cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

TIKVAH-ETHIOPIA

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Show more
Advertising posts
1 340 649Subscribers
+60324 hours
+3 1287 days
+28 89930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

" ሰላም እና ፍትህ ለማስፈን ያጠፋ መጠየቅ አለበት " - አቶ ጌታቸው ረዳ በማህበራዊ ሚዲያ " ህወሓት ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ሊዋሃድ ድርድር እየተካሄደ ነው " የሚሉት መረጃዎች ፍጹም ሐሰተኛ ናቸው ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ለ ' ቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ' ተናግረዋል። ብልፅግና እና ህወሓት ንግግር ማድረግ መጀመራቸውን የገለጹት አቶ ጌታቸው "  እነዚህ ንግግሮች ከውህደት ጋር የተያያዙ አይደሉም " ብለዋል። " የቅርብ ጊዜው ንግግራችን የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተግባራዊ ስለማድረግ ነው። ውህደት አጀንዳም ሆኖ አያውቅም " ሲሉ ገልጸዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር ስላላቸው የስራ ግኝኑት በተመለከተ ፥ " ጥሩ የሥራ ግንኙነት ነው ያለን። የራሳችን የሆነ ልዩነት አለን። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ አመለካከቶች አሉን " ብለዋል። " የፕሪቶሪያው ስምምነት #አብረን_እንድንሠራ ዕድል ስለሰጠን፤ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ልዩነቶቻችን ምንም ይሁኑ ምን አብረን እንድንሠራ አስችሎናል። ይህም ወደፊት ይቀጥላል ብዬ አስባለሁ " ሲሉ ተናግረዋል። በሌላ በኩል ፤ አቶ ጌታቸው በጦርነቱ ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ በሙሉ ተጠያቂ መሆን አለባቸው ብለዋል። " ማንም ሰው ቢሆን፤ እኔን ጨምሮ መጠየቅ አለብን። ማንም ነጻ እንዲሆን መፈቀድ የለበትም። ሰላም እና ፍትህ ለማስፈን ያጠፋ መጠየቅ አለበት " ሲሉ ገልጸዋል። #BBC #FocusonAfrica @tikvahethiopia
Show all...
👏 212😡 73 44🤔 18🕊 15🙏 11😢 4😱 3
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት  አቶ ጌታቸው ረዳ ከ ' ቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ' ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር። በቃለምልልሱ ፥ ባለፉት ሳምንታት በአማራ እና ትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች የነበረው ግጭት በ " የሚሊሻ አባላት " መካከል እንጂ መደበኛ ኃይሎች የተሳተፉበት አልነበረም ብለዋል። " አማራ ክልል በኩል የነበሩ ሚሊሻዎች የተለያዩ አስጊ እንቅስቃሴያዎችን ሲያደርጉ ነበር። በእኛ በኩል ያሉ የሚሊሻ አባላት ምላሽ ሰጥተዋል " ሲሉ ገልጸዋል። የአማራ ክልል ያወጣውን መግለጫም  " መሬት ላይ ያለውን እውነታ ያላገናዘበ " ብለዋል። የሰላም ስምምነቱ #ተፈጻሚ_እንዳይሆን እያደረገ ያለው " ሕጋዊ የልሆነ የአማራ አስተዳደር ነው " ሲሉ ተደምጠዋል። አቶ ጌታቸው በዚሁ ቃለ ምልልስ ፥ በሰላም ስምምነቱ መሰረት በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉትን ሰዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ከስምምነት መደረሱን አስታውሰዋል። " ሕጋዊ ያልሆኑ አስተዳደሮችን ለማፍረስ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር አብረን እየሠራን ነው። ከአማራ ክልል ጋርም ቢሆን በተወሰነ ደረጃ አብረን እየሠራን ነው " ብለዋል። " የፕሪቶሪያው ስምምነት ተፈጻሚ እንዳይሆን የሚሹ አካላት እንዳሉ ግን በጣም እርግጠኞች ነን " ሲሉ ተደምጠዋል። አቶ ጌታቸው እነዚህ አካላት እነማን እነደሆኑ በግልጽ በስም ጠርተው አልጠቀሱም። #BBC #FocusonAfrica @tikvahethiopia
Show all...
😡 136 101🕊 22👏 18😭 8🥰 4🙏 1
#Raya እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ሪፖርት መሰረት ከራያ አላማጣ ገጠራማ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሺህ በልጧል። 42 ሺህ ዜጎች ቆቦ ፤ 8,300 ሰዎች ሰቆጣ ይገኛሉ። የተፈናቀሉት ከራያ አላማጣ፣ ዛታ፣ ኦፍላ ነው። አብዛኞቹ ህጻናት ፣ ሴቶች ፣ ወጣቶች እና በእድሜ የገፉ አዛውንቶች ናቸው። #UNOCHA @tikvahethiopia
Show all...
😭 90😢 19👏 17😡 11 4🙏 4🤔 3🥰 2😱 2
#Update ባይደን ፊርማቸውን አኑረዋል ፤ ቲክቶክ " ፍርድ ቤት እንተያይ " ብሏል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በባይት ዳንስ ባለቤትነት ያለው " #ቲክቶክ " ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ ተሽጦ ከቻይና ካልተፋታ በመላው አሜሪካ #እንዲታገድ የቀረበላቸው ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ሕግ ሆኖ  እንዲወጣ አድርገዋል። " ቲክቶክ " ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ እንዲሸጥ የተሰጠው ጊዜ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ብቻ ነው። በዚህ ጊዜ ይህንን ካላደረገ #እስከወዲያኛው ከአሜሪካ እንደሚታገድ ተገልጿል። አሁን በአሜሪካ ብቻ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት " ቲክቶክ " ሙሉ በሙሉ የመታገዱ ነገር #እውን ወደ መሆኑ ተቃርቧል። የቲክቶክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ሹ ዚ ቼው ፥ " የትም አንሄድም። ለመብታችን በፍርድ ቤት እንታገላለን። ሀቁ እና ህገ መንግስቱ ከጎናችን ናቸው፣ እናሸንፋለን ብለን እንጠብቃለን " ሲሉ ተናግረዋል። በሌላ በኩል ፤ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን ፣ እስራኤል እና ታይዋን የቀረበው የ95 ቢሊዮን ዶላር የድጋፍ ጥቅል ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል። @tikvahethiopia
Show all...
" ሰዎቹ ናቸው አታልለውኝ እዚያ ድረስ የወሰዱኝ " - ቀሲስ በላይ መኮንን የቀሲስ በላይ መኮንን ጠበቃ አቶ ቱሊ ባይሳ ስለ ዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር። በዚህም ወቅት ፥ ደንበኛቸው ቀሲስ በላይ መኮንን በሐሰተኛ ሰነድ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማውጣት ሙከራ ተደርጎበታል የተባለው ቦታ የተገኙት " ሰዎች አታልለዋቸው " እንደሆነ ለፍ/ቤት መናገራቸውን ገልጸዋል። ጠበቃ ቱሊ ፤ " እሳቸው በቦታው ከመገኘት ውጪ ደብዳቤውን በማዘጋጀት፣ በመቀበል በዚህ ወንጀል ውስጥ ተሳትፎ የላቸውም " ያሉ ሲሆን " ደብዳቤው ላይ የእሳቸው ስም፣ የባንክ ቁጥር የለም። የቤተ ክርስቲያን የሂሳብ ቁጥር የለም " ብለዋል። " ከመጀመሪያውም ወንጀሉ በሌሎች ሰዎች የተሞከረ ቢሆንም እሳቸውን አይመለከትም " ሲሉ ገልጸዋል። በችሎቱ ላይ ለመናገር ዕድል ያገኙት ቀሲስ በላይ የአፍሪካ ኅብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገኙት " ሰዎች ወስደዋቸው " እና " #ተታልለው " እንደሆነ ተናግረዋል። " በዚያ ቦታ ላይ ከመገኘት ውጪ ምንም የፈጸሙት ድርጊት እንደሌለ " ገልጸዋል። ቀሲስ በላይ ፦ " ሰዎቹ ናቸው አታልለውኝ እዚያ ድረስ የወሰዱኝ። እኔ ወደዚያ የሄድኩት ለመተባበር፣ ይህ ሰነድ ‘ትክክለኛ ሰነድ ነው አይደለም’ የሚለውን የባንክ ማናጀሮችን ለመጠየቅ ነው እንጂ በምንም ሁኔታ በሰነዱ ለመገልገል አስቤ አይደለም። ጉዳዩ ዞሮ እኔ ታሳሪ ሆንኩኝ እንጂ፤ ሰነዱ ‘ትክክል አይደለም’ የሚል የባንክ ማናጀሩ ሲገልጹልኝ ወዲያው ፖሊስ ያስጠራሁት እኔ ነኝ " ማለታቸውን ጠበቃው ተናግረዋል። ቀሲስ በላይ ሰነዱን አዘጋጅተዋል የተባሉ ሰዎች " ማምለጣቸውን " እንዲሁም ስለ ሰነዶቹ " የሚያውቁት እና መመርመር ያላባቸው " እነሱ እንደሆኑም ለፍርድ ቤቱ አንስተዋል ተብሏል። በዛሬው የፍ/ ቤት ውሎ የቀረበው የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ ለመርማሪ ፖሊስ ስምንት ተጨማሪ ቀን መሰጠቱ ይታወቃል። የመረጃው ምንጭ ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ነው። @tikvahethiopia
Show all...
" ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንጀምራለን፤ ... የንግድ ቻርተር አውሮፕላኖችንም ተከራይተናል " - ጠ/ሚር ሪሺ ሱናክ ዩናይትድ ኪንግደም በቁጣዮቹ ከ10 እስከ 12 ሳምንታት ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ #ሩዋንዳ መላክ ትጀምራለች። የዩናይትድ ኪንግደም ፓርላማ ስደተኞች/ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለመመለስ የተያዘውን እቅድ መጀመር የሚያስችለውን " የሩዋንዳ እቅድ " የተሰኘውን ረቂቅ ሕግ ትላንት አጽድቋል። ጠ/ሚር ሪሺ ሱናክ፥ " በቀጣዮቹ ከ10 እስከ 12 ሳምንታት ባለው ጊዜ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንጀምራለን " ብለዋል። ለዚህም ፤ የንግድ ቻርተር አውሮፕላኖች ኪራይ መፈጸሙና ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የሚወስዱ ሰራተኞችም መሰልጠናቸው ተነግሯል። 52,000 ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ምስራቅ አፍሪካዋ ሩዋንዳ ይዘዋወራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በቅርብ አመታት ፦ - #ከአፍሪካ ፣ - ከመካከለኛው ምስራቅ - ከኢስያ ጦርነት እና ድህነት የሚሸሹ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞች ዩናይትድ ኪንግደም ገብተዋል። እነኚህ ስደተኞቹ በህገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት በትንንሽ ጀልባዎች ተጉዘው ነው የሚገቡት። #ሮይተርስ @tikvahethiopia
Show all...
#AddisAbaba በአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ድንጋይ እና አፈር ተደርምሶ የ7 ሰዎች ሕይወት አፏል። አደጋው የደረሰው በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ወረዳ 12 " ጠሮ መስጂድ " አካባቢ ነው። ለሊት 11 ሰዓት ገደማ ለቤት ግንባታ የተከመረ ድንጋይ እና አፈር ከላይ ወደ ታች (ወደ ቤቱ) ተንዶ 3 ክፍል ያለው ቤት ላይ አደጋ ደርሷል። በዚህም ቤት ውስጥ ተኝተው የነበሩ 7 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ሟቾቹ ፦ ➡ የ4 ዓመት ህጻን ፣ ➡ ሶስት የ11 እና የ12 ዓመት ታዳጊዎች  ➡ ከ25 እስከ 30 ዓመት ያሉ 3 ወጣቶች ናቸው። ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች የሁለት ቤተሰብ አባላት እንደሆኑ ታውቋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ አደጋው የደረሰበት ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ ምርመራ ላይ ነው። መረጃው የአዲስ አበባ እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ነው። @tikvahethiopia
Show all...
ከፊታችን ሚያዚያ 25 ቀን 2016 ጀምሮ ወደ ሶማሌ ክልል #ቀብሪደሃር ከተማ በሳምንት ሁለት ቀን የበረራ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል። አየር መንገዱ በሶማሌ ክልል ከጅግጅጋና ጎዴ ቀጥሎ #ቀብሪደሃር ሶስተኛው መዳረሻው ይሆናል። @tikvahethiopia
Show all...
196👏 65🙏 9😡 7🥰 5🤔 5😱 2🕊 2
“ ገዳሙ በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛል ” - አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም በዙራያው በሰፈሩ ሰዎች የታዘ መሬቱን ለማስመለስ የካሳ ክፍያ መጠየቁን አስታወቀ። በአማራ ክልል የሚገኘው ገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም ከ30,000 እስከ 50,000 የሚሆኑ ፀበልተኞች እንደሚጸበሉበት ይሁን እንጂ የገዳሙ መሬት ሰዎች ስለሰፈሩበት እንኳን ለጸበልተኞች ለመነኮሳቱም እጅግ በመጣበቡ፣ “ ገዳሙ በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛል ” ተብሏል። የገዳሙ ይዞታ የጠበበው ከበርካታ ዓመታት ጀምሮ ለመፈወስ ወደ ስፍራው የሚሄዱ ፈውስ ያገኙ ጸበልተኞችና አርሶአደሮች ከሕመማቸው ከተፈወሱ በኋላ በገዳሙ መሬት ቤት እየሰሩ እዚያው በመኖራቸው መሆኑን የገዳሙ መነኮሳት አስረድተዋል። ሰዎቹ በአንድ ሳይሆን ቀስ በቀስ እዛው መኖር እንደጀመሩ ጠቁሟል።   በገዳሙ ይዞታ የሰፈሩ ከ250 በላይ አባውራዎች ይነሱ ዘንድ ለጠየቁት ካሳና ለሌሎች አገልግሎቶች ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ አሳውቋል። ለዚህም ሚያዚያ 19/2016 ዓ/ም በካፒታል ሆቴል የገቢ ማሰባሰብ መርሀ ግብር እንደተዘጋጀ፣ በመሆኑም በውስጥም በውጪ ያሉ ኢትዮጵያዊያን እርብርብ እንዲያደርጉ ገዳሙ ጥሪ አቅርቧል። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Show all...
#SafaricomEthiopia መልካሙን ዜና ከሳፋሪኮም ሰምተዋል?! 🎁ዕለታዊ የዳታ ጥቅል ስንገዛ ቀኑን ሙሉ፣ ሳምንታዊ የዳታ ጥቅል ስንገዛ ሳምንቱን በሙሉ እንዲሁም ወርሃዊ የዳታ ጥቅል በምግዛት ወሩን ሙሉ ከሳፋሪኮም ወደ ሳፋሪኮም መስመር በነጻ እንደዋወል! ዳታ እንግዛ! በነጻ እንደዋወል! የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ትክክለኛ መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት ቀጥሎ በሚገኙት ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲከታተሉ  እንጋብዛለን። 👉 Facebook 👉Telegram 👉 Twitter 👉Instagram 👉 YouTube
Show all...
51😡 11🙏 5🥰 4👏 3