cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . #ዝማሬ_ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

إظهار المزيد
Advertising posts
135 648المشتركون
+12524 hour
+3457 يوم
+80030 يوم

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

“በዐቢይ ጾም መጀመሪያ ሱባኤ ፀሐይ እስኪገባ ይጹሙ፣ ሌሎቹን ሳምንታት እስከ 11 ሰዓት ይጹሙ፥ በሰሙነ ሕማማት ግን ኮከብ እስኪወጣ ይጹሙ” ብለዋል። (ፍት.ነገ.አን 15፥595)። ፍትሐ ነገሥት ቁጥር 578 ላይ ደግሞ “(የሰሙነ ሕማማትን) ዓርብንና ቅዳሜን ግን ሁለቱንም በአንድነት ይጹሟቸው፣ የሚችል እስከ ሌሊት ዶሮ ጩኸት ድረስ ምንም ምን አይቅመስባቸው፣ ሁለቱን በአንድነት መጾም የማይቻለው ግን ቅዳሜን ይጹም” ተብሎ ህግ ተሠርቷል። 👉 @ortodoxmezmur
إظهار الكل...
87🕊 2🥰 1
ሕማማት ክፍል 2 👉 ይሁዳ የመረጠው ጌታ ✍ ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ 🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
إظهار الكل...
ሼር ያድርጉ 🔺
ሕማማት ክፍል 1 👉 የመጀመሪያው ቁስል! አሳልፎ የሚሰጥህ ማነው? ✍ ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ 🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ #ሼር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
إظهار الكل...
21
ሼር ያድርጉ 🔺
​​​​​​በሰሞነ ሕማማት የሚጸለዩት እና የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው? ሼር በማድረግ ለወዳጆቻችሁ አድርሱ አሳውቁ! ከነገ ጀምሮ የጌታችንን ሕማም የምናስብበት ሰሞን ነው። እንደ ቅድስት ቤተ-ክርስትያናችን ሥርዓት በዚህ በሰሞነ ሕማማት የምንጸልያቸውና ለጊዜው የምንታቀባቸው ጸሎቶች አሉ። 👉 በሰሞነ ሕማማት የምንጸልያቸው ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው? በሰሞነ ሕማማት አጥብቀን የምንጸልያቸው ጸሎቶች ውዳሴ ማርያም:ዳዊት: ሰይፈ ሥላሴ:ሰይፈ መለኮት:ድርሳነ ማሕየዊ ውዳሴ አምላክ ናቸው። እመቤታችን ድንግል ማርያም በዚህ በሰሞነ ሕማም በልጅዋ ምክንያት ብዙ እንግልት ስለደረሰባት የእሷን ምስጋና የሆነውን ውዳሴ ማርያም አናስታጉልም። ውዳሴ ማርያም ማመስገኛ መማጸኛ ስለሆነ እንጸልያለን። ምክንያቱም በዚህ በሰሞነ ሕማማት መከራ ተቀብሎ ሞቶ ሕይወቱን የሰጠንን ጌታ በሥጋ ወልዳለችን በውዳሴዋ እናስባታለን። የቅዱስ ዳዊት ድርሰት የሆነው ታላቁ መዝሙረ ዳዊት በትንቢት ክፍሉ ስለ ጌታችን ሕማም ስቃይ እና ሞት የሚናገርና በዳዊት ምስጋና በምድር የሰው ልጆች በሰማይ ቅዱሳን መላእክት ስለሚያመሰግኑ እንጸልየዋለን። ሰይፈ ሥላሴ ከሦስቱ አካላት እግዚአብሔር ወልድን የሚያመሰግን አምላክነቱን የሚመሰክር እና የሚመሰጥር በመሆኑ እንጸልየዋለን። ሰይፈ መለኮት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ስለ ምስጢረ መለኮት እና ስለ ጌታችን አምላክነት ስለሚናገር እንጸልየዋለን። ድርሳነ ማሕየዊ በቅዱስ ዮሐንስ ወልደ-ነጎድጓድ የዓይን እማኝነት እና የቃል ምስክርነት የተጻፈና የጌታችንን መከራ ስቃይ እንግልት እና ሞት በልዩ ሁኔታ የሚናገር በመሆኑ ልክ እንደ ውዳሴ ማርየም የየእለት/የየቀን ስላለው ብንጸልየው በዓይነ ሕሊና ቀራንዮ ወሰዶ በነፍሳችን የጌታችንን ሰማያዊ ውለታ የሚስልብንና በመጸለያችን ልዩ ጸጋና ክብር የሚያሰጥ የቃል-ኪዳን ጸሎት በመሆኑ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ብንጸልየው እጅጉን እንጠቀምበታለን። ውዳሴ አምላክም የጌታችን ምስጋና በመሆኑ መጸለይ እንችላለን። 👉 በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው? በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩትን ጸሎቶች ጠቅለል አድርገን ስናያቸው ድርሳናት ገድላት እና መልካ መልኮች ናቸው። ይህም የሆነው በሰሞነ ሕማማት ጌታችን ለእኛ ለሰው ልጆች ብሎ የተቀበላቸውን ስቃይ እና መከራ ሞት የምናስብበት እና የምናለቅስበት እንጂ ሌሎቹን በድርሳናቸው በገድላቸው በመልካቸው የምናመሰግንበት ጊዜ ስላልሆነ ነው። በተረፈ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ለራሳችሁ ለሀገራችሁ ብቻ አትጸልዩ ለዓለም ሕዝብ ለአሕዛብ በሙሉ ጸልዩ። ምክንያቱም ለእነሱ የመጣ ሰማያዊ ቁጣ በቀጥታም በተዘዋዋሪም ለእኛም ይተርፋልና። እነሱ ሲለበለቡ እኛ መቃጠላችን እነሱ ሲሰበሩ እኛ ወለም ማለታችን እነሱ ሲሞቱ ሞት ደጃፋችን መቆምን በማሰብ ለእነሱም እንጸልይ። የእነሱ መከራ ሲርቅ ነው የኛም የሚርቀው። 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
إظهار الكل...

182🥰 7🕊 5
👉 ሆሣዕና 👉 የዐብይ ጾም ስምንተኛ ሳምንት 🎤 በመ/ር ዶ/ር ዘበነ ለማ #ሼር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
إظهار الكل...
35🕊 7🤬 1
ሰላምሽ ዛሬ ነው ሰላምሽ ዛሬ ነው እየሩሳሌም ወደአንች መጥቷልና አምላክ ዘላአለም/2/  ሆሣእና በአርያም እያሉ ዘመሩ  ሕፃናት በኢየሩሳሌም  አንቺ ቤተልሄም የዳዊት ከተማ የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/2 / ኪሩቤል መንበሩን የሚሸከሙለት መስቀል ተሸከመ ሊሆነን መድኃኒት /2 / የኢየሱስን ሕማም ደናግልም አይተው እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው /2/  💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
إظهار الكل...
21🔥 1🥰 1🕊 1
1/08/15 ዓ.ም መዝሙር ዘሆሳዕና "ወእንዘ ሰሙን" ✝ በዕለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚሰበክ ምስባክ። ዲ/ን - ዕብ 9÷11- ፍ ም ን/ዲ - 1ጴጥ 4÷1-12 ን/ካ - ግብ፡ሐዋ 28÷11-ፍ ም የዕለቱ_ምስባክ - መዝ 8÷2 እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ በእንተ ጸላኢ ከመ ትንሥቶ ለጸላኢ ወለገፋዒ ትርጒም፦ ጠላትን ለማሳፈር ቂመኛንና ግፈኛንም ለማጥፋት ከህፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ:: ወንጌል፦ ዮሐ 5÷11-31 ቅዳሴ: ዘጎርጎርዮስ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
إظهار الكل...
67🕊 6🥰 3🔥 1
#መዝ 49÷1 እምሥራቀ ፀሐይ እስከነዓረብ ወእምጽዮን ሥነ ስብሐቲሁ እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ 👉 @ortodoxmezmur
إظهار الكل...
21
#መዝ 146÷1 ትሴብሖ ኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ወሰብሒዮ ለአምላክኪ ጽዮን እስመ አጽንዐ መናሥግተ ኆኃትኪ 👉 @ortodoxmezmur
إظهار الكل...
24
#መዝ 121÷1 ተፈሣሕኩ እስመ ይቤሉኒ ቤተ እግዚአብሔር ነሐውር ወቆማ እገሪነ ውስተ አዕፃድኪ ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌምሰ ሕንጽት ከመ ሀገር . 👉 @ortodoxmezmur
إظهار الكل...
28