شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 شـبـاب السـلــفـــيـــيــن 的分析概览
频道 شـبـاب السـلــفـــيـــيــن (@nuredinal_arebi) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 28 175 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 2 563,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 1 295 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 28 175 名订阅者。
根据 16 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -251,过去 24 小时变化为 -12,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 13.19%。内容发布后 24 小时内通常能获得 6.66% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 719 次浏览,首日通常累积 1 877 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 35。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“👉«ሰለፍያ ቀጥተኛ የሀቅ መንገድ ብሎም አይነኬ ፅኑ ተራራ ነው።»
ለአስተያዬትና እርማት”
凭借高频更新(最新数据采集于 17 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
28 175
订阅者
-1224 小时
-837 天
-25130 天
帖子存档
👉የበሳል ሚስት መገለጫዎች‼️
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
«ትዳር የወንድ ልጅ ሀላፊነት ብቻ የሚመስላቸው የዋሆች ትዳርን አያውቁትም ይልቁንም ትዳር #የሴት ልጅ የጥበባዊነት መለኪያ ነው።
🔸ከጠባብነት ርቃ ጠቢብነትን የተላበሰች ጀግና ሴት ለትዳር ደርሳለች።
«.....ለትዳር ዝግጁ የሆነች ሴት መገለጫዋ የሚከተሉት ናቸው።»
🔸ባሏን ታከብራለች የማክበሯ ምልክት ሲያጠፋ የምትሔድበት መንገድ ይወስነዋል።
🔸ስሜቷን ትቆጣጠራለች።
🔸በቁጣ ጊዜ ውሳኔ አታሳርፍም።
🔸አለመግባባትን በአክብሮት ታስረዳለች።
🔹ስህተቷን ትቀበላለች።
🔹ይቅርታ መጠየቅም ትችላለች።
🔹ችግርን በዝምታ ወይም በኩርፊያ ወይም በበቀል ሳይሆን በውይይት ለመፍታት ትሞክራለች።
♦️ትዳሯን በሚስጥር ትይዘዋለች።
♦️የባሏን ድክመት ለማንም አታጋልጥም።
♦️ባሏን ታደንቀዋለች።
♦️የባሏን መልካምነት ታስተውላለች።
🔸የሚያስፈልጋትን ለባሏ በግልፅ ትናገራለች።
✅በቤተሰብና በጓደኞች ጉዳይ ጤናማ ድንበር ታደርጋለች።
🔸ባሏን ከሌሎች ወንዶች ጋር አታወዳድርም።
🔸የትዳሯን ድንበር ትጠብቃለች።
✅ችግር ሲመጣ «እኔ እና አንተ» ሳይሆን «እኛ እና ችግሩ»ብላ ትመለከታለች።
🔹ራሷን ለባሏ ታስዋለች።
🔹ባሏን ታከብረዋለች፡፡
✅በፍቅር ብቻ ሳይሆን በሀላፊነት በትዕግስትና በመማር ትዳሯን ትገነባለች።
👉....ማሳሰቢያ‼️
መልካም ሚስት ማለት ፍፁም ሚስት ማለት ሳይሆን ስህተቷን ተረድታ ራሷን ለማሻሻል የምትማር እንቁ ማለት ነች።
....ኑረዲን አል-ዓረብ..✍️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
«ከሆዴ አስገብቻት»
----------------------
በግ መስሎኝ በልቼ የዱር አውሬ ስጋ፡
ሆደን እያመመኝ ሲያስታውከኝ ነጋ፡
ህመሙ ከባድ ነው ባይሰጥም ላደጋ፡
ስጋው ተመርዞ በማላውቀው ነገር፡
ምቀኛው በርክቶ በዚህች የጉድ ሀገር፡
ወደ ስኬት ማማ እንደት እንሻገር!?
ወንድ ልጅ እንደ ሴት ነገር ካላመጠ፡
የወንድሙን ፀጋ ለሱ ከቋመጠ፡
እምድጃ ለምድጃ ከተርመጠመጠ፡
ምኑን ወንድ ሆነው ክብሩ ከተላጠ፡
ከነገ ህልሙ ላይ ተስፋ ከቆረጠ፡
የታገሰ ሁሉ መናገር ሲጀምር፡
ወዳጅ ላለው ወንድም ሴራውን ሲቀምር፡
ቂጡን መውጋት ነበር ያናድዳል የምር‼️
የዱር አውሬ ስጋ የበግ መስላ ገብታ፡
የውስጤ ላይ ፈጥራ ተራራ ጉብታ፡
ውስጤ ሰላም ጠፍቷል ትረብሸኛለች፡
ስወጣም ስገባም ታሳምመኛለች፡
የበግ ስጋ መብላት ይሆናል ወይ ስጋት፡
ምነው ከልቤ ላይ ተከለብኝ ውጋት፡
ልቤ ብልጥ እንድቶን እስኪ ምን ላድርጋት፡
ይሁን ብዬ በላሁ መቼም አይሰለቻት፡
ምን አደርጋታለሁ እስኪ እሷን ይመቻት፡
ማንነቷን ሳላውቅ ከሆደ አስገብቻት፡
.....ኑር...✍️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
ሁሉም ህዝብ በሚገለገልበት መንግስታዊ ተቋም ውስጥ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በመገንባት ስብከት እያካሄዱ ነው። የፈፀሙት ጥፋት አልበቃ ብሎ ጭራሽ መከራከር ምን የሚሉት እብሪት ነው? ይሄ የታየው ነው። በዚህ አይነት ስንት ለሚዲያ ያልበቃ ጥፋት ይኖራል? የሚመለከተው ክፍል የችግሩ አካል መሆኑ ነው እንዲህ የልብ ልብ የሰጣቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
👉ስትሸከሙት እንደ ጅል ለሚያያችሁ ላኩለት‼️
«በድንበርህ እርጋ!!»
----------------------
ወዳጄ ነው ብዬ በብዛት ታገስኩት፡
አብረን በላንና ቢነክሰኝም ሳምኩት፡
ደግ ሁን ተብዬ ነውና ያደኩት፡
ክፉ መሆንን ነው እስካሁን ያልቻልኩት፡
.....ግና...
ሁሌ አልኖርምና መንጋ ውሻ ሳግድ፡
ያንን ውሻ ተውኩት ብወደውም በግድ፡
ከእንግድህ አይመጣም እኔን የሚሰብር፡
መውደድ ምን ይሰራል ከሌለበት ክብር፡
ነገር አታማስል እዚህና እዛጋ፡
ከላይ ከታች አትበል ከቆላ ከደጋ፡
አንተን ላልመሰለው አትለጥፍ ታርጋ፡
በቅዠትህ አልም በድንበርህ እርጋ፡
...በኑር...✍️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
🔴 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🔴
✨ ✨
ልዩና ያማረ የሰርግ ፕሮግራም አዘጋጅተንላችኋል።
🎙️ የፕሮግራሙ መሪዎች (አቅራቢዎች)
❶ ኑረዲን አል-አረቢ
❷ አቡ ሁዘይፋ
🌟 የዕለቱ ተጋባዥ እንግዶችና ኡስታዞች 🌟
❶ ሸይኽ አቡ-ሀኒፋ (ከገርባ)
❷ ኡስታዝ ፉዓድ ሙሀመድ
❸ ኡስታዝ አቡ-ሐሳን
❹ ኡስታዝ አቡ ሒበቱሏህ
❺ ኡስታዝ አቡ ሻኪራ
❻ ኡስታዝ ጦይብ አህመድ (ከአሶሳ)
💡 እንዲሁም ስማቸው ያልተጠቀሱ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ኡስታዞችና እንግዶችም ይገኛሉ፤ እንዳያመልጥዎ!
🕒 የፕሮግራሙ ሰዓት
🇸🇦 በሳዑዲ" 8:30
🇦🇪 በዱባይ" 9:30
🇪🇹 በኢትዮጵያ" 3:30
📢 ፕሮግራሙ የሚተላለፍበት ቻናል፦ ➡️ ✈️https://t.me/nuredinal_arebi
«ያስደንቃል አባት»
----------------
ሁሉን የሚቀይር በአንድት የቃል ሀባ
ልጁ ሰላም ነኝ ሲል የፊካ አበባ፡
ላንተ የተሰጠው ምን ተአምር ነው አባ⁉️
አባት የቻለውን፤
ነሚችል አባት ነው ሌላ የለም የትም፡
አባት ግን ዘወትር አይወራለትም፡
ሁሉም እናት ይላል አትመለከትም⁉️
የጥርስ አለመኖር ጉረሮን ላይከድነው፡
ግዙፍ ውለታውን ማንም ላይመጥነው፡
ባይወራለትም አባት ግን አባት ነው፡
ቤቱን የሚያደምቀው፤
እራሱን አፍዝዞ እንደቆዬ ቀለም፡
አምሮቱን ውጦ እንጂ፤
እንደ ሰው መብለጭለጭ ጠልቶትኮ አይደለም፡
በሆዱ ችሎ እንጅ፤
ሀዘኑን በደሉን አምቆ እሚከርመው፡
ጡትኮ አይወጣም አባት የረገመው፡
ማንም ሲበድለው፤
ነገውን በማሰብ እድሜውን ቢፈጅም፡
በአባት እንባ ላይ የተሰራ ህይወት ለማንም አይበጅም፡
በምኑ ይፅናና ጠቦ ሲያስቸግረው የኑሮ ሰንሰለት፡
ማልቀስኮ አይችልም በእንባ እንዳይወጣለት፡
እረፍት እያማረው፤
ሁልጊዜ ለራሱ ልፋት ቢሰርግም፡
አባት ልጁን እንጂ ጓደኛ አይፈልግም፡
ስለ አባት ለማውራት ፊደልን ሰድሮ፡
ስለ አባት ለመፃፍ ሀሳብን ወድሮ፡
አይበቃም አመታት አምናና ዘንድሮ፡
ስለ አባት ማንነት ለመተንተን በቃል፡
ከቆመበት ቦታ ካለበት ከፍታ መቆም ይጠይቃል፡
ከአባት እቅፍ መራቅ፤
በጣም ነው የሚያመው፡
ፈገግታው ብቻ ነው፤
መንፈስ የሚያክመው፡
ከአሏህ የተቸረ ብሩክ ልዩ ቅባት፡
ሰው የመሆን ቅኔ የግዙፍ ዛፍ ነባት፡
ልጄ ብቻ ሲለን ያስደንቃል አባት፡
......ኑር.....
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」
╭─────────
┆ የኡስታዝ አቡ አምር ኑርየ ጎቤ
┆ የተመራረጡ ሙሀደራዎች
╰───────────╯
┌⧿⧿⛉
├✓46 ሙሀደራዎች የያዘ
├✓279MB ብቻ
├╶╶╶
├⎙አሁኑኑ ዳውንሎድ በማድረግ
│ይጠቀሙ!
│
┝ለሌሎችም ሼር በማድረግ የአጅሩ
│ተቋዳሽ ይሁኑ!
└───────────
┌╼────────────
┢⎘ ለመሰል ስራዎች ይቀላቀላሉን
┃
┡🖇http://t.me/Yusuf_App1
└╼────────────╯
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
💫ታላቅ ብስራት
📍📌በመርከዝ ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል ሲሰጥ የነበረው የዑምደቱል አህካም ትምህርት በመጠናቀቁ ምክናየት
👉➛ቀጣይ عقيدة الواسطية
የዓቂደቱል ዋሲጥያ ትምህርት ሊጀመር ስለሆነ
መርከዙ ለትንሽ ተማሪወች እዲል ሰጥቷል ፈጥናችሁ ተመዝገቡ
አጋጣሚው ለትንሽ ተማሪወች ብቻ ነው
ለመመዝገብ
📌📌📌📌📌📌📌📌📌
@Abu_hessan_aliy_yusuf
@Abu_hessan_aliy_yusuf
+9
#ከመርካቶ
ከመርካቶ የተለያዩ የፕላስቲክ እና የቤት ዉስጥ እቃዎችን በብዛት ማዘዝ ስትፈልጉ ኑር ማርኬት ጋር ማግኘት ትችላላችሁ።
🛒 በጥራት
💵 በተመጣጣኝ ዋጋ
🚚 ያለ ምንም ውጣ ውረድ ያሉበት ሀገር እንልካለን
የቴሌግራም ሊንኩን በመጫን ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➴➘➷
https://t.me/Noor_Market24
ስልክ 0965252565
🚨 በዚህ ዘርፍ ለተሰማሩ እህት ወንድሞች ሼር ያድርጉ
«ከኛ የለም ባንዳ»
በእምነታችን ብቻ ነጥለው ሲጠሉን፡
ኢትዮጲያን የጋጧት እንደ ቆረቆንዳ፡
ከውጭ ሀይሎች ላይ ተቀብሎ አጀንዳ፡
የሀበሻ ምድር ታሪኳ ቢቀዳ፡
ሁሉም የነሱ ነው ከኛ የለም ባንዳ፡
እስኪ አንድ ጥቀሱ እኔ ልፈርበት፡
የትኛው ሙስሊም ነው በሀገር ያፌዘበት፡
ያውም ገፍታችሁት እየተጨቆነ፡
ሀገሩን ሊዋጋ መች ነው የወሰነ!?
ስሙን እያያችሁ ስትጠሉት በእምነቱ፡
አሞራ ሲበላው ክቡር ሰውነቱ፡
ባንዳወቹ እናንተ ተወቃሾቹ እኛ፡
ሀገር ሻጭ እናንተ መተታም ቀማኛ፡
ጠባቦች እናንተ ክፉ መተተኛ፡
እስኪ እውነት ይነገር ይውጣ ከነ ጓዳው፡
መቼ ነው ሙስሊሙ ሀበሻን የከዳው⁉️
.....ኑር...
«በስማችን እና በኃይማኖታችን ብቻ መሰረት አድርገው "የግብፅ ተላላኪ" ሲሉን የነበሩ እና ራሳቸውን የሀገር ጠባቂ እና ባለ አደራ ነን ሲሊ የኖሩ፤ ዛሬ እነርሱ ዘንቢል አንጠልጥለው ግብፅን እየለመኑ ነው።»
Jawar Mohammed 👌
Repost from نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے
አንዳንዴ... ምን ሆነሃል ስትባል የማትመልሰው ብዙ መሆን አለ። ለመናገር የማይመቹ፤ ለመተው የማይቀሉ ብዙ ስሜቶች አሉ ፤ ላንተ ብቻ የከበደ ለሌላው የቀለለ ነገር አለ።
አንዳንዴ... ምን ሆነሃል ስትባል “ምንም!” ብለህ የምታልፈው በውስጥህ ብቻ የምትይዘው አንተ ብቻ የምትታመምበት ጉዳይ አለ።
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
ለሀገራችን አሏህ ሰላሙን ያውርድልን።
➤ንጉስ ያላቸው #ንቦች ማር ይበላሉ።
ንጉስ የሌላቸው #ዝንቦች ጥንብን ይልሳሉ
t.me/nuredinal_arebi
1% እንኳን ተስፋ ካለህ፣ ሞክር‼️
------------------------------
በጌታህ ተመካ በሀላልህ ጠንክር፡
ባገኘኸው ሽንቁር የቻልከውን ሞክር፡
♦️#ጀግናዬ....
አውቃለሁ ምናልባት የምትፈልገው ነገር ከባድ ይሆናል።
ምናልባት መንገዱ ረጅም ነው።
ምናልባት ሌሎች አይቻልም ይሉህ ይሆናል።
ግን ስማኝ ልምከርህ አሁንም 1% እድል ካለ፣ ሳትሞክር ተስፋ አትቁረጥ!
ስኬት አንዳንድ ጊዜ በትልቅ እርምጃ አይጀምርም ይልቁንስ ማንም በማያየው ትንሽ ውሳኔ ይጀምራል።
ዛሬ መሞከር፣
ነገ መማር፣
ከዚያም እንደገና መነሳት።
አንድ ጊዜ ልትወድቅ ትችላለህ፤
ይህ ግን ለዘላለም እንደማታሳካ አያረጋግጥም።
ስህተትህን ተማርበት፣
አቅጣጫህን አስተካክልና ጉዞህን ቀጥል..............
አዎ፣ ሁሉም ነገር በጥረት ብቻ አይሳካም። ግን ሳትሞክር የሚቻለውን እድል ማግኘትህ አይቀርም።
አንድ ትንሽ ተስፋ፣
አንድ የድፍረት እርምጃ፣
አንድ ተጨማሪ ሙከራ… የሚቀጥለውን ታሪክህን ሊቀይረው ይችላል!
🔥እድል ካገኘህ ሞክር።
ከወደቅክ ተማር።
ከተማርክ እንደገና ተነስ!
በሁሉም እንቅስቃሴህ ላይ ግን አሏህን አትርሳ አደራ‼️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
