cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Tikvah-University

Show more
Advertising posts
213 185Subscribers
+8024 hours
+1 4347 days
+3 13830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 154 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም የሰለጠኑ 110 እንዲሁም በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን የተከታተሉ 44 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል። በመጀመሪያ ዲግሪ ከተመረቁት መካከል107ቱ በጤና ሳይንስ የትምህርት መስኮች የሰለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ @tikvahuniversity
Show all...
👍 5
#HawassaUniversity👏 የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፊታችን ሰኞ የጨረር ህክምና መስጠት ይጀምራል። ማዕከሉ ለመጀመሪያ ዙር ፈቃደኛ ሆነው በተገኙ 30 ታካሚዎች ነው የጨረር ህክምና አገልግሎት መስጠት የሚጀምረው። #ኢፕድ @tikvahethiopia
Show all...
👏 22👍 7 2👎 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ " ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው " ብለዋል። በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ ሲሉ አሳውቀዋል። ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፤ ፈተናው በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል። ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጸዋል። የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል። ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ብለዋል። #MoE @tikvahethiopia
Show all...
#DebreBerhanUniversity የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በሥራ ገበታቸው ላይ ከታዩ አንድ ወር እንዳለፋቸው አል-ዐይን አማርኛ የተቋሙን አንድ አመራር በመጥቀስ ዘግቧል፡፡ ፕሬዝዳንቱ "የት እንዳሉ እንደማይታወቅ" ዘገባው ጠቅሷል፡፡ ከሦስት ዓመት በፊት የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በቢሯቸው ከታዩ አንድ ወር አልፏቸዋል ተብሏል። "ፕሬዝዳንቱ ከመጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ. ም ጀምሮ በሥራ ላይ አይተናቸው አናውቅም" ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር ለአል-ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡ "ከተጠቀሰው ቀን አንስቶ ፕሬዝዳንቱ የት እንደሔዱና መቼ እንደሚመለሱ አናውቅም" ያሉት የተቋሙ አመራር፤ "ፕሬዝዳንቱ በቢሮ መታየት ካቆሙ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ባልታወቁ ኃይሎች መታገታቸውን ሰምተናል" ሲሉም አክለዋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መሰወርን አስመልክቶ አል-ዐይን አማርኛ የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ፣ የሰሜን ሸዋ ኮማንድ ፖስት፣ ትምህርት ሚኒስቴር እና የደብረ ብረሃን ከተማ ፖሊስ ምላሽ እንዲሰጡ ያደረገው ጥረት አለመሳካቱን ገልጿል። የፕሬዝዳንቱ ቤተሰብ ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጡ አል-ዐይን ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረትም አልተሳካም። የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትን በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው እንዲሁም ትምህርት ሚኒስቴር የሚሉትን ወደናንተ እናደርሳለን፡፡ #አልዐይንአማርኛ @tikvahuniversity
Show all...
👍 121😱 23👏 12 10👎 8😢 5🙏 5
Ready to empower the next generation of learners? Join us on EdTech Mondays for an eye-opening discussion on Financing EdTech Startups in Ethiopia! Discover how investors are igniting innovation and driving change in the education landscape, overcoming unique challenges to support promising ventures. From bridging the digital divide to enhancing learning outcomes, explore the transformative potential of investing in EdTech startups. Tune in and be part of the movement to revolutionize education in Ethiopia! Monday, April 29th at 8:10 pm on Fana FM 98.1 for insights that matter. #EdTechEthiopia #EducationInnovation #JoinTheConversation #Ethiopia #DigitalLiteracy #TechnologyInEducation #EdTechMondaysEthiopia #EquityInEducation #Ethiopia #DigitalLiteracy #ShegaMedia #MastercardFoundation
Show all...
👍 18 6👎 2
#ይጠንቀቁ "ሰርተፊኬት የሚያሰጡ ነጻ የኦንላይን ስልጠና " የሚሉ ማስታወቂያዎች በማኅበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወሩ መሆኑን ተመልክተናል፡፡ ማስታወቂያዎቹ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን እንዲሁም የትምህርት ሚኒስቴርን ስም ይጠቅሳሉ፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ማስታወቂያዎች ሐሰተኛ መሆናቸውን ዩኒቨርሲዎቹ አረጋግጠዋል፡፡ "የተቋሜን ስም በመጠቀም የሚፈፀም የማጭበርበር ተግባር ሰለሆነ የሚመለከተው ሁሉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስባለው" ብሏል መቐለ ዩኒቨርሲቲ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመሳሳይ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ከጥቂት ሳምንታት በፊት አውጥቶ እንደደነበር አይዘነጋም፡፡ "በተለያዩ ድረ-ገጾች እና ማኅበራዊ ሚዲያዎች የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ስም እና አርማ በመጠቀም ከሚተላለፉ ሐሰተኛ መረጃዎች እንዲጠነቀቁ" ብሏል ዩኒቨርሲቲው፡፡ @tikvahuniversity
Show all...
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሥራ መደቦች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ ➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 19 ➤ የትምህርት ደረጃ፦ የመጀመሪያ እና 2ኛ ዲግሪ ➤ የሥራ ልምድ፦ ዜሮ ዓመትና ከዚያ በላይ ➤ የሥራ ቦታ፦ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ➤ የማመልከቻ ጊዜ፦ ከሚያዝያ 17/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ➤ የምዝገባ ቦታ፦ አዲስ አበባ አሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ቢሮ ወይም ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. B-4 ለተጨማሪ መረጃ፦ አ.አ. 0111-26-01-24 ፖ.ሳ.ቁ. 1362 @tikvahuniversity
Show all...
ማክሰኞ ሚያዚያ 22/2016 ዓ.ም 20ኛ ዙር የግራፊክስ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኢዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክስ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና ይጀምራል። 🔔 ቀድመው ይመዝገቡ! 👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና 👉 ከ15 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት 👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት 👉 Advanced Graphics + Video Editing + Motion Graphics + Digital Marketing በአንድ ላይ ☎️ ለበለጠ መረጃ፦  0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ የበለጠ ይጠብቁ ...         ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት Facebook | Telegram | Instagram | LinkedIn
Show all...
👍 13👎 3😢 1🙏 1
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ምክትል ፕሬዝዳንቶች ተመድበውለታል፡፡ ካሳሁን አህመድ (ዶ/ር) የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ፣ ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመድበዋል፡፡ ማርየ በለጠ (ዶ/ር) የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና ቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው በትምህርት ሚኒስቴር እና በቦርድ አፅዳቂነት ተመድበዋል፡፡ አዲስ የተሾሙት አመራሮች ከተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ትውውቅ አድርገዋል፡፡ @tikvahuniversity
Show all...
👍 31👎 23 8🙏 3👏 1😢 1
#YHMC የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በዲግሪ መርሐግብር ማስተማር ጀመረ። ኮሌጁ በዛሬው ዕለት 79 ተማሪዎችን በመቀበል በዲግሪ መርሐግብር ትምህርት መስጠት መጀመሩ ተሰምቷል። ኮሌጁ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ማስተማር የጀመረባቸው መስኮች፦ ➤ በድንገተኛ ሕክምና ነርስነት (Emergency and Critical Nursing) ➤ በጨቅላ ሕጻናት ነርስነት (Neonatal Nursing) ➤ በአጠቃላይ ነርስነት (Comprehensive Nursing) ➤ በላቦራቶሪ ባለሙያ (Medical Lab) @tikvahuniversity
Show all...
👍 86 23