ያስገነባውን የኤክስፒሪየንስ ማዕከል ጎበኙ፡፡ በጉብኝቱ ወቅት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የኤክስፒሪየንስ ማዕከሉ መገንባት በጣም አስፈላጊ እና በጥሩ ሁኔታ የተገነባ መሆኑን በመግለጽ ማዕከሉ የወጣቶችን የፈጠራ ክህሎት የሚያነሳሳ፣ በዲጂታል ሥነ-ምህዳሩ የተሰማሩ ተዋናዮች አዳዲስ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በተግባር የሚሞክሩበት እና ወደ ፈጠራ የሚቀይሩበት ማዕከል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አክለውም የኤክስፒሪየንስ ማዕከሉ ለሀገራችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መፋጠን እና ሁለንተናዊ እድገት አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና የሚኖረው መሆኑን በመረዳት፣ ወጣት የቴክኖሎጂ አልሚዎች ያላቸውን ራዕይ ለማሳካት በር የሚከፍትላቸው መሆኑን እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት ማዕከሉን በመጎብኘት የተግባር ተሞክሮዎችን ማከናወን የሚችሉበት መሆኑን በመግለጽ ማዕከሉን ሊጎበኙት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በአድዋ ሙዚየም የገነባነውን ኤክስፒሪየንስ ማዕከላችን በመጎብኘት ስለሰጡን ግብዓት እና አበረታች አስተያየት ከልብ እናመሠግናለን፡፡ #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica @PMEthiopia #GSMA #ITU
Показать все...
የሀገራችንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚቃኝ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሀገር አቀፍ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ የተከበሩ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ እንዲሁም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በተገኙበት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተካሄደ! በመርሃ ግብሩ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ጉዞ፣ የተገኙ ስኬቶች እና ተግዳሮቶች ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በተደረገ የመድረክ ላይ ወግ ፣ ዘርፉን ከሚመሩ ባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገ የፖነል ውይይት ተዳሰዋል። በውይይቱ ወቅት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታ ረገድ ሀገራችን መልካም ጅማሮዎች እና ወሳኝ ምዕራፎች ላይ የምትገኝ መሆኗን አንስተው በመሰረተ ልማት፣ በኢንተርኔት ተደራሽነት እንዲሁም በዲጂታል ፋይናንስ የተሰሩት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ አክለውም፣ መንግስት ለዲጂታል ጉዞ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኑን በመግለጽ የግሉ ዘርፍ በበኩሉ በዲጂታል ሥነምህዳሩ የተፈጠረለትን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በዘርፉ ላይ የሚጠበቅበትን ሚና መጫወት እንደሚገባው አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምናደርገውን ጉዞ በይበልጥ ለማፋጠን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ ሃገራዊ ካውንስል እንዲቋቋም አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡ #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #DigitalEconomy #MINT #PMO #EthiopianCommunicationAuthority #GSMA #ITU #SmartAfrica #HOPR #HOF
Показать все...
መጋቢትን ለባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት! በዚህ ወር በማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን በሚቀላቀሉ አዲስ ተከታዮች (Followers) ብዛት ልክ 30 ብር እንዲሁም በሚጋሩ ልጥፎች (Share) ልክ 10 ብር ለባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት እንለግሳለን! እርስዎም ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይከተሉ፤ ፖስቶቻችንን ያጋሩ፤ ለወገን ድጋፍ ይተባበሩ! ቴሌግራም፡ https://t.me/ethio_telecom ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/ethiotelecom ኢንስታግራም ፡https://www.instagram.com/ethiotelecom/ ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/ethio-telecom ዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/c/EthiotelecomETH ቲክቶክ፡ http://www.tiktok.com/@ethio_telecom?lang=en ዘላቂ የጋራ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለወገን ብሩህ ተስፋ! #MatchingFundForSustainableFuture #Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
Показать все...
🙏 73👍 53🥰 12 11🤪 2
ከቴሌብር አካውንትዎ ወደ ሌላ የቴሌብር ደንበኛ አካዉንት ገንዘብ እንዴት ማስተላለፍ እንደሚችሉ ይመልከቱ
Показать все...
👍 81😁 20 19😡 11😢 2🥰 1👏 1
Войдите и получите доступ к детальной информации

Мы откроем вам доступ после авторизации. Мы обещаем, это быстро!