ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

شـبـاب السـلــفـــيـــيــن

شـبـاب السـلــفـــيـــيــن

الذهاب إلى القناة على Telegram

👉«ሰለፍያ ቀጥተኛ የሀቅ መንገድ ብሎም አይነኬ ፅኑ ተራራ ነው።» ለአስተያዬትና እርማት

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام شـبـاب السـلــفـــيـــيــن

تُعد قناة شـبـاب السـلــفـــيـــيــن (@nuredinal_arebi) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 28 204 مشتركاً، محتلاً المرتبة 2 564 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 1 294 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 28 204 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 15 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار -241، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -16، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 13.78‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 6.79‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 3 887 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 914 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 37.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“👉«ሰለፍያ ቀጥተኛ የሀቅ መንገድ ብሎም አይነኬ ፅኑ ተራራ ነው።» ለአስተያዬትና እርማት”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 16 أكتوبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

28 204
المشتركون
-1624 ساعات
-827 أيام
-24130 أيام
أرشيف المشاركات
​🔴 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🔴 ✨ ✨ ​ልዩና ያማረ የሰርግ ፕሮግራም አዘጋጅተንላችኋል። ​🎙️ የፕሮግራሙ መሪዎች (አቅራቢዎች) ​❶ ኑረዲን አል-አረቢ ​❷ አቡ ሁዘይ
​🔴 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🔴 ✨ ✨ ​ልዩና ያማረ የሰርግ ፕሮግራም አዘጋጅተንላችኋል። ​🎙️ የፕሮግራሙ መሪዎች (አቅራቢዎች) ​❶ ኑረዲን አል-አረቢ ​❷ አቡ ሁዘይፋ ​🌟 የዕለቱ ተጋባዥ እንግዶችና ኡስታዞች 🌟 ​❶ ሸይኽ አቡ-ሀኒፋ (ከገርባ) ​❷ ኡስታዝ ፉዓድ ሙሀመድ ​❸ ኡስታዝ አቡ-ሐሳን ​❹ ኡስታዝ አቡ ሒበቱሏህ ​❺ ኡስታዝ አቡ ሻኪራ ​❻ ኡስታዝ ጦይብ አህመድ (ከአሶሳ) ​💡 እንዲሁም ስማቸው ያልተጠቀሱ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ኡስታዞችና እንግዶችም ይገኛሉ፤ እንዳያመልጥዎ! ​🕒 የፕሮግራሙ ሰዓት 🇸🇦 በሳዑዲ" 8:30 🇦🇪 በዱባይ" 9:30 🇪🇹 በኢትዮጵያ" 3:30 ​📢 ፕሮግራሙ የሚተላለፍበት ቻናል፦ ➡️ ✈️https://t.me/nuredinal_arebi

«ያስደንቃል አባት» ---------------- ሁሉን የሚቀይር በአንድት የቃል ሀባ ልጁ ሰላም ነኝ ሲል የፊካ አበባ፡ ላንተ የተሰጠው ምን ተአምር ነው አባ⁉️ አባት የቻለውን፤ ነሚችል አባት ነው ሌላ የለም የትም፡ አባት ግን ዘወትር አይወራለትም፡ ሁሉም እናት ይላል አትመለከትም⁉️ የጥርስ አለመኖር ጉረሮን ላይከድነው፡ ግዙፍ ውለታውን ማንም ላይመጥነው፡ ባይወራለትም አባት ግን አባት ነው፡ ቤቱን የሚያደምቀው፤ እራሱን አፍዝዞ እንደቆዬ ቀለም፡ አምሮቱን ውጦ እንጂ፤ እንደ ሰው መብለጭለጭ ጠልቶትኮ አይደለም፡ በሆዱ ችሎ እንጅ፤ ሀዘኑን በደሉን አምቆ እሚከርመው፡ ጡትኮ አይወጣም አባት የረገመው፡ ማንም ሲበድለው፤ ነገውን በማሰብ እድሜውን ቢፈጅም፡ በአባት እንባ ላይ የተሰራ ህይወት ለማንም አይበጅም፡ በምኑ ይፅናና ጠቦ ሲያስቸግረው የኑሮ ሰንሰለት፡ ማልቀስኮ አይችልም በእንባ እንዳይወጣለት፡ እረፍት እያማረው፤ ሁልጊዜ ለራሱ ልፋት ቢሰርግም፡ አባት ልጁን እንጂ ጓደኛ አይፈልግም፡ ስለ አባት ለማውራት ፊደልን ሰድሮ፡ ስለ አባት ለመፃፍ ሀሳብን ወድሮ፡ አይበቃም አመታት አምናና ዘንድሮ፡ ስለ አባት ማንነት ለመተንተን በቃል፡ ከቆመበት ቦታ ካለበት ከፍታ መቆም ይጠይቃል፡ ከአባት እቅፍ መራቅ፤ በጣም ነው የሚያመው፡ ፈገግታው ብቻ ነው፤ መንፈስ የሚያክመው፡ ከአሏህ የተቸረ ብሩክ ልዩ ቅባት፡ ሰው የመሆን ቅኔ የግዙፍ ዛፍ ነባት፡ ልጄ ብቻ ሲለን ያስደንቃል አባት፡ ......ኑር..... http://t.me/nuredinal_arebi http://t.me/nuredinal_arebi

「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」 ╭───────── ┆ የኡስታዝ አቡ አምር ኑርየ ጎቤ ┆  የተመራረጡ ሙሀደራዎች  ╰───────────╯ ┌⧿⧿⛉ ├✓46 ሙሀደራዎች የያዘ ├✓279MB ብቻ ├╶╶╶ ├⎙አሁኑኑ ዳውንሎድ በማድረግ │ይጠቀሙ! │ ┝ለሌሎችም ሼር በማድረግ የአጅሩ │ተቋዳሽ ይሁኑ! └─────────── ┌╼──────────── ┢⎘  ለመሰል ስራዎች ይቀላቀላሉን ┃ ┡🖇http://t.me/Yusuf_App1 └╼────────────╯

7696357824041470738.mp37.70 KB

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 💫ታላቅ ብስራት 📍📌በመርከዝ ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል ሲሰጥ የነበረው የዑምደቱል አህካም ትምህርት በመጠናቀቁ ምክናየት 👉➛ቀጣይ عقيدة الواسط
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 💫ታላቅ ብስራት 📍📌በመርከዝ ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል ሲሰጥ የነበረው የዑምደቱል አህካም ትምህርት በመጠናቀቁ ምክናየት 👉➛ቀጣይ عقيدة الواسطية የዓቂደቱል ዋሲጥያ ትምህርት ሊጀመር ስለሆነ መርከዙ ለትንሽ ተማሪወች እዲል ሰጥቷል ፈጥናችሁ ተመዝገቡ አጋጣሚው ለትንሽ ተማሪወች ብቻ ነው ለመመዝገብ 📌📌📌📌📌📌📌📌📌 @Abu_hessan_aliy_yusuf @Abu_hessan_aliy_yusuf

#ከመርካቶ ከመርካቶ የተለያዩ የፕላስቲክ እና የቤት ዉስጥ እቃዎችን በብዛት ማዘዝ ስትፈልጉ ኑር ማርኬት ጋር ማግኘት ትችላላችሁ። 🛒 በጥራት 💵 በተመጣጣኝ ዋጋ 🚚 ያለ ምንም ውጣ ውረድ ያሉበት
+9
#ከመርካቶ ከመርካቶ የተለያዩ የፕላስቲክ እና የቤት ዉስጥ እቃዎችን በብዛት ማዘዝ ስትፈልጉ ኑር ማርኬት ጋር ማግኘት ትችላላችሁ። 🛒 በጥራት 💵 በተመጣጣኝ ዋጋ 🚚 ያለ ምንም ውጣ ውረድ ያሉበት ሀገር እንልካለን የቴሌግራም ሊንኩን በመጫን ቻናላችንን ይቀላቀሉ ➴➘➷ https://t.me/Noor_Market24 ስልክ 0965252565 ​🚨 በዚህ ዘርፍ ለተሰማሩ እህት ወንድሞች ሼር ያድርጉ

رسالة صوتية02:17

«ከኛ የለም ባንዳ» በእምነታችን ብቻ ነጥለው ሲጠሉን፡ ኢትዮጲያን የጋጧት እንደ ቆረቆንዳ፡ ከውጭ ሀይሎች ላይ ተቀብሎ አጀንዳ፡ የሀበሻ ምድር ታሪኳ ቢቀዳ፡ ሁሉም የነሱ ነው ከኛ የለም ባንዳ፡ እስኪ አንድ ጥቀሱ እኔ ልፈርበት፡ የትኛው ሙስሊም ነው በሀገር ያፌዘበት፡ ያውም ገፍታችሁት እየተጨቆነ፡ ሀገሩን ሊዋጋ መች ነው የወሰነ!? ስሙን እያያችሁ ስትጠሉት በእምነቱ፡ አሞራ ሲበላው ክቡር ሰውነቱ፡ ባንዳወቹ እናንተ ተወቃሾቹ እኛ፡ ሀገር ሻጭ እናንተ መተታም ቀማኛ፡ ጠባቦች እናንተ ክፉ መተተኛ፡ እስኪ እውነት ይነገር ይውጣ ከነ ጓዳው፡ መቼ ነው ሙስሊሙ ሀበሻን የከዳው⁉️ .....ኑር...

«በስማችን እና በኃይማኖታችን ብቻ መሰረት አድርገው "የግብፅ ተላላኪ" ሲሉን የነበሩ እና ራሳቸውን የሀገር ጠባቂ እና ባለ አደራ ነን ሲሊ የኖሩ፤ ዛሬ እነርሱ ዘንቢል አንጠልጥለው ግብፅን እየለመኑ ነው።» Jawar Mohammed 👌

አንዳንዴ... ምን ሆነሃል ስትባል የማትመልሰው ብዙ መሆን አለ። ለመናገር የማይመቹ፤ ለመተው የማይቀሉ ብዙ ስሜቶች አሉ ፤ ላንተ ብቻ የከበደ ለሌላው የቀለለ ነገር አለ። አንዳንዴ... ምን ሆነሃል ስትባል “ምንም!” ብለህ የምታልፈው በውስጥህ ብቻ የምትይዘው አንተ ብቻ የምትታመምበት ጉዳይ አለ። t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman

ለሀገራችን አሏህ ሰላሙን ያውርድልን። ➤ንጉስ ያላቸው #ንቦች ማር ይበላሉ። ንጉስ የሌላቸው #ዝንቦች ጥንብን ይልሳሉ t.me/nuredinal_arebi

رسالة صوتية02:57

1% እንኳን ተስፋ ካለህ፣ ሞክር‼️ ------------------------------ በጌታህ ተመካ በሀላልህ ጠንክር፡ ባገኘኸው ሽንቁር የቻልከውን ሞክር፡ ♦️#ጀግናዬ.... አውቃለሁ ምናልባት የምትፈልገው ነገር ከባድ ይሆናል። ምናልባት መንገዱ ረጅም ነው። ምናልባት ሌሎች አይቻልም ይሉህ ይሆናል። ግን ስማኝ ልምከርህ  አሁንም 1% እድል ካለ፣ ሳትሞክር ተስፋ አትቁረጥ! ስኬት አንዳንድ ጊዜ በትልቅ እርምጃ አይጀምርም ይልቁንስ ማንም በማያየው ትንሽ ውሳኔ ይጀምራል። ዛሬ መሞከር፣ ነገ መማር፣ ከዚያም እንደገና መነሳት። አንድ ጊዜ ልትወድቅ ትችላለህ፤ ይህ ግን ለዘላለም እንደማታሳካ አያረጋግጥም። ስህተትህን ተማርበት፣ አቅጣጫህን አስተካክልና ጉዞህን ቀጥል.............. አዎ፣ ሁሉም ነገር በጥረት ብቻ አይሳካም። ግን ሳትሞክር የሚቻለውን እድል ማግኘትህ አይቀርም። አንድ ትንሽ ተስፋ፣ አንድ የድፍረት እርምጃ፣ አንድ ተጨማሪ ሙከራ… የሚቀጥለውን ታሪክህን ሊቀይረው ይችላል! 🔥እድል ካገኘህ ሞክር። ከወደቅክ ተማር። ከተማርክ እንደገና ተነስ! በሁሉም እንቅስቃሴህ ላይ ግን አሏህን አትርሳ አደራ‼️ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

ሴት የማህበረሰቡ ግማሽ ነች፡፡ ቀሪውን ግማሽ ደግሞ ትወልዳለች፡፡ ስለሆነም የሷ መስተካከል የኡማው መስተካከል ነው፡፡ ጥፋቷም የህዝብ ጥፋት፡፡ ስትስተካከል ዓኢሻኛ ታወራለች፤ ሐምዛን ትወልዳለች፤ ፋጢማን ለዐልይ ታዘጋጃለች፤ ድንቅ ለሆነ የማህበረሰብ ግንባታ የማይነቃነቅ መሠረት ትሆናለች፡፡ ስትጠፋም ታዲያ አይጣል ነው፡፡ አጥፍቶ ጠፊ! በየጥጉ የተለጠፉ ራቁት ምስሎች ሁሉ የሷ መፈክር ይመስሏታል፡፡ ራቁት በሆነች ቁጥር የበለጠ “ነፃነት” ይሰማታል፡፡ ከአቡ ለሀብ ጋር ተጣምራ “ሐማለተል ሐጦብ” ሆና፣ ሻሮኖችን ፈልፍላ ራይስኛ ፈንጥዛ፣ ቡሽኛ ሂወት እየመራች ሁሉንም ይዛ ወደ ገደል! ያ ረቢ አንተ እህቶቻችንን የነ ዓኢሻን ምሳሌ የሚከተሉ አድርግል፡፡ (ኢብኑ ሙነወር፣ 2001) = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

«ባይሆን ደስ ይለኝ ነበር» ......ግን ሆነ..ተከናወነ...በስ‼️ እንዲህ ባይሆን ደስ ይለኝ ነበር ። ስንማር ካነበብናቸው #መፅሐፍ ላይ ያየናቸው ክፉ ገፀ-ባህሪያት ሩቅ የመሰሉን...#ጓደኞቻችን ሆነው ባያስገርሙን ደስ ይለኝ ነበር፤ ብቻ መፅሐፍ እና ፊልሞች የውሸት ናቸው ብለን እንዳሰብነው እንደዛው ውሸት ቢሆን ደስ ይለኝ ነበር። ....ግና በተግባር ሆነ እጃችንን በአፋችን ጭነን #ሱብሀነክ ብለን ፀጥ አልን። ...እንድንታገስ ያደረከን ጌታ ሆይ ምስጋና ይግባህ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

🕌 የደሴ መስጂደ አስ-ሱና የእርዳታ ጥሪ! ዛሬ የምናበረክተው የነገውን የዕውቀት ብርሃን ለማስፋት ነው! በአላህ ፈቃድ የሚተላለፍ የዒልም ብርሃን፤ ከዱንያ ሕይወታችን በኋላም የሚቀጥል ሰደቀተል ጃሪያ ነው! 📢 ለዓለም ዙሪያ ለምትገኙ ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሙሉ የተላለፈ የኸይር ጥሪ! በደሴ ከተማ የሰለፊዮች ዐይን ፣ የሱና ብርሃን መፍለቂያ እና የቁርአንና የሸሪዓ ዕውቀት መማሪያ የሆነችው መስጂደ አስ-ሱና ዛሬ በእናንተ እገዛ የሚታሰብ ታሪክ ለመሥራት በር ከፍታለች! በቅርብ ጊዜ ይህ መስጂድ በትንሽ ቦታ፣ ቆርቆሮ በቆርቆሮ በትንሽ ቦታ ላይ ፣ በትንሽ አቅምና በታላቅ ተስፋ ተጀመረች። በሸይኽ መሐመድ መኪን መሪነት የተለያዩ ቂርኣቶች፣ የዳዕዋ ፕሮግራሞች፣ የዒልም ደርሶችና የኮርስ ትምህርቶች ሲሰጡባት ቆይተዋል። በዚያ ትንሽ ቦታ ውስጥ የአላህ ቃል ተነብቧል፤ የነቢዩ ﷺ ሱና ተምሯል፤ የዒልም ተማሪዎች ተቀምጠዋል፤ የብዙ ሕፃናትም ልብ በቁርአን ብርሃን እንዲበራ ጥረት ተደርጓል። ነገር ግን፣ አልሐምዱ ሊላህ! ዛሬ በዚህች መስጂድ የሚቀሩ ሕፃናት ቁጥር እጅግ ጨምሯል። ይህ የሚያስደስት የኸይር ዜና ቢሆንም፣ የሚማሩበት ቦታ መድረሳ ጠባብ በመሆኑ ትልቅ ፈተና ሆኗብናል። ዛሬ በዚያ ጠባብ መድረሳ ውስጥ የሚቀመጡት ሕፃናት የነገው የኡማችን ተስፋዎች ናቸው። ከእነርሱ መካከል የቁርአን ሐፊዞች፣ የሐዲስ ዕውቀት ተሸካሚዎች፣ የሱና ጥሪ አስተላላፊዎችና ለእስልምና የሚጠቅሙ የዒልም ሰዎች ሊወጡ ይችላሉ። እነዚህ ሕፃናት የአላህን መጽሐፍ በሰፊ ቦታ፣ በተመቻቸ አካባቢና በተሻለ የመማሪያ ሁኔታ እንዲማሩ ማድረግ የእኛ የዛሬ ኃላፊነት ነው። ⚠️ ወዳጆቻችን ሆይ! የዚህ ታላቅ ኸይር ተባባሪዎች እንሁን! የመስጂደ አስ-ሱናን የመማሪያ ቦታ ለማስፋፋት፣ ሕፃናቱ የሚቀሩበትን መድረሳ ለማሻሻልና የቁርአንና የሱና ትምህርት የበለጠ እንዲስፋፋ ለማድረግ የእናንተን ድጋፍ እንሻለን። አንዳንዶቻችን ብዙ ልናዋጣ እንችላለን፤ ሌሎቻችን ደግሞ ትንሽ ልናዋጣ እንችላለን። ነገር ግን በአላህ ዘንድ የሚቀበለው በቁጥር ብቻ የሚለካ ሳይሆን በኢኽላስና በመልካም ዓላማ የሚመዘን ነው። በትንሽ አቅማችሁ ትልቅ ለውጥ ማምጣት ትችላላችሁ! አንድ ሕፃን በእናንተ ድጋፍ ቁርአንን በትክክል ቢያነብ፣ አንድ ተማሪ ትክክለኛ የዲኑን ዕውቀት ቢያገኝ፣ አንድ ልጅ የተማረውን ዕውቀት ለሌሎች ቢያስተላልፍ፣ የእናንተ እገዛ በዚህ መልካም ሥራ ውስጥ ድርሻ እንዲኖረው አላህ ሊያደርግ ይችላል። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «إِذَا مَاتَ الْإِنْسَانُ انْقَطَعَ عَنْهُ عَمَلُهُ إِلَّا مِنْ ثَلَاثَةٍ: إِلَّا مِنْ صَدَقَةٍ جَارِيَةٍ، أَوْ عِلْمٍ يُنْتَفَعُ بِهِ، أَوْ وَلَدٍ صَالِحٍ يَدْعُو لَهُ». “የሰው ልጅ በሞተ ጊዜ ሥራው ይቋረጣል፤ ከሦስት ነገሮች በስተቀር፦ የሚቀጥል ሰደቃ፣ ከእርሱ የሚጠቀምበት ዕውቀት፣ ለእርሱ ዱዓ የሚያደርግ መልካም ልጅ።” 📚 ሰሒሕ ሙስሊም፣ 1631 ወንድሞችና እህቶች ሆይ! ዛሬ በመስጂድ ማስፋፊያ ላይ የምናዋጣው ገንዘብ የዛሬ ድጋፍ ብቻ አይደለም። በዚያ ቦታ ቁርአን ሲነበብ፣ የአላህ ዲን ሲማር፣ ልጆች ሲያድጉና የሚጠቅም ዕውቀት ሲተላለፍ፣ አላህ ከምሕረቱ ድርሻ እንዲያደርግልን የምንሻበት ታላቅ እድል ነው። እኛ እዚህ ምድር ላይ ለዘላለም አንኖርም። ነገር ግን በኢኽላስ የተሠራ መልካም ሥራ አላህ ከተቀበለው፣ ከሞታችን በኋላም የምንጠብቀው የኸይር ምክንያት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ዛሬ የምንችለውን እናድርግ፤ የምንችለውን እናዋጣ፤ ሌሎችም እንዲሳተፉ እንጋብዝ። ምናልባት በእኛ የተነሳ የአላህ ዲን የሚማሩ ልጆች ቁጥር ይጨምር ይሆናል። ⚠️ዛሬ የእናንተ ድጋፍ የእነዚህ ሕፃናት ተስፋ ነው! 🌍 በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በዓለም ዙሪያ ለምትኖሩ ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን፦ በዚህ የኸይር ሥራ ላይ የቻላችሁትን ያህል ድጋፍ እንድታደርጉልን በአላህ ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን። የምትሰጡት ትንሽ ቢመስልም አትናቁት። የምታደርጉት ድጋፍ በአላህ ፈቃድ ለብዙ ሕፃናት የዒልም መንገድ ሊያመቻች ይችላል። ካልቻላችሁ ደግሞ ይህን ጥሪ ለሌሎች በማድረስ ተባበሩን። የኸይርን መንገድ የሚያመለክትም ከሠሪው ምንዳ ያገኛል። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 🏦 የመስጂደ አስ-ሱና የባንክ ሂሳቦች 💳 1. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) 1000469830277 💳 2. ዘምዘም ባንክ 0005649620101 💳 3. ሂጅራ ባንክ 1000030300001 📌 ከላይ የተጠቀሱት የባንክ ሂሳቦች በመስጂደ አስ-ሱና ስም የተመዘገቡ ናቸው። ስለ መስጅዱ ሙሉ መረጃ ለማገኘትና ለመጠየቅ ስልክ፦+251914718693 ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📣 ይህን መልእክት ሼር በማድረግ ለመስጂደ አስ-ሱና ማስፋፊያ የሚያግዙ ወንድሞችና እህቶች እንዲደርሱ እንርዳ! 🕌 በመስጂደ አስ-ሱና — ላይ የማናደርገው የዛሬው ድጋፋችን፣ የነገው የዒልም ብርሃን ያሰፋል!

ታላቅ የሙሓደራና የኒያ ፕርግራም እለተ ሀሙስ ጥቅምት 5 ቀን 2019 በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ቤደር ከተማ ለሚገነባው አል ሂዳያ መርከዝ የገቢ ማሰባሰቢያና የሙሓደራ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል። የእለ
ታላቅ የሙሓደራና የኒያ ፕርግራም እለተ ሀሙስ ጥቅምት 5 ቀን 2019 በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ቤደር ከተማ ለሚገነባው አል ሂዳያ መርከዝ የገቢ ማሰባሰቢያና የሙሓደራ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል። የእለቱ ተጋባዥ ኡስታዞች ❶ኡስታዝ አቡ ሉቅማን ❷ኡስታዝ አቡ ፈውዛን አብድሽኩር ❸ኡስታዝ አቡ ሂበቲላህ ሑሰይን ❹ኡስታዝ አቡ ኡሰይሚን አብዱረሕማን ❺ኡስታዝ አቡ አዩብ የፕሮግራም መሪዎች ❶ መሀመድ ሲራጅ አል-ኬሚሴ ❷ አቡ ሁዘይፋ(ሀይደር) 📆ቀን የፊታችን ሀሙስ ⏱ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ መርከዙ ከአላህ በታች በእናንተው ርብርብ ተጀምሯል። ነገር ግን አሁን ላይ እጃችን ላይ የነበረው ገንዘብ አልቆ ስራው ሊቆም ነው። ይህ መርከዝ እውን ሆኖ ተማሪዎችን መቀበል እንዲጀምር የሁላችንም ትብብር ያስፈልጋል። ፕሮግራሙ የሚቀርብበት ቻናል t.me/Achachir_mkroch የመርከዙ የቴሌግራም ግሩፕ t.me/+h5YVkNAk55hkYWI8 ⤴️ ሼር አድርጉት

ما أجمل الحديث مع الله! 🤍 ♦️ከአሏህ ጋር መነጋገር እንዴት ደስ ይላል‼️ أن تجلس في هدوء الليل، أو في نهاية يومك، فتُقبل على الله بقلبك، وتُخبره بكل ما في صدرك، بما أسعدك وما أحزنك، بما تخشاه وما ترجوه، بما عجزت عن البوح به للخلق، وما لا تستطيع حتى أن ترتّب كلماته في قلبك. በሌሊቱ ጸጥታ በሰፈነ ጊዜ ወይም በቀኑ መጨረሻ ላይ ቁጭ ብለህ ወደ አሏህ ዞር ብለህ በልብህ ውስጥ ያለውን ሁሉ፣ ምን እንዳስደሰተህና፣ ምን እንዳሳዘነህ፣ ምን እንዳስፈራህ፣ ምን እንደምጠብቅ ...ለሰዎች መግለጽ ያልቻልክበትን እና በልብህ ውስጥ ያሉትን ቃላት እንኳን ማዘጋጀት የማትችለውን ነገር #ለሀያሉ አምላክ መንገር። ያ አሏህ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi